Professional Documents
Culture Documents
NRCM May 2015 Checklist
NRCM May 2015 Checklist
ም ቼክ- ሊስት
1. በአፈርና ውሃ ጥበቃ
በአጠቃላይ በተፋሰሱ መሰራት ካለበት የስነ-አካላዊ አፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ሽፋን ከ 80% በላይ
ያጠናቀቁ፤
የለሙ ተፋሰሶችን ለመሬቱ ባለይዞታዎች ርክክብ በማድረግ 100% ከልቅ ግጦሽ ነጻ ማድረግ
መተዳደሪያ ደንቡን ተግባራዊ ማድረግ፤
ከሚመለከታቸው ጽ/ቤቶች እና የስራ ቡድኖች ጋር በመቀናጀት የለሙ ተፋሰሶችን በተለያዩ የገቢ
ማስገኛ ስራዎች ማለትም በደን ልማት፤በእንስሳት ማድለብ እና ርባታ፤በንብ ማነብ እና በፍራፍሬ
ልማት ወደ ስራ በማስገባት ለተፋሰሱ ተጠቃሚዎች የገቢ ማንጭ እንዲሆኑ ማስቻል፤
2. በደንና አግሮፎረስትሪ
ለተከላ ብቁ ጠንካራ እና ጤነኛ ችግኝ ለማድረስ ለተፈሉ ችግኞች አስፈላጊውን እንክብካቤ አጠናክሮ
ማስቀጠል (ማዛመት፤አረም ማረም፤ማሳሳት….)፤
1
የተፈላ ችግኝ መረጃ በዝርያ ለዞን መላክ፤
በፕላስቲክ ለሚፈላ ችግኝ ትኩረት መስጠት (በወረዳውም ሆነ በቀበሌ መጋዘን አንድ ጥቅል ፖሊቲን
መክረም የለበትም)፤
የአግሮፎረስትሪ ፓኬጆችን ከሪፖርት ባለፈ ሙያዊ የጥራት ደረጃቸውን ተከትሎ በመስራት ረገድ ሰፊ
ክፍተት የሚታይ በመሆኑ ከወዲሁ በየፓኬጁ የተለየውን መሬትና ተጠቃሚ ትክክለኛነት በማረጋገጥ
መሬት ማስነካት (የ GPS ኮርዲኔት፤የተጠቃሚዎች ዝርዝር ፤ስልጠና መስጠት)፤
አሁን ያለውን የዝናብ ሁኔታ በመጠቀም በቀጥታ ዘር እና በሳር ግንጣይ የስነ-አካላዊ ስራዎችን
በእጽዋት ማጠናከር፤
የጥራት ደረጃውን የጠበቀ የችግኝ ጉድጓድ ዝግጅት ከተከላ ወቅት አንድ ወር ቀደም ብሎ ማጠናቀቅ፤
ለአረንጓዴ አሻራ ልማት ወረዳዊ እና የቀበሌ ማስጀመሪያ ቦታ መረጃ በተላከው ፎርማት መሰረት
እስከ ግንቦት 10/2015 ዓ.ም ለዞን መላክ፤
2
የልማታዊ ሴፍቲኔት ቀሪውን 50% የማህበረሰብ ስራዎችን በኖርም እና በጥራት ሁሉንም
የፕሮግራሙን ተጠቃሚዎች በማሳተፍ ማጠናቀቅ፤
እስካሁን ባለን ልምድ ከዞን ካልተጠየቀ በስተቀር በየሳምንቱ በስልክ፤በኢሜል እና በቴሌግራም መረጃ
የመስጠት ልምዱ ደካማ ነው፡፡ በመሆኑም በዚህ ዓመት ከዚህ ችግር በመውጣት በእጃችሁ
የሚገኘውን መረጃ በተላከው የሳምንታዊ ሪፖርት ቅጽ መሰረት በየሳምንቱ ለዞን እንዲደርስ
ማድረግ፤
የሪፖርት ተዓማኒነት ችግርን ለመቅረፍ መረጃ በየተፋሰሱ እንዲያዝ ማድረግ በመስክ ለክቶ
ማረጋገጥ፤
3
በአካባቢ ላይ እና የህ/ሰቡን የኑሮ ሁኔታ በማሻሻል ለውጥ ያመጡ ተፋሰሶችን ምርጥ ተሞክሮ
መቀመር፤