You are on page 1of 1

ቁጥር____________________

ቀን_____________________

ለ ______________________________
ደብረ ማርቆስ፤

ጉዳዩ፡- የገንዘብ ድጋፍ እንዲያደርጉልን ስለመጠየቅ

ከላይ በርዕሱ ለመግለጽ እንደተሞከረው ከተማችን ደብረ ማርቆስ ወደ ሪጅኦ ፖሊታን ከተማነት ማደጓን ተከትሎ
ለተፈፃሚነቱ ጉልህ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ግለሰቦችና ተቋማት የምስጋናና የእውቅና ፕሮግራም የተዘጋጀ ሲሆን ከዚሁ ጎን
ለጎን በከተማችን የተሰሩ የልማት ስራዎችን ለመመረቅና የቀጣዩን በጀት ዓመት በጥሩ ሁኔታና በሙሉ አቅም

ለማስጀመር የሚረዳ ፕሮግራም የክልላችን ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ነሃሴ 22/2014 ዓ.ም በደማቅ ሁኔታ
በከተማችን ደብረ ማርቆስ የሚካሄድ መሆኑ ይታወቃል፡፡

በመሆኑም እርስዎ/ተቋምዎ/ ለከተማችን እድገት ካለዎ ከፍተኛ ፍላጎትና ተነሳሽነት አንፃር ለፕሮጋራሙ መሳካት

አዎንታዊ ሚና እንደሚያረጋግጡ በመተማመን ለዚሁ ዓላማ የሚውል ብር--------------------- የገንዘብ ድጋፍ


እንዲያደርጉልን እየጠየቅን ለሚያደርጉልን የተለመደ ድጋፍዎና እገዛዎ በደብረ ማርቆስ ከተማ ህዝብና አስተዳደር ስም
ከወዲሁ ምስጋና እናቀርባለን፡፡

"ትብብርና ቅንጅት፤ ለከተማችን እድገት"

You might also like