You are on page 1of 20

የ ኢትዮጵያ የ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት

የ ተሽከርካሪዎች ስምሪትና አጠቃቀም መመሪያ

መመሪ ያ ቁጥር ፡ 821/2013

ግንቦት 2009 ዓ.ም


አዲስ አበባ
ክፍል አንድ፡

1
ጠቅላላ
1. መግቢያ

የ ኢትዮጵያ የ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የ ገ ንዘብና ኢኮኖሚትብብር ሚ/ር ባወጣውየ ፌደራል


መንግስት ተሸከርካሪዎች ስምሪትና አጠቃቀም መመሪያ ቁጥር 32/2004 መሰረት አድርጎ ይህንን
መመሪያ አውጥቷል፡ ፡

2. አጭር ርዕስ

ይህ መመሪያ “የ ኢትዮጵያ የ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት የ ተሽከርካሪዎች ስምሪትና አጠቃቀም


መመሪያ ” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡ ፡

3. ትርጉም

የ ቃሉ አግባብ ሌላ ትርጉም የ ሚሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ መመሪያ ውስጥ ያሉ ቃላትና ሃረጎ ች
በኢትዮጵያ ፌደራላዊ መንግስት የ ግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 649/2001 የ ተሰጣቸውን
ትርጉም ይይዛሉ፡ ፡ ከዚህ በተጨማሪም ለዚህ መመሪያ አፈጻጸም፡ -

3.1 “የ በላይ ኃላፊ” ማለት ዋና ዳይሬክተር እና ምክትል ዋና ዳይሬክተር ማለት ነ ው፡ ፡


3.2 “ኢንስቲትዩት” ማለት ዋና መ/ቤትን ጨምሮ በሥሩ የ ሚገ ኙ የ ምርምር ማዕከላትን
የ ሚያስተዳድረውየ ኢትዮጵያ የ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ማለት ነ ው፡ ፡
3.3 “ኃላፊዎች” በኢንስቲትዩቱ ውስጥ የ ሚገ ኙ የ ስራ ሂደት ዳይሬክተሮች እና የ ማዕከል
ዳይሬክተሮች ማለት ነ ው፡ ፡
3.4 “ተሸከርካሪ” ማለት በመንገ ድ ላይ በሞተር የ ሚንቀሳቀስ ወይም የ ሚጎ ተት ለሰው ወይም
ለዕቃ ማጓጓዣ የ ሚውል ማንኛውም ተሸከርካሪ ማለት ነ ው፡ ፡
3.5 “ልዩ መታወቂያ” ማለት የ ኢንስቲትዩቱን ተሸከርካሪዎች ለሚያሽከረክሩ ኃላፊዎች
የ ኢንስቲትዩቱን ተሸከርካሪ ለማሽከርከር የ ተፈቀደላቸው መሆኑን ለማረጋገ ጥ የ ሚሰጥ
የ መታወቂያ ካርድ ነ ው፡ ፡
4. የ መመሪያውዓላማ

2
የ ትራንስፖርት ተሽከርካሪ ስምሪት አጠቃቀም ወጭ ቆጣቢ፣ ቀልጣፋ፣ ኃላፊነ ትንና ተጠያቂነ ትን
ባካተተ አሠራር የ ተጠቃሚዎችን ፍላጐት በማርካት የ ኢንስቲትዩቱን ተልዕኮ እንዲሳካ ለማድረግ
ነ ው፡ ፡

5. የ መመሪያውተፈጻሚነ ት ወሰን
ይህ መመሪያ በዋናውመ/ቤትና በኢንስቲትዩቱ ስር በሚገ ኙ ሁሉም ማዕከላት ተፈጻሚይሆናል፡ ፡

ክፍል ሁለት
6. የ ኢንስቲትዩቱ ተሸከርካሪ መረጃ አያያዝ፤ ሥምሪት፤ አጠቃቀምናቁጥጥር
6.1 የ ኢንስቲትዩቱ ተሸከርካሪ የ ህይወት ታሪክ መረጃ አያያዝ
6.1.1 ኢንስቲትዩቱ በግዥ፣ በስጦታ፣ በዝውውር፣ በኪራይና በሌሎች መሰል መንገ ዶች ተረክቦ
ለሚጠቀምበት ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ የ ተለየ የ ግል ማህደር በመክፈት በማህደሩ
ውስጥ ቢያንስ የ ሚከተሉትን መረጃዎች መዝግቦ ይይዛል፡ ፡
ሀ) የ ተሸከርካሪውሰሌዳ ቁጥር፣ አይነ ትና ሞዴል
ለ) የ ጭነ ቱ ልክ (በሰው፣ በኩንታል፣ በኪዩቢክ ሜትር፣ በሊትር)
ሐ) የ ቻንሲና የ ሞተር ቁጥሮች
መ) የ ሚጠቀመውየ ነ ዳጅ ዓይነ ት
ሠ) የ ተገ ዛበት ወይም በመ/ቤቱ ባለቤትነ ት ስር የ ዋለበት ቀንና ዓመተ ምህረት
ረ) ተሸከርካሪውየ ተገ ኘበት ሁኔታ፡ -በግዥ፤ በስጦታ፤ በርዳታ ወዘተ...
ሰ) የ ተሽከርካሪውዋጋ
ሸ) የ ባለቤትነ ት መታወቂያ ደብተር
6.1.2 በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 የ ተጠቀሱት መረጃዎች በበቂ ምክንያት ተሟልተው
ያልተገ ኙ እንደሆነ ባሉት መረጃዎች መሰረት ርክክብ ከተፈጸመ በኋላ ያልተገ ኙትን

3
መረጃዎች ዝርዝርና ምክንያት በተሽከርካሪውየ ህይወት ታሪክ ውስጥ ተመዝግቦ
ይያዛል፡ ፡ ያልተሟሉትንም መረጃዎች እንዲሟሉ ጥረት ይደረጋል፡ ፡
6.1.3 እያንዳንዱ የ ኢንስቲትዩቱ ተሽከርካሪ የ ህይወት ታሪክ መዝገ ብ የ ተሽከርካሪው
ርክክብ ከተፈጸመበት ጊዜ ጀምሮ እስኪወገ ድ ድረስ በኪ/ሜየ ሚጠቀመውን የ ነ ዳጅ፣
ዘይትና ቅባት ፍጆታ መጠን፣ የ ጥገ ና ወጪየ ተጓዘውኪ/ሜመጠን በማን ይዞታ ስር
እንደነ በረ ወዘተ አካቶ መያዝ አለበት፡ ፡
6.1.4 የ ተሽከርካሪውየ ህይወት ታሪክ መዝገ ብ ቢያንስ በዓመት አንድ ጊዜ እየ ተፈተሸ
ወቅታዊ መደረግ ይኖርበታል፡ ፡
6.1.5 መረጃ አያያዙ ዘመናዊ የ ሆነ ና በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የ ተደገ ፈ መሆን
አለበት፡ ፡

6.2. የ ኢንስቲትዩቱ ተሽከርካሪ ስምሪት


በኢንስቲትዩቱ ዋናውመ/ቤትና በማዕከላት ቀላልና ከባድ ተሽከርካሪዎች ለመስክ ጉዞ፣
ለከተማ ውስጥ ሥራና ለሠራተኞች ትራንስፖርት አገ ልግሎት ተለይተውይደለደላሉ፣
6.2.1 ተሽከርካሪዎችን በቅንጅት ለመጠቀም እንዲያስችል ሥምሪታቸው በፑል ይሆናል፤
የ ሥራ ሂደቶች የ ሥምሪት ጥያቄው በየ ሥራ ሂደቱ ተቀናጅቶ ይቀርባል፡ ፡ በዚህ
መሠረት የ ቀጣዩ ወር የ መስክ እንቅስቃሴና የ ተሸከርካሪ ጥያቄ ወሩ ከመድረሱ ከ
7 (ሰባት) ቀናት በፊት ለትራንስፖርት ሥምሪት ይቀርባል፡ ፡

6.2.2 ለድንገ ተኛ የ መስክ ሥራዎች የ ተሸከርካሪ አገ ልግሎት ጥያቄ ሲቀርብ ካለው


አቅርቦት ጋር በማመጣጠን የ ኢንስቲትዩቱ አስተዳደርና አቅም ግንባታ ም/ዋና
ዳይሬክተር ወይም ውክልና የ ተሰተው ክፍል አስቸኳይነ ቱን ገ ምግሞ ጥያቄው
እንዲስተናገ ድ ይደረጋል፡ ፡
6.2.3 ለማንኛውም የ ተፈቀደ የ መስክ ጉዞ ተሽከርካሪ ለማሰማራት በትራንስፖርት
ሥምሪትና ጥገ ና ቡድን የ ተፈረመ የ መንግስት የ ተሸከርካሪዎች አገ ልግሎት
መጠየ ቂያና መዘዋወሪያ ቅፅ መያዝ አለበት፡ ፡
6.2.4 የ ሥራ ሂደቶች/ ሠራተኞች የ ከተማ ውስጥ የ ትራንስፖርት አገ ልግሎት ሲፈልጉ
የ ተሽከርካሪ አገ ልግሎት መጠየ ቂያ ቅፅ ተሞልቶና በሚመለከተው የ ሥራ ሂደት
4
ኃላፊ ተፈቅዶ ለትራንስፖርት ሥምሪት ቡድን ከቀረበ በኋላ አገ ልግሎቱ የ ሚሰጠው
በቅደም ተከተልና በማቀናጀት ይሆናል፡ ፡
6.2.5 ለከተማ ውስጥ አገ ልግሎት የ ተመደቡ አነ ስተኛ ተሸከርካሪዎች ጥገ ና ሲገ ቡና ሌላ
ተመጣጣኝ ተሽከርካሪ መመደብ የ ማይቻል ሆኖ ሲገ ኝ ለመስክ ስራ የ ተመደቡ
ተሸከርካሪዎች በትራንስፖርት ሥምሪትና ጥገ ና ቡድን አማካኝነ ት በከተማ ሥራ
ላይ እንዲውሉ ማድረግ ይቻላል፡ ፡
6.2.6 አሽከርካሪዎች ከመስክ ጉዞ ሲመለሱ በተዘጋጀው ቅፅ መሠረት አፈጻጸማቸውን
ለትራንስፖርት ሥምሪት ቡድን ሪፖርት ያደርጋሉ፤
6.2.7 ለኃላፊዎች የ ተደለደሉ አነ ስተኛ ተሽከርካሪዎች ለጥገ ና ወደ ጋራዥ ሲገ ቡ
አቅርቦቱና የ ስራው ባህሪ እየ ታየ አነ ስተኛ ተሸከርካሪ እንዲመደብ
ይደረጋል፡ ፡
6.2.8 በግል ተሸከርካሪ የ ተመደበላቸው ሃላፊዎችና ባለሙያዎች በዓመት ፈቃድ እንዲሁም
ከአንድ ወር በላይ በሚሰጥ ሥልጠና ምክንያት በማይኖሩበት ጊዜ ተሸከርካሪውን
ለትራንስፖርት ሥምሪትና ጥገ ና ቡድን ማስረከብ አለባቸው፡ ፡
6.2.9 በግል ተሸከርካሪ የ ተመደበላቸው ሃላፊዎችና ባለሙያዎች በበላይ ኃላፊ
ካልተፈቀደላቸውበስተቀር ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭከ45 ኪ/ሜበላይ ማሽከርከር
አይችሉም፡ ፡
6.2.10 የ ሥራ ሂደት ዳይሬክቶሬቶች የ ቀጣዩን ሳምንት የ ከተማ ውስጥ የ ተሽከርካሪ
ጥያቄአቸውን ዘወትር አርብ እስከ ቀኑ 5፡ 00 ሰዓት ድረስ ለትራንስፖርት
ስምሪትና ጥገ ና ቡድን ያቀርባሉ፡ ፡ የ ትራንስፖርት ስምሪት ቡድንም የ ቀረበለትን
ጥያቄ በማቀናጀት ፕሮግራም ያወጣል፤ ለጠያቂው ያሳውቃል፡ ፡ ሆኖም በማዕከል
የ ማዕከሉን ዳይሬክተር በማፀደቅ ዘወትር ሰኞ እስከ ጠዋቱ 4፡ 00 ሰዓት ባለው
ጊዜ ውስጥ ለጠያቂውየ ሥራ ሂደት ወይም ቡድን ያሳውቃል፡ ፡
6.2.11 የ ትራንስፖርት ስምሪት ባለሙያው በቀረበው ሳምንታዊ፣ ወርሃዊ የ ተሽከርካሪ
ጥያቄ መሠረት በተሽከርካሪዎች መዘዋወሪያ ቅጽና በበር የ ይለፍ ፈቃድ ላይ መነ ሻ
ኪሎ ሜትርን ጨምሮ በመመዝገ ብ እየ ፈረመበት አገ ልግሎት እንዲሰጥ ያደርጋል፣

5
6.2.12 የ ስምሪት ባለሙያው የ ቀረቡለትን የ ተሽከርካሪ ስምሪት ጥያቄዎችለማቀናጀት
ችግር ካጋጠመው ከሚመለከታቸው የ ሥራ ሂደት ዳይሬክተሮች/ከማዕከልከዳይሬክተሩ
ጋር በመወያየ ት ችግሩ እንዲፈታ ያደርጋል፡ ፡
6.2.13 ከአቅም በላይ የ ሆነ ችግር ካላጋጠመ በቀር የ ተሸከርካሪዎችን አያያዝ
ውጤታማ ለማድረግ ለአንድ ተሽከርካሪ አንድ ሾፌር እንዲመደብ ይደረጋል፡ ፡
6.2.14 ኢንስቲትዩቱ ተሸከርካሪ የ ሚመድበው ባለው አቅም ነ ው፡ ፡ ሆኖም ከሥራው
አስፈላጊነ ት አንጻር የ ተሸከርካሪ ዕጥረት ሲያጋጥም በጀት መኖሩን በማረጋገ ጥ
የ መንግስት የ አገ ልግሎት ግዢን ደምብና መመሪያ በመከተል ተሸከርካሪበመከራየ ት
አገ ልግሎት እንዲሰጥ ይደረጋል፡ ፡

6.3. በሁኔታዎች አስገ ዳጅነ ት ከዕቅድ ውጪ የ ሚቀርቡ የ ተሽከርካሪ አገ ልግሎት ጥያቄዎችን


ስለማስተናገ ድ
6.3.1 ለከተማ ስምሪት፡ - በዋናው መ/ቤት በሥራ ሂደት ዳይሬክተሮች፣ በማዕከላት
በማዕከሉ ዳይሬክተር ሲፈቀድ፣
6.3.2 ለመስክ ስምሪት፡ - በዋናው መ/ቤት በበላይ ኃላፊው፣ በማዕከላት በማዕከሉ
ዳይሬክተር ሲፈቀድ አገ ልግሎቱ እንዲሰጥ ይደረጋል፡ ፡
 በመስክ ጉዞ ላይ አሽከርካሪው ከአቅም በላይ የ ሆነ ችግር ሲገ ጥመው
ለትራንስፖርት ስምሪትና ጥገ ና ቡድን አስተባባሪ በማሳወቅ ተገ ቢው የ መንጃ
ፈቃድ ደረጃ ያለው ተጓዥ እስከ ሚቀጥለው ከተማ ድረስ ብቻ እንዲያሽከረክር
ይፈቅዳል፣
 የ ሠራተኛ መጓጓዣ ሰርቪስ መኪና በተለያዩ ምክንያቶች አገ ልግሎቱ ቢቋረጥ ከሌላ
ማዕከል በውሰት ወይንም ከሌላ ድርጅት በኪራይ አገ ልግሎቱን እንዲያገ ኙ
የ ስምሪት ባለሙያው ከትራንስፖርት ተ/ጥ/ዳይሬክተሩ ጋር በመነ ጋገ ር እንዲፈፀም
ያደርጋል፡ ፡ ሆኖም የ ተጠቀሰው አማራጭ ሳይሳካ ቢቀር ሠራተኛው በራሱ
ትራንስፖርት በመጠቀም በሥራውላይ እንዲገ ኝ ያሳውቃል፣

6
 ለጉዞ በተፈቀደው የ ጊዜ ገ ደብ ውስጥ መጠናቀቅ ያልቻሉ የ መስክ ሥራዎች
ሲያጋጥሙለማጠናቀቅ የ ሚያስችል ተጨማሪ ቀናት በቡድን መሪው ለሥራ ሂደት
ዳይሬክተር ወይም ለማዕከል ዳይሬክተር አሳውቆ ማስፈቀድ ይችላል፣

ክፍል ሶስት

7. ስለ ተሸከርካሪ ድልድልና የ ትራንስፖርት አበል አከፋፈል


7.1. በግል ስለሚመደብ ተሸከርካሪ
በኢንስቲትዩትደረጃ የ ሚገ ኙ ሁሉም የ ምርምርና የ ድጋፍ ሰጭ ዳይሬክተሮችና የ ማዕከል
ዳይሬክተሮች ልዩ የ ተሸከርካሪ አገ ልግሎት እንደሚያስፈልጋቸው ይታወቃል፡ ፡ ስለሆነ ም የ ስራ
ኃላፊነ ትንና ባህሪን ባገ ናዘበ መልኩ ከዚህ በታች በተጠቀሰው ቅደም ተከተል መሰረት
የ ተሸከርካሪ ድልድሉ በበላይ አመራሩ እየ ታየ ይወሰናል፡ ፡

በዋናውመ/ቤት
 ለምርምር ዳይሬክተሮች፤
 ለቴክኒክ ድጋፍ ሰጭዳይሬክተሮች፤
 ለአስተዳደር ድጋፍ ሰጭዳይሬክተሮችና ባለሙያዎች (ፕሮቶኮልና ኢንሹራንስ)፤

በማዕከል
 የ ማዕከል ዳይሬክተሮች፤ ፣ በማዕከል የ ሚገ ኙ የ ምርምር ዳይሬክተሮች

7.2. የ ትራንስፖርት አበል አከፋፈልና የ ነ ዳጅ ድልድል

7
ኢንስቲትዩቱ በተሽከርካሪ ውስንነ ት ከላይ ለተገ ለፁት የ ሥራ ኃላፊዎች በሙሉ ተሽከርካሪ
መደልደል የ ማይቻል ሆኖ ሲገ ኝና እንዲሁም ያሉትን ተሽከርካሪዎች ዕድሜ በማራዘም፣ በቁጠባ
ለመጠቀም እንዲቻል የ ትራንስፖርት አበል እንዲከፈላቸው ይደረጋል፡ ፡ የ አበሉ ተመን
አመዳደብ ተሽከርካሪ ቢመደብ ሊወጣ የ ሚችለውን የ ተሽከርካሪ ወጪ /የ ነ ዳጅ፣ ዘይት፣
የ ቅባት፣ የ ጥገ ናና ..ወዘተ/ በማገ ናዘብ ነ ው፡ ፡ በመሆኑም፡ -

ሀ) የ ምርምርና የ ቴክኒክ ድጋፍ ሰጪየ ስራ ሂደት ዳይሬክተር/ማዕከል ዳይሬክተር


የ ስራ መሪዎች፣ የ ተመራማሪዎችና የ ቴክኒክ/ላቦራቶሪ ረዳቶች የ ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም ፓኬጅ
በማስመልከት ከጠቅላይ ሚ/ር ጽ/ቤት በተፈቀደውና ከሲቪል ሰርቪስ ሚ/ር ሰኔ 13 ቀን 2006
ዓ.ም. በቁጥር ሲ.ሰ.ሚ 13.1/ጠ10/10/226 በተጻፈ ደብዳቤ በተላከው የ አፈጻጸም መመሪያ
መሰረት ተፈጻሚይሆናል፡ ፡

ለ) የ አስተዳደር ድጋፍ ሰጪየ ስራ ሂደት ዳይሬክተር

ተሸከርካሪ ሊመደብለት ላልቻለ የ ድጋፍ ሰጪ የ ሥራ ሂደት ዳይሬክተር ስለሚከፈለው


የ ትራንስፖርት አበል በተመለከተ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አስፈጻሚ መ/ቤቶች ግልጽ መመሪያ
ለተቋሙሲደርስ የ ሚፈጸም ይሆናል፡ ፡
ሐ) የ ነ ዳጅ ድልድል

ተሸከርካሪ በግል ለተመደበለት ኃላፊ/ ባለሙያ

 ቤንዚን በወር 160 ሊትር እንዲሁም ናፍጣ በወር 200 ሊትር ይመደብለታል፡ ፡

ክፍል አራት

8. ለተሸከርካሪ የ ሚውሉ ግብዓቶች አጠቃቀም፤ አያያዝና ቁጥጥር

8.1 ነ ዳጅ፣ ዘይትና ቅባት አያያዝ፣ አጠቃቀምና ቁጥጥር

በከተማና በመስክ ጉዞ ላይ የ ሚወጣውን ነ ዳጅ፣ ዘይትና ቅባት ወጭ ለመቆጣጠርና


ለተፈቀደውሥራ ብቻ መዋሉን ለማረጋገ ጥ የ ሚከተሉት ተግባራት ይከናወናሉ፡ ፡

8
8.1.1 የ እያንዳንዱ ተሽከርካሪ የ ነ ዳጅ፣ ዘይትና ቅባት ፍጆታ ጥናት በሥምሪትና ጥገ ና
ባለሙያዎች ተዘጋጅቶ በሥራ ሂደቱ ዳይሬክተር ፀድቆ በሠንጠረዥ ይቀመጣል፣

8.1.2 ተሸከርካሪ በግል ለተመደበላቸው የ ስራ ኃላፊዎች ለከተማ ውስጥ እንቅስቃሴ


በሳምንት አንድ ጊዜ የ ተመደበላቸውን የ ነ ዳጅ ኮታ እንዲዘጋጅ ይደረጋል፣

8.1.3 የ ስምሪት ባለሙያው ለመስክ ጉዞ የ ተመደበ ተሽከርካሪ የ ነ ዳጅ፣ ዘይትና ቅባት


እንዲሁም አነ ስተኛ ጥገ ና ወጭዎችን አስልቶ ለጉዞው ቡድን መሪ ወጪእንዲያደረግ
ያሳውቃል፣

8.1.4 የ መስክ ጉዞ ቡድን መሪው ተሽከርካሪው የ ሚያስፈልገ ውን ነ ዳጅ፣ ዘይትና ቅባት


በመስክ ላይ ከሚገ ኝ ነ ዳጅ ማደያ በመግዛት ደረሰኝ መቀበል ይኖርበታል፣ በጉዞ
ላይ ላጋጠሙ አነ ስተኛ ጥገ ናዎች ወጪዎችም በተመሳሳይ መልኩ ደረሰኝ ይቀበላል፣

8.1.5 የ ቡድን መሪው በመስክ ጉዞ ወቅት ያወጣውን የ ነ ዳጅ፣ የ ዘይትና ቅባት እንዲሁም
የ ጥገ ና ወጪዎችን ዝርዝር ከአሽከርካሪው ጋር በማረጋገ ጥ ከመስክ ጉዞ መልስ
ሂሳቡን በ7 ቀናት ውስጥ ማወራረድ ይኖርበታል፤

8.1.6 አሽከርካሪው በከተማና በመስክ ጉዞ መጀመሪያና በጉዞው ላይ የ ተሞላውን ነ ዳጅ፣


ዘይትና ቅባት እንዲሁም ኪሎ ሜትር በተሽከርካሪ እንቅስቃሴ መቆጣጠሪያ (Log
Book) ላይ ይመዘግባል፣ የ ስምሪት ባለሙያውም መረጃው በትክክል መመዝገ ቡን
ያረጋግጣል፡ ፡

8.1.7 በአንቀጽ 8.1.6 መሰረት ኢንስቲትዩቱ አሰራሩን ወጥ ለማድረግ እንዲያግዘው ሁሉም


ተሸከርካሪዎች ጌጅ እንዲኖራቸውየ ማድረግ ግዴታ አለበት፡ ፡

8.1.8 የ ስምሪት ባለሙያው የ ሳምንቱ የ ተሽከርካሪዎች የ ነ ዳጅ፣ ዘይትና ቅባት ፍጆታ


ከተጓዙት ኪሎ ሜትር ጋር አገ ናዝቦ አግባብነ ቱን በማረጋገ ጥ
ለተሸከርካሪ፤ እርሻመሳሪያዎች ጥገ ናና ትራንስፖርት ማኔጅመንት ዳይሬክተር ሪፖርት
ያቀርባል፡ ፡

8.2 የ ተሽከርካሪዎች መለዋወጫዕቃዎች አቅርቦት፣ አያያዝና አጠቃቀም

9
8.2.1 በንብረት ክፍል ውስጥ በቂ ክምችት ያለመኖሩ እንዲሁምለግዢው በቂ በጀት መኖሩ
ሲረጋገ ጥ የ ጠቅላላ ተሽከርካሪዎች መለዋወጫ ባትሪ፣ ጐማና የ ውስጥ
ላስቲክ(ከነ መዳሪ) ግዥ ጥያቄ በጥገ ና ባለሙያ ተዘጋጅቶ ይቀርባል፣

8.2.2 በመስክ ጉዞ ላይ ብልሽት ላጋጠመው ተሽከርካሪ ለሚያጋጥሙያልተጠበቁ ሁኔታዎች


እስከ ብር 1,500 ወይም በዓመት ውስጥ እስከ ብር 30,000 ድረስ የ ሚደረግ ግዥ
በመስክ ሰራተኛው እና በሾፌር አማካኝነ ት ተፈጽሞ ጥገ ናው ይከናወናል፣ የ ተለወጡ
የ መለዋወጫ ዕቃዎችንም አሽከርካሪው በጥንቃቄ ይዞ ለጥገ ና ክፍሉ ያስረክባል፣
የ ጥገ ናውም አግባብነ ት በጥገ ናውባለሙያ ይረጋገ ጣል፣

8.2.3 የ ተሽከርካሪ ጥገ ና ባለሙያው በግዢ የ ሚቀርቡ የ መለዋወጫዕቃዎችክፍያ ከመፈፀሙ


በፊት በተጠየ ቀውመሠረት ጥራታቸውተጠብቆ መቅረባቸውን ያረጋግጣል፣

8.2.4 ማንኛውም ግዥ ከተመዘገ በ አስመጪኩባንያ ወይም ዕቃ አቅራቢ መሆን ይኖርበታል፣

8.2.5 በአስመጪኩባንያዎች ጋራዥ ውስጥ ከሚከናወን የ ተሽከርካሪዎች ጥገ ና በስተቀር፣


በውስጥና በውጪጋራዦች ለሚደረግ ጥገ ና የ ሚያስፈልግ የ መለዋወጫዕቃ ግዥ በዋናው
መ/ቤት ወይንም በማዕከላት ብቻ ይፈጸማል፣

8.2.6 ማናቸውም በግዥ ወይም በእርዳታ ወይም በስጦታ የ ሚመጡ የ ተሽከርካሪ መለዋወጫ
ዕቃዎችበንብረት ክምችትና ክፍፍልክፍል ገ ቢና ወጪይደረጋሉ፣

8.2.7 ከንብረትክምችትና ክፍፍልክፍል ወጪ የ ሆኑ የ ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች በዋናው


መ/ቤትና ማዕከላት ጋራዥ የ መለዋወጫግምጃ ቤት ገ ቢ ተደርገ ውበመጠየ ቂያ ቅጽ ወጪ
እየ ሆኑ በተሽከርካሪ ላይ እንዲገ ጠሙይደረጋል፣

8.2.8 የ ጥገ ና ባለሙያውአዳዲስ መለዋወጫዎች በትክክል በተሽከርካሪው ላይ መገ ጠማቸውን


ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፣

8.2.9 የ ጥገ ናባለሙያው ያገ ለገ ሉ መለዋወጫዎችንበትክክል መዝግቦ ላገ ለገ ሉ መለዋወጫ


ዕቃዎች ማከማቻ መጋዘን በቅጽ አስፈርሞ ያስረከባል፣

10
8.2.10

ገ ለገ ሉ የ ተሽከርካሪ ጐማዎች እንዲተኩ ሾፌሩ/ተጠቃሚው/ ሲጠይቅ፣ የ ጥያቄው


ትክክለኛነ ት በጥገ ና ባለሙያው ተረጋግጦ የ ጐማ መተኪያ ቅጽ ይሞላል፣ አሮጌዎቹ
ተፈትተውአዲሶቹ ይገ ጠማሉ፣

8.2.11

ገ ለገ ሉ ጐማዎች መጀመሪያ ወጭ ከሆኑበት ቅጽ ጋር የ ምርት ቁጥራቸው ተገ ናዝቦ


ላገ ለገ ሉ ዕቃዎች ማከማቻ መጋዘን ገ ቢ ይደረጋሉ፣

8.2.12

ዋናው መ/ቤትና በማዕከላት የ ሚገ ኙ የ ተሽከርካሪ መለዋወጫዎችን በትውስት ወይንም


በዝውውር መጠቀም ይቻላል፡ ፡

ክፍል አምስት

9. የ ኢንስቲትዩቱ ተሸከርካሪ ጥገ ና

ኢንስቲትዩቱ በዋናውመ/ቤትና በምርምር ማዕከላት የ ሚገ ኙ ተሽከርካሪዎች የ ማያቋርጥ የ ስምሪት


አገ ልግሎት መስጠት እንዲችሉ የ ሚከተሉት የ ጥገ ና አማራጮችን ይጠቀማል፡ ፡

9.1 በውስጥ ጋራዥ የ ሚከናወን የ ተሽከርካሪ ጥገ ና

9.1.1 አሽከርካሪው /ሾፌሩ/ የ ተሽከርካሪ ጥገ ና ጥያቄ ለቅርብ ኃላፊውያቀርባል፣

9.1.2 የ ጥገ ና ባለሙያ የ ጥገ ና ጥያቄውን መዝግቦ ይረከባል፣ ይመረምራል /ይፈትሻል/


ጥገ ናውእንዲከናወን ያደርጋል፣

9.1.3 የ ጥገ ና ባለሙያው መለወጥ የ ሚገ ባቸው የ መለዋወጫ ዕቃዎችን ዝርዝር ከነ መለያ


ቁጥራቸው (Part number) ያዘጋጃል፣ መለዋወጫው ዕቃ በግምጃ ቤት ውስጥ

11
መኖሩን በማረጋገ ጥ ወጭ ያደረጋል፣ ያለመኖሩ ከተረጋገ ጠ የ ግዥ መጠየ ቂያ ሞልቶ
ይጠየ ቃል፣ የ ተረከበውንም አዲስ መለዋወጫተሽከርካሪውላይ ይገ ጥማል፣

9.1.4 ጥገ ናው የ ተጠናቀቀለት ተሽከርካሪ በጥገ ና ባለሙያ ተፈትሾ ሲረጋገ ጥ አሽከርካሪው


/ሾፌሩ/ በቀረበውየ ጥገ ና ጥያቄ መሠረት መጠገ ኑን አረጋግጦ ይረከባል፣

9.1.5 የ ጥገ ና ባለሙያዎች ስለተከናወኑ የ ጥገ ና ሥራዎች ከጊዜ፣ ከወጪ ከጥራትና


የ ብልሽቱን መንስኤ በየ 15 ቀኑ በመወያየ ት ይገ መግማሉ፣ ለዳይሬክቶሬቱ ሪፖርት
ያቀርባሉ፣

9.2. በውጭጋራዥ የ ሚከናወን የ ተሽከርካሪ ጥገ ና


9.2.1 የ ጥገ ና አፈጻጸም
የ ተሸከርካሪው ብልሽት በውስጥ ጋራዥ መከናወን የ ማይችል መሆኑ ሲረጋገ ጥ
በአቅራቢያ ያሉትን ከፍተኛ የ ጥገ ና አቅም ያላቸው የ ግል ጋራዦችን በመንግስት
መመሪያ መሰረት በማወዳደር የ ሚጠገ ን ሆኖ፤
 አሽከርካሪው /ሾፌሩ/ የ ተሽከርካሪ ጥገ ና ጥያቄ ለቅርብ ኃላፊውያቀርባል፣
 የ ቀረበው የ ተሽከርካሪ ጥገ ና ጥያቄ በጥገ ና ባለሙያ ይመረመራል፤ በውጭ
ጥገ ና መጠገ ን እንዳለበት ሲታመንበት ባለሙያው የ ውጭ ጥገ ና መጠየ ቂያና
የ አገ ልግሎት ግዥ መጠየ ቂያ ይሞላል፣
 የ ተመረጠውጋራዥ ለጥገ ና የ ሚያስፈልገ ውን የ መለዋወጫዕቃ ብዛትና ዓይነ ት
ዝርዝር በጽሑፍ አቅርቦ በዳይሬክቶሬቱ ሲታመንበት የ ዕቃ ግዥ
መጠየ ቂያበጥገ ና ባለሙያው ተሞልቶ /በትራንስፖርት ተ/ጥ/ዳይሬክተር
ተረጋግጦ ግዢውእንዲፈጸም ይደረጋል፣
 የ ጥገ ና ባለሙያው የ ጥገ ናውን ሂደትና አፈጻጸሙን የ መከታተል ኃላፊነ ት
አለበት፣
 ጥገ ናው እንደተጠናቀቀ አሽከርካሪውና የ ጥገ ና ባለሙያው በጋራ ሆነ ው
በመፈተሽ በጥያቄው መሠረት ጥገ ናው መከናወኑን ያረጋግጣሉ፣ የ ጥገ ና
ባለሙያውም ተሽከርካሪውንና ያገ ለገ ሉ መለዋወጫዎችን ከጠጋኝ ድርጅት
ይረከባል፣

12
 የ እያንዳንዱ ተሽከርካሪ የ ጥገ ና ወጭና የ ብልሽቱ ዓይነ ት በተሽከርካሪው
የ ሕይወት ታሪክ ላይ በስምሪት ባለሙያው እንዲሞላ፣ የ ጥገ ና ባለሙያው
በዝርዝር አዘጋጅቶ ያቀርብለታል፣
 በጥገ ና ባለሙያዎችና በውጭጋራዥ የ ተጠገ ኑ ተሽከርካሪዎች መግለጫበየ ወሩ
ለሚመለከተውክፍል ሪፖርት ይደረጋል፣

9.2.2 የ ጥገ ና ኮሚቴ ስለማቋቋም

በውጭ የ ሚከናወኑ የ ተሸከርካሪ ጥገ ናዎችን የ ሚከታተልና የ ሚያስፈጽም በዋናው


መ/ቤትና በማዕከላት ቁጥራቸውከ3 ያላነ ሰና ከ5 ያልበለጠ አባላት ያሉበት ኮሚቴ
ይቋቋማል፡ ፡ የ ሚቋቋመውም ኮሚቴ ከዚህ በታች የ ተዘረዘሩት ተግባርና ሃላፊነ ቶች
ይኖሩታል፡ ፡
 የ ውጭ ጥገ ና በሚያስፈልግበት ወቅት በአስፈላጊነ ቱ ላይ ተወያይቶ የ ውሳኔ
አስተያየ ት ለማዕከሉ ዳይሬክተር ያቀርባል፣
 የ ማዕከሉ ዳይሬክተር ጥገ ናው እንዲከናወን ሲያምንበት የ መንግስትን የ ግዥ
መመሪያ መሰረት በማድረግ የ ጥገ ናውን ሂደት በቅርብ ተከታትሎ እንዲፈጸም
ያደርጋል፡ ፡
 ለውድድር የ ቀረቡትን ጋራዦች ደረጃቸውን፣ የ ፋይናንስ አቅማቸውን፣
የ ኢንሹራንስ ሽፋናቸውን እንዲሁም ቀደም ሲል የ ነ በራቸውን መልካም
አፈጻጸም ገ ምግሞ ደረጃ በማውጣት ለሚመለከተውየ ሥራሂደት ያቀርባል፣
 አሸናፊ በሆነ ውም ድርጅት ብቻ ጥገ ናውመከናወኑን ይከታተላል፣ ያረጋግጣል፣
 በጥገ ና ሂደቱ ላይ የ አፈጻጸም ችግር ካጋጠመ ከሚመለከታቸውጋር በመነ ጋገ ር
ችግሩ መፍትሄ እንዲያገ ኝ ጥረት ያደርጋል፤ እንደአስፈላጊነ ቱ ለማዕከሉ
ዳይሬክተር ወቅታዊ ሪፖርት ያቀርባል፡ ፡

9.3. በተሽከርካሪ አስመጪኩባንያዎች /ድርጅቶች/ ጋራዥ ውስጥ ስለማስጠገ ን፣


 የ ዋናው አምራች ኩባንያ ወኪል ጋራዦች /ድርጅቶች/ ወደ ሀገ ር ውስጥ ለሚያስገ ቧቸው
ተሽከርካሪዎች ብቁ የ ጥገ ና ጋራዥና ጥራታቸውን የ ጠበቁ (Jenuine) የ መለዋወጫ
ዕቃዎች አቅርቦት ያላቸው መሆኑ ሲታመንበት በእነ ኚሁ ጋራዦች ውስጥ ተሽከርካሪዎች
እንዲጠገ ኑ ይደረጋል፣
13
9.4. በተደራጁ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋራዥ ውስጥ በትብብር
ማስጠገ ን፣

 በውስጥ አቅም፣ በግል እንዲሁም በዋና አምራች ኩባንያ አስመጪ ጋራዦች ውስጥ
ማስጠገ ን ካልተቻለ በዋናው መ/ቤትና በማዕከላት አቅራቢያ የ ተደራጁ ጋራዦች ባሏቸው
መንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር ስምምነ ት በማድረግና መለዋወጫዎችን
በማቅረብ የ ተሽከርካሪ ጥገ ና እንዲከናወን ይደረጋል፡ ፡

ክፍል ስድስት

10. የ ኢንስቲትዩቱ የ ሥራ ኃላፊዎችና ሾፌሮች ተግባርና ኃላፊነ ት


ተሽከርካሪ በግል የ ተፈቀደለት ኃላፊ ተግባርና ሃላፊነ ት
o በሚያሽከረክርበት ጊዜ የ ተሰጠውን ልዩ የ ማሽከርከር ፍቃድ ይይዛል፣ በማንኛውም የ ህግ አስከባሪ
አካል ሲጠየ ቅ ያሳያል፣ ለሌላ ሰውአሳልፎ መስጠት አይችልም፣
o ተሽከርካሪውንና በውስጡያለውን መገ ልገ ያ መሣሪያ /ክሪክ፣ መፍቻ፣ ትርፍ ጐማ፣ ...ወዘተ/ ይረከባል፣
ጊዜውን ጠብቆ ሰርቪስ ያስደርጋል፣ ደህንነ ቱን ይጠብቃል፣ ይንከባከባል፣
o በተሽከርካሪውላይ ለሚደርሰውአደጋ ኃላፊነ ት አለበት፤ ይህም ማለት በተመደበለት ተሽከርካሪ
አደጋ በሚደርስበትጊዜ በትራፊክ ፖሊስ በሚሰጥ ማረጋገ ጫጥፋተኛ ሆኖ ከተገ ኘ በደንቡ መሠረት
የ ኤክሰስ ክፍያይከፍላል፣ አደጋውእንደደረሰም ለትራንስፖርት ስምሪት ባለሙያ ሪፖርት ያደርጋል፣
o ተሸከርካሪ በግል የ ተመደበለት ኃላፊ ከኃላፊነ ት ሲነ ሳ የ ተረከበውን ልዩ የ ማሽከርከር ፍቃድ፣
ተሽከርካሪውንና በውስጡያሉትንተጓዳኝ መሣሪያዎችን በተረከበውመሠረት ያስረክባል፣
o ከኢንስቲትዩቱ የ በላይ ኃላፊዎች በስተቀር ሌሎች ኃላፊዎች ተሽከርካሪዎቻቸውን ተገ ልግለው
በመ/ቤቱ ቅጥር ግቢ ሲያቆሙቀጥለውእስኪገ ለገ ሉ ድረስ ባለውጊዜ ተሽከርካሪው
ለስራከተፈለገ በስምሪት ባለሙያ እየ ተረጋገ ጠ ተጨማሪአገ ልግሎትእንዲሰጥ ይደረጋል፣ ለዚሁ ሥራ
የ ወጣውነ ዳጅ እንዲተካይደረጋል፣
o የ ማሽከርከር ልዩ ፈቃድ የ ተሰጠውኃላፊ የ ተመደበለትን ተሽከርካሪ ከጥገ ና ባለሙያ በስተቀር
ለሌላ ሰውእንዲያሽከረክር መስጠት አይፈቀድለትም፡ ፡

10.2. የ ኢንስቲትዩቱ ሾፌር ተግባርና ሃላፊነ ት


 የ ኢንስቲትዩቱ ንብረት የ ሆነ ተሽከርካሪን እንዲያሽከረክር ኃላፊነ ት የ ተሰጠውሾፌር
የ ራሱንና አገ ልግሎት የ ሚሰጣቸውን ተሳፋሪዎችደህንነ ት እንዲሁም የ አገ ሪቱን የ መንገ ድ
14
ትራንስፖርት ህግና ደንብ ከማክበር ባሻገ ር በባለቤትነ ት ስሜት በጥንቃቄ የ ማሽከርከር
እንዲሁምተሸከርካሪዉን በእንክብካቤ የ መያዝ ኃላፊነ ት አለበት፡ ፡
 በመሆኑም የ ሚከተሉትንተግባርና ኃላፊነ ቶች እንዲሁም የ ሥነ -ምግባር መርሆዎችንመጠበቅ
ይኖርበታል፡ ፡
 ሾፌሩ ለሥራ ከመሰማራቱ በፊት ራሱንና ተሽከርካሪውን ለሥራ ዝግጁ ማድረግ፣
 ከመጠጥ፣ ከአደንዛዥዕጽና ሱሰኝነ ት ራስን መጠበቅ፣
 የ ግልና የ ተሽከርካሪ ንጽህናንመጠበቅ፣
 የ ኢንስቲትዩትን ተሽከርካሪ ከተመደበበት ተግባር ውጭለሌላ አገ ልግሎት አለማዋል፣
 ለተሽከርካሪውየ ሚሰጠውን ነ ዳጅ፣ ዘይትና ቅባት በታማኝነ ት ለተመደበለት ሥራ ብቻ
ማዋል፣
 አገ ልግሎት የ ሚሰጥበትን ሰዓት ማክበር፣
 በሥራቦታ ወይም በጉዞ ላይ ባጋጣሚየ ሚሰማቸውን የ መ/ቤቱን ሚስጢ ሮች መጠበቅ፣
 የ ጥንቃቄ ቀበቶ ማሰርና ተሳፋሪዎች እንዲያስሩ ማድረግ፣
 ዘወትር የ መንጃ ፈቃዱን መያዝና ማሳደስ፣
 በጉዞ ወቅት ሾፌሩና ረዳቱ የ ተቋሙሠራተኞች መሆናቸውን የ ሚያረጋግጥ መታወቂያ /ባጅ/

በደረት ማንጠልጠል አለባቸው፣


 የ ተሽከርካሪ የ ዕለት መቆጣጠሪያ መዝገ ብ (Log Book) የ ሚጠይቀውን መረጃ በየ ቀኑ
በአግባቡ መዝግቦ በተሽከርካሪውውስጥ መያዝ፣
 በተሽከርካሪውየ ዕቃ መጫኛ ሥፍራ ላይ ሰውአለመጫን፣
 በተሽከርካሪ ውስጥ ተሳፋሪውንም ሆነ አካባቢውን የ ሚረብሽ የ ሙዚቃ ድምፅ አለማሰማት
እንዲሁም የ እምነ ት መዝሙሮችን አለመክፈት፣
 ጽሁፎችንና ምስሎችን በተሽከሪካሪውላይ አለመለጠፍ፣
 ለረዳቱ ተሽከርካሪውን እንዲያሽከረክር አለመፍቀድ፣
 ሞተር ብስክሌት በሚያሽከረክሩበት ጊዜ እንደሄልሜት ያሉ የ አደጋ መከላከያ መሣሪያዎችን
መጠቀም፣
 ከኢንስቲትዩቱ የ ሚሰጠውን የ ሥራ ልብስ /ዩኒፎርም/ በንጽህና ጠብቆ መልበስ፣
 እያሽከረከሩ ተንቀሳቃሽ ስልኮች ወይም ኢርፎን አለመጠቀም፣
 ለሥራ በከተማም ሆነ በመስክ የ ተሰማራን ተሽከርካሪ ከቡድን መሪውና ከተጠቃሚዎች እውቅና
ውጭወደ ሌላ ቦታ አለማንቀሳቀስ፣
 ከተሸከርካሪውየ ጭነ ት ልክ በላይ አለመጫን፣

15
 ከመስክ ጉዞ መልስ ተሽከርካሪውን አጥቦ፣ አጽድቶና ግሪስ አድርጐ ለሚቀጥለውስምሪት
ዝግጁ ማድረግ፣
 በሚያሽከረክረውተሸከርካሪ ላይ ስርቆት፣ ብልሽት ወይም አደጋ ቢያጋጥም በአካባቢው
ለሚገ ኝ ፖሊስና
 ለመ/ቤቱ የ ትራንስፖርት ክፍል ኃላፊና ኢንሹራንስ ኦፊሰር ወዲያውኑ ዝርዝር ሪፖርት
በስልክ ወይም በጽሁፍ ማቅረብ፣

ከመስክ ጉዞ መልስ ለቅርብ አለቃውስለጉዞውበጽሁፍ ሪፖርት ማቅረብ፤ እነ ዚህንና


10.2.23
ሌሎችም ከአንድ
መንግሥት ሠራተኛ የ ሚጠበቁ ተመሳሳይ መልካምሥነ -ምግባሮችአሽከርካሪው/ሾፌሩ/ አክብሮ ሊገ ኝ
ይገ ባል፡ ፡
አሽከርካሪው/ሾፌሩ የ ኢንስቲትዩቱን ተሽከርካሪ በመንግሥት መ/ቤት ወይንም ለጥበቃ አመቺ
10.2.24
በሆነ ቦታ ማሳደር አለበት፣
ከሥነ -ምግባር ውጭየ ሆነ አሽከርካሪ በፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1064/2010 እና
የ ሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 77/1994 መሠረት ጥፋቱ በዲስኘሊን ኮሚቴ የ ሚታይ
ይሆናል፡ ፡
ከተሸከርካሪ ተጠቃሚዎች የ ሚጠበቁ ስነ ምግባሮች
የ ኢንስቲትዩቱን ወይም የ ማዕከሉን ተሸከርካሪ ለከተማ ውስጥና ለመስክ ሥራዎች እንዲሁም
የ ትራንስፖርት ሰርቪስ አገ ልግሎት የ ሚጠቀም ተገ ልጋይ ከዚህ በታች የ ተጠቀሱትን ሥነ ምግባሮች
እንዲያሟላ ይጠበቃል፡ ፡

ለከተማ ስምሪት
የ ተመደበለትን ተሸከርካሪ ለመንግስት ሥራ አገ ልግሎት ብቻ ማዋል፤
በከተማ ውስጥ ጉዞ ወቅት የ ሥራ ጊዜን በአግባቡ መጠቀም፤
ጉዞው ከሌሎች ግለሰቦችና የ ስራ ሂደቶች ጋር በጣምራ ከሆነ በመግባባት ተሸከርካሪውን መጠቀም፤
ጊዜንና ጉልበትን ለመቆጠብ፣ የ ነ ዳጅ ፍጆታን እንዲሁም ወጪን ለመመጠን ተሸከርካሪን በጥምር
ለመጠቀም ዝግጁ መሆን፤
ለሥራ የ ሚሄዱበትን አካባቢና መ/ቤት በቅድሚያ ማወቅ፤
16
በመስክ ጉዞ
 አብረውከሚጓዙት የ ሥራ ባልደረቦች ጋር ተግባብቶ መጓዝ፤
 የ ጉዞ መነ ሻ ሰዓትን አክብሮ በቦታውመገ ኘት፤
 ተሸከርካሪ የ ሚመደበው ጉዞው ለተፈቀደለት ሰው ብቻ መሆኑን ጠንቅቆ በማወቅ አስፈላጊውን
መፈጸም፤
 የ ተመደበውን ተሸከርካሪ ጤንነ ትና ንጽህና መጠበቅ፤
 በጉዞ ላይ የ ሌሎች ቡድን አባላትን መብት ማክበር፤
 ለጉዞ የ ተፈቀደውን ጊዜ በአግባቡ በመጠቀም ወደ መደበኛ የ ሥራ ቦታ መመለስ፤

በከተማ ውስጥ ትራንስፖርት ሰርቪስ


 የ ትራንስፖርት ሰርቪስ ተጠቃሚ በሰርቪስ ተሸከርካሪ ውስጥ ማናቸውንም ዓይነ ት ቁሻሻ
ባለመጣል የ ተሸከርካሪውን ንጽህና የ መጠበቅ፤
 ተጠቃሚውበየ ፌርማታውየ ተመደበውን የ መሳፈሪያ ሰዓት አክብሮ መገ ኘት፤
 የ ትራንስፖርት ሰርቪስ ተሸከርካሪ ከዋናው መ/ቤት/ከማዕከል መነ ሻ ሰዓትን አክብሮ
በመሳፈሪያውቦታ መገ ኘት፤
 የ ትራንስፖርት ሰርቪስ ተሸከርካሪ ላይ የ ሌላውን ተጠቃሚ ምቾት የ ሚነ ሱ ድርጊቶች
አለመፈጸም፤
 እያንዳንዱ ተጠቃሚየ ግል ንጽህናውን መጠበቅ ይኖርበታል፤
 በትራንስፖርት ሰርቪስ ተሸከርካሪ ላይ ያሉትን ቁሳቁሶች በአግባቡ መጠቀም፤

17
ክፍል ሰባት

11.
11.1
በማንኛውም የ ኢንስቲትዩቱ ተሸከርካሪ ላይ የ ሚደርስ አደጋ ኢንስቲትዩቱ በገ ባው ውል
መሰረት
የ መድህን ሽፋን እንዲያገ ኝ ይደረጋል፡ ፡
11.2
የ ትራንስፖርት ስምሪት በኢንስቲትዩቱ የ ታቀዱ የ ምርምር ሥራዎችን በሚፈለገ ው መጠንና
ጥራትበአጭር ጊዜእንዲሳኩ ከሚያደርገ ውያላሰለሰ ጥረት ጐን ለጐን በኢንስቲትዩቱ ዋናው
መ/ቤትና በማዕከላት ሠራተኞች፣ ወርክሾፖች ውስጥና በተሽከርካሪዎች ላይ ሊደርሱ የ ሚችሉ
አደጋዎችን ለመከላከል ከዚህ ቀጥሎ የ ተጠቀሱት ተግባራት መከናወን አለባቸው፣
11.2.1 በኢንስቲትዩቱ ዋናው መ/ቤትና በማዕከላት በሚገ ኙ ወርክሾፖች ውስጥና
በተሽከርካሪዎች ላይ ሊደርሱ የ ሚችሉ አደጋዎችን ለመከላከል የ ሚረዱ
መሣሪያዎችንና የ እሳት ማጥፊያዎችን በየ ጊዜው ጥራታቸውና የ አገ ልግሎት ጊዜያቸው
እየ ታየ እንዲታደሱና እንዲስተካከሉ በማድረግና አመቺ በሆኑ ሥፍራዎች በማስቀመጥ
አደጋውን ለመከላከል እንዲያስችሉ ዝግጁ ማድረግ፣

11.2.2 የ እሳት አደጋ ሊያስከትሉ የ ሚችሉ ሁኔታዎችን ለማስወገ ድ ጥረት እየ ተደረገ


አደጋዎች ቢያጋጥሙ ሠራተኞች ሳይደናገ ጡ አደጋውን በቁጥጥር ሥር
ሊያውሉስለሚችሉበት ሀኔታና ስለ እሳት አደጋ መከላከያ መሣሪያዎች አጠቃቀም
ለጥገ ና ባለሙያዎች፣ ለአሽከርካሪዎች፣ ለጥበቃ ሠራተኞች.. ወዘተ ሥልጠና መስጠት፣

11.2.3 በኤሌክትሪክ በሚሽከረከሩ መሣሪያዎች፣ በብረታ ብረት ብየ ዳና ቅጥቀጣ እንዲሁም


በቀለም ቅብ ወቅት የ ተለያዩ አደጋዎች ሊደርሱ ስለሚችሉ፣ ከፍተኛ ጥንቃቄ
ማድረግ፣

11.2.4 በእያንዳንዱ ተሸከርካሪ ላይ የ እሳት አደጋ መከላከያ እንዲገ ጠም ማድረግና


መጠቀም፣

18
ክፍል ስምንት
12. ስለ ሪፖርት አቀራረብ

12.1

ኢንስቲትዩቱ ሥር የ ሚገ ኙ ሁሉም የ ምርምር ማዕከላት በተሸከርካሪ ስምሪትአጠቃቀም ላይ


የ ተከናወኑ ተግባራትን ያጠቃለለ ግልጽና ተጨባጭ የ ሆነ ወርሃዊ ሪፖርት በማዕከሉ
ዳይሬክተር ተረጋግጦ ወር በገ ባ እስከ 5ኛው ቀን ለኢንስቲትዩቱ ትራ/ተ/እ/መ/ጥ
ዳይሬክቶሬት መድረስ አለበት፡ ፡

12.2
የ ኢንስቲትዩቱ ትራ/ተ/እ/መ/ጥ ዳይሬክቶሬትም የ ማዕከላቱንና የ ዋናውን መ/ቤት ወርሃዊ
ሪፖርት በማጠናቀር ለኢንስቲትዩቱ የ በላይ አመራር ያቀርባል እንዲሁም ሌሎች ባለ ድርሻ
አካላት ይልካል፡ ፡

ክፍል ዘጠኝ
ልዩ ልዩ

13.

 የ ኢንስቲትዩቱ ተሸከርካሪ፤ መለዋወጫ፤ ባትሪና ጎ ማ አወጋገ ድን በተመለከተ በመንግስት

ንብረት አስተዳደር መመሪያ ቁጥር 9/2003 ላይ ስለ መንግስትንብረት አስተዳደርና

አወጋገ ድ የ ሚደነ ግጉ አንቀፆች በሥራ ላይ ያሉት የ መንግስት የ ቋሚንብረት አስተዳደር እና

የ ስቶክ አስተዳደር ማንዋሎች እንደአግባብነ ታቸውለኢንስቲትዩቱ ተሸከርካሪዎች ተፈፃ ሚነ ት

ይኖራቸዋል፡ ፡

 የ ኢንስቲትዩቱ የ ሥራ ሂደቶችና ማዕከላት ከዚህ መመሪያ ጋር አባሪ የ ሆኑትን ቅፆች መጠቀም

አለባቸው፡ ፡
19
 አገ ልግሎታቸውን የ ጨረሱ የ ተሽከርካሪ መለዋወጫዎች በመንግስት የ ንብረት አወጋገ ድ መመሪያ

መሰረት እንዲወገ ዱ ይደረጋል፡ ፡

14. ጾታዊ አገ ላለጽ


በዚህ መመሪያ ውስጥ በወንድ ጾታ የ ተገ ለጹት ሁሉ ለሴት ጾታም ያገ ለግላሉ፡ ፡
15. የ ተሻረ መመሪያ እንዲሁም ሰርኩላሮች
መስከረም 1978 ዓ.ም በኢንስቲትዩቱ የ ወጣው የ ትራንስፖርት አገ ልግሎት መመሪያ እንዲሁም
የ ኢንስቲትዩቱን የ ተሸከርካሪ ስምሪትና አጠቃቀም ለማሻሻል በተለያየ ጊዜ ከኢንስቲትዩቱ የ ተላለፉ
ሰርኩላሮች በዚህ መመሪያ ተሸረዋል፡ ፡

16. መመሪያውበሥራ ላይ የ ሚውልበት ጊዜ ጊዜ

ይህ መመሪያ በኢንስቲትዩቱ በላይ ኃላፊ ከፀደቀበት ከዛሬ ሐምሌ 1 ቀን 2011 ዓ.ም ጀምሮ በሥራ
ላይ ይውላል፡ ፡

መመሪያውን ያጸደቀውየ ኢንስቲትዩቱ የ በላይ አመራር

ስም፡ ፊርማ፡ ቀን፡

20

You might also like