You are on page 1of 5

ቤተሰብ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ

የተወሰነ መሠረታዊ የኀብረት ሥራ


ማህበር፤

የሁለተኛው የሩብ ዓመት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት

የካቲት 28 ቀን 2015 ዓ/ም


በሁለተኛው ሩብ ዓመት ማለትም ከህዳር 1 ቀን 2015 ዓ/ም እስከ ጥር 30 ቀን 2015 ዓ/ም
ያለውን የአባላት ሁኔታ፤ የተለያዩ የቁጠባ መጠን፤ የዕጣ (የሼር) ሁኔታ ለባለፉት ሦስት
ወራቶች (ሁለተኛው ሩብ ዓመት) እንዲሁም የግማሽ ዓመቱን አጠቃላይ የሥራ እንቅስቃሴ
አፈፃፀምን የያዘ ሪፖርት ሲሆን፤ በሪፖርቱም ውስጥ ዋና ዋና የተሠሩ እና ያልተሠሩ
(መሠራት ያለባቸው) ሥራዎች በዝርዝር ተካተዋል፡፡

ከኀብረት ሥራ ማህበራት መሠረታዊ ሃሣብ ውስጥ ዋነኛውና ቀዳሚው የሰው ኃይል ልማት
(Social Capital) ሲሆን፤ ይህውም ዝቅተኛውን እና መካከለኛውን የማህበረሰብ ክፍል
በማሳተፍ፤ ያላቸውን ክህሎት በመለየት፤ መርዳት፤ መደገፍ፤ ማሠልጠን እራሣቸውንና
ቤተሰባቸውን አሻሽለው፤ ለሃገር ለወገን የሚጠቅሙ ዜጎች እንዲሆኑ ማስቻል በመሆኑ፤ በቂ
የሰው ኃይል ሲኖረን ቁጠባችን ያድጋል፤ የምንሰጠው አገልግሎት ይሰፋል፤ ለአባሎቻችን በበቂ
ሁኔታ ያለባቸውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን መፍታት እንችላለን፡፡

ስለሆነም በምሥረታችን ወቅት ከመዘገብናቸው 310 አባላት፤ 151 አባላት ብቻ መስፈርቱን


በማሟላት የጀመርነው የኀብረት ሥራ ማህበራችን፤ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት አስር (10)
አባላትን፤ በሁለተኛው ሩብ ዓመት አስራ አራት (14) አባላትን በመጨመር፤ በአሁኑ ሠዓት
መረጃቸው (ዳታቸው) ሙሉ በሙሉ የተመዘገበ አጠቃላይ 175 አባላት ሲኖሩን፤ ከነሱም
ውስጥ 121 አባላት ክፍያቸውን በተለያየ ደረጃ የከፈሉ ሲሆኑ የቀሩት 54 አባላት መረጃቸው
(ዳታቸው) በሚገባ ተሟልቶ ምንም ዓይነት ክፍያ ያልጀመሩ አባላት ናቸው፤ በበጀት ዓመቱ
2015 ዓ/ም እናሣካዋለን ካልነው የአባላት ብዛት፤ በባለፉት ስድስት ወራቶች ከመቶ 7.74%
ብቻ ያሣካን ሲሆን፤ ይህም መረጃ የሚያሣየን አባላትን በሚመለከት ዝቅተኛ የሥራ አፈፃፀም
እንዳለን ይህውም በሚቀጥሉት ወራቶች አባላትን በማሰባሰብ ዙሪያ ሰፊ ሥራ መስራት
ያመላክተናል፡፡

75 ዕጣዎች (ሼሮች) በመጀመሪያው ሩብ ዓመት፤ 162 ዕጣዎች (ሼሮች) በሁለተኛው ሩብ


ዓመት አጠቃላይ በግማሽ ዓመቱ የተሸጠ የዕጣ (የሼር) ብዛት 237 ሲሆን፤ ከመጀመሪያው ሩብ
ዓመት የተሻለ የሼር ሽያጭ አፈፃፀም በሁለተኛው ሩብ ዓመት የታየበት መሆኑን ያሣየናል፤
በበጀት ዓመቱ በ2015 ዓ/ም ለአባሎቻችን በጠቅላላ ጉባዔው ያቀረብነው አጠቃላይ የዕጣ (የሼር)
መጠን 5000 ሆኖ ለእያንዳንዱ አባል እስከ 20 ዕጣ (ሼር) ሲሆን በግማሽ ዓመት ውስጥ
ከመቶ 4.74% ዕጣዎችን ብቻ የሸጥን ሲሆን ቀሪ ከመቶ 95.26% ወይንም 4,763 ዕጣዎች
በያዝነው በጀት ዓመት ያልተሸጡ መሆናቸውን ሪፖርቱ ያሣየናል፡፡
በሁለተኛው ሩብ ዓመት ከኀብረት ሥራ ማህበሩ ብር 50,000.00 ለስራ ማስኬጃ እና ለተለያዩ
ጉዳዮች ወጪ ያደረግን ሲሆን (ዝርዝር በቃለ ጉባዔ ቀርቧል)፤ ከአዲስ እና ከነባሩ አባላት
ከተለያዩ ቁጠባዎች፤ ከዕጣ፤ ከባንክ ወለድ እና ከመመዝገቢያ ከባለፉት ሦስት ወራቶች
(ከሁለተኛው ሩብ ዓመት) አጠቃላይ ብር 309,333.09 የገባ ሲሆን ከባለፉት ስድስት ወራቶች
አጠቃላይ ብር 551,333.10 ወደ ማህበሩ ገቢ ሆኑዋል፤ በሁለተኛው ሩብ ዓመት ከተሠሩ ዋና
ዋና ሥራዎች መካከል፡ -

 ቋሚ የቢሮ ዕቃዎች እና በቢሮ ውስጥ ሥራዎችን ለመሥራት የሚያስፈልጉ መሠረታዊ


አላቂ ዕቃዎችን የማሟላት ሥራ፤
 ለጉለሌ ክፍለ ከተማ ኀብረት ሥራ ጽ/ቤት፤ የቀሩና ማሟላት የሚገቡን ዶክመንቶች
የማሟላት ሥራ፤
 ለቅጥር ሠራተኞች ውል በማዘጋጀት ማዋዋል በተጨማሪም የደሞዝ ክፍያ ፔሮል
ተዘጋጅቶ ወደ ስራ ገብቷል፤
 ለሥራው የሚያገለግሉ የተለያዩ ፎርሞችንና ደረሠኞችን በማዘጋጀት ወደ ሥራ
አስገብተናል ለምሣሌ፡ - የዕቃ ግዢ ማዘዣ ፎርም፤ ያለደረሠኝ ለሚገዙ ዕቃዎች ደረሠኝ፤
የጥቃቅን ክፍያ ፎርሞች፤ ያለደረሠኝ ለሚገዙ ዕቃዎችና አገልግሎቶች የሚያገለግል
ፎርሞች ወዘተ…
 ለአዳዲስ አባላት የሚያገለግል የተለያዩ የማንቂያ መልዕክት ያላቸው የህትመት ውጤቶችን
በማሣተም፤ በተመረጡ ቦታዎች ኀብረት ሥራ ማህበሩን የማስተዋወቅ ሥራ ተሠርቷል፤
 ኮሚሽንን በተመለከተ፤ መደበኛ አባል ሆኖ 10 አዳዲስ አባል ለሚያመጣ፤ ካመጣቸው
አባላት ከመመዝገቢያቸው 10% ወይንም ብር 1,000.00፤ አባል ያልሆነ ከሆነ
ከሚያመጣቸው አዳዲስ አባላት ከእያንዳንዱ 20% ማለትም ብር 200.00፤ ከኀብረት ሥራ
ማህበሩ ጋራ በጋር ለመሥራት የሚያስቡ ድርጅቶች፤ ባንኮች ወዘተ… ለሚያመጣ
ማንኛውም አባል 20%፤ በስጦታ ወይንም በጥሬ ዕቃም ከተነኘ የመጣው ስጦታ ወይንም
ጥሬ ዕቃ ወደ ገንዘብ ተገምቶ 20% የኮሚሽን ክፍያ እንደሚያገኝ ቦርዱ ወስኖ ወደ ሥራ
ተገብቷል፤
 እስፖንሰሮችን በተመለከተ ከባለ ፀጋዎች፤ ከሃብታሞች ወይንም ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር
የውይይት መድረክ በማመቻቸት፤ ጥሩ ዶክመንታሪ በድምፅ እና በቪዲዮ ወዘተ…
ለማዘጋጀት ዝርዝር የፕሮግራሙ አፈፃፀም ተቀርጿል፤
በሁለተኛው ዕሩብ ዓመት ያልተሠሩና መሠራት የነበረባቸው ዋና ዋና ሥራዎች መካከል፡ -

 ክፍለ ከተማው በሚያዘን መሠረት የሂሣብ አያያዛችንን በሂሳብ ሌጀሩ ላይ ማስጀመር፤


 ለሚከፈሉ ማናቸውም ክፍያዎች፤ ለሚገዙ ማናቸውም ዕቃዎችና አገልግሎቶች፤
(በስጦታም ሆነ በተለያዩ ሁኔታ ገቢ የተደረጉ ዕቃዎችና አገልግሎቶች) ለኀብረት ሥራ
ማህበራችን ወሣኝ መረጃዎች በመሆናቸው በጥንቃቄ በመመዝገብ፤ በዶክመንት የማስቀመጥ
ሥራዎች፤
 የኀብረት ሥራ ማህበሩን ንብረቶች (በስጦታም የተገኙትን) በተገቢው ሁኔታ፤ በክፍለ
ከተማው ወይንም በኀብረት ሥራ ማህበሩ ፎርም ላይ የመመዝገብ ሥራዎች፤
 የተሞክሮ ልውውጥን ከተመሣሣይ የገንዘብ ቁጠባና ብድር የኀብረት ሥራ ማህበራት ልምድ
የመውሰድ ሥራዎች፤
 የኀብረት ሥራ ማህበሩን የኮሚሽን ህግን ወይንም መተግበሪያ ሰነዱን በማዘጋጀት፤
በፊርማችን የማፀደቅ ሥራዎች፤
 የኮሚሽን ሠራተኞችን በተመለከተ አዳዲስ አባላትን ወደ ኀብረት ስራ ማህበሩ እንዲያመጡ፤
ያላቸውን ፕሮፖዛል እንዲያቀርቡ በማድረግ ለውይይት እንዲቀርብ መሥራት፤
 የውጪው የቤተሰብ ማስታወቂያ አሁን ያለውን በማሻሻል ወይንም በሚያመች ሁኔታ
ከህንፃው አስተዳደር ጋር በመነጋገር እንዲለጠፍ መስራት፤
 የኅብረት ሥራ ማህበሩን ድህረ-ገጽ (Website)፤ ቴሌግራም (Telegram)፤ በራሪ ወረቀቶች
እና ፌስ-ቡክ (Facebook) የማህበራዊ ሚዲያዎችን በስፋት በማስተዋወቅ፤ ለአዳዲስ
አባላትና ነባሩ አባል የተለያዩ መረጃዎችን እንዲያገኙና መረጃዎችን እንዲለዋወጡ የማድረግ
ሥራ መስራት፤
 የገንዘብ አያያዝንና አጠቃቀምን፤ ፒቲ ካሽ (ቦርዱ የወሰነውን 5,000.00 ብር) አተገባበርን
በተመለከተ መስራት፤
 የተለያዩ አገልግሎቶችን መጠየቅ የሚያስችሉ ፎርሞችን፤ አባላቱ የተለያዩ አገልግሎቶችን
የሚያገኙበትን ሁኔታ ማመቻቸት፤ ለምሣሌ ብድር ለሚጠይቅ፤ ለፍላጎት ቁጠባ፤ ለወለድ
አልባ ቁጠባ ወዘተ… ማዘጋጀት፤
 አዲስ አባላትን ለሚያመጡ፤ ለተለያዩ የቁጠባ ዓይነቶች፤ የብድር ታሪኮች ወዘተ…
የሚመዘገቡበት የአባላት ሌጀር ወይንም መረጃ ወይንም ፕሮፋይል፤ ለነባር የኀብረት ሥራ
ማህበሩ አባላት የመመዝገብ፤ በቋት ውስጥ የማስቀመጥ ሥርዓትን መዘርጋት፤
 በዓመቱ ምን ያህል አባላት እንዲኖሩን፤ ቁጠባችንን፤ የምናበድረውን ብድር ወዘተ…
በሚመለከት ዝርዝር ዕቅድ ማዘጋጀት፤
 የኀብረት ሥራ ማህበሩ ያለበትን የመስራት አባላት (የግለሰብ) ዕዳዎችን በመለየት፤
ማሣወቅ፤ ማወቅ፤ ወደ ዕጣ (ሼር) የሚቀየሩ ካሉም በህጉና ደንቡ መሠረት የመተግበር
ሥራዎች፤

ዋና ዋናዎቹ ሲሆኑ፤ በመጪው ወራቶች ወይንም በሦስተኛው ሩብ ዓመት ከላይ የተዘረዘሩት


ያልተሠሩ ሥራዎች ላይ ትኩረት አድርገን መሥራት ከሁሉም የሥራ አስፈፃሚ የቦርድ አባል
ይጠበቃል፡፡ በተጨማሪም የኀብረት ሥራ ማህበሩን ከጀመርን አሁን የያዝነው ወር ሰባተኛ
እንደመሆኑ ከአባላት ለሚነሱ የብድር ጥያቄዎች ተመጣጣኝ ምላሽ የምንሰጥበት፤ መጠነኛም
ቢሆን የሰበሰብነውን ገንዘብ ለአባላት መልሰን የምንሸጥበት፤ በብዛት አዳዲስ አባላት
የምንመዘግብበት፤ መረጃቸውን (ዳታቸው) በሚገባ አሟልተው ነገር ግን ምንም ዓይነት ክፍያ
ያልጀመሩትን 54 አባላትን ወደ ክፍያ የምናስገባበት፤ ለአባላት እንደየ ሙያቸው ውጤት ተኮር
ሥልጠናዎችን የምንሰጥበት፤ ኀብረት ሥራ ማህበሩን ለአባላትና ለተለያዩ ድርጅቶች በስፋት
የምናስተዋውቅበት፤ ለአባሉ የኀብረት ሥራ ማህበሩን ዓላማዎች ደንቦች እና መመሪያዎች
በሚገባ የምናስተምርበት፤ የአባሉን የመቆጠብ የማደግና የመበልፀግ ሞራል የምንገነባበት፤
የእስፖንሰሮችንና አብረውን የሚሰሩ ድርጅቶችን በመለየት፤ አክሲዮኖችን በመሸጥ ወደ ኀብረት
ሥራ ማህበሩ የምናመጣበት፤ በስፋት የልምድ ተሞክሮ ልውውጦችን የምናደርግበት፤ የውስጥ
አሠራሮቻችንን ከምናገኘው የልምድ ተሞክሮ በመነሣት የምናዘምንበት እና በአሁን ሠዓት
ያለውን የአባላት የሥራ አስፈፃሚና የቦርድ መቀዛቀዝ እንደ አጀማመራችን የምንነቃቃበት
እንዲሆን ለሁሉም አባል ጥሪ አቀርባለሁ፡፡

በመጨረሻም ከኦሮሚያ የኀብረት ሥራ ባንክ ጋር የተጀመርነው የገንዘብ ቁጠባና ብድር


ኦንላይን ሥርዓት (Sacco Link CPO) ሲስተም፤ በሁሉም የሃገሪቱ የገንዘብ ቁጠባና ብድር
ማህበራትን ያቀፈና ዘመናዊ ሥርዓትን የመዘርጋት አካሄድ በመሆኑ ባንኩን በኀብረት ሥራ
ማህበሩ ስም እያመሠገንኩ፤ ከዚህ በፊት የተለያዩ የውጪ ድርጅቶች ጀምረውት ነገር ግን
መጨረስ ያልቻሉትን፤ ባንኩ ትልቅ ገንዘብ በመመደብ ለማህበራቱ ትልቅ ዓቅምና ቀላል የሆነ
የብድርና የቁጠባ ሥርዓትን በኦንላይን እየሰጠ ይገኛል፤ በሚቀጥለው ሦስተኛው ሩብ ዓመት
ሪፖርት ላይ በዝርዝር የሚቀርብ ይሆናል፡፡

You might also like