You are on page 1of 11

አቤኔዘር ኮምፒውተር ሽያጭ

አዘጋጅ ፡- አቤኔዘር መስፍን

ሚያዝያ 2015 ዓ.ም

1
ማውጫ
ተ.ቁ ገፅ
የሽፋን ገፅ...............................................................................................................................................................1
ማውጫ..........................................................................................................................................................2
መግቢያ...........................................................................................................................................................3
የማህበሩ ጠቅላላ እንቅስቃሴ..........................................................................................................................3
 ራዕይ
 ተልዕኮ
 ግብ
 እሴቶች
መልካም አጋጣሚዎች...................................................................................................................................4
ሊሻሻሉ የሚገባቸው ሁኔታዎች.........................................................................................................5
የምርት ዝግጅት..............................................................................................................................................5
የፋይናንስ ፍላጎት.............................................................................................................................................5
እቅድ............................................................................................................................................................6
የገበያ ጥናት......................................................................................................................................................6
የገበያ ዕቅድ.......................................................................................................................................................7
አመታዊ የወጪና ገቢ ዝርዝር......................................................................................................................9
የ 2015 የገቢና ወጪ መግለጫ..............................................................................................................10
ማጠቃለያ....................................................................................................................................................10

2
መግቢያ
የድርጅቱ ስምና አድራሻ
አድራሻ፡- ቢሾፍቱ ኢትዮጵያ
ቀበሌ 01 የቤት.ቁ. 869
ስልክ. ቁጥር +251939386687. +251911950339

ኢሜል abenumoss@gmail.com
አቤኔዘር የዶሮ እርባታ በአቤኔዘር መስፍን አማካኝነት የተቋቋመ ሲሆን ከሀረር TVET ኮሌጅ በ ዲፕሎም
የተመረቀ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በቢሾፍቱ ከተማ በግል የስራ ዘርፍ በኮምፒውተር ሽያጭ ሱቅ በመክፈት ስራ
በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

ጠቅላላ እንቅስቃሴ
እንደሚታወቀው ማንኛውም ሰው የኑሮ ሁኔታውን ለማሻሻል በቁርጠኝነትና በትጋት መስራት እንዲሁም መንግስት በፈጠረው ምቹ
ሁኔታን አሟጦ መጠቀም ለድርድር የሚቀርብ ሳይሆን ዛሬ ነገ ሳይባል የሚጠቀሙበት ነው፡፡ ይህን የዶሮ እርባታ ሳቋቁም
በመጀመሪያ ለራሴ የስራ እድል መፍጠር ሲሆን በትጋት በመስራትም ትርፋማ በማድረግ ኑሮዬን በማሻሻል ለሌሎችም የስራ
እድል መፍጠር ነው፡፡
የመረጥኩት የስራ ዘርፍ በተገቢው ሁኔታ ሀገራችን ወደ ቴክኖሎጂ እየሄደች ያለችበት መንገድ አንፃር ከተሰራበት አዋጭ በመሆኑ
ካለኝ ልምድና እውቀት በመነሳሳት ትርፋማ እንደሚሆን በራስ መተማመን ወደ ስራው ገብቻለሁ፡፡ ይህ የኮምፒውተር ሽያጭ
እንቅስቃሴ ለተለያዩ የግልና የመንግስት ተቋማት እንዲሁም ሆቴሎችና የንግድ ተቋማት ብዙ ፍላጎትና አቅርቦት የፈልጋሉ
ሀገራችንም አየሄደችበት ያለውን የዲጂታል እና የቴክኖሎጂ ጉዞ አብሮ ለመጓዝ እንዲሁም ሌላው አለም የደረሰበት ደረጃ
ለመድረስ ትልቁን ድርሻ ይይዛል፡፡
ይህንን የኮምፒውተር ሽያጭ ለማቋቋም ስነሳ በእጄ የሚገኙ መልካም አጋጣሚዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡
- ንግዱን እንዴት ማንቀሳቀስ እንዳለብን ስልጠናና እውቀት ያለን መሆኑ
- ከ 2 ዓመት በላይ በዚህ ዘርፍ ላይ እና ሽያጭ ልምድ ያለን መሆኑን
- ለዚህ ስራ የሚሆን በመሃል ከተማ የመስሪያ ቦታ ያለን መሆኑን
- ለኮምፒውተር ሽያጭ የሚያስፈልጉ ምቹ ቦታ፣ መደርደሪያዎች፣ አልሙኒየም ዲስፐላይ እና የመሳሰሉት ንብረቶች ያሉን መሆኑ
- ስራውን ለማከናወን የሚያስችል በቂ ልምድ ያለው የሰው ሀይል መኖሩ
እነዚህ በሙሉ በማዋሀድ ከእናንተ የብድር እና ቁጠባ ተቋም የገንዘብ ብድር ድጋፍ ብናገኝ እቅዳችን ከግብ ማድረስ
እንደምንችል ድምዳሜ ላይ ደርሰናል፡፡

3
ራዕይ
ዘመናዊ የሆነ እና ጥራት ያላቸውን ኮምፒውተሮችና ተዛማጅ እቃዎች ለህብረተሰቡ ማቅረብ
ተልዕኮ
ዘመናዊ የሆነ እና ጥራት ያላቸውን ኮምፒውተሮችና ተዛማጅ እቃዎች ለህብረተሰቡ ማቅረብ ማቅረብ ነው፡፡ ቀጣይነት ባለው ልማት
ውስጥ የተሻሻለና ተወዳዳሪነት ያለው በመሆን የደንበኞችን ፍላጎት በስፋትና በጥራት ማርካት ነው፡፡ ደንበኞች ከጊዜ ወደ ጊዜ
ከሚያሳዩት ፍላጎት ጋር ተመጣጣኝ እድገት በማስመዝገብ የንግድ እንቅስቃሴያችንን እያሳደግን እንዲሁም እያስፋፋን
የአገራችንን የቴክኖሎጂ ግስጋሴ ውስጥ ተሳትፎ ማድረግ ነው፡፡
ግብ
ለቀጣዩ ትውልድ ጥራት ያላቸውን ከፐምፒውተሮችና ተዛማጅ እቃዎችን የማህበረሰቡን ፍላጎት ባማከለ ሁኔታ ያለንን ግብዓት
አማጦ በመጠቀም በገበያ ያለውን ፍላጎት ማማላት ነው፡፡ ከግዜ ወደ ግዜ እያደገና እየሰፋ ያለውን የገበያ ፍላጎት ደረጃውን
በጠበቀ ሁኔታ ለህብረተሰቡ ተመጣጣኝና ጥራት ባለው መልኩ ለገበያ ማቅረብ ነው፡፡ እያደገና እየተስፋፋ የሚሄድ በጥራትና
አለማችን የደረሰበትን የቴክኖሎጂ ጥግ የሆኑትን ከውጪ በማስገባትና እንዲሁመ በሃገር ውስጥ በመገጣጠም ምሳሌ መሆን
የሚችል ማህበራዊ ሀላፊነቶችን የሚወጣ ማህበር ማድረግ ነው፡፡
እሴቶች
በስራ ሂደታችን ውስጥ የሚከተሉትን እሴቶች በቀን ተቀን እንቅስቃሴያችን አንደ ስንቅ የምንጠቀምበት ይሆናል፡፡
 ደንበኞችን ያማከለ አገልግሎት መስጠት
 ውጤታማ ለመሆን ያለመ ቁርጠኝነት
 ሀላፊነት
 ተጠያቂነት
 ቀጣይነት ያለው ስራ
 መልካም የሥራ ግንኙነት
 ማህበራዊ ሀላፊነትን መወጣት
 ጥራትና ደህንነቱ የተጠበቀ ተዋፅዖ ማቅረብ

መልካም አጋጣሚዎች
 የንግድ እንቅስቃሴ እና ቴክኖሎጂው በስፋት እያደገና እየሰፋ መምጣቱ
 የግሉን ዘርፍ የሚያበረታታ የመንግስት ፖሊሲ መኖሩ
 የስልጠና የብድር አቅርቦት በመንግስት በኩል መኖሩ
 የባለሞያዎች ክትትል መኖሩ

4
ሊሻሻሉ የሚገባቸው ሁኔታዎች
 በተፈለገው ጊዜ የብድር አገልግሎት ማቅረብ አለመቻል
 ጉዳዮችን በማስፈፀም ሂደት ውስጥ በፍጥነትና በአጭር ጊዜ ያለማከናወን
 በባለጉዳዮች የቀጠሮ ቀን ጉደዩ የሚመለከታቸው የስራ ሀላፊዎች መገኘት አለመቻል
ገጥሞን የነበረ ችግር
ሃሌል ኮምፒውተር በ 2011 ዓ.ም የተመሰረተ ሲሆን የብድር አገልግሎት ለማግኘት ሰፊ ጥረት ቢያደርግም ሳይከናወንለት
ቀርቷል፡፡ ተስፋ ሳንቆርጥ ከቤተሰብና ከጓደኞቻችን በመበደር አሁን ያለንበት ልንደርስ ችለናል፡፡
ዝግጅት
ይህ የኮምፒውተር ስራ የወደፊት ምልከታው ጥራት ያለውን ዝቃ ከውጭ ከማስገባት ጀምሮ በሃገር ውስጥ በመገጣጠም
ለማህበረሰቡ ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ ጥራት ያለውን እቃ ማቅረብ ነው፡፡ እንዲሁም ስራውን በሌላ ቦታ የማስፋትና የመክፈት
እቅድ ይይዛል፡፡

የፋይናንስ ፍላጎት
ሃሌል ኮምፒውተር የመስሪያ ቦታ ቤት የተከራየ ሲሆን ለስራው የሚያስፈልጉ ቋሚ እቃዎች ግምታቸው ከ 50 ሺህ ብር በላይ
የሆነ ሲሆን ስራውን ለማስፋትና ለማሳደግ በብድር መልክ 300,000 (ሶስት መቶ ሺ ብር) የሚያስፈልገን ሲሆን ሌሎች
ወጪዎች በራሴ የሚሸፈኑ ይሆናል ማለት ነው፡፡

እቅድ
እንደሚታወቅው ይህን የኮምፒውተር እና ተዛማጅ ስራዎችን ስንመሰርት የመጀመሪያ ግባችን የስራ እድልን በመፍጠር ትርፋማ
መሆን ነው፡፡ ይህን በማድረግ ደግሞ ዘመናዊ በሆነ መንገድ ጥራት ያለውን ምርት ለደንበኞች በተገቢው ሁኔታ በማቅረብ ዘላቂነት ያለው
ደንበኛን ማግኘት ነው፡፡ ይህንን ወደ ተሻሻለ እርከን ለማድረስ የተማረ እና የሰለጠነ የሰው ሀይል ያለን መሆኑን ንግዳችንን
አቀላጥፈን መጓዝ እንድንችል ይረዳናል፡፡

5
 የአጭር ጊዜ እቅድ
የአጭር ጊዜ እቅዶቻችንን በሚከተለው መልክ ማስቀመጥ ችለናል
- ለእራሳችን የስራ እድል መፍጠር
- አቅማችንን ማደራጀት
- አገልግሎቶቻችንን ለደንበኞች በስፋት ማቅረብ
- ሌላ ሰፋ ያለ የማርቢያ ቦታ ማዘጋጀት
 የረጅም ጊዜ እቅድ
የረጅም ጊዜ እቅዶቻችንን በሚከተለው መልክ አስቀምጠናል
- ቅርንጫፎቻችንን በተለያዩ ቦታዎች ማስፋት
- በስፋት የስራ እድል መፍጠር
- ወደ አምራች ኢንዱስትሪ ማደግ
- ንግዳችንን ወደ ሌላ የንግድ ዘርፍ ማስፋት
- በተጨማሪ ሞባይል እና የቴክኖሎጂ እቃዎችን ማምረትና ለገበያ ማቅረብ

የንግዱ ሁኔታ
በሀገሪቱ እየታየ ባለው ከፍተኛ የኢኮኖሚ እድገት የሰዎች የመግዛት አቅም ከጊዜ ወደ ግዜ እየጨመረ መጥቷል ይህ የኑሮ መሻሻል
የንግዱን እንቅስቃሴ እያቀላጠፈ ሲሆን ከዚህ እንቅስቃሴ መሀል በኮምፒውተር እና በቴክኖሎጂው ዘርፍ ከፍተኛ ፍላጎት ያለ
ሲሆን የአቅራቢዎችም የአምራቾች እጥረትም እንዳለ ማስተዋል ይቻላል፡፡ ከዚህም በመነሳት በዚህ የንግድ ዘርፍ ላይ
መሰማራት ከሚያስገኘው ጠቀም ያለ ትርፍ ባሻገር በገቢያው ላይ የሚታየውን ፍላጎት የድርሻችንን ለመሙላት ትልቅ መነሳሳት
ፈጥሮብናል፡፡

የገበያ ተወዳዳሪዎች ምልከታ


በንግድ እንቅስቃሴያችን ዙሪያ የተለያዩ ተወዳዳሪዎች የሚገኙ ሲሆን በአገሪቱ ያለው ፍላጎት ደግሞ ከአቅራቢዎች የማቅረብ
አቅም እጅግ ይበልጣል፡፡ ይህ በመሆኑ በከተማው የሚገኙ በቁጥር በርከት ያሉ ጥቃቅን አቅራቢዎች ቢኖሩም ነገር ግን ከገበያ ጋር
ያላቸው ትስስር ደካማ በመሆኑ ከሽያጫቸው በሚገባው መልኩ ተጠቃሚ ሲሆኑ አይታይም፡፡ ስለዚህ እኔም ይህንን ክፍተት
በመመልከት በገበያ ውስጥ ያለው ልምድ በመጠቀም በስፋት ተጠቃሚ በሚያደርገው ቀጥተኛ መንገድ በመግባት
ከተወዳዳሪዎቻችን በተሻለ መልኩ ትርፋማ መሆን እንችላለን፡፡

የገበያ ጥናት
ገበያ በውስጡ ገዢዎችንና ሻጮችን የያዘ ሲሆን በአቀራረባቸውና በፍላጎታቸው የተለያዩ ናቸው፡፡ለምሳሌ በፍላጎታቸው፣
በአቅርቦት አይነት፣ የአገዛዝና የሽያጭ ባህል ይለያያል፡፡ ሌላው ገበያን በማጥናት ሂደት ውስጥ ለተማሪ የዊሆኑ፣ መልሶ ለመሸጥ
የሚገዙ፣ ለመንግስት እና ለግል መስሪያ ቤትና አንዲሁም ለሆቴሎች የሚሆን በሚል ከፋፍለን ማየት እንችላለን፡፡ ከዚህ
በመነሳት የሚጠቀመው ቁንፅል የገበያ ሂደት የሌለው ሲሆን በስፋት ለሚረከቡ ለመንግስት መስሪያ ቤቶች

6
ለኢንተርኔት ካፌዎች ቅድሚያ በመስጠት የሚሸጥ ሲሆን ወደፊት በማስፋፊያው ሂደት ውስጥ በከተማ ውስጥ የተለያዩ ብራንቾችን
ሱቆች በመክፈትም ሽያጭ ያከናውናል፡፡ ስለዚህም ዋነኛ የገበያ ትኩረቶቻችን
 ለመንግስትና ለግል መስሪያ ቤቶች
 ኢንተርኔት ካፌዎች
 ተማሪዎች ወደዩኒቨርሲቲ በሜገቡበት ወቅት
ሃሌል ኮምፒውተር በሀገሪቱ ያለውን ምቹ የገበያ አማራጮች ሙሉ ለሙሉ አማጦ ለመጠቀም አቅደል፡፡
የገበያ ዕቅድ
1. የንግድ እንቅስቃሴ
ሃሌል ኮምፒውተር ሽያጭ ቀልጣፋ የሆነ የንግድ አካሄድና አርኪ የደንበኞች አያያዝ አስመልክቶ ስልጠና እና በተግባር
የተፈተነ የልምድ ልውውጥ በዘርፍ ካሉ አአቅራቢዎች ወስዷል፡፡ ይህም የንግድ እንቅስቃሴን አሳድጎ በማስኬድ ሂደት ውስጥ
የሚኖሩ ተግዳሮቶችን በቀላሉ ማለፍና ውጤታማ መሆን ይችላል ማለት ነው፡፡ የአካባቢያዊ ዳሰሳና የህብረተሰቡን ፍላጎት
አስቀድመን በማወቃችን ሱቃችን ሊይዘው የሚገባውን መንገድ እንዲሁም ስኬታማ ሊያደርጉን የሚችሉ የገበያ ሁኔታ ልምድና
የአካሄድ እውቀት ያለን በመሆኑ ስኬታማ እንደምንሆን እርግጠኛ ነኝ፡፡
2. የገበያ መዳረሻ
ሃሌል ኮምፒውተር ቋሚና ጊዜያዊ ደንበኞች የሚኖሩት ይሆናል፡፡ ቋሚ ደንበኞች መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት
ይሆናሉ፡፡ በጊዜያዊና ተለዋዋጭ ደንበኞች የግል የንግድ ተቋም እንዲሁም የሽያጭ ማዕከላትን የምንጠቀም ሲሆን
በአገልግሎታችን አሰጣጥ ከተጠቀሱት መካከል ቋሚ ደንበኞችን የምናፈራ ይሆናል፡፡

ማህበሩ ያሉት ንብረቶች ዝርዝር

የንብረቶች ዝርዝር ብዛት

30 የሜሆኑ ላፕቶፖችን የሚይዝ መደርደሩያ 1

2 ሜትር አልሙኒየም ዲስፕይ 1

ጠረቤዛ 2

ተሸከርካሪ ወንበር 1

ዲስፐሌይ ቦርድ 1

7
የኮምፒውተርና ተዛማጅ እቃዎች መነሻ ወጪ ዝርዝር

የወጪ አይነት መጠን መለኪያ የአንዱ ዋጋ ጠቅላላ ዋጋ

ጂ 3 ላፐቶፕ 7 ብዛት 24000 168000

780 ዴስክቶፐ 6 ብዛት 8000 48000

የላፕቶፕ ሃርድ ዲስክ 10 ብዛት 1800 18000

የዴስክቶፐ ሃርድ ዲስክ 10 ብዛት 2000 20000

1 ቴራ ኤክስተርናል ሃርድ 6 ብዛት 4500 27000


ዲስክ
ማውዝ 25 ብዛት 350 8750

ኪቦርድ 25 ብዛት 350 8750

ሰራተኛ 1 ብዛት 1500 1500

ጠቅላላ ዋጋ 300,000

8
የኮምፒውተርና ተዛማጅ እቃዎች አመታዊ ሽያጭ

የሽያጭ አይነት መጠን በወር በወር የአንዱ ዋጋ ጠቅላላ ዋጋ አመታዊ ጠቅላላ


ጠቅላላ የሽያጭ ጊዜ አመታዊ
ብዛት አማካኝ ብዛት ሽያጭ

ጂ 3 ላፐቶፕ 3 28000 84000 9 ወር 756,000

780 ዴስክቶፐ 4 9500 38000 9 ወር 342,000


የላፕቶፕ ሃርድ ዲስክ 6 2500 15000 8 ወር 120,000
የዴስክቶፐ ሃርድ ዲስክ 6 2800 16800 8 ወር 134,400
1 ቴራ ኤክስተርናል 3 6000 18000 6 ወር 108,000
ሃርድ ዲስክ
ማውዝ 12 500 6000 10 60,000
ኪቦርድ 12 500 6000 10 60,000
ጠቅላላ ዋጋ 1,580,000

ሃሌል ኮመፒውተር
የ 2015 ዓ.ም የገቢና ወጪ መግለጫ

የተለያዩ ወጪዎች ዴቢት ክሬዲት


ጂ 3 ላፐቶፕ 168000

780 ዴስክቶፐ 48000

የላፕቶፕ ሃርድ ዲስክ 18000

የዴስክቶፐ ሃርድ ዲስክ 20000


1 ቴራ ኤክስተርናል ሃርድ ዲስክ
27000
ማውዝ
8750
ኪቦርድ
8750

ሰራተኛ 1500

የብድርወለድ 40500
የሚመለስ ብድር 300000
የግብር ክፍያ 30000
አመታዊ ቁጠባ 300000

9
(ሀ)ጠቅላላድምር 970,500

የገቢዎች ዝርዝር

የኮምፒውተርና ተዛማጅ እቃዎች አመታዊ ሽያጭ 1,580,000

(ለ)ጠቅላላ ድምር 1,580,000


(ለ-ሀ) ጠቅላላ ትርፍ 609,500

10
ማጠቃለያ
ከላይ ለማስቀመጥ እንደሞከርኩት የስራ ዝግጅትና እቅዱን ሙሉ ለሙሉ በስራ ላይ ለማዋል ዝግጁ ስሆን የገንዘብ ድጋፍ
ግን ከድርጅታችሁ እፈልጋለው፡፡ ይህ የዶሮ እርባታ ስራ ውጤታማ እንደሚሆን በመተማመን አንድናገር ካስቻሉኝ
ሁኔታዎች መካከል በጥቂቱ ለመከለስ ሞክራለዉ፡፡
 ጫጩት በማሳደግና በመንከባከብ ልምድ ያለው መሆኑ
 እንዴት ማደግ እንዳለባችውና ውጤታማ መሆን እንደሚችሉ ጠንቅቆ ያውቃል
 ጥራቱ ጠብቆ ለገበያ ማቅረብ ይችላል
 ገበያ ውስጥ ለመግባት ልምድና ብቃት አለን
 በአዲስ አበባ ከሚገኙ ሱፐር ማርኬቶችና ሆቴሎች ጋር በጣም የጠበቀ ትስስር
ያለው ነው
 ሌሎች ትላልቅ የዶሮ አርቢዎችን አሰራርና የእድገት መንገድ በማጥናት መከተል የሚገባውን መንገድ ጠ n ሚ የሆኑ
መረጃዎችን በእጁ ይዟል፡፡
 በተማረ የሰው ሀይል የተጠናከረ መሆኑ
ስለዚህም የዶሮ እርባታ ስራችን ተገቢውን ድጋፍ ከእናንተ ማግኘት ከቻለ ባለው ልምድና ቁርጠኛነት በመታገዝ በአምስት
አመታት ውስጥ ወደ መካከለኛ ባለሀብትነት እንደሚሸጋገር ምንም ጥርጥር የለውም ፡፡
እግዚያብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ!

11

You might also like