You are on page 1of 2

የደብረ ማርቆስ ከተማ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ሳምንታዊ ሪፖርት ሀምሌ

05/2014 ዓ.ም
መግቢያ
የኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ የ 2015 ዓ.ም የበጀት ዓመት መነሻ ዕቅድ አዘጋጅቶ ወደ ተግባር
መግባቱ ይታወቃል፡፡የመምሪያችን ስትራቴጂ ምጉልበት በሰፊዉ የሚጠቀም፤ ኤክስፖርትመርየሆነ፤ የልማታዊ
ባለሃብቱን አቅም መጠቀም የሚችል፤ ወደ ላቀ ፈጣን ኢንዱስትሪ ልማት የሚያደርሰን የገበያ
ተወዳዳሪነትን በመገንባት ላይ የተመሰረተ እንዲሁም አንዱ በአንዱ ላይ የሚመሰረት ተመጋጋቢ የሆነ
ኢንዱስትሪን ማልማት እንደመሆኑ መጠን በታቀደው ዕቅድ መሰረት የተግባራትን አፈጻጸም በየጊዜ ሰሌዳው
ከፋፍሎ አፈፃፀማቸውን በጥብቅ ዲሲፕሊን መከታተል አስፈላጊ ነው፡፡ ለውጤታማነቱም በድጋፍና ክትትል
የሚታዩ ከቡድን ቡድን፤ ከባላሙያ ባለሙያ የመፈፀም ልዩነቶች ችግሮችን በመለየት የማስተካከያ
እርምጃዎችን በመውሰድ ቀሪ ተግባራትን ለመፈፀም የሚያስችል እቅዶችን በጊዜ ሰሌዳ ከፋፍለን ወደ
ተግባራዊ ስምሪት ገብተናል፡፡
በዚህ መሰረት ከሳምንት እቅዳችንን መካከል በሳምንቱ ውስጥ የተከናወኑ ተግባራትን አፈፃፀም
የሚያሳይ ሪፖርት ከዚህ እንደ ሚከተለዉ ተዘጋጅቷል፡፡
የመምሪያችንን አመራርና ባለሙያዎች የመፈጸም አቅም ከማሳደግ አኳያ
ከዓበይትተግባራትአፈፃፀምየተከናወኑተግባራት
ፕሮሞሽን

 ከኢንቨስትመንትማስፋፊያስራዎችአንፃር
 አቅምና ክህሎት ያላቸዉን ባለሃብቶችን መለየት 3
 ወደ ኢንቨስትመንት ሊገቡ የሚችሉ አዳዲስ የሃገር ዉስጥ ባለሃብቶችን መለየት 3
 በሳምንቱ ውስጥ 4 በራሪ ወረቀት ተሰራጭቶል
 የተመለመሉ እና ፕሮፋይል የተዘጋጀላቸዉ ባለሃብቶች ብዛት 3

 በአግሮ ፕሮሰሲንግ 1

 በኬሚካል ኮንስትራክሽን 2
 በየተቋማቸው መረጃወችን በማዘጋጀት በድረ ገጽና በማህበራዊ ሚዲያ መልቀቅ 1

 ተከታይ ብዛት 4272

 አስተያየት የሰጡ 5

 ለሌሎች ያጋሩ 10

 እወደዋለሁ ያሉ 70

 በቢሮው የሚለቀቁ መረጃወችን ማጋራት 2


 እወደዋለሁያሉ 18
 የደብረ ብርሃንን የተቀላጠፈ የሁለገብ የኢንዱስትሪ መንደር ውሥጥ ለባለሃብቱ መሬት የማስተላለፍ ሁኔታ

ልምድ በመውሰድ ከተማችን ላይ ለመተግበር ያለመ የመምሪያችን ኃላፊን ጨምሮ ሌሎች የባለድርሻ

ተቋማት ኃላፊዎች የተገኙበት የልምድ ልውውጥ ተካሂዷል፡፡

ከፍቃድና ምዝገባ ስራዎቻችን አንፃር


በሳምንቱ ውስጥ ፍቃድ ያሳደሱ ፕሮጀክቶች ብዛት 3 ሲሆን በዘርፍ ሲታይ
. በኬሚካል - 2
.በቱሪዝም----1

ከኢንዱስትሪ ዞን ልማት ስራዎች አንፃር


ደ/ማርቆስ ከተማ አስተዳደር መብራት ኃይል ዲስትሪክት ድረስ በመሄድ
 ዳት ኢንዱስትሪያል ትሬዲንግ ግራናይት ማምረቻ ፋብሪካ -በግንባታው ውስጥ የተዘረጋው የኤሌክትሪክ ፖል እንዲነሳለት
የማስነሻ ግምት ዋጋ ከፍሎ እያለበተ ለያየ ጊዜ የተለያየ ቀጠሮ በመስጠት ባለሃብቶችን ማጉላላት ተገቢ እንዳልሆነ
በማስረዳት ክሬኑ አዲስ አበባ መሄዱ ነው እንደተመለሰ እንሠራዋለን የሚል ምላሽ ተሰጥቷል ፡፡
 ክልላችን ለሁለገብ ኢንዱስትሪ ፓርክ የመብራት መስመር ማስዘርጊያ የሚውል 4,197,730.64 ብር /አራት
ሚሊዮን አንድ መቶ ዘጠና ሰባት ሺ ሰባት መቶ ሰላሳ ብር ከ 64 ሣንቲም/ መመደቡ ይታወቃል፡፡ በዚህም
መሰረት ወደ ተግባር የተገባ ሲሆን ስራውን ለማከናወን ጨረታ የወጣ ሲሆን በዚህ ምክንያት የጊዜ መጓተት
እንዳይኖር በማሰብ ለፖል ተከላ የሚሆን የቁፋሮ ስራ በመ/ቤቱ (በኢ.ኤ.ኃ.ኮ) ተነሳሽነት ተጀምሯል፡፡
 የአቶ ተስፋየ ዓለማየሁ - ሚስማር ፋብሪካ ማሽኖችን ተክሎ ማምረት ለመጀመር አሁን ላይ እያጋጠመው
ያለውን የመብራት የኃይል እጥረት ለመቅረፍ ከፓርኮች ልማት እና ከባለሃብቱ ጋር እየተወያየን እንገኛለን፡፡
 ሁለገብ የኢንዱስትሪ መንደር ውስጥ 1.2 ኪ.ሜ የጠጠር መንገድና 1.2 ኪ.ሜ የዲች ስራ በዓለም ባንክ ስራ
ለማሰራት የመጨረሻ እቅዱ የፀደቀ ሲሆን ትግበራውም ከሌሎች ከጸደቁ የከተማችን ሌሎች ፕሮጀክቶች ጋር
የሚጀመር ይሆናል፡፡

ከኢንዱስትሪ ልማት ቡድን ስራዎች አንፃር


o የ 4 አምራች ኢንዱስትሪዎች ውስጥ ድረስ በመግባት የስራ ዕንቅስቃሴአቸዉን ማየት ተችሏል፡፡

o የታዩ ኢንዱስትሪዎች፡- ቢያድጌ ከበደ ዳቦ ማምረቻ፣ ግዛቸዉ ሱራፌልና ጓደኞቹ የብሎኬት


ማምረቻ፣ ሃብታሙ አዳነ እንጨትና ብረት እና ሮዳስ የቤትና የቢሮ ዕቃ ማምረቻ በማምረቻ
ሸዳቸዉ ዉስጥ በመግባት የስራ እንቅስቃሴአቸዉን ማየት ተችለሏል፡፡

You might also like