You are on page 1of 14

ኢኽላስ የልማትና መረዳጃ ዕድር

አጭር ገለፃ
1. ኢኽላስ የልማትና መረዳጃ እድር
የቅደመ ምስረታ ስብሰባ በበኒን መሰጅድ
የተደረገ ሲሆን አደራጆች መርጦ፤
በይፋ በ25/005/2010 በ ሳልኮን ቢሮ ተመስርቷል፡፡
በሰብሰባው ላይ የተገኙ አባላት 12 የመስራች
አባላት ናቸው
1. የተቋሙ አመሰራረት እና አላማ አጭር
መግለጫ /ምክንያት/
ይህ ተቋም በአባላቶቹ መሀከል መልካም ግንኝነት
ለመፍጠር ፣በደስታም በሀዘንም ጊዜ ለመተባበር ፣
በትውልድ አከባቢያችን እና በሀገራችን በሚደረጉ
የልማት እንቅስቃሴዎች የበኩላችን ድርሻ ለማበርከት፣
አባላቶቹ በኢስላማዊ እውቀት ለማበልፀግ እንዲሁም
ለተተኪው ትውልድ ምሳሌ ለመሆንን የተቋቋመ
ማህበር ነው፡፡
1. ‹ኢኽላስ› ለምን ተባለ?
.የስያሜ ትርጓሜ ‹ኢኽላስ› ማለት ስራን ጥርት
ማድረግ ማለት ሲሆን የእድሩን አላማና
ዋና ተግባር ይጠቁማል፡፡
1. የማሕበሩ አላማ
ማሕበሩ በልማትና መረዳጃ ዘርፎች ያተኮሩ የሚከተሉት አላማዎች ይኖሩታል
A. እርዳታ
 በህመም ጊዜ እንደ አስፈላጊነቱ የገንዘብና ቁሳቁስ እርዳታ መስጠት
 የሞት አደጋ በደረሰ ጊዜ የገንዘብ እርዳታ መስጠት ፣እቃዎችን ማዋስ፣ማቃበር፣ማስተዛዘን
 በልዩ ልዩ ምክንያቶች በአባላትም ሆነ በሌሎች ወገኖች ላይ ችግር ሲደርስ ገንዘብና
የቁሳቁስ እርዳታ ማድረግና ማቋቋም
B. ልማትና ስነ ምግባር
 እንደ ጤናና ትምህርት ያሉ ችግሮችን ለዘለቄታው በሚፈቱ አማራጮች ላይ በማተኮር
የበጎ አድራጎት ስራዎችን ማከናወን፡፡
 ወላጅ አልባ ህፃናትንና አካል ጉዳተኞችን መርዳት፣መንከባከብ፣ማስተማር ፣በስነ
ምግባር የታነጹ ዜጎች የሚሆኑበትን መንገድ ማመቻቸት
 ህፃናቶች በስነ ምግባር የታነፁ ዜጎች እንዲሆኑ የሞራል ትምህርት እንዲያገኙ
ማመቻቸት
 አባላትን መንፈሳዊ እሴቶች ለማዳበር የሚጠቅሙ ፕሮግራሞችን ማዘጋጀትና መደገፍ
የማሕበሩ አላማ…….የቀጠለ
C. ፕሮጀክቶች
የገቢ ማስገኛ ፕሮጀክቶችን በመቅረፅ ፣ባለሙያዎችን በማስተባበርና
ነፃ ህዝባዊ አገልግሎት እንዲሰጡ በማድረግ ለስራ አጥ ወገኖች
የስራ እድል መፍጠር የእድሩን አላማ ለማስፈፀም የሚረዱ
አስፈላጊ የሆኑ ልማታዊና ማህበራዊ ተቋማትን ማቋቋም መገንባትና
ማስተዳደር፡፡
የአገርህን የማወቅና የቱሪዝም ጉዞዎችን በማካሄድ ማህበረሰቡ
ሰለሀገሩ እንዲያውቅ ማስቻል፡፡
የማህበሩ አባላቶቹ አዋጭነታቸው የተረጋገጠ የስራ መስኮችና
ሌሎች የልማት ስራዎች ለመስራት ማስቻል
ወጣቶች ከሱስና ከመሰል ጎጂ ባህሪዎች ነፃ የሆኑና አገርን
የሚጠቅሙ ዜጋ እንዲሆኑ ለማድረግ የተለያዩ ስልቶች በመቅረፅ
መንቀሳቀስ
2. አባልነት
 እድሩ በመተዳደሪያ ደንቡ መሰረት መደበኛ ፣ተባባሪና የክብር አባላት ደረጃዎች
ይኖሩታል፡፡
i. ተባባሪ
 ማንኛውም እድሜው ከ18 አመት በላይ የሆነ ሰው በመተዳደሪያ ደንቡ መሰረት
ሀ.የእድሩን አላማ ከተቀበለ
ለ.መዋጮ ለመክፈል እና ለእድሩ የሙያ ወይም የጉልበት አገልግሎት ለመስጠት ፈቃደኛ ከሆነ
ሐ.ከእድሩ ባህሪ ጋር በተያያዘ በጠቅላላ ጉባኤ የተመረጡ መስፈርቶችና ካሟላ፣የእድሩ ተባባሪ አባል
ለመሆን ማመልከት ይችላል፡፡
ii. መደበኛ
ማንኛውም ተባባሪ አባል ወደ መደበኛ አባልነት መሸጋገር የሚችለው ተባባሪ
አባል ከሆነ በኃላ ማንኛውም የሚፈለግበትን ግዴታ በአግባቡ መወጣቱ
ሲረጋገጥና በስራ አስፈጻሚ ኮሜቴው ተቀባይነት ሲያገኝ ይሆናል
iii. የክብር አባል
የክብር አባልነት በጠቅላላ ጉባኤው የሚፀድቅ የአባልነት ደረጃ ነው
 የአባልነት መብት
ማንኛውም የማህበሩ መደበኛ አባላት እኩል መብት የሚኖራቸው ሆኖ
እያንዳንዱ መደበኛ አባል
 በሀዘንናችግር ጊዜ በውስጥ ደንቡ በተጠቀሰው መሠረት ማንኛውንም የመረዳጃ
አገልግሎት የማግኘት
 የመምረጥ፣የመመረጥና የእድሩን እንቅስቃሴና አሰፈላጊውን መረጃ ጠይቆ
የማግኘት
 በጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ የመገኘትና ስለ ዕድሩ እንቅስቃሴ አስተያየትና ድምፅ
የመሰጠት መብት አለው፡፡
የማህበሩ ተባባሪና የክብር አባላት የመምረጥ መብት የሌላቸው
ሆኖ፣የዕድሩን የልማት ዘርፍ እንቅስቃሴና ማንኛውንም ተጓዳኝ
መረጃዎችን ጠይቆ የማግኘት ፣ሪፖርት የማድመጥ/የማግኘት አስተያየት
የመሰጠትና እድሩ በሚያቋቁማቸውና በሚገነባቸው ልማታዊና
ማህበራዊ ተቋማት በደንቡ መሠረት የመገልገል መብት ይኖሯቸዋል፡፡
 የአባላት ግዴታ
ማንኛውም መደበኛ አባል በሀዘን በቀብር ስነስርአቶች
የመገኘት ግዴታ አለበት
ማንኛውም መደበኛ አባል የአባልነት መዋጮውን በየወሩ
የመክፈል ግዴታ አለበት
እንደ መደበኛ አባል ከእድር አባልነት ሲወጣ የሚፈለግበትን
ውዝፍ እዳ የመክፈል ግዴታ አለበት
ማንኛውም መደበኛ አባል የእድሩን ዓላማ ለማሳካት
የሚጠበቅበትን አገልግሎት የመሰጠት ግዴታ አለበት
3. የዕድሩ የገቢ ምንጭ
ከአዲስ መደበኛ አባላት የሚሰበሰብ የመመዝገቢያ ክፍያ
ከመደበኛ አባላት በየወሩ የሚሰበሰብ የመረዳጃ መዋጮ
ከመደበኛ፣ተባባሪና፣የክብር አባላት የሚሰበሰብ የልማት መዋጮ
ከተለያዩ በጎ አድራጊ ወገኖች፣ድርጅቶችና (ማህበረሰቦች)
ወይም ከመንግስት በመልካም ፈቃድ ከሚደረግ ገንዘብ ወይም
ንብረት ልገሳ፣ዕርዳታና ድጎማ
እድሩ ከሚያቋቁማቸው ሌሎች የገቢ ማሰገኛ ፕሮጀክቶችና
ተቋማት የሚገኝ ገቢ ይሆናል
4. የማህበሩ አወቃር
ጠቅላላ ጉባኤ

ኦዲተር
የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ

አማካሪ ቦርድ

ሰብሳቢ

ምክትል ሰብሳቢ

ዋና ፀሀፊ

ሂሳብ ሹም

ገንዘብ ያዥ

የኮሚቴ
ንብረት ክፍል
አባል
 የጠቅላላ ጉባኤ ሥልጣንና ተግባር
ጠቅላላ ጉባኤ:
መስራችና መደበኛ አባላትን የሚያካትት ሆኖ ጠቅላላ
ጉባኤዉ የዕድሩ መደበኛ አባላት ስብስብ እና የማህበሩ
የበላይ አካል ነዉ፤
የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት፣ ኦዲተርና ቦርድ አባላትን
ይመርጣል፣ይሽራል የማህበሩን አማካሪ ቦርድ ይሰይማል፤
የጠቅላላ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባ በአመት አንድ ጊዜ
የሚካሂድ ሆኖ አስቸኳይ ስብሰባ ሊጠራ ይችላል፤
 የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ
 የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ኮሚቴው የማህበሩን ሰብሳቢ
ም/ሰብሳቢና ፀሀፊውን ጨምሮ ሰባት አባላት ይኖሩታል፤
 የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት የአገልግሎት ዘመን አንድ
ዓመት ይሆናል
 የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ለ ቦታው ብቁ ሆነው
እስከተገኙ ድረስ ቢበዛ እስከ
ሶስት ጊዜ ሊመረጡ ይችላሉ፡፡
በማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ስለተገኛችሁ እያመሰገንን

ስሜትዎን ያጋሩን?

You might also like