Professional Documents
Culture Documents
0
ተባረክ እሸት ቡና ኃ/የተ/የግ/ማህበር የንግድ ሥራ እቅድ
መስከረም/2016
ማውጫ
ክፍል-I: የ 2016 የታጠበ ቡና ንግድ ስራ እና የብድር አከፋፈል እቅድ አጠቃላ መነሻ ሀሳብ (EXECUTIVE SUMMARY)............3
1
ተባረክ እሸት ቡና ኃ/የተ/የግ/ማህበር የንግድ ሥራ እቅድ
4.1 ዓለም አቀፍ የቡና ፍላጎት (WORLD MARKET FACTS AND TRENDS)...............................................................................10
4.2 የገበያ መዳራሻና ተሳታፊ አካላት (COFFEE MARKET ACTORS).......................................................................................11
4.3 የገበያ ተወዳዳሪነት (MARKETE COMPETITION)...........................................................................................................11
4.4 የመሸጫ ዋጋ አወሳሰን (PRICE FOR INPUT AND OUT PUT).........................................................................................12
4.5 ምርት ስርጭት ጊዜ ሰሌዳ (MARKET DISTRBUTION).....................................................................................................13
2
ተባረክ እሸት ቡና ኃ/የተ/የግ/ማህበር የንግድ ሥራ እቅድ
4.4.2.2 INTERNAL RATE OF RETURN.............................................................................................................................26
8.4.2.3 የብድር ፍያ የሚጀመርበት ዓመት (PAY BACK PERIOD).............................................................................................26
8.4.3 የ 2016 ብድር አከፋፍል ሁኔታ (Loan Repaymebt Schdule)............................................................................26
ክፍል-X: ማጠቃልያና መደምደሚያ (SUMMARY AND CONCLUSIONS).........................................................................27
ተባረክ እሸት ቡና ኃ/የተ/የግ/ማህበር ድርጅት የታጠበ ቡና ንግድ ስራ እቅድ በ2016 የቡና ምርት ዘመን
ለሚያከናውነው የታጠበ ቡን ምርት የቀይ እሸት ቡና ግዥና ምርቱን ለማዘጋጀት የሚያስፈልግ የምርት
ማዘጋጃ ግብዓት ቁሳቁስ ግዥ ሚውል እና ለሰራተኛ ደመወዝና የጉልበት ክፍያ የሚውል የስራ ማስኬጃ ብድር
በ2016 ዓ/ም የስራ ዘመን ለማግኘት የታጠበ ቡና ለመዘጋጀት የቀረበ የንግድ ስራ እቅድ ነው፡፡
የድርጅቱ የንግድ ስራ ቅድ ዝግጀት ዋናው ዓላማ በታጠበ ንድድ ስራ ዘርፍ ከፍተኛ የሆነ ተወዳዳሪነት ያለበት
ንግድ ስራ ስለሆነ በምርት ዘመኑ ለሚደረገው የታጠበ ቡና ስራ ላይ ተወዳዳሪ በመሆን መጠኑ ያደገና ጥራቱ
የተጠበ የታጠበ ቡና ምርት በማዘጋጀት ለሀገር ውጥና ለውጪ ገበያ ለማቅረብ በዚህም ትርፍ በማግኘት
ተጠቃሚ መሆንና ከቡናው ክፍለ ኢኮኖሚ ለሀገራችን የውጪ ምንዛሬ ግኝት ላይ ተሳታፊ በመሆን የድርሻዬን
ለማበርከት ስራውን ለማከናወን የሚያስችል ዘላቂ የስራ የገንዘብ ምንጭ ማግኘት ነው፡፡
ተባረክ እሸት ቡና ኃ/የተ/የግ/ማህበር የታጠበ ቡና ማዘጋጃ ኢንዱስትሪ በአቶ በረከት ሀይሌ አስኪያጅነት
የሚመራ ድርጅት ሲሆን የአለም አቀፍ የጥራት ደረጃ የሚያሟላ ጥራቱ የተጠበቀ፣ መጠኑ ያደገና ዱካውን
3
ተባረክ እሸት ቡና ኃ/የተ/የግ/ማህበር የንግድ ሥራ እቅድ
የከተለ የታጠበ ቡና ከነሸሚዙ ለሀገር ውስጥና ለወጪ ገበያ ለማቅረብ ልምድ ባለው ስራ አስኪያጅ የሚመራ
ድርጅት ነው፡፡ ድርጅቱም ፍትሀዊና እኩል ተጠቃሚነትን የሚፈጥር ገቢ የማመንጨትና ለወደፊትም ድርጅቱ
በዘላቂነት እንድቀጥል በማስቻል የደንበኞች/ የተጠቃሚዎችን ፍላጎት በላቀ ሁኔታ በማረጋገጥ ከፍተኛ
ተባረክ እሸት ቡና ኃ/የተ/የግ/ማህበር የታጠበ ቡና ምርት አዘገጃጀት ከዘጠኝ አመታት በላይ የካበት ልምድ
ያለው ሲሆን በእያንዳንዱ አመታት በአማካኝ ከ600,000 እስከ 750,000 ኪ/ግ ቀይ እሸት ቡናን በመግዛትና
በማዘጋጀት ኢትዮጵያ ምርት ገበያ በማቅረብ በመሸጥ ከፍተኛ የንግድ ስራ ልምድ ያለው ድርጅት ነው፡፡
ስለሆነም የዓለም አቀፍና የሀገር አቀፍ የቡናን ዋጋ ትንበያና እለታዊ የዋጋ ሁኔት መሰረት በማድረግ ለአካባቢው
ቡና አምራች ማህበረሰብ በታጠበ ቡና ስራ ወቅት የቀይ እሸት ቡና ግብይት ለአምራቹ በቅርበት አገልግሎት
የገበያ አማራጭ በመፍጠር ተቃሚ የሚሆኑበትን መፍጠር በዚህ የንግድ ስራ እቅድ ትኩረት የሚሰጠው ተግባር
ነው፡፡
በዚህ ንግድ ሥራ የሚገኘው የስራ ማስኬጃ ካፒታል የታጠበ ቡና ምርት ለማዘጋጀት የቀይ እሸት ቡና ግዥና
ምርቱን ለማዘጋጀት የሚያስፈልግ የምርት ማዘጋጃ ግብዓት ቁሳቁስ ግዥ ሚውል እና ለሰራተኛ ደመወዝና
የጉልበት ክፍያ የሚውል የስራ ማስኬጃ በማግኘት ስራውን ያለችግር ለማከናወን አስፈላጊ በመሆኑ ነው፡፡ የቀይ
እሸት ቡና ከዓመት ዓመት በከፍተኛ ሁኔት እየጨመረ በመምጣቱ ድርጅቱ ባለው ካፒታል ብቻ ስራውን በሙሉ
አቅሙ መስራ የሚያስችል ባለመሆኑ ተጨማሪ ከባንክ መበደር በማስፈለጉ በዚህም ድርጅቱ ምርት በወቅቱ
በመሆኑም ተባረክ እሸት ቡና ኃ/የተ/የግ/ማህበር በ2016 የቡና ምርት ዘመን ለሚያዘጋጀው የታጠበ ቡና ምርት
የ2016 ምርት ዘመን የነበረውን የቀይ እሸት ቡና ሶስት የግብይት ወቅት ( መነሻ፣ መሀልና መጨረሻ) የነበረውን 1ኪ/ግ
እይ እሸት ቡና አማካኝ ዋጋ 42 ብር በመውሰድ ታሳቢ ተደርጎ የተሰላ ሲሆን አጠቃላይ በጀት ዓመቱ 900,000 ኪ/ግ
ቀይ እሸት ቡና ገዝቶ 166.500 ቶን የታጠበ ቡና ከነሸሚዙ እና 15.750 ቶን ተንሳፋፊና ልቃሚ ቅሽር በማዘጋጀት
ለገበያ ለማቅረብ በቀጥታና በተዘዋሪ ለምርት ዝግጅት የሚውል የብድር ፍላጎቱ ብር 39,703,309.24 ለፕሮጀክቱ ስራ
ማዘሰኬጃ እንደሚያስፈልገው ተጠንቶ ቀርቧል፡፡
4
ተባረክ እሸት ቡና ኃ/የተ/የግ/ማህበር የንግድ ሥራ እቅድ
የቡና ምርት በሚፈለገው ጥራት፣ መጠን፣ ዓይነት፣ በወቅቱ ለደንበኞቹ በኢትዮጵያ ምርት ገበያ ወይም በቀጥታ
የቡና ግብይት ትስስር ከላኪ ጋር በመዋዋል ለዓለም አቀፍ ገበያ በማቅረብ አገሪቱ የሚታገኘውን ውጪ ምንዛሪ
ከፍ ማድረግ፤
ለኪሳራ ያልተዳረገ የወጭና ገቢ ሚዛን የጠበቀ ትርፋማ የገንዘብ ፍሰት በመፍጠር( positive cash flow
from operations) በትርፍና ኪሳራ ማመዛዘኛ ስሌት መሰረት 30% የሆነ ትርፍ ከሽያጩ ማመንጨትና
ድርጅቱን ትርፋማ ማድረግ፤
የድርጅቱ ተልዕኮ፡ ከፍተኛ የቡና ጥራት ደረጃ ያለው ምርት ለሀገርና ለውጭ ገበያ በማቅረብ ለቡና ገዥዎቹ
ዱካን የተከተል ጥራት ያለው ምርት በታማኝነት የደንበኞቹን ፍላጎት ማርካት፡፡ ተባረክ እሸት ቡና
ኃ/የተ/የግ/ማህበር የንግድ ስራ እቅድ ተግባር ላይ ማዋል፣ ለድርጅቱ ሰራተኞችና ለቡና አምራች አርሶ አደሮች
በታጠበ ቡና ምርት ጥራት አጠባበቅ፣ አዘገጃጀትና አያያዝ ላይ በማተኮር ስልጠና መስጠጥ የደንበኞችን ፍላጎት
በተገቢው ማሟላት የሚያስችል አገልግሎት፣ የአካባቢ ስነ-ምዳር በመጠበቅ ደንበኛው በሚፈልገው ልክ ወይም
በበለጠ አገልግሎት መስጠት፡፡
ራዕይ (Our vision): ተባረክ እሸት ቡና ኃ/የተ/የግ/ማህበር በአካባቢው ከሚገኙ ኢንዱስትሪዎች የታጠበ ቡና
በማዘጋጀት ቁንጮ ሆኖ መገኘት አሰራሩ ሊለካ የሚችለው በደንበኞች፣ በድርጅቱ ሰራተኞች፣ በባለድርሻ
አካላትና በአካባቢው በሚኖሩ ቡና አምራቾች ስለሆነ በነሱ ዘንድ ተቀባይነቱ የተረጋገጠ መሆኑ፡፡
ጥራት ያለው ምርትና አገልግሎት አሰጣጥን ለዘላቂነት በማስጠበቅ የደበኛ አገልጋይነትን ማጎልበት፣
የድርጅቱ ባለበት አካባቢ በሚሰራው ንግድ ስራ የድርጅቱን አዋጭነት በከፍተኛ ደረጃ ማስጠበቅና
5
ተባረክ እሸት ቡና ኃ/የተ/የግ/ማህበር የንግድ ሥራ እቅድ
ተባረክ እሸት ቡና ኃ/የተ/የግ/ማህበር ቡና አዘጋጅና አቅራቢ ህጋዊ ድርጅት በሲዳማ ክልል በደቡብ ሲዳማ ዞን
በዳሌ ወረዳ ሃይሌ ቀበሌ የሚገኝ የቡና ምርት በማዘጋጀት ወደ ኢትጵያ ምርት ገበያ ለማቅረብ በህጋዊነት
የአቅራቢነት ፈቃድ ወስዶ በክልሉ ንግድ ቢሮና በእርሻና ተፈጥሮ ሀብ ቢሮ ተመዝግቦ ስራበላይ የሚገኝ ነው፡፡
የሀገራችንን የቡና ምርትና ምርታማነት በማሳደግ በዓለም አሁን ካለችበት አምስተኛ የቡና ምርት አምራችነት
ወደ ሁለተኛ ደረጃ ለማሳደግ በመንግስት በኩል ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ያለ እና የግብይት ስርዓቱንም ከተለያዩ
ዓለም አቀፍ የግብይ አሰራሮች አብሮ የሚዘምንበት ስርዓት ለመገንባት የግብይት አዋጁ፣ ደንቡንና መመሪያ
በማሻሻል የግብይት ሪፎርም በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡ በሆኑም የቡና ልማትና ግብይ ትስስር ግንኙነት አሰራር ላይ
የተመሰረት የቡና ምርት ኢክስፖርት የማድረግን አሰራር ፈቅዷል፡፡ ይህም ተባረክ እሸት ቡና ኃ/የተ/የግ/ማህበር
ተባረክ እሸት ቡና ኃ/የተ/የግ/ማህበር የታጠበ ቡና አቅራቢ ድርጅትም ከኢትዮጵያ ምርት ገበያ፣ ከኢትጵያ
ንግድ ባንክና ከሌሎች ንግድ ባንክ ተቋም በጥሩ የስራ ግንዩነት በቡና ንግድ ስራ ከፍተኛ የሆነ ልምድ ያዳበረ
ድርጅት ነው፡፡ ከአነስተኛ ቡና አምራቾች ጋር በቀጥታ የግብይት ግኑኝነት በጋራ የመስራት እውቀት ያለው
በመሆኑ ለአካባቢው ማህበረሰብ ጥሩ የግብይት አማረጭ ሆኖ ቆይቷል፡፡ እንዲሁም ለአካባቢ ማህበረሰብ የስራ
እድል ለሌላቸው የስራ እድል በመፍጠር የገቢ ምንጭ የሚፈጥሩበትን እድል ፈጥሯል፡፡
ድርጅቱ የቡና ምርትን በጥራት በማዘጋጀት ልምድ ያለው በመሆኑ በሀገር አቅፍ ተወዳደሪ በመሆን ግብይቱ ላይ
ልዩነት በመፍጠር ጥራት ያለው ምርት ለደበኞቹ የማቅረብ አቅም አለው፡፡ በዚህም በአካባቢው ከሚገኙ የታጠበ
ቡና አዘጋጅና አቅራቢ ድርጅቶች ውስጥ ምርትን በጥራት በማዘጋጀት ረገድ በመሰለፍ ጥራት ያለው ቡና ለሀገር
6
ተባረክ እሸት ቡና ኃ/የተ/የግ/ማህበር የንግድ ሥራ እቅድ
በአዲሱ የንግድ አዋጅ፣ደንብና መመሪያ አሰራር መሰረት ከአነስተኛ የቡና አምራቾች አርሶ አደሮች በሚደረግ ቀጥተኛ
የቡና ንግድ ትስስር ግንኙነት (Out-growers) ውጤታማ የተሳካ ስራ ለመስራት አሁን ያለውን የቡና ማዘጋጃ
ኢንዱስትሪ አሰራሩን በመቀየር በዚህ የስራ ንግድ እቅድ ውስጥ በማካተት ተወዳዳሪ የሚያደርጉ (Processor’s
competitive Advantages) አሰራሮችን ላይ ትኩረትረ በመስጠት በመስራት የታጠበ ቡና ምርት አዘገጃጀቱ የተሳካ
ለማድረግ፡-
ከመነሻ እስከ መጨረሻ ዱካን የተከተለ ምርት ማዘጋጀት (End-to- end quality and traceability
management)፤
ፍትሐዊና ዘላቂነት ያለው ግብይት የሰፈነበት እንዲሆን መስራት (Equitable and commercially
የአካባቢውን ማህበረሰብ ዕውቀት ሊያሻሽል ሚችል አሰራር መተግበር ያካትታል (Social and
የንግድ ስራ እቅድ አስፈላጊነቱ ዓላማውን ለማሳካት ለታጠበ ቡና ምርት ማዘጋጃ ስራ ማስኬጃ በጀት በብድር
በሟሟላ በቀጣይ የታጠበ ቡና ለማዘጋጀት፤ በቂ የምርት ግብዓት በመግዛት አለም አቀፍ ኤክስፖርት ደረጃን
የሚያሟላ ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረብ፡፡ በዚህም የድርጅቱን ትርፋማነት ማረጋገጥ፡፡
ወረዳዎች፣7 ከተማ አስተዳደር እና 625 የቀበሌ አስተዳደር ይዞ የተዋቀረና (6,538.17 km2) ወይም 2,524.40
7
ተባረክ እሸት ቡና ኃ/የተ/የግ/ማህበር የንግድ ሥራ እቅድ
ስኮየር ኪሎሜትር የቆዳ ስፋት ያለው ሲሆን ክልሉ 6,200,000 በየሕዝብ ብዛት ያለው እና ከዚህ ውስጥ 91 ከመቶ
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ ቡና ከሚያመርቱት የሀገራችን ክልሎች አንዱ ሲሆን የቡና ምርት ለማምረት ከፍተኛ
ተስማሚ ስነ-ምዳር ያለው በመሆኑ ቀዳሚ ስፍራ ይዞ ይገኛል፡፡ ከክልሉ ግብርና ቢሮ በተገኘው መረጃ መሰረት
154,000 ሄክታር በቡና የተሸፈነ መሬት የሚገኝ መሆኑ ከተገኘ መረጃው መረዳት ተችሏል፡፡
ዳሌ ወረዳ ይህ ፐሮጀክት የሚገኝበት ወረዳ ሲሆን በከፍተኛ ቡና አምራችነቱ ይታወቃል፡፡ ወረዳው 26,000 ሄ/ር
የሚሸፍን ሲሆን 11,093 ሄክታር መሬት በቡና ሰብል የተሸፈነ መረትና 34,438 ቡና አምራች አርሶ አደሮች
የሚገኙበት በአማካኝ ከአንድ ሄክታር 8.02 ኩታል ንጽሁ የተቀሸረ ቡና የሚገኝ መሆኑ በወረዳው 2010 የቡና ምርት
ትመና መረጃ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በመሆኑም ከዓመት ወደ ዓመት እያደገ የመጣውን የአርሶ አደሩ የገበያ ፍላጎትና የምርት
ግብይት አሰራሩን በቀጣይነት ለማሻሻል እንዲቻል የቡና ግብይት ተዋኒያኑ ተተኪ የሌለው ሚና እንደሚጫወቱ
ይታመናል፡፡ የደቡብ ክልል ተፈጥሮ በለገሰው ምቹ ሁኔታና መንግስት ለምርትና ማርታማነት ዕድገት በሰጠው ከፍተኛ
ትኩረት ከጊዜ ወደ ጊዜ ዕድገት እየተመዘገበ ሲሆን የግል ባለሀብቶች የግብይት ተሳትፎ ድርሻ እጅግ ከፍተኛ ነው፡፡ በክልሉ
የግል የቡና አቅራቢዎች የቡና ግብይት ተሳትፎ ከ 90% በላይ የገበያ ድርሻ ማድረስ ተችሏል፡፡ ከላይ መመልከት
እንደተቻለው የወረዳውን አርሶ አደሮች ከቡና ምርት ገቢ ተጠቃሚ ለማድረግ በቡና ማጠብ ስራ የተሰማሩ ባለሀብቶችን
በማበረታታት በወረዳው 28 የታጠበ ቡና ማዘጋጃ ኢንዱስትሪ የሚገኙ ሲሆን ተባረክ እሸት ቡና ኃ/የተ/የግ/ማህበር
በመሆኑም ወረዳው በያዝነው በጀት ዓመት የታጠበ ቡና ምርት ለማዘጋጀት 19,817 ቶን እሸት ቡና ለመሰብሰብ ያቀደ
ሲሆን ከዚህ ውስጥ ተባረክ እሸት ቡና ኃ/የተ/የግ/ማህበር የታጠበ ቡና ማዘጋጃ ድርጅት 900 ቶን እሸት ቡና መሰብሰብ
ብርማ ሽፋንና የእርጥበት መጠኑ 11-12% የሆነ ደረቅ ፍሬ ሲሆን የታጠበ ቡና የማዘጋጀት ሂደትን አልፎ
ተቆልጦና ተፈጨቶ ለሚዘጋጅ የቡና መጠጥ ዋና ግብአት አገልግሎት የሚውል ማለት ነው፡፡
8
ተባረክ እሸት ቡና ኃ/የተ/የግ/ማህበር የንግድ ሥራ እቅድ
የቡና ምርት በሁለት ዋና የምርት የማዘጋጀት ሂደት የሚዘጋጅ ሲሆን አንዱ የታጠበ ቡና አዘገጃጀት ሂደት
ሲሆን ሁለተኛው ያልታጠበ ቡና አዘገጃጀት ሂደት ነው፡፡ በዚህ ንግድ ስራ እቅድ መሰረት የታጠበ ቡና
የማዘጋጀት ሂደት ማለት ረጅም የዝግጅት ሂደት ያለው ውኃን በመጠቀም የላይኛውን ገለፈት
ፈሳሽ አካል በመዘፍዘፍ የማስለቅ ሂደት የሚከተልና በመቀጠልም ተፈላጊ የእርጥበት መጠን
ጨምሮ ከፍተኛ የሰው ኃል ጉልበት የሚፈልግ የአሰራር ሂደትን የሚከተል ማለት ነው፡፡
የታጠበ ቡና ከነሸሚዙ ምርት በሙሉ የታጠበ ቡና አዘገጃጀት የሚመረት ሆኖ አራት ዋና ዋና የአዘገጃጀት ሂደቶችን
ያልፋል ማለትም መፈልፈል፣ መዘፍዘፍ፣ ማጠብ፣ ማድረቅና በማከማቸት ለገበያ ማቅረብ ሲሆን በአለም አቀፍ ገበያ
ከሚቀርበው ቡና ምርት የታጠበ ቡና ከነሸሚዙ በመጠንና በገበያ ተፈላጊነት ከፍተኛ ድርሻ ያለው የተሻለ ዋጋ
ሲሆን ጥራት የሚወስኑ ሁኔታዎች ብዙ ቢሆኑም ዋና ዋናዎቹ ቦታኒካል፣ ዝርያ፣ ስነ-ምህዳር፣ አየር ሁነታና
በተጨማሪ የምርት አያያዝ በማብቀል ጊዜ ምርት በሚሰበሰብት ወቅት ምርት አዘገጃጀቱ አከመቻቸቱ
የሚፈጠሩ ጉድለቶችን በመቀነስ ለጥራት ከፍተኛ ዋጋ አላውን ተግባር እውን በማድረግ ይሰራል፡፡ የቡና ምርት
ለሰው በምግብነት የሚያገለግል ስሆነ የሰውን ጤና የማያውክ፣ በቡናው ውስጥ የሚገኙ ባዕድ አካላት የጸዳ
ማለትም ከሻገታ፣ ነፍሳት ቅሪት መሰረታዊ የጥራት መለኪያ ተሟሉ በማድረግ ይተገብራል፡፡ በተጨማሪ
የግዥ ውል መስፈርትን፣ የመጠኝ ተመሳሳይነትና የገዥን ፍላጎት የሚአረካ መሰረታዊ ዝቀግት ያለው መሆኑን
በማረጋገጥ ያከናውናል፡፡
9
ተባረክ እሸት ቡና ኃ/የተ/የግ/ማህበር የንግድ ሥራ እቅድ
ያልተፈለገ የቡና ምርት ግብይትን ለመጠበቅና የቡና ምርት ተፈላጊነትን በገበያው በዘላቂነት ለማቆየት የቡና
ጥራት ደረጃ ወሳኝ መሰረታዊ ጉዳይ ሲሆን በዚህ ድርጅት የሚዘጋጅ የቡና ምርት ደረጃ አለም አቀፍ ደረጃን
ማሟላት እዳለበት ታልሞ የሚሰራ ነው፡፡ አለም አቀፍ ደረጃ ማለት ኢንተርናሽናል ኮፊ ኦርጋናይዜሽን
(International Coffee Organization has put in place Resolution 407 of February 2002 and
ICO, 2002) ያስቀመጠውን ዝቅተኛ መስፈርት ማሟላት አለበት ማለት ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የኢትዮጵያ
4.1 ዓለም አቀፍ የቡና ፍላጎት (World Market Facts and Trends)
በአለም አቀፍ ደረጃ የቡና ምርት ፍላጎት የሚወሰነው በምርት ጥራት ደረጀና በተጨማሪም የቡና ምርትን
ለመጠጥነት የሚያዘጋጁ ኢንዱስትረዎች ፍጎት ይወሰናል፡፡ ሌላው የከተሞች መስፋፋት ጋር ተያይዞ የሚመጣ
ፍላጎት ነው፡፡. እያደገ የመጣውን የዓለም አቀፍ የቡና ምርት አቅርቦት በተመለከተ በአመሪካ ከሚገኝ የቡና
10
ተባረክ እሸት ቡና ኃ/የተ/የግ/ማህበር የንግድ ሥራ እቅድ
አቅርቦት ላይ ምርምር ከሚያደርግ ድርጅት( USDA office of Global Analysis December 2022)
የተገኘው መረጃ ሰንጠረዥ 5.2 ተመልክቷል፡፡ ላለፉት ሰባት አመታት ዓመታዊ አማካኝ የቡና ምርት ፍላጎትና
አቅርቦት 8% እና 7% በቅደም ተከተል እድገት አሳይቷል፡፡. ይህም የፍላጎት ምንጭ ለዚህ ድርጅት ስራ አዋጭ
Table 4.1 World Green Coffee Export Demand and Supply in (“000”) Tones
World
Year World Demand/Import GR % Supply/Export GR %
2017 93171 58510
2018 95013 2% 59183 1%
2019 92653 -3% 56703 -4%
2020 96115 4% 60874 7%
2021 96574 0% 61225 1%
2022 98547 2% 60571 -1%
2023 101130 3% 62813 4%
Average 8% 7%
Source: Foreign Agricultural Service/USDA office of Global Analysis December 2022
ዓለም አቀፍ ግብይት በፈላጊና በተፈላጊ አገራት መካከል የሚደረግ ልውውጥ ቢሆንም በዓለም የሕዝብ ቁጥር መጨመር
በአንዱ አካባቢ ያለው ትርፍ ምርትና ምቹ ሁኔታ የሌላው ክፍል ጉድለት የሚሞላ በመሆኑ እና በዓለም ባለው ትስስር
በገራችን ከሚመረት የቡና ምርት መካከል እስከ አሁን የቡና ምርት የሚረከቡ ገዥዎች በአሜሪካ፣በጃፓንና አውሮፓ ያሉ
በቡና ምርት ግብይት መስክ የሚኖሩት ዋነኛ ተወዳዳሪዎች መሠረታዊ ኅብረት ስራ ማህበራት እና ሌሎች
የግል ቡና አቅራቢ ነጋዴዎች ሲሆኑ ተባረክ እሸት ቡና ኃ/የተ/የግ/ማህበ ርድርጅት ጥራቱን የጠበቀ ምርት
ባጠረ ግብይት ሰንሰለት ከቀጥታ ከአርሶ አደሮች በመግዛትና ጥራት መሠረት ያደረገ የተሻለ ዋጋ በመክፈል
በጥራት በማዘጋጀት በቀጥታ የግብይት ትስስር ወደ ውጪ በመላክ ከሚገኘው የተሻለ ትርፍ ተፎካካሪዎች
ማሸነፍ አቅዶ ይሰራል፡፡ በመሆኑም ከፍተኛ መጠን ያለው ጥራትና ደረጃውን የጠበቀ ምርት በመሰብሰብና ወደ
ውጪ በተመጣጠነ ትርፍ በቀጥታ የግብይት ትስስር ለላኪዎች በማቅረብ ውድድሩን ለማሸነፍ አቅዷል፡፡
11
ተባረክ እሸት ቡና ኃ/የተ/የግ/ማህበር የንግድ ሥራ እቅድ
አምራች አርሶ አደሮችን በተሻለ የእሸት ቡና ዋጋ ተጠቃሚ ለማድረግ እና በአትዮጵያ ምርት ገበያ ምርትን
ይሁን እንጂ ድርጅቱ የሚሰጠው አገልግሎትና ከንግድ እንቅስቃሴው አ/አደሩ የሚያገኙት ጥቅም ቀጣይነት
ተመጣጣኝ ትርፍ ማግኘት ይኖርበታል፡፡ በመሆኑም ድርጅቱ የሚገዛውንና የሚሸጠውን ምርት የዋጋ አወሳሰን
ይህንን ታሳቢ ያደረገ ይሆናል፡፡ በዚህም መሰረት ድርጅቱ ለሽያጭ የሚያቀርበው የቡና ምርት መሸጫ ዋጋ
ለመወሰን ምርቱን ለማምረት የግብይትና የማዘጋጃ ወጪዎችን፣ የወለድ ወጪንና የመሳሰሉትን አጠቃልሎ
በመደመር እና በዚህ ላይ ወቅታዊ ተጨባጭ የገበያ ዋጋ ትንተና ላይ በመመስረት የተወሰነ የትርፍ ማርጂን
ከዚህ በተጨማሪ የኢትዮጵያ ምር ገበያ ከ 20010 እከ 2014 ድረስ የአንድ ፈረሱላ/17 ኪ/ግ/ የሽያጭ ዋጋ
መረጃ ለአወሳሰን መነሻ እንዲሆን ተወስዷል፡፡ የቀይ እሸት ቡና ግዥ የ 2015 ምርት ዘመን የነበረው ዋጋ
መነሻ፣ መካከለኛና መጨረሻ ላይ ያለው በአማካን በመውሰድ ሲሆን ከታች በሰንጠረዥ 4.4 በተመለከተው
መሰረት የድርጅቱ የ 1 ኪ/ግ እሸት ቡና መግዥና የታጠበ ቡና ማሸጫ ዋጋን በሰንጠረዥ 4.4፡ መሰረት
እደሚከተለው ቀርቧል፡፡
ደንበኞች የሚፈለጉትን ምርት በሚፈለጉበት ቦታ እና ጊዜ ለማግኘት እንዲችሉና ለማቅረብ ይመች ዘንድ የምርት ገበያ ማቅረቢያ ስርአት
በሚገባ መዘርጋት ይኖርበታል፡፡ በዚህ መሠረት የምርት ማከማቻ መጋዘን በጥሩ ሁኔታ በመያዝና የትራንስፖርት አመች በሆነ ቦታ
12
ተባረክ እሸት ቡና ኃ/የተ/የግ/ማህበር የንግድ ሥራ እቅድ
በማከማቸት በወቅቱ ወደ ምርት ገበያ እንዲቀርበረ ይደረጋል፡፡ በዚህ መሰረትም እንደየምርት ዘመኑ የአቅርቦት ምርት መጠን የተለያየ
ቢሆንም የታጠበ ቡና የአቅርቦት ጊዜን በመከተል ምርቱን ኪህ በታች በተቀመጡ ወራቶች ለገበያ እድቀርብ ይደረጋል፡፡
ለኢትዮጵያ ምርት ገበያ በማቅረብ ደረጃ በማስወሰን ወይም በቀጥ የገበያ ትስሰር ከላኪዎች ጋር በመዋዋል የተሻለ ትርፍ
ዲስክ ቁጥር ነው፡፡ የድርጅቱ የታጠበ ቡና ማዘጋጃ ማሽኑ 4-መፈልፈያ ዲስክ የተገጠመለት ሲሆን በሰዓት
የመፈልፍል አቅም 4000 ኪ/ግ በሰዓት ሲሆን ነገር ግን ድርጅቱ የማዘጋጀት አቅሙ የሚወሰነው ድርጅቱ
ያለው ሁለንተናዊ ድርጅታዊ አቅም ማለትም የካፒታልና የውስጥ ቅድመ ዝግጅት ነው፡፡ ይሁን እንጂ ድርጅ
በቂ የስራ ማስኬጃ ባለማግኘቱ ምክንያት ለ 2016 በጀት ዓመት የታጠበ ቡና ለማዘጋጀት 900,000 ኪ/ግ ቀይ
እሸትቡ ለመሰብሰብ ያቀደ ሲሆን ይህም የምርት ማዘጋጃ አቅም ውስጥ 50% ብቻ ነው፡፡ በዚህ መሰረትም
13
ተባረክ እሸት ቡና ኃ/የተ/የግ/ማህበር የንግድ ሥራ እቅድ
ለታጠበ ቡና ለማዘጋጀት በቀን 6 ሰዓት በዓመት 78 የስራ ቀናት ይኖሩታል፡፡ ስለሆነም የድርጅቱ ቡና አመታዊ
ምርት የማዘጋጀት አቅሙ ከዚህ በታች በሰንጠረዥ መተለከተው መሰረት እንደሆነ በእቅድ ተይዟል
እደሚከተለው ቀርቧል፡፡
ተባረክ እሸት ቡና ኃ/የተ/የግ/ማህበር ከላይ በተተቀሰው ምርት እቅደ መሰረት ፕሮጀክቱ የእሸት ቡና
የመሰብሰብ አቅም መነሻ በማድረግ እና የሁለት አመት የታጠበ ቡና አዘጋጅቶ ለማእከላዊ ገበያ ያቀረበውን
መነሻ ሀሳብ ተደርጎ የዘመኑ የታጠበ ቡና ምርት የገበያ አቅርቦት ቡና እደሚከተለው ታቅዷል፡፡ ለበለጠ በረመጃ
የታጠበና ቡና ለማዘጋጀት የሚያስፈልግ አመታዊ የእሸት ቡና አቅርቦት መነሻ መሰረት የንግድ ስራ እቅድ አቅም ባገናዘ ሁኔታ ለታጠበ
ቀርቧል፡፡
14
ተባረክ እሸት ቡና ኃ/የተ/የግ/ማህበር የንግድ ሥራ እቅድ
ሠንጠረዥ 5.1.4: የቀይእሸት ቡና አቅርቦት ፍላጎትና ግዥ
ድርጅቱ የታጠበ ቡና ለማዘጋጀት እሸት ቡናው በማሽን ተፈልፍሎ ከታጠበ በኋላ ምርቱ የሚደርቅበት፣ የሚከማችበትና
የሚጓጓዝበት ልዩ ልዩ ቁሳቁስ ግብዓቶች ያስፈልጋሉ፡፡ ይሁን እንጂ ወጪ ቆጣቢ አሰራር ለመከተል የግድ ስለሚል
ከመለስጠና ጥገና በስተቀር ከዚህ በፊት ድርጅ የተጠቀመባቸውን የአልጋ ማድረቂያና ሌሎች ቁሳቁስ ስራ ላይ የሚውል
ሲሆን መቋተሪያ ጆንያ ምረቱ ጋር አብሮ ስለሚሸጥ አዲስ ያስፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከታች በተዘረዘረው ሰንጠረዥ ስሌት
መሰረት የሚያስፈልግ የጆንያ መጠንና ተዛማጅ ወጪ 227,813 ብር ሲሆን ለበለጠ መረጃ ሰንጠረዡን መመልከት
ይቻላል፡፡
የምርት ዓመት
መግለጫ መለኪያ መጠን
ነጠላ ዋጋ ለ 2016 በጀት ዓመት
ብር ብር
ጆንያ ባለ 100 ኪ/ግ ቁጥር 969 235 227,813
የተያያዥነት ያላቸው ቋሚ ንብሮች ማለትም የታጠበ ቡና ማዘጋጃ ኢንዱስትሪ ከነሙሉ የውስጥ ክፍሎቹ፣
ለድርጅተ ሰራተኞች ስራ እንቅስቃሴ የሚያገለግል ዳብል ካፕ መኪና በኪራይ፣ ለድርጅቱ ጽ/ቤት አገልግሎ
የሚውል የውስጥ ቁሳቁስና የሰራተኛ መገለገያ ቁሳቁስ እና የቡና ምርት የተለያዩ መጀመሪ ደረጃ ግብይት
ማእከላት ምርት መረከቢያ ጣሊያን ሰራስ ሚዛኖች ይገኛሉ፡፡ በአጠቃላይ ከዚህ ድርጅት ጋር በቀጥታ
አገልግሎት የሚውሎ ቋሚ ንብረቶች በገንዘብ ሲገመቱ ብር 5,715,000 የሚገመት ነው፡፡ ለበለመጠ መረጃ
15
ተባረክ እሸት ቡና ኃ/የተ/የግ/ማህበር የንግድ ሥራ እቅድ
ሠንጠረዥ 5.2: የድርጅቱ ቋሚ ንብረት ዓይነትና ግምት
በየአመቱ የታጠበ ቡና ኢንዱስትሪ ወይም ማሽን ለማስጠገን የሚያስገልግ 90,797 ብር ዕቅድ ተይዟል፡፡
ሥራ ባለው የሥራ የስጋትና የአመራር ትኩረት ማነስ ለሚከሰት አደጋ ለሚያቀርበው የቡና ምርት፣ ላሉት
ማኅበራት እንደሆኑ ይታወቃል፡፡ ተባረክ እሸት ቡና ኃ/የተ/የግ/ማህበ ርድርጅት በግል የተመሰረተና በሸበድኖ
ወረዳና በሲዳማ ዞን ንግድ ቢሮ ህጋዊ ሰውነት አገኝቶ በስራ ላይ ያለ ድርጅ ሲሆን በወረዳ ምርትን ከአምራቹ
በማሰባሰብና በማዘጋጀት ምርትን በጥራትና በብዛት ለገበያ ለማቅረብ ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር ሲሆን በአገሪቱ
ሕግ መሰረት በዞንና በወረዳ ደረጃ የተመዘገበና ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው ነው፡፡
16
ተባረክ እሸት ቡና ኃ/የተ/የግ/ማህበር የንግድ ሥራ እቅድ
5.6. የስራ ዝርዝርና መርሀ ግብር
ተ/ ቁ የስራ ዝርዝር መርሀ-ግብር
ሀምሌ ነሀሴ መስ ጥም ህዳር ታህ ጥር የካ መጋ ሚያ
1 የልጋግ ጉድጓድ ጥረጋ
2 የገንዳ ጥገና
3 የመዘፊዘፊያ ቦይ ጥገና
4 ቋት ጥገና
5 ማሽን ጥገና
6 ግብይት ማዕከል ግንባታ
7 የአልጋ ስራ
8 የግቢ ምንጣሮ
9 የእጄታ ወንፊት ጥገና
10 የግቢ ጽዳት
11 ሚዛን ማስመረመር
12 ብቃት ማረጋገጫና ንግድ ፈቃድ ማደስ
13 ብድር ማፈላለግ
14 ግዥ ደረሰኝ ማሳተም
15 የእሸት ቡና ግዥ መፈጸም
16 የታጠበ ቡና ዝግጅት
17 የተዘጋጀ ምርት ገበያ ማቅረብ
o ባለፋት ዓመታት በሥራው ልምድና አቅም መፍጠሩ፣ o ገበያው በሚፈለገው መልኩ ሙሉ በሙሉ በጥራት
o የመንግስት ትኩረትና ድጋፍ ያለው መሆኑ፣ አለማዘጋጀት፤
17
ተባረክ እሸት ቡና ኃ/የተ/የግ/ማህበር የንግድ ሥራ እቅድ
ሃይል አስተዳደር፣ መጋዘን አስተዳደር፣ ሂሳብ ሰራተኛ፣ ጸሀፊና የጥበቃ ሰራተኛ ጨምሮ እንደየ ስራው ስፋትና የስራ
ወቅቱ የሚሟላ ከፍተኛ እውቀትና ሰለጠነ የሰው ሃይል ያስፈልጋል፡፡ የታጠበ ቡና ዝግጅት የሚዘጋጀው በአንድ
ድርጅታዊ ስትራክችር ስር እንደ የስራ ክፍሉ የሚደራጅ ሆኖ በአንድ ዋና ስራ አስኪያጅና ምትል ስራ አስኪያጅ ተጠሪነት
ሀኖ ይመራል፡፡ የቋሚ ሰራተኞቹ የደመወዝ ክፍያ የሀገሪቱን የኑሮ ሁኔታ፣ የፕሮጀቱን ትርፋማነትና አቅም ባገናዘበ ሁኔታ
ታይቶ ደመወዛቸው የሚወሰን ሲሆን 5% በየአመቱ የደመወዝ እድገት ይኖረዋል፡፡ በተጫማሪ ለሰራተኖቹ ከደመዎዝ
በተጨማሪ ሌሎች ጥቅማጥቅም 10% ቦነስ በያአመቱ ይታሰባል፡፡ በአጠቃላይ ተባረክ እሸት ቡና
ኃ/የተ/የግ/ማህበርድርጅት ድርጅታዊ መዋቅርና የሚያስፈልግ የሰው ሃይል ከዚህ በታች በተቀመጠው ስዕልና
ሰንጠረጅ መመልከት ይቻላል፡፡
18
ተባረክ እሸት ቡና ኃ/የተ/የግ/ማህበር የንግድ ሥራ እቅድ
ተባረክ እሸት ቡና ኃ/የተ/የግ/ማህበርድርጅት የንግድ የስራ እቅድ የታጠበ ቡና ዝግጅት በአንድ የምርት ወቅት
የሚከናወን ሲሆን ለታጠበ ለተከታታይ 90 የስራ ቀን ለቃሚ፣ አጣቢና የሚያደርቅ የጉልበት ሰራተኛ ያስፈልጋል፡፡
19
ተባረክ እሸት ቡና ኃ/የተ/የግ/ማህበር የንግድ ሥራ እቅድ
በአጠቃላይ በዚህ የምርት ወቅት 90 የቀን ሰራተኛ በፕሮጀክቱ እቅድ መሰረት ያስፈልጋል፡፡ ድርጅቱ የሴቶችን
ተጠቃሚነት ልዩ ትኩረት ስለሚሰጠው 60% የሚሆኑት ሴቶች ይሆናሉ፡፡ የክፍያው ሁኔታ እንደ ወቅቱ አካባቢ ተጨባጭ
የመቀነስና የመጨመር ሁኔታ እንዳለ ከግምት ውስጥ በማስገባት ለቀን ሰራተኛ የሚከፈለው በቀን ከ 35 እስከ 50 ብር
እንደሚደርስ በንግድ ስራ እቅዱ ታሳቢ ተደርጎ ተይዟል፡፡
ስሌቶች መነሻ የፋይናስ ስሌቶች የተወሰኑት አማካሪ ባለሙያው ከድርጅቱ ጋር ባደረገው ውይይትና በሀገራችን
የንግድ ስራ የሚያገለግሉ በወጡ የፋይናስ ስሌት ቀመር ዋቢ መረጃዎችን በመጨመር የንግድ ስራ እቅድ
working capital for follow-up of the project and Production/Operating cost) ለበለጠ መረጃ
ከታች በሰንጠረዥ መሰረት ቀርቧ፡፡
20
ተባረክ እሸት ቡና ኃ/የተ/የግ/ማህበር የንግድ ሥራ እቅድ
Description Basis Basis
Salaries Expenses As per salary estimations
Staff Benefits 10% of Payroll
Insurance 1% of equipment Cost
Administrations expense 6% of Sales
Production 99% of Sales
Selling Expenses 5 % of Sales
Utilities price growth
Water and electric city price growth rate % 5%
8.1.2 የምርት ውጤት ስሌት መነሻ ሀሳብ (Revenue Projections and Assumptions)
የምርት ኮንፈርሽን ሬሸዮ ስሌት የተወሰደው ከዚህ በፊት ከተሰሩ የታጠበ ቡና ውጤ አወሳሰድ በምርም ከተገኙ
መረጃዎች ነው፡፡
ሲሰላ ማሽኑ በቀን 6 ሰዓት እደሚሰራ፣ ምርት ለማዘጋጀት 78 የስራ ቀናት እንደሚፈጅ ታሳቢ የተደረገ ሲሆን
በአጠቃላይ ከታጠበ ቡና ዝግጅት የተገኘውን 17ኪ/ግ ንጽህ የታጠበ ቡና 400 ብር ለመሸጥ እና ተንሳፋፊና ልቃሚ
ቅሽር 17ኪ/ግ 125 ሂሳብ ብር ያልተጣር ሽያጭ ገቢ እንደሚገኝ ታሳሚ በማድረግ በድምሩ ከታጠበ ቡና ከነሸሚዙና
ከተንሳፋፊና ልቃሚ ቅሽር በ2016 በጀት አመት 68,569,000 ብር የፕሮጀክቱ የሽያጭ ገቢ ይሆናል፡፡ ዝርዝር
21
ተባረክ እሸት ቡና ኃ/የተ/የግ/ማህበር የንግድ ሥራ እቅድ
ምርት
የታጠበ ንጽሁ ቡና በኪ/ግ 166500
ተንሳፋፊና ልቃሚ ቅሽር በኪ/ግ 15750
የሽያጭ ዋጋ
የታጠበ ቡና ከነሸሚዙ ብር 400
ያልተጣራ ሽያጭ ገቢ
ከታጠበ ቡና ከነሸሚዙ ብር 66,600,000
ማዘጋጃ ወጪ ማለትም የጥሬ ምርት ግዥ፣ የታጠበ ቡና ማዘጋጃ ወጪ፣ የምርት ማጓጓዣ፣ የምርት አቅርቦት
ማጓጓዣ እና ለስራ አስተዳደር ማለትም የደመወዝና የጉልበት ክፍያ፣ የማጠቢያ ኢንዱስትሪው ኦቨርሄድ ወጪ
22
ተባረክ እሸት ቡና ኃ/የተ/የግ/ማህበር የንግድ ሥራ እቅድ
ለጉልበት(Lobar cost) 221,250.00 221,250.00
በ 2016 ዓ.ም እሸት ቡና ከአርሶ አደሮች በማሰባሰብና በማዘጋጀት ለኢትዮጵያ ምርት ገበያ ለማቅረብ ለምርት ግዢ እና
100% ከየኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በብድር የሚቀርብ ይሆናል፡፡ ለበለጠ መረጃ ከላይ ሰንጠረዥ 8.2 የተመለከተውን
መመልከት ይቻላል፡፡
23
ተባረክ እሸት ቡና ኃ/የተ/የግ/ማህበር የንግድ ሥራ እቅድ
8.3 የንግድ ስራው ፋይናስ አዋጭነት (FINANCIAL VIAITYBIL)
የድርጅቱ ትርፍና ኪሳራ ማመዛዘኛ ትንታኔ እደሚያመለክተው ጠቅላላ የስራና አስተዳደራዊ ወጭና
የመንግስት ታክስ ወጪ ክፍያ ተቀንሶ ጭምር የድርጅቱ የተጣራ ትርፍ ብር 15.782 ሚሊዮን በ 2016 በጀት
አመት የሚጠበቅ ሲሆን ይህ የድርጅቱ ስራ በቀጣይ አራት ተከታታይ አመታታ የሚቀጥል በመሆኑ የቀጣውም
አመታት አዋጭነት አብሮ የተሰራ ስለሆነ ዋቢነት በተገለጸው እዝል /Annuxe 2.1/ ላይ መመልከት ይቻላል፡፡
ድርጅቱ በሚያገኘው የብድር ምንጭ መሰረት የገቢና ወጭ አተገባበር የገንዘብ ፍሰት ትንተና መረጃ ውጤት
እደሚያሳየው ለስራው በቂ ገንዘብ ድርጅቱ እደሚኖረው እና ስራው ለሚፈልገው ወጪና ብድሩ በመመለስ
ረገድ ችግር እደማያስከትል ለስራው መሀል ተጨማሪ የገንዘብ ፍላጎት እደማይፈጥር ስሌቱ ጤናማ የገንዘብ
ፍሰት ያሳያል፡፡ በተጨማሪም ጤናማ የገንዘብ ገቢና የወጪ ፍሰት የሚያመለክት በመሆኑ ከባንክ የሚገኘውን
ብር በመመለስ ረገድ ችግር ካለመፍጠሩም በላይ የሚመረተውን የቡና ምር አዋጭ ዋጋ ሲገኝ ጠብቆ ለመሽጥ
መደላድል ይፈጥራል፡፡ በዚህም ድርጅቱ ጤናማ የገንዘብ ፍሰትን በመቆጣጠር የሚያስከትለውን ኪሳራ
ያስወግዳል፡፡ ስለሆነም የድርጅቱ የገንዘብ ብድር ፍሰት ከመነሻው ዓመት ጀምሮ ጤናማ የመሆኑን በባላንስ ሽት
ስሌት የሚያሳይ ስለሆነ የድርጅቱ ስራ አዋጪነት ያለው መሆን ማረጋገጥ ተችላል፡፡ ለበለጠ መረጀ
የፀጋ፣ ወጨና ኪሳራ ማመዛዘኛ ስሌት እንደሚያመለክተው በብድር የሚገኘው የገንዘብ ምንጪ በበቂ ሁኔት የድርጅቱን
የታጠበ ቡና ስራ የሚያሰራ በቂ ሁኔታ የሚያጠናክር የገንዘብ ምንጪ እደሚሆን ይጠቁማል፡፡ ስለሆነም ተባረክ እሸት ቡና
ኃ/የተ/የግ/ማህበር የታጠበ ቡና ማዘጋጃ ንግድ ስራ ጤናማ የተጣራ ገቢና ጤናማ የገንዘብ አቋም እንዳለው ያሳያል፡፡
ስለሆነም ድርጅቱ በስራው ላይ ምንም አይነት አስቸጋሪ ሁኔታን ወይም ምንም አይነት አስገዳጅ እዳ ውስጥ እደማያስገባ
የሚያመለክት እንዳሁም በበለጠ ድርጅቱ የተነሳበትን የንግድ ስራ ዓላማ በሙሉ አቅሙ ማሳካት እደሚችል የፀጋ፣
ወጨና ኪሳራ ማመዛዘኛ (BALANCE SHEET) ስሌቱ ያረጋግጣል፡፡ ለበለጠ መረጃ በዋቢነት /Annexure-2.3/ ላይ
24
ተባረክ እሸት ቡና ኃ/የተ/የግ/ማህበር የንግድ ሥራ እቅድ
8.4 የድርጅቱን የገንዘብ አጠቃቀም መገምገም (FINANCIAL EVALUATION)
የድርጅቱ ንግድ ስራ ብድር የመመለስ ደረጃ /IRR / ስሌት ከመንግስት ታክስ ክፍያ በፊት 383% ሲሆን 603%
ከመንግስት ግብር ክፍያ በኋል እና ኔት ፐርስነተ ቫልዩ (net present value at 10 % discount rate) ብር
ከዜሮ የሚበልጥ በመሆኑ የወጪና ገቢ ሚዛንን ስሌቱን እዋጭ መሆኑን ያሳያል፡፡ በመሆኑም የዚህ ሬሽዮ
መለኪያ ህግጋት መሰረት የ IRR ውጤቱ ከዜሮ የበለጠ ስለሆነ የንግድ ስራው አዋጭነት ያለው መሆኑን
ያረጋግጣል፡፡.
25
ተባረክ እሸት ቡና ኃ/የተ/የግ/ማህበር የንግድ ሥራ እቅድ
8.4.3 የ 2016 ብድር አከፋፍል ሁኔታ (Loan Repaymebt Schdule)
ተባረክ እሸት ቡና ኃ/የተ/የግ/ማህበርቡና ማዘጋጃ ኢንዱስትሪ የንግድ ስራ እቅድ በ 2016 ዓ/ም ለታጠበ ቡና ምርት
ማዘጋጃና የግብይት የስራ ማስኬጃ ጨምሮ አዲስ ብድር ብር 39,703,309.24 ሲሆን ከታች በሰንጠረዥ በተጠቀሰው
መሰረት ይሆናል፡፡ ስለሆነም የ 2016 በጀት ዓመት ብድር የመክፈያ ጊዜ ሰሌዳ መሰረት የሚከፈል ሲሆን የብድር
26
ተባረክ እሸት ቡና ኃ/የተ/የግ/ማህበር የንግድ ሥራ እቅድ
ይህም ውጤት የድርጅቱን የታጠበ ቡና የማምረት እቅድ የሚያጠናክር ስሲሆን ምርትን ያለኪሳራ ለመሸጥ
ሁኔታን ይፈጥራል፡፡ እንድሁም የቡና አምራቹን ተጠቃ የሚያደርግ አሰራር ስለሚፈጥር ከአምራቹ ጋር
ድርጅቱን ያስተሳስራል በዚህም ከአምራቹ ጥራት ያለው የቀይ እሸት ቡና አቅርቦት ያለችግር ማግኘት
ያስችላል፡፡ በሌላ በኩል እንደስጋት የተቀመጠውን የገበያ ተወዳዳሪት በተለይም የቡና አምራች ህብረት ስራ
ማህበራት ምርታቸውን በውጭ ስለሚሰጡ ጠጨማሪ ፕርሜር ክፍያ ስለሚአገኙ የማህበሩ አባል ያልሆኑ አርሶ
አደሮች ምርታጨውን ለህብረት ስራ ስለሚሸጡ የቀይ እሸት ምርት የማግኘት ተግዳሮት ድርጅቱን
መከተል ያፈልጋል፡.
የስራ ማስኬጃ ፍላጎት በስ ላይ ለማዋል በመሻነት የተወሰዱት የትንተና ኖርም መሰረት ስራውን
በማከናወን ድርጅቱ ትርፋማ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ በመሆኑም ይህ የንግድ ስራ እቅድ ጤናማ የሆነ
የገንዘብ ፍሰት ያከለው በመሆኑ የሚፈጠረውን የገንዘብ ግሽበትና ማክሮ ኢኮኖሚ ሁነታዎችን
ማረጋጋት ይችላል፡፡ የድርጅቱን ትርፋማ ለማረጋገጥ የቡና አምራች አርሶ አደሮችን በታጠበቡና
በመፍጠር በቂ የእሸት ቡና ምርት አቅርቦት መፍጠ የሚስችል ተግባር የትኩረት አቅጣጫ በማድረግ
27
ተባረክ እሸት ቡና ኃ/የተ/የግ/ማህበር የንግድ ሥራ እቅድ
መስራት ያስፈልጋል፡፡. በመጨራሻም የንግድ ስራ እቅዱ ውጤታማ እንድሆን ከፍተኛ ጥራት ያለው
28
ተባረክ እሸት ቡና ኃ/የተ/የግ/ማህበር የንግድ ሥራ እቅድ
Rate ( % ) Y0 Y1
Description ye
Building 5% 4,105 205
Machinery 10% 1,091 109
Equipment 10% 1,033 103
Furniture and Fixtures 20% 52 10
Motor & vehicles 15% 1,600 240
Pre-operating cost 20% 311 62
Total (000 birr) 8,192 462
29
ተባረክ እሸት ቡና ኃ/የተ/የግ/ማህበር የንግድ ሥራ እቅድ
ANNEXTURE-2
34
ተባረክ እሸት ቡና ኃ/የተ/የግ/ማህበር የንግድ ሥራ እቅድ
2.2 PROJECTED CASH FLOWS
Year Y0 2016
Net income 15,782
Plus depreciation 463
Less increase in inventory - (3,105)
Less increase in accounts receivable - (3,428)
Plus increase in accounts payable - 1,165
Cash flow from operations - 10,875
Less investment - -
Cash flow from operations and invests 3,156 10,875
Plus net new equity capital raised - -
Less dividends paid - -
Plus net new long-term debt - 39,703
Plus net new bank borrowings - 3,156
Cash flow from ops, and fin - 53,734
Beginning cash balance - -
Ending cash balance - 53,734
36
ተባረክ እሸት ቡና ኃ/የተ/የግ/ማህበር የንግድ ሥራ እቅድ
2.4 PROJECTED INTERNAL RATE OF RETUREN (000 Birr)
36