You are on page 1of 14

የንግድ ዕቅድ(Business Plan)

መጋቢት 2016 ዓ.ም


ታርጫ
አጠቃሎ(Executive Summary)
"በህብረት እንደግ“ የእህል በረንዳ የንግድ ድርጅት በደቡብ ምዕራብ ክልላዊ
መንግስት ዳዉሮ ዞን ታርጫ ከተማ አስተዳደር በመጋቢት 10/2016 ዓ.ም
ተቋቁሞ በችርቻሮ ንግድ ሥራ ዘርፍ በመሥራት ይገኛል፡፡የድርጅታችን
ደንበኞች በዳዉሮ ዞን ታርጫ ከተማ አስተዳደር የሚኖሩ የህብረተሰብክፍሎች
ሲሆኑ ለምግብ ፍጆታ የሚያስፈልጉ ምርቶች በከተማዉ ከሚገኙ ደንበኞች
ቁጥር አንጻር በበቂ ሁኔታ እየቀረበና ደንበኞችን እያረካ ካለመሆኑ የተነሳ
ድርጅታችን ይህንን ክፍተት ለመሙላት ይቻል ዘንድ የሚፈለገዉን ምርት
በቀጥታ ከአምራቾች ማሳ በመቀበል በችርቻሮ ያቀርባል፡፡

ድርጅታችን በሥሩ ወ፡ 3 ሴ፡ 2 ድምር፡ 5 አባላትን የያዘና የንግድ ሥራዉን ከአባላት የግል


ቁጠባ በተገኘ ካፒታል ብር 50000 የጀመረና አሁን ካፒታሉ ብር 75000 ደርሷል፡፡
ድርጅታችን ለደንበኞች ጥራቱን የጠበቀ ምርት በማቅረብ እስከ ሚያዝያ 10/2016 ዓ.ም
ድረስ የደንበኛ ቁጥሩን በ7.5% ለማሳደግ ግብ አስቀምጦ እየሠራ ይገኛል፡፡ በየቀኑ
እየጨመረ ያለዉን ደንበኛ ቁጥር ለማርካትና አቅርቦቱን የበለጠ ከፍ ለማድረግ አሁን
ያለዉን ካፒታል እጅግ ዝቅተኛ በመሆኑ አሁን ያለዉን የካፒታል መጠን ብር 75000 ወደ
275000 ከፍ በማድረግ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ቅድመ ዝግጅት ያጠናቀቀ ሲሆን
የብር 200000 ፈንድ ድጋፍ ከ-------- ድርጅት ለማግኘት ታሳቢ በማድረግ ይህ የንግድ
ዕቅድ ተዘጋጅቷል፡፡
የድርጅቱ መግለጫ(Company Description)

"በህብረት እንደግ“ የእህል በረንዳ የንግድ ድርጅት ዋና ተልዕኮ በታርጫ ከተማ

አስተዳደር ለሚኖሩ ነዋሪዎች ጥራት ያለዉን የእህል ምርት በማቅረብ ደንበኞቹን

ማርካት ነዉ፡፡ ድርጅታችን በሥሩ ወ፡3 ሴ፡2 ድ፡5 አባላት ያለዉ ሲሆን 1 ሥራ

አስኪያጅ 1 ፀሐፊ 1 ገ/ያዥ 1 ኦዲተርና 1 ንብረት ክፍል በመሆን ተዋቅሯል፡፡


የገበያ ትንታኔ(Market Analysis)
"በህብረት እንደግ“ የእህል በረንዳ የንግድ ድርጅት በእህል ችርቻሮ የንግድ ዘርፍ ሥር

የሚመደብና የታለሙ የታርጫ ከተማ አስተዳዳር ነዋሪዎች የታለሙ ደንበኞች

ናቸዉ፡፡

በከተማዉ 4 የእህል በረንዳ ድርጅቶች ያሉ ሲሆን እነርሱም 111፣222፣333፣444 ሲሆኑ

እነዚህም ተፎካካረረዎቻቻን ሲሆኑ ድርጅታችን ደንበኛን ለመሳብ ጥራት ያለዉን

እህል በሌሎች አቅራቢዎች በኪሎ 5 ብር ዝቅ በማድረግና በከተማ ዉስጥ ደንበኞች

ምርቱን ሲገዙ እስከቤታቸዉ ድረስ የትራንስፖርት አገልግሎት በነጻ ለመስጠት

ትኩረት አድርጎ ይሰራል፡፡


አገልግሎት/ምርት(Service/Product Line)

"በህብረት እንደግ“ የእህል በረንዳ የንግድ ድርጅት የተለያዩ የእህል ዓይነቶችን


ለደንበኞች የሚያቀርብ ሲሆን ምርቱን በቀጥታ ከአምራቾች ማሣ በኩንታል/በኪሎ
በመቀበል የትራንስፖርትና ሎሎች መሰረታዊ ወጪዎችን በማካተት ለተጠቃሚ
ደንበኞች በተመጣጣኝ ዋጋ ለማቅረብ ይሠራል፡፡

ሠንጠረዥ 1. የእህል ዓይነቶችን ዝርዝር የዋጋ መጠን


የዋጋ መጠን (በኩንታል) የዋጋ መጠን( በኪሎ) ምርመራ
ተ.ቁ የእህል ዓይነት ብር ሳንቲም ብር ሳንተም

1
2
3
4
ግብይትና ሽያጭ(Marketing & Sales)
"በህብረት እንደግ“ የእህል በረንዳ የንግድ ድርጅት ምርት እስከተጠቃሚዉ ድረስ

በማቅረብ አገልግሎት የሚሰጥና ከደንበኞች ጋር በአካልም ሆነ በቴክኖሎጂ ቀጥተኛ

ግንኙነት በማድረግ የሚሰራ ሲሆን ከ1 ዓመት በሗላ አቅሙን ከፍ በማድረግ ከታርጫ

ከተማ አስተዳደር ዉጭ ደንበኞችን በመፍጠር ሰፊ አገልግሎት ለመስጠት ግብ

አስቀምጦ ይሠራል፡፡
የተጠየቀዉ/የተፈለገዉ የገንዘብ መጠን(Funding Request)

"በህብረት እንደግ“ የእህል በረንዳ የንግድ ድርጅት ሥራዉን የጀመረዉ ከአባላት ቁጠባ
በተገኘዉ ብር 50000 ሲሆኑ በየወቅቱ እየጨመረ ካለዉ የተጠቃሚ ቁጥር አንጻር
አገልግሎቱን የበለጠ ተደራሽ ለማድረግ ካፒታሉን ወደ ብር 275000 ብርከፍ
ለማድረግ ያለመ ሲሆን ተጨማሪዉን ብር 200000 ብር ከድርጅታቹ ----
ድጋፍ/ብድር የሚጠበቅ ነዉ፡፡
ድርጅቱ አቅሙን ከፍ እስከሚያደርግ ድረስ የሽያጭ ተግባሩን ራሳቸዉ አባላቱ
የሚያከናዉኑና የሒሳብ እንቅስቃሴዉን በተመለከተ በዝርዝር በተዘጋጀ የገቢና ወጪ
መዝገብ እየተመዘገበ በግልጸኝነት ይሠራል፡፡

ሠንጠረዥ 2፡ የተፈለገዉን የገንዘብ መጠን ዝርዝር ማሳያ

የሚያስፈልግ ገንዘብ መጠን ምርመራ


ተ.ቁ ዝርዝር ጉዳዮች ብር ሳንቲም
የፋይናንስ ትንበያ(Financial Projection)
"በህብረት እንደግ“ የእህል በረንዳ የንግድ ድርጅት አገልግሎቱን በማስፋት በታርጫ
ከተማ አስተዳደር ለሚገኙ ነዋሪዎች ተገቢዉን አገልግሎት ለመስጠት ከታች
በሰንጠረዥ ላይ የተመለከተዉ የፋይናንስ ትንበያ ቀርቧል፡፡

ሠንጠረዥ 3፡ አጠቃላይ የፋይናንስ ትንበያ

የገንዘብ መጠን ምርመራ


ተ.ቁ ግብዓት/ርዕሰ ጉዳይ ብር ሳንቲም

1 እህል ግዥ
2 የቤት ኪራይ
3 ሚዛን ግዥ

ድምር

You might also like