You are on page 1of 17

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ

የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለሥልጣን

የ2014-2015 የፕሮግራም በጀት የተጠቃለለ የፕሮግራሞች


የበጀት ጥያቄ

መጋቢት 2013 ዓ.ም


አዲስ አበባ

1
1. መግቢያ

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት አገሪቱን ከድህነት ለማውጣት የሚያስችል


ፖሊሲና ስትራቴጂ ነድፎ ለተግባራዊነቱ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ ረገድ መንግስት ፈጣንና ቀጣይነት
ያለዉ ልማት ለማምጣት እንዲችል ካቋቋማቸዉ ተቋማት አንዱ የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ
ባለስልጣን ነዉ፡፡ ባለስልጣኑ በተሰጠዉ ስልጣንና ተግባር መሰረት የአገሪቱ የዱር እንስሳትና የመኖሪያ
አካባቢያቸዉ እንዲጠበቅ፣እንዲለሙና ዘላቂ ጥቅም እንዲሰጡ ለማድረግ በርካታ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ
ላይ ይገኛል፡፡በዚህ መሰረት ላለፉት ዘጠኝ ዓመት ከመንፈቅ የፕሮግራም በጀት አሰራርን በመከተል በዘርፉ
በተደረገው እንቅስቃሴ በርካታ ውጤቶች ተመዝግበዋል፡፡

ተቋሙ ከ 2004 በጀት ዓመት ጀምሮ የሀገሪቱን የመካከለኛ ዘመን እቅድና የተቋሙን የ›ምስት ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ
መሠረት በማድረግ የፕሮግራም በጀት አሰራርን ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ባለስልጣኑ በየዓመቱ የሚመደብለትን ውስን ሃብት
ለ 13 የዱር እንስሳት ጥበቃ ቦታዎች በማከፋፈልና ስራዎችን በማስተባበር እንዲሁም ለክልሎች የተለያዩ ድጋፎችን
በመስጠት ለእቅዱ ስኬት በርካታ ስራዎችን አከናውኗል፡፡

የተቋሙ ፕሮግራም በጀት አደረጃጀት በአምስት ፕሮግራሞች የተደራጀ ሲሆን ለነዚህ ፕሮግራሞች ማስፈጸሚያ
በየዓመቱ ከመንግስት የሚመደበው የመደበኛና ካፒታል በጀት መጠነኛ በሆነ ሁኔታ እየጨመረ የመጣ ቢሆንም ዘርፉ
በመሠረታዊነት ማሟላት ካለበት የመሰረተ-ልማትና ተዛማጅ አገልግሎቶች አኳያ ሲታይ በተለይ በካፒታል በጀት
አመዳደብ ረገድ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ነው፡፡

ባለሥልጣን መ/ቤቱ የአራተኛው ዙር የፕሮግራም በጀት አካል የሆነውን የ 2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያ
ስድስት ወራት ድረስ ያለውን የበጀት አጠቃቀምና የተገኙ ውጤቶችን፤ በአፈጻጸም ሂደት ያጋጠሙ
ችግሮችንና የተወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎችን በመገምገም የቀጣይ ሁለት ዓመታት ፕሮግራም በጀት (2014 -
2015) በአምስት ፕሮግራሞች እና አሥር ውጤቶችን በዝርዝር በማስቀመጥ እንዲሁም የ 2014 በጀት ዓመት
ዓመታዊ ዝርዝር የፕሮግራም በጀት ፍላጎት አዘጋጅቶ አቅርቧል፡፡

2. የ 2013 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የፕሮግራም በጀት አፈጻጸም፤


የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለሥልጣን የ 2013 በጀት ዓመት የስድስት ወራት የፕሮግራም
በጀት አፈጻጸም በአምስት ፕሮግራሞች በማጠቃለል እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

2
አስተዳደርና አመራር
የባለስልጣን መ/ቤቱን ዋና የስራ ሂደት የሚያግዙ የፋይናንስና ንብረት አስተዳደር፣ የኦዲት ፣ የዕቅድ ዝግጅት፣
ክትትልና ግምገማ ፣ የህዝብ ግንኙነት ፣ የወጣቶችና የሴቶችን ተጠቃሚነት የሚያረጋግጡ የተለያዩ የሥርዓተ
ፆታና ወጣቶች ላይ ያተኮሩ ስራዎች ፣ የህግ አገልግሎት ፣የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች፣የስነ ምግባር ክትትል፣የሰው
ሃይል ልማትና የኢንፎርሜሽን ኮሚዩኒኬሽን ሥራዎችን የሚያካትት ሲሆን አጠቃላይ የዱር እንስሳት ልማትና
ጥበቃ ሥራዎችን በተመለከተ መቶ በመቶ የድጋፍ አገልግሎት ለመስጠት በታቀደው መሰረት የተቀናጀ የድጋፍ
አገልግሎት ተሰጥቷል፡፡

የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ


በስድስት ወሩ በ13ቱም የጥበቃ ቦታዎች የባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ መንገድ 24.2 በመቶ የጥበቃና ቁጥጥር ሽፋን
በመስጠት ጥበቃ ቦታዎችን ከህገ-ወጥ ድርጊቶች ነጻ ለማድረግ ታቅዶ የጥበቃ ቦታዎቹ ባላቸው የሰው-ኃይል እና

የአካባቢ ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት 912.13 ሺህ ሰው ሰዓት የጥበቃና ቁጥጥር ስራ ማከናወን ተችሏል፡፡
በዚህም መሰረት በተካሄደው የጥበቃና ቁጥጥር ሥራ 23.15 በመቶ የቁጥጥር ሽፋን ተግባራዊ ማድረግ ተችሏል፡፡ይህም
ከታቀደው ጋር ሲነጻጸር 95 በመቶ ነው፡፡

በጥበቃ ቦታዎችና ከጥበቃ ቦታዎች ውጪ የሚካሄድ ህገ-ወጥ የዱር እንስሳት እና ውጤቶቻቸው ዝውውርን
ለመቀነስ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ህገ-ወጥ የዱር እንስሳትና ውጤቶቻቸው ዝውውር
በሚካሄድባቸው ቦታዎች ላይ 8 የቁጥጥርና ክትትል ስራ ለማካሄድ ታቅዶ በ 8 የተለያዩ አካባቢዎች በኦሮሚያ
ብ/ክልል (ዱከም፣ ቢሾፍቱ፣ ሞጆ፣ መቂ፣ ዝዋይ፣ ሻሸመኔ፣ አዳሚቱሉ፣ አዋሽ መልካሳና ሶደሬ)፣ በደቡብ ክልል
(ሃዋሳ አሞራ ገደል ፓርክ) የክትትልና ቁጥጥር ስራ ማከናወን ተችሏል፡፡ አፈጻጸሙ 53 በመቶ ነው፡፡

የጥበቃ ቦታዎችን(200 ሄ/ር) ከወራሪና ተዛማች ዕጽዋት ነጻ ለማድረግ ታቅዶ በአዋሽ ብሄራዊ ፓርክ በአዋሽ
፣አብጃታ ሻላ እና ነጭሳር ብ/ፓርኮች 160 ሄክታር መሬት የሚሸፍን ወራሪና ተዛማጅ እጽዋት ማስወገድ
ተችልል፡፡ አፈጻጸሙ 80 ፐርሰንት ነው፡፡

በዱር እንስሳት ጥበቃ ቦታዎች 78 ሚሊዮን ቶን (ስንቅሌ የቀርኬዎች መጠለያ እና አልጣሽ ብ/ፓርክ) ውስጥ
የካርቦን ምጠት መጠን ለመለካት ታቅዶ በስንቅሌ የቆርኬዎች መጠለያ ያሉ ደኖች በዓመት ያገለሉትን የካርቦን
መጠን/ክምችት ልኬት በራስ ሃይል የተሰራ ሲሆን በተገኘው ውጤት መሰረት 0.0019 ሚሊዮን ቶን ካርቦን

የመያዝ አቅም እንዳለው ለማወቅ ተችሏል፡፡ አፈጻጸሙ 50% ነው፡፡

የዱር እንስሳት ልማትና አጠቃቀም

3
በግማሽ ዓመቱ መጨረሻ የጥበቃ ቦታዎችን ለ 40,000 የአገር ውስጥና የውጭ አገር ቱሪስቶች ለማስጎብኘት

ታቅዶ 5,563 የውጭ ዜጎች እና ኢትዮጵያውያን ፓርኮችን ጎብኝተዋል፡፡ እንዲሁም ከዱር እንስሳቱና

ከመኖሪያ አካባቢያቸው ጉብኝት፣ ከስፖርታዊ አደንና ከልዩ ልዩ አገልግሎት ክፍያዎች ብር 50 ሚሊዮን ገቢ

ለማሰባሰብ ታቅዶ ብር 9.87 ሚሊዮን ገቢ ተገኝቷል፡፡ አፈጻጸሙም 20 ፐርሰንት ነው፡፡ አፈጻጸሙ ዝቅተኛ

የሆነው የኮቪድ 19 በሽታ በቱሪስት ፍሰቱ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ በማሳደሩ ነው፡፡


ለቱሪስቶች የመመልከቻ ቦታዎችን /view points/ በማመቻቸት የጥበቃ ቦታዎችን 60 በመቶ ለጉብኝት ምቹ
ለማድረግ ታቅዶ በጥበቃ ቦታዎች(አዋሽ፣ ነጭሳር እና አብጃታ ሻላ ብ/ፓርኮች) በሚገኙ የተለያዩ የቱሪስት
መገልገያ እና የቱሪስት አገልግሎት ሰጪ መሰረት-ልማቶችን አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል በማካሄድ የጥበቃ
ቦታዎችን 59 በመቶ ምቹ ለማድረግ ተችሏል፡፡ አፈጻጸሙ ከታቀደው ጋር ሲነጻጸር 98 ፐርሰንት ነው፡፡

የህብረተሰብ አጋርነትና የዱር እንስሳት ትምህርት ፕሮግራም


በበጀት ዓመቱ ስድስት ወራት በጥበቃ ቦታዎች አካባቢ በኢኮቱሪዝም እና ከኢኮቱሪዝም ውጪ በሆኑ የስራ

ዘርፎች የተደራጁ ማህበራትን በማጠናከር እና አዲስ ማህበራትን በማቋቋም ከዘርፉ በሚያገኙት ገቢ 9000

የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ታቅዶ በንብ ማነብ፣በሳር አጨዳ እና ስንደዶ ለቀማ ፣በከብት

ማደለብ፣በፈረስ አከራይነት፣በሃር ትል ምርት ፣ደንብ ማስከበር፣በማገዶ ቆጣቢ ምድጃ ማምረትና

መሸጥ፣በወፍጮ እና ችግኝ ማፍላት የስራ መስኮች የተሰማሩ 50 ማህበራትን(የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ)

ማጠናከር ሲቻል 24 አዲስ ማህበራትን ማቋቋም ተችሏል፡፡ በዚህም 12,720 (4487 ሴቶቸ) የህብረተሰብ

ክፍሎችን ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡ አፈጻጸሙ ከመቶ ፐርሰንት በላይ ነው፡፡

ለህብረተሰቡ እና ባለድርሻ አካላት የጥበቃ ቦታዎችን ማልማትና መጠበቅ ያለውን ፋይዳ በተመለከተ

ለ 85,400 የተለያዩ ባለድርሻ አካላትና እና የህ/ብ ክፍሎች ግንዛቤ ለማስጨበጥ ታቅዶ ለ 68,367(21,865

ሴቶች) የህብረተሰብ ክፍሎች ግንዛቤ እንዲጨብጡ ተደርጓል፡፡አፈጻጸሙ ከታቀደው ጋር ሲነጻጸር 80 ፐርሰንት

ነው፡፡

ጥናትና ምርምር ፕሮግራም

4
በበጀት ዓመቱ አጋማሽ ውስጥ 6 የጥናትና ምርምር ውጤቶችን ለተጠቃሚው ተደራሽ ለማድረግ ታቅዶ 16
የጥናትና ምርምር ውጤቶች ለተጠቃሚው በሚያመች መልኩ በማደራጀት ተደራሽ ማድረግ ተችሏል፡፡
አፈጻጸሙ ከታቀደው ጋር ሲነጻጸር ከመቶ ፐርሰንት በላይ ነው፡፡

የፋይናንስ አፈጻጸም አፈጻጸም፤

በ 2013 በጀት ዓመት ለየኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን በአጠቃላይ
ብር 137,278,500.00 ፕሮግራም በጀት የተደገፈልት ሲሆን ከዚህ ውስጥ ብር 108,057,000.00 ለመደበኛ
እንዲሁም ብር 29,221,500.00 ለካፒታል በጀት የተመደበ ነው፡፡ ከተመደበው አጠቃላይ ወጪ ውስጥ
ለካፒታል ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ የተፈቀደው በጀት 21 በመቶ ብቻ ነው፡፡

በ 2013 በጀት ዓመት ስድስት ወራት ለመደበኛ ስራዎች ማስፈጸሚያ የተመደበውን ብር 80,692,000 በስራ
ላይ ለማዋል ታቅዶ ብር 48,000,000 ስራ ላይ ውሏል፡፡ አፈጻጸሙ 60 ፐርሰንት ነው፡፡
በካፒታል በጀት ረገድ በስድስት ወሩ ለሶስት ዋና ዋና ፕሮጀክቶች የግንባታ ስራ ማስፈጸሚያ(የሬንጀሮች

መኖሪያ ቤቶች፣ የጽ/ቤት የግንባታ እና የጥበቃ ቦታዎች አዲስ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ስራ) ከተመደበው ብር

17,000,000 ውስጥ ብር 2,889,442 በስራ ላይ ውሏል፡፡ ይህም የካፒታል በጀት አፈጻጸሙ 17 ፐርሰንት

መሆኑን ያመለክታል፡፡ ለአፈጻጸሙ ዝቅተኛ መሆን በኮቪድ 19 በሽታ ምክንያት የፕሮጀክቶቹ የቅድመ

ኮንስትራክሽን ስራዎች በመዘግየታቸው ነው፡፡

3. የ 2014-2015 ፕሮግራም በጀት ማጠቃለያ

የ 2013-2017 የአምስት ዓመት ዕቅድ ለመፈጸም የተጠየቀው በጀት የሚያደርገው አስተዋጽኦ በተመለከተ፡-
ለአራተኛው ዙር የፕሮግራም በጀት መርሃ-ግብር(2014-2015) ማስፈጸሚያ የተጠየቀው/ የተሰጠው ጣሪያ
የባለስልጣኑን የመካከለኛ ዘመን ዕቅድ (2013-2017) ተግባራዊ ለማድረግ ከፍተኛ አስታዋጽኦ ያደርጋል፡፡
የአራተኛው ዙር የፕሮግራም በጀት መነሻ ያደረገው የዘርፉን የአምስት ዓመት ዕቅድ (2013-2017) በመሆኑ
በስትራቴጂክ ዕቅዱ ላይ የተመለከቱት ስትራቴጂያዊ ግቦች እና አመላካቾች በፕሮግራም በጀቱ ላይ
ከተቀመጡት ፕሮግራሞችና ውጤቶች ጋር የተሳሰሩ/የተጣጣሙ በመሆኑ የተጠየቀው የፕሮግራም በጀት
የተቋሙን የመካከለኛ ዘመን የልማት ዕቅድ ለመፈጸም ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል፡፡

የመደበኛ እና የካፒታል ወጪ ማጠቃለያ፤የበጀት ጥያቄው ከተሰጠው ጣሪያ ጋር ያለው ንጽጽር፤-

5
ለኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን አምስት ፕሮግራሞችና አሥር ውጤቶች ማስፈጸሚያ
ለሁለት ዓመት(2014-2015) በአጠቃላይ ብር 604,500.03 ሺህ የተጠየቀ ሲሆን ለ 2014 እና ለ 2015 በጀት
ዓመት በቅደም ተከተል ብር 297,266.30 ሺህ እና ብር 307,237.73 የፕሮግራም በጀት ተጠይቋል፡፡ ይህም
በበጀት አይነት ሲታይ ከተጠየቀው ብር 604,500.03 ሺህ ውስጥ ብር 233,784 ሺህ ለመደበኛ ስራዎች
እንዲሁም ብር 370,716.30 ሺህ ለካፒታል ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ እንዲውል የቀረበ ነው፡፡ ለፕሮግራም
በጀት ዘመኑ የተጠየቀው በጀት ከተሰጠው ጣሪያ ጋር ሲነጻጸር በብር 291,407.30 ሺህ ከፍ ብሎ የቀረበ ሲሆን
ይህም የሆነበት መሰረታዊ ምክንያት አስቀድሞ የዲዛይን ሥራው የተጠናቀቀው የተቋሙ ቢሮ የግንባታ ስራ
ከ 2014 በጀት ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ታሳቢ ተደርጎ የካፒታል በጀት ጥያቄ በመቅረቡ ነው፡፡

ባለስልጣኑ በዕቅድ ለያዛቸው የተለያዩ ስራዎች ማስፈጸሚያ ለ 2014 እና ለ 2015 በጀት ዓመት በቅደም
ተከተል የብር የብር 148,626 ሺህ እና የብር 164,466.73 ሺህ የፕሮግራም በጀት ጣሪያ ተሰጥቶታል፡፡ለ 2014
እና ለ 2015 በጀት ዓመት ከተሰጠው የበጀት ጣሪያ በቅደም ተከተል ብር 30,000 ሺህ (20.20 በመቶ) እና
37,041.73 ሺህ(22.52 በመቶ) ለካፒታል በጀት የሚውል ነው፡፡

ለ 2014 በጀት ዓመት ለማሳካት የታቀዱ ዋና ዋና ውጤቶች


የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን ፕሮግራም በጀት በአምስት ፕሮግራሞች የተደራጀ
ሲሆን በ 2014 በጀት ዓመት ለማሳካት እንቅስቃሴ የሚደረግባቸው አሥር ውጤቶች አንደሚከተለው
ተመልክተዋል፤-
 የተሰጠ የድጋፍ አገልግሎት(100%)
 ከህገ ወጥ ድርጊቶች ነጻ የሆኑ የጥበቃ ቦታዎች ሽፋን(27%)
 በጥበቃ ቦታዎችና ከጥበቃ ቦታዎች ውጪ የቀነሰ ህገ-ወጥ የዱር እንስሳት እና ውጤቶቻቸው ንግድ
ዝውውር(42)
 ከመጤና አላስፈላጊ እጽዋት የፀዱ/ያገገሙ የጥበቃ ቦታዎች(1000 ሄ/ር)
 በጥበቃ ቦታዎች የቀነሰ የአየር ንብረት ለውጥ አሉታዊ ተጽዕኖ፤የጥበቃ ቦታዎች የካርቦን ምጠት
(Sequestration) ክምችት (195 ሚሊዬን ቶን)
 ያደገ የቱሪስት ፍሰት(160000)
 በጥበቃ ቦታዎች ውስጥ ለቱሪስቶች የተፈጠረ ምቹ ሁኔታ(61%)
 በዱር እንስሳት የጥበቃ ቦታዎች አካባቢ ተጠቃሚ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች(30000)
 በዱር እንስሳት ልማት፤ ጥበቃና አጠቃቀም ረገድ ያደገ የህ/ሰብ ግንዛቤ (170000)
 በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የተካሄዱና ተደራሽ የተደረጉ የጥናትና ምርምር ውጤቶች(17)

6
በ 2014 በጀት ዓመት የሚከናወኑ ዋና ዋና የካፒታል ፕሮጀክቶች፡-
በአምስት ዓመቱ ስትራቴጂክ ዕቅድ መሰረት(2013-2017) እንዲሁም በሦስት ዓመቱ የፕሮግራም በጀት
መርሃ-ግብር መሰረት በ 2014 በጀት ዓመት ከፍተኛ የሬንጀርሶች መኖሪያ ቤት ችግር ባሉባቸው 3 የጥበቃ
ቦታዎች የሬንጀርሶች መኖሪያ ቤት ለመገንባት፣በጥበቃ ቦታዎች ያለውን ከፍተኛ የጽ/ቤት ችግር ደረጃ በደረጃ
ለማቃለል በበጀት ዓመቱ አንገብጋቢ የጽ/ቤት ችግር ባለባቸው ሁለት ብ/ፓርኮች 2 ጽ/ቤቶችን ለመገንባት
እንዲሁም በሶስት ጥበቃ ቦታዎች 20 ኪ/ሜ አዲስ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ለማሰራት ታቅዷል፡፡ ከዚህም
በተጨማሪ በጀቱ የሚፈቀድ ከሆነ ቀደም ሲል የዲዛይን ሥራው የተጠናቀቀውን እና የግንባታ ቦታ
የተዘጋጀለትን የባለስልጣኑን ቢሮ በካፒታል በጀት የሚገነባ ይሆናል፡፡

በ 2014 በጀት ዓመት ትኩረት የሚደረግባቸው ዋና ዋና ጉዳዮች እና ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችና የመፍትሄ
እርምጃዎች፡-

በ 2014 በጀት ዓመት ትኩረት የሚደረግባቸው ዋና ዋና ጉዳዮች

 ከሚመለከታቸው የመንግሰት አካላት እና ሌሎች ዘርፎች ጋር በመቀናጀት የማህበረሰብ ጥበቃ ቦታዎችን


በማቋቋም፣ በኢኮ ቱሪዝምና ከኢኮ ቱሪዝም ውጪ በሆኑ የስራ መስኮች ህብረተሰቡን
በማሳተፍ፣የክህሎት ስልጠና የመስጠትና መጠነ ሰፊ የስራ እድል በመፍጠር ህብረተሰቡን የማህበራዊ
አገልግሎቶች ተጠቃሚ የማድረግ ስራዎች ትኩረት ተሰጥቷቸው በስፋት ይከናወናሉ፤
 የዱር እንስሳት እና መኖሪያ አካባቢያቸውን ማልማትና መጠበቅ ለህብረተሰቡ እና ለአገር ልማት ያለውን
ፋይዳ አስመልክቶ በየደረጃው ለሚገኙ ባለድርሻ አካላት ግንዛቤ የማስጨበጥ ሥራዎች እንዲሁም
ትምህርቱ ያመጣውን የባህሪ ለውጥ በየጊዜው የመገምገም ስራዎች በትኩረት የሚከናወኑ ይሆናል፤
 የጥበቃ ቦታዎችን በአሰራር፣ በአደረጃጀት፣ በግብዓትና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የማደራጀት፣ ለሬንጀሮች
ስልጠና በመስጠት ክህሎታቸውን የማሳደግ እንዲሁም የተደራጀና አሳታፊ ንቅናቄ በመፍጠር በየደረጃው
ከሚገኘው የህብረተሰብ ክፍል ጋር በመቀናጀት እና የህግ ማሰከበር አቅምን በማሳደግ ውጤታማ የጥበቃና
ቁጥጥር ስራዎችን በትኩረት ማከናወን፤
 የጥበቃ ቦታዎችን በማብቃት፣ በፌደራል፣ በከልል፣ በዞን እና በወረዳ ደረጃ የሚገኙ አግባብ ያላቸውን
ባለድርሻ አካላት በዕውቀት እና በክህሎት በማዘጋጀት እና የመረጃ ግንኙነት ስርዓት በመፍጠር ዘላቂነት
ያለው ተቋማዊ ህገወጥ የዱር እንስሳት እና ውጤቶቻቸው ንግድና ዝውውር ቁጥጥር ማካሄድ፣
 ዘርፉን በዘመናዊ ቴክኖሎጂና አሰራር በማጠናከር የጥበቃ ቦታዎችን መሰረት ያደረገ ችግር ፈቺ የጥናት
ውጤቶችን በማፍለቅ እና የተጠኑ ጥናቶችን ወደ ትግበራ ለማሸጋገር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎችን
የማመቻቸት ሥራዎች በትኩረት ይናወናሉ፤

7
 የጥበቃ ቦታዎች የአደጋ መከላከል ስትራቴጂና አሰራር በመዘርጋት፣ የዩኒቨርሲቲዎችን አቅም በመጠቀምና
ጥናትን መሰረት በማድረግ የመከላከል፣ መልሰው እንዲያገግሙ እና እንዲበለጽጉ በማድረግ የማልማት
ስራዎች ትኩረት ተሰጥቷቸው ይከናወናሉ፤
 አሳታፊ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥናት በማካሄድ፣ የጥበቃ ቦታዎች ዳግም ክለላ የማካሄድ ፣ለጥበቃ
ቦታዎች የህግ ማዕቀፍ በማዘጋጀት በስርዓተ-አያያዝ ዕቅድ እንዲመሩ የማድረግ ተግባራት ትኩረት
ተቸሯቸው ይከናወናሉ፤
 ዘርፉ በህግ ማዕቀፍ ክፍተት ያለበትና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የተደራጀ ባለመሆኑ በቀጣይ ወቅታዊ ውሳኔ
ሰጭነት ሊያረጋግጥ የሚያስቸል የህግ ማዕቀፍ እና ዘርፉን በቴክኖሎጂ እንዲመራ የማድረግ ስራዎች
በትኩረት ተግባራዊ ይደረጋሉ፤
 የግል ባላሀብቱን ተሳትፎ የሚያጎለብቱ አሰራሮችን ተግባራዊ በማድረግ፣ የአለምአቀፍ አጋር አካላትን
ድጋፍ በማፈላለግ እና ተቋማዊ ስልጣን ከተሰጠው የመንግስት ተቋማት ጋር ቅንጅታዊ አሰራር በመፍጠር
የማልማት ስራዎች ትኩረት የሚሰጣቸው ይሆናል፤
 የተቋሙን የሰው ኃይል ፍላጎት በማጥናት እና በስትራቴጂ ማዕቀፍ በመመራት የተቋሙን ሰራተኞች
በዕውቀትና በክህሎት የማሳደግ ስራዎች ትኩረት ተቸሯቸው ተግባራዊ የሚደረጉ ይሆናል፤

ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችና የመፍትሔ እርምጃዎች


ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮች

 በባለስልጣን መ/ቤቱ የተዘጋጁና እና የሚዘጋጁ አዋጆች፣ ደንቦች እና ማስፈፀሚያ መመሪያዎች

በሚመለከተው አካል በወቅቱ ላይፀድቅ ይችላል፡፡

 የጥበቃ ቦታዎች ካለባቸው የመጥፋት አደጋ ለመታደግ በሚደረገው እንቅስቃሴ በየደረጃው ከሚገኙ

የመንግስት መዋቅር እና መንግስታዊ ካልሆኑ ባለድርሻ አካላት የሚጠበቀው ተሳትፎና ድጋፍ

በሚፈለገው ደረጃ እና በወቅቱ ምላሽ ላያገኝ ይችላል፤

 ባለስልጣኑ በጥበቃ ቦታዎች በየጊዜው የሚከሰተውን የእሳት ቃጠሎ በሚፈለገው ፍጥነት ለመቆጣጠር
ተቋማዊ አቅም የሌለው መሆኑ(በክህሎትና በማቴሪያል)፤

 የኮቪድ 19 ወረርሺኝ አሁንም ቢሆን በተለይ በልማትና ጥበቃ ስራው እና በቱሪስት ፍሰቱ ላይ ችግር
እያስከተለ እንዲሁም ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት የሚሰሩ ስራዎችን በከፍተኛ ሁኔታ
ማስተጓጎሉ፤

8
 በአንዳንድ አካባቢ የጸጥታና ሰላም አለመረጋጋት ሁኔታ የሚካሄደውን ክትትልና ድጋፍ በመገደብ

መደበኛ ስራን ሊያስተጓጉል ይችላል፤

 በጥበቃ ቦታዎች የሚታየውን የመሠረተ-ልማት ችግር ደረጃ በደረጃ ለመቅረፍ የሚመደበው ውስን

የካፒታል በጀት እያደር ከሚጨምረው የግንባታ ዋጋ አንጻር ብቃት ያለው የሥራ ተቋራጭ ላይገኝ

ይችላል፤

 የዘርፉ የሥራ ባህሪ ከፊል ወታደራዊ /Para Military/ እንደመሆኑ እና ካለው የስራ እንቅስቃሴ ስፋት
አንጻር የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃና ቁጥጥር ስራውን በሚፈለገው አግባብ ለማከናወን ከፍተኛ የሆነ
የመስክ ተሸከርካሪ ችግር ያለበት መሆኑ፣

የመፍትሔ እርምጃዎች

 የተዘጋጁና የሚዘጋጁ የባለስልጣን መ/ቤቱን አዋጆችና ደንቦች በሚመለከተው አካል ወቅታዊ ውሳኔ

እንዲያገኙ የዘርፉን የበላይ አመራር እና ቁልፍ ባለድርሻ አካላት አቅም መጠቀም፣ ያልተቆራረጠ

ክትትል ማድረግ፤

 የባለድርሻ አካላትን ግንዛቤ በማስፋት፣ በንቅናቄ መድረኮች ሥምምነት ላይ የተደረሰባቸውን የጋራ

ውሳኔዎች ወደ ተግባር በማሸጋገር፣ የሚያስፈልጉ አደረጃጀቶችና አሰራሮችን በመተግበር እንዲሁም

የተጠናከረ ክትትላዊ ድጋፍ በማድረግ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ እና ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል

ማድረግ፣

 በጥበቃ ቦታዎች በየጊዜው የሚነሳውን እሳት ቃጠሎ ለመቆጣጠር ቁልፍ ከሆኑ ባለድርሻ እና አጋር
አካላት ጋር በመተባበር ተቋማዊ አቅም መፍጠር እንዲሁም የአካባቢ ባለድርሻ
አካላትን(የዞን፣የወረዳ፣የቀበሌ፣መከላከያ ሰራዊት፣ፌደራል ፖሊስ፣የሃገር ሽማግሌዎች) በማስተባበር
ቃጠሎውን ለማጥፋጥ ጥረት ይደረጋለል፤

 በጥበቃ ቦታዎች ለሚገኙ ሬንጀርሶችና ሠራተኞች እንዲሁም በአካባቢው ለሚኖሩ ማህበረሰቦች


አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የግንዛቤ ትምህርት መስጠትና በሽታውን ለመከላከል የሚረዱ
ግብዓቶችን በማቅረብ ችግሩን ለመከላከል ጥረት ማድረግ፤

 የፌደራል እና የክልል ከፍተኛ የፖለቲካ አመራሮች መድረክ በማመቻቸት ዳግም ክለላ ለማካሄድ

የሚያስፈልጉ ውሳኔዎች እና የትግበራ አመራር እንዲዘጋጅ ማድረግ፤ በዞንና በወረዳ ደረጃ አመራር

እንዲሰጥበት በማድረግ ተመሳሳይ መድረኮችን በወረዳ ደረጃ በማመቻቸት አፈፃፀሙን መገምገም እና

መከታተል፣

9
 የሚመደበውን ውስን የካፒታል በጀት በጣም አንገብጋቢ ለሆኑ የመሰረተ-ልማት ፕሮጀክቶች በማዋል

እንዲሁም ከመንግስት የፋይናንስ ተቋማት ጋር በመመካከር ተግባራዊ ማድረግ፣

 ጥበቃ ቦታዎች ያሉባቸውን የተሽከርካሪና ሌሎች የሎጂስቲክ ችግሮችን ለመፍታት ለሚመለከተው

የመንግስት ባለድርሻ አካል ችግሩን በማቅረብ መፍትሄ እንዲሰጥበት ጥረት ይደረጋል፤ በተጨማሪም

የአጋር አካላትን ድጋፍና ትብብር በመጠየቅ ችግሩን ለመፍታት ጥረት ማድረግ የሚሉት ለሚያጋጥሙ

ችግሮች የተቀመጡ የመፍትሄ ሃሳቦች ናቸው፡፡

4. የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለሥልጣን ተልዕኮ እና ራዕይ

ተልዕኮ

የኢትዮጵያ የዱር እንስሳትንና መኖሪያ አካባቢያቸውን የህብረተሰብና የባለድርሻ አካላትን ንቁ ተሳትፎ

በማረጋገጥ፣ አገራዊና ዓለም አቀፍ ህጎችና ስምምነቶች በማስከበር፣በሳይንሳዊ መንገድ በማልማትና

10
በመጠበቅ፣ ለሀገራችን ህዝብ ብሎም ለዓለም ህብረተሰብ ዘላቂ ስነ-ምህዳራዊ፤ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ

ጥቅም እንዲሰጡ ማድረግና ለመጭው ትውልድ በቅርስነት ማስተላለፍ ነው፡፡

ራዕይ

በ 2022 የዱር እንስሳትና መኖሪያ አካባቢያቸው እሴቶች ለአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማትና ለስነምህዳር ጥበቃ
የሚኖራቸውን አስተዋጽኦ በማላቅ የማህበረሰቡ የባለቤትነት ስሜት አድጎ ማየት፤

ዕሴቶች

 ሙያዊ ጽናት

 ፈጠራ

 አሳታፊነትና አጋርነት

 አረንጓዴነት

 ግልጽነትና ተጠያቂነት

 ቅንነት

 ብዝኃነትን ማክበር

5. የፕሮግራም በጀቱ ከመካከለኛ ዘመን የዘርፍ ዕቅድ (2013-2015) ጋር ያለው ትስስር፣

የኢትዮጵያ የዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለስልጣን የሁለተኛውን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ
አዘጋጅቶ ላለፉት አምስት ዓመታት(2008-2012) አሁን ደግሞ የሃገሪቱን የ 1 ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ
መሰረት በማድረግ የአምስት ዓመት የልማት ስትራቴጂክ ዕቅድ (2013-2017) አዘጋጅቶ ተግባራዊ
በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ በአፈጻጸም ሂደቱም በርካታ ውጤቶች ተመዝግበዋል፡፡ አገሪቱ ከምትከተለው
አረንጓዴ ልማት ስትራቴጂ ጋር በተያያዘ የአየር ንብረት ለውጥን የሚቋቋም አረንጓዲ ኢኮኖሚ ከመገንባት
አኳያ ጥበቃ ቦታዎች ያላቸው ደርሻ ከፍተኛ ነው፡፡ዘርፉ የሚመራበት የአምስት ዓመት ዕቅድ ተዘጋቶ ወደ
በስራ ተገብቷል፡፡ በዘርፍ ደረጃ የአምስት ዓመት ዕቅዱን ለማሳካት ከተቀመጡት ስትራቴጂያዊ ግቦች
መካከል በዱር እንስሳትና መኖሪያ አካባቢያቸው የሚፈጸሙ ህገወጥ ዲርጊቶችን መቀነስ፤ህገ ወጥ የዱር

11
እንስሳትና ውጤቶቻቸው ዝውውር ቁጥጥር ውጤታማነት ማሳደግ፤ጉዳት የደረሰባቸውን የዱር
እንስሳትና መኖሪያ አካባቢያቸውን መልሶ ማበልጸግ፤የአየር ንብረት ለውጥ አሉታዊ ተጽዕኖዎችን
መቀነስ፤ኢኮ ቱሪዝምን፣ የዱር እንስሳትና ውጤቶቻቸውን እና የቱሪዝም ገበያን ማስፋፋት፤በዱር
እንስሳት ልማት፣ጥበቃና አጠቃቀም የህብረተሰብን ተጠቃሚነት ማሳደግ፤የዱር እንስሳት ዘርፍ
የህብረተሰብ ግንባቤ እና ትምህርት ተደራሽነት ሽፋን ማሳደግ፤የዱር እንስሳት ዘርፍ ጥናትና ምርምር
ማስፋፋት እና በዱር እንስሳት ዘርፍ የመሠረተ ልማት አውታሮች ግንባታን ማስፋፋት የሚሉት ዋና
ዋናዎቹ ናቸው፡፡ በተመሳሳይ መልኩ በሦስት ዓመቱ የፕሮግራም በጀት ዘመን(2013-2015) የተደራጁት
ፕሮግራሞች፣ውጤቶችና የውጤት አመላካቾች በመካከለኛ ዘመን ዕቅዱ ከተቀመጡ ስትራቴጂያዊ ግቦች
ጋር በሚገባ የተሳሰሩ በመሆኑ በፕሮግራም በጀቱ አፈጻጸም የተገኙ ውጤቶች በቀጥታም ይሁን
በተዘዋዋሪ መንገድ ለአምስት ዓመቱ ዕቅድ ስኬት ከፍተኛ ድርሻና አስተዋጽኦ አላቸው፡፡ በመሆኑም
የፕሮግራም በጀቱ በአምስት ዓመቱ ከታቀዱ የዱር እንስሳት ልማት፣ ጥበቃና አጠቃቀም ስራዎች ጋር
የተሳሰሩ በመሆኑ ዕቅዱን በላቀ ደረጃ ለመተግበር ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው፡፡

12
ሠንጠረዥ 1

6. የ 2014-2015 የፕሮግራም በጀት ማቅረቢያ

ስትራቴጂክ SMART ዓላማዎች፤ፕሮግራሞች፤ውጤቶች፤የውጤት አመላካቾች እና ግቦች ማጠቃለያ

ዓላማዎች ፕሮግራሞች ውጤቶች አመላካቾች የ 2014


ግቦች
ዓላማ 1፡ የተሰጠ የድጋፍ አገልግሎት የተሰጠ የድጋፍ አገልግሎት በመቶኛ 100
ፕሮግራም 1፡ አስተዳደርና አመራር
የተቋሙን ተልዕኮ ለማሳካት
የሚያስችሉ የድጋፍ አገልግሎቶችን 100
በመቶ በመስጠት የተቋሙ ተልዕኮ በላቀ
ደረጃ እንዲሳካ ለማድረግ ነው፡፡
ዓላማ 2 ፡ ፕሮግራም 2፡ የዱር እንስሳት ልማትና በጥበቃ ቦታዎች የተገነባ በጥበቃ ቦታዎች የተገነባ መሰረተ
ጥበቃ ቦታዎች አካባቢ በሚኖሩ እና ጥበቃ፤ ልማት በመቶኛ
መሰረተ ልማት 3
ከሌላ አካባቢ በሚመጡ የህብረተሰብ  የተገነባ የስካውት መኖሪያ ቤት
ክፍሎች በብ/ፓርኮችና መጠለያዎች ላይ በቁጥር
ከሚደርስ የተለያየ ህገወጥ ጫና የፀዱ
2
የጥበቃ ቦታዎች ክልል በ 2012 በጀት  በጥበቃ ቦታዎች የተገነባ
ዓመት ካለበት 65 በመቶ በ 2015 ወደ 80 ጽ/ቤት በቁጥር
በመቶ ለማሳደግ ነው፡፡ 20
 አዲስ የተገነባ መንገድ
በኪ/ሜ
በጥበቃ እና ከጥበቃ ቦታዎች ውጭ የሚካሄዱ ከህገ ወጥ ድርጊቶች ነጻ የሆኑ
ያደገ የጥበቃና ቁጥጥር ሽፋን 27
ህገወጥ ተግባራትን በመቆጣጠር የህግ የበላይነትን የጥበቃ ቦታዎች
በመቶኛ
ማስከበር ፤እንዲሁም ለዱር እንስሳት መኖሪያነት
ምቹ እንዲሆኑ የባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ
ማበልጸግና ማልማት

13
ዓላማዎች ፕሮግራሞች ውጤቶች አመላካቾች የ 2014
ግቦች
በጥበቃ ቦታዎችና ከጥበቃ በሀገሪቱ ህገ-ወጥ የዱር እንስሳት 42
ቦታዎች ውጪ የቀነሰ ህገ- በሚካሄድባቸው ቦታዎች ላይ
ወጥ የዱር እንስሳት እና የተካሄደ የቁጥጥርና ክትትል ስራ
ውጤቶቻቸው ንግድ በቁጥር
ዝውውር
ያገገሙ የጥበቃ ቦታዎች ከመጤና አላስፈላጊ እፅዋት የፀዱ 2/1000
ስፋት የጥበቃ ቦታዎች በቁጥር/ሄክታር
የጥበቃ ቦታዎች የካርቦን ምጠት 195
በጥበቃ ቦታዎች የቀነሰ የአየር
(Sequestration) ክምችት (ሚሊዬን
ንብረት ለውጥ አሉታዊ
ቶን)
ተጽህኖ
ዓላማ 3 ፡ ፕሮግራም 3 ፡የዱር እንስሳት አጠቃቀም የጎብኚዎች ቁጥር በሺህ 160.00
ያደገ የቱሪሰት ፍሰት
የሃገሩቱን የዱር እንስሳት ሃበት፣መኖሪያ የዱር እንስሳት እና መኖሪያ አካባቢያቸዉን
አካባቢያቸውንና መልከአ ምድር ለሀገር ሳይንሳዊና በዘላቂነት የአጠቃቀም ዓይነቶችን
ውስጥና ለውጭ ቱሪስቶች በማልማትና ለደንበኞች በማስተዋወቅ በአለም
በማስተዋወቅ የቱሪስት ፍሰቱን በ 2012 አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና ጥራት ያለው አገልግሎትና
ምርት በማቅረብ ከዘርፉ አገሪቱ ማግኘት ያለባትን
በጀት ዓመት ካለበት 350,000 በ 2015
ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት በላቀ ደረጃ ለማጎልበት
በጀት ዓመት ወደ 480,000 ማሳደግ ነው፡፡

ያደገ የቱሪዝም አገልግሎት በመቶኛ 62


በጥበቃ ቦታዎች ውስጥ
ለቱሪስቶች የተፈጠረ ምቹ
ሁኔታ
ዓላማ 4 ፡ ፕሮግራም 4፤ የህብረተሰብ አጋርነትና በዱር እንስሳት የጥበቃ ቦታዎች ተጠቃሚ የሆኑ ማህበራትና የህ/ሰብ 20000
በጥበቃ ቦታዎች አካባቢ የሚኖሩ ዱር እንስሳት ትምህርት አካባቢ ተቋቁመው ተጠቃሚ ክፍሎች በቁጥር
የህብረተሰብ ክፍሎች የዱር እንስሳትን የሆኑ ማህበራት/የህብረተሰብ
ማልማትና መጠበቅ ያለው በጥበቃ ቦታዎች አካባቢ ለሚኖሩ ክፍሎች
ኢኮኖሚያዊ፣ማህበራዊና ባህላዊ ፋይዳ የህብረተሰብ ክፍሎች ስርዓተ ጾታን

14
ዓላማዎች ፕሮግራሞች ውጤቶች አመላካቾች የ 2014
ግቦች
ላይ ግንዛቤ በማሳደግና በተለያዩ የሙያ ባገናዘበ መልኩ አማራጭ የገቢ ምንጮችን
ዘርፍ በማደራጀት የተሳታፊ አባላትን በመፍጠር ተሳታፊነታቸዉን በማሳደግ
ቁጥር በ 2012 በጀት ዓመት ካለበት ለሴክተሩ የሚያበረክቱት አጋርነት ቀጣይና
120,000 በ 2015 በጀት ዓመት ወደ ዘላቂ እንዲሆን የሚያደርግ ሲሆን
300,000(30 በመቶ ሴቶች) ማሳደግ በተጨማሪም ለሁሉም የህብረተሰብ
ክፍሎች ፤የዉሳኔ ሰጪ አካላት፤
የመስተዳድር አካላትና ሌሎች ቁልፍ የሆኑ
መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ
ባለድርሻ አካላት በዱር እንስሳቱ ጥበቃ፤
ልማትና አጠቃቀም ዙርያ የግንዛቤ
ማስጨበጫ ትምህርት መስጠት
እንዲሁም በሰውና በዱር እንሰሳት መካከል
የሚከሰቱ ግጭቶችን ለመቀነስ
የሚያስችል መፍትሄ በማቅረብ ሴክተሩ
ተልኮዉን እንዲያሳካ የሚሰራ ነዉ፡፡
በዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ በዱር እንስሳት ልማት፣ጥበቃና 170,000
ያደገ የህብረተሰብ ግንዘቤ አጠቃቀም ዙሪያ ግንዛቤ ያገኙ
የህብረተሰብ ክፍሎች በቁጥር
ዓላማ 5፡ ፕሮግራም 5፤ ጥናትና ምርምር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ለተጠቃሚው ተደራሽ የተደረጉ 17
በዱር እንስሳትና መኖሪያ አካባቢያቸው የተካሄዱና ተደራሽ የተደረጉ የጥናትና ምርምር ውጤቶች
የዱር እንስሳትና መኖሪያ አካባቢያቸው ጥናትና
ላይ የተለያዩ ጥናቶችና ምርምሮችን የጥናትና ምርምር ውጤቶች በቁጥር
በማካሄድ ለዱር እንስሳት ልማት፣ ምርምር / ለዱር እንስሳት ልማት፣ ጥበቃና
ጥበቃና አጠቃቀም አጋዥ የሆኑ አጠቃቀም አጋዥ የሆነ ጥናትና ምርምር በማካሄድ
የጥናትና ምርምር ግኝቶችን በ 2012 የጥበቃና ቁጥጥር ስራዎችን በሳይንሳዊ መንገድ
በጀት ዓመት ካለበት በቁጥር 147 በማካሄድ ውጤታማነቱን ማሳደግ
የጥናቶችና ግኝቶችን በ 2015 በጀት

15
ዓላማዎች ፕሮግራሞች ውጤቶች አመላካቾች የ 2014
ግቦች
ዓመት በቁጥር ወደ 171 ማሳደግ

ሠንጠረዥ 2

የ 2014- 2015 የፕሮግራም በጀት ጥያቄ በፕሮግራም ደረጃ (ማጠቃለያ) በሚሊዮን ብር


የ 2014-2015 የመካከለኛ ዘመን ወጪ የገንዘቡ ምንጭ
ፕሮግራም/የወጪ አይነት ከመንግስት ግምጃ ከመ/ቤቱ ከውጭ
2014 2015 ድምር ቤት ገቢ ዕርዳታ ብድር ድምር
ጠቅላላ የፕሮግራም ድምር 148,626,000 164,466,730 313,092,730 313,092,730 313,092,730
118,626,000 127,425,000 246,051,000 246,051,000 246,051,000
የመደበኛ ወጪ
30,000,000 37,041,730 67,041,730 67,041,730 67,041,730
የካፒታል ወጪ
የፕሮግራም 1፡ አስተዳደርና 31,237,893.04 32,557,743.04 63,795,636.08 63,795,636.08 63,795,636.08
አመራር

16
31,237,893.04 32,557,743.04 63,795,636.08 63,795,636.08 63,795,636.08
የመደበኛ ወጪ
የፕሮግራም 2፡ የዱር እንስሳት 79,014,160.09 120,455,390.09 229,469,550.18 229,469,550.18 229,469,550.18
ልማትና ጥበቃ
የመደበኛ ወጪ 79,014,160.09 83,413,660.09 162,427,820.18 162,427,820.18 162,427,820.18

የካፒታል ወጪ 30,000,000 37,041,730 67,041,730 67,041,730 67,041,730

የፕሮግራም 3፡ የዱር እንስሳት 2,136,613.77 3,016,513.77 5,153,127.54 5,153,127.54 5,153,127.54


አጠቃቀም
2,136,613.77 3,016,513.77 5,153,127.54 5,153,127.54 5,153,127.54
የመደበኛ ወጪ
የፕሮግራም 4፡ የህብረተሰብ 3,045,529.80 3,925,429.80 6,970,959.60 6,970,959.60 6,970,959.60
አጋርነትና የዱር እንስሳት
ትምህርት
3,045,529.80 3,925,429.80 6,970,959.60 6,970,959.60 6,970,959.60
የመደበኛ ወጪ
የፕሮግራም 5፡ጥናትና ምርምር 3,188,803.30 4,508,653.3 7,697,456.60 7,697,456.60 7,697,456.60

የመደበኛ ወጪ 3,188,803.30 4,508,653.3 7,697,456.60 7,697,456.60 7,697,456.60

17

You might also like