You are on page 1of 7

© ቡድን 6 የንግድ አማካሪ የከተማ ውስጥ የታክሲ አገልግሎት አዋጭነት

ጥናት

የፕረጄክቱ ስም ከገበያ እስከ መሸንቲ የከተማ ውስጥ ታክሲ


አገልግሎት መስጠት አዋጭነት ጥናት

የባለቤት ስም ወ/ሪት ውብአለም

አማካሪ ቡድን 6

ጥር 31, 2018 እ.ኤ.አ


© ቡድን 6 የንግድ አማካሪ የከተማ ውስጥ የታክሲ አገልግሎት አዋጭነት
ጥናት

ማውጫ

1. አላማ......................................................................................................................................................2
2. የአጠናን ዘዴ.............................................................................................................................................2
3. የገበያ ጥናት..............................................................................................................................................3
4. ቴክኒካል ጥናት........................................................................................................................................4
5. ፋይናንስ.................................................................................................................................................5
6. የጥናቱ ውጤትና ምክር............................................................................................................................5

ሠንጠረዥ 1 የገበያ ጥናት መረጃ መሰብሰቢያ ቅፅ..................................................................................................6


ሠንጠረዥ 2 የፋይናንስ ትርፍና ኪሳራ መግለጫ (የ 6 አመት ፎረካስት).....................................................................7

1. አላማ
ወ/ሪት ውብአለም ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ቶሎ ለመድረስ ለሚፈልጉ ደንበኞች በከተማ ውስጥ የታክሲ አገልግሎት
ለመስጠት በማሰብ የሚከተሉትን አላማዎች አስቀምጠው፤የእርሳቸውንም ሆነ የሌላ ሰው ገንዘብ ኢንቨስት ለማድረግ

ገፅ 1 of 7
© ቡድን 6 የንግድ አማካሪ የከተማ ውስጥ የታክሲ አገልግሎት አዋጭነት
ጥናት

የሚያስችል ውሳኔ ለማግኘት በፈለጉት መሰረት በሚከተሉት አላመዎች ላይ ጥናታዊ ምክርና የአዋጭነት የውሳኔ ሀሳብ
መስጠት ይሆናል፡፡
 ከአንድ ስፍራ ወደ ሌላ ስፍራ በፍጥነት ለመድረስ ለሚሹ ጓዛቸው ቀላል የሆነን ተሳፋሪዎች ዘና አድርጎ
የሚያስቀምጥና በተፈለገው ጊዜ ሊገኝ የሚችል ታክሲ በከተማ ውስጥ እዉን ማድረግ
 ከገበያ እስከ መሸንቲ ስራው ቢጀምር ውጤታማ መሆን መቻል
 ከፍተኛ ተሳፋሪ በሚኖርበት ጊዜ ብቻ በየ 30 ደቂቃው ታክሲዋ ቢሞላም ባይሞላም የያዘችውን ይዛ
ለመንቀሳቀስ
 የኢንቨስትመንቱ ትርፋማነትና አማራጭ የፋይንናስ ምንጮችን ለማወቅ የሚያስችል መረጃ ማግኘት

2. የአጠናን ዘዴ
ይህን ጥናት ለማከናወን ወ/ሪት ውብአለም የከተማ ውስጥ ታክሲ አገልግሎት ለመስጠት በአቀረቡት ዝርዝር
ፍላጎትና ወሰን መሰረት አማካሪ ቡድኑ አዋጭና ትክክለኛ የሆኑ ለመረጃው ቅርብ የሆኑ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ
የመረጃ ምንጮችን በመለየት የጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት በመድረግ የመስክ ስራ አካሂዷል፤
 የመጀመሪያ የመረጃ ምንጮችን በአካል በማግኘት ኢንተርቪውና ውይይት በማድረግ መረጃ
ተሰብስቧል፡፡
 የስምሪትና የተራ ተቆጣጣሪዎች
 የታክሲ ሾፌሮችና ረዳጾች
 የታክሲ ባለንብረቶች

 ካልአይ(ሁለተኛ) የመረጃ ምንጮችን በአካል ቃለ መጠይቅ በማድረግና በስልክ መረጃ ተሰብስቧል


 የጋራዥ በለቤቶችን
 የአበዳሪ ተቋማትን(አባይ ባንክ፣ ንግድ ባንክ)

3. የገበያ ጥናት
የገበያ ጥናቱ ወሰን ከባህዳር ከተማ ከገበያ እስከ መሸንቲ ያለውን የገበያ ሁኔታ በመጀመሪያ የመረጃ ምንጮችን
በመጠቀምና የስምሪቱን ሁኔታ ከከተማዋ የመንገድና ትራነስፖርት መመሪያና ስርአት አኳያ በማጥናት
የሚከተሉትን መሰረታዊ መረጃዎች ተገኝተዋል፤
 የስምሪት ሁኔታ
ከገበያ እስከ መሸንቲ የታክሲ አገልግሎት ለመስጠት የከተማዋ የታክሲ ማህበርና የትራንስፓርት
ስምሪት ቢበዛ ወር አንድ ጊዜ በምደባ የሚሰራ ሲሆን ወረፋ ጠብቆ ብቻ አገልግሎት መስጠት
ይቻላል፡፡
 የተወዳዳሪዎች ብዛት
በዚህ ቀጠና አገልግሎት ለመስጠት ብዛት ከ 20-30 የሚሆኑ ታክሲዎች የተመደቡ ሲሆን ቢያንስ
5 የሚሆኑ በብልሽትና በተለያየ ሁኔታ አገልግሎት ሳይሰጡ ይቀራሉ፡፡
 የገበያ ድርሻ
ከተሰማሩት አገልግሎት ሰጪ ስምሪቶች አኳያ አዲስ ቢሰማራ 5% የገበያ ድርሻ አለው፡፡

ገፅ 2 of 7
© ቡድን 6 የንግድ አማካሪ የከተማ ውስጥ የታክሲ አገልግሎት አዋጭነት
ጥናት

 አማካይ የጉዞ ምልልስ በ 1 ቀን፡ በቀን በአማካይ 4 ዙር (ደርሶ መልስ መስራት ይቻላል)
 የተሽከርካሪ አይነትና ሁኔታ
አሁን የሚገኙት ተሽከርካሪዎች አብዛኞቹ ያገለገሉ ሲሆኑ አልፎ አልፎ አዲስ/ብዙ ያልሰራ
ይመደባል፡፡
 ከመነሻ እስከ መድረሻ የሚወስደው ጊዜ አማካይ፡ በአማካይ በአንድ ጉዞ 45 ደቂቃ መድረስ
ይቻላል፡፡
 ደርሶ መልስ የሚፈጀው የነዳጅ ወጪ መጠን፡ ደርሶ መልስ በአማካይ 70 ብር ለነዳጅ ይወጣል፡፡
 ተሳፋሪዎች የሚበዙበት ቀንና የተሳፋሪ ሁኔታ
በሳምንት ውስጥ ካሉ ቀናት ውስጥ ቅዳሜና ሰኞ እና ሀሙስ ብዙ ተሳፋሪዎች ለገበያና ለስራ
ስለሚንቀሳቀሱ ጥሩ የጉዞ ምልልሶች ስለሚኖሩ ጥሩ ገቢ ይገኝባቸዋል፤ በሳምንት ውስጥ ባሉ
ቀናት ውስጥ በአማካይ 4 ዙር ደርሶ መልስ መስራት የሚቻል ሲሆን ወደ ፊትም ብዙ የፋብሪካ
ግንባታዎ፣የአነስተኛ የቤት ክራይን ታሳቢ በማድረግና የገበያ እንቅስቃሴን መሰረት በማድረግ ብዙ
ደንበኞች አገልግሎት እንደሚፈልጉ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
 የአንድ ጉዞ ታሪፍ፡ በመንገድና ትራንስፓርት ባለስልጣን የተወሰነ የታሪፍ መጠን 10.61 ብር
ሲሆን እንደሁኔታ ለሻሻል የሚችል ታሪፍ ነው፡፡
 ሌሎች መረጃዎች በአባሪነት በሰንጠረዥ 1 ተዘርዝረው ይገኛሉ

4. ቴክኒካል ጥናት
ይህ የጥናት ክፍል የምንጠቀመውን የተሽከርካሪ አይነት፣ አቅም፣ የመንገድ ሁኔታ፣ የጊዜ አጠቃቀም የጉዞ ሁኔታ
የሚዳስስ ይሆናል፡፡

 የተሸከርካሪ ሁኔታ
በአብዛኛው በስራ ላይ ተሰማርተው ያሉ የታክሲ አይነቶች 3 ኤል ታክሲ አይነቶች ሲሆኑ 80-100 ኪ.ሜ/በሰአት
መነዳት የሚችሉ ናቸው፡፡ ያገለገሉ በአማካይ 275000 ብር በገበያ ላይ ሊገዙ የሚችሉ ሲሆኑ በጣም አዲስ
ያልሆኑ ሰከንድ ሀንድ 12 ሰው መጫን የሚችሉ እስከ 700000 ብር በአማካይ ይገኛሉ፡፡
 የከተማ ክልል የፍጥነት ወሰን ገደብ
በመንገድና ትራንስፓርት ህግ መሰረት በከተማ ክልል ውስጥ ከ 60 ኪ.ሜ/በሰአት መንዳት ክልክል እንደሆነና
እንደሚያስቀጣም ያስቀምጣል፡፡ ስለሆነም ከገበያ እስከ መሸንቲ ያለው ክልል በከተማ ስለሚከለል በተጠቀሰው
ፍጥነት ገደብ በታች ማሽከርከር ግድ ይላል፡፡
 የመነሻና መድረሻ ርቀት በኪ.ሜ
ከገበያ መሸንቲ በአማካይ 21 ኪ.ሜ
 የጊዜ አጠቃቀምና የስጋት ስሌት
በአንድ ኡዞ ከገበያ እስከ መሸንቲ ያለውን ፈጣኑን የመድረሻ ጊዜ ለማወቅ የፍጥነት ወሰን ገደብንና ኪ.ሜትሩን
ተጠቅመን በማስላት ማግኘት የሚቻል ሲሆን ይህ ጊዜ ምንም የትራፊክ መዘግየትም ሆነ ጥበቃ ሳይኖር የተሸከርካሪውን
የነዳጅ ፍጆታንና የጉዞ ምልልስን ለመገመትና ለማወቅ የሚያስችል ነው፡፡

=21x1 ገፅ 3 of 7
ሰዓት =0.35 ሰዓት
60
© ቡድን 6 የንግድ አማካሪ የከተማ ውስጥ የታክሲ አገልግሎት አዋጭነት
ጥናት

ከውጤቱ እንደሚታየው በአንድ ዚር (ትሪፕ) ከገበያ እስከ መሸንቲ ያለምንም ማቋረጥ በከፍተኛ
ፍጥነት(60 ኪ.ሜ/ሰዓት) ቢያሽከረክሩ መድረስ እንደሚቻል ያሳያል፡፡
ስለሆነም ከ 21 ደቂቃዎች በታች ተመላልሶ ለመስራት የሞገደኝነት አነዳድን ሊያመጣ የሚችል ንብረትንና
ህይወትን ሊጎዳ የሚችል አላስፈላጊ ወጭን ሊያስከትል ይችላል፡፡
 የመጫን አቅም ሁሉም ታክሲዎች 12 ሰዎች መጫን ይችላሉ
 የተሽከርካሪ አስፈላጊ የመለዋወጫና የጥገና ወጪዎች
በሠንጠረዥ 1 ላይ መረጃውን ማግኘት ይቻላል

5. ፋይናንስ
ከገበያ ወደ መሸንቱ ደርሶ መልስ ካለው የገበያ ተወዳዳሪ ብዛትና ድርሻ አኳያ አገልግሎት መስጠት የሚቻለው ወረፋን
ጠብቆና ቢበዛ በ 1 ወር ውስጥ 1/4 ኛውን ቀናት በሺፍት ተመደቦ ስለሆነ እና በቀን 4 ዙር በአማካይ ስለሚሰራ በአማካይ
በ 1 አመት ውስጥ 90 ቀናት በመስራት ለ 6480 ሰዎች አገልግሎት በመስጠት 68752.80 ብር ገቢ ይገኛል፡፡

በአገለገለ ተሽከረካሪ ስራዉን ለማስጀመር 365229.00 ብር መስሪያ ካፒታል ያስፈልጋል፡፡ የገቢ ትርፍ ማግኘት
የሚቻለው ከ 3 ኛው አመት ጀምሮ በመሆኑና ካሚታሉን መመለስ የሚችለው ከስድስት አመት በኋላ ይሆናል፡፡ ስለሆነም
ትርፋማነቱ ሲታይ ብዙ የሚጠቅም እንዳልሆነ ሲሆን ከአበዳሪም ሆነ የራስን ገንዘብ ኢንቨስት ማድረግ አይመከርም፡፡

6. የጥናቱ ውጤትና ምክር


ከላይ ከአላማው በመነሳት በተገኙት የገበያ ጥናቶች፣የቴክኒካል ጥናቶችና የፋይናንስ ውጤቶች መሰረት የቢዝነስ
አዋጭነት ጥናቱ ከገበያ እስከ መሸንቲ ባለው የጉዞ መስመር አገልግሎቱን መጀመር በታሰበው ልክ አዋጭ ስላልሆነ
ብድርም ሆነ የራስን ገንዘብ ኢንቨስት ማድረግ አይመከርም፡፡

ገፅ 4 of 7
© ቡድን 6 የንግድ አማካሪ የከተማ ውስጥ የታክሲ አገልግሎት አዋጭነት
ጥናት

ሠንጠረዥ 1 የገበያ ጥናት መረጃ መሰብሰቢያ ቅፅ

የገበያ ጥናት መረጃ መሰባሰቢያ ፎርም


የፕሮጄክቱ ስም፡ የታክሲ አገልግሎት ከባህር ዳር እስከ መሸንቲ መስጠት አዋጭነት ጥናት
1  
2 መረጃ ማሰባሰቢያ ዘዴ፡ ቃለ መጠይቅ  
ተ.ቁ የመረጃው አይነት የተገኘው ዉጤት
1 ከበህዳር ስምሪት ቦታ እስከ መሸንቲ ያለው ርቀት 21 ኪ.ሜ
2 በቀን የሚሰማሩ የታክሲዎች ብዛት 20-30
3 በአንድ ጉዞ የከፈል ታሪፍ 10.60 ብር
4 በአንድ ጉዞ ከመነሻ እስከ መድረሻው የሚወስደ ጊዜ 45 ደቂቃ
5 ስምሪቱን በስንት ጊዜ ሊገኝ ይችላል በ 1 ወር አንድ ሳምንት
በሳምንት ውስጥ ቅዳሜ 5 ደርሶ መልስ፣ ሰኞ 4
6 በእያንዳንዱ የስራ ቀን ተሳፋሪ የሚበዛበት ጊዜ ጊዜ
7 በመነሻና በመድረሻ መካከል የሚሳፈር ሰው ብዛት 5 ሰዎች
ዝቅተኛ የቤት ክራይ ለግኘትና ፋብሪካዎች
በመጀመራቸ የቀን ሰራተኞችና ዝቅተኛ
8 ወደ ፊት ሊኖሩ ይችላሉ ተብለው የሚገመቱ ደንበኞች የማህበረሰብ ኗሪዎች ወደ ይባብ ስለሚገኙ
9 እቃ የሌላቸው ካላቸው አንጸር በመቶኛ ስሌት 71.43%
10 አገልግሎት የሰጠ መኪና የሚገዛበት ዋጋ 275000
11 አዲስ መኪና ለመግዛት የሚያስችል ዋጋ 7000
12 ለታሲዋ ጥገና በአመት ሊወጣ የሚችል ወጭ 20000
13 ለተራ አስከባሪ ለስምሪትና ምዝገባ 10 በቀን ፣200 ብር አመት
14 የሾፌር ደመወዝና ጥቅማጥቅም 1500
ያገለገለ መኪናን ወደ ታክሲነት ለመቀየር፣ለግጭት መከላከያ‹ ለመስታወት ፣ ወዘተ
15 አስፈላጊ ወጭ 170565
  ቅባት  
15.1 የመሞተር ዘይት 15/40 6050
15.2 የትራንስሚሽን 90 1275
15.3 ዲፈረንሻል ዘይተ 90 1020
15.4 የነዳጅ ወጭ 112800
  መለዋወጫ  
15.5 ጎማ 15000
15.6 የፍሪን ሸነራ 2100
  ፊልትሮ  
15.7 የነዳጅ ማጣሪያ 200
15.8 የዘይት ማጣሪያ 1920
15.9 የአየር ማጣሪያ 400

ገፅ 5 of 7
© ቡድን 6 የንግድ አማካሪ የከተማ ውስጥ የታክሲ አገልግሎት አዋጭነት
ጥናት

16 ኢሹራንስ 3 ኛ ወገን 1800


17 የመኪና ኢንሹራንስ 18000
     

ሠንጠረዥ 2 የፋይናንስ ትርፍና ኪሳራ መግለጫ (የ 6 አመት ፎረካስት)

ከገበያ እስከ መሸንቲ የታክሲ አገልግሎት ፕሮጄክትድ የ 6 አመት ትርፍና ኪሳራ (ፎርካስቲንግ ኢንካም ስቴትመንት)መግለጫ
አመት 1 2 3 4 5 6
የስራ ቀን ብዛት 90 90 90 90 90 90
የተጠቃሚ ብዛት በቁጥር 6480 6480 6480 6480 6480 6480
የአገልግሎት ወጭ የአንድ ጉዞ ዋጋ ብር 10.61 12.2015 15.86195 15.86195 15.86195 15.86195
ጠቅላላ ገቢ(3x4) 68752.8 79065.72 102785.4 102785.4 102785.4 102785.4
የተሸከርካሪ ግዥ(ኢነቨስትመንት) 275000 0 0 0 0 0
የሰራተኛ ደመወዝና ጥቅማጥቅም ወጪ 18000 18000 18000 18000 18000 18000
የመለዋወጫ፣የጥገና፣የነዳጅ እና ሌሎች ወጪዎች 44079 44079 44079 44079 44079 44079
አስተዳደራዊ ወጪ 3350 3350 3350 3350 3350 3350
ኢንሹራንስ 19800 19800 19800 19800 19800 19800
ግብር 5000 5000 5000 5000 5000 5000
ወጪ 1(6+7+8+9+10+11) 365229 90229 90229 90229 90229 90229
ትርፍ ከእርጅና ቅናሽ በፊት(5-12) -296476.2 -11163.3 12556.44 12556.44 12556.44 12556.44
እርጅና ቅናሽ 4125 3712.5 2970 2079 1247.4 873.18
ወጪ 2(15=14) 4125 3712.5 2970 2079 1247.4 873.18
ጠቅላላ ወጭ(12+15) 369354 93941.5 93199 92308 91476.4 91102.18
የተጣራ ትርፍ -300601.2 -14875.8 9586.436 10477.44 11309.04 11683.26
የትርፍ ግብር 2%            

ገፅ 6 of 7

You might also like