Professional Documents
Culture Documents
Letter To Client No 12 For Advance
Letter To Client No 12 For Advance
የደ/ቁ፡-________________
ጉዳዩ፡-ለኦሮሚያ ባንክ ሆራ ቅርንጫፍ ለቀሪ የኘሮጀክቱ ቅድመ ክፍያ ዋስትና እድሳት የማሳወቂያ /ማስረጃ
ደብዳቤ እንድትፅፉልን ስለመጠየቅ
ድርጅታችን ኢ ቲ ኤ ኢንጂነሪንግ ኃ/የተ./ የግል ማህበር ከአሰሪው የፌደራል ማረሚያ ቤቶች ኮሚሽን ጋር ለማእከላዊ
ማዕድ ቤት የኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራ ለመስራት ውል የተዋዋለ መሆኑ ይታወቃል፡
ለዚህም፣ ተቋራጩ በአሰሪው ቅጥር ግቢ ውስጥ እየሰራ ለሚገኘው ስራ የኘሮጀክቱ ቅድመ ክፍያ ዋስትና
ለማሳደስ አሰሪው መ/ቤት በደብዳቤ እንዲያሳውቃቸው የጠየቁን ስለሆነ፣ በእናንተ በኩል ለኦሮሚያ ባንክ
ሆራ.ቅርንጫፍ ለቀሪ የኘሮጀክቱ ቅድመ ክፍያ ዋስትና እድሳት የማሳወቂያ/ማስረጃ ደብዳቤ እንድትልኩልንና
በተጨማሪም የኘሮጀክቱ ቅድመ ክፍያ ዋስትና መጠን ብር ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ
15,125,619.60 (አስራ አምስት ሚሊዮን አንድ መቶ ሀያ አምስት ሺ ስድስት መቶ አስራ ዘጠኝ ብር ከ
60 ሳንቲም) በአሀዝና በፊደል ተመላክቶ አብሮ እንዲጠቀስልን ስንል፣ መ/ቤታችሁን በታላቅ አክብሮት
እንጠይቃለን።
ከሰላምታ ጋር
ሙሉአለም ሙሉጌታ
ዋና ስራ አስኪያጅ