Professional Documents
Culture Documents
4th Audit Findings
4th Audit Findings
በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ የ 2014 በጀት አመት ሂሳብ ኦዲት
ሲደረግ በተገኙት የውስጥ ቁጥጥር ድክመቶች ሌሎች ግድፈቶችን ለኢንዱስትሪ ፓርኩ ስራ አስኪያጅ ግንዛቤ
እንዲያገኙ ማድረግ፡፡
በኦዲቱ ወቅት ግልጽ ያልተደረጉ ጉዳዮች ቢኖሩ ማብራሪያ እንዲሰጥባቸውና ያልቀረቡ ማስረጃዎችና ሰነዶች
ካሉ እንዲቀርቡ ማድረግ እና
1. በ BPV ቁጥር 20630 የሰልዳ ቁጥር ኮድ 3 - 54532 ET ተሸከርካሪ ጥገና እንዲጠገን ትእዛዝ የተሰጠበት
ጥገና እንደሚአስፈልግው የተጠየቀበት እና የክፍያ ትዕዛዝ የተሰጠበት ደብባቤ ሳይያያዙ ክፍያው ተከፍሎ ከላይ
በተጠቀስው BPV ቁጥር በቀን 23/04/2022 ብር 44,999.91 /አርባ አራት ሽህ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ዘጠኝ ብር
ማኔጅመንቱ የሰጠው ሃሳብ ፡- የተሸከርካሪዎች ጥገና ሲደረጉ የጥገና አገልግሎት የሰጠው ድርጅት ጥገናዎችን
ሲአጠናቅቁ የክፍያ ጥያቄ በመጠየቅና የፋይናነስና አስተዳደር አገልግሎት ክፍል ጥያቄ ለተቋሙ የበላይ ኃላፊ
በማስፈቀድ ክፍያዎች እንዲከፈሉ፡፡ለክፍያውም አስፈላጊ የሚባሉ አስረጅ (ደጋፊ) ማስረጃዎችም
ተደራጅተው ከክፍያ ሰነዱ ጋር እንዲያያዙ ውሳኔ ተሰጥቶበታል፡፡
2. በቀን 09/06/2022 BPV ቁጥር 20680 ለተሸከርካሪ ፍላጎት በተቀመጠው Specification መሰረት ግዥ
ያልተፈጸመ መሆኑን ኢንዱስትሪ ፓርኩ ከ 2005 ሞዴል በላይ ግዥ እንዲፈጸም ፍላጎት ያለው ቢሆንም
ግዥው ከ 2003 ሞዴል በላይ ግዥ የተፈጸመ መሆኑን በተደረገው ኦዲት ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡
ግብአቶች በተሰበሰበው የዋጋ ማወዳደሪያ መሰረት በተራ ቁጥር 3 ላይ 96M3 Compost በቀረቡት ዋጋ
መሰረት ወንደሰን ከድርና ጓደኞቹ የጭግኝ ማፍሊያና ገጸ ምድር ህ/ስ/ማ ዝቅተኛ ዋጋ ያቀረቡ ቢሆንም በየነ
ሃብታሙና ጓደኞቹ የጭግኝ ማፍሊያና ገጸ ምድር ህ/ስ/ማ አሸናፊ እንዲሆኑ በማድረግ ኢንዱስትሪ ፓርኩ ብር
10,500 /አስር ሽህ አምስት መቶ/ በብልጫ ክፍያ የተከፈል መሆኑን በ BPV ቁጥር 20621 በቀን
18/04/2022 ክፍያ የተከፈለና የተወራረደ መሆኑን በተደረገው ኦዲት ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡
ከስራ ክፍሉ የተሰጠ ምላሽ፡- በመጠይቁ ላይ በቃለ ጉባኤው የተሰራው በ 2005 እና ከዚያ በላይ በሚል ሲሆን
በስህተት በጅርጅቱ በኩል በ 2003 እና ከዚያ በላይ በሚል የተያያዘ በመሆኑ ነው፡፡ የዋጋ ውድድር የተደረገው
ማኔጅመንቱ የሰጠው ሃሳብ ፡- ኢንዱስትሪ ፓርኩ ባዘጋጀው ስፔስፊኬሽን መሰረት ስለመገዛቱ የሚአስረዱ
በሚአቀርቡት ዋጋ መሆኑን በሚገልጽ መልኩ እንዲሆን በተያያዘ መልኩ ማስረጃዎችንም በማደራጀት ከክፍያ
ሰነዱ ጋር ይያያዝ፡፡
3. በ BPV ቁጥር 20719 እና 20718 የአመት ፈቃድ ወደ ገንዘብ እንዲቀየር በተወሰነው መሰረት የአመት ፈቃድ
ወደ ገንዘብ ሲቀየር መንግስት ባስቀመጠው አሰላልን መሰረት ባለደረገ መልኩ ለመንግስት ገቢ መደረግ የነበረበት
የስራ ግብር ብር 1,500 ለእያንዳንዱ በድምሩ ብር 3,000 / ሶስት ሽህ ብር ከተጣራ ክፍያ ጋር ተደምሮ
ከስራ ክፍሉ የተሰጠ ምላሽ፡- በሁለቱም የክፍያ ሰነዶች ላይ የስራ ግብር የተሰላው ከጠቅላላ ተከፋይ ሂሳብ ላይ
በመሆኑ ትክክለኛ ስሌት መሆኑን አረጋግጠናል ነገር ግን ገቢዎች የወጣ የአመት ፈቃድ ስሌት የተለየ በመሆኑ
በዚሁ እንዲስተካከል በሚሰራበት ወቅት ብር 48.58 ከአቶ ሲሳይ ብር 70.46 ከአቶ ትንሳኤ እላፊ ተከፍሏል
ይህም ገቢ እንዲደረግ ተደርጓል፡፡
ማኔጅመንቱ የሰጠው ሃሳብ ፡- አሰራሩ ከዋናው መስሪያ ቤት ጋር በማነጻጸር እንዲሁም የአመት ፈቃድ ወደ
ገንዘብ ሲቀየር የመንግስት መመሪያን መሰረት ባደረገ መልኩ መሆኑን መከናወኑንና መከፈሉን በጥልቀት
በመመርመር የአሰራር ጥሰት ካለው ገንዘቡ ተመላሽ ይደረግ፡፡
4. በ BPV ቁጥር 20640 በቀን 29/04/2020 የኢትዮጵያ ጎማ ቁጠባ ስራ ሃ/የተ/የግ/ ማህበር ብቸኛ አቅራቢ
መሆኑ ባልተረጋገጠበት መልኩና ማህበሩ በ 2014 በጀተ አመት የንግድ ፈቃድ ባልታደሰ መልኩ ግዥው
ከሆነው ከኢትጵያ ጎማ ቁጠባ በመሆኑ እና ከ 10,000 ብር በታች በመሆኑ በቀጥታ ግዥ የተስተናገደ ሲሆን
ማኔጅመንቱ የሰጠው ሃሳብ ፡- አቅራቢ ድርጅቱ የመንግስት የልማት ድርጅት ሲሆን የንግድ ፈቃዱ ያልታደሰ
መሆኑን የሚአረጋግጥ ማስረጃዎች ተመርምረው ቀጣይ የሚከናወኑ ግዥዎች ላይ በጥንቃቄ ይከናወኑ ፡፡
5. ኢንዱስትሪ ፓርኩ ከሃዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚመጡትን ስላጅ የኢንዱስትሪ ፓርኩ የፋሳሽ ማጣሪያ
ማእከል ከሃዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚመጡትን ስላጅ ዝርዝር መረጃ ሪፖርት አለማድረግና ከሃዋሳ ኢ/ፓ
ከስራ ክፍሉ የተሰጠ ምላሽ፡- ከሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ በየጊዜው የሚጻፍ ደብዳቤ የለም ሆኖም ለዚህ
ማስረጃ ከጉሙሩክ የሚላክ የመኪናውን የጭነት ልክ በኪሎ ግራም ተመዝኖና ተረጋግጦ ሁለት ኮፒ ይላካል
ማኔጅመንቱ የሰጠው ሃሳብ ፡- ከሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚመጡ ስላጆች በጥንቃቄ ማስረጃዎች
እንዲያያዙና ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚመጡ ማንኛውም ወጪ የሐዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ እንዲሸፍን ጥብቅ
ቁጥጥርና ክትትል ይደረግ፡፡
6. በ 2014 በጀተ አመት የበጀት አጠቃቀም በተመለከተ በቅርንጫፍ ኢንዱስትሪ ፓርኩ 68.54% በጀት
የተጠቀምን ሲሆን ያልተጠቀምንበት በጀት 31.46 % መሆኑን በወርሃዊ ሪፖርት ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡
በዝርዝር
ለምሳሌም የጥበቃ ድርጅት ክፍያዎች የጥገና ስራዎች ላይ ግዥዎች አለመከናወናቸው ይህም የግልጽ ጨረታ ተከፋይ
ማኔጅመንቱ የሰጠው ሃሳብ ፡- በ 2015 ያለን የበጀት አጠቃቀም ስኬታማ እንዲሆን እንዲሰራ አስተያየት የተሰጠ ሲሆን
የ 2014 በጅ አጠቃቀም ያጋጠሙ ችግሮች የፋይናንስና አስተዳደር ክፍል ያስቀመጣቸው ሃሳቦች በዚህ በጀተ አመት
7. የኢንደስትሪ ፓርኩ የጥቃቅን ግዥ ሲከናወን ጥብቅ ቁጥጥርና ክትትል እየተደረገ መሆኑን ለማረጋገጥ ኦዲት
ሲደረግ ኢንዱስትሪ ፓርኩ የግዥ ባለሙያዎች ተመላሽ ገንዘብ ስለማድረጋቸው ምንም አይነት ማረጋገጫ
አለመኖሩን በተደረገው ኦዲት ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡
ከስራ ክፍሉ የተሰጠ ምላሽ፡- በጥቃቅን ግዥ ሲደረግ ለእቃው የሚአወጣው ዋጋ ግምት ተወስዶ በቅድሚያ
መጠየቂያ ሰነድ ወጪ ይሆንና እቃውን ገዝተው በሚአስረክቡበት ወቅት የቅድሚያ መጠየቂያው ተሰርዞ
(አገልግሎቱን ጨረሰ )ተመላሽ ሂሳብን ለገንዘብ ያዥ ገቢ ይደረጋል ይህ ገንዘብ ከመመለስ የተሸለ አሰራር በመሆኑ
ነው፡፡
ማኔጅመንቱ የሰጠው ሃሳብ ፡- ተመላሽ ሂሳቦች መመለሳቸውን በሚገልጽ መልኩ ማስረጃዎች ይያያዙ
መመሪያዎችን በማይጥሱ መልኩ ፈጣን እና ቀልጣፋ አሰራር ካለ ስራው እንዲተገበር አስተያየት ተሰጥቶበታል፡፡
በመጨረሻም የኢንዱስትሪ ፓርኩ ዋና ስራ አስኪያጅ በሰጡት ማጠቃለያ መሰረት የመረጃ ክፍተት ያለባቸው
የክፍያ ሰነዶች የክፍያውን ሂደት ሊአስረዱ የሚችሉ ደጋፊ ማስረጃዎች እየተደራጁና ከክፍያ ሰነዱ ጋር እንዲያያዙ
ለዚህም ቁጥጥሩና ክትትሉ ተጠናክሮ እንዲቀጥል፡፡ በፕሮፎርማ የሚገዙ ግዥዎች አቅራቢዎች የሚወዳደሩት
በጥቅል ወይም በተናጠል መሆኑን የሚገልጹ ሃሳቦች በማወዳደሪያው ላይ እንደአስፈላጊቱ የሚገለጹበት መንገድ
ይመቻች፡፡ ማስተካከያ ያልተወሰደባቸው የኦዲት ግኝቶች ትኩረት በማድረግ የማሽተካከያ ስራዎች እንዲሰሩ
የኦዲት ባለሙያውም የኦዲት ግኝት መወቅቱ ምላሽ እንዲሰጣቸውን ድጋፍ እንዲደረግላቸው በማለት የእለቱ
የኦዲት የመውጪያ ስብሰባ ተጠናቋል፡፡
የአመት ፈቃድ ወደ ገንዘብ ሲቀየር አሰላል