You are on page 1of 8

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

"ወንድሞች በኀብረት ቢቀመጡ እነሆ መልካም ነዉ እነሆም ያማረ ነዉ፡፡" መዝ.ዳ 132፡1
መግቢያ

በእግዚአብሔር ፍቃድ፤ በአባቶች ትጋትና በጎ ተነሳሽነት በ 1984 ዓ/ም የተመሰረተዉ ማህበረ ቅዱሳን በአገር ዉስጥና ከአገር
ዉጭ ለቅድስት ቤቲ/ያናችን የተለያዩ መንፈሳዊ አገልግሎቶችን ሲያከናወን መቆየቱ ይታወቃል፡፡በዚሁ መሠረት ማህበሩ በሥሩ
ከሚያቅፋቸዉ መንፈሳዊ አገልግሎት ክፍሎች መካከል አንዱ የሂሳብና ክዋኔ ኦዲት ክፍል ሆኖ በዉስጡ ሁለት ጉዳዮችን
ይዟል፡፡የመጀመሪያዉ የሂሳብ ኦዲት/Finace audit/- የሂሳብ ሥራዎችን ኦዲት የሚያደርግ ሲሆን ሁለተኛዉ ደግሞ ክዋኔ
ኦዲት/Performance audit/ -ጠቅላላ የማዕከሉ አገልግሎት ክፍሎች ሥራዎች በቅዱስ ስኖዶስ በፀደቀዉ መተዳደሪያ ደንብና
መመሪያ መሠረት መከናወኑን የሚያረጋግጥ እና በተጨማሪ ማንኛዉም በማዕከሉ አገልግሎት ላይ የሚታዩ ክፍተቶች
እንድስተካከል የመንፈሳዊ ሙያና ምክር አገልግሎት የሚሰጥ ነጻና ገለልተኛ ክፍል ነዉ፡፡ይህ በእንድእንዳለ የኢ /ኦ/ተ/ቤቲ/ያ
ሴ/ት/ቤቶች/ማ/መምሪያ ማህበረ ቅዱሳን ጂንካ ማዕከል በ 2014 ዓ/ም የማዕከሉ ምስረታ 20 ኛ ዓመት ጠቅላላ ጉባኤ የቀረበ
የኦዲት ሪፖርት በየክፍላት ከዚህ በታች እንደሚከተለዉ ይሆናል፡፡

1/ በጽ/ቤት አገልግሎት ክፍል የተሰሩ ሥራዎችን በተመለከተ፡-

 የማዕከሉ ሥራዎችን በተገቢ እንድሰራ ክትትል የማድረግ ሥራ ተሰርቷል


 በየሳምንቱ ዕሮቡ ከ 11፡30-1፡00 ድረስ የሥራ አስፈጻሚ ዉይይት የተደረገ ቢሆንም ቀደም ተብሎ በጽ /ቤት
በኩል/ሰብሳቢ፤ፀሐፊና ም/ሰብሳቢ/ሆኖ በአንድነት ተወያይቶ አጀንዳ የሚያቀርቡበት ጊዜ ትንሽ መሆኑን፤
 ጽ/ቤት በ 2014 ዓ.ም በጠቅላላ ጉባኤ አጀንዳ አስይዞ ካስወሰነው ውሳኔ አንፃር የጽ /ቤት ግንባታ ኮሚቴው ወደ ሥራ
በማስገባት አባላት በወሰኑት መሠረት የወር ደመወዝ በአንድ ዓመት ክፊያ እንዲጀምሩ አድርጓል፡፡
 ለአዳዲስ አባላትና ለነባሪ አባላት በተለያዩ ጊዜ ከሰዉ ሀብት ጋር በመሆን ስልጠና ሰጥቷል፤
 አዳድስ አባላት ወደ ተለያዪ ንዑስ ሥራ ክፍል ምደባ ስሰጥ የሥራ ተግባራትን እንድያዉቁ ተደርጓል፤
 ጽ/ቤቱ በተለያዩ ጊዜ ከባለድርሻ አካለት ጋር ዉይይት ያደረገ ቢሆንም ከአጋር አካላት ጋር ያን ያህል ዉይይት
እንዳልተደረገ ለመገንዘብ ተችሏል፡፡
 ከዋና ማዕከልና ከማስተባበሪያ የሚላኩ ደብዳቤዎች ተቀብሎ ምላሽ የመስጠት ስራ ተሰርቷል፤
 በወረዳ ማዕከላት የህዝብ ጉባኤ ስካሄድ ማህበሩ ተጋብዞ ስብከተወንጌል መምህራንን በመመደብ ጉባኤዉ በጥሩ ሁኔታ
እንድያልፍ ተደርጓል፤
 ዋና ማዕከልና ማስተባበሪ ማዕከል ባዘጋጀዉ ስልጠናም ሆነ የጋራ ዉይይት ላይ አባላቱ
እንድሳተፍ የማስተባበሪ ስራ ሰርቷል፡፡
 በዚህ 2014 ዓ.ም ጽ/ቤቱ ከፍተኛ ድጋፍ በማድረግ አምስት የአብያተ ክርስቲያናት እና ሁለት የአብነት
ት/ቤቶች ግንባታ አጠናቆ እንዲመረቁ አድርጓል፡፡
ክፍሉ አጠቃላይ ከዕቅዱ አንፃር ያከናወነው ሲታይ -------- ፐርሰንት ነው
2/ በትምህርተ ወንገልና ሐዋሪያዊ አገልግሎት ክፍል የተሰሩ ሥራዎችን በተመለከተ፡-

በዋና ማዕከል በጀት ድጋፍ ስብከተ ወንገል ባልተስፋፉ አከባቢዎች ወንገለ ሰባኪያን በድጎማ እንድሰሩ በተላለፈዉ
መሠረት ኦሞራቴ፤ጋዘር፤ገሊላናማሌ ወ/ ማዕከል በየወሩ ብር ወጪ እየተደረገ ስብከተ ወንጌልን
የማስፋፋት እና በቁጥር ወ ሴ ድ ኢ-ምዕመናን ወደ እናት ቤቲ/ያ እንድቀላቀሉ ተደርጓል፤ ከመናፍቅነት
የተመለሱ ------------------ ፣አእስልምና የተመለሱ ----------------------
በስብከተ ወንጌል ሲገነቡ የነበሩ አምስት አቢያተ ክርስቲያናት በዚህ ዓመት ተጠናቀው ተመርቀዋል፡፡
(አጆ፣ጎልዲያ፣ጋንችሬ፣ ይርጋ እና ካፑሲያ)
የጎሳ መሪዎች ስልጠና በማሌ ----- እና በዳሰነች ------- የጎሳ መሪዎች ስልጠና እንዲያገኙ በማድረግ በአከባቢው
ስብከተ ወንጌል እንዲስፋፋ ከፍተኛ አስተዋጽ አድርጓል፡፡
በዚህ 2014 ዓ.ም ክፍሉ በስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ አምስት የአብያተ
ክርስቲያናት ግንባታ --------------------- ብር ወጪ የተደረገባቸው ተጠናቀው እንዲመረቁ አድርጓል፡፡ለእነዘህ
አብያተ ክርስቲያናት ለአንድ አመት የአንድ ካህን ደመወዝ በጅቶ እየሰራ ይገኛል፡፡

3/ የልማት ዕቅድ አገልግሎት ክፍል የተሰሩ ሥራዎችን በተመለከተ፡-

 የ 2014 የማዕከሉ ዕቅድ በስትራቴጅክ ዕቅድ መሠረት የተዘጋጀ ቢሆንም ለሚመለከታቸዉ አካትላ በወቅቱ
ያለማስተላለም፤
 ክፍሉ በየሩበረ ዓመት የክፍላት ዕቅድ ክንዉንን የመገምገም ሥራ ወቅቱን ጠብቆ በተደራጀ መልኩ አልተከናወነም፤
 የክፍላትን በዕቅዳቸው መሠረት ሥራዎችን እየመሩ መሆኑን ተገቢው ክትትል አልተደረገም ይህም በጽ/ቤት ላይ
ተጨማሪ ጫና ፈጥሯል፡፡
 ክፍሉ የ 2014 ዕቅድ ክንዉንን እና የ 2015 ዕቅድን የማዘጋጀት ሥራ ተሰርቷል፡፡

4/ የሰዉ ሀብት ልማትናስልጠና አገልግሎት ክፍል የተሰሩ ሥራዎችን በተመለከተ፡-

 በተለያዩ ጊዜ ለአባለት ስልጠና ተስጥቷል፡፡ በዚሁ መሠረት ሰልጠና የተሰጠባቸዉ ርዕሶች


 መንፈሳዊ የአግልግሎት ምንነትና አስፈላጊነት
 መንፈሳዊ አግልግሎትን መመዘን
 መንፈሳዊነት እና መንፈሳዊ ህይወት
 አባልና አባልነት/ ለአዳደስ አባላት/
 የአገልግሎት ክፍላት ተግባራት ለአጠቃላይ አባልና ለየክፍላት
 የቤተሰብ መዋቅር
 የእግዚአብሔር ሀሳብ ማገልገልና የአገልግሎት ምንነት
 የኦርቶዶክሳዊነት ዉጊያዎች መግለጫ
 ማህበራዊ ሚዲያ ለቤቲ/ያንና ለንባብ
 የወጣቶች ሁለንተናዊ የመሪነት ሚና ለምን አስፈለገ /ለማዕከሉ፤ለወረዳ ማዕከልና ለሴ/ት/ቤት/
 ወቅታዊ የቤቲ/ያን ችግር/ለማዕከሉና ለወረዳ ማዕከላት/
 ስልታዊ ዕቅድ አተገባበሪ/ለማዕከሉና ለወረዳ ማዕከላት/
ስለማህበሩ አመጣጥ፤ትላንት ምን ሰራ፤ዛሬ ምን እየሰራ ነዉ እና ለነጌ ምን እንዳቀደ/ ለአዳድስ
አአባላት/ የተሰጠ ሲሆን አብዘኛዉ ስልጠና በማዕከላት ላይ ያዘናበለ ስለሆነ በቀጣይ ለወረዳ
ማዕከላትና ግንኙነት ጣቢያ ትኩረት ብደረግ እንላለን፡፡

 የሰዉ ሀብት መረጃና ማደራጀት አገ/ት ንዑስ ክፍል፡-


 ይህ ክፍሉ የአባላት መመዝገቢያ ቅጽና መከታተያ ደብተር በማዘጋጀት በየመርሃ- ግብራት አባላትን
ክትትልና ቁጥጥር አድርጓል፤
 ለአባላት የቤተሰብ መዋቅርን በማቋቋም በጂንካ ዙሪያ ወረዳ ማዕከል ክትትል ተደርጓል፤
 የወረዳ ማዕከላትና ግንኙነት ጣቢያዎችን በመከታተል የአድስና ነባሪ አባላት መረጃ እንድደራጅ
ተደርጓል

ተ/ቁ ማዕከል/የወረዳ ማዕከል የአባላት ብዛት ድምር ወርሃዊ የማይከፍል


ስም ነባሪ አድስ አተዋጾኦ
የሚከፍሉ
1. ጂንካ ዙሪያ ማዕከል
2. ገሊላ ወረዳ ማዕከል
3. ኦሞራቴ ወረዳ ማዕከል
4. ማሌ ወረዳ ማዕከል
5. ቀይአፈር ወረዳ ማዕከል
6 ጋዘር ወረዳ ማዕከል
 በአጠቃላይ የአባላት ብዛት ሲሆን ከዚህ ዉስጥ ወርሃዊ አስተዋጾኦ እየከፈለ
ያለዉ ሆኖ አፈጻጸሙ % ብቻ ነው፡፡ ወርሃዊ አስተዋጽ ሰብስበው ለማዕከል
እየላኩ ያሉ ወረዳ ማዕከላት ጂንካ ዙሪያ ፣ ቀይአፈር፣ገሊላ እና ማሌ ወረዳ ማዕከላት ናቸው፡፡
በ 2014 እስካሁን ያላኩ ወረዳ ማዕከላት ኦሞራቴ እና ጋዘር ወረዳ ማዕከላት ናቸው፡፡ በዚህ ዓመት
ወርሃዊ አስተዋጽኦ ያላኩ እና እያላኩ ያሉም ወረዳ ማዕከላት ወርሃዊ አስተዋጾኦ በባንክ እንድሆን
ሥራ ቢሰራ የተሻለ አፈጻጸም ሊመዘገብ ስለሚችል ልዩ ትኩረት እንድደረግ እየጦቅምን የአባላት
መረጃ አሰባሰብና አያያዝ ግልጽ በሆነ መልኩ ተደራጅቶ እንድቀመጥ አስተያየታችን ነዉ፡፡

 የሰዉ ሀብት ስምርትና ክትትል አገ/ት ንዑስ ክፍል፡-


አባላት በተሰጥአቸዉ መሠረት ወደ አገልግሎት ክፍላት እንድመደቡ በዚህ ዓመት 2 ጊዜ ምዝገባና ክትትል
ተደርጓል፤
አባላት በመንፈሳዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ እንድሳተፉ የማስተባበር ስራ ተሰርቷል/ለምሳሌ በልማት፤
በህዝብ ጉባኤ፤በደስታና ሀዘን ወቅት መዙሙርና ትምህርተ ወንገል እና ሌሎች አስተዋጾ በማድረግ እንድሳረፉ
ተደርጓል፡፡
ከሌላ ማዕከላት የሚመጡትም ሆነ ወደ ሌላቦታ በተለያዩ ምክንያት የሚሄዱትን መሸና ከመስጠት
የሚመጡ አባላትን ተከታትሎ ወደ አገልግሎት ከማስገባት አንፃር ሰፊ ክፍተት ያለበት በመሆኑ
በቀጣይ ጠንካራ ስራ መስራት ይጠበቃል፡፡

5/ ሂሳብና ንብረት አገልግሎት ክፍል የተሰሩ ሥራዎችን በተመለከተ፡ -

 የማዕከሉ ሂሳብ ገቢና ወጪን በተመለከተ፡-


 ከ 2013 የዞሬ የባንክ ከወጪ ቀሪ ሂሳብ -----------------------------------------------ብር
 ከሐምለ 1/2013-ሰኔ 30/2014 ድረስ ከወርሃዊ አስተዋጾኦ የተሰበሰበ ሂሳብ------ብር
 ጠቅላላ የተሰበሰበ ገቢ ሂሰብ -----------------------------------------------------------ብር
 ከሐምለ 1/2013-ሰኔ 30/2014 ድረስ ያለዉ ጠቅላላ ወጪ ሂሳብ ------------------ብር
 በካዝና/ባንክ ከወጪ ቀሪ ሂሳብ --------------------------------------------------ብር መሆኑን ለማረጋገጥ ተችሏል፡፡
 ለማዕከሉ የራሱ የሆነ የሂሳብ ባንክ አካዉንት መኖሩ፤
 ከመያዝያ 2012 ዓ/ም ጀምሮ የማዕከሉ አባላት ብዛታቸዉ 30 የሚሆኑት ክፍያቸዉ በባንክ system አድርጎ ወርሃዊ አማካይ ብር
እየተገኘ ሲሆን በኢ/ያ ንግድ ባንክ ላይ የባንክ ደብተር የሌላቸውን ሳያካትት የወርሃዊ አስተዋጾኦ ገቢ አሰባሰብ ሂደቱ ቀልጣፋ፤
ጊዜ ቆጣብና መንጠባጠቦችን ያሰቀረ ነው፡፡
 ወርሃዊ አስተዋጾኦ ለከፈሉ አባላት ደረሰኝ ከመስጠት ጋር በተለይም በባንክ የሚከፍሉ አባላት ጋር ያለውን ክፍተት ትኩረት ሰጥቶ መፍታት
ያስፈልጋል፤
 የማዕከሉ ቋሚና አላቂ ንብረቶች በመዝገብ ተመዝግቦ እንድቀመጥ የተደረገ ሲሆን ለቋሚ ንብረቶች መለያ ቁጥር ተሰጥቷል፡፡
የሚወገዱትን በመለየት ተመዝግበው ተይዘዋል፡፡
 ከተሰበሰበዉ ወርሃዊ አስተዋጾኦ ዉስጥ የማዕከሉና ዋና ማዕከል ድርሻ ከመላክ አንፃር

ተ/ የወረዳ ማዕከል ስም ገንዘቡ ፔርሰንት የገንዘብ ገንዘቡ ተ/ የማዕከል ገንዘቡ ፔርሰን የገንዘብ ገንዘቡ
ቁ የተላከበ መጠን የተላከበት ቁ ስም የተላከበ ት መጠን የተላከበት
ት ዓ/ም ሩብ ዓመት ት ዓ/ም ሩብ
ዓመት
1. ጂንካ ዙሪያ 80% 1. 40%
2. ገሊላ 80% 2. 40%
3. ኦሞራቴ 80% 3. 40%
4. ማሌ 80%
5. ቀይአፈር 80%
6 ጋዘር ወረዳ

 በ 2014 ዓ.ም ከወረዳ ማዕከላት ከተሰበሰበዉ ወርሃዊ አስተዋጾኦ 40% ወደ ዋና ማዕከል የተላለፈ ሂሳብ ብር
ሲሆን የማዕከል ድርሻ ብር ሆኖ የወረዳ ማዕከል ድርሻ ደግሞ ብር
ነዉ፡፡ ይህ በፐርሰንት % እና ነዉ፡፡ ስለዚህ ወረዳ ማዕከላት የገቢ አሰባሰብ
ሂደቱን ለማቀላጠፍ ልክ እንደ ጂንካ ዙሪያ ወ/ ማዕከላት አስተዋጾአቸዉን በባንክ sysetem ማድረግ ተገቢ ነዉ፡፡
 ከ 2014 ዓ.ም ከ 4 ቱ ወረዳ ማዕከላት የተላከ 80% ሂሳብ ብር ሲሆን የዋና ማዕከል ድርሻ
ብር ቢሆንም የዋና ማዕከል ድርሻ ብር እና ጂንካ ዙሪያ
ወረዳ ማዕከል ብር በድምሩ ብር ያልተላለፈ ሂሰብ በመሆኑ ማዕከሉ
በ 4 ኛ ሩብ ዓመት ከሚልከዉ ድርሻ ጋር ደምሮ እንድያስተላልፍ እንድደረግ እንገልጻለን፡፡

6/ የሙያና ተራድዮ አገልግሎት ክፍል የተሰሩ ሥራዎችን በተመለከተ፡-

 በክፍሉ ተጠሪ ሆኖ የተመደበው በአግባቡ እየሰራ ባለመሆኑ ጽ/ቤቱ በቦታው ሌላ መድቦ ለማሰራት የሰው ኃይል እጥረት
በመኖሩ ተደርቦ እየተሰራ የቆየ ክፍል ነው፡፡
 ክፍሉ በየወሩ 21 የዝክር መርሃ -ግብር ላይ የፀበል ጻዲቅ የማቅረብ ሥራ መስራቱ፤
 በሀዘን፤በሰርግ፤በክርስትና እና በዕርገት በዓላት ላይ የሚያስፈልጉ ነገሮችን የማቅረብ ሥራ መሰራቱ፤
 ክፍሉ ለዝክርና ማህበራዊ ጉዳዮችን ለማሳለፍ ከአባላቱ በየወሩ 20 ብር በማዋጣት መርሃ-ግብር እንድያልፍ ተደርጓል፡፡

7/ የግቢ ጉባኤ አገልግሎት ክፍል የተሰሩ ሥራዎችን በተመለከተ፡-


 ለጂንካ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ተማሪዎች የተከታታይ ኮርስ የሚሰጥ ስብከተ ወንገል እንድመደብ
የተደረገ ቢሆንም አሁንም የመምህሪን ወንገል እጥረት መኖሩን ክፍሉ ይገልጻል፡፡
 ለጂንካ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ ተማሪዎች በየድፓርትመንት በቤተሰብ መዋቅር እንድደራጁ እና የንስሐ አባት
እንድይዙ ተደርጓል፡፡
 ከ 1 ኛ እስከ 4 ኛ ዓመት ድረስ ላሉት ለ ግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ተከታታይ ኮርስ እንድሰጥ ተደርጓል፡፡
 ለክፍሉ የራሱ የሆነ ባንክ አካዉንት መኖሩ፤
 ከ 2013 ዓ/ም ወደ 2014 ዓ/ም የዞሬ ሂሳብ -----------------------------ብር 32,956
ጠቅላላ የተሰበሰበ ሂሳብ ----------------------------------------------ብር 525,910.50
ጠቅላላ የገቢ ሂሳብ ድምር --------------------------------------------ብር 558,866.00
ጠቅላላ የወጪ ሂሳብ ድምር ------------------------------------------ብር 465,558.00
ከወጪ ቀሪ በባንክ የሚገኝ ሂሳብ ------------------------------------ብር 93,308.50 ነዉ፡፡
 የግቢ ጉባኤው ገቢዎችን በባንክ አካውንት እያስገባ ወጪ እያደረገ የመጠቀም ልምዱ በዚሁ አጠናክሮ መቀጠል
ይኖርበታል፡፡ በተጨማሪ የባንክ አካውንቱ ሁለቱ ፈራሚዎች የማዕከሉ ቢሆንም ሶስተኛው ከጊቢ ጉባኤው የተወከለ
ተማሪ ተመርቆ የሄደ ስለሆነ አሁን ባሉት ተማሪዎች እንዲተካ መደረግ አለበት፡፡በቀጣይ የሂሳብ አያያዝ ሂደት ላይ
ተጨማሪ ግንዛቤ መፍጠር ሥራ መስራት ያስፈልጋል፡፡
 ለጂንካ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ጉባኤ ተማሪዎች የመሰብሰቢያ አደራሽ እጥረት በመኖሩ ይህን ችግር ለመፍታት
331,810 ብር ወጪ በማድረግ አዳራሽ በማስገንባት ላይ ይገኛል፡፡ ይህን ተግባር በተሸለ ደረጃ በማሳደግ ግቢ ጉባኤው
የተሸሉ ሥራዎችን መስራት እንዲችሉ ክትትልና ድጋፍ ማጠናከር ያስፈልጋል፡፡
 የ 2 ቱ ግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ለቤቲ/ያ የተኛዉንም ልማታዊ ሥራዎች ቤቲ/ያኗ ስታዉጅ ክፍሉ በማስተባበሪ የልማት ሥራ
እንድሰራ አድርጓል፡፡
8/ የቅ/መ/አብ/ገ/ አገልግሎት ክፍል የተሰሩ ሥራዎችን በተመለከተ፡-

 በዚህ 2014 ዓ.ም ክፍሉ ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ሁለት የአብነት ት/ቤቶችን በሰንማ እና በኮይቤ
ግንባታቸውን --------------------- ብር ወጪ አጠናቆ እንዲመረቁ አድርጓል፡፡
 በዚህ ዓመት ለአብነት ት/ቤት መምህራን ድጎማ ብር ወጪ በማድረግ
ተማሪዎች እንዲማሩ በማድረግ ተማሪዎች ዲቁና ተቀብለዋል፡፡ በቀጣይ ክፍሉ የሰው
ኃይሉን በማደራጀት ተማሪዎች ያሉበትን ደረጃና የትምህርት አሰጣጡን ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ
ይጠበቅበታል፡፡
 ለታርጫ ም/ቅ/ተ/ኃ/ቤቲ/ያንና ለቶጫ ባታ ማሪያም ቤተ/ያን የአብነት ተማሪዎች ለሚያስተምሩ 2 ቱ ማሪገታዎች ከዋና
ማዕከል የተላከ ድጎማ በጀት ብር 10,150.00 እንድደርሳቸዉ ተደርጓል፡፡
 ለኢሠራ ወረዳ ዳሊ ቅ/ጊዮርግስ ቤቲ/ያን የአብነት ተማሪዎችን ለሚያስተምር መርጌታ በማዕከሉ አባላት ብር 5,600.00
ድጎማ ተድረጓል፡፡
 ለሰመራ ቅ/ገብርኤል ቤቲ/ያን አባላትን በማሳተፍ መጾር መስቀል፤የማዕጠንት መስቀል፤ባለ ምልክት ቅዳሴ መጽሐፍ፤የወንገል
መጽሐፍ፤ብርትና ከስኩስት ጠቅላላ በብር 4,600.00 ተገዝቶ ድጎማ ተደርጓል፡፡
 ከዋና ማዕከል የተላከ 3 ሙሉ ተከኖ ልብስ ለቶጫ ወረዳ መናገሻ ኢየሱስ ቤቲ/ያን፤ጌና ቃራዎ ፅዮን ማሪያም እና ኢሠራ
ታዛ ኪዳነ ምህረት ቤቲ/ያን ድጎማ ተደርጓል፡፡
 ከዋና ማዕከልና ማስተባበሪያ በተጠየቅነዉ መሠረት 1 ካህን ከቶጫና 1 ካህን ከታርጫ አጥቢያ በመላክ ስልጠና
እንድያገኙ ተደርጓል፡፡
 የደብራችን አገልጋይ አባቶች መኖሪያ ቤት ማስዋብና ቀለም ለማስቀባት አባላትን በማስተባበር ብር 1,600.00
እንድሰበሰብ ተደርጎ ሥራዉ እንድሰራ ተደርጓል፡፡
 የሸባ መዳኒዓለም ቤቲ/ያን የማስዋቢያ ሥራ አባላትን በማስተባበሪ ለኮርንስና ለቀለም ብር 6,050.00 ተሰብስቦ
ሥራዉ እንድሰራ ተደርጓል፡፡
 ለታርጫ ቅድስት ኪዳኔ ምህረት ቤቲ/ያ ግንባታ አባላትን በማስተባባር 15 ኩንታል ሲምንቶ በብር ሲተመን ብር
6,950.00 ድጋፍ ተደርጓል፡፡
 ለታርጫ ምህረተ ቅዱስ ገብርኤል ወሚካኤል ቤቲ/ያ አጥር ለማጠር ቆርቆሮ ብዛት 10 ቅጠል በገንዘብ ስተመን ብር
2,000.00 አባላትን በማስተባበሪ ለህንጻ አሰር ኮሚቴ ገቢ ተደርጓል፡፡
 የፋስካ በዓልን አስመልክቶ ነደያንን ለማስፈሰግ ብር 1,000.00 ከአባላት ተሰብሶ በሥራ ላይ ዉሏል፡፡
 የአብነት ት/ቤት ግንባታ ቦታ ማስመንጠሪያ ከክፍሉ ብር 450.00 ወጪ ሆኖ ሥራዉ ተሰርቷል፡፡

ተ/ቁ የወረዳ ስም የአብነት ት/ት ምርመራ


የሚከታተሉ
ተማሪዎች
ብዛት
1.
2.
3.
ድምር 153

9/ በወረዳ ማዕከላት አገልግሎት ክፍል የተሰሩ ሥራዎችን በተመለከተ፡-

በማዕከሉ የሚገኙ ወረዳ ማዕከላትና ግንኙነት ጣቢያዎች አገልግሎት ቅኝት ከጽ/ቤት ጋር በመሆን አከናውኗል፡፡ነባራዊ
ሁኔታዎችን የሚያሳይ ዳሰሳ ጥናት በከፍል መደረጉን፤
ለወረዳ ማዕከላትና ግንኙነት ጣቢያዎች ድጋፍ ሥራ መሰራቱን፤
ግንኙነት ጣቢያ የሚያስፈልጉ አከባቢዎችን 75% ልየታ መደረጉን
የወረዳ ማዕከል ከማዕከሉ አቻ ክፍሎች ጋር ተናብቦ እንድሰራ የማድረግ ሥራ መሰራቱ፤
የቅኝት መስፈርትን በማዘጋጀት የወረዳ ማዕከላትና ግንኙነት ጣቢያዎችን እንድገመገም መደረጉ/ቃራዎ፤ቶጫ፤ወልድኃነ፤አባ
እና ከጪ /

ወስብሐት ለእግዚአብሔር !

You might also like