You are on page 1of 20

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

የአሽከርካሪ ተሽከርካሪ ፈቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን


የ 2012 የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ

የአሽከርካሪ ዘርፍ
የማጠቃለያ ሪፖርት
የሪፖርት ይዘት
መግቢያ
 የቁልፍ ተግባራት አፈፃፀም
የአበይት ተግባራት አፈፃፀም
 ከእቅድ ውጭ የተከናወኑ ተግባራት
 በዘርፋ ያሉትን ችግሮች ለማስተካል የተሰሩ የለውጥና የአሰራር ማሻሻያ ስራዎች
የኮርና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል የተከናወኑ ተግባራት
 በበጀት ግምቱ የነበረ ጠንካራ ጎኖች፡ ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ መፍትሔዎች
 በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች
 ማጠቃለያ
ባለፈው በጀት አመት አሽከርካሪ ጋር ተያይዞ ተገልጋዩ ህብረተሰብ ያለ

እንግልት መንጃ ፈቃድ መስጠት ላይ ከፍተኛ የነበሩ የመልካም


መግቢያ
አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች በስፋት መቅረፍ የተቻለ
ሲሆን፡፡

 የዚህ ችግር መንስዔዎች መነሻ በመለየት በ2012 የተቋሙን አቅም

በአደረጃጀት፣ በአሰራርና በሰው ሀይል ከማጠናከርና በዘለቂነት እየገነቡ


ከመሄድ ጎን ለጎን የዘርፉን መሰረታዊ ችግሮችና ቁልፍ ጉዳዮች
በመለየት፣ የችግሮቹን መንስኤዎች በጥልቀት በመረዳትና አገልግሎት
አሰጣጡን ደረጃ በደረጃ በማሻሻል በዘርፉ መልካም አስተዳደርን እውን
ለማድረግ ታቅዶ ተግባራዊ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ በዚህ መሰረት የ2012
የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡
የቁልፍ ተግባራት አፈፃፀም

የኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብን በማዳከምና የአገልጋይነት አስተሳሰብ ተግባር እንዲጉለብት


ከማድረግ አኳያ የተሰሩ ሥራዎች

 በዘርፋ የሚታዩ የኪራይ ሰብሳቢነት ምንጮችን በመለየት


የማክሰሚያ እቅድ ተዘጋጅቶ በአሰራር ችግሮችን የሚቀርፋበት
ሁኔታ ተመቻችቷል፡፡
 ሠራተኛው በWአት ወደ ስራ እንዲገባና እንዲወጣ በማድረግ ረገድ
የተሻለ ሥራ ተከናውኗል
 ለሥራ ክፍሉ የተመደቡ ሀብትና ንብረት ለተመደበለት ዓላማ
እንዲውል አግባብ ያለውን ቁጥጥር ከማድረግ በተጨማሪ
በንብረትነት እንዲመዘገብ ተደርጓል፡፡
የቀጠለ ..
 በተገልጋይ በኩል የሚስተዋሉ ያለ አግባብ አገልግሎት ለማግኘት

በተለይ በሀሰተኛና ባልተሟላ ሰነድ የመንጃ ፈቃድ እድሳት


ለማግኘት የሚዳረግን ጥረትና ዝንባሌ የመከላከል ሥራ ተከናውኗል፡፡
ህገ ወጥ ጉዳይ አስፈፃሚዎችን ከፈፃሚው ለሚደረግ ያልተገባ
ግንኙነት ለመከላከል ለ248 የመስክ አሰልጣኞች እና ለ36
የማሰልጠኛ ተቋማት ጉዳይ አስፈፃሚዎች የምክክር መድረክ
በማዘጋጀት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ተከናውኗል
ለአንድ ማሰልጠኛ ተቋም ከመመሪያ ውጭ እየሰራ በመገኘቱ

ስልጠና እንዳያከናውን ለ 4 ወራት የእግድ እርምጃ ተወስኖበታል


የቀጠለ ..
ለ3 ተቋማት የቃል ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል

 ከኤርትራውያን ስደተኞች የመንጃ ፍቃድ ጋር በተያያዘ ስህተቱን

ለፈፀሙ ፈፃሚዎችና የስልጠና ተቋማት ላይ በአሰራሩ መሠረት


የእርምት እርምጃ ተወስዷል
 በቃሊቲ አዲስ ህገ ወጥ ተግባርን ፈጽመው በመገኘታቸው ለ11

ፈፃሚዎች ተጠያቂ እንዲሆኑ ተደርጓል ( ከቃል ማሰጠንቀቂያ እሰከ


እግድ)
ለ14 የማሰልጠኛ ተቋማት አሰልጣኞች በስነምግባር ጉድለት ምክንያት

ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው መሆኑ


በዘርፋ በየደረጃው ለሚገኙ ባለሙያዎች አመራሮች ፈፃሚዎች እና የህዝብ ክንፋ ተልእኮን ለመወጣት እንዲፈጥርለት ከማድረግ አንፃር

 የ2012 በጀት ዓመት ረቂቅ እቅዱ የውስጥና የውጭ የመልካም አስተዳደር


በማዘጋጀት ለረቂቅ እቅዱ ላይ ሁሉም እቅዱ በማዘጋጀት የጋራ በማድረግ
ፈፃሚዎችና 71 የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ በበጀት ዓመቱ የተለያዩ ስራዎች
ተቋማት ጋር በመወያየት ከመድረኩ ተሰተናግደዋል፡፡
ግብአት በመውሰድ እቅድ የመከለስና
የማዳበር ስራ ተከናውኗል፡፡
 አዲስ ስራተኞችን ከነባር ሠራተኞች
ጋር የልምድ ልውውጥ እና የስልጠና
 መሪ እቅዱን መነሻ በማድረግ እስከ ስራ ተከናውኗል፡፡
ፈፃሚ የቢ.ኤስ. ሲ ዕቅድ እንዲወርድና
ፈፃሚውም የግልና የራስ እቅዱ የማቀድ
ሥራ ተከናውኗል፡፡
የመልካም አስተዳደር ለማስፈን የተጠናውን ተግባራት

በማእከል ደረጃ 16 ቅሬታዎች


በማእከል ደረጃ አንድ
ቀርበው 16ቱም የተፈቱ ናቸው
 የተገልጋይ እና የፈፃሚ እርካታን የተገልጋይና አንድ የፈፃሚ
ደረጃ ለማወቅ የአስተያየት የእርካታ ዳሰሣ ጥናት የተጠና
መስጫ ሳጥንና መዝገብ
በማእከልና በሁሉም ቅ/ጽ/ቤት ሲሆን 97.3% የተገልጋይ እና
የተዘጋጀና በነፃ አስተያየታቸውን 22.3 % የፈፃሚ የእርካታ ደረጃ
እንዲሰጡ ተደርጓል፡፡
መሆኑን ያሣያል፡፡
አገልግሎት አሰጣጡ በእስታንዳርዱ መሠረት ስለመሆኑ የሚሰጡ አገልግሎቶች በእለት መመዝገቢያ እየተመዘገቡና ከእስታንዳርዱ ጋር የማነፃፀረ ሥራ የሚከናወን መሆኑ፡፡

5ቱ ከተቀመጠው እስታንዳርድ በላይ


በዚህም መሠረት 11 አገልግሎቶች እስታንዳርዱ
አገልግሎት እየተሰጠ ባቸው የሚገኙ
የወጣላቸው ሲሆኑ 2 እስታንዳርድ ያልወጣላቸው
ሲሆኑ እነሱም  የመንጃ ፈቃድ ልዩነት ጥያቄ
 አጠራጣሪና ውስብስብ የሆኑ የአሽከረካሪ
ፋይሎች ከ10ሩም ቅ/ጽ/ቤት ይጣራልኝ የማጣራት አገልግሎት
ጥያቄን አጣርቶ መልስ መስጠት  የመንጃ ፈቃድ ጠፋብኝ ጥያቄ
 ከባድ አደጋ ያስከተሉ አሽከርካሪዎችን  የመንጃ ፈቃድ በሌላ ሰው ስም ሆነ
መንጃ ፈቃድ ማሣገድ ናቸው ጥያቄ
 ከ11ዱም እስታንዳርድ የወጣላቸው  የስልጣኝ ስም ገቢ ማድረግ እና
ውስጥ 3 ከእስታንዳርድ በታች ፡3  የሰልጣኝ ስም ወጪ ማድረግ
በእስታንዳርዱ መሠረት እና 5 ከእስታንዳርድ በላይ የሆኑበት ምክንያት
አገልግሎቶች ከእስታንዳርዱ በላይ 3ቱ እስታንዳርዱ ሲወጣላቸው ነባራዊ
አገልግሎት ያገኙ ናቸው ሁኔታ ያላገናዘበ የነበረ በመሆኑ አና 2ቱ
በሲስተም በቴክኖሎጂ ይሰራል ተብሎ
በመታቀዱ ነው
የአበይት ተግባር ክንውን
 ተ.ቁ የአገልግ’ሎት ዓይነት እቅድ ክንውን
ክንውን በ%
1 አዲስ መንጃ ፈቃድ መስጠት 80000 53059 66.32

2 መንጃ ፈቃድ ማደስ 137403 129223 94.05

3 ምትክ መስጠት / የጠፋ/ መንጃ ፈቃድ 28918 29635 102.48

4 የኢንተርናሽናል ትክክለኛነት ማረጋገጥ 5175 4023 77.74

5የአሽ/ማ/ፈ/እግድ ማንሳትና ምዝገባ ማከናወን 5225 3841 73.51

6የአሽ/መንጃ ፈቃድ የስም ለውጥ 3084 2955 95.82

7 ፋይል ዝውውር ከአ.አ ወደ ክልል 313 135 43.13


8 ፋይል ዝውውር ከክልል ወደ አዲስ አበባ 446 360 80.72
9የአሸ/መንጃ ፈቃድ እርማት 8803.00 7464.00 84.79
የውጭ እና የመከላከያ መንጃ ፈቃድ ለውጥ
10 7600 4331 56.99
11 የእጩ አሽ/ምዝገባና ቀጠሮ መስጠት 180000 175513 97.51
12 የንድፍ ሀሣብ ቀጠሮ መስጠት 80000 98468 123.09
13 የተግባር ፈተና ስም መስጠት 1000000 76945 7.69
14 የንድፍ ሀሣብ ፈተና መስጠት 80000 89813 112.27
15 የተግባር ፈተና የወሰዱ 100000 61205 61.21
የመንጃ ፈቃድ እድሳት አሳልፈው ለሚመጠ የማጣሪያ የተግባር
16 ፈተና መስጠት 4000 2669 66.73

17 የተሰብሰቢ ገቢ 355697586 77875648 21.89


በማዕከል በአሽ/ዘርፍ የተሰጡ አገልግሎቶች ዝርዝር
ተ.ቁ የታቀዱ ተግባራት ዝርዝር እቅድ ክንዉን አፈጻጸም /ንጽጽር/ በመቶኛ ምርመራ

የመንጃ ፈቃድ የደረጃ ልዩነት ጥያቄን በማጣራት ምላሽ ለመስጠት የታቀደ ሲሆን የመጣ ጥያቄ 12 ክንዉን 11 100 % ወይም 12 ተገልጋይ 11 91.66%

ሲሆን በማጣራት ላይ የሚገኝ ፡፡ አፈጻጸም በፐርሰንት ነዉ

የመንጃ ፈቃድ ፋይል ጠፋብኝ ጥያቄ መፍታት 100 % ወይም 224 ተገልጋይ 153 68.3%

የመንጃ ፈቃድ በሌላ ሰው ስም ሆነ ጥያቄን መለፍታት 100% ወይም 9 ተገልጋይ 9 100%

ለተለያዩ አካላት የአሽከርካሪ መረጃዎች መስጠት 100% 12 12 100%


5. 4 2 50%
የአሽከርካሪ አገልግሎት ድጋፍ እና ክትትል መስጠት
6. አገልግሎት ለመስጠት አጠራጣሪና ዉስብስ የሆኑ የአሽከርካሪ ፋይሎችን ከየቅርንጫፉ በማእከል ተጣርተዉ ዉሳኔ የመጣ ፋይል 48 43 89% ከመደበኛ እቅድ
ዉጪ የተሰራ
እንዲሰጥባቸዉ የሚላኩ ፋይሎችን አጣርቶ ዉሳኔ መስጠት

7. ከባድ የአካል ጉዳትና የሞት አደጋ ያስከተሉ አሽከርካሪዎችን ከአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት የመጡ 156 130 100%

አሽከርካሪዎችን መንጃ ፈቃድ ውስጥ ሲሆን

8 3 1 33.3%
ለአዲስ አሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት የተሰጠ የብቃት ማረጋገጫ ፊቃድ
9 90 90 100%
የአሽ/ ማሰልጠኛ ተቋማት የብቃት ማረጋገጫ ፊቃድ እድሳት አገልግሎት መስጠት፡
10 524 686 131%
የአሽከርካሪ አሰልጣኝ መታወቂያ ማደስ
11 230 147 64%
የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማትን ድጋፍና ክትትል ማድረግ፡
12 50‚000 46800 93.6%
የአሽከርካሪ ማሰልጠኛ ተቋማት አዲስ ሰልጣኞችን ስልጠና እንዲያስጀምሩ ፍቃድ መስጠት ፡

13 52‚000 46778 90%


ስልጠና የጨረሱ እጩ ሰልጣኞች ፈተና እንዲቀጠርላቸው ማረጋገጫ መስጠት
14 900 897 99.7%
የማሰልጠኛ ተሸከርካሪ ቴክኒክ ምርመራ
15 446,200 691,680 155%
ከሚሰጡ አገልግሎቶች የተሰበሰበ አጠቃላይ ገቢ
ከእቅድ ውጭ የተከናወኑ ተግባራት
አገልግሎት ለመስጠት አጠራጣሪና ውስብሰብ የሆኑ የአሸከርካሪ ፋይሎች 48
ፋይሎች ወደ ማዕከል የተላኩ ሲሆን 43 የተጣሩ የከዚህ ውስጥ 32 ተገቢነት
ያላቸው ሆነው በመገኘታቸው አገልግሎት እንዲያገኙ ተደርገዋል 11 ፋይሎች
ደግሞ ተገቢነት የሌላቸው መሆኑ በመረጋገጡ አገልግሎት ማግኘት የማይችሉ
ናቸው ቀሪዎቹ 5 ፋይሎች በመጣራት ሂደት ላይ የሚገኙ ናቸው፡፡
ከባድ የአካል ጉዳትና የሞት አደጋ ያስከተሉ አሽከርካሪዎች ከአዲስ አበባ
ትራፊክ ማነጅመንት የመጡ የ156 አሸከርካሪዎችን የመንጃ ፈቃድ
ይታገድልኝ ጥያቄ ውስጥ የ130 መንጃ ፈቃድ የታገደ ሲሆን 3 በሂደት ላየ
ናቸው የተቀሩት 4 የኦሮሚያ ፣ 2 የፌዲራል ትራንስፖርት ፣ 7 በሌላ ግለሰብ
ስም የሚገኝ 4 የተሳሰተ ቁጥር እና 6 በድጋሚ የተላከ መሆኑን በመግለጽ
ለሚመለከተው አሳውቀናል
የቀጠለ …
 በማእከል በዳይሬክተሩ ቢሮ ፋይሎችን የማደራጀትና ቢሮውን ለሥራ
ምቹ የማድረግ ስራ ተከናውኗል ፡፡
 800 የማሰልጠኛ ተቋማት የማሰልጠኛ ተሸከርካሪዎች በማሰልጠኛ
ስም መሆናቸውንና ለማሰልጠኛ አገልግሎት የተመዘገቡ መሆናቸውን
የማጥራት ስራ ተከናውኗል ፡፡
 የአሽ/ማ/ተቋማት በሙሉ ለ4 የንድፈ ሀሣብ መመዘኛ ቦታዎች ላይ
የመደልደል ሥራ እና የተቋማቶችን ተሸከርካሪዎች ብዛት መሰረት
ለ10ሩም ቅ/ፅ/ቤት ዳታ ኢንኮደሮች የመደልደል ሥራ ተከናውኗል፡፡
የቀጠለ …
የተግባር ፈተና የመፈተን አቅምን ለማሳደግ የሚያስችል የዳሰሳ ጥናት
የማዘግጀት ሥራ ተከናውኗል፡፡

የ 909 የንድፈ-ሀሳብና የተግባር አሰልጣኞች (የሚያሰለጥኑበትን


ካታጎሪ፡የት/ት ዝግጅት፡መንጃ ፈቃድ፡ያላቸው አፕሩቫልና የት/ት ደረጃ
በዝርዝር በመያዝ) በኤክስል እንዲደራጅ ተደርጓል፡፡
በዘርፋ ያሉትን ችግሮች ለማስተካከል የተሰሩ የለውጥና የአሰራር ሥራዎች
አሰራሩን በቴክኖሎጂ በቴክኖሎጂ እንዲዘምን ከማደረግ አኳያ
 የነበረውን የማንዋል የተግባር ፈተና በCCTV ካሜራ በመታገዝ ሙሉ በሙሉ
የመፈተንና የውጤት መጠመር ስራ መሠራቱ
 የተግባር ፈተና ውጤት ቀድሞ በ3 ቀናት ውስጥ በማስታወቂያ በመለጠፍ ይሰጥ
የነበረውን በአዲሱ አሰራር በኪዩስክ ማሽን በ3ዐ ደቂቃ ተገልጋዮ ራሱ ውጤቱን
እንዲያውቀው እየተደረገ መሆኑ፡፡
የቀጠለ …
የአሽከርካሪ አገልግሎት አሰጣጥ ሲሰተም በማዘመን በማእከልና
በቃሊቲ አዲስ ቅ/ጽ/ቤት ይሰጥ የነበረውን አገልግሎቶች በ1ዐ ሩም
ቅ/ጽ/ቤት እንዲሰጥ መደረጉ፤
በእጩ ሰልጣኞች ገቢና ወጪ እንዲመራም የፈተና የቀጠሮ
በማንዋል ይሰጥ የነበረውን በአሁኑ ወቅት በሲስተም በመታገዝ
በማእከል ከሰው ንክኪ ነፃ በሆነ መልኩ ለመስጠት እየተሰራ መሆኑ
የጠፋ ፋይል ማፈላለግን በተመለከተ አገልግሎት ፈላጊ በ11 ዱም
ቅ/ጽ/ቤት ሳይዘዋወር በቴሌግራም ግሩፕ መረጃዎችን በመለዋወጥ
አገልግሎት ለመስጠት እየተሰራ መሆኑ
የአሰራር ማሻሻያ ከማድረግ አኳያ

የቅበላ አቅምን ከማሳደግ አኳያ በንድፍ ሀሣብ ፈተና ከቃሊቲ አዲስ


በተጨማሪ በ3 (ሦስት )ቅ/ጽ/ቤቶች ለመስጠት እየተሰራ ሲሆን በሁለቱ
ዝግጅቱ ተጠናቆ በን/ስ ላፍቶ ዝግጁ ለማድረግ በመስራት ላይ መሆኑ
እንዲሁም የተግባር ተፈና የመፈተን አቅም ለማሳደግ ምድብ 4 ለሥራ ዝግጁ
የተደረጉ መሆኑ፤
 በንድፈ ሀሣብ ፈተና ላይ ያሉትን ግድፈቶች በዝርዘርና በጥናት በመለየት

የማስተካከያ ስራ እንዲሰራ ለፌዲራል ትራንስፖርት የተላከ መሆኑ፤


በአዋጅ 1074/2010 ያልውን ክፍተት ለመሙላት የህዝብ2 የአሰለጣጠን አና

ያፈታተን አሰራር መመሪያ ጥናት ተጠናቆ ለማናጅመንት እንዲቀርብ የተዘጋጀ


መሆኑ
-የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል የተከናወኑ
ተግባራት
የቫይረሱን ስርጭት ለመግታትና ማህበራዊ ርቀትን በመጠበቅ የተከናወኑ ተግባራት
ለፈፃሚዎች የንፅህና መጠበቂያ ፡የአፍና አፍንጫ መሸፈኛጭንብል እንዲደርሰው
መደረጉ
ተገልጋይ የሚበዛባቸውን የአገልግሎት አይነት በመለየት ከዚም ውስጥ የንድፈ-ሀሳብ
ሰልጣኞች በቴክኖሎጂ በመታገዝ ሰልጣኙ በየቤቱ እንዲሰለጥን ተደርጋል፡፡
በተጨማሪም በቃሊቲ አዲስ ቅ/ፅ/ቤት ግቢ ውስጥ የሚሰጡ የንድፈ-ሀሳብና የተግባር
ፈተና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማይጥስ መልኩ በቀን መስጠት የሚቻለውን አገልግሎት
ቁጥር በመወሰን የመከላከል ስራ ተሰርቷል፡፡
በቃሊቲ አዲስ በመግቢያ ቦታ የእጅ መታጠቢያ፡ አልኮልና ሳኒታይዘር በማዘጋጀት
የማሰተናገድ ሥራ ተሰርቷል፡፡
የሙቀት መለኪያ መሳሪያ በመጠቀም ተገልጋዩ ሙቀቱን እየተለካ እንዲገባ ተደርጓል፡፡
በተግባር ማለማመጃ ቦታ ድንገተኛ ቅኝት በማድረግ 5(አምስት) አሰልጣኞች
በተገቢው ሁኔታ ማስክና ሳኒታይዘር ይዘው ባለመገኘታቸው የማሰተካከያ ሥራ
ተሰርቷል፡
በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች

 የቢሮ መጥበብ ችግር እና ለስራው አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶች ከምንሰጠዉ አገልግሎት አኳያ ታይቶ( ፋርጎ
ፕሪነተር ፣ላሚነሽን፣ፕሪንተር ፣ ፎቶ ኮፒ ማሽን እና ሲዲ.ኤም. ኤ) እንዲሟሉ ትኩረት ቢሰጠዉ
በእዉቀት ላይ የተመሰረተ ድጋፍ ለማድረግ የሚያስችል የክህሎትና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ቢመቻች፤
የተሰበሰቡ ሰርኩላሮችና ለአሰራር ግልጸኝነት በጥናት የተለዩ ለስራዉ አፈጻጸም የሚረዳ መመሪያ አስፈላጊ
ስለሆነ ረቂቅ መመሪያዉ እንዲጸድቅ ትኩረት ቢሰጠዉ
ስራዉን በተፈለገዉ ጊዜ ለማከናወን እንዲቻል ተሸከርካሪ በቋሚነት ቢመደብ
ለየባለሙያዎች በጥናት የተፈቀደ የመዘዋወሪያ አበል 1 አመት ሙሉ ሳይከፈላቸው የቀረ በመሆኑ በቀጠይ
ምላሽ ቢሰጥ
የቃሊቲ ኮምፕልክስ ግቢ የማስተዳደሩ ተግባር እልባት እንዲያገኝ ማድረግ
የተግባር መፈተኛ ቦታ የማስፋት ሥራ እና ያለውን የተበላሸ የመጠገን ሥራ ማከናወን
የአሽከርካሪ መለማመጃ ቦታ ዘላቂ መፍትሄ እንዲኖረው ማደረግ
የዕጩ አሽከርካሪ የተግባር ፈተና በተሻለ ሲሲቲቪ ካሜራ እንዲከናወን የተጀመረው ግዢ ተፈፃሚ እንዲሆን
መከታተል፡፡
የዕጩ አሽከርካሪዎች የንድፈ ሀሳብ የፈተና አሰራር ሙሉ በሙሉ በቴክኖሎጂ የተደገፈ እንዲሆን እየተሰራ
ያለውን ሥራ አጠናክሮ ማስቀጠል፡፡
 
ሁ !! !
ሰግና ለ
አመ

You might also like