Professional Documents
Culture Documents
Legal Frame Work2010
Legal Frame Work2010
•
1. በፋይናንስ አስተዳደር አዋጅ 128/2002
የተመለከቱ
• አንቀጽ 5፡- ኃላፊነትና ተጠያቂነት
እያንዳንዱ የመንግስት መስሪያ ቤት የበላይ ኃላፊ፤
የዚህ አዋጅና በአዋጁ መሠረት የወጡትን ደንቦችና ድንጋጌዎች
በኃላፊነት በሚመራዉ መስሪያ ቤት ዉስጥ ሙሉ በሙሉና
በተገቢዉ መንገድ ተግባራዊ መሆናቸዉን የማረጋገጥ
ኃላፊነት አለበት ይላል፡፡
ስለ መንግሥት ፋይናንስ አስተዳደር የህግ ማዕቀፍ
የቀጠለ….
• አንቀጽ 7፡- የመንግስት መስሪያ ቤቶች የበላይ ኃላፊዎች
ኃላፊነት
1. የመንግስት መስሪያ ቤቶች የበላይ ኃላፊዎች በኃላፊነታቸዉ ሥር
የሚገኘዉ የመንግስት ሀብት ለተገቢ እና አግባብ ባለዉ የመንግስት
አካል ለጸደቀ ዓላማ ብቻ መዋሉን እንዲሁም አጠቃቀሙ ቁጠባን፣
ብቃትን እና ዉጤታማነትን በከፍተኛ ደረጃ ሊያስገኝ በሚችል
መንገድ መፈጸሙን የማረጋገጥ ኃላፊነት አለባቸወ፡፡
. በፋይናንስ አስተዳደር አዋጅ 128/2002 የበላይ ኃላፊዎችየቀጠለ…
1. ቢሮዉ የዘረጋዉ የፋይናንስ አስተዳደር ሳይጣስ በየመስሪያ ቤቱ
የፋይናንስ አስተዳደር ሥርዓት መዘርጋትንና በትክክል የሚሠራ
መሆኑን የማረጋገጥ፣
2 . በመ/ቤቱ በተዘረጋዉ በዉስጥ ቁጥጥር ሥርዓት እያንዳንዱ
ሰራተኛ ኃላፊነቱን ላይቶ ማከናወን የሚያስችል አስፈላጊ የሥራ
ክፍፍል የተደረገበት መሆኑን ያረጋግጣል፣
የኃላፊዎች ኃላፊነቶች የቀጠለ…
3. ወቅታዊና አግባብ ያለዉ አስተማማኝ የፋይናንስ መረጃና ትንታኔ
መዘጋጀቱንና መሠራጨቱን ማረጋገጥ፣
4. የመስሪያ ቤቱ የሂሳብ ሪፖርት በጊዜ ሰሌዳዉ መሠረት ለፋይናንስና
ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ/ ቢሮ መላኩን የማረጋገጥ፣
5. የመ/ቤቱ ሠራተኞች የፋይናንስ አስተዳደር አዋጁን፣ አዋጁን መሠረት
በማድረግ የሚወጣዉን ደንብና መመሪያዎች እንዲሁም የተዘረጋዉን
የአሰራር ሥርዓት በመከተል ተግባራቸዉን ማከናወናቸዉን፣ የዉስጥ
ኦዲት ጊዜዉን ጠብቆ መፈፀሙን ያረጋግጣሉ፣
በፋይናንስ አስተዳደር አዋጅ 128/2002 ...
6. በቢሮዉ በሚወጣዉ መመሪያ መሠረት መ/ቤቶች ዓመታዊ
በጀታቸዉን አዘጋጅቶ ማቅረባቸዉን ያረጋግጣሉ፣
7. የመ/ቤቱን/የወረዳዉን/የዞን የሥራ ፕሮግራም በመገምገም የጥሬ
ገንዘብ ፍላጎትና ፍሰት ዕቅድ ያቀርባሉ፣
8. በዉስጥ ኦዲት ሪፖርት በተመለከተዉ መሠረት በኦዲት ግኝቶች
ላይ አስፈላጊ እርምጃ መዉሰድ፣
አዋጁን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያግዙ በቢሮዉ የወጡ ዝርዝር
ተግባራትን የያዙ መመሪያዎች በሥራ ላይ የዋሉ አሉ፡
32