You are on page 1of 7

I.

ግዥና የግብዓት አቅርቦት ክፍል ተግባርና ኃላፊነት


 የአቅርቦት ችግር እንዳይኖር ለምርት ክፍልና ለአጠቃላይ ድርጅቱ አስፈላጊ የሆኑ ግብዓቶችን
ፍላጎት ከተለያዩ የስራ ክፍሎች ይሰበስባል፡ የፍላጎት መግለጪያ ቅጽ ያዘጋጃል፣ የግዢ መጠየቂያ
ቅጽ ይሞላል፣ መገዛት ያለበትን መጠንና ጥራት ከስራአስኪያጅ ጋር በመሆን ይወስናል
 ከድርጅቱ ስራ አስኪያጅና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር ቅድሚያ ሊሰጣቸው
የሚገባውን በቅደም ተከተል ማዘጋጀት ይኖርበታል
 በቅደም ተከተላቸው መሰረት አስፈላጊው የግዥ መጠየቂያና የግዢ ማዘዣ ሰነዶች እንዲዘጋጁ
ያደርጋል
 በሰነዶቹ ላይ መፈረም ያለባቸው አካላት እንዲፈርሙ ያደርጋል
 የዕቃው ግዢ ተፈጻሚ እንዲሆን ያደርጋል
 ንብረቱን ወደድርጅቱ ንብረት ክፍል ገቢ ያደርጋል
 ገቢ ሲደረግ ከንብረት ክፍል ጋር የንብረትና የሰነድ ርክክብ ይፈጽማል
 እንዳስፈላጊነቱ የቅርብ አለቃው ተጨማሪ ስራዎችን ሲያዘው ሊሰራ ይገባል

II. የንብረት ክፍል ተግባርና ኃላፊነት


 ከግዥና የግብዓት አቅርቦት የተገዙ ንብረቶችን ይረከባል:-
 የተረከበውን ንብረት ከሚመለከተው ክፍል በሚቀርብለት መጠየቂያ መሰረት ንብረቱን ቆጥሮና
ለክቶ /መዝኖ/ ያስረክባል
 የመረካከቢያ ሰነድ ላይ ይፈርማል፣ ያስፈርማል ሰነዱን ዶክመንት አድርጎ ያስቀምጣል
 ስቶክ ካርድ ላይ ገቢና ወጪ የሆኑ ንብረቶችንና እቃዎችን መረጃ ይመዘግባል
 እንዳስፈላጊነቱ መረጃውን ከፋይናንስ ጋር ተናብቦ ይሰራል፤ ለስራ አስኪያጅ በሪፖርት መልክ
ያቀርባል
 በንብረት ላይ ጉዳት እንዳይደርስ አስፈላጊውን ክትትል ያደርጋል፤ ችግር ሲፈጠር ከሚመለከተው
ጋር በመሆን ይፈታል
 የግብዓት እጥረት እንዳይከሰት ያለውን ቀሪ ግብዓት መረጃ ለግዥና ግብዓት አቅርቦት በማቅረብ
እንዲገዛለት በመጠየቂያ ይጠይቃል
 የተመረቱ ምርቶችን መረጃ በየቀኑ ለስራአስኪያጅ ክፍል ሪፖርት ያደርጋል
 የተመረቱ ምርቶችን ስቶክ ካርድ ላይ ገቢና ወጪ የሆኑ ምርቶችን መረጃ ይመዘግባል፤ ሲፈለግ
ያቀርባል
 የተሸጠ ምርት ሲኖር የወጪ ማዘዣ አስፈርሞ ወጪ ያደርጋል
 ያሉትን የግብዓት፣ ጥሬ ዕቃና ምርት ቆጠራ አድርጎ ይመዘግባል፤ የሚያስፈልጉትን ደግሞ ከምርት
ክፍል ጋር በመነጋገር ለግዥና ግብዓት አቅርቦት ያሣውቃል
 ሳምንታዊና ወርሀዊ ሪፖርት በማዘጋጀት ለሚመለከተው አካል ያቀርባል
 እንዳስፈላጊነቱ የቅርብ አለቃው ተጨማሪ ስራዎችን ሲያዘው ሊሰራ ይገባል

III. ፋይናንስ ተግባርና ኃላፊነት

 ፋይናንሻል ዕቅድ ያዘጋጃል፤ በዕቅዱ መሰረት ተፈጻሚ ያደርጋል


 የግዥ ሰነዶች መሟላታቸውን አይቶና አረጋግጦ ክፍያ እንዲፈጸም ለካሸር ያስተላልፋል
 የገቢና የወጪ ሰነዶችን በሚገባ ሰንዶ ይይዛል
 የ VAT, withholding, excise tax, income tax, pension ና ሌሎች የግብር ዓይነቶችን ወቅቱን
ጠብቆ ለሚመለከተው የመንግስት አካል ገቢ ያደርጋል
 በስራ ላይ ያሉ ሰራተኞችን መረጃ ከየስራ ክፍሉ ይሰበስባል
 ወርሀዊ ደሞዝ ለሰራተኞች ይከፍላል፤ ኦቨር ታይም ያሰላል፣ በስሌቱ መሰረት ክፍያ ይፈጽማል
 ወርሀዊ፣ የሩብ ዓመትና ዓመታዊ ሪፖርቶችን ያቀርባል፤ ያስገባል፣ ይከታተላል
 ክሊራንስ ሲያስፈልግ ይቀበላል
 ኦዲት ያስደርጋል
 ለድርጅቱ ስራ አስኪያጅና ባለቤቶች ፋይናንሻል ሪፖርት በሩብ ዓመት ያቀርባል

IV. Marketing team /የገበያ ልማት ቡድን ተግባርና ኃላፊነት


 የምርት ክፍሉ የሚያመርታቸው ምርቶች በገበያ የተመራ መሆን እንዲችል የገበያ ጥናት ማድረግ ይኖርበታል
 በገበያ ጥናቱ መሰረት ትዕዛዝ መቀበልና በትዕዛዙ መሰረት እንዲመረት ማስደረግ፤ ካልሆነ ደግሞ የገበያ ጥናቱንና
የማሽኖችን የማምረት አቅም ግምት ውስጥ በማስገባት ምርት እንዲመረት ማድረግ
 የተመረቱ ምርቶችን መረጃ ከንብረት ክፍል ይወስዳል ለሽያጭ ያቀርባል
 በስልክ፣ በአካል፣ በኢሜል፣ በማህበራዊ ሚዲያና በሌሎች መገናኛ ዘዴዎች የድርጅቱን ምርቶች
የሚተዋወቅበትን መንገድ ያመቻቻል አዳዲስ ደንበኞችን ያመጣል
 የነባር ደንበኞችን መረጃ ያሰባስባል፣ ግንኙነቱን ያጠናክራል፣
 በምርቱ ላይ ደንበኞች ያላቸውን አስተያየት ይቀበላል፣ መስተካከል ያለበትን ለድርጅቱ ስራ አስኪያጅ
ያቀርባል
 የሽያጭ ዕቅድና /Marketing Plan የሽያጭ ዒላማ/Sales Target ያዘጋጃል፤ በዕቅዱ መሰረት
ተፈጻሚ ያደርጋል
 ሽያጭ ሲኖር ኦርደር ለገንዘብ ያዥና ለንብረት ክፍል ያቀርባል ንብረት ክፍል የምርቱን ዓይነት ለይቶ
ያዘጋጃል ገንዘብ ተቀባይ ሂሳብ ይሰራል፤ በቀረበው ኦርደር መሰረት ግብይቱ ተፈጻሚ ይደረጋል
 እንዳስፈላጊነቱ የቅርብ አለቃው ተጨማሪ ስራዎችን ሲያዘው ሊሰራ ይገባል

V. የስራ አስኪያጅ ተግባርና ኃላፊነት

 አጠቃላይ የድርጅቱን ዕቅድ ያወጣል፤ የወጣው ዕቅድ ተፈጻሚ እንዲሆን ከሁሉም ሰራተኞች ጋር
ተባብሮ ይሰራል
 የምርት መረጃ ከንብረት ክፍል በየሳመንቱ/በየወሩ ይቀበላል
 የግብይት/የሽያጭ ስራዎች እንዲፋጠኑ ከ marketing team ጋር አብሮ ይሰራል
 የጥሬ ዕቃና የግብዓት መረጃ ከንብረት ክፍል በመውሰድ ግዢ ያሚያስፈልጋቸውን ከግዢና የግብዓት
አቅርቦት ጋር በመነጋገር እንዳስፈላጊነቱ ቅደም ተከተል በማውጣትና ያለውን የገንዘብ አቅም ግምት
ውስጥ በማስገባት የሚያስፈልገው ግዢ እንዲፈጸም ያደርጋል
 የሽያጭ መረጃ በመሰብሰብ በጣም ተፈላጊ የሆኑ የምርት ዓይነቶችን ወይንም በፍጥነት የሚሸጡ
የምርት ዓይነቶችን በመለየት ለምርት ክፍል ትኩረት ሊሰጥባቸው የሚገቡ የምርት ዓይነቶችን
ማስገንዘብና ተፈጻሚነቱን መከታተል
 ከወለድ ነጻ የብድር አቅርቦት በተፋጠነ መንገድ እንዲሄድ ከባንኮች ጋር ግንኙነት መፍጠርና ሂደቱን
እየተከታተሉ የሚፈለገውን እያቀረቡ ብድሩ እንዲፈቀድ ማስቻል
 መከፈል ያለባቸው ዕዳዎች በወቅቱ እንዲከፈሉ ማድረግ
 የፋይናንስ መረጃዎችን ወጪና ገቢ በየጊዜው መሰብሰብ፤ የመንግስት ግብር በወቅቱ መከፈሉን
መከታተልና እንዲከፈል ማድረግ
 ስራዎች በታቀደው መልኩ እየሄዱ መሆናቸውን ይከታተላል፤ መስተካከል ያለባቸውን ያስተካክላል
 የድርጅቱን የሰው ኃይል አስተዳደር ስራ ይሰራል
 በሁሉም ዲፓርትመንቶች ያለውን የሥራ ሂደት ይከታተላል፣ ክፍተቱን ያርማል፣ ስራቸውን
ይገመግማል፣ ሪፖርት ይቀበላል ማስተካከያ ይሰጣል

VI. ፕሮዳክሽን ማናጀር

 የሚሰሩ ስራዎችን ወርሀዊ ዕቅድ ያወጣል


 ወርሀዊ ታርጌት ያስቀምጣል
 በታርጌቱ መሰረት ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ያረጋግጣል
 HD ባለ 20 ፤ 3 ና አምስት ተመጣጥነው እየተጠቀሙ መሆኑን ያረጋግጣል
 የቴብል ጥሬ ዕቃ በተገቢው መንገድ እየተጠቀሙ መሆኑን ያረጋግጣል
 በቀንም በማታም የተመረቱ ምርቶችን ቆጥሮ፣ ፈርሞና አስፈርሞ ይረከባል
 የተመረቱ ምርቶችን ያሥጭናል ተጪነው ሲወጡ ስቶክ ባላንስ ያደርጋል
 ሰራተኞች በስራ ገበታቸው መገኘታቸውን ያረጋግጣል፤ ያልገባ ሰራተኛ ካለ ለሚመለከተው አካል ሪፖርት ያደርጋል
 ሰራተኞች በስራ ላይ የሚገጥማቸውን ችግሮች እንዲቀርፉ ከሌሎች አመራር አካላት ጋር በመሆን አብሮ ይሰራል
 የስቶክ መጠኑን ሪፖርት ለሚመለከተው አካል በየቀኑ ሪፖርት ያድርጋል
 የቀረው ጥሬ ዕቃ ለምን ያህል ጊዜ እንደሚያሰራ ግምታዊ ስሌት በመስራት ቀድሞ ያሳውቃል
 ጥሬ ዕቃ ከቆሻሻ ጋር እንዳይወጣ፣ እንዳይባክን አስፈላጊው ጥንቃቄ ያደርጋል
 ጥሬ ዕቃ ያስጭናል፣ ያስወርዳል፣ ያስደረድራል፣ የስራ አካባቢ እንዲጸዳ ያስደርጋል
 ከውጪ ለሚመጣ ጥሬ ዕቃ ማስቀመጫ ቦታ ያመቻቻል፣

VII. የተሸከርካሪ ስምሪትና ቁጥጥር

 ነዳጅ መሙላት፣
 የተሸከርካሪ ጥገና፣
 ወቅታዊ ሰርቪስ
 የተሸከርካሪ ዓመታዊ ምርመራ (ቦሎ)፣ ኢንሹራንስ እድሳት
 የሹፌር ምደባና ስምሪት
 የሚወጡ መኪኖችን መከታተልና የወጡበትን ምክኒያት ማረጋገጥ፣ እንዲወጡ ፈቃድ መስጠት
VIII. የማሽን ጥገናና ደህንነት ክትትል

 ማሽኖች ችግር ገጥሟቸው ሲቆሙ፣ የገጠማቸውን ችግር መለየት


 በቅድሚያ ወደስራ እንዲገቡ አፋጣኝ መፍትሄ መፈለግ
 ችግሩ የተፈጠረው በሰራተኞች ቸልተኝነት መሆኑ ከተረጋገጠ፤ ችግሩን የፈጠሩትን ሰራተኞች እነማን እንደሆኑ
ማወቅ
 ማንነታቸው ከታወቀ በኋላ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ለሚመለከተው አካል ማስተላለፍ
 ማሽኖች ሰርቪስ በሚያስፈልጋቸው ጊዜ ሰርቪስ እንዲደረጉ ማመቻቸት
 የማሽን መለዋወጫ ዕቃዎችን ቀድሞ መዘጋጀት ያለባቸውን ቀድሞ ማዘጋጀት
 መለዋወጫ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ ግዢ ተፈጽሞ በተቻለ ፍጥነት ለስራ እንዲደርስ ማድረግ
 በቀን ቢያንስ አንድ ጊዜ ሁሉንም ማሽኖች ዞሮ በማየት ያሉበትን ሁኔታ በማስታወሻ ማስፈር
 አስቸኳይ እርምት የሚያስፈልጋቸውን በፍጥነት ማስተካከያ እንዲደረግ ማዘዝና አፈጻጸሙንም መከታተል
 የማሽኖችን እድሜ ሊያራዝሙ የሚችሉ ነገሮችን እንደዚሁም ስራ እንዳይስተጓጎል እገዛ ሊያደርጉ የሚችሉ ነገሮችን
ከሽፍት ሊደሮችና ከባለሙያ ጋር መነጋገር ተግባራዊ እንዲሆኑ መጣር፡፡

You might also like