You are on page 1of 4

ማህበራችን የኢትዮጵያ አይ.ኤፍ.አር.ኤስ.

የሂሳብ ባለሙያዎች ማህበር


ለሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ በመዝገብ ቁጥር 5074 ተመዝግቦ
የሚንቀሳቀስ ሲሆን ከዚህ በታች የተቀመጡት እና ህገራችን ኢትዮጵያ አንድ
ወጥ የሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያለውን ዘመናዊውን የሂሳብ
አያያዝ እና ወደስቶክ ገበያው መግባት እንድትችል በአይ.ኤፍ.አር.ኤስ
የሰለጠኑ የሂሳብ ባለሙያዎችን አባል በማድረግ ዘመናዊው አሰራር መተግበር
እንዲችል ባለሙያዎች በብዛት እንዲኖሩ ማድረግና ስልጠናዎችን ለአባላቱ
መስጠት ዋና ተግባሩ አድርጎ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል ። ለማፍራት እንዲች
ለማህበሩ ዓላማ መሳካት ሌት ተቀን የሚጥሩ በትምህርት ብቃታቸው
በፋናንሻል ኢንጂነሪንግ ማስተር ያላቸው እንዲሁም ዶክተሬት ዲግሪ ያካቸው
አሁንም በማስተማር ያሉ የማህበሩ አባላቶች ይገኛሉ ።
መስከረም 2015
ለሪፖርት አቅራቢ አካላት በሙሉ ጉዳዩ፡ የሪፖርት ማቅረቢያ ጊዜ እና የሪፖርት
አቅራቢዎች መለያ መስፈርት ስለመሻሻሉ መንግስት ከፍተኛ የጥራት ደረጃ ያለው የፋይናንስ
ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ ሥርዓት በመዘርጋት የተመቸ የንግድ አና የኢንቨስትመንት
ከባቢ በመፍጠር ኢንቨስትመንትን ለማበረታታት የሚኖረውን ከፍተኛ ጠቀሜታ፣ እንዱሁም
የተጠናከረ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ሙያ የኢኮኖሚ ዕድገቱን ለመደገፍ፣ ለማበረታታት እና
ለማረጋጋት የሚጫወተውን ቁልፍ ሚና በመገንዘብ በሀገር ውስጥ በሚገኙ በግል እና
በመንግስት ዘርፍ ባሉ ድርጅቶች ላይ ተፈፃሚ የሚሆን የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀት እና
አቀራረብ ሥርዓት መዘርጋት አስፈላጊ ሆኖ ስላገኘዉ አዋጅ ቁጥር 847/2006 ን እና
አዋጁንም ለማስፈፀም “የኢትዮጵያ የሂሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ” ማቋቋሚያ ሥልጣን እና
ተግባሩን መወሰኛ የሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ቁጥር 332/2007 ን አውጥቷል።

በአዋጁ አንቀፅ 5/1 ላይ ተፈጻሚነት የሚኖራቸዉ የፋይናንስ ሪፖርት ደረጃዎች በማለት


ዓለም አቀፉ የሂሳብ አያያዝ ደረጃዎች ቦርድ ያወጣቸዉን፡
ሀ/ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት አዘገጃጀት እና አቀራረብ ደረጃዎች፣

ለ/ ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት አቀራረብ ደረጃዎች ለአነስተኛ እና መካከለኛ ድርጅቶች


እና ሐ/ ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ማህበራት ዓለምአቀፍ የፐብሊክ ሴክተር የፋይናንስ
ሪፖርት አዘገጃጀትና አቀራረብ ደረጃዎችን እንዲተገብሩ ተደንግጓል፡፡
በአዋጁ አንቀጽ 4/2/መ/ ቦርዱ ሪፖርት አቅራቢ አካላትን የህዝብ ጥቅም ያለባቸዉ አካላት
ወይም አነስተኛ እና መካከለኛ ድርጅቶች ብሎ መለየት የሚያስችል መስፈርት እንደሚያወጣ
እና በአዋጁ አንቀጽ 8/1 ማንኛዉም ሪፖርት አቅራቢ አካል ቦርዱ በሚያወጣዉ የጊዜ ሰሌዳ
መሰረት ሪፖርቱን ለቦርዱ ማቅረብ አንዳለበት ተደንግጓል። በዚሁ መሰረት ቦርዱ የአምሰት
ዓመት ስተራቴጂክ እቅድ ላይ የትግበራ ጊዜ እና የሪፖርት አቅራቢ አካላት መለያ መሰፈርት
አዘጋጅቶ የደረጃዎቹን ትግበራ ክትትል ሲያደርግ ቆይቷል። ሆኖም ግን በቦርዱ እና በሪፖርት
አቅራቢዎች በተከሰቱ ዉስጣዊ እና ዉጫዊ ምክንያቶች አፈፃፀሙ ዝቅተኛ ሆኖ በመገኘቱ
ቦርዱ የሪፖርት ማቅረቢያ ጊዜዉን እና የመለያ መስፈርቶቹን እንደሚከተለዉ አሻሽሏል። ይህ
ማሻሻያ የሚያገለግለዉ አስከ አሁን የትግበራ ሥራ ላልጀመሩ ሪፖርት አቅራቢዎች ሲሆን
ያለፈውን የትግበራ ጊዜ ጠብቀው ሪፖርታቸዉን ለቦርዱ ያቀረቡትን ወይም ለማቅረብ በሂደት
ላይ ያሉትን በዚህ አጋጣሚ እያመሰገንን የተሻሻለዉ የትግበራ ጊዜ የማይመለከታቸዉ መሆኑን
እየገለጽን የሪፖርት ማቅረቢያ ጊዜውና የመጠን መለያ መስፈርቶቹ እንደሚከተለው
ቀርበዋል፡፡
1. የሪፖርት ማቅረቢያ ጊዜ o እስከ 2015 ዓ.ም/ እ.ኤ.አ 2023/ ሙሉ ደረጃዎችን /full
IFRS/ የሚተገብሩ፡
 ከፍተኛ የህዝብ ጥቅም ያለባቸዉ (Significant PIEs)፣
 ሌሎች የህዝብ ጥቅም ያለባቸዉ (Other PIEs) ሲሆኑ፣ o አስከ 2016 ዓ.ም
/እ.ኤ.አ 2024/
 አነስተኛ እና መካከለኛ ድርጅቶች /IFRS for SMEs/ ደረጃዎችን እና
 የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና ማህበራት /IPSASs/ የሚተገብሩ ሆኖ
2. የመጠን መለያ መስፈርት o ከፍተኛ የህዝብ ጥቅም ያለባቸው
ሀ. የሚያወጡትን የግዴታ የምስክር ወረቀት /Debt or equity/ ቍጥጥር
በሚደረግበት ሥርዓት ዉስጥ ለግብይት ያዋለ/ለማዋል በዝግጅት ላይ ያለ ማንኛዉም
ኩባንያ፣
ለ. ባንኮች፣ ኢንሹራንሶች እና ሌሎች የፋይናንስ ተቋማት፣
ሐ. በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ በመንግስት ቁጥጥር ስር ያሉ የልማት ድርጅቶች፣
መ. የአክሲዮን ኩባንያዎች፣
ሠ. በሚመለከተዉ የመንግስት አካል ቁጥጥር የሚደረግበት የጡረታ፡ የፕሮቪደንት
ፈንድ እና ተመሳሳይ ተቋም፣
ረ. የህብረት ሥራ ዩኒየኖች፣ ሰ. ቁጥጥር የሚደረግባቸዉ የሸማቾች ማህበራት፣
ሸ. በሚመለከተዉ አካል ቁጥጥር የሚደረግባቸዉ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች እና
ማህበራት፣ እና
ቀ. የኢትዮዽያ የምርት ገበያ አባላት ናቸው፡፡
o ሌሎች የህዝብ ጥቅም ያለባቸዉ ድርጅቶች
 ዓመታዊ ሽያጭ፡- 300 ሚሊዮን ብር እና ከዚያ በላይ፣
 ጠቅላላ ሀብት/ንብረት፡- 200 ሚሊዮን ብር እና ከዚያ በላይ፣
 ጠቅላላ ዕዳ፡- 200 ሚሊዮን ብር እና ከዚያ በላይ፣ እንዲሁም
 የሠራተኛ ቍጥር ፡- 200 እና ከዚያ በላይ ያላቸው ሆኖ ከአራቱ መስፈርቶች ሁለቱን
የሚያሟሉ
o አነስተኛ እና መካከለኛ ድርጅቶች
 ዓመታዊ ገቢ/ሽያጭ፡- ከ 20 ሚሊዮን ብር እስከ 300 ሚሊዮን ብር፣
 ጠቅላላ ሀብት/ንብረት፡- ከ 20 ሚሊዮን ብር እስከ 200 ሚሊዮን ብር፣
 ጠቅላላ ዕዳ፡– ከ 20 ሚሊዮን ብር እስከ 200 ሚሊዮን ብር እና
 የሠራተኛ ቁጥር፡- ከ 20-200 ሠራተኛ ያላቸው ሆኖ ከአራቱ ሁለቱን መስፈርቶች
የሚያሟሉ ለአነስተኛ እና መካከለኛ ድርጀቶች የሚያገለግለ ዉን /IFRS for SMEs/
ይከተላሉ። 3. ማንኛውም ኩባንያ
ሀ. በተ.ቁ 2.1 ላይ ለሌሎች የህዝብ ጥቅም ያለባቸዉ ድርጅቶች የተቀመጡ የመጠን
መለያዎችን የማያሟላ ከሆነ፡
ለ. እዳዉን/የአክሲዮን ድርሻዉን ቁጥጥር በሚደረግበት የካፒታል ገበያ ላይ
ያላዋለ/ለማዋል በዝግጅት ላይ ያልሆነ፣
ሐ. የብዙ ሰዎችን ሀብት/ንብረት የማስተዳደር ኃላፊነት የሌለበት ከሆነ /IFRS for
SMEs/ን የሚተገብር መሆኑን እንገልፃለን፡፡

ከሰላምታ ጋር

ማህበሩ

You might also like