Professional Documents
Culture Documents
Plan Power Point
Plan Power Point
– መግቢያ
• በ2016 በጀት ዓመት ይሰራሉ ተብሎ የተያዙ ዋና ዋና ግቦች ተቋማዊ ማስፈጸም አቅም፣ ሃብት አጠቃቀም እና አገልግሎት አሰጣጥ አሰራር
ማጎልበት፣ የቤት ልማት አስተዳደር ማሳደግ ፣ለተጠቃሚዎች የማስተላለፍ እና የቤቶች የመረጃ አያያዝ ስረዓትን ማሻሻል ሲሆኑ በመኖሪያ
ቤት ህብረት ስራ ማህበራት ቢሮው በ2005 ዓ.ም የ20/80 እና የ40/60 ከተማ አስተዳደሩ ባወረደው 30/70 ፕሮግራም መሰረት 26
አባዎራዎች የጋራ መኖርያ ቤት ህብረት ስራ እንዲደራጁ መረጃ አደራጅተን ለክ/ከተማ ልከናል፡፡ በዚህ በጀት ዓመትም ቢሮው
የሚያስቀምጠው አቅጣጫ መሰረት መረጃ የማደራጀት ስራ ይሰራል፡፡ የመንግስት ቤቶች መረጃ 1135 በማደራጀት እና ወደ በለፀገው ሶፍት
ዌር የማስገባ ስራ ተከናውኑዋል፡፡ ስለሆነም ወደ በለጸገው ሶፍት ዌር የገባውን መረጃ በ2016 የማረም እና የማስተካከል ስራ ይሰራል፡፡
• የመንግስት መኖሪያ ቤቶችን፣ንግድ ቤቶችን እንዲሁም የጋራ መኖሪያ ቤቶችን መረጃ በNUHDM SYSTE Mሙሉ በሙሉ የማስገባት ሥራ
• ከመንግስት መኖሪያ ቤቶች እና /ንግድ ቤቶች 4 ሚሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ለመሰብሰብ ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል፡፡
• የመንግስት ቤቶች በህገወጥ እንዳይያዙ መቆጣጠር እና የተያዙትን ቤቶች በማስለቀቅ ህጋዊ በሆነ መንገድ ለሚገባቸው ዜጎች የማስተላለፍ
ሥራ ይሰራል፡፡ እንዲሁም ለልማት ተነሽና የተፈጥሮ አደጋ ተነሽዎች የጋራ መኖሪያ ምትክ ቤት በምርጫቸው መሰረት እንዲስተናገዱ
• 1.2.1.1. ራዕይ
• በ2017 ዓ.ም የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች አቅም ያገናዘበና ለኑሮ ምቹ የሆነ የመኖሪያ ቤት ተጠቃሚ ሆነው ማየት፡፡
• 1.2.1.2. ተልዕኮ
• በአዲስ አበባ ከተማ ያለዉን ከፍተኛ የሆነ የመኖሪያ ቤት ፍላጎት ለማሟላት ጥራት ያለውና ወጪ ቆጣቢ ቤት በማስገንባት፣በፍትሐዊነት እንዲተላለፍ በማድረግ፤ ቀልጣፋና
ውጤታማ የቤት አስተዳደር ስርዓት በመዘርጋትና በመተግበር የከተማዋ ነዋሪዎች ተጠቃሚነትን ማሳደግ፡፡
• 1.2.1.3. የጽ/ቤቱ ተግባርና ኃላፊነት
• 1. የጽ/ቤቱን እቅድ ያቅዳል ፣ ይተገብራል ፣ ይገመግማል ፣ በበላይነት ይመራል
• 2. ከቢሮ የሚወርዱ ፖሊሲዎች፣ ዝርዝር የህግ ማዕቀፎች እንዲሁም ስታንዳርድ በወረዳ ተፈጻሚ መሆናቸውን ያረጋግጣል፤ የማሻሻያ ግብዓቶች ያሰባስባል፤
ለሚመለከተው አካል ያስተላልፋል፤ ተግባራዊነቱንም ይቆጣጠራል፤
• 3. የሚያስተዳድራቸውን ቤቶች መረጃ በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ይይዛል፤ የመኖሪያ ቤት ዓይነቶችን መደብና ደረጃ ያወጣል፤ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ይሰጣል፤
• 4. የጋራ መኖሪያ ቤት ማህበራት የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎችን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር ችግሮቹ እንዲወገዱ ያደርጋል፤
• 5. በወጪ እና ጊዜ ቆጣቢ ለሚገነቡ ግንባታዎች የሚያስፈልገውን ሰፋፊ የመንግስት ቤቶች ይዞታ ይለያል ቁጥጥር ያደርጋል፡፡
• 6. በአነስተኛና መካከለኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ነዋሪዎች በተለይም ሴቶች፣ አካል ጉዳተኞች በቤት ልማት ፍትሐዊ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ይሰራል፡፡
• 7. የመንግስት ቤቶች አላግባብ ወደ ግል እንዳይዞሩ ከፍተኛ ጥበቃ ያደርጋል፣
• የሚያስተዳድራቸውን ቤቶች ያከራያል፤ እንዲጠገን ያደርጋል፣
• በጋራ መኖሪያ ቤቶች ህብረተሰቡን የሚያውኩ እና ህገ-ወጥ ተግባራትን የሚፈፅሙ አካላትን ከሚመለከተው አካል ጋር በመሆን ቁጥጥር
ያደርጋል፤ እርምጃ እንዲወሰድ ያደርጋል፤
• የከተማ አስተዳሩ ንብረት የሆኑ የመኖሪያ፣ ንግድ ቤቶች፣ ለኪራይ አገልግሎት ተገነቡ ቤቶች እንዲሁም የጋራ መኖሪያ ቤቶች በህገ-ወጥ
መንገድ ከያዙት አካላት ያስለቅቃል፡፡
– የተቋሙ እሴቶች
•
ጥራት ያለው የቤት አቅርቦት፣
• ወጭ ቆጣቢነት፣
• ለአካባቢ ጥበቃና ለሥራ ላይ ደህንነት ትኩረት መስጠት፣
• ተገልጋይ ተኮርና አክብሮት፣
• ፍትሀዊነት፣
• ግልፅነት፣
• ተጠያቂነት
• ከዚህ በታች የቀረበው የድርጊት መርሐ-ግብር ካላይ በሀተታ የቀረቡትን ግቦች፣ አላማዎች እና ዝርዝር ተግባራት በ2016 ዓ.ም በምን
ያክል መጠን፣ ክብደት እና ጊዜ እንደሚከናወኑ በሚያሳይ ደረጃ የ2016 በጀት አመት እቅድን ማዘጋጀት ተችሏል፡፡
• በድርጊት መርሃ ግብሩ 2 ግቦች፣12 ዓላማዎችና 49 ተግባራት በዝርዝር የተካተቱበት ሲሆን ይህንንም በየወራቱ እና በየሩብ አመት
•
•
•
•
•
•
•
•
•
•
•
•
•
•
• ክፍል 4
• የዓመቱን ዕቅድ ለማሰካት የሚተገበሩ ማስፈጸሚያዎች
• በ2016 በጀት አመት ለመፈፀም የታቀዱ የየዘርፉ የልማት ግቦችን ውጤታማ በሆነ ደረጃ ለማሳካት እና የተቀመጡ አላማዎች
ጋር ለመድረስ ይቻል ዘንድ ከዚህ በታች የተዘረዘሩት አብይ ጉዳዮችን የማስፈጸሚያሥልችናሂደቶችንመከወን አስፈላጊ ነው።
– የተቋማዊየለውጥ (Transformation)አጀንዲዎች
• የተዘጋጀውን እቅድ ወደ ተግባር ለመቀየር የተለያዩ የለውጥ ሥራዎችን ማከናወን የሚያስፈልግ ሲሆን እነዚህን የለውጥ
ሥራዎች በአግባቡ በመተግበር ከእቅዱ የሚፈለጉ ውጤቶችን እና ለውጦችን እውን ለማድረግ ይረዳል፡፡ ተቋማዊ ለውጥ
ለማምጣት የሚተገበሩ የተለያዩ አጀንዳዎችና ለውጦች ያሉ ሲሆን ከተቋማችን አሰራርና ተግባር አንጻር ዋና ዋናዎቹ፡-
• የመልካም አስተዳደርን የሚያሰፍኑ እንዲሁም የአገልግሎት አሰጣጡን የሚያዘምኑ ስርዓቶችን መዘርጋት፣
• ጊዜን፣ ሀብትን እና የሰው ኃይል ጉልበትን የሚቆጥቡ አዳዲስ የግንባታ ቴክኖሎጂዎችን መተግበር፣
– የፖሊሲ ሪፎርም አጀንዳዎች
• አዲዲስፖሊሲዎች
• ተቋማችን ባለው የረጅም ጊዜ ልምድ በመነሳት የቤት ልማትን አስመልክቶ የሚዘጋጁ ፖሊሲዎች እንዲዳብሩ የሚያስችሉ
ግብዓቶችን በማቅረብ እና በመሳተፍ ድጋፍ ያደርጋል፡፡
• ነባርፖሊሲ
• ከቤት ልማቱ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ፖሊሲዎችን በመለየት ከከተማችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማጣጣም እንዲተገበሩ
እንዲሁም የምንመራባቸው ደንቦች፣ መመሪያዎች እና አሰራሮች ፖሊሲዎቹን የተመሠረቱ እንዲሆን ይደረጋል፡፡
•
•
•
– የኢኮቴና ዲጅታላ ይዜሽን አጀንዳዎች
• የተቋማችን የቤት መረጃዎች በዘመናዊ የመረጃ ቋት (DATA BASE) ለማስተዳደር የሚያስችል
ማዕከላዊ መረጃ ማደራጃ (DATA CENTER) ፡፡
• የውስጥ ሥራዎችን የተመለከቱ የመረጃ ልውውጥ በቴክኖሎጂ /በኔትወርክ/ በማገናኘት ከእጅ ንክኪ ነፃ
የሆነ የአሠራር ሥርዓት መዘርጋት የሚያስችል መሠረተ ልማት ይገነባል፡፡
• የዘመናዊ ቴክኖሎጂ ግብአቶችን እና ሀብቶችን በአግባቡ ማስተዳደር እና የመጠገን ስራዎችን በመስራት
የአገልግሎት አሰጣጥ እንዳይቆራረጥ የማድረግ ሥራ ተደራሽ እንዲሆን ይደረጋል፡፡
•
– የአፈጻጸምክትትልናግምገማሥርዓት
• የክትትል፣ ድጋፍና ግምገማ ስርዓት፡-
• የጽ/ቤቱ አጠቃላይ ሥራዎች በተያዘው ዕቅድ መሠረት እንዲተገበሩ የበላይ አመራሩ በጀነራል ካውንስል
በየ15 ቀን እየገመገመ የማስተካከያ እና የማበረታቻ ድጋፍ ያደርጋል፤ ውሳኔ ይወስናል፡፡
• የጽ/ቤቱ ሰራተኞች የቤት አስተዳደር ስርዓቱን ክትትልና ድጋፍ ያደርጋሉ፣
• የለውጥና መልካም አስተዳደር ሰራዎች የአቻ ፎረም ውጤታማነት፣ የለውጥ ሥራ አተገባበር እና
አገልግሎት አሰጣጥ አፈጻጸምን እየገመገመ የማስተካከያ እርምጃዎች እንዲወሰዱ ድጋፍ እና ክትትል
ያደርጋል፣
• የዕቅድ ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ቡድኑ የዕቅድ አፈጻጸምን እየገመገመ የማስተካከያ እርምጃዎች
እንዲወሰዱ ድጋፍ ክትትል ያደርጋል፣
– የግምገማና ሪፖርት ስርዓት
• በጽ/ቤቱ ስር ያሉ ቡድኖች ተጠሪ የወረዳ ቤቶች አስተዳደር ጽ/ቤቶች ወርሃዊ፣ የሩብ አመት፣ የግማሽ አመት
እና አመታዊ የተገመገመ የጽሁፍ ሪፖርት በማዘጋጀት ጽ/ቤቱ ኃላፊዎች በወቅቱ ያቀርባሉ፡፡
• በሚቀርቡ ሪፖርቶች እና የተግባር ክንውንን መሠረት በማድረግ በተቋሙ የበላይ አመራር፣ በሚመለከታቸው
ቡድን እና በክፍለ ከተማ አስተዳደሩ ስልጣን በሰጣቸው ተቋማትየዕቅድ አፈጻፀም በየሩብ
አመቱእንዲገመገም ይደረጋል፡፡
ማጠቃለያ
• የመጠለያ ችግር ያለባቸውን የህብረተሰብ ክፍሎች የቤት ባለቤት የማድረግ ጉዳይ ትልቁ ፈተናችን እንደሆነ
እንገነዘባለን፡፡ ስለሆነም ጊዜና ወጪ ቆጣቢ ቤቶች ከተማው ጋር በመተባባር እና በመስራት ፍትሀዊ የቤት
ማስተላለፍ ስራ መስራት ያስፈልጋል፡፡
• በወረዳ አቅም የሚሰሩ ስራዎችን በትኩረት መስራት ይገባናል፡፡ በህገ ወጥ የተያዙ ቤቶችን በማስለቀቅ በከፋ
ችግር ውስጥ ላሉ ወገኖች 8 የተገመገሙ መረጃቸውችን እንዲተላለፉ ተደርጉዋል፡
• ይህን ተግባራዊ ለማድረግ የብልሹ አሰራር አመለካከትና ተግባር በመድፈቅ፣ የሰራዊት ግንባታና የለዉጥ
ስራዎችን ትኩረት በመስጠት፣ መልካም አስተዳደር በማስፈን፣ የአግልግሎት አሰጣጥ ሂደትን በማሻሻል፣
ክፍተት የሚታይባቸውን ፈፃሚዎች፣ ቡድን መሪዎችና ወረዳዎች በመደገፍ፣ በአፈፃፀማቸዉ የተሻሉትን
በማበረታት፣ የተሻለ አሰራርና ተሞክሮዎችን በማስፋት፣ ለህዝብ ክንፍ በቂ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ ዕቅዱ
ዉጤታማ ማድረግ ይጠበቅብናል ስለሆነም ሁሉንም አካላት ርብርብ እንዲያደርግ ጥብቅ ክትትል
ይደረጋል፡፡
•