You are on page 1of 2

የምስራቅ ጎጃም ዞን የአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን ቡድን ለወረዳ ኢንስፔክሽን ቡድኖች የተዘጋጀ የህዳር

ወር 2015 ዓ.ምወርሃዊ ቼክሊስት

1. ከዞን ትምህርት መምሪያ በተሰጠው የተከለሰ መነሻ ዕቅድ መሠረት በወሩ በየፕሮግራሙ ኢንስፔክሽን

ሊሰራላቸው ከታቀዱ ተቋማት በዕቅዱ መሠረት መፈጸምና በወቅቱ ለዞንት ምህርት መምሪያ

አጠቃላይ ኢንስፔክሽን ቡድን ማሳወቅ፣ (35%)

2. በሁሉም ፕሮግራሞች የኢንስፔክሽን ሱፐርቪዥን አገልግሎት የሚሰራላቸውን ተቋማት ከወረዳው

ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማገናዘብና በማቀድና በተያዘው ጊዜ በመፈፀም በወቅቱ ለዞን አጠቃላይ

ትምህርት ኢንስፔክሽን ቡድን ገላጭ ሪፖርት ማድረስ፣(20%)

3. በየደረጃው ለሚገኙ ምክር ቤቶች /ትምህርት ቤቶች ለቀበሌ ምክር ቤት ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት

/የስራቡድኑ/ ደግሞ ለወረዳ ምክር ቤቶች በወቅቱ በኢንስፔክሽን ግኝቶች ዙሪያ የተጠቃለለ ሪፖርት

ከማቅረብና በሚታዩ ችግሮች ላይ እንዲመከርባቸውና አቅጣጫ እንዲቀመጥባቸው ማድረግ፣(5%)

4. የትምህርት ተቋማት በኢንስፔክሽን የተለዩ ክፍተቶችን ለሚመለከታቸው የስራ ቡድኖችና


ለትምህርት አመራሩ በማሳወቅ እንዲሟሉና ለመማርማ ስተማር ምቹ መሆናቸውን ክትትል
ማድረግ፣(10%)

5. በስራ ቡድኑ የስራ እንቅስቃሴውን አስመልክቶ የደንበኞችን ርካታ ለመለካትና ማሻሻያ ለማድረግ

የዳሰሳ ጥናት በ 6 ወር ውስጥ 1 የዳሰሳ ጥናት ማድረግ፣(5%)

6. ስልጠና ያልወሰዱና በአዲስ ወደ ስራ ቡድኑ የተቀላቀሉ ባለሙያዎችን በመለየት በወረዳ ደረጃ የስራ

መግቢያ ስልጠና በመስጠት ወደ ስራ ማስገባት፣ መደገፍ መከታተልና አቅማቸውን ማሳደግና ለዞን

ኢንስፔክሽን ቡድን በወቅቱ በስም ዝርዝር ማሳወቅ፣(5%)

7. የይዞታ ማረጋገጫ ካርታና ፕላን የሌላቸው ትምህርት ተቋማት የይዞታ ማረጋገጫ እንዲኖራቸው

ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ርብርብ ማድረግና ተጨባጭ ውጤት እንዲመዘገብ

መስራት፣(10%)
8. በአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን ከ 2006 ዓ.ም ጀምሮ እስካሁኑ ሠዓት ድረስ የኢንስፔክሽን

አገልግሎት ያገኙ ተቋማትን በየፕሮግራሙ በመለየትና በየዓመተ ምህረቱ በማጠቃለል በሶፍት እና

በሃርድኮፒ በተሟላ ሁኔታ አደራጅቶ መያዝ፣(5%)

9. ተሞክሮ መቀመርና ማስፋት የተቀመረውን ተሞክሮ ለዞን ትም/መምሪያ ኢን/ቡድን ማሳወቅ (5%)

You might also like