You are on page 1of 21

የኢትዮጵያ ፌዳራሊዊ ዱሞክራሲያዊ

ሪፐብሉክ

ሇሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበ የ2016 በጀት ዓመት የበጀት

መግሇጫ

አህመዴ ሺዳ

የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር

ሰኔ 1/2015 ዓ.ም.

Budget Speech
የ2016 በጀት መግሇጫ (Budget Speech)

የተከበሩ አፈ ጉባኤ
የተከበራችሁ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባሊት

የሚኒስትሮች ም/ቤት ግንቦት 29 ቀን 2015 ዓ.ም. ባካሄዯው መዯበኛ ስብሰባው የ2016


በጀት ዓመት የፌዳራሌ መንግስት አጠቃሊይ በጀት 801.65 ቢሉዮን ብር እንዱሆን
በመዯገፍ በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት እንዱጸዴቅ መቅረቡ ይታወሳሌ፡፡ ዛሬ በዚህ ም/ቤት
የተገኘሁትም በየዓመቱ እንዯሚዯረገው ይህ የቀረበው የ2016 በጀት ዓመት የፌዳራሌ
መንግስት ረቂቅ በጀት የተመሠረተበትን ኢኮኖሚያዊ ታሳቢዎችና በጀቱ ትኩረት
ያዯረገባቸውን ፕሮግራሞች በሚመሇከት ሇተከበረው ም/ቤት ዝርዝር መግሇጫ
ሇማቅረብ ነው፡፡ ይህ የማቀርበው መግሇጫም ተዯግፎ ስሇቀረበው በጀት በፌዳራሌ
መንግስት የፋይናንስ አስተዲዯር አዋጅ ቁጥር 648/2001 አንቀጽ 22 ንዐስ አንቀጽ
1(ሇ) መሠረት የተዘጋጀ ማብራሪያ ነው፡፡

የተከበሩ አፈ ጉባኤ
የተከበራችሁ የም/ቤት አባሊት

መንግስት ባሇፉት ዓመታት በሀገር በቀሌ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም በዋና ዋና


አጠቃሊይ ኢኮኖሚ (የማክሮ ኢኮኖሚ)፣ መዋቅራዊና እና በዘርፍ የታቀደ ማሻሻያዎችን
በትጋት ተግባራዊ በማዴረግ ትሌሌቅ ሇውጦች እንዱመዘገቡ ከፍተኛ ጥረት ሲያዯርግ
መቆየቱ የሚታወቅ ነው፡፡ እንዯ ሀገር የገጠሙንን መጠነ ሰፊ ችግሮች በጽናት እና
በስሌት በመቋቋም እነዚህን የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች (ሪፎርሞች) ተግባራዊ በማዴረግ
ፈጣን የኢኮኖሚ ዕዴገቱን ቀጣይነት ማረጋገጥ ከመቻለም በሊይ ኢኮኖሚው ተጽእኖችን
የመቋቋም አቅም (resilience) እንዱገነባ አስችሎሌ፡፡ በዚህም መሠረት ባሇፉት
ዓመታት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የ6.1 በመቶ አማካይ ዕዴገት አስመዝግቧሌ፡፡ ይህም
ዕዴገት የመነጨው በግብርና፣ በኢንደስትሪና በአገሌግልት ዘርፎች በተመዘገበው መጠነ
ሰፊ ዕዴገት ነው፡፡ ይህ የተመዘገበው የኢኮኖሚ ዕዴገትም የዜጎች የነፍስ ወከፍ ገቢ
በ2011 በጀት ዓመት ከነበረበት 983 የአሜሪካን ድሊር በ2014 ወዯ 1218 የአሜሪካን
ድሊር ከፍ እንዱሌ አዴርጓሌ፡፡ ሆኖም የኢኮኖሚ ዕዴገቱን በ10 ዓመቱ የሌማት ዕቅዴ
በተቀመጠው የ10 መቶ ዕዴገት ግብ መጠን ማሳዯግ አሁንም ከፍተኛ ጥረትን
1
የ2016 በጀት መግሇጫ (Budget Speech)

የሚጠይቅ ሲሆን፣ ባሇፉት ዓመታት የተከሰቱት ተዯራራቢ ቀውሶች (shocks) ይህ


ግብ እንዲይሳካ ዋና ምክንያት ሆነዋሌ፡፡

የሀገር በቀሌ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ትግበራው እንዱሁም የኤክስፖርት አፈጻጸማችን


ከዓመታት ማሽቆሌቆሌ በኋሊ ዕዴገት እንዱያሳይ ማዴረጉ ላሊው ስኬት ነው፡፡ የውጭ
ቀጥታ ኢንቨስትመንትና በውጭ ሀገር የሚኖሩ ዜጎች ወዯ ሀገር የሚሌኩት ገንዘብ
(remittance) ገቢም እንዱሁ በኮቪዴ ወረርሽኝ ተጽእኖ ከነበረበት ዝቅተኛ አፈጻጸም
በማንሰራራት ዕዴገት አሳይቷሌ፡፡ በመሆኑም የመርቻንዲይዝ (የሸቀጦች) ኤክስፖርት
ገቢ የ15 በመቶ አማካይ ዕዴገት በማስመዝገብ ሇመጀመሪያ ጊዜ በ2014 በጀት ዓመት
4.1 ቢሉዮን ድሊር ገቢ ሇመሰብሰብ ተችሎሌ፡፡ እንዱሁም በ2014 በጀት ዓመት 7.5
ቢሉዮን የአሜሪካን ድሊር ገቢ በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወዯ ሀገር የሊኩ
ሲሆን፣ የውጭ ሀገር ቀጥታ ኢንቨስትመንት ዯግሞ በሶስቱ የሪፎርም ዓመታት የ3.1
በመቶ አማካይ ዕዴገት አስመዝግቧሌ፡፡ ይህ አፈጻጸም መሌካም የሚባሌና በአስቸጋሪ
ወቅት የተመዘገበ ቢሆንም፣ የንግዴ ሚዛን ጉዴሇታችንን በራሳችን አቅም ሇመሸፈን
አሁንም የኤክስፖርትን አፈጻጸም ከዚህ በሊቀ ዯረጃ ሊይ ማዴረስ የግዴ አስፈሊጊ ነው፡፡

የመንግስት ሌማት ዴርጅቶችን ሇማሻሻሌ ተግባራዊ የተዯረጉ የሪፎርም ሥራዎች


የዴርጅቶቹ የሥራ አፈጻጸም እንዱሻሻሌ ከመርዲቱም በሊይ ተወዲዲሪ እንዱሆኑና
ተጨማሪ ሀብት እንዱፈጥሩ የሚያስችሌ መሠረት ተጥሎሌ፡፡ በተዯረጉት ሪፎርሞች
የአብዛኛው የመንግስት ሌማት ዴርጅቶች ገቢና ትርፍ መጠን ያዯገ ሲሆን የኮርፖሬት
አመራራቸውም እየተሻሻሇ ይገኛሌ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ተግባራዊ የተዯረጉ የማሻሻያ
ሥራዎችን ሇመግሇጽ ያህሌ፣ በቴላኮም ዘርፍ የነበረውን የመንግስት ሞኖፖሉ
በማንሳት ሇግሌ ዘርፍ ተሳትፎ ክፍት በማዴረግ (telecom sector liberalization)
በዘርፉ ተወዲዲሪነት እንዱኖር ማዴረግ ተችሎሌ፡፡ በዚህም መሠረት ከኢትዮ ቴላኮም
በተጨማሪ ሇአንዴ ዓሇም ዓቀፍ የቴላኮም ካምፓኒ ፈቃዴ በመስጠት ሥራ እንዱጀምር
የተዯረገ ሲሆን፣ ሀገሪቱም ከዚህ ፈቃዴ ክፍያ በውጭ ምንዛሬ 1 ቢሉዮን የአሜሪካን
ድሊር ገቢ እንዴታገኝ ማዴረግ ተችሎሌ፡፡ እንዱሁም፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት
2
የ2016 በጀት መግሇጫ (Budget Speech)

ሆሌዱንግ ተቋቁሞ ሥራ የጀመረ ሲሆን፣ ይህም የመንግስት ሌማት ዴርጅቶች


ተጨማሪ ሀብት እንዱፈጥሩ እና የጋራ ኢንስትመንት ሇማስፋፋት የሚያስችሌ
ይሆናሌ፡፡ በተጨማሪም፣ ከፍተኛ የዕዲ ጫና ያሇባቸውን የመንግስት የሌማት ዴርጅቶች
ዕዲ የሚረከብና የሚያስተዲዴር የዕዲና ሀብት አስተዲዯር ኮርፖሬሽን የተቋቋመ ሲሆን፣
ይህም የመንግስት የሌማት ዴርጅቶቹ የፋይናንስ ጤንነትን በማሻሻሌ ወዯ ትርፋማነት
እንዱሸጋገሩ የሚረዲ ከፍተኛ እርምጃ ነው፡፡ እንዱሁም የመንግስት ሌማት ዴርጅቶችን
ተወዲዲሪነት እና ውጤታማነት ሇማረጋገጥ ዴርጅቶቹ የሚመሩበት ህግ በጥናት ሊይ
በመመሥረት በርካታ ማሻሻያዎች ተዯርገውበት ረቂቅ ህጉ በም/ቤቱ እንዱጸዴቅ
ቀርቧሌ፡፡ በአጠቃሊይ የመንግስት ሌማት ዴርጅቶችን የኦፕሬሽንና የአመራር
(governance) አቅምን የሚያሻሽለ በርካታ የሪፎርም እርምጃዎች ተግባራዊ
በመዯረጋቸው የዴርጅቶቹ አፈጻጸምና ተወዲዲሪነትን ማሻሻሌ ተችሎሌ፡፡

በላሊ በኩሌ ቀሌጣፋና ውጠታማ የመንግስት ፋይናንስ አስተዲዯር ሥርዓትን በመቅረጽ


ተግባራዊ ማዴረግ የተቻሇ ሲሆን፣ የመንግሥት ፋይናንስ አስተዲዯርና ቁጥጥር
ሥርዓቱን ውጤታማ ሇማዴረግ የሚያስችለ በርካታ ተግባራት በመከናወን ሊይ
ናቸው፡፡ ከነዚህም መካካሌ የመንግሥት ግዢና ንብረት አስተዲዯር አዋጅ ማሻሻያ
ተዘጋጅቶ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እንዱጸዴቅ ቀርቧሌ፡፡ እንዱሁም የአዋጁ
ማስፈፀሚያ ረቂቅ መመሪያዎች ተዘጋጅተው ሥራ ሊይ ሇማዋሌ ቅዴመ ዝግጅት
እየተዯረገ ይገኛሌ፡፡ የመንግስት ግዥ ስርዓትን በማዘመን ቀሌጣፋ፣ ግሌፅና ውጤታማ
ግዥዎችን ሇማከናወን የሚያስችሌ በቴክኖልጂ የተዯገፈ ስርዓት ሇምቶ የተጠናቀቀ
ሲሆን፣ በዚህም መሰረት የኤላክትሮኒክ የመንግሥት ግዢ ሥርዓት (Electronic
Government Procurement) በ73 የፌዯራሌ መ/ቤቶች ሊይ ተግበራዊ ተዯርጓሌ፡፡
በቀሩት መ/ቤቶችም ትግበራው በቀጣዩ በጀት ዓመት ተጠናክሮ የሚቀጥሌ ይሆናሌ፡፡
በተጨማሪም የኢትዮጵያ ሂሣብ ባሇሙያዎች ማሠሌጠኛ ኢንስቲትዩት ማቋቋሚያ
ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቶ ሇሚኒስትሮች ም/ቤት ቀርቧሌ፡፡ እንዱሁም ዓሇም አቀፍ
የፐብሉክ ሴክተር የሂሳብ አያያዝ ዯረጃዎች (IPSAS) ትግበራን በበሊይነት የሚመራ

3
የ2016 በጀት መግሇጫ (Budget Speech)

የሚኒስትሮች ስትሪንግ ኮሚቴ ተቋቁሞ ቀጣይ ስራዎችን ሇማከናወን ዝግጅት


እየተዯረገ ይገኛሌ፡፡ በላሊ በኩሌ ዜጎች ስሇሀገራዊ በጀት ዝግጅት ሂዯትና መረጃ
አውቀውና ተረዴተው በበጀት ትግበራ ሂዯት ሊይ በባሇቤትነት እንዱሳተፉና
እንዱቆጣጠሩ ሇማዴረግ በህግ አውጭው አካሌ ሇ2015 በጀት ዓመት የፀዯቀውን በጀት
ሇሁለም ዜጎች በቀሊሌና ሉገባ በሚችሌ መሌኩ አዘጋጅቶ ሇማሠረጨት በታቀዯው
መሠረት የዜጎች የበጀት መረጃ ሠነዴ (Citizens Budget) ተዘጋጅቶ መረጃው
ተሰራጭቷሌ፡፡ እንዱሁም የኢትዮጵያ የበጀት ስርዓት ግሌፅነት ዯረጃን ሇመሇካት
የሚያስችሌ 2ኛ ዙር የዲሰሳ ጥናት በዓሇም አቀፍ የበጀት አጋርነት ዴርጅት ተካሄድ
ውጤቱ እየተጠበቀ ይገኛሌ፡፡ ይህም ያሇብንን ክፍተት በመሇየት ማሻሻያዎችን
በመቅረጽ ተግበራዊ ሇማዴረግ የሚረዲ ይሆናሌ፡፡

የገንዘብ እና የፋይናንስ ዘርፉን ሇማዘመን በተወሰደ የማሻሻያ እርምጃዎች፣ በሥራ ሊይ


ያለ የገንዘብ ፖሉሲ ማስፈጸሚያ መሳሪያዎችን ሇማጠናከርና አዲዱስ መሳሪያዎችን
ሥራ ሊይ ሇማዋሌ ያስቻሇ ከመሆኑም በሊይ የፋይናንስ ዘርፉ ጉሌህ ዕዴገት
እንዱያሳይና የፋይናንስ አካታችነት (financial inclusion) እንዱሻሻሌ አዴርጓሌ፡፡
በመሆኑም የፋይናንስ አካታችነት መሇኪያዎች ከፍተኛ መሻሻሌ እያሳዩ ሲሆን፣
የዱጂታሌ ፋይናንስ አገሌግልት ሇዚህ መስፋፋት ትሌቅ አስተዋጽኦ አበርክተዋሌ፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞ የትሬዠሪ ቢሌ ገበያው እንዱጠናከር ተዯርጓሌ፣ የባንኮች
የተቀማጭና የብዴር ገንዘብ ከፍተኛ ጭማሪ አሳይቷሌ፣ የዱጂታሌና የሞባይሌ ገንዘብ
የፋይናንስ አገሌግልት በከፍተኛ ዯረጃ ተስፋፍቷሌ፣ የተንቀሳቃሽ ንብረት ዋስትና
መብት ተፈቅድ በሥራ ሊይ ሇማዋሌ እንቅስቃሴዎች ተጀምረዋሌ፣ እንዱሁም በሸሪዓ
ሊይ የተመሠረቱ የፋይናንስ አገሌግሇቶች አገሌግልቶች በከፍተኛ ፍጥነት እየተስፋፉ
ይገኛለ፡፡ ከነዚህ በተጨማሪም የካፒታሌ ገበያ ሥርዓትን ተግባራዊ ሇማዴረግ በርካታ
ሥራዎች እየተከናወኑ የሚገኙ ሲሆን፣ የግለን ዘርፍ የፋይናንስ አቅርቦት ሇማሻሻሌ
የሚያስችለ እርምጃዎችም ተግባራዊ በመዯረጋቸው ተጨባጭ ሇውጦች ተገኝተዋሌ፡፡

4
የ2016 በጀት መግሇጫ (Budget Speech)

በኢንቨስትመንትና ንግዴ ዘርፎች ተግባራዊ የተዯረጉ ማሻሻያዎች የኢንቨስትመንትን


ማዕቀፍ ሇማዘመን የረደ ከመሆናቸውም ባሻገር በኢትዮጵያ ውስጥ የንግዴ ሥራን
ሇማከናወን የሚወስዯውን ጊዜና ወጪ ሇመቀነስ አስችሎሌ፡፡ ከዚህም ጋር ተያይዞ
ኢንቨስትመንትን በመሳብና በመንከባከብ የኢንቨስትመንት አካባቢን ዘመናዊ የማዴረግ
ዓሊማ ያሇው አዱስ የኢንስትመንት ህግ ጸዴቆ ተግባራዊ እየተዯረገ ይገኛሌ፡፡
እንዱሁም፣ የንግዴ አገሌግልት ሇማግኘት የሚያስፈሌገውን ጊዜና ወጪ ሇመቀነስ
ያስቻለ ከ80 በሊይ የህግና አስተዲዯር ማሻሻያዎች ተግባራዊ የተዯረጉ ሲሆን፣ የአንዴ
መስኮት የኤላክትሮኒክ ፖርታሌ አገሌግልትን ተግባራዊ ማዴረግ በመቻለ የንግዴ
ክሉራንስ አገሌግልት ሇመስጠት ይወስዴ የነበረውን አማካይ ጊዜ ከ44 ቀናት ወዯ 13
ቀናት መቀነስ ተችሎሌ፡፡ ከነዚህም በተጨማሪ ከ1950ዎቹ ጀምሮ ሥራ ሊይ የነበረውን
የንግዴ ህግ የዓሇም አቀፍ ምርጥ ተሞክሮዎችን በማካተት አዱስ ዘመናዊ ህግ ጸዴቆ
ሥራ ሊይ እንዱውሌ ተዯርጓሌ፡፡ በአጠቃሊይ በነዚህ ዘርፎች ቁሌፍ የሆኑ የፖሉሲና
መዋቅራዊ ማሻሻያዎችን ተግባራዊ በማዴረግ የኢንስትመንትና የንግዴ ማነቆዎችን
ማስወገዴ የተቻሇ ሲሆን፣ የዘርፎቹን አፈጻጸም የበሇጠ ውጤታማ እና ቀሌጣፋ
ሇማዴረግ የአገሌግልት ማሻሻያዎቹ በቀጣይም በጥሌቀት እየተፈተሹ ተግባራዊ
እንዯሚዯረጉ ይጠበቃሌ፡፡

የሀገር በቀሌ የኢኮኖሚ ሪፎርም ትግበራው በልጀስቲክስ ዘርፉ ወጪ እንዱቀንስና


የተሻሇ ቅሌጥፍና እንዱኖር ሇማዴረግ ተጨባጭ እርምጃዎች ተግባራዊ እንዱሆኑ
አዴርጓሌ፡፡ በዚህም በዘርፉ በርካታ የንዐስ ዘርፍ ልጀስቲክ አገሌግልቶች ሇግሌና
ሇውጭ ኢንቨስትመንት ተከፍተዋሌ፣ የዯረቅ ወዯቦች ግንባታ፣ ኦፐሬሽንና ማኔጅመንት
ሇውዴዴር ክፍት ተዯርገዋሌ፡፡ በመሆኑም የጉምሩክ የወዯብ ክሉራንስ፣ የጭነት
መቆጣጠሪያዎችና የአገሌግልት ጥራትን ጨምሮ የዘርፉን አፈጻጸም ሇመሇካት
የተቀመጡ የአፈጻጸም አመሌካቾች መሻሻሌ አሳይተዋሌ፡፡ ከጥቂት ዓመታት በፊት
ሥራ የጀመረው ዘመናዊ የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አገሌግልትም በልጀስቲክ ዘርፉ ከፍተኛ
አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛሌ፡፡

5
የ2016 በጀት መግሇጫ (Budget Speech)

በግብርናው ዘርፍ ረገዴ ተግባራዊ የተዯረጉ ማሻሻያዎች የሀገሪቱን እምቅ አቅም


ሇመጠቀም የሚያስችሌ አቅምን ሇመፍጠር መሠረት የጣሇ ሲሆን፣ የምግብ ዋስትናን
ሇማረጋገጥ፣ ኤክስፖርትን ሇማሳዯግና ከውጭ ሲገባ የነበረውን የምግብ አቅርቦት
በሀገር ውስጥ ምርት መተካት ያስቻሇ ነው፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞም በግብርናው ዘርፍ
የግለን ዘርፍ ተሳትፎ ሇማሳዯግና ተወዲዲሪነትን ሇማረጋጋጥ የግብርና ግብዓት ገበያው
የሚመራበት የህግ ማዕቀፍ ተከሌሷሌ፣ በርካታ የግብርና መካናይዜሽን መሳሪያዎችና
ግብዓቶች ከቀረጥ ነጻ የሚገቡበት ሥርዓት ተዘርግቷሌ፣ የአረንጓዳ አሻራ ፕሮግራም
ተግባራዊነት ህብረተሰቡ የአትክሌትና ፍራፍሬ ምርትን በማምረት ሥራ ሊይ
እንዱሳተፍ ሰፊ ንቅናቄን ከመፍጠሩም በሊይ የሀገሪቱን እምቅ አቅም ሇማሌማት ዕገዛ
እያዯረገ ነው፡፡

የማዕዴን ዘርፉን ዕምቅ አቅም በተሻሇ ሇመጠቀም የማዕዴንና የፔትሮሉየም


ኢንደስትሪዎችን ሇማሻሻሌ አስፈሊጊ የሆኑ የህግና የፖሉሲ ማዕቀፍ ማሻሻያዎችም
የተዯረጉ ሲሆን፣ የዱጂታሌ የማዕዴን ፈቃዴና የኢንቨስትመንት ማኔጅመንት ሥርዓት
ሥራ ሊይ ውሎሌ፣ በማዕዴን ዘርፉ በህጋዊ ሥርዓት መንቀሳቀስን ሇማረጋገጥ በዘርፉ
የሚሳተፉ ባህሊዊ አምራቾች (artisanal) እና የጥቃቅንና አነስተኛ አምራቾች
የሚመሩበት የሀገር ዓቀፍ የማዕዴን ስትራቴጂ ተዘጋጅቶ ሥራ ሊይ ውሎሌ፡፡
እንዱሁም የዴንጋይ ከሰሌ የመሳሰለ የኢንደስትሪ ግብዓቶችን ኢምፖርት በሀገር
ውስጥ ምርት ሇመተካት ጥረቶች እየተረጉ ሲሆን፣ ትሌሌቅ የማዕዴን ካምፓኒዎች
በዘርፉ በማዕዴን ሥራ ሊይ እንዱሰማሩ ኢንስትመንትን የማስተዋወቅ ሥራዎች
እየተካሄደ ነው፡፡ ይህም ዘርፉ የኤክስፖርትን ገቢ ሇማሳዯግና ሇኢምፖርት
የሚወጣውን ወጪ በመቀነስ ረገዴ የሚኖረውን አስተዋጽኦ እንዯሚያሳዴግ ይጠበቃሌ፡፡

በኢንፎርሜሽን ኮሙኒኬሽን ቴክኖልጂ ዘርፍ የዱጂታሌ ኢኮኖሚን እምቅ አቅም


ሇኢኮኖሚ ዕዴገት ምንጭነት ሇመጠቀም የፖሉሲና ስትራቴጂ መሠረቶችን ሇመዘርጋት
የሚያስችለ ማሻሻያዎች በዘርፉ ተግባራዊ የተዯረጉ ሲሆን፣ የተቀናጀ ብሔራዊ
ዱጂታሌ ስትራቴጂ ተቀርጾ ተግባራዊ እየተዯረገ ይገኛሌ፣ እንዱሁም የዱጂታሌ
6
የ2016 በጀት መግሇጫ (Budget Speech)

ሌውውጥን፣ የኤላክትሮኒክ ንግዴንና የዱጂታሌ መንግስታዊ አገሌግሇቶችን


ሇማበረታታት የሚያስችለ የተሇያዩ የህግ ማዕቀፎችና ፖሉሲዎች ተግባራዊ እየተዯረጉ
ነው፡፡ እነዚህም ዜጎች የንግዴ እንቅስቃሴዎችንና መንግስታዊ አገሌግልቶችን በዱጂታሌ
ሥርዓት በሰፊው እንዱጠቀሙ ከማስቻለም ባሻገር የኢኮኖሚ ዕዴገቱን ሇማፋጠን
ከፍተኛ ዕገዛ እያዯረጉ ይገኛለ፡፡

የተከበሩ አፈ ጉባኤ
የተከበራችሁ የም/ቤት አባሊት

የአገር በቀሌ የኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተግበራዊ ሇማዴረግ መንግስት በቁርጠኝነት


በወሰዲቸው እርምጃዎች ከዚህ በሊይ ከተጠቀሱትም ውጭ የተገኙ በርካታ አዎንታዊ
ውጤቶችን መጥቀስ የሚቻሌ ቢሆንም የቀረቡት ሇግንዛቤ በቂ ናቸው የሚሌ ዕምነት
አሇኝ፡፡ ሆኖም ባሇፉት ዓመታት ሇሪፎርም ትግበራው ተግዲሮት የነበሩና በቀጣይ
ትኩረት ሉዯረግባቸው የሚገቡ ጉዲዮችን ማንሳት ተገቢ ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ባሇፉት
ዓመታት የኮቪዴ-19 ወረርሽኝ፣ የአንበጣ መንጋ፣ የጎርፍና የዴርቅ አዯጋዎች፣ የአገር
ውስጥ ግጭቶች እና ጦርነት፣ እንዱሁም የዓሇም የመሠረታዊ ሸቀጦች ዋጋ መናር
የሪፎርም ትግበራውን በማስተጓጎሌ ሇኢኮኖሚው ተግዲሮቶችን ያስከተለ እንቅፋቶች
ነበሩ፡፡ እነዚህም የሪፎርም ትግበራው ከዚህም በሊይ ስኬት እንዲያስመዘግብ የራሳቸውን
ሚና ተጫውተዋሌ፡፡ በመሆኑም በቀጣዩ የሀገር በቀሌ የኢኮኖሚ ማሻሻያ እነዚህን
የኢኮኖሚ ተግዲሮቶች ሇመቅረፍ ትኩረት ተሰጥቶ የሚሰራ ይሆናሌ፡፡

የተከበሩ አፈ ጉባኤ
የተከበራችሁ የም/ቤት አባሊት

ከእነዚህ ተግዲሮቶች መካከሌ በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶ የሚሰራበት ጉዲይ በፊስካሌ


ዘርፉ ያጋጠሙ ተግዲሮቶችን ሇመቅረፍ የሚሰሩ ተግበራትን የሚመሇከት ነው፡፡
ከዚህም ጋር ተያይዞ ኢኮኖሚው ሉያመነጨው የሚችሇውን የመንግስትን የአገር ውስጥ
ገቢ እምቅ አቅም አሟጦ ሇመሰብሰብ የሚያስችለ ማሻሻያዎችን ተግባራዊ በማዴረግ
የሌማት ፋይናንስ ፍሊጎቶቻችንን በራሳችን የመሸፈን አቅማችንን በማሳዯግ እና

7
የ2016 በጀት መግሇጫ (Budget Speech)

የመንግስትን የፊስካሌ ጉዴሇት ጤናማ በማዴረግ ሊይ ትኩረት ተዯርጎ መስራት ተገቢ


ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ባሇፉት ዓመታት የታክስ ገቢና የውጭ ዕርዲታና ብዴር አሰባሰብ
ዝቅተኛ አፈጻጸም በማሳየታቸው የተያዘውን የገቢ ዕቅዴ ማሳካት አሌተቻሌም፡፡
በተመሳሳይም ከሌማት አጋሮች የሚጠበቀው የሌማት ዴጋፍ በከፍተኛ ዯረጃ የቀነሰ
ሲሆን፣ በበጀት ዴጋፍ መሌክ ይገኛሌ ተብል የተያዘው ዕቅዴ ሙለ ሇሙለ ሳይገኝ
ቀርቷሌ፡፡ በአንጻሩ ዯግሞ የተከሰቱት አዯጋዎች የመንግስት ወጪ ፍሊጎት እጅግ
እንዱንር ያዯረጉ ሲሆን፣ እነዚህን ተጨማሪ የሰብዓዊ ዴጋፍ፣ የህግ ማስከበርና የዕዲ
ክፍያ እና የዏፈር ማዲበሪያ ዴጎማ ተጨማሪ ወጪዎች ሇመሸፈን በተወሰነ ዯረጃ
በበጀት ታቅዯው የነበሩ የሌማት ወጪዎችን ማሸጋሸግ ከመጠየቁም በሊይ የገጠመንን
ተጨማሪ የበጀት ጉዴሇት ከሀገር ውስጥ ተጨማሪ ብዴር በመውሰዴ መሸፈን የግዴ
ሆኗሌ፡፡ እንዱሁም በሀገር በቀሌ ማሻሻያው የአጠቃሊይ የመንግስት የውጭ ዕዲ ስጋት
ዯረጃን ወዯ መካከሇኛ ስጋት ዯረጃ ሇመቀነስ የተዯረጉት የዕዲ ሽግሽግ ስምምነት ጥረቶች
የተወሰኑ ስኬቶች ቢያስገኙም፣ በተሇይ በዕዲ ስጋት ቅነሳው ሊይ ትርጉም ያሇው ሇውጥ
ያመጣሌ ተብል ተስፋ የተጣሇበት የG20 Common Framework ዕዴሌ በተፈሇገው
ፍጥነት ተግባራዊ ባሇመዯረጉ እና በመዘግየቱ ቀጣይ የቤት ሥራ ሆኗሌ፡፡

ላሊውና በቀጣይ ትኩረት የሚሻው የኢኮኖሚው ተግዲሮት የዋጋ ንረት ሲሆን፣


በሪፎርም ትግበራ ዘመን ውስጥ የዋጋ ንረት ሇረዥም ወራት ከ30 በመቶ በሊይ ሆኖ
ቆይቷሌ፡፡ ሇዋጋ ንረቱ እንዯ መንስኤ የሚታዪ ጉዲዮች በርካታ ሲሆኑ፣ የምርትና
ምርታማነት በበቂ ሁኔታ አሇመጠናከር፣ የአገር ውስጥ የንግዴ ሰንሰሇት፣ የፊሲካሌ
ጉዴሇት አሸፋፈን እና የዓሇም ዓቀፍ ሸቀጦች ዋጋ ዕዴገት ተጽእኖ በዋናነት የሚጠቀሱ
ምክንቶች ናቸው፡፡ የዋጋ ንረት የሸማቹን የመግዛት አቅም የሚያዲክም ከመሆኑም
በሊይ በረዥም ጊዜ የኢኮኖሚውን አፈጻጸም እጅጉን የሚጎዲ በመሆኑ ቀጣይነት ያሇው
እርምጃ ተወስድ መስተካከሌ የሚገባው የኢኮኖሚ ተግዲሮት ነው፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ
መንግስት ሇጊዜውም ቢሆን ዝቅተኛ ገቢ ያሇው ህብረተሰብ ሊይ ያሇውን ጫና ሇማርገብ
እንዱረዲ የመሠረታዊ ምግብ ሸቀጦች አቅርቦት እንዱሻሻሌ ቀረጥና ታክስ

8
የ2016 በጀት መግሇጫ (Budget Speech)

ሳይከፈሌባቸው እንዱገቡ በማዴረግ እና የማዲበሪያ ዋጋን በዴጎማ ሇማቅረብ እንዱቻሌ


በጀት በመመዯብ ችግሩ እንዱቃሇሌ ሇማዴረግ ጥረት ተዯርጓሌ፡፡ በቀጣይም የዋጋ
ንረትን በማረጋጋት የኑሮ ውዴነትን ሇመቅረፍ የተጀመሩ ምርታማነትን ሉያሳዴጉ
የሚችለ ማሻሻያዎችን እና ላልች የዋጋ ንረትን ሉያረጋጉ የሚችለ እርምጃዎችን
መውሰዴ ተገቢ ይሆናሌ፡፡

እንዱሁም የውጭ የኢኮኖሚ ዘርፍ (Balance of Payment) በእነዚህ በተከሰቱት


አዯጋዎች ከፍተኛ ተጽእኖ የዯረሰበት ላሊው ሲሆን፣ የኤክስፖርት ገቢያችን አሁን
ከተገኘው አፈጻጸም በሊይ እንዲይሆን ከማዴረጉም በሊይ፣ የኢምፖርት ዕቃዎች፣
በተሇይም የማዲበሪያና የነዲጅ እንዱሁም የመንግስት ዕዲ ክፍያ ወጪዎች እንዱጨምር
ያዯረገ ሲሆን፣ በአንጻሩ ዯግሞ የሌማት አጋሮች ሇኢትዮጵያ የሚሰጡትን ዴጋፍ
በመቀነሳቸውና የቀጥታ በጀት ዴጋፍ በማቆማቸው የውጭ ኦፊሲያሌ ፍሰት (official
transfer) በከፍተኛ ዯረጃ እንዱቀንስ አዴርጓሌ፡፡ ይህም የሀገሪቱ የውጭ ክፍያ ሚዛን
እንዱሰፋ ምክንያት ሆኗሌ፡፡ በመሆኑም የክፍያ ሚዛን ጉዴሇትን ሇማጥበብና የውጭ
ምንዛሬ አቅርቦትን ሇማሻሻሌ በቀጣይ ሰሊማችንን በማጽናት የምርታማነት፣
የፕሮሞሽንና የዱፕልማሲ ሥራዎችን በማከናወን የውጭ ካፒታሌ ፍሰት እንዱጨምር
ትኩረት አዴርጎ መስራት ተገቢ ነው፡፡

የተከበሩ አፈ ጉባኤ
የተከበራችሁ የም/ቤት አባሊት

እነዚህን የገጠሙንን የኢኮኖሚ ተግዲሮቶች ሇመፍታትና በመጀመሪያው የአገር በቀሌ


የኢኮኖሚ ማሻሻያ እስከአሁን ተግባራዊ ያሌተዯረጉ እና አዲዱስ ማሻሻያዎችን አጠናክሮ
ተግባራዊ ሇማዴረግና የኢኮኖሚ ዕዴገቱን ሇማስቀጠሌ የሀገር በቀሌ የኢኮኖሚ ማሻሻያ
ሁሇተኛው ምዕራፍ ረቂቅ የተዘጋጀ ሲሆን፣ ምክክር እየተዯረገበት ይገኛሌ፡፡ በዚህም
የገጠሙንን ተግዲሮቶች ሇመፍታት የሚያስችለ የማክሮ ኢኮኖሚ፣ የፊስካሌ እና
ፋይናንሻሌ ፖሉሲዎች እና የኢንስትመንትና የንግዴ አካባቢዎችን ምቹ ሇማዴረግ
እንዱሁም የዘርፎችን ምርታማነት እና ተወዲዲሪነት ሇመጨመር የሚያስችለ መጠነ

9
የ2016 በጀት መግሇጫ (Budget Speech)

ሰፊ ማሻሻያዎች ተግበራዊ የሚዯረጉ ይሆናለ፡፡ ይህ የቀረበው የቀጣዩ በጀት ዓመት


ረቂቅ በጀትም እነዚህን የኢኮኖሚ ሪፎርሞች እና በእነዚህ ሊይ በመመሥረት የተዘጋጁ
የቀጣዩ በጀት ዓመት ማክሮ ኢኮኖሚ ትንበያዎችን ታሳቢ በማዴረግ የተዘጋጀ ነው፡፡

ረቂቅ በጀቱ የተዘጋጀው የተቀመጡ ዋና ዋና የፊሲካሌ ግቦችን፣ በጀቱ ቅዴሚያ


ትኩረት የሚያዯርግባቸውን የገቢ እና የወጪ ፖሉሲ አቅጣጫዎችን፣ ወቅታዊ የማክሮ
ኢኮኖሚ ሁኔታን እና የፊሲካሌ አቅምን ባገናዘበ መሌኩ ነው፡፡ እነዚህ በሁሇተኛው
ምዕራፍ የሀገር በቀሌ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ውስጥ የተካተቱ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሉሲዎች
ተግበራዊ ሲዯረጉ በቀጣዮቹ ዓመታት የማክሮ ኢኮኖሚው መሻሻሌ እንዯሚያሳይ ታሳቢ
የተዯረገ ሲሆን፣ የመንግስት የፊሲካሌ ተግዲሮቶችም በየዯረጃው እየተቀረፉና ትኩረቱ
በሌማት ሊይ እንዯሚሆን ከፍተኛ ግምት ተወስዶሌ፡፡ በተሇይም በቀጣይ ዓመታት
የተረጋጋ የማክሮ ኢኮኖሚን ማረጋገጥና ይህም የኢኮኖሚ ዕዴገት እንዱመዘገብ አስቻይ
ሁኔታዎች እንዱፈጠሩ ሇማዴረግ በማሻሻያው እንዯ ግብ የተያዘ ነው፡፡ ሇዚህም
የመንግስት ገቢ አሰባሰብን ሇማሻሻሌ፣ ብቁና የግሌ ዘርፉን ተሳትፎ ሇማረጋገጥ የሚረዲ
የፐብሉክ ኢንስትመንት እንዱኖር ሇማዴረግ፣ የመንግስትን ዕዲ ስጋት ዯረጃ ሇመቀነስ፣
የውጭ ምንዛሬ ፍሊጎትን ሇማሟሊት እና የፋይናንስ አቅርቦትን ሇማሻሻሌ የሚያስችለ
በርካታ ተግባራት ሇማከናወን ታቅዶሌ፡፡

የመንግስት ገቢ አሰባሰብን ሇማሻሻሌ ግብር ከፋይ ተኮር እና ውጤታማ የታክስ


አስተዲዯር ሥርዓት ሇመዘርጋት የሚያስችለ ተግበራትን ሇማከናወን የታቀዯ ሲሆን፣
አካታች የኢኮኖሚ ዕዴገትን እና የታክስ ገቢ አሰባሰብን የሚዯግፉ የታክስ ፖሉሲዎችና
ህጎችም ተግበራዊ ይሆናለ፡፡ በዚህም የታክስ አስተዲዯር አገሌግልቱ ከግብር ከፋዩ ጋር
የሚኖርን የማህበራዊ ውሌ (social contract) ማዕከሌ ያዯረገ ዯንበኛን የማገሌገሌ
ባህሌ እንዱዲብር የሚያዯርግ ሥርዓት እንዱዘረጋ የሚያዯርግ አገሌግልት እንዱኖር
ማስቻሌ ሲሆን፣ ግሌጽና ቀሊሌ የታክስ አስተዲዯር እንዱኖር፣ ሥርዓቱ
በዱጂታሊይዜሽን እንዱታገዝ የማዴረግ፣ ውጤታማ የታክስ ኦዱት እንዱዘረጋ
የማዴረግና የታክስ ማበረታቻ ሇታሇመሇት ዓሊማ መዋለንና ዓሊማውን ማሳካቱ
10
የ2016 በጀት መግሇጫ (Budget Speech)

የሚገመገምበት ሥርዓትን መዘርጋት ይሆናሌ፡፡ ሇዚህም በገቢ አሰባሰቡ እመርታ


እንዱኖርና የኢኮኖሚ ዕዴገቱን በመዯገፍ እንዱሁም የታክስ መሠረትን በማስፋት፣
ፍትሀዊነትን በማረጋገጥና በአፈጻጸም ሊይ የተመሠረተ የማበረታቻ ሥርዓት ሊይ
ያተኮረ የመካከሇኛ ዘመን የገቢ ስትራቴጂ (Medium-Term Revenue Strategy-
MTRS) ተቀርጾ ተግባራዊ የሚዯረግ ይሆናሌ፡፡

በላሊ በኩሌ የመንግስት ኢንቨስትመንት ትኩረት ሌማትን የሚያረጋግጥና የኢኮኖሚ


ዕዴገትን የሚያፋጥን፣ የግሌ ኢንቨስትመንትን ሇማሳሇጥ የሚረዲ፣ እንዱሁም
የመንግስት ሌማት ዴርጅቶች ማሻሻያ ተጠናክሮ ተግበራዊ እንዱሆን በማዴረግ
ተወዲዲሪነትንና ውጤታማነት የሚያረጋግጥ እንዱሆን የሚያስችለ ማሻሻያዎች
ተግባራዊ የሚዯረጉ ይሆናሌ፡፡ በዚህም የካፒታሌና የመዯበኛ ወጪዎችን በማመጣጠን
ሇሌማትና ዕዴገት አስተዋጽኦ ሇሚያዯርጉ ዘርፎች ወጪዎች ትኩረት መስጠት፣
የፐብሉክ ኢንስትመንት ውጤታማነትን ሇማሻሻሌ የሚያስችለ የፐብሉክ
ኢንቨስትመንት ማኔጅመንት መሳሪያዎችን በተጠናከረ ሁኔታ ተግበራዊ ማዴረግ፣ እና
የመንግስት ግዥ እና ሪፖርት ሥርዓት በዱጂታሌ ቴክኖልጂ የታገዘ እንዱሆን
ማዴረግን ባካተተ መሌክ የመንግስት ፋይናንስ አስተዲዯር ማሻሻያዎችን በተጠናከረ
መንገዴ ተግባራዊ ማዴረግ የመሳሰለ በርካታ ተግባራት ሥራ ሊይ የሚውለ ይሆናለ፡፡
በተጨማሪ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆሌዱንግ ስትራቴጂያዊ የመንግስት
ኢንቨስትመንት ክንዴ እንዱሆን ማጠናከር፣ የመንግስትና የግሌ አጋርነት የግሌ ዘርፉን
ኢንቨስትመንት የበሇጠ ሇማሳሇጥ እንዱያስችሌ ማጠናከር እና ላልች የመንግስት
የሌማት ዴርጅቶች ማሻሻያዎች ተግበራዊ የሚዯረጉ ይሆናሌ፡፡

ከዚህም በተጨማሪ በንግዴና ኢንቨስትመንት የገበያን ተዯራሽነትና ተወዲዲሪነት


ሇማሻሻሌ፣ የመካከሇኛና ጥቃቅን ኢንተርፕራይዞችን ዕዴገት ሇማፋጠን፣ የውጭ
ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰትንና አስተዋጽኦውን ሇማሻሻሌ፣ እና የተቀሊጠፈ
የሠራተኛ-አሰሪ የክርክር ጉዲዮች አሰጣጥ እንዱኖር ሇማዴረግ የሚያስችለ
ማሻሻያዎችን፣ እንዱሁም የኢኮኖሚ ዕዴገቱን ሇማፋጠን ወሳኝ የሆኑ ዘርፎችን
11
የ2016 በጀት መግሇጫ (Budget Speech)

ምርታማነትና ተወዲዲሪነት ሇማሳዯግ የሚያበቁ በሪፎርም ፕሮግራሙ የታቀደ በርካታ


ማሻሻያዎች ተግባራዊ የሚዯረጉ ይሆናሌ፡፡

በተጨማሪም የማሻሻያ ዕቅደን በብቃትና በስኬታማነት ተግባራዊ ሇማዴረግ የሚቻሇው


የመንግስትን የመፈጸም አቅም በማጎሌበት በመሆኑ፣ ብቁና ውጤታማ የሲሌ ሰርቪስ
ተቋማት እና አዯረጃጀት እንዱኖር ሇማዴረግ እንዱሁም የተቀናጀ የሲቪሌ ሰርቪስ
መረጃ አያያዝና ብሌሹ አሰራርን ሇማስወገዴ እና ውጤታማና ዘመናዊ አገሌግልትን
ሇመስጠት የሚያስችለ ማሻሻያዎች ተግበራዊ ይዯረጋለ፡፡ የሲቪሌ ሰርቪስ ሪፎርሙ
በፌዳራሌ እና በክሌሌ ተቋማት በተጠናከረና ባሌተማከሇ መንገዴ ተግባራዊ የሚዯረግ
ሲሆን፣ የመንግስትን በጀት በውጤታማነት እና በቁጠባ ሇመጠቀም ከፍተኛ ፋይዲ
ይኖረዋሌ፡፡

የተከበሩ አፈ ጉባኤ
የተከበራችሁ የም/ቤት አባሊት

ከሊይ ሇመግሇጽ እንዯሞከርኩት ባሇፉት ዓመታት መንግስት በሀገር በቀሌ የኢኮኖሚ


ማሻሻያ የተካተቱ መጠነ ሰፊ የኢኮኖሚ ሪፎርም እርምጃዎችን ተግባራዊ በማዴረጉ፣
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ የተሇያዩ ተጽእኖዎችን በመቋቋም ከ6 በመቶ በሊይ አማካይ
ዓመታዊ ዕዴገት ማስመዝገብ እና ዕዴገቱ ቀጣይ እንዱሆን ማዴረግ ተችሎሌ፡፡ ይህም
የግብርና ምርታማነትን ሇማሻሻሌ፣ የኢንደስትሪና የአገሌግልት ዘርፉን ዕዴገት
ሇመዯገፍ በተዯረጉ ከፍተኛ ጥረቶች የተገኘ ውጤት ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ
የኤክስፖርት ገቢ ባሇፉት ዓመታት ከፍተኛ መሻሻሌ የታየበት ሲሆን የውጭ ቀጥተኛ
ኢንስትመንትም በአንጻራዊነት ዕዴገት አሳይቷሌ፡፡ ሆኖም ባሇፉት ዓመታት ሀገራችን
ያጋጠሟት ዘርፈ-ብዙ ውስጣዊ እና ዓሇም ዓቀፋዊ ተጽእኖዎች በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ
ሊይ ከፍተኛ ጫናዎችን በማሳዯራቸው በርካታ የኢኮኖሚ ተግዲሮቶች ተከስተዋሌ፡፡
በተሇይም የተከሰቱት ቀውሶች በፊሲካሌ ሊይ ያስከተለትን ተጽእኖ ሇማስተካከሌ
ዓመታትን መፍጀቱ የማይቀር በመሆኑ፣ የመንግስት በጀት በአጭርና በመካከሇኛ ጊዜ
ሉከተሌ የሚገባውን ትኩረት በጥንቃቄ በማየት መወሰን ተገቢ ይሆናሌ፡፡ ይህ ረቂቅ

12
የ2016 በጀት መግሇጫ (Budget Speech)

ዓመታዊ በጀትም ሲዘጋጅ፣ ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው፡፡ በአጠቃሊይ ከሊይ
የቀረቡ የሪፎርም ዕቅድች ተግባራዊነትን መሰረት በማዴረግ በማክሮ ኢኮኖሚ ረገዴ
ታሳቢ የተዯረጉ ጉዲዮች የሚከተለት ናቸው፡፡

የኢኮኖሚ ዕዴገቱን ቀጣይ ከማዴረግ አንጻር በቀጣዮቹ ዓመታት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ


ከገጠሙት ቀውሶች ተሊቆ ሙለ ሇሙለ ጤናማ አቋም ሊይ እንዯሚዯርስ ታሳቢ
የተዯረገ ሲሆን፣ በያዝነው በጀት ዓመት ኢኮኖሚው ከገጠሙት ቀውሶች በተወሰነ ዯረጃ
ተጽኦኖው ረገብ በማሇቱና በመንግስት በኩሌም ኢኮኖሚው እንዱያንሰራራ እየተዯረጉ
ያለ ጥረቶች የተሻሇ ዕዴሌ እንዯሚፈጥሩ ታሳቢ በማዴረግ፣ ኢኮኖሚው ከነበረው
ችግር በማገገም የ7.5 በመቶ ዕዴገት እንዯሚያስመዘግብ ተገምቷሌ፡፡ እንዱሁም፣
በ2016 በጀት ዓመት የ7.9 በመቶ ዕዴገት እንዯሚመዘገብ ትንበያ የተዯረገ ሲሆን፣
የአጠቃሊይ ዋጋ ዕዴገት የተወሰነ ቅናሽ እንዯሚያሳይና ባሇሁሇት አሃዝ ሆኖ
እንዯሚቀጥሌ ግምት ተወስዶሌ፡፡

የገቢ ዕቃዎች ዋጋ (Value of goods import) በ2015 በጀት ዓመት የ7.2 በመቶ
ዕዴገት እንዯሚያሳይ የተገመተ ሲሆን፣ በ2016 የ18.9 በመቶ ዕዴገት እንዯሚኖረው
ታሳቢ ተዯርጓሌ፡፡ ከገንዘብ ፖሉሲ አንጻር በመካከሇኛ ዘመን ውስጥ ጥብቅ የገንዘብ
ፖሉሲ ተግባራዊ እንዯሚዯረግ፣ የገንዘብ አቅርቦትን በመገዯብ አሁን የሚታየውን
ከፍተኛ የዋጋ ንረት ሇማረጋጋት ጥረት እንዯሚዯረግ፣ ሇበጀት ጉዴሇት መሸፈኛ
ከብሔራዊ ባንክ በቀጥታ የሚወሰዯው ብዴር ከፍተኛ ቅናሽ እንዯሚያሳይ፣ ባሇፉት
ዓመታት በተሇያዩ የገንዘብ ብዴር ዘዳዎች (monetary instruments) ወዯ ኢኮኖሚው
ውስጥ የተሰራጨውን ገንዘብ መሌሶ ሇመሰብሰብ በገንዘብ ፖሉሲው እርምጃ
እንዯሚወሰዴ (liquidity mopping up)፣ እንዱሁም በአጠቃሊይ ተገቢ የሆነ የገንዘብ
አቅርቦት (broad money) ዕዴገት እንዱኖር እንዯሚዯረግ ታሳቢ ተዯርጓሌ።

በፊሲካሌ ፖሉሲ ረገዴ፣ የታክስ ገቢ አሰባሰብ እመርታዊ ሇውጥ እንዱያመጣ


የሚያስችለ የታክስ ፖሉሲ ማሇትም፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ማሻሻያ፣ የኤክሳይዝ
ታክስ አዋጅ ማሻሻያ፣ የኤክሳይዝ ቴምብር፣ እና የማህበራዊ ዋስትና ሌማት ቀረጥ
13
የ2016 በጀት መግሇጫ (Budget Speech)

(social welfare development duty) የመሳሰለ የታክስ ህጎችን ተግባራዊ የሚዯረጉ


ይሆናሌ፡፡ እንዱሁም በታክስ አስተዲዯሩ ረገዴም ትርጉም ያሇው ሇውጥ ሇማምጣት
የሚያስችለ ማሻሻያዎች ተግባራዊ የሚዯረጉ ሲሆን፣ በተሇይም የገቢዎችና ጉምሩክ
መ/ቤቶች የሰው ሀይሌና ተቋማዊ አቅምና የአሠራር ችግሮችን እና አዯረጃጀቱን
በጥሌቀት በመፈተሽ አስፈሊጊ የሆኑ ማሻሻያዎች ተግባራዊ የሚዯረጉ ይሆናሌ፡፡
ሇዚህም በተግባር ተጨባጭ ሇውጥ እንዱመጣ በመንግስት በኩሌ አስፈሊጊው ዴጋፍ
ሁለ እንዯሚዯረግ ታሳቢ ተዯርጓሌ፡፡ ከታክስ ገቢ በተጨማሪም ታክስ ካሌሆኑ
ምንጮች የሚሰበሰቡት ገቢዎች አቅምን አሟጦ ሇመጠቀም በሚያስችሌ መሌክ
በዝርዝር በማየት በገቢ ዕቅደ እንዱካተቱ ተዯርጓሌ፡፡ እንዱሁም በዕርዲታ እና ብዴር
መሌክ ከሌማት አጋሮች የሚገኘው ሀብት በመጠኑም ቢሆን እንዱካተት ተዯርጓሌ፡፡

በወጪ ረገዴ፣ አሁን ካሇው ከፍተኛ የፋይናንስ እጥረት አኳያ የተጀመሩ ፕሮጀክቶችን
ሇማስጨረስ፣ ሇዕዲ ክፍያ፣ በጦርነቱ የወዯሙ መሠረተ ሌማቶችና አገሌግልቶች ወዯ
ቀዴሞ ይዞታቸው መሌሶ ሇማቋቋምና ሇዕሇት ዕርዲታ፣ ሇአፈር ማዲበሪያ ዴጎማ
እንዱሁም ሇብሔራዊ ክሌሊዊ መንግስታት የበጀት ዴጋፍ ቅዴሚያ ትኩረት
ተሰጥቷሌ፡፡ በተሇይም አሁን ያሇው የፋይናንስ እጥረት ሁለንም የወጪ ፍሊጎቶቻችንን
በማዕቀፉ ሇማካተት የማያስችሌ በመሆኑ የተጀመሩ የካፒታሌ ፕሮጀክቶችም ቢሆኑ፣
የክፍያ ጊዜያቸውን በማሸጋሸግ የወጪ በጀት ቅነሳ ማዴረግ እንዯሚያስፈሌግ ጭምር
ታሳቢ በማዴረግ የተዘጋጀ ረቂቅ በጀት መሆኑን ሇማስገንዘብ እፈሌጋሇሁ፡፡ ከዚህም ጋር
ተያይዞ የ2016 በጀት ዓመት የመዯበኛ ወጪ ጣሪያን ሇመወሰን በሰሜኑ ጦርነት ረገዴ
የተዯረሰውን የሰሊም ስምምነት መሰረት በማዴረግ ሇሀገር መከሊከያ የሚያስፈሌገው
ወጪ ባሇፈው በጀት ዓመት ከነበረው አንጻር በመጠኑ ዝቅ እንዱሌ በማዴረግ፣
በጦርነቱ እና በአየር ንብረት ሇውጥ ምክንያት ሇተጎደ ዜጎች የዕሇት ዕርዲታ ሇማቅረብ
እና ሇሌማታዊ ሴፍቲኔት የሚያስፈሌገውን ወጪ፣ ከቅርብ ዓመታት ወዱህ በከፍተኛ
ሁኔታ እየጨመረ የመጣውን የአገር ውስጥ እና የውጭ ሀገር ዕዲ ክፍያም ታሳቢ
በማዴረግ የተዘጋጀ ነው፡፡ የካፒታሌ ወጪ ፍሊጎትን በተመሇከተ በመካሄዴ ሊይ ሊለ

14
የ2016 በጀት መግሇጫ (Budget Speech)

ነባር ፕሮጀክቶች አሁን ያሇውን ዕቅዴ ከማሳካትና እንዱጠናቀቁ ከማዴረግ አንፃር


ቅዴሚያ የተሰጠ ቢሆንም በቀጣይ በጀት ዓመት አዲዱስ የካፒታሌ ፕሮጀክቶች በበጀት
ማካተት እንዯማይቻሌና በተወሰነ ዯረጃ የነባር ፕሮጀክቶችንም የክፍያ ጊዜን በማራዘም
ወጪው እንዱሸጋሸግ በማዴረግ፤ በጦርነቱ የወዯሙ መሠረተ ሌማቶችና አገሌግልቶች
ወዯ ቀዴሞው ይዞታቸው ሇመመሇስ የመሌሶ ማቋቋም ስራን ታሳቢ በማዴረግ የተዘጋጀ
ነዉ፡፡ ሇ2016 የተያዘው የፌዳራሌ መንግስት የመዯበኛና የካፒታሌ በጀት ካሇው
የፊሲካሌ ጫና አንጻር ቅናሽ እንዱኖረው ቢዯረግም ሇብሔራዊ ክሌሊዊ መንግስት
የሚመዯበው የበጀት ዴጋፍ ግን በተቻሇ መጠን በነበረበት እንዱቆይ ሇማዴረግ
ተችሎሌ፡፡ በመሆኑም የክሌልች የበጀት ዴጋፍ አመዲዯብ የፌዳራሌ መንግስት ያሇውን
ሀብት መጠንና የፌዳራሌ መንግስት የግዳታ ወጪዎችና የበጀት ጫናን ግምት ውስጥ
በማስገባት፣ ክሌልች ከ2013 በጀት ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ ከተዯረገው የጋራ ገቢ
ቀመር ማሻሻያ ከፍተኛ ተጠቃሚ መሆናቸውንና ይህ በአንጻሩ ዯግሞ የፌዳራሌ
መንግስትን የገቢ ቋት በእጅጉ የቀነሰ መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ እና አዱሱ
የንብረት ግብርም ተጨማሪ የገቢ አቅም እንዯሚፈጥርሊቸው ታሳቢ በማዴረግ ነው፡፡
በላሊ በኩሌ ሇክሌልች የሚዯረገው የዘሊቂ ሌማት ግቦች ዴጋፍ የተጀመሩ የአግሮ
ኢንደስትሪ ግንባታዎችን ሇማጠናቀቅና በአነስተኛ መስኖ ስራዎች ዴጋፍ ሊይ ብቻ
እንዱያተኩር ታሳቢ በማዴረግ የተመዯበ ነው፡፡

በአጠቃሊይ የ2016 በጀት ዓመት ረቂቅ የፌዳራሌ መንግስት በጀት ጤናማ የፊሲካሌ
ሁኔታን የማረጋገጥ (Fiscal consolidation) አቅጣጫን ተከትል የተዘጋጀ ሲሆን፣
ከሀገር በቀሌ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ሁሇተኛው ምዕራፍ ዕቅዴ ጋር ተጣጥሞ የተዘጋጀ ነው።
ከዚህ ጋር ተያይዞም የመንግስትን የፊሲካሌ አቅም ሇማጠናከር የመንግስት የሀገር
ውስጥ ገቢ አሰባሰብ ሊይ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ መስራት አማራጭ የላሇው
መሆኑን መገንዘብ ይገባሌ፡፡ እንዱሁም ሀገራችን በየጊዜው በሚገጥማት የተፈጥሮ
አዯጋዎች ምክንያት የሚከሰቱ ተጽእኖዎች የሚፈጥሩትን የፊሲካሌ ጫና በዕቅዴና
በተዯራጀ መሌክ ሇመቀነስ የሚያግዙ ሥርዓቶችም ሇመዘርጋት የተሇያዩ ስራዎች

15
የ2016 በጀት መግሇጫ (Budget Speech)

እየተከናወኑ ሲሆን፣ እነዚህንም ተግባራዊ በማዴረግ የፊሲካሌ ሥርዓቱ እንዱጠናከር


ይዯረጋሌ። በተጨማሪም የመንግስት ፕሮጀክቶችን አፈጻጸም ሇማጠናከር የፐብሉክ
ኢንቨስትመንት ዕቅዴ ሥርዓት በተጠናከረ መንገዴ ተግባራዊ የሚዯረግ ይሆናሌ፡፡

የተከበሩ አፈ ጉባኤ
የተከበራችሁ የም/ቤት አባሊት

ከሊይ በዝርዝር የቀረቡትን ዋና ዋና ታሳቢዎች ከግምት ውስጥ በማስገባት አጠቃሇይ


የፌዳራሌ መንግሥት የ2016 በጀት ዓመት ረቂቅ በጀት በዝርዝር ተዘጋጅቶ የቀረበ
ሲሆን፣ በጀቱንም ሇማዘጋጀት ከባሇበጀት መ/ቤቶች ጋር ሰፊ ውይይቶችና ምክክሮች
ተዯርጎበት በሚኒስትሮች ም/ቤት ተዯግፎ የቀረበውን የፌዳራሌ መንግስት የገቢና
የወጪ በጀት እንዯሚከተሇው በዝርዝር አቀርባሇሁ፡፡

በገቢ ረገዴ በ2016 በጀት ዓመት ጠቅሊሊ ገቢ የውጭ ዕርዲታን ጨምሮ ብር 520.6
ቢሉዮን እንዯሚዯርስ የተገመተ ሲሆን፣ ይህም በ2015 በጀት ዓመት ከነዚህ ምንጮች
ይሰበሰባሌ ተብል ከተገመተው አንጻር የ27.7 በመቶ ጭማሪ አሇው፡፡ ይህም ጠቅሊሊ
ገቢ ብር 440.8 ቢሉዮን ከታክስ፣ ብር 38.7 ቢሉዮን ታክስ ካሌሆኑ ምንጮች፣
እንዱሁም ብር 6.3 ቢሉዮን ከቀጥታ የበጀት ዴጋፍ እና ብር 34.8 ቢሉዮን
ከፕሮጀክቶች ዕርዲታ እንዯሚገኝ የተገመተ ነው፡፡ ከዚህ ከታቀዯው ጠቅሊሊ ገቢ ውስጥ
92.1 በመቶ የሚሆነው ዴርሻ ከታክስ እና ታክስ ካሌሆኑ የገቢ ምንጮች እንዯሚገኝ
የታቀዯ ገቢ ነው፡፡ በላሊ በኩሌ ከታክስ ገቢ ሇመሰብሰብ የታቀዯው ብር 440.8 ቢሉዮን
ገቢ የጠቅሊሊ የገቢና ዕርዲታው 84.7 በመቶ ዴርሻ የያዘ ሲሆን፣ በ2015 ከታክስ ገቢ
ይሰበሰባሌ ተብል ከታቀዯው ብር 348 ቢሉዮን የገቢ ግምት አንጻር የ26.7 በመቶ
ጭማሪ አሇው፡፡ በላሊ በኩሌ ታክስ ካሌሆኑ ምንጮች ሇመሰብሰብ ከታቀዯው ብር 38.7
ቢሉዮን ውስጥ ብር 20.8 ቢሉዮን (53.7 በመቶው) የሚሆነው ከመንግስት የሌማት
ዴርጅቶች የትርፍ ዴርሻ የሚገኝ ገቢ ነው፡፡ የውጭ ዕርዲታን በተመሇከተ ሇ2016
በጀት ዓመት ወጪ መሸፈኛ ብር 41.1 ቢሉዮን ከሌማት አጋሮች እንዯሚገኝ የታቀዯ
ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ ብር 6.3 ቢሉዮን በቀጥታ ወዯ መንግስት ማዕከሊዊ ግምጃ ቤት

16
የ2016 በጀት መግሇጫ (Budget Speech)

የሚፈስ ሲሆን ቀሪው ብር 34.8 ቢሉዮን ዯግሞ በቀጥታ ሇተወሰኑ ፕሮጀክቶች


ማስፈጸሚያ በዕርዲታ የሚገኝ ነው፡፡ ይህ በ2016 በጀት ዓመት ከውጭ ዕርዲታ
እንዯሚገኝ የታቀዯው ገቢ በ2015 በጀት ዓመት ይገኛሌ ተብል ከተገመተው ገቢ
አንጻር የ33.4 በመቶ ጭማሪ ሲሆን፣ ከጠቅሊሊ የ2016 የገቢና ዕርዲታ ዕቅዴ 7.9
በመቶው ነው፡፡

የተከበሩ አፈ ጉባኤ
የተከበራችሁ የምክር ቤቱ አባሊት

ከሊይ በዝርዝር የቀረቡትን ዋና ዋና የወጪ ታሳቢዎች ከግምት ውስጥ በማስገባት


የተዘጋጀው አጠቃሊይ የፌዳራሌ መንግሥት የ2016 ጠቅሊሊ የወጪ በጀት ብር
801.65 ቢሉዮን ሲሆን ይህም ሇ2015 ከጸዯቀው የወጪ በጀት ጋር ሲነጻጸር የ1.9
በመቶ ዕዴገት ያሳያሌ፡፡ ከዚሁ ጠቅሊሊ የወጪ በጀት ውስጥ ሇፌዳራሌ መንግስት
ሇመዯበኛ ወጪ ብር 370.14 ቢሉዮን፣ ሇካፒታሌ ብር 203.44 ቢሉዮን እንዱሁም
ሇክሌሌ መንግሥታት ዴጋፍ ብር 214.07 ቢሉዮን እና ሇዘሊቂ የሌማት ግቦች
ማስፈጸሚያ ብር 14 ቢሉዮን ተዯግፎ የቀረበ ነው፡፡

በአጠቃሊይ ተዯግፎ ከቀረበው ጠቅሊሊ ወጪ ውስጥ ከፍተኛውን ዴርሻ የያዘው


ሇመዯበኛ ወጪ የተመዯበው ሲሆን፣ ይህም የጠቅሊሊ በጀቱ 46.2 በመቶው ነው፡፡
ይህም ሇመዯበኛ የተዯሇዯሇው በጀት ሇ2015 ከጸዯቀው መዯበኛ በጀት አንጻር የ7.25
በመቶ ብሌጫ አሇው፡፡ ከዚህ ሇመዯበኛ ከተመዯበው ወጪ በጀት ውስጥ 63.6 በመቶ
የሚሆነው ከፍተኛው ዴርሻ የተመዯበው ሇሀገር ውስጥና ሇውጭ ዕዲ ክፍያ፣
ሇማዲበሪያ ዴጎማ የበጀት ዴጋፍ፣ ሇአዯጋ መከሊከሌ እና ሇመጠባበቂያ የተዯሇዯሇ ነው፡፡
በአጠቃሊይ የ2016 የመዯበኛ በጀት በየመ/ቤቱ ያሇውን አዱሱን አዯረጃጀት ታሳቢ
በማዴረግ፣ የበጀት አጠቃቀም በቁጠባና በውጤታማነት ሊይ ያተኮረ እንዯሚሆን፣
እንዱሁም አዲዱስ የሠራተኛ ቅጥር እንዯማይኖር ታሳቢ በማዴረግ የተዘጋጀ መሆኑን
መገንዘብ ተገቢ ነው፡፡

17
የ2016 በጀት መግሇጫ (Budget Speech)

በላሊ በኩሌ ሇ2016 በጀት ዓመት ሇፌዳራሌ መንግስት የካፒታሌ በጀት የተዯሇዯሇው
ብር 203.44 ቢሉዮን በጀት የጠቅሊሊ ወጪ በጀቱ 25.4 በመቶ ሲሆን በ2015
ከተመዯበው ጋር ሲነጻጸር የ6.7 በመቶ ቅናሽ ያሳያሌ፡፡ ይህም የካፒታሌ በጀት ወጪ
አሸፋፈኑ ሲታይ ብር 146.1 ቢሉዮን ከመንግስት ግ/ቤት፣ ብር 31.6 ቢሉዮን
ከፕሮጀክቶች ዕርዲታ እንዱሁም ብር 25.7 ቢሉዮን ከፕሮጀክቶች ብዴር እንዯሚሸፈን
የተያዘ ነው፡፡ ከዚህ ሇካፒታሌ ከተመዯበው የወጪ በጀት ውስጥ 81.8 በመቶ
የሚሆነው ሇማህበራዊና ኢኮኖሚ ዘርፎች የተመዯበ በጀት ሲሆን፣ ከጠቅሊሊ ካፒታሌ
በጀት ውስጥ 68.7 በመቶ የሚሆነው የተመዯበው ቅዴሚያ ትኩረት ሇተሰጣቸው
የመንገዴ፣ የትምህርት፣ የግብርናና ገጠር ሌማት፣ የውሃና የጤና ዘርፎች ነባር
ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ ነው፡፡ እንዱሁም በጦርነቱ ምክንያት የወዯሙ ንብረቶች እና
አገሌግልት መስጫ ተቋማትን ወዯ ነበሩበት መሌሶ ሇመገንባትና ሇማቋቋም
ሇተጀመረው ፕሮጀክት ከመንግስት ግምጃ ቤት ብር 20.0 ቢሉዮን ተዯግፎ ቀርቧሌ፡፡

በተጨማሪም ሇ2016 በጀት ዓመት ሇክሌሌ መንግስታት የበጀት ዴጋፍ ብር 214.07


ቢሉዮን የተዯገፈ ሲሆን፣ ይህም ሇ2015 ተመዴቦ ከነበረው ብር 209.38 ቢሉዮን
አንጻር የ2.24 በመቶ ጭማሪ አሇው፡፡ ከዚህ ሇክሌልች ከተመዯበው በጀት ውስጥም
ከመንግስት ግምጃ ቤት የሚሸፈነው ብር 205 ቢሉዮን ነው፡፡ እንዱሁም ሇዘሊቂ
የሌማት ግቦች ማስፈጸሚያ ዴጋፍ ሇክሌልች ሇ2016 ብር 14.0 ቢሉዮን የተመዯበ
ሲሆን፣ ይህም ሇአግሮ ፕሮሰሲንግ፣ ሇስራ ዕዴሌ ፈጠራ እንዱሁም በክሌልች
ሇሚካሄደ ሇአነስተኛ እና መካከሇኛ መስኖ ሌማት ካፒታሌ ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ
የሚውሌ ነው፡፡

የተከበሩ አፈ ጉባኤ
የተከበራችሁ የምክር ቤቱ አባሊት

ከዚህ በሊይ በዝርዘር ሇማቅረብ እንዯሞከርኩት በ2016 በጀት ዓመት የፌዳራሌ


መንግስት ከሀገር ውስጥ ገቢ እና ከውጭ አገር ዕርዲታ ምንጮች በዴምሩ ብር 520.6
ቢሉዮን ገቢ ሇመሰብሰብ የሚያስችሌ ዕቅዴ ያዘጋጀ ሲሆን፣ ሇመዯበኛ፣ ሇካፒታሌ እና

18
የ2016 በጀት መግሇጫ (Budget Speech)

ሇብሔራዊ ክሌሊዊ መንግስታት የበጀት ዴጋፍና የዘሊቂ የሌማት ግቦች ማጠናከሪያ


ወጪ ጠቅሊሊ ብር 801.65 ቢሉዮን የወጪ በጀት ተዯግፎ ቀርቧሌ፡፡ በዚህም መሠረት
በታቀዯው ገቢና ወጪ መካከሌ የብር ብር 281.05 ቢሉዮን ያሌተጣራ የበጀት ጉዴሇት
(gross budget deficit) የታየ ሲሆን፣ ይህንንም የበጀት ጉዴሇት ሇመሸፈን ብር
39.01 ቢሉዮን ከውጭ ሀገር እና ብር 242.04 ቢሉዮን ከሀገር ውስጥ በዴምሩ ብር
281.05 ቢሉዮን ያሌተጣራ ብዴር (gross borrowing) በመውሰዴ ሇመሸፈን
ታቅዶሌ፡፡ የበጀት ጉዴሇቱን ሇመሸፈን ሇመበዯር ከታቀዯው ብር 281.05 ቢሉዮን
ጠቅሊሊ ያሌተጣራ የሀገር ውስጥና የውጭ ብዴር ውስጥ ብር 53.7 ቢሉዮን የሚሆነው
ተመሌሶ ሇሀገር ውስጥና ሇውጭ ዋና ብዴር ክፍያ የሚውሌ በመሆኑ የተጣራ የበጀት
ጉዴሇት (net budget deficit) መጠኑ ብር 227 ቢሉዮን ይሆናሌ፡፡ በመሆኑም
የተጣራ የበጀት ጉዴሇት መጠኑ ከአጠቃሊይ የሀገር ምርት ያሇው ዴርሻ 2.1 በመቶ
ሲሆን፣ የተጣራ የሀገር ውስጥ ብዴር ዯግሞ ከአጠቃሊይ የሀገር ምርት ያሇው ዴርሻ
2.2 በመቶ ነው፡፡ ይህም የተረጋጋ የማክሮ ኢኮኖሚ እንዱኖር ሇማዴረግ ከተያዘው
የፊሲካሌና የገንዘብ ፖሉሲ ጋር የተጣጣመ ሲሆን፣ ከዚህ ከተያዘው ጠቅሊሊ ብዴር
ውስጥ ከፍተኛው ዴርሻ የሀገር ውስጥ ብዴር ከመሆኑ አንጻር በዋጋ ንረት ሊይ የጎሊ
ተጽእኖ እንዲይፈጥር አብዛኛው ብዴር የትሬዠሪ ቢሌና የመካከሇኛ ዘመን ቦንዴ
በመሸጥ ሇመውሰዴ የታቀዯ ብዴር ነው፡፡

የተከበሩ አፈ ጉባኤ
የተከበራችሁ የምክር ቤቱ አባሊት

በአጠቃሊይ ይህ ሇ2016 ተዯግፎ የቀረበው ረቂቅ የፌዳራሌ መንግስት በጀት ካሇፉት


ዓመታት በጀት ጋር ሲነጻጸር የሌማት ፍሊጎታችንን ሇማሳካት በቂ ባይሆንም የተጀመሩ
የሌማት ፕሮጀክቶችን ሇማስጨረስ የሚበቃ ሲሆን፣ የገጠሙንን የፊሲካሌ ተግዲሮቶች
በማስተካከሌ በቀጣይ ጤናማ የፊሲካሌ አቋም እንዱኖረን ሇማዴረግ ወሳኝ መሆኑን
በመገንዘብ ሁለም የሚመሇከታቸው ባሇዴርሻ አካሊት ሇትግበራው የበኩሊቸውን ጥረት
ማዴረግ ተገቢ ይሆናሌ፡፡ ከዚህ አንጻር ባሇበጀት መ/ቤቶች አስፈሊጊውን ዝግጅት ሁለ

19
የ2016 በጀት መግሇጫ (Budget Speech)

በማዴረግ የተመዯበሊቸውን በጀት ሇታሇመሇት ዓሊማ በቁጠባና በሊቀ ውጤታማነት


ጥቅም ሊይ ማዋሌ ይጠበቅባቸዋሌ፡፡ ሇዚህም የሚጸዴቀውን በጀት የመንግስትን
የፋይናንስ፣ የግዥ እና የንብረት አስተዲዯር ህጎችን ብቻ ተከትሇው በጀቱን በቁጠባና
በውጤታማነት ስራ ሊይ ማዋሌ የሚገባቸው ሲሆን በገንዘብ ሚኒስቴር በኩሌም
አስፈሊጊው ዴጋፍ ሁለ እንዯሚዯረግ እያረጋገጥኩ፣ በጀቱ በአግባቡ ሥራ መዋለን
ሇማረጋገጥም አስፈሊጊው የክትትሌና የቁጥጥር ስራን በማጠናከር የተጀመረው
ተጠያቂነትን የማረጋገጥ እንቅስቃሴ ተጠናክሮ እንዯሚቀጥሌ ሇመግሇጽ እወዲሇሁ፡፡
በተጨማሪም ይህ የ2016 የፌዳራሌ መንግስት በጀት ተግባራዊ ሉሆን የሚችሇው
የሀገር ውስጥ ገቢ አሰባሰብ ከላሊው ጊዜ የተሇየ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት
የታቀዯውን ገቢ ስናሳካ ብቻ በመሆኑ ይህም የሁለንም ባሇዴርሻ አካሊት ርብርብ
የሚጠይቅ መሆኑን ሇማሳሰብ እፈሌጋሇሁ፡፡ ሇዚህም የተከበረው ም/ቤትም ሆነ
የሚመሇከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች የጀመሩት ዴጋፍ ተጠናክሮ ዕገዛ እንዱዯረግሌን
በአክብሮት እጠይቃሇሁ፡፡

እንዱሁም ይህ የ2016 በጀት ዓመት የፌዳራሌ መንግስት በጀት በተሳካ ሁኔታ


ተግባራዊ እንዱሆን እየተመኘሁ፣ የበጀት ዝግጅቱ የተሳካ እንዱሆን የበጀት
ጥያቄያቸውን በተቀመጠው የጊዜ ሰላዲና በተዘጋጀው የበጀት ሥርዓት መሰረት ሊቀረቡ
አስፈጻሚ አካሊት፣ በረቂቅ በጀቱ ሊይ ሰፊ ውይይት በማካሄዴና በመዯገፍ የሚኒስትሮች
ምክር ቤት ወቅቱን ጠብቆ ሇዚህ ምክር ቤት እንዱቀርብ በማዴረጉ እንዱሁም የመገናኛ
ብዘኃን ተቋማት የበጀት መረጃዎችን ሇሕዝብ በማስተሊሇፍ ሊዯረጉት አስተዋጽኦ
በመ/ቤቴ ስም ሊመሰግን እወዲሇሁ፡፡

በመጨረሻም ይህን ተዯግፎ የቀረበውን የ2016 በጀት ዓመት የፌዳራሌ መንግስት


በጀት የተከበረው ምክር ቤት እንዱያፀዴቀው በአክብሮት እጠይቃሇሁ፡፡

አመሰግናሇሁ፡፡

20

You might also like