You are on page 1of 2

የህዳር ወር ቼክሊስት

I. የአፈርና ውሃ ጥበቃ ተግባራ


 የቅድመ-ዝግጅት ስራን ማጠናቀቅ
 የሚሰራ የሰው ሃይል ልየታን ማጠናቀቅ
 የልማትና የቅየሳ መሳሪያ ማጠናቀቅ
 በተለዩት ተፋሰስ ልክ አስራ ሁለት አስራሁለት ቀያሽን ለይቶ ማሰልጠን
 የተፋሰስ ልየታን ማጠናቀቅ፡፡ ልየታው የቀበሌ ተፋሰስ ጥመርታው ≥ 2.5 እንዲሆን
አልሞ መስራት
 የተለዩ ነባር ተፋሰሶችን ክለሳና የተፋሰስ ዶኩመንት የማሟላት ስራን ማጠናቀቅ
 የተለዩ አዲስ ተፋሰሶችን ጥናት ማጠናቀቅ
 በየደረጃው ያሉ የተፋሰስ አደረጃጀትን ማለትም የወረዳ፣ የቀበሌና የንኡስ ተፋሰሶችን
አደረጃጀት ማደራጀት
 የተፋሰስ ተቋማት ግንባታን ማለትም ተፋሰሶችን ወደ ህብረት ስራ ማህበር የማሸጋገር
ስራን ለማከናወን ከተፋሰስ ማህበረሰቡ ጋር ውይይትና የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራን
መስራት
 በየቀበሌው ቢያንስ አንድና በወረዳ ቢያንስ 3 ሞዴል ተፋሰሶችን ለይቶ ለመስራት
ያስችል ዘንድ ተፋሰሶችን የመለየትና ማጥናት የመሳሰሉ ተግባራትን ከወዲሁ መስራት
II. የጥምር ደን ተግባራት
 በየስትራቴጂው የችግኝ የተከላ ቦታ ልየታን ማጠናቀቅ
 የተለዩ የተከላ ቦታን የካርታ ስራ ማጠናቀቅ
 የችግኝ ጣቢያ ዝግጅት ማለትም የእርሻ ስራ፣ ክስካሶ፣ ኮምፖስት ግልበጣ ወዘተን ማከናወን
 የመደብ ዝግጅት
 የግብአት አቅርቦት ማለትም የዘር፣ ፖሊቲን ቲዩብ እና የልማት መሳሪያን ማዘጋጀትና
ማቅረብ
 በተለያዩ ስተራቴጅዎች ማለትም በግል፣ በልማት ቡድን፣ በማህበራት ወዘተ ችግኝ
የሚያዘጋጁ አርሶ አደሮችን መለየትና ሙያዊ ድጋ መስጠት
 ለመደበኛ ችግኝ ጣቢያዎች አስፈላጊውን በጀት እንዲበጀት ማድረግ
 የተተከሉ ችግኞች ክብካቤ
 የአረም፣ ኩትኳቶ፣ ጥበቃና አጥር ስራን መስራት
 የጽድቀት መመዘኛ በየዝርያው መሰረት ማዘጋጀት
 የበችግኝ ጣቢያ ፎርማኖችን ስልጠና መስጠት
 በፕሮጀክት የሚደገፉ ች/ጣቢያዎችን በሙሉ አቅማቸው ችግኝ እንዲያዘጋጁ በቂና
ወቅታዊ ድጋፍ መስጠት
 የችግኝ ጣቢያ መጋዘኖችን በንጽህና መያዝ
 የተጎዱና ተከልለው እያገገሙ ያሉ ተፋሰሶችን መንከባከብ
III. ፕሮጀክቶችና ፕሮጋራሞች
III.1 ሴፍቲኔት
 የ 40% ፐብሊክ ዎርክ ስራን ከዘመቻ ስራ በፊት ማጠናቀቅ
 የ BCC ስራ ከጤና ባለሙያዎች ጋር በመተባበር ጎን ለጎን ከ 40% ቱ ጋር ማከናወን
 Operational and maintenance በተመለከተ bylaw, handing over, user group,
watershed association ማደራጀትና ከተፋሰስ ተቋማት ጋር አብሮ እንዲሄድ
ማድረግ

III.2 ካልም ፒ ፎር አር
 የተፋሰስ ህብረት ስራ ተጠቃሚዎች አባላትን ቁጥር ማሳደግ
 በተዘዋዋሪ ፈንድ የተገዙ እንስሳን ያሉበትን ደረጃ መከታተል መረጃ መያዝ
 የካልም ተፋሰስ በሞቢላይዜሽን ወቅት እራሳቸውን ችለው እንደሚንቀሳቀሱ ታሳቢ
በመውሰድ የአደረጃጀት ስራውን ማጠናቀቅ
 የተገነቡ ጽ/ቤቶችን ወደስራ ማስገባት

ቁጥር------------

ቀን---------------

ለሁሉም ቀበሌ ግብርና ጽ/ቤት

ባሉበት

ጉዳዩ፡-የህዳር ወርን ቼክሊስት ስለመላ ይመለከታል

ከላይ በርእሱ ለመግለጽ እንደተሞከረው በበጀት አመቱ ልናከናውናቸው ያቀድናቸውን ተግባራት


በጊዜ፣ በጥራትና በተሻለ መጠን ለመፈጸም ወቅቱን የጠበቀ ቼክሊስት ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ
ይህንን ቼክሊስት ለማዘገጀት ተችሏል፡፡ ስለሆነም ሁሉም ቀበሌ በቼክሊስቱ የተዘረዘሩ ተግባራትንና
ሌሎች ያልተጠቀሱ ተግባራትን በማካተት በጥብቅ ድስፕሊን በመምራት እንዲፈጸም እንድታደርጉ
እናሳስባለን፡፡

ከሰላምታ ጋር!

You might also like