You are on page 1of 5

ቁጥር፦------------------------

ቀን፦--------------------------
ለሚመለከተው ሁሉ

ጉዳዩ፦ መልካም የስራ አፈፃፀም መስጠትን ይመለከታል

ድርጅታችን ሰንሻይን ፍላንሮፊ ፋውንዴሽን በደ/ብርሃን ከተማ በእቴጌ ጣይቱ ክፍለ ከተማ በሎሬት አፈወርቅ ተክሌ
ቀበሌ ያሰራው ት/ቤት ውስጥ የሚገኝ የግሪነሪ ቦታን ለማልማት ከካሳሁን ዘላለም የአበባቦች ፥ የውበት ዛፎች
መሸጫ እና ማምረቻ ድርጅት ጋር በቀን------------------ውል የተዋዋልን ሲሆን በውላችን መሰረት
የሚያስፈልገውን የሰው ሃይል አሰማርቶ በጥሩ ስነምግባር ወደ 930 የውበት ዛፎች ችግኞችን እና 1050 ካሜ
የሚሸፍን ሳር ተክሎ እስኪፀድቅ ድረስ ተንከባክቦ አስረክቦናል፨

ስለሆነም ከካሳሁን ዘላለም የአበባቦች ፥ የውበት ዛፎች መሸጫ እና ማምረቻ ድርጅት በት/ቤት ውስጥ
የሚገኘውን የግሪነሪ ቦታ በአጥጋቢ ሁኔታ ስላለማልን እና የት/ቤቱን ገፅታ ስለቀየረልን ይህንን የመልካም ስራ
አፈፃፀም የሰጠን መሆኑን እናሳውቃለን፨

“ከሰላምታ ጋር”
ቁጥር፦------------------------

ቀን፦--------------------------

ለሚመለከተው ሁሉ

ጉዳዩ፦ መልካም የስራ አፈፃፀም መስጠትን ይመለከታል

ድርጅታችን ፊቤላ የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ (በላይነህ ክንዴ የመኪና መገጣጠሚያ) በደ/ብርሃን ከተማ ጠባሴ
ክፍለ ከተማ በገነባነው የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ ውስጥ የአረንጓዴ ቦታ እንዲያለማልን ከካሳሁን ዘላለም
የአበባቦች ፥ የውበት ዛፎች መሸጫ እና ማምረቻ ድርጅት ጋር የተስማማን ሲሆን በውላችን መሰረት
የሚያስፈልገውን የሰው ሃይል አሰማርቶ በጥሩ ስነምግባር 4000 በላይ አበቦች፥የውበት ዛፎች እና ሃገር በቀል ዛፎች
ችግኞችን እና ሳር ተክሎ እስኪፀድቅ ድረስ ተንከባክቦ አስረክቦናል፨
ስለሆነም ከካሳሁን ዘላለም የአበባቦች ፥ የውበት ዛፎች መሸጫ እና ማምረቻ ድርጅት በመኪና መገጣጠሚያ
ፋብሪካው ውስጥ የተለያዩ ችግኞችን በአጥጋቢ ሁኔታ በማልማት የፋብሪካ ጊቢውን ማራኪ ስላደረገል እና
ከተማውን ከአየር ብክለት ለመከላከል የበኩላችንን አስተዋፅኦ እንድናበረክት ስለቻልን ይህንን የመልካም ስራ
አፈፃፀም የሰጠን መሆኑን እናሳውቃለን፨

“ከሰላምታ ጋር”
ቁጥር፦------------------------

ቀን፦--------------------------

ለሚመለከተው ሁሉ

ጉዳዩ፦ የምስጋና ምስክር ወረቀት መስጠትን ይመለከታል

የደ/ብ/ሪ/ፖ/ከ/አስ/ወጣት እና ስፖርት መምሪያ የሚያስተባብረው የወሰን ተሻጋሪ በጎ ፈቃደኞች በደ/ብርሃን ከተማ


በ 2014 ዓም ክረምት ላይ በከተማው የተለያዩ ቦታዎች ላይ የተለያዩ ችግኞችን መትከላቸው ይታወቃል፨
ስለሆነም ካሳሁን ዘላለም የአበባቦች ፥ የውበት ዛፎች መሸጫ እና ማምረቻ ድርጅት ከ 100 በላይ ችግኞችን በበጎ
ፈቃደኝነት ስላቀረበልን እና ከተማችንን ውብ እና ፅዱ ለማድረግ ያለን ራእይ ለማሳካት ስለረዳን ይህንን የምስጋና
የምስክር ወረቀት የሰጠን መሆኑን እናሳውቃለን፨

“ከሰላምታ ጋር”
ቁጥር፦------------------------

ቀን፦--------------------------

ለሚመለከተው ሁሉ

ጉዳዩ፦ የምስጋና ምስክር ወረቀት መስጠትን ይመለከታል

የደ/ብ/ሪ/ፖ/ከ/አስ/ፖሊስ መምሪያ በጣይቱ ክፍለ ከተማ ባስገነባው የፖሊስ ጣቢያ ግቢን ገፅታን ለማሳመር
በያዝነው እቅድ መሰረት ግቢው ውስጥ በሚገኙ የአረንጓዴ ልማት ቦታዎች ውስጥ የተለያዩ የውበት አበቦች እና
ዛፎች ችግኞችን ካሳሁን ዘላለም የአበባቦች ፥ የውበት ዛፎች መሸጫ እና ማምረቻ ድርጅት በበጎ ፈቃደኝነት
ለአካባቢው ተስማሚ የሆኑ ችግኞችን በመምረጥ ያለምንም ክፍያ አቅርቦልናል፨
ስለሆነም ከካሳሁን ዘላለም የአበባቦች ፥ የውበት ዛፎች መሸጫ እና ማምረቻ ድርጅት ላደረጉል የችግኝ ድጋፍ እና
የሙያ ትብብር ይህንን የምስጋና የምስክር ወረቀት የሰጠን መሆኑን እናሳውቃለን፨

“ከሰላምታ ጋር”
ቀን፦26/07/15
ለደ/ብ/ሪ/ፖ/ከ/አስ/ባህል እና ቱሪዝም ተጠሪ ፅ/ቤት
ደ/ብርሃን
ጉዳዩ፦የድጋፍ ደብዳቤ እንዲሰጠኝ ስለመጠየቅ
በከተማ አስተዳደር ውስጥ በመንገድ አካፋይ(ሚዲያን) እና በከተማው በተዘጋጁ የአረንጓዴ ልማት ቦታዎች ላይ
የሚተከሉ ችግኞችን በየአመቱ ለከተማ አስተዳደሩ በማቅረብ ከተማው አሁን ያለውን ገፅታ እንዲይዝ ለማድረግ
ከፍተኛ አስተዋፆ ሳደርግ ቆይቻለሁ፨ በተጨማሪም የቱሪስት መዳረሻ ቦታዎችን ለአካባቢው ተስማሚ የሆኑ
ችግኞችን መርጦ በማቅረብ ለቱሪስት መስህብ ምቹ ሁኔታን በመፍጠር ላይ እገኛለሁ፨

ስለሆነም መ/ቤታችሁ ይህንን በመጥቀስ የድጋፍ ደብዳቤ እንዲፅፍልኝ ስል እጠይቃለሁ፨


ከሰላምታ ጋር

ካሳሁን ዘላለም

You might also like