You are on page 1of 13

የስራ ዝርዝር መግለጫ

የስራ መጠሪያ ፡- ጠቅላላ አገልግሎት

ተጠሪነቱ ፡- ሎጀስቲክስ

የስራ ክፍል፡- ሲድሃፋጌ እንፋሎት ሃይል ማመንጫ

ዝርዝር ተግባራት
1. ለፕሮጀክቱ አገልግሎቱ የሚያስፈልጉ ነገሮችን ያቅዳል በዕቅድ የተያዙትንም እንዲገዙ ወይም

ከዋናው ቢሮ እንዲላኩ ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን ያስፈፅማል፡፡

2. ለብዙሃን አገልግሎት የሚሰጡ ዕቃዎችን በስሙ ወጪ በማድረግ ለአገልግሎት እንዲውሉ

ያደርጋል ደህንነታቸውንም ይጠብቃል፡፡

3. በስሩ ያሉ የስራ መደቦች ማለትም ጥበቃ፣ፅዳትና አትክልተኛ የመሳሰሉትን ስራቸውን በአግባቡ

መስራቱን ይከታተላል፡፡

4. ለሰራተኛው (ለፕሮጀክቱ ሠራተኞች) የሚያስፈልጉ ውሃ፣ማብራት፣ሰርቪስ የመሳሰሉትን

ሠራተኛው በአግባቡ ተጠቃሚ እንዲሆን ከሚመለከተው አካል ጋር በመነጋገር ያመቻቻል፡፡

5. የአገልግሎት ጥያቄዎችን ከሰራተኞች ሲነሱ ጥያቄውን ለሚመለከተው አካል በማቅረብ ምላሽ

እንዲሰጥ ያደርጋል፡፡

6. የተሸከርካሪዎች ስምሪት ይቆጣጠራል የጉዞ መለኪያ መዝገብ በመያዝ የጉዞ መጠንና የነዳጅ

ፍጆታን ይቆጣጠራል፡፡

7. ንብረት ከካምፕ በሚወጣበት ግዜ የሚመለከተውን አካል ፈርሞ ወጪ እንዲሆን ይቆጣጠራል፡፡

8. የስልክ ፣የውሃ እና የመብራት ብልሽት ሲከሰት (ሲያጋጥም) የሚመለከተውን ሠራተኛ በመያዝ

ጥገና እንዲደረግ ያደርጋል፡፡


9. የስልክ የውሃና የመብራ ክፍያዎችን በወቅቱ ክፍያ እንዲፈፀም ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን

ተፈፃሚ እንዲሆን ያደርጋል፡፡

10.ወደ ፕሮጀክት የሚመጡ እንግዶችን በመቀበል ማረፊያ ቤት ያዘጋጃል፡፡ ለእንግዶቹ የሚያስፈልጉ

ዕቃዎችን ወጪ በማድረግ እንዲጠቀሙ ያደርጋል፡፡

11.ለሠራተኞች አገልግሎት በመስጠት ላይ ላሉ ሻውር ቤት፣መፀዳጃ ቤቶችና የመኖሪያ ቤቶች

ደህንነታቸውና ንፅህናቸው እንዲጠበቁ ያደርጋል ሲበላሹም በወቅቱ ጥገና እንዲያገኙ ያደርጋል፡፡

12.በተጨማሪም ኃላፊው የሚያዘውን ስራ የመስራት ግዴታ አለበት፡፡


የስራ ዝርዝር መግለጫ
የስራ መጠሪያ ፡- ሲቪል መሀንዲስ

ተጠሪነቱ ፡- ለሲቪል ስራዎች ኃላፊ

የስራ ክፍል፡- ሲቪል ስራዎች

ዝርዝር ተግባራት
1. ለግንባታ ስራዎች የሚገዙ የጨረታ ሠነዶችን በመመርመርና በማጥናት የፕሮጀክቱን ዋጋ

ይተምናል አስፈላጊም ሆኖ ሲገኝ የጨረታ (technical document) ዝግጅት ላይ ይሳተፋል፡፡

2. የገበያ ዋጋን በየወቅቱ እየተከታተለ የጉልበት፣የእቃዎችንና የማሽነሪ ዋጋ መረጀዎችን ለሲቪል

ስራዎች ያቀርባል፡፡

3. የለውጥና የተጨማሪ ስራ ትዕዛዞች ዋጋ ይተምናል አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ የስራ ዝርዝር ያዘጋጃል፡፡

4. በሰብ ኮንትራክተሩ ተዘጋጅቶ ለአማካሪ የሚቀርቡ የክፍያ ጥያቄዎችን አግባብነታቸውን

ይከታተላል፡፡

5. የግንባታ ጥራት ከአማካሪው ድርጅት ጋር በመሆን ይከታተላል ችግርም ሲኖር ከሚመለከተው

አካል ጋር በመሆን መፍትሄ ይሰጣል፡፡

6. የኮንትራት ዶክመንቱን መነሻ በማድረግ ኳንቲቲ ያወጣል፡፡

7. ስራዎች በተቀመጠላቸው ድሮዊንግ መሠረት እየተሰሩ እንደሆነ ይከታተላል፡፡

8. የግንባታው ስራን በተመለከተ በሚደረግ ስብሰባዎች ላይ በመሳተፍ አስፈላጊውን ድጋፍ

ያደርጋል፡፡

9. የግንባታውን የስራ ሂደት በተመለከተ ለበላይ ኃላፊው ወርሃዊ ሪፖርት ያደርጋል፡፡

10.በተጨማሪ ኃላፊው የሚያዘውን ስራ የመስራት ግዴታ አለበት፡፡


የስራ ዝርዝር መግለጫ
የስራ መጠሪያ ፡- ኤሌክትሪሺያን

ተጠሪነቱ ፡- ለጠቅላላ አገልግሎት

የስራ ክፍል፡- ሎጀስቲክስ

ዝርዝር ተግባራት
1. የፕሮጀክቱን መኖሪያ ቤቶችና ቢሮዎች መስመር ዝርጋታ ይሰራል፡፡

2. የተበላሹ የኤሌትሪክ መስመሮችን ይጠግናል፡፡

3. ለማብራት አገልግሎት የሚያስፈልጉ ዕቃዎችን በዕቅድ በመያዝ ግዢ እንዲፈፀም ከሚመለከተው

አካል ጋር በመሆን ለተፈፃሚነቱ ይሰራል፡፡

4. መስመሮች ጉዳት ከማድረሳቸው በፊት ፍተሻ በማድረግ ጥገና ያደርጋል፡፡

5. ለፕሮጀክቱ አገልግሎት በመስጠት ላይ ላሉት ጀነሬተሮች ኦፕሬት ያደርጋል አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ

መለስተኛ ሰርቪስ ያደርጋል፡፡

6. የጀነሬተር ሰርቪስ ጊዜውን በመጠበቅ ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን ሰርቪስ እንዲያደርግ

ያደርጋል፡፡

7. የጀነሬተሩን ደህንነት ለመጠበቅ አዋራዎችንና ዝገቶች እንዳይኖር የማፅዳት ስራዎችን ይሰራል፡፡

8. በተጨማሪም ኃላፊው የሚያዘውን ማንኛውንም ስራ የመስራት ግዴታ አለበት፡፡


የስራ ዝርዝር መግለጫ
የስራ መጠሪያ ፡- ንብረት ፀሀፊ

ተጠሪነቱ ፡- ለንብረት ክፍል ሰራተኛ

የስራ ክፍል፡- ሎጀስቲክ

ዝርዝር ተግባራት
1. የግዢ ጥያቄ ሲቀርብ መጠይቅ በመሙላት ለሚመለከተው አካል ለማስፈረም ያቀርባል፡፡

2. ንብረት በሚጠየቅበት ጊዜ ስቶር ሪኮዝሽን በመሙላት ለኃላፊው ያቀርባል፡፡

3. ገቢ የሚደረጉ ዕቃዎችን በንብረት መረካከቢያ ላይ በመመዝገብ አስረካቢውን እና ተረካቢውን

በማስፈረም ሰነድ ያዘጋጃል፡፡

4. ወጪ የሚደረጉ ንብረቶችን በሰነድ ላይ በማዘጋጀት የሚመለከተውን አካል አስፈርሞ ለንብረት

ክፍል ሠራተኛው በማቅረብ ዕቃውን ወጪ እንዲሆን ያመቻቻል፡፡

5. የቋሚ ዕቃ መመዝገቢያ መዝገብ በመያዝ ምዝገባ ያካሂዳል ሎኬሹንም መዝግቦ ይይዛል፡፡

6. ወርሃዊ የገቢና የወጪ ዝርዝር በመመዝገብ ለሚመለከተው አካል ሪፖርት ያደርጋል፡፡

7. በተጨማሪም ኃላፊው የሚያዘውን ስራ የመስራት ግዴታ አለበት፡፡


የስራ ዝርዝር መግለጫ
የስራ መጠሪያ ፡- ቀላል ተሽከርካሪ ሹፌር

ተጠሪነቱ ፡- ለጠቅላላ አገልግሎት

የስራ ክፍል፡- ሎጀስቲክስ

ጥቅል ስራዎች
ደምቡና ህጉ በሚፈቅደዉ መሰረት በሚሰጠው የስራ ትዕዛዝ የትራፊክን ህግና ደንብ በመከተል አነስተኛ ተሸከርካሪዎች

ያሽከረክራል እንደ አስፈላጊነቱ እቃዎችን በመሸከም ይጭናል፣ያስጭናል፣በጉዞ ላይ ጭነት በዝናብና በንፋስ ጉዳት

እንዳይደርስበት በሸራ ይሸፍናል፣ያራግፋል፣ወደ ሚቀመጥበት ክፍል በመውሰድ ያስረክባል ፡፡

1. የትራፊክ ህግና ደንብን በመጠበቅ ነጂውን ጨምሮ እስከ አስራ ሁለት መቀመጫ ያላቸውን አነስተኛ

ተሸከርካሪዎች ያሽከረክራል፡፡

2. ለስራ ከመሰማራቱ በፊት የመኪናውን ደህንነትና ጥንካሬ፣ፍሬን፣ጎማዎችን፣ መብራቶችን፣የዝናብ መጥረጊዎችን

፣የኪሎ ሜትርና የነዳጅ መቆጣጠሪያ የመሳሰሉትን በትክክል መስራታቸውን እንዲሁም በቂ ነዳጅ ፣ዘይት፣ቅባት

የመሳሰሉትን መኪና ውስጥ መኖሩን ያረጋግጣል፡፡

3. ለመኪናው መገልገያ የሚሆኑ እንደ ክሪክ ተለዋጭ ጎማዎችን ፣የመለዋወጫ መፍቻዎችን ፣የመጀመሪያ እርዳታ

መስጫና የመሳሉትን ዕቃዎች ይረከባል በጥንቃቄ በመያዝ ስራ ላይ ያውላል ፡፡

4. በተሸከርካሪው መዘዋወሪያ ቅፅ ላይ የመነሻና መድረሻ ኪሎ ሜትር የሚጓዙ ሰዎችን ወይም የጭነት ዕቃ ዝርዝር

የነዳጅ ፍጆታና ጉዞ የወሰደውን ጊዜ በአግባቡ መዝግቦ ለኃላፊው ያስረክባል፡፡

5. በጉዞ ላይ እንዳለ ብልሽት ቢያጋጥመው በአመች የመገናኛ ዘዴ ወዲያውኑ ያሳውቃል የጥገና አገልግሎት ሊያገኝ

የሚችልበትን ዘዴ ሁሉ ያፈላልጋል፡፡

6. ተሸከርካሪው በጉዞ ላይ ሆነ ቆሞ የግጭት አደጋ ቢደርስበት ጉዳዩን በወቅቱ ለትራፊክ ፖሊስ በማመልከት ፕላን

ያስነሳል ስለሁኔታውም ለኃላፊው በፁሁፍ ሪፖርት ያደርጋል፡፡

7. የተሸከርካሪውን የሰርቪስ ጊዜ በመጠበቅ ለሚመለከተው ክፍል ሪፖርት ያደርጋል፣ በትክክል ሰርቪስ መደረጉን

ያረጋግጣል አነስተኛ ጥቃቅን የሆኑ የጥገና ስራዎችን ያሰራል ያስተካክላል፡፡

8. የሚሰራበትን ተሸከርካሪ ንፅህናና ደህንነቱ በሚገባ ይጠብቃል፡፡

9. በተጨማሪ ኃላፊው የሚያዘውን ተጨማሪ ስራ የመስራት ግዴታ አለበት ፡፡


የስራ ዝርዝር መግለጫ
የስራ መጠሪያ፡- የንብረት ክፍል ሠራተኛ (Store Keper)

ተጠሪነቱ፡- ለንብረት አስተዳደር

የስራ ክፍል፡- ሎጀስቲክስ


1.ጥቅል ስራዎች
ከቅርብ ኃላፊው በሚሰጠው አጠቃላይ መመሪያ መሰረት ተገዝተው የሚመጡትንና ከዋና ቢሮ የሚላኩ ዕቃዎችን

በአይነት፣ በመጠን፣ በብዛት ቆጥሮ በመረካከቢያ ሰነድ ላይ ፈርሞ ይረከባል፡፡ የተረከባቸውን ዕቃዎች በአይነታቸው እየለየ

ቢን ካርድ ላይ እየመዘገበ ያስቀምጣቸዋል/ይደረድራቸዋል ወጪ የሚያደርጋቸውን ንብረቶች በጥንቃቄ እየመዘገበ ሚዛን

/ባላንስ ይሰራል ለሰራው አፈፃፀም ሪፖርት ያቀርባል፡፡

1. እቃዎችን በአይነታቸው በስቶክ ቁጥራቸው መሰረት ተለያይተው ለስራው በቀላሉ ሊገኝ በሚችልበት ስርዓትና

ሁኔታ እየደረደረ ያስቀምጣል፡፡

2. አዲስ የሚመጡ ዕቃዎችን በቢን ካርድ መዝግቦ ይይዛል፡፡

3. ገቢና ወጪ የሆኑ ንብረቶች የሚያሳይ ወርሃዊ ዘገባዎችን ለቅርብ ኃላፊው ያቀርባል፡፡

4. የክፍሉን ንፅህና ይጠብቃል፡፡

5. በሚመለከተው ኃላፊ ተፈርመው የሚመጡ የዕቃ መጠየቂያ/ማዘዣ ቅፆችን ወይም ሰነዶችን ትክክለኛነት

እያረጋገጠ ተረካቢውን አስፈርሞ መለዋወጫ እቃዎችን ቆጥሮ ያስረክባል፡፡

6. የንብረት ቆጠራ በሚካሄድበት ወቅት መጋዘኑ ውስጥ ያለውን ንብረት አስቆጥሮ ይፈርማል ፡፡

7. በመጋዘኑ ውስጥ ያሉትን ንብረቶች ለአደጋና ለስርቆት ሳይጋለጥ በጥንቃቄ እንዲቀመጥ ያደርጋል፡፡

8. ስለ ስራው ክንውንና ሂደት ስላጋጠመው ችግሮች ሪፖርት ለቅርብ ኃላፊው ያቀርባል፡፡

9. በተጨማሪ በኃላፊው የሚታዘዘውን ስራ የመስራት ግዴታ አለበት ፡፡


የስራ ዝርዝር መግለጫ
የስራ መጠሪያ ፡- የፅዳት ሰራተኛ

ተጠሪነቱ ፡- ለጠቅላላ አገልግሎት

የስራ ክፍል ፡- ሎጀስቲክስ

ዋና ዋና ተግባራት
በሚሰጠው ዝርዝር መመሪያ መሰረት በፕሮጀክቱ የሚገኙ ቢሮዎችን የቢሮ ዕቃዎችን የመፀዳጃ ክፍሎችን ደረጃዎችን

ኮሊደሮችን ሌሎች ሊፀዱ የሚገባቸውን ቦታዎችና ዕቃዎችን ይጠርጋል ያጥባል ይወለውላል፡፡

ዝርዝር ተግባራት
1. በተመደበበት አካባቢ የሚገኙ የቢሮዎችንና በቢሮ ውስጥ የሚገኙ ጠረጴዛ፣ወንበር፣ ምንጣፍና የቢሮ መረጃዎችን

እንዲሁም ሌሎች ዕቃዎችን በጥንቃቄ ያፀዳል፡፡

2. ፅዳት ሲካሄድ አቧራ ሊይዙ የሚችሉ እንደ መስታወት፣መስኮትና ሻተር የመሳሰሉትን በንፁህ ጨርቅ በመጠቀም

ይወለወላል፡፡

3. ከቢሮና ከአካባቢው የሚወጡ ከአገልግሎት ውጪ የሆኑ ወረቀቶችን ሚስጥርነታቸውን በመጠበቅ በቆሻሻ

ማጠራቀሚያ በማከማቸት ያቃጥላል ያስወግዳል፡፡

4. የመፀዳጃ ቤቶችን ግድግዳዎችንና የመሳሰሉትን ያፀዳል፣ጣራና ግድግዳ ላይ የሚታዩ የሸረሪት ድሮችንና አቧራ

በረጅም መጥረጊያ ያስወግዳል፡፡

5. እንደአስፈላጊነቱ ከሌሎች የስራ ባልደረቦች ጋር በመሆን በሚሰጠው ፕሮግራም መሰረት ስፋት ያላቸውን

የመሰብሰቢያ አዳራሽ ግምጃ ቤት(ንብረት ክፍል) መዝገብ ቤት የመሳሰሉትን ያፀዳል፡፡

6. ለፅዳት የሚገለገልባቸውን እቃዎች በጥንቃቄና በቁጠባ ይጠብቃል፡፡

7. የፅዳት ስራውን ሲያጠናቅ መብራት መጥፋቱን፣ የውሃ ቧንቧ መዘጋቱን እና ቢሮዎች መቆለፋቸውን ያረጋግጣል፡፡

8. ቢሮዎችን በሚያፀዳበት ወቅት የሚያዩትን ሚስጥሮች የመጠበቅ ግዴታ አለበት

9. በተጨማሪ ኃላፊው የሚየዘውን ተጨማሪ ስራ የመስራት ግዴታ አለበት፡፡


የስራ ዝርዝር መግለጫ
የስራ መጠሪያ ፡- የፐርሶኔል ሠራተኛ

ተጠሪነቱ ፡- ለሰው ኃይል ቡድን

የስራ ክፍል፡- አስተዳደርና ፋይናንስ

ዋና ዋና ተግባራት
የድርጅቱን ሠራተኞች የቅጥር ምደባ፣ዝውውር፣ዕድገት፣ስንብት በአፈፃፀም መመሪያ መሰረት ይፈፅማል፡፡ ስለ ቡድኑ

እንቅስቃሴ ሪፖርት ያዘጋጃል፡፡

ዝርዝር ተግባራት
1. ስለ ድርጅቱ የወጡ መመሪያዎችን በአግባቡ ተግባራዊ ያደርጋል መደረጋቸውን ይቆጣጠራል፣ ያረጋግጣል፣እንደ

አስፈላጊነቱ የማሻሻያ ሃሳብ ያቀርባል ፣ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል ፡፡

2. ክፍት የስራ መደቦች በሚኖሩበት ጊዜ ከሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎች የሚቀርብ ጥያቄዎችን በመቀበል

በዝውውር ፣በምደባ፣በደረጃ እድገት ወይም በቅጥር እንዲሟሉ ማስታወቂያ ያወጣል ዕጩዎችን እንዲወዳደሩ

በማድረግ ክፍት የስራ መደቡን ያሟላል፡፡

3. የተቀጠሩ ሠራተኞችን የግል ማህደር በማዘጋጀት ለሪከርድና ማህደር ይልካል፡፡

4. የቅጥር፣የእድገት ወይም የዝውውር ምርጫ አጠናቆ በማስወሰን ተገቢውን ፎርማሊቲ በሟሟላት ሠራተኞች

በወቅቱ ስራ እንዲጀምሩ ያደርጋል፡፡

5. አዲስ ሠራተኞችን ከነባሮች ያስተዋውቃል፣ስለድርጅቱ አላማና ተግባር ስለ ዋና ዋና ደንብና መመሪያዎች ስለ

አደረጃጀቱ ገለፃ ያደርጋል፡፡

6. የሙከራና የቋሚ ቅጥር ሠራተኞች የስራ አፈፃፀም በየወቅቱ ተሟልቶ እንዲደርሰው ያደርጋል፣ትክክለኛነቱን

ያረጋግጣል በአስፈላጊው ጊዜ ጥቅም ላይ ያውላል፡፡

7. በስራ ዘርፎች ፕሮግራም መሰረት ልዩ ልዩ ተግባራት ጊዜያዊ ወይም የኮንትራት ሠራተኞችን ጥያቄ ሲቀርብ

ተገቢውን ማጣራት በማድረግ ሠራተኞችን በመመልመል የቅጥር ፎርማሊቲዎችን ያጠናቅቃል፣ከስራ ዘርፎች ጋር

ያገናኛል፣በወቅቱ እንዲሰናበቱ ያደርጋል፡፡


8. በዲሲፒሊን፣በጡረታ፣በሰራተኛው ፍላጎት፣ስራው በመጠናቀቁ የሚደረጉ ስንብቶችን አስፈላጊውን ፎርማሊቲ

በሟሟላት እንዲሰናበቱ ያደርጋል፡፡

9. የድርጅቱን ሰራተኞች ብዛት በትምህርት ደረጃና አይነት፣በዕድሜ፣በፆታ፣በደሞዝ፣በአገልግሎት አይነትና ዘመን

፣በሚሰሩበት የስራ ዘርፍ እና በመሳሰሉት መዝግቦ በመያዝ ፋይል ያደራጃል፡፡

10. ለሚቀርቡ የማስረጃ ጥያቄዎች ተገቢነታቸውን በማረጋገጥ እንዲሰጥ ያደርጋል፡፡

11. የዲሲፒሊን ጉድለት በመለየት ለሚመለከተው ያስተላልፋል ተመጣጣኝ የሆነ የውሳኔ ሃሳብ በማቅረብ ውሳኔ

ይሰጣል፡፡

12. የሠራተኞችን የፍቃድ ጥያቄ በመቀበል የጥያቄውን ተገቢነት በማጣራት ውሳኔ ይሰጣል፡፡

13. የስራ አፋፃፀም ምዘና ፎርሞችን ለክፍሎች ያሰራጫል የአፋፃፀም ምዘናው እንዲሟላ ይከታተላል ፡፡

14. ተሞልቶ የሚቀርቡለትን የስራ አፈፃፀም ምዘና ውጤት በማየት የእርምታ፣የማስተካከያ፣የማበረታቻ ስራዎችን

በማከናወን ከሰራተኛው ማህደር ጋር ያያይዛል፡፡

15. የደመወዝ ሰነድ ተዘጋጅቶ ሲቀርብ በማጣራት ለሚመለከተው ያስተላልፋል፡፡

16. በተጨማሪም ኃላፊው የሚያዘውን ስራ የመስራት ግዴታ አለበት፡፡


የስራ ዝርዝር መግለጫ
የስራ መጠሪያ ፡- ገንዘብ ያዥ

ተጠሪነቱ ፡- ለጠቅላላ ሂሳብ

የስራ ክፍል፡- አስተዳደርና ፋይናንስ

ዝርዝር ተግባራት
1. ለፕሮጀክቱ የተመደበውን የስራ ማስኬጃ ገንዘብ ተረክቦ ያስቀምጣል በሚሰጠው መመሪያና ትዕዛዝ መሰረት

ክፍያ ይፈፅማል ፣የፒቲ ካሽ ሪፖርትና መጠየቂያ ፎርም እያዘጋጀና እየሞላ ያቀርባል፡፡

2. ወጪ የሆነን የስራ ማስኬጃ ገንዘብ ሂሳብ ያወራርዳል እንዲተካም ይጠይቃል፡፡

3. በድርጅቱ የገንዘብ መሰብሰቢያ ሰነድ የድርጅቱን ገንዘብ ይሰበስባል፡፡

4. የሚሰበስባቸውን ገንዘቦች የፋይናንስ መመሪያው በሚፈቅደው መሠረት በባንክ ገቢ ያደርጋል፣የባንክ አድቫይስ

ኮፒዎችንም በአግባቡ ፋይል ያደርጋል፡፡

5. ገንዘብ የሰበሰበባቸውን የገንዘብ መቀበያ ሰነዶችና የባንክ ዲፖዚት ስሊፕ ለሒሳብ ምዝጋባና ሪፖርት ዝግጅት

በሰነድ ማስረከቢያ ቅፅ ያስረክባል፡፡

6. ማንኛውም የድርጅቱ ገንዘብ በካዝና ያስቀምጣል፣ ይቆጣጠራል፡፡

7. በየቀኑ የሚሰበስባቸውን ገንዘቦች (daily cash collection summary) ያዘጋጃል፡፡

8. የሚመመደቡለትን ፒቲ ካሽ በአግባቡ አስቀምጦ ከፒቲ ካሽ መከፈል የሚገባቸውን ክፍያ በተገቢው መልኩ

ያከናውናል፡፡

9. ክፍያ የተፈፀመባቸውን ማናቸውንም ሰነዶች ለገቢ መሰብሰብና የክፍያ አገልግሎት እስኪያስረክብ ድረስ በአግባቡ

ፋይል አድርጎ ያስቀምጣል ፡፡

10. በተዘጋጀው ፔሮል መሰረት በየወሩ ለሰራተኞች ደመወዝ ይከፋላል፡፡ ከሰራተኞች የሚሰበሰበውን ታክስና ሌሎች

ተቀናናሽ ለማዘጋጀት እንዲቻል የደመወዝ መክፈያ ፔሮል ኮፒ ለክፍያ ቡድን ያስረክባል፡፡


11. ለሂሳብ ምርመራ ኦዲተሮች በሚመጡበት ወቅት በካዝና ያለ ገንዘብ ያስቆጥራል በእጅ የሚገኙትንም ሰነዶች

ያስመረምራል፡፡

12. በተጨማሪ ኃላፊው የሚያዘውን ስራ የመስራት ግዴታ አለበት፡፡

የስራ ዝርዝር መግለጫ


የስራ መጠሪያ፡- አካውንታንት

ተጠሪነቱ፡- ለጠቅላላ ሂሳብ ሃላፊ

የስራ ክፍል፡- አስተዳደርና ፋይናንስ

ዝርዝር ተግባራት
1. የቼክ ክፍያ ቫውቸሮች ደጋፊ ሰነዶችን በሚገባ መሟላታቸውንና የምዝገባ መለያ ቁጥር በትክክል መፈፀሙን

መርምሮ ያረጋግጣል፣ስህተቶች ተፈፅመው ከተገኙ ያስተካክላል፡፡

2. ልዩ ልዩ ሰነዶችን ከመመሪያና ከሌሎች ደንቦች ጋር በማገናዘብ ትክክለኛውን አረጋግጦ ይመዘግባል፡፡

3. በኮንስትራክሽን ስራ ልዩ ልዩ ገቢ በደረሰኝ የሚሰበሰብ ገንዘብ ደረሰኝ ተከታታይ መሆኑን በተሰበሰበ ማግስት

ተጠቃሎ ባንክ መግባቱን ያረጋግጣል ለክፍሉ የሚደርሰውን የገንዘብ ደረሰኝ ከባንክ ደረሰኝ ጋር በማመሳከር

ትክክለኛነቱን በየዕለቱ ያረጋግጣል፡፡

4. ከበጀትና ኮስት ትንተና በሚደርሰው የንብረት ወጪ ማጠቃለያ መሠረት የሂሳብ ምዝገባ ያካሂዳል፡፡

5. የማወራረጃ ሰነዶች ትክክለኛ መሆናቸውን አረጋግጦ ሂሳብ ያወራርዳል፡፡

6. የባንክ አድቫይሶችን በወቅቱ ሂሳብ እንዲመዘገቡ ያደርጋል፣ተመላሽ ቼክ ሌሎች ያልተጣሩ ገቢዎች ወይም

ወጪዎች ካሉ ወቅታዊ ማጣራት አካሂዶ ዝርዝሩን ለክፍያ ገቢ ኢንቬስትመንት ያቀርባል፡፡

7. ወርሃዊየባንክ ስቴትመንት ዝርዝሩን ሂሳቡን ከፕሮጀክቱ የባንክ ሂሳብ ጋር ያነፃፅራል ፣ያስታርቃል ልዩነት ከታየ

ተገቢውን ማጣራት ያከናውናል፣የባንክ ሂሳብ ማስታረቅ መግለጫ ያዘጋጃል፡፡

8. የክፍሉን የሂሳብ ሰነዶች መረጃዎች በጥንቃቄ ይይዛል በመረጃም ሆነ በግልባጭ የፋይናንስ አስተዳደር ሳያውቅ

ፎቶ ኮፒ ተደርጎ ለሌላ ድርጅት እንዳይደርስ ጥንቃቄ ያደርጋል፡፡

9. ወርሃዊ፣የሩብ አመትና ልዩ ልዩ የሂሳብ መግለጫዎችን ያዘጋጃል ለሚመለከተው አካል እንዲደርስ ያደርጋል፡፡


10. ከፕሮጀክቱ የሚሰበሰበውን የስራ ግብር እና ከተከፋይ ሂሳብ ላይ ተቀናናሽ የተደረገውን ለሚመለከተው መስሪያ

ቤት በወቅቱ ገቢ እንዲደረግ ያደርጋል፡፡

11. የድርጅቱን አመታዊ ሂሳብ ያዘጋጃል ትርፍና ኪሳራ ሂሳብ መግለጫ ያዘጋጃል፡፡

12. ከንብረት ክፍል የሚሠጡትን የገቢና የወጪ ሰነዶችን ትክክለኛነቱን በማረጋገጥ በቢን ካርድ ላይ በመዝገብ

ባላንሱን ይቆጣጠራል፡፡

13. የባንክ ወጪ ማዘዛዎችን (cheek payment voucher) ኮድ ያደርጋል፡፡

14. በወጪ ማዘዣ የማይፈፀሙ ክፍያዎችን ማለትም በደብዳቤ ትዕዛዝ (bank order) የሚፈፅሙ ክፍያዎችን በሙሉ

ተገቢው ሰነድ እንዲኖራቸው ያደርጋል፣በባንክም ማስረጃ (Bank Advice) መሰረት ኮድ ያደርጋል፡፡

15. በተጨማሪ ኃላፊው የሚያዘውን ስራ የመስራት ግዴታ አለበት፡፡

You might also like