You are on page 1of 53

ክፍል አንድ፡- አጠቃላይ ሁኔታ

1.1 መግቢያ
የፌዴራል ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ በአገር አቀፍ ደረጃ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስርዓት በመዘርጋት የኩነቶች

ምዝገባ ወጥና ቀጣይነት ባለው የአሰራር ስርዓት ላይ እንዲመሰረት ተግባሩን በበላይነት የማስተባበር፣ በአገር

ደረጃ ከኩነቶች ምዝገባ የተገኘውን መረጃ በማእከል አደራጅቶ በመያዝ ለአገሪቱ ፖሊሲ ቀረጻ፣ ስትራቴጂክ

እቅድ አቅጣጫ፣ ለማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ለተለያዩ ፕሮግራሞች እቅድ ብቁና ጥራቱን የጠበቀ መረጃ

የማቅረብ ተልዕኮ የተሰጠው ተቋም ነዉ::

ኤጀንሲዉ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ በመላ አገሪቱ ተግባራዊ ከተደረገበት ጊዜ ጀምሮ በህግ የተሰጠውን ተግባርና

ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት በምዝገባ ቅድመ ዝግጅት ወቅት አመታዊ እቅዱን በማዘጋጀትና ፈጻሚ ፣

ባለድርሻና ተባባሪ አካላት በእቅዱ ዙሪያ የጋራ መግባባት እንዲፈጥሩ በማድረግ የምዝገባ ስራዉ በመላ አገሪቱ

እንዲጀምር ተደርጓል፡፡

የምዝገባ ስራዉ ከተጀመረ በኋላም በምዝገባ ሂደት ላይ ያጋጠሙ ችግሮችን በመለየት እና ከመዝጋቢ እና

ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በመስራት የአዋጅ ማሻሻያ ጨምሮ በርካታ ማስተካከያዎች የተደረጉ ሲሆን

በየደረጃዉ የሚገኘዉን መዝጋቢ አካል አቅም ለማሳደግ የሚያስችሉ ስልጠናዎችን በስፋት በመስጠት

እንዲሁም ህብረተሰቡ በወሳኝ ኩነት ምዝገባ ዙሪያ ግንዛቤ በመፍጠር ተሳትፎዉን ሊያሳድጉ የሚችሉ የግንዛቤ

ማሥጨበጫ መድረኮችን በማዘጋጀት የምዝገባ ስራዉ ዉጤታማ እንዲሆን ለማድረግ ሰፊ ርብርብ ሲደረግ

ቆይቷል፡፡

በመላ አገሪቱ የተጀመረዉን የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስራ ቀጣይነት ለማረጋገጥ የተከናወኑ ስራዎች አበረታች

ቢሆኑም የምዝገባ ስራዉን በሚፈለገዉ ፍጥነት እና የጥራት ደረጃ በማከናወን ረገድ ፈታኝ ሁኔታዎች

ያጋጠሙ ሲሆን በተለይም በየደረጃዉ የሚገኘዉ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ መዋቅር የምዝገባ ስራዉን የተሟላ

እዉቀት እና ክህሎት ይዞ በመምራት ረገድ ዉስንነት ያለበት መሆኑ ፣ የምዝገባ ስራዉን ተግባራዊ በማድረግ

ረገድ ወሳኝ ድርሻ ያለዉ የቀበሌ ስራ አስኪያጅ ለስራዉ ተገቢዉን ትኩረት በመስጠትና ባለቤት ሆኖ

1
በመፈጸም ረገድ ክፍተት ያለበት በመሆኑ በምዝገባዉ ጥራት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ያሳደረ መሆኑ ፣ በየደረጃዉ

የሚገኙ የዘርፉ ባለድርሻ አካላት ስርአቱን በመደገፍ ረገድ የሚጠበቅባቸዉን ሚና በሚፈለገዉ ደረጃ እየተወጡ

አለመሆኑ ፣ የምዘገባ ስራዉ በሁሉም የምዝገባ ጽ/ቤቶች አለመጀመር እንዲሁም የወሳኝ ኩነት ምዝገባ

ስራዉን ዉጤታማ በማድረግ ረገድ ወሳኝ ሚና ያለዉ የጤናዉ ዘርፍ ሃላፊነቱን በሚፈለገዉ ደረጃ

አለመወጣት በምዝገባዉ አጀማመር ላይ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እንደነበሩ አፈጻጸሙ ያሳያል፡፡

በመሆኑም የምዝገባዉን ቀጣይነት ለማረጋገጥ እንዲቻል በምዝገባዉ አፈጻጸም ላይ የታዩ ጠንካራ አፈጻጸሞችን የበለጠ

ተጠናክረዉ እንዲቀጥሉ ለማድረግ እንዲሁም ከምዝገባ ፍጥነት ፣ ተደራሽነትና ጥራት ጋር ተያይዞ በተለዩ ቁልፍ ችግሮችና

በቀጣይ የመፍትሄ አቅጣጫዎች ዙሪያ በየደረጃዉ ከሚገኘዉ መዝጋቢ እና ባለድርሻ አካላት ጋር የጋራ መግባባት በመፍጠር

የምዝገባ ስራዉ አስተማማኝ መሰረት ላይ እንዲያርፍ ለማድረግ እንዲቻል በኤጀንሲ ደረጃ የኤጀንሲዉን የ 2009-

2012 ስትራቴጅክ እቅድ ፣ የኤጀንሲዉን የ 2009 በጀት አመት እቅድ አፈጻጸም ፣ የተገልጋይ እና ባለድርሻ

አካላት ፍላጎት መነሻ በማድረግ በ 2010 በጀት አመት ሊከናወኑ የሚገባቸዉን ግቦች፣ ዋና እና ዝርዝር

ተግባራት ፣ በእቅድ አፈጻጸም ወቅት ተግባራዊ የሚደረግ የድጋፍና ክትትል ስርአት እንዲሁም በአፈጻጸም ወቅት

የሚያጋጥሙ ችግሮች፣ መፍትሔዎች እና የቀጣይ አቅጣጫ የሚያመላክት እቅድ እንዲዘጋጅ ተደርጓል፡፡

1.2 የኤጀንሲው ራዕይ፣ተልዕኮና እሴቶች

 የኤጀንሲው ራዕይ /VISION/

በ 2017 የኩነቶች ምዝገባ ለዜጐች ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ተጠቃሚነት፣ ለሕግ የበላይነት እና

ተጠያቂነት በመላ ሀገሪቱ ዋነኛና አስተማማኝ የመረጃ ምንጭ ሆኖ ማየት፣


2
 የኤጀንሲው ተልዕኮ /MISSION/

 ስለ ኩነት ምዝገባ አገራዊ ፋይዳ ህብረተሰቡ ያለውን ግንዛቤ በማሳደግ፤ የኩነት መረጃ በመልካም

ፈቃደኝነት እና ተነሳሽነት የማስመዝገብ ባህልን ማጐልበት፣

 ዘመናዊ የአሰራር ስርዓትን በመጠቀም ደህንነቱ የተረጋገጠ የኩነት መረጃ በብቃትና በጥራት

በመሰብሰብ ለፖሊሲ ቀረፃ፣ለአገራዊ ስትራቴጂ አቅጣጫ እና ለማህበራዊ አገልግሎት ጥቅም

እንዲውል ማድረግ፣

 በጥናትና ምርምር አዳዲስ የአሰራር ስልት በመቀየስ በአገር አቀፍ ደረጃ ወጥ እና ዘመናዊ የመረጃ

ቅብብሎሽ ስርዓት መገንባት ነው፡፡

 የኤጀንሲው ዕሴቶች

 የሕብረተሰቡን መረጃ ደህንነት መጠበቅ፣

 አሳታፊነት እና ፍትሃዊ ተጠቃሚነት፣

 ፈጣንና ውጤታማ አገልግሎት፣

 ግልጸኝነትና ተጠያቂነት፣

 ምስጢር ጠባቂነት፣

ክፍል ሁለት፡- የእቅዱ መነሻ ሁኔታዎች


የፌዴራል ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ የ 2010 በጀት አመት እቅድ ሲዘጋጅ በዉጫዊ ሁኔታ ዳሰሳ ላይ ክልሎችና

የከተማ አስተዳደሮች ፣ የወሳኝ ኩነቶችን የሚመዘግቡ የፌዴራል ተቋማት እና የባለድርሻና ተባባሪ አካላት ስርአቱን

በመደገፍ ረገድ የነበራቸዉን ሚና በጥንካሬና በድክመት የተዳሰሰ ሲሆን በዉስጣዊ ሁኔታ ዳሰሳ ላይም የኤጀንሲዊ

የመሰረታዊ የስራ ሂደት (BPR) ጥናት ሰነድ ፣ የኤጀንሲው ሚዛናዊ ውጤት ተኮር (BSC) 2009 - 2012 ዓ.ም

ጥናት ሰነድ እንዲሁም አገራዊ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ምክር ቤት ፣ የኤጀንሲው የስራ አመራር ቦርድ እና የኤጀንሲዉ

3
አመራር እና ፈጻሚ ስርአቱን በመደገፍ ረገድ የነበራቸዉን ሚና በጥንካሬና በድክመት በመዳሰስ ለእቅዱ እንደ መነሻ

ሁኔታ ተደርገው ተወስደዋል፡፡

2.1 ውጫዊ ሁኔታ

2.1.1 የክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ሁኔታ

 በአመለካከት ረገድ

 ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የምዝገባ ስራዉ ለህዝቡ ቀጣይ እድገት ጠቃሚ መሆኑን በእምነት በመያዝ

እና መረጃዉ ለተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ እንዳለዉ በአመለካከት በመዉሰድ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ

አሰራር ስርአቱን ተግባራዊ በማድረግ ሂደት ፈታኝ ሁኔታዎች ቢኖሩም ማሳካት ይቻላል የሚል እምነት እና

አመለካከት በመያዝ ምዝገባዉን በሁሉም የአገሪቱ ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች እውን እንዲሆን

ለማድረግ ያደረገዉ ጥረት እና የነበረዉ ተነሳሽነት አበረታች ነዉ፡፡

 በክልል እና ከተማ አስተዳደር ደረጃ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስርአቱን እዉን ለማድረግ እንዲቻል የተደረገዉ

ጥረት አበረታች ቢሆንም የምዝገባ ስራዉን ዉጤታማ ለማድረግ በሚደረገዉ ጥረት በየደረጃዉ ከሚገኙ ወሳኝ

ባለድርሻ አካላት ጋር ጠንካራ ቅንጅት በመፍጠር በጋራ መስራት ወሳኝ ተግባር መሆኑን በእምነት በመያዝ እና

ለተግባራዊነቱ በሚፈለገዉ ደረጃ በመንቀሳቀስ ረገድ ክፍተት የነበረ ሲሆን የምዝገባ ስርአቱን ተግባራዊ

በማድረግ ሂደት የሚያስፈልጉ ግብአቶችን በራስ ተነሳሽነት በማሟላት ረገድ በአመለካከት ደረጃ ችግሮች

የነበሩ መሆኑን በተለያየ ጊዜ የተደረጉ ግምገማዎች ያመላክታሉ፡፡

 ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የምዝገባ ስርአቱን እዉን በማድረግ ረገድ ያሳዩት አበረታች ጥረት እንዳለ ሆኖ

የምዝገባ ስራዉ ከጀመረ በኋላ የምዝገባ ጥራት እና ሽፋን በሚፈለገዉ ደረጃ እንዲደርስ ከማድረግ አንጻር

ክፍተት የታየ ሲሆን በክልል እና ከተማ አስተዳደር ደረጃ ከአመለካከት አንጻር የታዩ ክፍተቶችን በቀጣይ እቅድ

በማካተት ትኩረት ተሰጥቶት እንዲፈታ ማድረግ ይጠበቃል፡፡

 በክህሎት ረገድ

 የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስራዉን ተግባራዊ በማድረግ ሂደት ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች በፌዴራል ደረጃ

የተሰጡ ስልጠናዎችን መነሻ በማድረግ በራስ አቅም ስልጠና በመስጠት እና የምዝገባ መመሪያዉን የማስተግበር

አቅማቸዉ እየተሻሻለ የመጣ መሆኑ እንዲሁም በምዝገባ አፈጻጸም ሂደት ላይ የታዩ የአፈጻጸም ችግሮችን

በራስ አቅም በመፍታት ረገድ ያሳዩት እንቅስቃሴ አበረታች መሆኑን የምዝገባ አፈጻጸሙ ያሳያል፡፡

4
 ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስራዉን በራስ አቅም ለመምራት የሚያደርጉት ጥረት

አበረታች ቢሆንም ምዝገባዉን በፌዴራል እና በክልል የስራ ቋንቋ ተጠቅሞ በማከናወን ፣ ምዝገባዉን

በሚፈለገዉ የጥራት ደረጃ እና የሚፈለጉ መሰረታዊ መረጃዎችን በሚያሟላ ሁኔታ ተግባራዊ በማድረግ ፣

በየደረጃዉ ያለ ፈጻሚ አካል መረጃን በሚፈለገዉ ደረጃ በማጣራት ረገድ ክፍተት ያለበት መሆኑ እንዲሁም

መረጃ አደራጅቶ በመያዝ እና ለአገልግሎት ዝግጁ በማደረግ ረገድ ክፍተት ያለ መሆኑ የምዝገባ አፈጻጸሙ

የሚያሳይ ሲሆን በክልል እና ከተማ አስተዳደር ደረጃ በክህሎት ረገድ የታዩ ክፍተቶችን በቀጣይ እቅድ በማካተት

ትኩረት ተሰጥቶት እንዲፈታ ማድረግ ይጠበቃል፡፡

 ከአሰራርና አደረጃጀት አንጻር

 የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስርአቱን ተግባራዊ ለማድረግ እንዲቻል ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ተቋማዊ

አደረጃጀታቸዉን እና የአሰራር ስርአታቸዉን እንዲመልሱ የማድረግ ስራ ትኩረት ተሰጥቶት የሚሰራ ቁልፍ

ስራ ነዉ፡፡ በዚህ መሰረት ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስርአቱን ተግባራዊ ለማድረግ

በፌዴራል ደረጃ የወጣዉን የወሳኝ ኩነት ምዝገባ አዋጅ መሰረት በማድረግ የምዘገባ ደንብ በማዘጋጀት እና

እንዲጸድቅ በማድረግ እንዲሁም በፌዴራል ደረጃ ተዘጋጅተዉ የሚላኩ የአፈጻጸም መመሪያዎችን ወደ ስራ

በማስገባት ረገድ የተሻለ እንቅስቃሴ በማድረግ ምዝገባዉ እንዲጀምር ያደረጉ መሆኑ በጥንካሬ የሚወሰድ

ነዉ፡፡

 በሌላ በኩል የምዝገባ ስራዉን ቀጣይነት ለማረጋገጥ እንዲቻል ከክልል ጀምሮ እስከ ታችኛዉ የአስተዳደር

መዋቅር ድረስ ተቋማዊ አደረጃጀቱን ከመመለስ ባሻገር የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስርአቱን ከማጠናከር አንጻር

ወሳኝ ድርሻ ያላቸዉን የህዝብ አደረጃጀቶችን በመጠቀም ወደ ስራ እንዲገቡ በማድረግ ረገድ አበረታች

እንቅስቃሴ ያደረጉ ሲሆን ይህም የምዝገባ ስርአቱን በማስቀጠል ረገድ በጎ አሰተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡

 ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ተቋማዊ አደረጃጀታቸዉን እና የአሰራር ስርአታቸዉን በመመለስ እና

የምዝገባ ስራዉን እዉን በማድረግ ረገድ የሰሩት ስራ አበረታች ቢሆንም በክልል እና በከተማ አስተዳደር ደረጃ

የሚገኙ ሁሉንም የምዝገባ አደረጃጀቶች በተሟላ ደረጃ የምዝገባ ስራዉን እንዲጀምሩ በማድረግ ረገድ

ክፍተት ያለ ሲሆን በተለይም የምዝገባ ስራዉን በማከናወን ረገድ ወሳኝ ድርሻ ያለዉ የቀበሌ መዋቅር

5
ተጠሪነቱ ለሌላ አካል መሆኑ ምዝገባዉን ዉጤታማ በማድረግ ረገድ ተግዳሮት መሆኑን የምዝገባዉ አፈጻጸም

ያሳያል፡፡

 በሌላ በኩል በምዝገባዉ ሂደት ዉስጥ ከሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት ጋር ጠንካራ እና ዉጤታማ

ቅንጅታዊ አሰራር ዘርግቶ በመንቀሳቀስ እና የሚላኩ ሪፖርቶችን እና መረጃዎችን በወቅቱና በትክክለኛ

መረጃ ላይ ተመስርቶ በመላክ ረገድ ክፍተት ያለ በመሆኑ በቀጣይ ትኩረት ሰጥቶ እንዲፈታ ማድረግ ይገባል፡፡

 በግብአት ረገድ

 የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስራን ተግባራዊ በማድረግ ሂደት በየደረጃዉ የሚገኙ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ መዋቅር

ተቋማዊ የሰዉ ሃይሉን እና የምዝገባ ግብአቶችን በወቅቱ እና በሚፈለገዉ መጠን እንዲያሟሉ የማድረግ ስራ

ወሳኝ ተግባር ተደርጎ የሚወሰድ ነዉ፡፡

 ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ለምዝገባ ስራዉ አስፈላጊ የሆኑ የሰዉ ሃይል እና የምዝገባ ግብአቶችን

በማሟላት ረገድ አበረታች እንቅስቃሴ ያደረጉ ሲሆን በዚህ ረገድ ከክልል ጀምሮ እስከ ወረዳ ባለዉ መዋቅር

አስፈላጊዉ የሰዉ ሃይል በአይነት እና በመጠን በማሟላት ወደ ስራ እንዲገባ በማድረግ ረገድ አበረታች

እንቅስቃሴ ያደረጉ ሲሆን በሌላ በኩል ምዝገባዉን ለማከናወን የሚያስችል የክብር መዝገብ እና የምስክር

ወረቀት እንዲሟላ እንዲሁም ለምዝገባ ስራዉ አስፈላጊ የሆኑ ሌሎች ግብአቶች እንዲሟላ በማድረግ ረገድ

አበረታች ስራ መስራት ተችሏል፡፡

 በክልል እና ከተማ አስተዳደር ደረጃ የምዝገባ ስራዉን ለማስጀመር የሚያስችል ግብአት በማሟላት ረገድ

የተከናወኑ ተግባራት ያሉ ቢሆንም የምዝገባ ስራዉን ለማስቀጠል የሚያስችል በቂ በጀት በመመደብ

የምዝገባ ስራዉ ለማከናወን የሚያስችል በቂ ቢሮ እና የመረጃ ማደራጃ ቦታ በማዘጋጀት ፣ በየደረጃዉ

የሚገኘዉን መዝጋቢ አካል ለመደገፍ የሚያስችል ተሽከርካሪ በመመደብ ረገድ ክፍተት ያለ በመሆኑ

በየደረጃዉ የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት እንዲሰሩ በእቅድ በማካተት መስራት ይገባል፡፡

6
 ከድጋፍና ክትትል አንፃር

 የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስርአቱን ቀጣይነት ለማረጋገጥ እንዲቻል በየደረጃዉ የሚገኘዉን

መዝጋቢ አካል በምዝገባ ወቅት የሚያጋጥመዉን ችግር ሊፈታ የሚችል የድጋፍ እና ክትትል

ስርአት በመዘርጋት ተግባራዊ ማድረግ ወሳኝ ተግባር ተደርጎ የሚወሰድ ነዉ ፡፡

 በዚህ ረገድ ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች በየደረጃዉ የሚገኘዉን መዝጋቢ አካል

የመፈጸም አቅም ለማሳደግ እና በምዝገባ ሂደት ላይ ያጋጠሙ ችግሮችን ለመፍታት

የሚያስችል የድጋፍ እና ክትትል ስራ እየሰሩ ሲሆን በፌዴራል ደረጃ የሚሰጡ ድጋፎችን

መሰረት በማድረግ በተጨባጭ ያጋጠሙ ችግሮችን በመፍታት ረገድ አበረታች ጥረት

አድርገዋል፡፡

 በሌላ በኩል በበድጋፍ እና ክትትል ወቅት የተለዩ ችግሮችን በራስ አቅም በመፍታት እንዲሁም

ከአቅም በላይ የሆኑ ችግሮችን ከፌዴራል ጋር በጋራ ተቀናጅቶ እንዲፈታ በማድረግ ረገድ

አበረታች እንቅስቃሴ ተደርጓል፡፡

 የምዝገባ ስርአቱን ቀጣይነት ለማረጋገጥ እንዲቻል በክልል እና ከተማ አስተዳደር ደረጃ የተሰሩ ስራዎች ያሉ

ቢሆንም የድጋፍና ክትትል ስራዉ ክፍተትን የለየ እና በእቅድ እንዲመራ በማድረግ እንዲሁም ዉጤት ላይ

መሰረት ያደረገ የድጋፍ እና ክትትል ስራ በመስራት ረገድ ክፍተት ያለ ሲሆን የምዝገባ ስራዉን ዉጤታማነት

ለማረጋገጥ የሚያስችል የድጋፍና ክትትል ስርአት እንዲዘረጋ ለማድረግ ትኩረት በመስጠት የሚሰራ ይሆናል፡፡

2.1.2 የወሳኝ ኩነቶችን የሚመዘግቡ የፌዴራል ተቋማት ሁኔታ፣

 በፌዴራል ደረጃ ኩነቶችን እንዲመዘግቡ በህግ ኃላፊነት የተጣለባቸው ተቋማት የአገር መከላከያ

ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ድርጅት፣ የውጭ ጉዳይ

7
ሚኒስቴር እና በብሄራዊ የመረጃ እና ደህንነት አገልግሎት የስደተኞችና ከስደት ተመላሽ ጉዳይ

አስተዳደር ናቸዉ ::

 የፌዴራል ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ የወሳኝ ኩነቶችን የሚመዘግቡ የፌዴራል ተቋማት የምዝገባ

ስራዉን ለመጀመር እንዲችሉ ለእያንዳንዳቸዉ የሚያገለግሉ የክብር መዝገብ ቅጽ፣ ምስክር ወረቀትና

የተጠቃለለ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ፣ የመረጃ አደረጃጀት፣ ቅብብሎሽ፣ አያያዝና አቅርቦት አፈፃፀም

መመሪያ እንደ ተቋማቱ ተጨባጭ ሁኔታ የማዘጋጀት ስራ የተሰራ መሆኑ እንዲሁም ተቋማቱ ቀድሞ

በነበረዉ ተቋማዊ አደረጃጀታቸዉ አማካይነት በመደበኛ ስራቸው የተፈጠሩ አደረጃጀቶች እና

የተዘረጉ የአሰራር ስርአቶች በመጠቀም የምዝገባ ስራዉን ለማከናወን የሚያስችል ምቹ ሁኔታ ያለ

መሆኑ በቀጣይ ተቋማቱ ለሚያከናዉኑት የምዝገባ ስራ ወሳኝ ግብአት በመሆን የሚጠቅም መሆኑን

ያሳያል፡፡

 በተቋማቱ የምዝገባ ስራዉን ለመጀመር የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎች ያሉ ቢሆንም ተቋማቱ በቀጣይ

የምዝገባ ስራዉን ለማከናወን ከኤጀንሲዉ ጋር በተፈጠረዉ የጋራ መግባባት መሰረት በቅድመ ዝግጅት

ደረጃ የሚከናወኑ ተግባራትን ትኩረት ሰጥቶ በማከናወን፣ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስርአቱን አገራዊ

ፋይዳ በመገንዘብ ለስራዉ ባለቤት ሆኖ በመንቀሳቀስ እና ተግባሩን ተቋማዊ አጀንዳ እንዲሆን

በማድረግ ረገድ ዉስንነት ያለባቸዉ ሲሆን የተጣለባቸውን የስራ ሃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ

ለማድረግ የጋራ እቅድ በማዉጣትና አፈጻጸሙን በታቀደ የጋራ ምክክር መድረክ በመገምገም የምዝገባ

ስራዉን ለመጀመር የሚያስችል ሰፊ ስራ መሰራት አለበት፡፡

2.1.3 የባለድርሻ አካላት ሁኔታ

 የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስርአት የባለ ብዙ ዘርፍ ባህሪ ያለዉ እና በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች በወጥነት ተግባራዊ የሚሆን

በመሆኑ ከወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስርአት ጋር ተያያዥነትና ትስስር ያለዉ ተልእኮ የተሰጣቸዉ ተቋማት ጋር በጠንካራ ግንኙነት

ላይ የተመሰረተ ቅንጅት መፍጠር ወሳኝ ጉዳይ ተደርጎ የሚወሰድ ነዉ፡፡ በመሆኑም ስርአቱን ከመደገፍ አንጻር ከቁልፍ

ባለድርሻ አካላት ጋር ለወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ መነሻ የሚሆኑ የተለያዩ ተግባራት ተከናውነዋል፡፡

 ለአብነት ለመጥቀስ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስራዉን ከመደገፍ አንጻር አፈጻጸሙን በየጊዜዉ

በመገምገም እና ድጋፍ በመስጠት እንዲሁም የምዝገባ ስራዉ ያለበትን የአፈጻጸም ደረጃ ሊያሳይ የሚችል ዳሰሳ በማድረግ

ግብረ መልስ በመስጠት ድጋፍ እያደረገ መሆኑ ፣ የፍትህ ዘርፉ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስርአቱን በመምራት እና በመደገፍ

8
ረገድ እያበረከተ ያለዉ አስተዋጽኦ አበረታች መሆኑ ፤ በጤና ተቋማት የሚከሰቱ ውልደትና ሞትን ለመመዝገብ

እንዲቻል ከጤናው ዘርፍ ጋር የጋራ መግባቢያ ሰነድ መፈራረም መቻሉ በቀጣይ ስርአቱን በመገንባት ሂደት ምቹ

ሁኔታ ያለ መሆኑን ያመላክታል::

 በሌላ በኩል በትምህርት ዘርፍ በኩል እድሜያቸዉ ለትምህርት የደረሱ ህጻናትን መረጃ መሰረት በማድረግ

የትምህርት ተሳትፎ እና ተደራሽነት ለማሻሻል ከልደት ምዝገባ የሚገኘውን መረጃ ለመጠቀም ተቋሙ ጋር

በጋራ ተቀናጅቶ ለመስራት ፍላጎት ያለ መሆኑ፣ የሴቶችና ሕፃናትን ሕጋዊና አስተዳደራዊ መብት ለማረጋገጥ

የኩነቶች መረጃ ያለዉን ፋይዳ በመገንዘብ በጋራ ተቀናጅቶ ለመስራት ፍላጎት ያለ መሆኑ ስርአቱን በቀጣይነት

በተጠናከረ ሁኔታ ተግባራዊ በማድረግ ረገድ ምቹ ሁኔታ ያለ መሆኑን ያሳያል::

 በተመሳሳይ በመገናኛ ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከቴክኖሎጂ ልማት አንፃር ያለዉ ልምድ፣ በማእከላዊ

ስታስቲክስ በኩል በህዝብና ቤቶች ቆጠራ እና በዳሰሳ ጥናት ላይ ተመስርቶ ስታትስቲክሶችን የማዉጣት ልምድ

ለቀጣይ ለወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ የአሰራር ስርአት ዝርጋታ ምቹ ሁኔታ መኖሩን የሚያመላክት ከመሆኑም በላይ

ከላይ ቁልፍ ባለድርሻ አካላት የተቋማቸዉን ግብ በአስተማማኝ መረጃ ላይ ተመስርቶ ከማሳካት አንጻር የወሳኝ

ኩነት ምዝገባ ስርአት ያለዉን ቁልፍ ድርሻ በመረዳት ስርአቱ እንዲገነባ ከፍተኛ ፍላጎት ያላቸዉ መሆኑ ለወሳኝ

ኩነት ምዝገባ ስርአት ግንባታ ያለዉ አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ያሳያል፡፡

 ሌላዉ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስርአቱን ዉጤታማ ከማድረግ አንጻር በሃይማኖት ተቋማት ልደትን፣ ሞት፣

ጋብቻና ፍች በመመዝገብ እንዲሁም ከወሳኝ ኩነት ምዝገባ መዋቅር ጋር በቅንጅት በመስራት ረገድ ያላቸዉ

ፍላጎት አበረታች መሆኑ ለስርአት ግንባታዉ የሚኖረዉ አስተዋጽኦዉ ከፍተኛ ነዉ፡፡

 ከላይ የተጠቀሱ ጉዳዮች የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስርአቱን አስተማማኝ መሰረት ላይ ለመጣል እንደ መልካም

አጋጣሚ የሚወሰዱ ቢሆንም በሁሉም ባለድርሻ አካላትና በኤጀንሲው መካከል ሊኖር የሚገባው

የጋራና የተናጠል ተግባር ተለይቶ በጠንካራ ቅንጅታዊ የአሰራር ስርአት እንዲደገፍ አለመደረጉ

፣በወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ ተሳታፊ የሆኑ ተቋማት የምዝገባ ስራዉን አጠናክሮ ለማስቀጠል

በሚኖራቸዉ ሚና ዙሪያ ከወዲሁ በቂ ዝግጅት አለማድረግ የሚስተዋሉ ችግሮች ሲሆኑ በተለይም

የጤናዉ ዘርፍ የጋራ መግባቢያ ሰነድ ከመፈራረም በዘለለ የልደት እና ሞት ማሳወቂያ ቅጽ አዘጋጅቶ

በየደረጃዉ ለሚገኙ የመንግስት እና የግል የጤና ተቋማት እንዲደርሳቸዉ እና ስርአቱ ተግባራዊ

እንዲሆን በማድረግ ረገድ ተገቢ ትኩረት ሰጥቶ አለመፈጸም በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቷቸዉ ሊፈቱ

የሚገባቸዉ ጉዳዮች ናቸዉ፡፡

9
2.1.4 የተባባሪ አካላት ሁኔታ

 የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ ለወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስራዉ ትኩረት በመስጠት ዘርፈ ብዙ ተግባራት እያከናወነ

ቢሆንም የምዝገባ ስርአቱ አዲስ፣ ሰፊና ሁሉን አቀፍ ባህሪ ያለዉ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ስርአቱን በተሟላ ደረጃ

ለመዘርጋት የሚያስፈልገዉን ሰፊ ሀብት ለማሰባሰብ የሚያስችል ስልት ነድፎ ተግባራዊ ማድረግ ወሳኝ ጉዳይ

ነዉ::

 ይህን ሰፊ የበጀት ክፍተት ለመሙላት ዘርፉን ለመደገፍ ፍላጎት ያላቸዉን ተባባሪ አካላት በመለየት እና ቀጣይነት

ያለዉ ግንኙነት በማድረግ በሚዘጋጁ የጋራ ምክክር መድረኮች አማካይነት ስርአቱን ለመገንባት ያለዉን ቴክኒካል

እና ፋይናንሻል ክፍተት በግልጽ በማሳየት ተባባሪ አካላት ድጋፍ ሊሰጡ የሚችሉበትን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር

በአገር ውስጥ የሚገኙ ተባባሪ አካላት ጋር የጋራ ፎረም በማቋቋም ድጋፍ ለማግኘት እየተደረገ ያለዉ

ጥረት አበረታች ነዉ::

 የተጀመሩ ግንኙነቶችን ተከትሎ የተወሰኑ ተባባሪ አካላት በተለይም ዩኒሴፍ እና የአለም ባንክ

የፌዴራል ½ የክልል እና የከተማ አስተዳደር የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲዎችን በፋይናንስ እና

በቴክኒክ በመደገፍ ረገድ አበረታች እንቅስቃሴ እያደረጉ ሲሆን ይህም በአገር አቀፍ ደረጃ

የተጀመረውን የምዝገባ ስራ አጠናክሮ ለማስቀጠል አጋዥ መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡

 በተባባሪ አካላት የተጀመረዉ የድጋፍ ስራ አበረታች ቢሆንም በተፈጠረዉ የጋራ መግባባት መሰረት

ሁሉም ተባባሪ አካላት ድጋፍ በመስጠት ረገድ ፈጥነዉ ወደ ስራ የገቡ አለመሆኑ ፣ የትብብር መስኩ

በአንድ ማዕከል የተቀናጀ አለመሆን ½ የተወሰኑ ክልሎችን ብቻ በተናጥል የመደገፍ ፍላጎት የሚታይ

መሆኑ እና የተደረገዉ ድጋፍ ከሚጠበቀዉ አንጻር ሲታይ በጣም አነስተኛ መሆኑ የምዝገባ ስራዉን

በተሟላ በጀትና የማስፈጸም አቅም ለማስቀጠል አሉታዊ ተፅእኖ የሚፈጥር ስለሆነ ይህን ሁኔታ

ለመቀየር በትኩረት መሰራት አለበት፡፡

 በተመሳሳይ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስርአቱን ዉጤታማ ለማድረግ በአገር አቀፍ ደረጃ የሚገኙ እና

የወሳኝ ኩነት መረጃን በመጠቀም የጥናት እና ምርምር ስራዎችን የሚሰሩ የሙያ ማህበራት እና ልዩ

ልዩ የህብረተሰብ አደረጃጀቶች በስርአት ግንባታዉ ዙሪያ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ የሚያገኙትን

ጥቅም በግልጽ በማሳየት ያላቸዉን ሙያዊ እዉቀት እንዲያበረክቱ ማድረግ ጠቃሚ ተደርጎ የሚወሰድ

ጉዳይ ነዉ::

10
 በዚህ መሰረት አደረጃጀቶቹ ከስርአቱ የሚያገኙትን ጥቅም ከወዲሁ ታሳቢ በማድረግ በትብብር

ለመስራት እያሳዩ ያለዉ ፍላጎት አበረታች ሲሆን ይህን ፍላጎት እንደ ምቹ ሁኔታ በመዉሰድ በእቅዱ

ላይ በግልጽ አካቶ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ተገቢ እና ወሳኝ ጉዳይ ተደርጎ የሚወሰድ ይሆናል ::

2.2 ዉስጣዊ ሁኔታ

2.2.1 የኤጀንሲዊ የመሰረታዊ የስራ ሂደት (BPR) ጥናት ሰነድ ፣

 ኤጀንሲዉ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስርአቱን በመላ አገሪቱ ተግባራዊ ለማድረግ እንዲችል ተቋማዊ

መዋቅሩን እና አደረጃጀቱን ሊመልስ የሚችል የመሰረታዊ የሥራ ሂደት ለዉጥ (BPR) ጥናት

በማስጠናት በጥናቱ መሰረት ተቋማዊ አደረጃጀቱን በመመለስ ወደ ስራ ገብቷል፡፡

 በኤጀንሲ ደረጃ ቀደም ሲል ተጠንቶ ወደ ስራ እንዲገባ የተደረገዉ የመሰረታዊ የሥራ ሂደት ለዉጥ

(BPR) ጥናት የኤጀንሲዉን አደረጃጀት ፣ የሰዉ ሃይል እና መከናወን የሚገባቸዉን ተግባራት

ያመላከተ እና ኤጀንሲዉ ስራዉን እንዲጀምር በማድረግ ረገድ ወሳኝ ድርሻ የነበረዉ ሲሆን ኤጀንሲዉ

የምዝገባ ስራዉን ሲጀምር ቀደም ሲል የተጠናዉ ተቋማዊ የመሰረታዊ የስራ ሂደት ለዉጥ ጥናት

ተቋማዊ ተልእኮዉን የሚሸከም አለመሆኑን በመረዳት ጥናቱን የመከለስ ስራ የሰራ መሆኑ በጥንካሬ

የሚወሰድ ነዉ ፡፡

 ኤጀንሲዉ ተቋማዊ የመሰረታዊ የስራ ሂደት ለዉጥ ጥናቱን በማስጠናት ወደ ስራ እንዲገባ በማድረግ

ረገድ አበረታች ተግባራትን ያከናወነ ቢሆንም ጥናቱ በኤጀንሲ ደረጃ መከናወን የሚገባቸዉን

ተግባራትን በተሟላ ሁኔታ በመለየት እና ተቋማዊ የሰዉ ሃይሉን በሚፈለገዉ ደረጃ በመመለስ ረገድ

ክፍተት ያለበት ሲሆን በዚህ ረገድ የታዩ ክፍተቶችን ለመቅረፍ እንዲቻል የተከለሰዉን የመሰረታዊ

የስራ ሂደት ለዉጥ ጥናት ፈጥኖ ወደ ተግባር እንዲገባ በማድረግ ረገድ ዉስንነት ያለ መሆኑን

አፈጻጸሙ ያሳያል ፡፡

 በመሆኑም ኤጀንሲዉ የተሰጠዉን ተልእኮ በብቃት ለመወጣት እንዲችል የተከለሰዉ የመሰረታዊ

የሥራ ሂደት ለዉጥ ጸድቆ ወደ ተግባር እንዲገባ በቀጣይ ትኩረት በመስጠት መስራት ይገባል፡፡

11
2.2.2 የኤጀንሲው ሚዛናዊ ውጤት ተኮር (BSC) 2009 - 2012 ዓ.ም ጥናት ሰነድ፣

 የኤጀንሲዉ ሚዛናዊ ውጤት ተኮር ሰነድ የተቋሙን ባለድርሻ እና ተገልጋይ ፍላጎት መነሻ በማድረግ

የተዘጋጀ መሆኑ፣ በኤጀንሲ ደረጃ ትኩረት ሊደረግባቸዉ የሚገቡ ስትራቴጅክ ጉዳዮችን የለየ መሆኑ ፣

ስትራቴጅክ ጉዳዮችን መነሻ በማድረግ ተቋማዊ የትኩረት መስኮችን ያመላከተ መሆኑ ፣ በኤጀንሲ

ደረጃ በስትራቴጅክ ዘመኑ መከናወን የሚገባቸዉን ግቦች እና ተግባራትን ያካተተ መሆኑ ፣ ተቋማዊ

እቅዱን የሚደገፉ ስትራቴጅክ እርምጃዎችን የለየ መሆኑ በስትራቴጅክ እቅድ ደረጃ በጥንካሬ

የሚታይና አመታዊ እቅዱንም በማዘጋጀት ሂደት ቁልፍ መነሻ ተደርጎ የሚወሰድ ነዉ ፡፡

 የኤጀንሲዉ የሚዛናዊ ውጤት ተኮር ሰነድ ከላይ የተጠቀሱ ጥንካሬዎች ያሉት ቢሆንም በስትራቴጅክ

ዘመኑ የተለዩ ግቦችን እና ተግባራትን ለማከናወን የሚያስችል በጀት የመለሰ አለመሆኑ፣ በኤጀንሲ

ደረጃ የሚዛናዊ ውጤት ተኮር ስርአቱን ተግባራዊ በማድረግ ረገድ በቂ የሰዉ ሃይል የተሟላ አለመሆኑ፣

የሚዛናዊ ውጤት ተኮር ስርአቱን በተሟላ ደረጃ ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል የምዘና ስርአት

አለመኖር የሚዛናዊ ዉጤት ተኮር ስርአቱን በመተግበር ሂደት ያጋጠሙ ችግሮች ሲሆኑ በቀጣይ

በማዳበር የተሟላ እንዲሆን በማድረግ ረገድ ትኩረት ተሰጥቶ የሚሰራ ይሆናል፡፡

2.2.3 አገራዊ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ምክር ቤት ሁኔታ

 የወሳኝ ኩነት ምዝገባ አገራዊ ምክር ቤት አገራዊ የምዝገባ ስርአቱን የሚመራ የኤጀንሲዉ ከፍተኛ

የስልጣን አካል ነዉ፡፡ ምክር ቤቱ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ ድጋፍና ዉሳኔ በሚሹ ጉዳዮች ላይ

ዉሳኔዎችን በማሳለፍ፣ የምዝገባ ስራዉን በተሟላ ሁኔታ ለማስቀጠል በመዝጋቢ ተቋማት የሚታዩ

የአፈጻጸም ክፍተቶችን በመገምገምና አቅጣጫ በመስጠት በውሱን ደረጃም ቢሆን የበኩሉን አስተዋጽኦ

እያበረከተ የሚገኝ ሲሆን ምክር ቤቱ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ አጀማመር ማብሰሪያ ፕሮግራም ላይ

በመገኘት በአገር አቀፍ ደረጃ የምዝገባ ስራዉን ለመጀመር የተከናወኑ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን

አፈጻጸም በመገምገም የቀጣይ አቅጣጫ ማስቀመጥ ችሏል፡፡

 የወሳኝ ኩነት ምዝገባ አገራዊ ምክር ቤት የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስርአቱን ለመገንባት ካለዉ ወሳኝ ሚና

አንጻር የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ሂደቱን ለማጠናከር የሚያስችል ወቅቱን የጠበቀ አቅጣጫ እና ዉሳኔ

በማስተላለፍ ½ የተወሰኑ ዉሳኔዎችን ተፈጻሚነት በመከታተል፣ ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት በምክር

12
ቤት ስብሰባ ላይ በተሟላ ሁኔታ በመገኘት ረገድ ክፍተት ያለ ሲሆን ምክር ቤቱ ለስርአት ዝርጋታዉ

ያለዉን ወሳኝ ድርሻ በመገንዘብ አደረጃጀቱን በላቀ ደረጃ ለመጠቀም በአፈጻጸም ወቅት የታዩ

ክፍተቶችን ለይቶ እንዲፈታ ማድረግ በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶት የሚሰራ ይሆናል::

2.2.4 የኤጀንሲዉ የስራ አመራር ቦርድ ሁኔታ ፣

 የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ የስራ አመራር ቦርድ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስርአቱን በመምራት ረገድ

ኤጀንሲዉን በቅርበት የሚደግፍ እና የስርአቱን ቀጣይነት ከማረጋገጥ አንጻር በመሰረታዊ ጉዳዮች ላይ

አቅጣጫ በመስጠት የሚመራ ወሳኝ አካል ነዉ፡፡

 የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ ስራ አመራር ቦርድ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስርአቱን በመምራት ረገድ

በምዝገባ ቅድመ ዝግጅት ወቅት የሚከናወኑ ተግባራትን በተሳካ ሁኔታ እንዲፈጻሙ ከመደገፍ እና

አቅጣጫ ከማስቀመጥ ባሻገር የምዝገባ ስራዉም ከተጀመረ ጊዜ አንስቶ በምዝገባዉ አተገባበር ላይ

የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመለየት እና ችግሮቹ እንዲፈቱ ድጋፍና አቅጣጫ በማሥቀመጥ አበረታች

ተግባራትን እያከናወነ መሆኑ ኤጀንሲዉ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስርአቱን ተግባራዊ በሚያደርግበት

ሂደት ዉጤታማ እንዲሆን ጉልህ አስተዋጽኦ አበርክቷል፡፡

 የኤጀንሲዉ የስራ አመራር ቦርድ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስራዉን በመምራትና በመደገፍ ረገድ

ያከናወናቸዉ ተግባራት አበረታች ቢሆኑም በስራ አመራር ቦርዱ የጋራ መድረክ ላይ የኤጀንሲዉ ቁልፍ

ባለድርሻ አካላት በተሟላ ደረጃ በመገኘት ሚናቸዉን በመወጣት እንዲሁም የቁልፍ ባለድርሻ

ተቋማትን በተለይም የጤና ጥበቃ ሚኒስቴርን አፈጻጸም ገምግሞ የማስተካከያ እርምጃ እንዲወሰድ

በማድረግ ፣ በተቀመጠዉ መርሃ ግብር መሰረት ተገኝቶ የቅርብ ድጋፍ በማድረግ በኩል ክፍተት ያለ

በመሆኑ በቀጣይ በጀት ዓመት የስራ አመራር ቦርዱን አቅም በመጠቀም ረገድ ትኩረት ተሰጥቶት

የሚሰራ ይሆናል::

13
2.2.5 የኤጀንሲዉ አመራርና ፈጻሚ ሁኔታ

2.2.5.1 የኤጀንሲዉ አመራር

 በአመለካከት ረገድ
 የኤጀንሲዉ አመራር አካል በ 2009 በጀት አመት በተቋም ደረጃ በእቅድ የተያዙ ተግባራትን

ለማስፈጸም እና የምዝገባ ስራዉን በብቃት ተግባራዊ ለማድረግ እንዲቻል የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስርዓቱን

በመዘርጋት ረገድ የሚከናወኑ ወሳኝ ተግባራትን በውስጥ አቅም ማከናወን ይቻላል የሚል እምነት በመያዝ ወደ

ስራ የገባ መሆኑ ምዝገባዉን ለማስቀጠል ወሳኝ እና ለሌሎች ስኬቶች መነሻ የነበረ አመለካከት ነዉ ብሎ መዉሰድ

ይቻላል፡፡

 የኤጀንሲዉ አመራር የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስራዉን ለማስጀመር የነበረዉ ፍላጎት እና ተነሳሽነት

የምዝገባ ስራዉም ከተጀመረ ጀምሮ በዉስን የሰዉ ሃይል ነገር ግን በላቀ ቅንጅት እና ጥረት ተልኮዉን

ማሳካት እንደሚቻል በማመን ለተፈጻሚነቱ ርብርብ እያደረገ መሆኑ ለቀጣይ ተቋማዊ ስኬት

መሰረት ነዉ ብሎ መዉሰድ ይቻላል፡፡

 የኤጀንሲዉ አመራር አካል ተቋማዊ ለዉጡን አጠናክሮ ለመቀጠል እንዲቻል በአመለካከት በመዉሰድ

ያከናወናቸዉ አበረታች ተግባራት ያሉ ቢሆንም በተቋም ደረጃ የተጀመረዉን የለውጥ ሰራዊት ግንባታ ለዕቅድ

አፈፃፀምን ውጤታማነት ያለውን ፋይዳ በመረዳት በዕምነት ወስዶ በላቀ ደረጃ ተግባራዊ በማድረግ

፣መልካም አስተዳደርን በማስፈን ረገድ የተለዩ ክፍተቶችን አንደ ቁልፍ ችግር ወስዶ በተሟላ ደረጃ

ለመፍታት ተገቢውን ጥረት በማድረግ ረገድ ዉስንነት የነበረበት ሲሆን በእቅድ የተያዙ ተግባራት

በተያዘላቸዉ መርሃ ግብር ከመፈጸም ይልቅ የጠባቂነት ችግር የነበረበት መሆኑን አፈጻጸሙ ያሳያል፡፡

14
 በሌላ በኩል የኤጀንሲዉ አመራር አካል የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር ያለውን አደጋ ተረድቶ

ከአድርባይነት በፀዳ መንፈስ የተሟላ ትግል በማድረግ፣ የለውጥ መሳሪያዎች ትግበራ ለዕቅድ

አፈፃፀምን ውጤታማነት ያላቸውን ፋይዳ በመረዳት በዕምነት ወስዶ በተሟላ ደረጃ በመተግበር

እንዲሁም በእቅድ የተያዙ ተግባራትን በእቅዱ መሰረት በተሟላ ደረጃ በመፈጸም ረገድ ክፍተት

ያለበት ሲሆን ስርአቱን ከመገንባት አንጻር በጅምር ደረጃ የታዩ ለዉጦችን ለማስቀጠል እንዲቻል

አመለካከቱ የተስተካከለ እና የተሟላ የለዉጥ ሰራዊት ገንብቶ መንቀሳቀስ እንዲቻል የተለዩ

ክፍተቶችን ትኩረት ሰጥቶ መፍታት ይገባል፡፡

 በክህሎት ረገድ

 ሌላዉ ከወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስርዓት ግንባታ ጋር ተያይዞ ትኩረት የሚሰጠዉ ጉዳይ የአመራሩን

የመፈጸም አቅም የማሳደግ ጉዳይ ነዉ ፡፡ በመሆኑም የተቋሙ አመራር አካል የወሳኝ ኩነት ምዝገባ

ስርዓት ግንባታ ዓለማቀፋዊ መርሆዎችን ፣ ስትራቴጂዎችንና ህጎችን ለማወቅ እና ለመረዳት ያደረገዉ

ጥረት አበረታች ከመሆኑም ባሻገር በምዝገባ ቅድመ ዝግጅት ወቅት የተፈጠረዉን አቅም የምዝገባ

ስራዉን ለማስጀመር በግብአትነት በመጠቀም ምዝገባዉን እንዲጀመር ያደረገ መሆኑ በጥንካሬ

የሚወሰድ ነዉ፡፡

 በሌላ በኩል የኤጀንሲዉ አመራር አካል የምዝገባ ስራውን ቀጣይነት ለማረጋገጥ በሚደረገዉ ጥረት

መዝጋቢ አካላትን ለማብቃት እንዲቻል የስልጠና ሰነዶችን በውስጥ አቅም በማዘጋጀት እና ስልጠና

እንዲሰጥ በማድረግ ፣ የተሰጡ ስልጠናዎች ያስገኙትን ዉጤት ለማወቅ የሚያስችል የዳሰሳ ጥናት

እንዲደረግ ጥረት በማድረግ ፣ በተቋሙ በተፈጠሩ የተለያዩ መድረኮች አማካይነት በየደረጃው

የዕውቀትና ክህሎት ልውውጥና ሽግግር እንዲደረግ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር አበረታች እንቅስቃሴ

የተደረገ ሲሆን ይህም በቀጣይ ተቋማዊ አቅም በመፍጠር የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስርአቱን ለማሳካት

በሚደረግዉ ጥረት ጉልህ አስተዋጽኦ የሚኖረዉ ይሆናል፡፡

 የተቋሙን አመራር የመፈጸም አቅም በማሳደግ ረገድ የተከናወኑ አበረታች ተግባራት ያሉ ቢሆንም ዕቅዶችን

በሚፈለገው የጥራት ደረጃ በማዘጋጀት፣ ሊከናወኑ የሚችሉ ተግባራትን ብቻ ለይቶ በማቀድ እና በተቀመጡ

መርሃ ግብሮች መሰረት በመፈጸም እንዲሁም ስራዎችን ጎን ለጎን አቀናጅቶ በመምራት ረገድ ክፍተቶች ያሉ

መሆኑ በአፈጻጸም ግምገማ ተለይቷል፡፡

15
 በሌላ በኩል አመራሩ ስትራቴጅክ ጉዳዮች ላይ በማትኮርና ስራን በኮሙኒኬሽን በመምራት ፣ የፈጻሚዉን

የአቅም ክፍተት በመለየት በሚፈለገው ደረጃ የማብቃት ስራ በመስራት እንዲሁም እቅድን መሠረት ያደረገና

ጥራቱንና ወቅቱን የጠበቀ ሪፖርት አዘጋጅቶ በማቅረብ ረገድ የክህሎት ክፍተት ያለበት ሲሆን የክህሎት

ክፍተቱን ለመሙላት በቀጣይ በእቅድ አካቶ መስራት ትኩረት የሚሰጠዉ ተግባር ይሆናል፡፡

 ከአሰራር እና አደረጃጀት አንጻር

 ተቋማዊ አሰራርና አደረጃጀቱን ከማጠናከር አንጻር የኤጀንሲዉ አመራር ከምዝገባ ቅድመ ዝግጅት ወቅት አንስቶ

የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስራዉን ለማስጀመር የሚያስችሉ መመሪያዎች እና የምዝገባ ሰነዶችን እንዲዘጋጁ በማድረግ

፣ አዋጁን እንዲሻሻል በማድረግ ፣ የአዋጁን መሻሻል መሰረት በማድረግ የአፈጻጸም መመሪያዎች እንዲሻሻሉ

በማድረግ እንዲሁም ለፌዴራል መዝጋቢ ተቋማት የምዝገባ ቁሳቁስ በማዘጋጀት እና ምዝገባ እንዲጀምሩ

በማድረግ ረገድ ሰፊ ርብርብ አድርጓል፡፡

 በተመሳሳይ አመራሩ ተቋማዊ ስራዎች ከልማዳዊ አሰራር ተላቀዉ በለውጥ ሥራ አመራር ስርዓት ለመምራት

የሚያስችል የመሠረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ ጥናት ተግባራዊ በማድረግ ረገድ አበረታች እንቅስቃሴ ያደረገ ሲሆን

የምዝገባ ስራዉም ከተጀመረ በኋላ ተቋማዊ ዕቅዱን በሚዛናዊ የውጤት ተኮር አስተቃቀድ ስልት እንዲዘጋጅ

በማድረግ እና ወደ ስራ እንዲገባ በማድረግ እንዲሁም የተቋሙን ተልዕኮ ማሳካት የሚያስችሉ የተለያዩ

አደረጃጀቶችን ፈጥሮ ወደ ስራ በማስገባት ረገድ አበረታች ጥረት ያደረገ ሲሆን ይህም ለቀጣይ እቅድ

ትግበራ አስተዋጽኦ የሚኖረዉ ይሆናል፡፡

 የኤጀንሲዉ አመራር ከአሰራር እና ከአደረጃጀት አኳያ ያከናወናቸዉ ከላይ የተጠቀሱ ተግባራት ያሉ

ቢሆንም ከፈፃሚው ጋር ያለውን የስራ ግንኙነት በተሟላ ግልፀኝነት መርህ ላይ ተመስርቶ

በማከናወን፣ በእቅድ የተያዙ ተግባራትን በጠንካራ ቅንጅታዊ አሰራር ላይ ተመስርቶ በመፈጸም

፣በየደረጃው የሚታዩ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በቀይጣነት ለመፍታት የሚያስችሉ

ተከታታይነት ያላቸዉ መድረኮችን በመፍጠር እና ተቋማዊ እቅዱን ከበጀትና ከግዥ እቅዱ ጋር

አጣጥሞ በመምራት ረገድ ክፍተት ያለበት ሲሆን ክፍተቱን መሰረት ያደረገ ቀጣይነት ያለዉ

የማብቃት ስራ በእቅድ ተይዞ የሚሰራ ይሆናል፡፡

 በሌላ በኩል በስራ ላይ ያለው የኤጀንሲው አደረጃጀት ተቋማዊ ተልዕኮውን በተሟላ ደረጃ እንዲሸከም

ለማድረግ እንዲቻል የተጀመረዉ የመሰረታዊ የስራ ሂደት ለዉጥ ጥናት ተጠናቆ ወደ ተግባር እንዲገባ

16
በማድረግ ፣ በሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የጉዲፈቻ ኩነት ምዝገባ እንዲጀመር ተገቢዉን

ድጋፍ በማድረግ እንዲሁም በእቅድ የተያዙ ተግባራትን በውጤት እየቃኙ በመምራት ረገድ ክፍተት

ታይቶበታል ፡፡

 በአጠቃላይ የኤጀንሲዉ አመራር የሚሰጡ ኃላፊነቶችን በተሟላ የተጠያቂነት መርህ ላይ ተመስርቶ

በመፈፀም ረገድ ክፍተት ያለበት ሲሆን ክፍተቱን ለመሙላት በቀጣይ ትኩረት በመስጠት መስራት

ይገባል፡፡

 ከግብአት አቅርቦት አንጻር

 የኤጀንሲዉ አመራር የግብአት አቅርቦት ስርአትን ከማጠናከር አንጻር የምዝገባ ስራዉን ለማስጀመር

የሚያስችሉ መመሪያዎች ፣ የክብር መዝገብ ፣ የምስክር ወረቀት እና ሌሎች ለምዝገባ ስራ ጠቃሚ

የሆኑ ግብአቶችን እንዲዘጋጁ እና ለሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ተደራሽ እንዲሆኑ

በማድረግ ረገድ ሰፊ ርብርብ አድርጓል፡፡

 የምዝገባ ስራዉም ከተጀመረ በኋላ ለፌዴራል መዝጋቢ ተቋማት የሚያገለግል መመሪያ ፣ የክብር

መዝገብ እና የምስክር ወረቀት በማዘጋጀት እና ለስርጭት ዝግጁ በማድረግ ፣ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ

ስራዉን ቀጣይነት በማረጋገጥ ረገድ ወሳኝ ሚና ያላቸዉ ግብአቶችን ለማሟላት የሚያስችል የበጀት

ድጋፍ በተባባሪ አካላት እንዲደረግ ጥረት በማድረግ ረገድ የተሻለ ስራ መስራት ችሏል፡፡

 በሌላ በኩል ኤጀንሲዉ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስርአቱን በተሻለ ሁኔታ ለመምራት የሚያስችለዉ ቢሮ

ከመንግስት በመረከብ እና ቢሮዉን በማደስ እንዲሁም ተቋማዊ ግብአቶችን በመጠቀም ረገድ የሚታዩ

ክፍተቶችን በመለየት እና እንዲስተካከሉ አቅጣጫ በማስቀመጥ ረገድ አበረታች እንቅስቃሴ ያደረገ

ሲሆን ከግብአት አቅርቦት ጋር ተያይዞ የተከናወኑ ተግባራት የምዝገባ ስራዉ ዉጤታማ እንዲሆን

ከማድረግ አኳያ ጉልህ አስተዋጽኦ የሚያበረክቱ ይሆናል፡፡

17
 የኤጀንሲዉ አመራር የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስርአቱን ለማጠናከር የሚያስችሉ ግብአቶችን በማሟላት

እና ጥቅም ላይ እንዲዉሉ ለማድረግ ያደረጋቸዉ ጥረቶች ያሉ ቢሆንም ኤጀንሲዉ የተሰጠዉን

ተልእኮ ለማሳካት ወሳኝ ግብአት የሆነዉን የሰዉ ሃይል በሚፈለገዉ ደረጃ በማሟላት እና የተገኙ

ግብአቶችን የተቋሙን ተልዕኮ በሚያሳካ መንገድ አሟጦ በመጠቀም ፣ በተቋም ደረጃ በግብአት

አጠቃቀም ዙሪያ የሚታዩ ችግሮችን በቀጣይነት በመገምገም እና ችግሩ በተሟላ ደረጃ እንዲፈታ

በማድረግ ረገድ ክፍተት ያለበት ሲሆን ክፍተቱን ለመሙላት በቀጣይ ትኩረት በመስጠት የሚሰራ ይሆናል፡፡

 ከድጋፍና ክትትል አንጻር

 የኤጀንሲዉ አመራር የድጋፍና ክትትል ስራዎችን ዉጤታማ ለማድረግ የወሳኝ ኩነት መዝጋቢ አካላት ምዝገባውን ከመጀመር

አንፃር ያሉበትን ነባራዊ ሁኔታ ለማወቅ የሚያስችል ዳሰሳ በማድረግ በተገኙ መረጃዎች ላይ ተመስርቶ ክፍተቶችን

ለመሙላት ያደረገዉ ጥረት አበረታች ነዉ፡፡

 በሌላ በኩል ኤጀንሲዉ በምዝገባ አፈጻጸም ላይ ያጋጠሙ ችግሮችን በድጋፍና ክትትል በመለየት የመፍትሄ አቅጣጫ

እንዲቀመጥ በማድረግ ረገድ ያከናወነዉ ተግባር የምዝገባ ስራዉን ዉጤታማነት ከማረጋገጥ አንጻር የሚኖረዉ አስተዋጥኦ

የጎላ ነዉ፡፡

 የኤጀንሲዉ አመራር ተቋማዊ የድጋፍ እና ክትትል ተግባሩን ዉጤታማ ለማደረግ ያከናወናቸዉ ተግባራት

አበረታች ቢሆኑም በእቅድ የሚመራ የድጋፍና ክትትል ስርአት ዘርግቶ ተግባራዊ በማድረግ እንዲሁም ቀጣይነት

ያለዉና ችግር ፈቺ የሆነ የክትትልና ድጋፍ ስርአት ዘርግቶ በመፈጸም ረገድ ክፍተቶች ታይተዉበታል፡፡

 በተመሳሳይ እቅድ አፈጻጸም ላይ ተመስርቶ ጠንካራ እና ቀጣይነት ያለዉ የእቅድ አፈፃፀም ግምገማና ግብረ -

መልስ ስርዓት ዘርግቶ ተግባራዊ በማድረግ ረገድ ዉስንነት ያለበት ሲሆን በዚህ ረገድ የታዩ ክፍተቶችን

በመቅረፍ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስርአቱን በጠንካራ የድጋፍና ክትትል ስርአት አማካይነት ዉጤታማ ለማድረግ

በቀጣይ ትኩረት ተሰጥቶ የሚሰራ ይሆናል፡፡

18
2.2.5.2 የኤጀንሲዉ ፈጻሚ

 በአመለካከት ረገድ
 የኤጀንሲዉ ፈጻሚ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስርዓቱን በመዘርጋት ረገድ የሚከናወኑ ተግባራትን በውስጥ አቅም

ማከናወን ይቻላል የሚል እምነት በመያዝ ወደ ስራ የገባ መሆኑ ምዝገባዉን ለማስቀጠል ወሳኝ እና ለሌሎች ስኬቶች

መነሻ የነበረ አመለካከት ነዉ ብሎ መዉሰድ የሚቻል ሲሆን በተመሳሳይ የምዝገባ ስራዉም ከተጀመረ በኋላም

በዉስን የሰዉ ሃይል ነገር ግን በላቀ ቅንጅት እና ጥረት ተልኮዉን ማሳካት እንደሚቻል በማመን

ለተፈጻሚነቱ ርብርብ እያደረገ መሆኑ ለቀጣይ ተቋማዊ ስኬት መሰረት ነዉ ብሎ መዉሰድ ይቻላል፡፡

 የኤጀንሲዉ ፈጻሚ አካል ተቋማዊ ለዉጡን አጠናክሮ ለመቀጠል እንዲቻል በአመለካከት በመዉሰድ ያከናወናቸዉ

አበረታች ተግባራት ያሉ ቢሆንም በተቋም ደረጃ የተጀመረዉን የለውጥ ሰራዊት ግንባታ ለዕቅድ አፈፃፀምን

ውጤታማነት ያለውን ፋይዳ በመረዳት በዕምነት ወስዶ በላቀ ደረጃ ተግባራዊ በማድረግ ፣መልካም

አስተዳደርን በማስፈን ረገድ የተለዩ ክፍተቶችን እንደ ቁልፍ ችግር ወስዶ ለመፍትሄዎቹ በጋራ

በመረባረብ ዉስንነት የነበረበት መሆኑ አፈጻጸሙ ያሳያል፡፡

 የኤጀንሲዉ ፈጻሚ የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና ተግባር ያለውን አደጋ ተረድቶ ከአድርባይነት በፀዳ

መንፈስ የተሟላ ትግል በማድረግ፣ የለውጥ መሳሪያዎች ትግበራ ለዕቅድ አፈፃፀምን ውጤታማነት

ያላቸውን ፋይዳ በመረዳት በዕምነት ወስዶ በተሟላ ደረጃ በመተግበር እንዲሁም በእቅድ የተያዙ

ተግባራትን በእቅዱ መሰረት በተሟላ ደረጃ በመፈጸም ረገድ ክፍተት ያለበት ሲሆን ስርአቱን ከመገንባት

አንጻር በጅምር ደረጃ የታዩ ለዉጦችን ለማስቀጠል እንዲቻል አመለካከቱ የተስተካከለ እና የተሟላ

የለዉጥ ሰራዊት ገንብቶ መንቀሳቀስ እንዲቻል የተለዩ ክፍተቶችን ትኩረት ሰጥቶ መፍታት ይገባል፡፡

 በክህሎት ረገድ

 የኤጀንሲዉ ፈጻሚ አካል የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስርዓት ግንባታ ዓለማቀፋዊ መርሆዎችን ፣

ስትራቴጂዎችንና ህጎችን ለማወቅ እና ለመረዳት ያደረገዉ ጥረት አበረታች ከመሆኑም ባሻገር

በምዝገባ ቅድመ ዝግጅት ወቅት የተፈጠረዉን አቅም የምዝገባ ስራዉን ለማስጀመር በግብአትነት

በመጠቀም ምዝገባዉን እንዲጀመር ያደረገ መሆኑ በጥንካሬ የሚወሰድ ሲሆን ፈፃሚዉ በተቋሙ

19
በተፈጠሩ የተለያዩ መድረኮች አማካይነት አቅሙን ለማሳግ እና የዕውቀትና ክህሎት ልውውጥና

ሽግግር መደረጉ በቀጣይ ተቋማዊ አቅም በመፍጠር የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስርአቱን ለማሳካት

በሚደረግዉ ጥረት ጉልህ አስተዋጽኦ ይኖረዋል፡፡

 የተቋሙ ፈጻሚ የመፈጸም አቅም በማሳደግ ረገድ የተከናወኑ አበረታች ተግባራት ያሉ ቢሆንም በእቅድ የተያዙ

ተግባራት አፈጻጸም ላይ የተሟላ ግንዛቤ በመያዝ ፣ የክህሎት ክፍተቱን በመለየት እና ለመሙላት በሚፈለገዉ

ደረጃ በመንቀሳቀስ እንዲሁም እቅድን መሠረት ያደረገና ጥራቱንና ወቅቱን የጠበቀ ሪፖርት አዘጋጅቶ በማቅረብ

ረገድ ዉስንነቶች ታይተዉበታል፡፡

 ከአሰራር እና አደረጃጀት አንጻር

 የኤጀንሲዉ ፈጻሚ አካል ተቋማዊ አሰራርና አደረጃጀቱን ከማጠናከር አንጻር ከምዝገባ ቅድመ ዝግጅት ወቅት

አንስቶ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስራዉን ለማስጀመር የሚያስችሉ መመሪያዎች እና የምዝገባ ሰነዶችን እንዲዘጋጁ

በማድረግ ሂደት የነቃ ተሳትፎ በማድረግ አበረታች ስራዎችን የሰራ ሲሆን በተቋማዊ የመሠረታዊ የሥራ ሂደት

ለውጥ ጥናት ዝግጅት እና ትግበራ ላይ እንዲሁም በተቋማዊ የሚዛናዊ ውጤት ተኮር እቅድ ዝግጅት እና

አተገባባር ላይ ተሳትፎ በማድረግ አበረታች ጥረት ያደረገ አድርጓል ፡፡

 የኤጀንሲዉ ፈጻሚ ከአሰራር እና ከአደረጃጀት አኳያ ከላይ የተጠቀሱ ጥንካሬዎች ያሉት ቢሆንም

በእቅድ የተያዙ ተግባራትን በጠንካራ ቅንጅታዊ አሰራር ላይ ተመስርቶ በመፈጸም እና በዕቅድ የተያዙ

ተግባራትን በውጤት እየቃኙ በመፈጸም ረገድ ክፍተት ያለበት ሲሆን ክፍተቱን ለመሙላት በቀጣይ

እቅድ አካቶ ትኩረት በመስጠት የሚሰራ ይሆናል፡፡

 ከግብአት አቅርቦት አንጻር


 የኤጀንሲዉ ፈጻሚ አካል የግብአት አቅርቦት ስርአትን ከማጠናከር አንጻር የምዝገባ ስራዉን

ለማስጀመር የሚያስችሉ መመሪያዎች ፣ የክብር መዝገብ ፣ የምስክር ወረቀት እና ሌሎች ለምዝገባ

ስራ ጠቃሚ የሆኑ ግብአቶችን እንዲዘጋጁ እና ለሁሉም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ተደራሽ

እንዲሆኑ በማድረግ ሂደት ሰፊ ርብርብ ያደረገ ሲሆን ኤጀንሲዉ ከመንግስት የተረከበዉ ቢሮ

አገልግሎት እንዲጀምር ለማድረግ ሰፊ ጥረት አድርጓል፡፡

20
 የኤጀንሲዉ ፈጻሚ ግብአቶችን በማሟላት እና ጥቅም ላይ እንዲዉሉ ለማድረግ ረገድ

የሚያደርጋቸዉ ጥረቶች ያሉ ቢሆንም የተገኙ ግብአቶችን የተቋሙን ተልዕኮ በሚያሳካ መንገድ

አሟጦ በመጠቀም ረገድ ክፍተት የነበረበት በመሆኑ በቀጣይ በትኩረት ሊፈታ ይገባዋል፡፡

 ከድጋፍና ክትትል አንጻር

 የኤጀንሲዉ ፈጻሚ አካል በድጋፍና ክትትል ስራዎች ላይ በመሳተፍ እና በመዝጋቢ አካላት ረገድ በአፈጻጸም ወቅት የሚታዩ

ችግችን ለመፍታት ያደረገዉ ጥረት የሚበረታታ ሲሆን የድጋፍ እና ክትትል ስራዎችን ችግር ፈቺ በሆነ ሁኔታ

በመፈጸም እና የሚፈለገዉን ዉጤት በማምጣት ረገድ ክፍተቶች ታይተዉበታል፡፡

ክፍል ሶስት ፡- የኤጀንሲዉ የ 2009 ዓ.ም እቅድ አፈጻጸም

ኤጀንሲዉ ተቋማዊ ስትራቴጅክ እቅዱን መነሻ በማድረግ በ 2009 በጀት አመት ለመፈጸም በእቅድ የተያዙ

ግቦችን እና ተግባራትን አፈጻጸም በመገምገም በእቅድ አፈጻጸም ወቅት የተለዩ ጠንካራ አፈጻጸሞችን በቀጣይ

በጀት አመት የበለጠ ተጠናክረዉ እንዲቀጥሉ ለማድረግ እንዲሁም በሚፈለገዉ ደረጃ ያልተፈጸሙ ግቦች እና

ተግባራትን በመለየት እና በምን ምክንያት ሳይፈጸሙ እንደቀሩ በማወቅ በ 2010 በጀት አመት እቅድ ላይ

ተካተዉ እንዲፈጸሙ ማድረግ ወሳኝ ተግባር ነዉ፡፡

በመሆኑም በክፍል ሶሰት በ 2009 በጀት አመት በዝግጅት ምእራፍ ፣ በተግባር ምእራፍ እና በማጠቃለያ

ምእራፍ ላይ በእቅድ ተይዘዉ የነበሩ ዋና ዋና ተግባራትን አፈጻጸም በጥንካሬ እና በድክመት በመለየት

የሚያሳይ የኤጀንሲዉ የ 2009 ዓ.ም እቅድ አፈጻጸም እንዲቀርብ ተደርጓል፡፡

3.1 የኤጀንሲዉ የ 2009 በጀት አመት እቅድ አፈጻጸም ጥንካሬዎች እና ድክመቶች

3.1.1 ዝግጅት ምእራፍ

3.1.1.1 ጥንካሬዎች

21
 የኤጀንሲዉን አመራር እና ፈፃሚ አቅም በማሳደግ ረገድ ፣

 የኤጀንሲዉን አመራር እና ፈጻሚ አካል የአፈጻጸም ክፍተት ለመለየት የሚያስችል የግምገማ መድረክ

በማዘጋጀት እና በመድረኩ የአመለካከት ፣ የክህሎት ፣ የአሰራር እና አደረጃጀት እንዲሁም የግብአት አቅርቦት

እና አጠቃቀም ክፍተቶችን በመለየት ክፍተቱን ለመሙላት ጥረት የተደረገ መሆኑ፣

 የኤጀንሲዉ ሰራተኛ ላይ የሚታዩ የአመለካከት እና የክህሎት ክፍተቶችን በመለየት መፍታት የሚያስችል

የጥልቅ ተሃድሶ መድረክ በማዘጋጀት እቅዱን በመፈጸም ረገድ በአመራር እና በፈጻሚ ደረጃ የነበሩ

ጥንካሬዎችን እና ክፍተቶችን በመለየት ተቋማዊ አፈጻጸሙን የተሻለ ለማደረግ የሚያስችል የጋራ መግባባት

እንዲፈጠር የተደረገ መሆኑ፣

 ኤጀንሲዉ በ 2009 በጀት አመት በእቅድ የያዛቸዉን ተግባራት አፈጻጸም በመገምገም የቀጣይ አቅጣጫ

ለማስቀመጥ እንዲቻል ከክልል እና ከተማ አስተዳደር የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲዎችን አፈጻጸም

ለመገምገም የሚያስችል ያጋራ ምክክር መድረክ በማዘጋጀት በእቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረኩ የታዩ

ጥንካሬዎችንና ድክመቶችን በመገምገም በቀጣይ አቅጣጫ ላይ የጋራ መግባባት እንዲፈጠር የማድረግ ስራ

የተሰራ መሆኑ፣

 በኤጀንሲዉ የ 2009-12 ስትራቴጅክ እቅድ እና የ 2009 ዓ.ም አመታዊ እቅድ ዙሪያ ለፌዴራል ፣

ለክልል እና ከተማ አስተዳደር ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ አመራርና ፈጻሚዎች ስልጠና ነክ

ኦረንቴሽን በመስጠት በእቅዱ ላይ በተካተቱ ተቋማዊ ስትራቴጂክ ጉዳዮች ፣ የትኩረት

መስኮች ፣ ግቦች እና የቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ ግልጽ ግንዛቤ እና የጋራ መግባባት እንዲፈጠር

መደረጉ፣

 የኤጀንሲዉን የሰዉ ሃይል አቅም በማሳደግ ተቋማዊ ተልእኮዉን ለማሳካት እንዲቻል ለኤጀንሲዉ

ሰራተኞች ከስራ አመራር ኢንስቲቲዩት እና ከፌዴራል ገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ጋር

በመቀናጀት በተለያዩ ርእሶች ዙሪያ ስልጠና እንዲወስዱ የተደረገ መሆኑ ፣

 የኤጀንሲዉን ሰራተኞች የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ዙሪያ የሚታዩ ክፍተቶችን በዳሰሳ ጥናት በመለየት

ክፍተቱን ለመሙላት የሚያስችል ስልቶች የተለዩ መሆኑ፣

22
 የግብአት አጠቃቀም አቅም በማሳደግ ረገድ ½

 በክልልና በከተማ አስተዳደር ደረጃ የምዝገባ ስራዉን ለማከናወን የሚያስችሉ የክብር መዝገብ እና

የምስክር ወረቀት ህትመቶችን የማሳተም እና የማሰራጨት ስራ የተከናወነ መሆኑ፣

 የምዝገባ ስራዉን ለማከናወን ወሳኝ የሆኑ መመሪያዎችን እንዲሁም ምዝገባዉን ለማከናወን

የሚያገለግሉ ካርቦን እና ማርከር የማሰራጨት ስራ የተከናወነ መሆኑ ፣

 የኤጀንሲዉን የሰው ኃይል ስምሪት ውጤታማ ከማድረግ አንጻር ፣

 በኤጀንሲ ደረጃ የሰው ኃይል ስምሪትና አያያዝ የውስጥ አሰራር ማኑዋል እንዲዘጋጅ መደረጉ ፣

 ተቋማዊ የሥራ ደረጃ ምዘና ጥናት መሰረት በማድረግ በተቋም ደረጃ የሚገኙ ሰራተኞች በተላከዉ መመሪያ መሰረት ፍትሃዊ

ዉድድር በማድረግ የመደልደል ስራ የተሰራ መሆኑ፣

 ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮችም ተቋማዊ መዋቅራቸዉን በመመለስ የሰዉ ሃይላቸዉን

እንዲያሟሉ ድጋፍ በማድረግ አበረታች እንቅስቀሴ የተደረገ መሆኑ ፣

 ኤጀንሲዉ ከመንግስት የተረከበዉን ቢሮ በኤጀንሲዉ ፍላጎት እና ለስራ ምቹ ሊሆን በሚችል አግባብ በማደስና

በአስፈላጊ የቢሮ ግብአቶችን በማደራጀት ሰራተኛዉ ለስራ ምቹ በሆነ ሁኔታ በአዲስ ቢሮ ስራ እንዲጀምር

የማድረግ ስራ የተሰራ መሆኑ፣

 የኤጀንሲዉን ሰራተኛ በህግ የተፈቀደለትን ጥቅማ ጥቅም በወቅቱ እንዲያገኝ የማድረግ ስራ የተሰራ መሆኑ ፣

 በኤጀንሲ ደረጃ የሚገኙ ሴቶችንና አካል ጉዳተኞችን ከእቅድ ዝግጅት ጀምሮ በትግበራ እና በአፈጻጸም ግምገማ ላይ

እንዲሳተፉ በማድረግ ተጠቃሚነታቸዉን ለማረጋገጥ ጥረት የተደረገ መሆኑ ፣

 የኤጀንሲዉን የበጀት አቅም በማሳደግ ረገድ ፣

 ከተባባሪ አካላት ጋር የጋራ መግባባት በመፍጠር ተቋማዊ ተልእኮዉን ለማሳካት የሚያስችል የበጀት ድጋፍ

እንዲደረግ የተደረገ መሆኑ ፣

 የ 2009 በጀት አመት የኤጀንሲዉ የፕሮግራም በጀት አፈጻጸም ከ 2008 በጀት አመት ተመሳሳይ ወቅት

አፈጻጸም ጋር ሲነጻጸር 18.7 % ብልጫ ያለዉ መሆኑ፣

3.1.1.2 ድክመቶች

23
 የኤጀንሲዉን አመራር እና ፈጻሚ አቅም ለማጠናር የሚያስችል የተሟላ ስልጠና በመስጠት እና የራስ ማብቂያ

እቅዱን በተሟላ ደረጃ ተግባራዊ በማድረግ ረገድ ክፍተት ያለ መሆኑ፣

 በበጀት አመቱ ክፍት መደቦችን በሰዉ ሃይል ለማሟላት በእቅድ የተያዙ ተግባራት በተሟላ ደረጃ የተፈጸመ አለመሆኑ፣

 የኤጀንሲውን ሰራተኞች የእውቀትና ክህሎት ክፍተት በዳሰሳ ጥናት ለመለየት በእቅድ የተያዘዉ ተግባር የተፈጸመ አለመሆኑ ፣

 የሴት ሰራተኞች የአቅም ክፍተት ለመሙላት የሚያስችል ስልጠና አለመሰጠቱ ፣

 ለኤጀንሲዉ ሰራተኞች በአካባቢ ጥበቃ፣ በኤች .አይ.ቪ፣ በአካል ጉዳተኞች፣ በሰብዓዊ መብት፣ በህፃናት መብት ዙሪያ

የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና አለመስጠቱ፣

 በበጀት አመቱ ለኤጀንሲዉ የተመደበ በጀት በተሟላ ደረጃ ስራ ላይ አለመዋሉ፣

3.1.2 የተግባር ምእራፍ

3.1.2.1 ጥንካሬዎች

 ተቋማዊ የለዉጥ ስራ አመራር ዉጤታማትን በማሻሻል ረገድ ፣

 የኤጀንሲዉን አደረጃጀቶች ለማጠናከር እንዲቻል አገራዊ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ምክር ቤት እና

የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስራ አመራር ቦርድ የኤጀንሲዉን አፈጻጸም በመገምገም እና በአፈጻጸም ወቅት

የታዩ ጥንካሬዎችን እና ድክመቶችን በመለየት የቀጣይ አቅጣጫ እንዲያስቀምጡ የማድረግ ስራ

የተሰራ መሆኑ ፣

 የኤጀንሲዉን የለዉጥ ሰራዊት አደረጃጀት ለማጠናከር እንዲቻል የለዉጥ ሰራዊት አደረጃጀት ለመፍጠር

የሚያስችል የለዉጥ ሰራዊት አደረጃጀት ማሥፈጸሚያ ማንዋል እንዲዘጋጅ በማድረግ እና

በማንዋሉን መሰረት በሁሉም የስራ ሂደቶች ደረጃ የ 1 ለ 5 እና የለዉጥ ቡድን የማደራጀት ስራ

በመስራት አደረጃጀቶቹ ወደ ስራ እንዲገቡ የማደረግ ስራ የተሰራ መሆኑ ፣

 ተቋማዊ ተልእኮዉን ለማሳካት እንዲቻል በሚዛናዊ ዉጤት ተኮር ምዘና ስርአት የተቃኘ

ተቋማዊ እቅድ በማዘጋጀት ወደ ተግባር እንዲገባ የተደረገ መሆኑ ፣

 የኤጀንሲዉን አመራር እና ፈጻሚ ያሳተፈ የሲቪል ሰርቪስ ቀን በማክበር እና በሲቪል ሰርቪስ

ቀን በአል አከባባር ላይ ሰራተኛዉን እያዝናና ሊያስተምር የሚችል የጥያቄና መልስ ዉድድር

ፕሮግራም በማዘጋጀት የተሻለ ዉጤት ላስመዘገቡ ሰራተኞች የማበረታቻ ሽልማት የተሰጠ

መሆኑ ፣

24
 በአመራሩ እና በፈጻሚ ደረጃ የሚታዩ የመልካም አስተዳደር እና የኪራይ ሰብሳቢነት ችግሮችን በግምገማ በመለየት

በማኔጅመንት እና በፈጻሚ ደረጃ ትግል እንዲደረግባቸዉ የማድረግ ስራ የተሰራ መሆኑ፣

 ከአማካሪ ድርጅት ጋር ተያይዞ የአሰራር ክፍተቱን የፈጠሩ የኤጀንሲዉ አካላት እና አማካሪ ደርጅቱ በህግ ተጠያቂ

እንዲሆኑ የማድረግ ስራ የተሰራ መሆኑ ፣

 ተቋማዊ የፋይናንስ አጠቃቀም ውጤታማነትን በማረጋገጥ ረገድ ½

 በኤጀንሲዉ የፋይናንስ እና የንብረት አጠቃቀም ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን በመለየት በቀጣይ እንዲስተካከሉ ለፈጻሚ አካላት የምክር

ድጋፍ የተሰጠ መሆኑ ፣

 የኤጀንሲዉን የበጀት አጠቃቀም አቅም ለማሳደግ እንዲቻል ከገንዘብ እና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ጋር

በመቀናጀት የኤጀንሲዉ ባለሙያዎች በፕሮግራም በጀት ዙሪያ ስልጠና እንዲያገኙ የማድረግ ስራ የተሰራ መሆኑ ፣

 የወሳኝ ኩነት መረጃ ምዝገባ፣ ቅብብሎሽ፣አቅርቦትና አጠቃቀም ስርአትን በማሻሻል

ረገድ፣

 ለሦስቱ ፌዴራል መዝጋቢ ተቋማት እና ለስደተኞች ለእያንዳንዳቸዉ የሚያገለግሉ የክብር መዝገብ

ቅጽ፣ምስክር ወረቀትና የተጠቃለለ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ፣ የመረጃ አደረጃጀት፣ ቅብብሎሽ፣ አያያዝና

አቅርቦት አፈፃፀም መመሪያ የማዘጋጀት ስራ የተሰራ መሆኑ ፣

 አዋጁን ለማሻሻል እንዲቻል ከፌዴራል ዋና አቃቤ ህግ ጋር በጋራ ጥናት በማድረግ የአዋጅ ማሻሻያዉ

ለሚኒስትሮች ም/ቤት እና ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀርቦ እንዲጸድቅ የተደረገ መሆኑ ፣

 ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የወሳኝ ኩነት መረጃዎችን ለፌዴራል ኤጀንሲዉ እንዲልኩ በማድረግ መረጃዎችን የመቀበል ፣ የማጥራት

እና የማደራጀት ስራ የተሰራ መሆኑ ፣

 ለህብረተሰቡ ፣ ለባለድርሻና ተባባሪ አካላት ግንዛቤ በመፍጠር ረገድ ፣

 የወሳኝ ኩነት ምዝገባ አጀማመር ማብሰሪያ መድረክ ሰፊ የህዝብ ንቅናቄ ሊፈጥር በሚችል መልኩ በማክበር

ህብረተሰቡ ግንዛቤ ፈጥሮ ተሳትፎዉ እንዲያድግ የማድረግ ስራ የተሰራ መሆኑ ፣

 የወሳኝ ኩነት ምዝገባ አስመልክቶ የቴሌቪቭን እና የሬዲዮ ስፖት እና ችሎት ፕሮግራም

በማዘጋጀት ኤጀንሲዉን የማስተዋወቅ ስራ የተሰራ መሆኑ፣

 የወሳኝ ኩነቶች ምዝገባ አስመልክቶ መልእክት የሚያስተላልፉ ቢል ቦርዶች፣ ፓስተሮች፣

ባነሮች ፣ አጀንዳዎች እና መጽሄቶች በማዘጋጀት ኤጀንሲዉን የማስተዋወቅ ስራ የተሰራ

መሆኑ፣

25
 የመረጃ አመዘጋገብ፣ አደረጃጀትና አያያዝ ደህንነትን በማሻሻል ረገድ ½

 የመረጃ ደህንነት ተጠብቆ ለማደራጀት የሚያስችል ባለብረት ፋይል ካቢኔት ግዥ ለመፈጸም

የሚያስችል የበጀት ድጋፍ በማፈላለግ ግዥዉን ለመፈጸም ጥረት እየተደረገ መሆኑ፣

 የወሳኝ ኩነት ምዝገባ መረጃ ደህንነቱ ተጠብቆ እንዲደራጅ ለማድረግ ኤጀንሲዉ ከመንግስት

የተሰጠዉን አሮጌ ህንጻ በርካታ በጀት በመመደብ ህንጻዉ መረጃ ለመያዝ አመች በሆነ ሁኔታ በማደስ

የመረጃ ማደራጃ ክፍሉን ዝግጁ የማድረግ ስራ የተሰራ መሆኑ ፣

 የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስርአት ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ ስትራቴጅ መቅረጽ ፣

 የወሳኝ ኩነት ምዝገባ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ስትራቴጂክ ፕላን ለማዘጋጀት እንዲቻል

መነሻ ጥናት በማስጠናት የጥናት ሪፖርት እንዲቀርብ የተደረገ መሆኑ፣

 የዘርፉን አመራሩንና ፈፃሚ የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም በማሳደግ ረገድ ½

 በወሳኝ ኩነት ምዝገባ ዙሪያ ስልጠና ለመስጠት የሚያስችል የክፍተት ዳሰሳ በማድረግ ስልጠና

ለመስጠት የሚያስችል ሰነድ የተዘጋጀ መሆኑ፣ ፣

 ሁሉንም ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ያሳተፈ እና የወረዳ መዋቅሩን ማእከል ያደረገ ስልጠና

የተሰጠ መሆኑ ፣

 የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስርአቱን በመገንባት ሂደት ወሳኝ ድርሻ ላላቸዉ ቁልፍ ባለድርሻ አካላት

የግንዛቤ ማሥጨበጫ መድረክ በማዘጋጀት የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስርአቱን በመገንባት ሂደት

የበኩላቸዉን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ መፍጠር መቻሉ፣

 ከተባባሪና ባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅታዊ አሰራር ስርዓትን ተግባራዊ ማድረግ ፣

 ከኤጀንሲዉ ቁልፍ ባለድርሻ ተቋም ከሆነዉ ከማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ጋር በቅንጅት የሚሰሩ ስራዎችን

በተጠናከረ አግባብ ለመስራት የሚያስችል የጋራ መግባቢያ ሰነድ በማዘጋጀት የመፈራረም ስራ የተሰራ መሆኑ ፣

26
 በኤጀንሲዉ ስራ አመራር ቦርድ ስብሰባ ላይ ወሳኝ ባለድርሻ አካላት ኤጀንሲዉን በመደገፍ ረገድ ያላቸዉ

አፈጻጸም በሪፖርት እንዲቀርብ በማድረግ ቦርዱ በቅንጅታዊ አሰራሩ ላይ በታዩ ክፍተቶች ዙሪያ አቅጣጫ

እንዲያስቀምጥ የማድረግ ስራ መሰራቱ ፣

3.1.2.2 ድክመቶች

 ተቋማዊ የለዉጥ ሰራዊት ግንባታ ስራዉ በተጠናከረ አግባብ በመምራት እና የኪራይ ሰብሳቢነት እና የመልካም አስተዳደር

ችግሮችን ቀጣይነት ባለዉ መድረክ በመታገል ረገድ ክፍተት ያለ መሆኑ፣

 ለመረጃ ቅብብሎሽ፣ አያያዝ፣ አቅርቦትና አጠቃቀም የሚያገለግል ማንዋል አለመዘጋጀቱ፣

 የወሳኝ ኩነት ማስረጃዎችን የማዘጋጀትና ለተጠቃሚዎች የማቅረብ ስራ ተግባራዊ አለመደረጉ፣

 ለህብረተሰቡ በስርአቱ ዙሪያ በቂ ግንዛቤ በመፍጠር ተሳትፎዉ በሚፈለገዉ ደረጃ ማሳደግ አለመቻሉ፣

 የመረጃ አያያዝ ደህንነትን ለማስጠበቅ የሚያስችል አሰራር ማንዋል አለመዘጋጀቱ ፣

 ከባለድርሻ አካላት ጋር ጠንካራ እና ቀጣይነት ያለዉ ቅንጅታዊ አሰራር አለመኖር፣

3.1.3 ማጠቃለያ ምእራፍ

3.1.3.1 ጥንካሬዎች

 የተገልጋይ፣ ባለድርሻና ተባባሪ አካላትን ዕርካታና አመኔታ በማሳደግ ረገድ ፣

 በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ የሚነሱ ቅሬታዎችን በመለየት ምላሽ ለመስጠት እንዲቻል ቅሬታ እና አቤቱታዎችን ተቀብሎ

የሚያስተናግድ ዳይሬክቶሬት በመሰየም ወደ ስራ እንዲገባ የተደረገ መሆኑ፣

 በምዝገባ ሂደቱ ላይ በአገልግሎት አሠጣጥ ረገድ የቅሬታ መንስኤ የሚሆኑ ጉዳዮችን በመለየት ችግሩን የአሰራር ስርአቱን

በማሻሻል እንዲፈታ የማድረግ ስራ መሰራቱ፣

 የአገልግሎት ተደራሽነትና ተጠቃሚነት በማሳደግ ረገድ ½

27
 በኤጀንሲ ደረጃ ልዩ ድጋፍ የሚሹ አካላትን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ከማጠናከር አንጻር በኤጀንሲዉ ደረጃ ልዩ

ድጋፍ የሚሹ አካላትን ፍላጎት መሰረት የደረገ እቅድ በማዘጋጀት ተግባራዊ ለማድረግ ጥረት የተደረገ መሆኑ፣

 የአገልግሎት ተደራሽነትና ተጠቃሚነትን በማሳደግ ረገድ ተቋማዊ አፈጻጸሙ ያለበትን የአፈጻጸም ደረጃ ለማወቅ

እንዲቻል ከህግ ማእቀፍ ፣ ከአደረጃጀት ፣ ከአቅም ግንባት ስራዎች አፈጻጸም እንዲሁም ከሪፖርት እና መረጃ ቅብብሎሽ

ስርአት አንጻር የዳሰሳ ጥናት ለማድረግ የሚያስችል ቅድመ ዝግጅት በማጠናቀቅ ጥናቱ እንዲጀመር የተደረገ መሆኑ፣

 የድጋፍና ክትትል አፈጻጸምን በተመለከተ ፣

 በኤጀንሲ ደረጃ የድጋፍና ክትትል ተግባራትን በመፈጸም ሂደት የሚታዩ የድጋፍና ክትትል ክፍተቶችን በዳሰሳ ጥናት የመለየት ስራ የተሰራ

መሆኑ ፣

 የክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮችን የምዝገባ አፈጻጸም ለማጠናከር የሚያችል ድጋፍ በማድረግ እና

በምዝገባ አጀማመር ላይ ያጋጠሙ ችግሮችን በመለየት የመፍትሄ አቅጣጫ እንዲቀመጥ የተደረገ

መሆኑ፣

3.1.3.2 ድክመቶች

 የተገልጋዮችን ቅሬታ ለመቀነስ የሚያስችሉ ስልቶችን በተሟላ ደረጃ ተግባራዊ በማድረግ ረገድ ክፍተት ያለ መሆኑ፣

 ተቋማዊ የድጋፍና ክትትል ስራዉ በእቅድ የሚመራ እና ቀጣይነት ያለዉ አለመሆን ፣

3.2 የተገኙ ዉጤቶች

 በየደረጃዉ ለሚገኙ 13,694 የወሳኝ ኩነት መዝጋቢ አካላት በወሳኝ ኩነት ምዝገባ ጽንሰ ሃሳብ እና አተገባባር

ዙሪያ ስልጠና በመስጠት የምዝገባ ስራዉን በባለቤትነት እንዲመሩ መደረጉ፣

 በየደረጃዉ ለሚገኙ 5,515,751 ለሚሆኑ ባለድርሻ አካላትና የህብረተሰብ ክፍል በወሳኝ ኩነት ምዝገባ ጽንሰ

ሃሳብ ዙሪያ ግንዛቤ በመፍጠር በምዝገባ ስራዉ ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ ምቹ ሁኔታ የተፈጠረ መሆኑ፣

 በአገር አቀፍ ደረጃ ለምዝገባ ስራ አስፈለጊ የሆኑ ግብአቶች እንዲሟሉ በማድረግ ምዝገባ መጀመር

ከሚገባቸዉ 18,616 ቀበሌዎች በ 15,527 /83.5%/ የምዝገባ ማእከላት የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስራ

እንዲጀመር መደረጉ ፣

28
 በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች ምዝገባዉን በጀመሩ የምዝገባ ማእከላት አማካይነት በአራቱም የኩነት አይነቶች

በእቅድ ከተያዘዉ 1,488,231 ኩነት መካከል 631,854 /42%/ ያህል ኩነት ምዝገባ በማከናወንና መረጃዉን

በመረከብ የማደራጀት ስራ የተሰራ መሆኑ፣

 የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስርአት ግንባታ ያለበትን የአፈጻጸም ደረጃ በዳሰሳ ጥናት በመለየት ስርአቱን በመገንባት

ረገድ በቀጣይ በሚከናወኑ ተግባራት ዙሪያ ግልጽ አቅጣጫ እንዲቀመጥ መደረጉ ፣

 በፌዴራል ደረጃ የወሳኝ ኩነት እንዲመዘግቡ በህግ ሃላፊነት የተሰጣቸዉ ተቋማት የምዝገባ ስራዉን

እንዲጀምሩ ለማድረግ የሚያስችል የምዝገባ መሳሪያዎችን የማዘጋጀት ስራ የተሰራ መሆኑ፣

 በሚፈለገዉ ደረጃ ባይሆንም ህብረተሰቡ በወሳኝ ኩነት ምዝገባ ጠቀሜታ ላይ ግንዛቤ የፈጠረ መሆኑ ፣

 በሚፈለገዉ ደረጃ ባይሆንም በየደረጃዉ የሚገኘዉ የፖለቲካ አመራር የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስርአቱን በመደገፍ

ረገድ ለወሳኝ ኩነት መዋቅሩን ለመደገፍ ጥረት ማድረግ የጀመረ መሆኑ ፣

 በሚፈለገዉ ደረጃ ባይሆንም የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስርአቱ ለመገንባት የሚያስፈልጉ ግብአቶችና ለማሟላት

እንዲቻል ከተባባሪ አካላት ጋር በተፈጠረ ግንኙነት አማካይነት ተባባሪ አካላት ስርአቱን በበጀትና በቴክኒክ

እንዲደግፉ መደረጉ ፣

 የኤጀንሲዉ አመራር እና ፈጻሚ በተለያየ ጊዜ በተሰጠዉ ስልጠና ፣ ልምድ ልዉዉጥ አማካይነት ስርአቱን

የመምራት እና የመፈጸም አቅሙ የተሻሻለ መሆኑ፣

 የወሳኝ ኩነት ምዝገባ መዋቅሩን በማጠናከር ረገድ ወሳኝ ሚና ያለዉ የሰዉ ሃይል በማሟላት ወደ ስምሪት

ገብቶ ተቋማዊ እቅዱን በመፈጻም ረገድ የበኩሉን ድረሻ እንዲወጣ የተደረገ መሆኑ፣ / ከፌዴራል እስከ ወረዳ

በእቅድ ከተያዘዉ 5878 ዉስጥ 4124 70% እንዲሟላ ተደርጓል /

3.3 በእቅድ አፈጻጸም ወቅት ያጋጠሙ ተግዳሮቶች

29
 የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስርአቱን በመደገፍ ረገድ ወሳኝ ሚና ያላቸዉ በየደረጃዉ የሚገኙ የዘርፉ

ባለድርሻ አካላት ስርአቱን በመደገፍ ረገድ የሚጠበቅባቸዉን ሚና በሚፈለገዉ ደረጃ እየተወጡ

አለመሆኑ በተለይም የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስራዉን ዉጤታማ በማድረግ ረገድ ወሳኝ ሚና ያለዉ

የጤናዉ ዘርፍ ሃላፊነቱን በሚፈለገዉ ደረጃ አለመወጣት ፣

 በየደረጃዉ የሚገኙ የወሳኝ ኩነት መዝጋቢ አካላት ምዝገባዉን በሚፈለገዉ የጥራት ደረጃ ለማከናወን

የሚያስችል በቂ አቅም የፈጠሩ አለመሆኑ፣

 በፌዴራል ደረጃ የወሳኝ ኩነት እንዲመዘግቡ በህግ ግዴታ የተጣለባቸዉ መዝጋቢ አካላት የምዝገባ

ስራዉን ባለመጀመራቸዉ ምክንያት በዉጭ አገር የሚገኙ ዜጎችን እና ትዉልደ ኢትዮጵያዉያን

አገልግሎቱን ለማግኘት የተቸገሩ መሆኑ፣

 የምዝገባ ስራዉን ተግባራዊ በማድረግ ረገድ ወሳኝ ድርሻ ያለዉ የቀበሌ ስራ አስኪያጅ ተጠሪነቱ ለሌላ

አካል በመሆኑ ለክትትልና ድጋፍ ስራ አስቸጋሪ በመሆኑ ለስራዉ ተገቢዉን ትኩረት በመስጠትና

ባለቤት ሆኖ በመፈጸም ረገድ ክፍተት የፈጠረ እና በምዝገባዉ ጥራት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ያሳደረ

መሆኑ ፣

 የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስርአት ግንባታ ላይ ህብረተሰቡ ያለዉን ተሳትፎ ለማጠናከር እንዲቻል

በየደረጃዉ የተሰራ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ያለ ቢሆንም ስርአቱ አዲስ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ

ህብረተሰቡ በስርአቱ ዙሪያ በቂ ግንዛቤ ያለዉ ባለመሆኑ ኩነቶችን የማስመዝገብ ተሳትፎዉ አነስተኛ

መሆኑ፣

 የወሳኝ ኩነት ምዝገባ አላማ የዜጎችን መረጃ በወቅቱና በጥራት በመመዝገብ መረጃዉ ለህግ፣

ለአስተዳደር እና ለስታትስቲክስ አገልግሎት እንዲዉል ማድረግ ሲሆን በተጨባጭ በምዝገባ ሂደቱ ላይ

ወቅታዊ የኩነት ምዝገባ ላይ ከማተኮር ይልቅ ጊዜዉ ያለፈበት ኩነት የማስመዝገብ ችግር ያለ መሆኑ፣

 የወሳኝ ኩነት ምዝገባ መረጃ በሚፈለገዉ የጥራት ደረጃ በመመዝገብ እና የመረጃዉን ደህንነት

በሚያረጋግጥ አኳሃን የማደራጀትና በየደረጃዉ ለሚገኙ አካላት የማስተላለፍ ስራ ለመስራት

በመንግስት እና በተባባሪ አካላት ድጋፍ ግብአቶችን ለማሟላት የተደረገ ጥረት ያለ ቢሆንም የበጀት

ፍላጎቱ ሰፊ በመሆኑ ይህን የበጀት ክፍተት ለመሙላት አስተማማኝ የበጀት ምንጭ አለመኖር፣

30
 የመረጃ ቅብብሎሽ ስርአቱ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጅ የተደገፈ ባለመሆኑ ምክንያት በአመዘጋገብ ፣

መረጃን ከቀበሌ ጀምሮ እስከ ፌዴራል ባለዉ መዋቅር ተደራሽ በማድረግ እንዲሁም መረጃዎችን

በአግባቡ በማደራጀት ረገድ የሚታዩ ክፍተቶች በመረጃዉ ጥራት እና ወቅታዊነት ላይ አሉታዊ

ተጽእኖ የፈጠረ መሆኑ፣

ስለሆነም በ 2009 በጀት አመት በእቅድ ተይዘዉ የተከናወኑ ተግባራት ያስገኙትን ዉጤት የበለጠ አጠናክሮ

ለመቀጠል እና እቅዱን በመፈጸም ረገድ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በመፍታት በ 2010 በጀት አመት የተሻለ

ዉጤት ለማስመዝገብ የሚያስችል እቅድ እንዲዘጋጅ ተደርጓል፡፡

ክፍል አራት፡- የፌዴራል ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ የ 2010 በጀት አመት

ዕቅድ

4.1 የመማማርና እድገት እይታ

ግብ 1:- የኤጀንሲዉን አመራር እና ፈፃሚ አቅም ማሳደግ ፣

 የኤጀንሲዉን እቅድ ማዘጋጀት፣


 የተቋሙን የ 2010 በጀት አመት ፊዚካል እቅድ ማዘጋጀት ፣
 በተቋሙ የ 2010 በጀት አመት ፊዚካል እቅድ ዙሪያ ለኤጀንሲዉ ሰራተኞች ኦረንቴሽን መስጠት ፣

 በተቋሙ የ 2010 በጀት አመት ፊዚካል እቅድ ዙሪያ ለክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች
ኦረንቴሽን መስጠት ፣
 የኤጀንሲዉ ዳይሬክቶሬቶች የተቋሙን እቅድ መነሻ በማድረግ የ 2010 ዓ.ም እቅድ እንዲያዘጋጁ
ማድረግ ፣
 የኤጀንሲዉ ዳይሬክቶሬቶች የ 2010 ዓ.ም እቅድ ለስራ ሂደቱ ፈጻሚዎች እንዲያወርዱ ማድረግ

 የኤጀንሲዉን የ 2010 እቅድ ለማሳካት ወሳኝ ድርሻ ያላቸዉን ሌሎች እቅዶች ማዘጋጀት፣
 የኤጀንሲዉን የ 2010 በጀት አመት የሰብአዊ መብት ድርጊት መርሃ ግብር እቅድ ማዘጋጀት፣
 የኤጀንሲዉን የ 2010 ዓ.ም የመልካም አስተዳደር እና የለዉጥ ስራዎች እቅድ ማዘጋጀት፣

 የኤጀንሲዉን የ 2010 ዓ.ም የግዥ እቅድ ማዘጋጀት፣

 የኤጀንሲዉን የ 2010 ዓ.ም የስልጠና እቅድ ማዘጋጀት፣

 የኤጀንሲዉን የ 2010 ዓ.ም የሰዉ ሃይል ስምሪት እቅድ ማዘጋጀት፣

31
 ተቋሙ የሥራ ሂደቶች የፈፃሚዉን የዕውቀትና የክህሎት ክፍተትን ለማሳደግ የሚያስችል የራስ ማብቂያ ዕቅድ
እንዲያዘጋጁ ማድረግ ፣
 የኤጀንሲው አመራር የመምራት አቅም ሊያጎለብት የሚችል ስልጠና መስጠት፣
 ለኤጀንሲዉ አመራር በሚዛናዊ ዉጤት ተኮር / BSC / ጽንሰ ሃሳብ እና አተገባበር ዙሪያ ስልጠና መስጠት ፣
 ለኤጀንሲዉ አመራር በፕሮግራም በጀት አጠቃቀም ዙሪያ ስልጠና መስጠት፣
 ለኤጀንሲዉ አመራር በትራንስፎርሜሽናል ሊደር ሽፕ ዙሪያ ስልጠና መስጠት ፣

 የኤጀንሲው ፈጻሚ የመፈጸም አቅም ሊያጎለብት የሚችል ስልጠና መስጠት፣


 በኤጀንሲ ደረጃ ድጋፍና ክትትል ለሚያደርጉ ፈጻሚዎች በድጋፍና ክትትል አተገባበር ዙሪያ ስልጠና
መስጠት፣
 ለኤጀንሲዉ የጥናትና ምርምር አሰራር ማሻሻያ ባለሙያዎች በጥናትና ምርምር ሪፖርት ዝግጅት ዙሪያ ስልጠና
መስጠት፣
 ለኤጀንሲዉ ሰራተኞች በሚዛናዊ ዉጤት ተኮር / BSC / ዙሪያ ስልጠና መስጠት ፣
 በኤጀንሲ ደረጃ አዲስ ለሚቀጠሩ ሰራተኞች በኤጀንሲዉ እና በዳይሬክቶሬቱ ተግባርና ሃላፊነት ዙሪያ
የኢንዳክሽን ስልጠና መስጠት፣
 ለኤጀንሲዉ የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች በፎቶ እና በቪዲዮ ቀረጻ ዙሪያ ስልጠና መስጠት፣
 ለኤጀንሲዉ የጨረታ ኮሚቴ እና ለጨረታ አጽዳቂ ኮሚቴ አባላት በግዥ ሂደት እና አተገባባር ዙሪያ ስልጠና
መስጠት ፣
 ለኤጀንሲዉ የበጀት እና ፋይናንስ ባለሙያዎች በፕሮግራም በጀት አጠቃቀም ዙሪያ ስልጠና መስጠት፣
 የተቋሙን ሴት ሰራተኞች አቅም ክፍተት ለመሙላት የሚያስችል ስልጠና መስጠት፣
 በ 2011 ዓ..ም ለመጀመሪያ እና ለሁለተኛ ዲግሪ የሚማሩ አመራርና ባለሙያዎችን የመለየት የማዘጋጀት ስራ
መስራት፣

የልምድ ልዉዉጥ እና የተሞክሮ ቅመራ ስራን ማጠናከር


 በተቋም ደረጃ የልምድ ልዉዉጥ ለማድረግ የሚያስችል የአፈጻጸም ማኑዋል ማዘጋጀት ፣

 በተዘጋጀዉ የልምድ ልዉዉጥ ማኑዋል ዙሪያ በኤጀንሲ ደረጃ የጋራ መግባባት መፍጠር ፣

 የኤጀንሲዉ ዳይሬክቶሬቶች የእርስ በእርስ የልምድ ልዉዉጥ የሚያደርጉበት አሰራር ተግባራዊ ማድረግ ፣

 የኤጀንሲዉ ስራ አመራር ቦርድ አባላት ፣ የኤጀንሲዉ ማኔጅመንት አባላት እና የቡድን መሪዎች የወሳኝ ኩነት ምዝገባ
አተገባበር ዙሪያ የዉጭ አገር ልምድ እንዲያገኙ ማድረግ፣
 በልምድ ልዉዉጥ ወቅት የተለዩ ምርጥ ልምዶችን መቀመር እና ማሰራጨት፣

 የኤጀንሲዉን ዳይሬክቶሬቶች በለዉጥ ስራዎች አተገባበር ፣ በእቅድ ፣ ሪፖርትና በጀት ዝግጅት ድጋፍ መስጠት፣
የግቡ ውጤት፡ የመፈፀም አቅማቸው ያደገ አመራርና ፈፃሚ ½
ግብ 2 :- ተቋማዊ የለዉጥ ስራ አመራር ዉጤታማትን ማሻሻል

32
የለውጥ ሥራ አመራር ስርዓትን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችሉ የለውጥ መሳሪያዎችን ማዘጋጀት፣
 የኤጀንሲዉን የዜጎች ቻርተር ማዘጋጀት፣

 የኤጀንሲዉን የሚዛናዊ ዉጤት ተኮር የምዝና ማንዋል ማዘጋጀት፣

 ኤጀንሲዉ ከዳይሬክቶሬቶች፣ የኤጀንሲዉ ዳይሬክቶሬቶች ከፈጻሚዉ ጋር ቲም ቻርተር በማዘጋጀት ተፈራርመዉ


ወደ ስራ እንዲገቡ ማድረግ፣

 በተቀረጹ የለውጥ ሥራ አመራር መሳሪያዎች ላይ ለአመራሩና ፈፃሚው ግንዛቤ መፍጠር፣

 በኤጀንሲ ደረጃ የፈጣን ለዉጥ አምጭ ተግባራትን / አቅጣጫ ጠቋሚ ፣ የቢሮ መግለጫ ፣ ባጅ ፣ የጠረንጴዛ መግለጫ
/ እንዲሟላ ማድረግ ፣
 ተቋማዊ ተግባራትን በተደራጀ የለዉጥ ሰራዊት እንዲመራ ማድረግ፣

 የኤጀንሲዉን የለዉጥ ሰራዊት አደረጃጀት ማኑዋል መከለስ፣

 በኤጀንሲ ደረጃ የተደራጁ የ 1 ለ 5 አደረጃጀቶች በየእለቱ ስራቸዉን እንዲገመግሙ ማድረግ ፣


 በኤጀንሲ ደረጃ የተደራጁ የለዉጥ ቡድን አደረጃጀቶች በየሳምንቱ ስራቸዉን እንዲገመግሙ ማድረግ ፣
 የኤጀንሲዉ ማኔጅመንት ተቋማዊ አፈጻጸሙን በየ 15 ቀኑ እንዲገመግም ማድረግ ፣
 ኤጀንሲዉ ተቋማዊ አፈጻጸሙን ከአጠቃላይ ሰራተኛ ጋር በየወሩ መገምገም ፣
 ተቋማዊ አፈጻጸሙን ከክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ጋር በጋራ መድረክ በየሩብ አመቱ መገምገም ፣
 በኤጀንሲ እና በስራ ሂደት ደረጃ ግንባር ቀደም ፈጻሚ ፣ 1 ለ 5 ፣ የለዉጥ ቡድን እና የስራ ሂደት መለየት፣
 በተቋም ደረጃ ለተለዩ ግንባር ቀደም ፈጻሚ ፣ 1 ለ 5 ፣ የለዉጥ ቡድን እና የስራ ሂደት እዉቅና መስጠት ፣
 በወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስራ የተሻለ አፈጻጸም ያላቸዉን ክልሎች መለየትና እዉቅና መስጠት ፣
 የኪራይ ሰብሳቢነት፣ የሴኩላሪዝም እንዲሁም የመልካም አስተዳደር ችግሮችን መለየትና መታገል፣

 በአመራርና በፈጻሚ ደረጃ የሚታዩ የኪራይ ሰብሳቢነት፣ የመልካም አስተዳደር እና የሴኩላሪዝም


አመለካከት እና ተግባራትን መለየት፣
 በተለዩት የኪራይ ሰብሳቢነት ፣የመልካም አስተዳደር እና የሴኩላሪዝም ችግሮች ላይ በለዉጥ ሰራዊት
መድረክ ትግል እንዲደረግበት ማድረግ፣
 በተቋም ደረጃ የኪራይ ሰብሳቢነት ፣የመልካም አስተዳደር እና የሴኩላሪዝም ችግሮችን በመቅረፍ ረገድ
የመጣዉን ለዉጥ መለየት፣

የግቡ ዉጤት :- የተሻሻለ የለውጥ ሥራ አመራር

ግብ 3: ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የመጠቀም አቅምን ማሳደግ ፣

33
 የኤጀንሲዉን አመራር እና ፈጻሚ የኢ/ቴክኖሎጅ አጠቃቀም ክፍተት ለመሙላት የሚያስችል ስልጠና
መስጠት፣
 ለኤጀንሲዉ ሰራተኞች የመሰረታዊ ኮምፒዉተር ስልጠና መስጠት፣
 ለኤጀንሲዉ ሰራተኞች የዳታ ኢንትሪና ቫሊዴሽን ስልጠና መስጠት ፣
 ለኤጀንሲዉ ሰራተኞች በኤስ ፒ ኤስ ኤስ ዘሪያ ስልጠና መስጠት፣
 ለኤጀንሲዉ የኢን/ ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች በአድቫንስድ ኔት ወርክ ዙሪያ ስልጠና መስጠት፣
 ለኤጀንሲዉ የኢን/ ኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች በፕሮግራሚንግ ዙሪያ ስልጠና መስጠት፣
 ለኤጀንሲዉ የህዝብ ግንኙነት ባለሙዎች በፊልም እና ፎቶ ኢዲቲንግ ዙሪያ ስልጠና መስጠት፣
 ለኤጀንሲዉ የህዝብ ግንኙነት ባለሙዎች በግራፊክስ ዙሪያ ስልጠና መስጠት፣
 ለኤጀንሲዉ የጥናት ምርምርና አሰራር ስርአት ባለሙያዎች በክብር መዝገብ እና የምስክር
ወረቀት ዲዛይን ዙሪያ ስልጠና መስጠት፣

የግቡ ውጤት፡- ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የመጠቀም አቅማቸው ያደገ አመራርና ፈፃሚ

ግብ 4:- የሰው ኃይል ስምሪት ውጤታማነትን ማሳደግ፣


 የተቋሙን የሰው ኃይል ማሟላት ፣
 ክፍት የስራ መደቦችን በመለየት በቅጥር ፣ በዝውውርና በደረጃ እድገት ማሟላት ፣

 ለኤጀንሲዉ ሰራተኞች ምቹ የስራ አካባቢ መፍጠር፣


 የኤጀንሲዉን ሰራተኞች ተጠቃሚ የሚያደርግ የደንብ ልብስ አጠቃቀም መመሪያ ማዘጋጀት ፣
 በኤጀንሲ ደረጃ የደንብ ልብስ የሚያስፈልጋቸዉ ሰራተኞች በመለየት እንዲሟላ ማድረግ ፣

 የተሽከርካሪ አገልግሎት ለሚያስፈልጋቸዉ ዳይሬክቶሬቶች አገልግሎቱ እንዲሟላ ማድረግ ፣

 ለኤጀንሲዉ ሰራተኞች ልዩ ልዩ የጽዳት እቃዎች እንዲቀርብ ማድረግ ፣

 የሰራተኛ ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ግብአቶች ማሟላት ፣

 ለኤጀንሲዉ ሰራተኞች በተመጣጣኝ ዋጋ የካፌ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ ፣

 ሰራተኞች የአመት ፈቃዳቸዉን በአግባቡ እንዲጠቀሙ የፈቃድ አሰጣጡ በእቅድ እንዲመራ ማደረግ ፣

 የኤጀንሲዉ ሴት ሰራተኞች ህጻናት ልጆቻቸዉን መንከባከቢያ ቦታ ለማዘጋጀት የሚያስችል ጥናት ማድረግ ፣


 በኤጀንሲ ደረጃ የባለ ብዙ ዘርፍ ተግባራትን ማከናወን፣
 በተቋሙ በሚከናወኑ ተግባራት ሴቶችንና አካል ጉዳተኞችን ማሳተፍ ፣

 በተቋም ደረጃ አለም አቀፍ የሴቶች ቀን /ማርች 8/ እንዲከበር ማድረግ ፣

 በተቋም ደረጃ የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ማክበር ፣

 በተቋም ደረጃ የአካል ጉዳተኞች ቀን ማክበር ፣

 በተቋም ደረጃ ኤች አይ ቪ ቀን ማክበር ፣

34
 በተቋም ደረጃ የግንቦት 20 በአል ማክበር ፣

 በተቋም ደረጃ የፍትህ ሳምንት በአል ማክበር ፣

 የተቋሙ ሰራተኛ በችግኝ ተከላ ፕሮግራም ላይ እንዲሳተፍ ማድረግ ፣


የግቡ ውጤት፡- ውጤታማ የሰው ኃይል ስምሪት

4.2 የዉስጥ አሰራር እይታ


ግብ 5:- የዘርፉን የግብአት አጠቃቀም አቅም ማሳደግ ½
 በፌዴራልና በክልል ደረጃ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስርአቱን ተግባራዊ ለማድረግና የመረጃ ደህንነት ለማስጠበቅ
የሚያስችሉ ግብአቶችን ማሟላት፣
 በፌዴራል ደረጃ መረጃ ለማደራጀት የሚያስችል ተንሸራታች ፋይል ካቢኔት እንዲሟላ ማድረግ፣
 በፌዴራል እና በክልል ደረጃ መረጃ ለመያዝ የሚያስችል ከፍተኛ አቅም ያላቸዉ ኮምፒዉተሮችንና ተዛማጅ
መሳሪያዎችን ማሟላት ፣
 በፌዴራል ደረጃ በመረጃ አደረጃጀት ላይ የሚያጋጥም አደጋን መከላከል የሚያስችል የእሳት ማጥፊያ መሳሪያ
ማሟላት፣
 በክልል ደረጃ ለሚገኙ ቀበሌዎች የመረጃ ማስቀመጫ /ሸልፍ/ እንዲሟላ ማድረግ፣
 በክልል ደረጃ ለሚገኙ ወረዳዎች የሞተር ሳይክል እንዲሟላ ማድረግ፣
 በቀበሌ ደረጃ የወሳኝ ኩነት መረጃ ቅብብሎሽ የሚያገለግል ቦርሳ ማሟላት፣
 በፌዴራል ደረጃ የመረጃ ደህንነት ለማረጋገጥ የሚያስችል ካሜራ እንዲሟላ ማድረግ፣
 በፌዴራል ደረጃ የመረጃዉን ደህንነት ሊያስጠብቅ የሚችል የኤሌትሪክ አጥር ማሰራት፣
 የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስርአቱን የሚደገፉ ግብአቶችን ማሰራጨት፣
 ለ 4 ቱ የፌዴራል መዝጋቢ ተቋማት የተዘጋጀዉን የክብር መዝገብ ማሰራጨት ፣
 ለ 4 ቱ የፌዴራል መዝጋቢ ተቋማት የተዘጋጀዉን የምስክር ወረቀት ማሰራጨት ፣
 ለክልሎች የጉዲፈቻ ምዝገባ ለማከናወን የሚያስችል የክብር መዝገብ እና የምስክር ወረቀት ማሰራጨት ፣
 ለክልሎች እና ለ 4 ቱ ፌዴራል መዝጋቢ ተቋማት የተዘጋጀዉን የምዝገባ አፈጻጸም መመሪያ ማሰራጨት፣
 የወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና የብሄራዊ መታወቂያ አዋጅ ማሻሻያ ቁጥር 1049/2009 ማሰራጨት፣
የግቡ ውጤት፡- የተሻሻለ የግብአት አጠቃቀም

ግብ 6:- የዘርፉን ድጋፍና ክትትል ሥርዓት ማሻሻል

 የድጋፍና ክትትል ስርዓቱን ለመምራት የሚያስችል ማኑዋል ማዘጋጀት፣


 በተቋም ደረጃ የተደረጉ ዳሰሳዎችና እቅድ አፈጻጸም ሪፖርቶችን መነሻ በማድረግ ማኑዋሉን ለማዘጋጀት
የሚያስችል መረጃዎችን መሰብሰብ ፣
 ተቋማዊ የድጋፍና ክትትል ስርዓቱን ለመፈጸም የሚያስችል የድጋፍና ክትትል ማኑዋል ማዘጋጀት፣

35
 በተዘጋጀዉ የድጋፍና ክትትል ማኑዋል ዙሪያ በኤጀንሲ ደረጃ የጋራ መግባባት መፍጠር ፣
 የድጋፍና ክትትል ተግባራትን ማከናወን ፣
 ድጋፍና ክትትል ለማድረግ የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን ማከናወን፣
 ለክልል እና ከተማ አስተዳደር ድጋፍና ክትትል ማድረግ፣

 ለፌዴራል መዝጋቢ ተቋማት ድጋፍና ክትትል ማድረግ፣

 የድጋፍና ክትትል ሂደቱን አፈጻጸም መገምገም ፣

 ተቋማዊ የህግ ድጋፍ አገልግሎት መስጠት፣


 በኤጀንሲ ደረጃ የሚዘጋጁ ዉሎች ላይ አስተያየት መስጠት ፣
 ለኤጀንሲዉ ሰራተኞች በፌዴራል መንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 515/1999፣ በመንግስት
ሰራተኞች የዲሲፕሊን አፈጻጸምና የቅሬታ አቀራረብ ደንብ ቁጥር 77/1994 እና ተያያዥ
መመሪያዎች ዙሪያ ግንዛቤ መፍጠር ፣
 ለኤጀንሲዉ ሰራተኞች በሰብዓዊ መብትና የህፃናት መብት ዙሪያ ግንዛቤ መፍጠር፣

 ኤጀንሲዉን በመወከል መክሰስና መከሰስ፣

 በኤጀንሲዉ የሚዘጋጁ መመሪያዎችን የህግ ቅርጽ ማስያዝ፣

 የኤጀንሲዉን አመራሮችና የስራ ሂደቶች በህግ ጉዳዮች ዙሪያ ማማከር፣

 የኤጀንሲዉን የሰብአዊ መብት የድርጊት መርሃ ግብር አፈጻጸም በመገምገምና ሪፖርት በማዘጋጀት
ለሚመከተዉ አካል ሪፖርት መላክ ፣

የግቡ ዉጤት: ውጤታማ የድጋፍና ክትትል አሰራር

ግብ 7:- የዘርፉን አመራሩንና ፈፃሚ የመፈጸምና የማስፈጸም አቅም ማሳደግ ½

 የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ማሰልጠኛ ሰነድ በማዘጋጀት ከመዝጋቢ አካላት የጋራ ማድረግ ፣
 የስልጠና አዘጋጃጀት እና አሰጣጥ ጋይድላይን ማዘጋጀት፣
 ለፌዴራል መዝጋቢ ተቋማት ስልጠና ለመስጠት የሚያስችል የስልጠና ሰነድ ማዘጋጀት፣
 ለክልሎች እና ከ/አስተዳደሮች ስልጠና ለመስጠት የሚያስችል የአዋጁን ማሻሻያና የዳሰሳ ጥናት
ግኝቶችን ያካተተ የስልጠና ማኑዋል ማዘጋጀት፣
 በተዘገጀዉ የስልጠና እቅድ እና የሥልጠና አተገባበር ዙሪያ ከመዝጋቢ አካላት ጋር የጋራ መግባባት
መፍጠር፣

36
 ለክልል ፣ ለከተማ አስተዳደር እና ለፌዴራል መዝጋቢ ተቋማት አመራር እና ባለሙያዎች ስልጠና መስጠት፣
 ለአራቱ የፌዴራል መዝጋቢ ተቋማት በምዝገባ አፈጻጸም መመሪያ ላይ ስልጠና መስጠት፣
 ለክልል እና ከተማ አስተዳደር አመራሮችና ባለሙያዎች በተሻሻለዉ የምዝገባ አፈጻጸም መመሪያ
ዙሪያ የአሰልጣኞች ስልጠና መስጠት፣
 ለክልልና ከተማ አስተዳደር ወ/ኩ/ም/ኤ/ አመራርና ባለሙያዎች በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ
አጠቃቀም ዙሪያ ቴክኒካዊ ስልጠና መስጠት ½
 በዳታ ኢንኮዲንግ፣ በዳታ ቬሪፊኬሽን ፣ ኢንትሪ እና ቫሊዴሽን ዙሪያ ለመረጃ ቅበላ ባለሙያዎች
ቴክኒካዊ ስልጠና መስጠት ½
 ለክልልና ከ/አስተዳደር የጥናትና ምርምር ባለሙያዎች በጥናትና ምርምር ክህሎት ዙሪያ ስልጠና
መስጠት፣
 ልዩ ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸዉ ክልሎች / አፋር፣ ጋምቤላ፣ ቤኒሻንጉል፣ ሶማሌ፣ ድሬዳዋ ፣ ሃረር /
አመራሮች እና ባለሙያዎች በወሳኝ ኩነት ምዝገባ ትግበራ ዙሪያ ስልጠና መስጠት፣
 በክልል እና ከተማ አስተዳደር ደረጃ ለሚገኙ የትምህርት እና ስልጠና ባለሙያዎች በስልጠና አሰጣጥ
ክህሎት ላይ ስልጠና መስጠት፣
 በድረ-ገፅ እና ማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም ዙሪያ ለክልልና ከተማ አስተዳደር የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች
ስልጠና መስጠት ፣
 በየደረጃዉ የተሰጡ ስልጠናዎችን አፈፃፀም ደረጃ ከክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ጋር በመገምገም
የቀጣይ አቅጣጫ ላይ መግባባት መፍጠር ½
 ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በወሳኝ ኩነት ምዝገባ ጽንሰ ሃሳብ እና አተገባበር ዙሪያ ስልጠና እንዲሰጡ ማድረግ፣
 በክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ደረጃ በሚሰጡ ስልጠናዎች ላይ የጋራ መግባባት መፍጠር፣

 ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በወሳኝ ኩነት ምዝገባ አፈጻጸም መመሪያ እና በሌሎች መሰረታዊ ርእሰ ጉዳዮች
ዙሪያ በየደረጃዉ ለሚገኙ አመራርና ፈጻሚ አካላት ስልጠና እንዲሰጡ ማድረግ፣
 በየደረጃው ለሚገኙ የዘርፉ አመራርና ፈፃሚ የልምድ ልውውጥ መድረክ ማዘጋጀት
 በክልል እና ከተማ አስተዳደር ደረጃ ተግባራዊ የሚደረገዉን የልምድ ልውውጥ ማስፈጸሚያ እቅድ ማዘጋጀት፣
 በፌዴራል አስተባባሪነት በክልሎች መካከል የልምድ ልዉዉጥ መድረክ በማዘጋጀት ተግባራዊ ማድረግ ፣
 የክልል እና ከተማ አስተዳደር አመራሮች እና የስራ ሂደት መሪዎች የዉጭ አገር ልምድ እንዲያገኙ ማድረግ፣
 የልምድ ልዉዉጥ መድረኩን ፋይዳ መገምገም ፣
የግቡ ውጤት፡- የማስፈፀምና የመፈፀም አቅማቸው ያደገ አመራርና ፈፃሚ

ግብ 8:- ዘመናዊ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሥርዓትን ማሻሻል ½


 የኔትዎርክ ዝርጋታና የሶፍትዌር ግንባታን ማከናወን፣
 የኤጀንሲዉ ዳታ ቤዝ የተገልጋይ ፍላጎት መሰረት በማድረግ ማዘጋጀት ፣
 የሶፍትዌር ኢንተርፌስ አፕሊኬሽን መገንባት ፣

37
 በኤጀንሲ ደረጃ የተዘጋጀዉን ድረ-ገጽ በየጊዜዉ እየተከታተሉ የተሟላ ይዘት እንዲኖረዉ ማድረግ ፣
 በፌዴራል እና በክልል ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ ደረጃ ኔትዎርክ መዘርጋት፣
 የኤጀንሲዉን ሰርቨር ለስራ ዝግጁ ማድረግ ፣
 የኢ-ለርኒንግ ስልጠና ለመስጠት የሚያስችል የዌብሳይት ፔጅ ማዘጋጀት ፣
 በኤጀንሲ ደረጃ የዳታ ሪከቨሪ ክፍል ማዘጋጀት ፣

 የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ስትራቴጂክ ሰነድ ማዘጋጀት፣


 የወሳኝ ኩነት ምዘገባ አይቲ ስትራቴጅ ለማዘጋጀት የሚያስችል የጨረታ ሰነድ ማዘጋጀት፣
 የአይቲ ስትራቴጅዉን ለማዘጋጀት የቀረቡ ተወዳዳሪ ድርጅቶችን ሰነድ ቴክኒካዊ ግምገማ ማድረግ፣

 የወሳኝ ኩነት ምዝገባ የአይቲ ስትራቴጅ ዝግጅት ጥናት ማካሄድ፣

የግቡ ዉጤት:- የተሻሻለ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሥርዓት

ግብ 9 ቅንጅታዊ የአሰራር ሥርዓትን ማሻሻል ½

 ተቋማት ጋር የጋራ መግባቢያ ሰነድ ማዘጋጀትና ወደ ስራ ማስገባት፣

 ከሃይማኖት ተቋማት፣ ከጠቅላይ ፍ/ቤት ፣ ከትም/ት ሚ/ር ፣ ከሴቶችና ህ/ጉ/ ሚ/ር ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችል
መግባቢያ ሰነድ ማዘጋጀት፣

 የተዘጋጀዉን የጋራ መግባቢያ ሰነድ የጋራ በማድረግ መፈራረም፣

 የተዘጋጀዉን የጋራ መግባቢያ ሰነድ አፈጻጸሙን መከታተልና መገምገም፣

 ከተባባሪ አካላት ጋር የምክክር መድረክ ማዘጋጀት፣


 ከተባባሪ አካላት ጋር የምክክር መድረክ ማስፈጸሚያ መርሃ ግብር እቅድ ማዘጋጀት፣

 ከተባባሪ አካላት ጋር የጋራ ምክክር መድረክ ማድረግ፣

 የተባባሪ አካላትን የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ስርአቱን በመደገፍ ረገድ የነበራቸዉን ሚና መገምገም ፣

 ኤጀንሲዉን በቴክኒካል ጉዳዮች ዙሪያ የሚያማክር የቴክኒክ ቡድን ማቋቋም፣

 ኤጀንሲዉን በቴክኒካል ጉዳዮች ዙሪያ የሚያማክር ከባለድርሻና ተባባሪ አካላት የተዉጣጣ የቴክኒክ ቡድን ማቋቋም፣

 የቴክኒክ ቡድኑ የጋራ ማስፈጸሚ እቅድ እንዲያዘጋጅ ማድረግ፣

 ለቴክኒካል ቡድኑ ስልጠና መስጠት፣

 የቴክኒክ ቡድኑ በእቅዱ መሰረት በየወሩ እየተገናኘ የጋራ ምክክር ማድረግ፣

 የቴክኒክ ቡድኑ በጋራ ያከናወናቸዉን ጉዳዮች ለኤጀንሲዉ በየጊዜዉ በሪፖርት እንዲያቀርብ ማድረግ፣

38
 በሥራ ላይ ያሉ ቅንጅታዊ አሠራሮችን አፈጻጸም መገምገም፣

 ከጤና ዘርፍ ጋር የተጀመረዉ ቅንጅታዊ ስራ ያለበትን የአፈጻጸም ደረጃ መገምገም፣

 ከማእከላዊ ስታትስቲስ ጋር የተጀመረዉ ቅንጅታዊ ስራ ያለበትን የአፈጻጸም ደረጃ መገምገም ፣

የግቡ ዉጤት:- የተሻሻለ ቅንጅታዊ አሰራር

ግብ 10: የህብረተሰቡንና ባለድርሻ አካላት ግንዛቤ ማሳደግ፣

 የኤሌክትሮኒክስ ሚዲያ በመጠቀም ህብረተሰቡ ስለ ወሳኝ ኩነቶች ግንዛቤ እንዲኖረዉ ማድረግ፣


 በወሳኝ ኩነት ምዝገባ አስፈላጊነትና ጥቅም ዙሪያ በ 5 ቋንቋ የሬዲዮና ቴሌቭዥን ስፖት ማዘጋጀት፣

 የተዘጋጁ ስፖቶችን በሬዲዎና ቴሌቭዥን ማስተላለፍ፣


 በወሳኝ ኩነት ምዝገባ ዙሪያ በሬዲዮ እና በቴሌቪዥን የሚተላለፉ ፕሮግራሞችን ማዘጋጀት፣
 በወሳኝ ኩነት ምዝገባ ዙሪያ ህብረተሰቡ በቀጥታ የሚሳተፍባቸዉ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ፕሮግራሞችን
ማዘጋጀትና ማስተላለፍ፣
 በወሳኝ ኩነት ምዝገባ ዙሪያ የችሎት ፕሮግራም ማስተላለፍ፣

 ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ዙሪያ ዶክመንተሪ ፊልም ማዘጋጀትና ማስተላለፍ፣

 በኤጀንሲው ድረ-ገፅ እና ማህበራዊ ሚዲያ ላይ አስፈላጊ መረጃዎችን በመጫን ኤጀንሲዉን ማስተዋወቅ ፣

 የህትመት ውጤቶችን በመጠቀም ህብረተሰቡ ስለ ወሳኝ ኩነቶች ግንዛቤ እንዲኖረዉ ማድረግ፣


 ኤጀንሲዉን የሚያስተዋዉቅ የቢል ቦርድ ህትመት በማዘጋጀት በግልጽ በሚታይ ቦታ እንዲቀመጥ ማድረግ

 የተለያዩ ትምህርታዊ መልዕክቶች የያዙ መጽሄቶችን ማሳተም ፣

 የተለያዩ መልዕክቶች የያዙ ሮል ባነሮችና ከለዉጥ ስራ ጋር ተያያዥ የሆኑ መልእክቶችን የሚያስተላልፉ


ህትመቶችን ማሳተም ፣
 ኤጀንሲዉን ለማስተዋወቅ የሚያስችል የጋዜጣ አምድ በመግዛት የተለያዩ ትምህርታዊ መልዕክቶች ማስተላለፍ ፣

 በወሳኝ ኩነት ምዝገባ ዙሪያ ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ግንዛቤ መፍጠር ፣


 በፌዴራል ፣ በክልል እና በከተማ አስተዳደር ደረጃ ለሚገኙ የሴትና ወጣት አደረጃጀት አመራሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ
መድረክ ማዘጋጀት፣
 ለትም/ት ሚ/ር ፣ ለሴቶች ህ/ ጉዳይ ሚ/ር ፣ ለሃይማኖት ተቋማት እና ለፍትህ አካላት የግንዛቤ
ማስጨበጫ መድረክ ማዘጋጀት ፣
 ለግል ጤና ተቋማት እና የጤና ማህበራት የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ማዘጋጀት፣

39
 በወሳኝ ኩነት ምዝገባ ጽንሰ ሃሳብ እና አስፈላጊነት ዙሪያ ለክልል እና ከተማ አስተዳደር ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ምክር
ቤት/ ቦርድ አባላት ግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ማዘጋጀት፣
 በወረዳ ደረጃ ለሚገኙ አስተዳዳሪዎች ፣ አደረጃጀት ፣ የፍትህ ጽ /ቤት እና የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ጽ /ቤት ሃላፊዎች
በወሳኝ ኩነት ምዝገባ እና አተገባበር ዙሪያ ግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ ማዘጋጀት፣
 በክልል እና በከተማ አስተዳደር ደረጃ ለሚገኙ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በወሳኝ ኩነት ምዝገባ ዙሪያ ግንዛቤ
መፍጠሪያ መድረክ ማዘጋጀት፣

የግቡ ውጤት፡- ግንዛቤው ያደገ ህብረተሰብ፣ የባለድርሻና የተባባሪ አካላት

ግብ 11 :- የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ጥራትና ሽፋንን ማሳደግ፣

 የወሳኝ ኩነት ምዝገባ መሳሪያዎችን ማዘጋጀት፣

 ለአራቱ የፌዴራል መዝጋቢ ተቋማት የሚያገለግል የክብር መዝገብ ማዘጋጀት፣


 ለአራቱ የፌዴራል መዝጋቢ ተቋማት የሚያገለግል የምስክር ወረቀት ማዘጋጀት፣
 ለክልሎች የጉዲፈቻ ምዝገባ ለማከናወን የሚያስችል የክብር መዝገብ እና የምስክር ወረቀት ማዘጋጀት፣
 ለክልሎች እና ለከተማ አስተዳደር የሚያገለግል የምዝገባ አፈጻጸም መመሪያ እንዲሻሻል ማድረግ ፣

 ለክልሎች እና ለ 4 ቱ ፌዴራል መዝጋቢ ተቋማት የሚያገለግል የምዝገባ አፈጻጸም መመሪያ ማሳተም ፣

 የፌዴራል መዝጋቢ ተቋማት የክፍያ ደንብ ማዘጋጀት፣


 የፌዴራል መዝጋቢ ተቋማት ምዝገባ እንዲጀምሩ ማድረግ ፣
 የስደተኞች እና ከስደት ተመላሽ ጉዳይ አስተዳደር የወሳኝ ኩነት ምዝገባ እንዲጀምር ማድረግ፣
 የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የወሳኝ ኩነት ምዝገባ እንዲጀምር ማድረግ፣
 የመከላካያ ሚኒስቴር የወሳኝ ኩነት ምዝገባ እንዲጀምር ማድረግ፣
 የኢትዮጵያ መርከቦች እና ሎጅሰቲክ አገልግለት ድርጅት የወሳኝ ኩነት ምዝገባ እንዲጀምር ማድረግ፣
 የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ጥራትና ሽፋን ያለበትን ደረጃ መለካት፣

 የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ጥራትና ሽፋን መለኪያ ስታንዳርድ ማዘጋጀት፣

 አገራዊ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ የጥራትና ሽፋን አመልካቾችን መቅረጽ፣

 በተዘጋጁ አገራዊ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ የጥራትና ሽፋን አመልካቾች ላይ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር
የጋራ ስምምነት መፍጠር፣
 በተዘጋጁ ስታንዳርዶችና አመልካቾች መሠረት የወሳኝ ኩነት መረጃ ምዝገባ ጥራትና ሽፋንን መለካት፣

 የወሳኝ ኩነት መረጃ ምዝገባ ጥራትና ሽፋን የደረሰበትን ደረጃ አስመልክቶ ለመዝጋቢ አካላት ዉጤቱን
መግለጽ ፣
 በወሳኝ ኩነት ምዝገባ አተገባበር ዙሪያ ጥናት ማካሄድ፣
 በወሳኝ ኩነት ምዝገባ ትግበራ ዙሪያ የዳሰሳ ጥናት ማካሄድ ፣

 በአገር አቀፍ ደረጃ የወሳኝ ኩነት የመከሰት መጠን በተመለከተ ጥናት ማድረግ ፣

40
 በአፋር ፣ ትግራይና አማራ ክልሎች በቤት ዉስጥ የሚከሰት ልደትና ሞት ምዝገባን በተመለከተ ጥናት
ማድረግ፣
 በቤት ዉስጥ የሚከሰት ልደትና ሞት ጥናት መሰረት በማድረግ የአሰራር ማኑዋል ማዘጋጀት፣
 ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የወሳኝ ኩነት እንዲመዘግቡ ማድረግ፣
 ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የልደት ኩነት እንዲመዘግቡ ማድረግ፣

 ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የጋብቻ ኩነት እንዲመዘግቡ ማድረግ፣

 ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የፍች ኩነት እንዲመዘግቡ ማድረግ፣

 ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች የሞት ኩነት እንዲመዘግቡ ማድረግ፣


የግቡ ዉጤት፡- ጥራትና ሽፋኑ የተረጋገጠ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ፣

ግብ 12፡- የወሳኝ ኩነት መረጃ ቅብብሎሽ ፣አደረጃጀትና አቅርቦት ስርአትን ማሻሻል፣


 በፌዴራል ደረጃ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ መረጃዎችን የመቀበል ፣ የማደራጀት እና የማቅረብ ስራ መስራት፣
 የወሳኝ ኩነት መረጃዎችን በኤሌክትሮኒክስ ለመቀበል የሚያስችል ማኑዋል ማዘጋጀት፣

 ከክልል እና ከተማ አስተዳደር ጋር በመረጃ አላላክ አመታዊ መርሃ ግብር ዙሪያ የጋራ መግባባት ላይ መድረስ ፣

 ከክልል እና ከተማ አስተዳደር የሚላኩ መረጃዎችን ቆጥሮ መረከብ፣

 ከክልል እና ከተማ አስተዳደር የሚላኩ መረጃዎችን ማጥራት፣

 ከክልል እና ከተማ አስተዳደር የሚላኩ መረጃዎችን ወደ ዳታ ቤዝ ማስገባት ፣

 ከክልል እና ከተማ አስተዳደር የሚላኩ መረጃዎችን ማደራጀት፣

 ከክልል እና ከተማ አስተዳደር የሚላኩ መረጃዎችን ለመረጃ ተጠቃሚ ተቋማት መላክ ፣

የግቡ ውጤት ፡- የተሻሻለ የወሳኝ ኩነት መረጃ ቅብብሎሽ፣ አቅርቦትና አጠቃቀም

5.3 የፋይናንስ እይታ


ግብ 13:- የበጀት አቅምን ማሳደግ ፣
 ከተባባሪ አካላት የበጀት ድጋፍ ለማግኘት የሚያስችሉ ተግባራትን ማከናወን፣

 የኤጀንሲዉን የበጀት ክፍተት ለመለየት የሚያስችል የኢንቨስትመንት ፕላን ማዘጋጀት ፣

 በኤጀንሲ ደረጃ ያለዉን የበጀት ክፍተት ለመሙላት እንዲቻል ከተባባሪ አካላት ጋር ቀጣይነት ያለዉ ግንኙነት

መፍጠር፣

41
 በተባባሪ አካላት ተቀባይነት ያገኙ የበጀት ድጋፎችና ለማስፈጸም የሚያስችል ጋር የጋራ ስምምነት ሰነድ

ማዘጋጀት ½

 በኤጀንሲ ደረጃ ከተባባሪ አካላት የተገኙ የበጀት ድጋፎች ወደ ትግበራ እንዲገቡ ቀጣይነት ያለዉ ክትትል
ማድረግ ፣

 ከተባባሪ አካላት የተገኘዉ ድጋፍ ለታለመለት አላማ መዋሉን መገምገም፣

የግቡ ዉጤት:- ያደገ የበጀት ድጋፍ

ግብ 14:- የፋይናንስ አጠቃቀም ውጤታማነትን ማሳደግ ½

 ተቋማዊ የፋይናንስ ስርአቱ ከእቅድና በጀት ጋር ተጣጥሞ የሚፈጸም መሆኑን ማረጋገጥ፣

 የኤጀንሲዉ የስራ ሂደቶች የወጭ ፍላጎታቸዉን በየወሩ እንዲያሳዉቁ ማድረግ፣

 የወጭ አጠቃቀም ሪፖርት በየወሩ ለስራ ሂደቶች እና ለሚመለታቸዉ አካላት በየበጀት ኮዱ እና የወጭ ርእስ ማሳወቅ፣

 የተቋሙን የበጀት አፈፃፀም መገምገም፣

 የኤጀንሲዉን የፋይናስ ሪፖርት በማዘጋጀት ለሚመለከታዉ ተቋማት እንዲደርስ ማድረግ ፣

 በዋና ኦዲተር እና በዉስጥ ኦዲት ለሚሰጡ የኦዲት ግኝቶች ላይ ወቅታዊ ምላሽ መስጠት፣

 በኤጀንሲ ደረጃ በእቅድ የሚመራና ግልጽ የግዥ አሰራር መዘርጋት ፣


 በግዥ ሂደቱ ላይ የሚታዩ የአሰራር ክፍተቶችን መለየት፣

 በተለዩ የአሰራር ክፍተቶች ዙሪያ ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር የጋራ መግባባት መፍጠር ፣

 በኤጀንሲ ደረጃ ለሚፈጸሙ ግዥዎች መሰረታዊ ቅድመ ሁኔታዎች እንዲሟሉ ማድረግ፣

 የኤጀንሲዉ ግዥ በተቀመጠለት መርሃ ግብር መሰረት መፈጸም፣

 በተቋም ደረጃ የተከናወኑ ግዥዎችን አፈጻጸም በተመለከተ የተደራጀ ሪፖርት ለማኔጅመንት ማቅረብ ፣

 የኤጀንሲዉን የፋይናንስ፣ የንብረት፣ የበጀትና የሰዉ ሃይል ስምሪት አጠቃቀም ኦዲት ማድረግ፣
 የተቋሙን የሰዉ ሃይል ስምሪት ኦዲት ማድረግ ፣
 የተቋሙን የመደበኛና የፕሮጀክት ሂሳቦችን አጠቃቀም ኦዲት ማድረግ ፣
 የተቋሙን የንብረት አጠቃቀም ኦዲት ማድረግ ፣
 የተቋሙን የግዥ አፈፃፀም ኦዲት ማድረግ ፣
 ለኤጀንሲዉ አመራር እና የማኔጅመንት አባላት የምክር አገልግሎት መስጠት፣
 በተገኙ የኦዲት ግኝቶች ላይ ማስተካከያ መደረጉን ክትትል በማድረግ ለማኔጅመንት ሪፖርት
ማቅረብ ፣
የግቡ ውጤት፡- ውጤታማ የፋይናንስ አጠቃቀም ½

42
5.4 የተገልጋይ እይታ
ግብ 15፡- የአገልግሎት ተደራሽነትና ተጠቃሚነት ማሳደግ ½
 የአገልግሎት ተደራሽነትና ተጠቃሚነትን ለማሳደግ የሚያስችሉ ተግባራትን ማከናወን፣
 ተገልጋዩ የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ሰርትፍኬት እንዲወስድ ማድረግ፣

 የወሳኝ ኩነት ምዝገባ አገልግሎት መስጠት ያልጀመሩ የምዝገባ ጽ/ቤቶችን ምዝገባ እንዲጀምሩ ማድረግ፣

 በየደረጃዉ የሚሰጡ የአቅም ግንባታ ተግባራት የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት በሚያረጋግጥ ሁኔታ
እንዲፈጸም ማድረግ፣

 ተገልጋዮች ማወቅ የሚገባቸዉን መረጃዎች ማህበራዊ ድረ-ገጽ በመጠቀም ተደራሽ እንዲሆን ማድረግ ፣

 የአገልግሎት ተደራሽነትና ተጠቃሚነትን ለማወቅ የሚያስችል የዳሳሳ ጥናት ማድረግ፣

የግቡ ውጤት፡- ያደገ የአገልግሎት ተደራሽነትና ተጠቃሚነት

ግብ 16 :- የተገልጋይና ባለድርሻ አካላትን ዕርካታና አመኔታ ማሳደግ ፣

 የኤጀንሲዉን ተገልጋይና ባለድርሻ አካላት በኤጀንሲዉ እቅድ ዝግጅትና አፈጻጸም ሂደት ላይ ማሳተፍ ፣
 ተገልጋይና ባለድርሻ አካላት የኤጀንሲዉን እቅድ አፈጻጸም የሚገመግሙበትን መድረክ ማዘጋጀት፣

 በመድረኩ ላይ የተገኙ ግብአቶች ለይቶ በማደራጀት በኤጀንሲዉ እቅድ ዉስጥ ማካተት፣

 በመድረኩ የተሰጡ ግብአቶችን ተግባራዊ በማድረግ አፈጻጸሙን ለተገልጋይና ባለድርሻ አካላት በሪፖርት
ማሳወቅ፣

 አገልግሎት ለማግኘት ወደ ኤጀንሲዉ የሚመጡ ተገልጋዮችን በአግባቡ ማስተናገድ፣


 በኤጀንሲዉ የሚሰጡ አገልግሎቶችን ለማግኘት የሚያስችሉ ቅድመ ሁኔታዎችን መለየትና
ማሳወቅ፣
 አገልግሎት ለማግኘት ወደ ኤጀንሲዉ ለሚመጡ ተገልጋዮች ማረፊያ ማዘጋጀት፣
 የአገልግሎት አሰጣጥ ፕሮግራም በማዘጋጀት ለኤጀንሲዉ ተገልጋዩች ማሳወቅ፣
 በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ለሚነሱ የተገልጋይ ቅሬታዎች ምላሽ መስጠት፣
 የኤጀንሲዉ ተገልጋይ በአገልግሎት አሰጣጥ ባለመርካት የሚያቀርበዉን ቅሬታ መቀበል፣

 በተገልጋይ ለቀረቡ ቅሬታዎች ፈጣን ምላሽ መስጠት፣

 በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚነሱ ቅሬታዎችንና የቅሬታ ምንጮችን በመለየት መፍትሄ መስጠት፣

 የኤጀንሲዉ ተገልጋይና ባለድርሻ አካላት እርካታ መለካት፣


 የኤጀንሲዉ ተገልጋይ አስተያየት የሚሰጥበት መዝገብ ፣ ሳጥን ፣ ቅጽ ማዘጋጀት፣

43
 የተዘጋጁ የአስተያየት መስጫ መሳሪያዎችን በመጠቀም ተገልጋዩ አስተያየት እንዲሰጥ
ማድረግ፣
 የኤጀንሲዉን ተገልጋይና ባለድርሻ አካላት የእርካታ ደረጃ መለካት፣
የግቡ ዉጤት ፡- ያደገ የተገልጋይና ባለድርሻ አካላት ዕርካታና አመኔታ፣

ክፍል አምስት ፡- የክትትልና ድጋፍ ፣ሪፖርት ፣ግምገማ እና ግብረ መልስ ስርዓት


በኤጀንሲ ደረጃ በእቅድ የተያዙ ግቦች ዋና ዋና ተግባራት እና ዝርዝር ተግባራትን ዉጤታማ በሆነ ሁኔታ

ለመፈጸም እንዲቻል በየደረጃዉ የሚገኘዉ አመራርና ፈጻሚ አካል የመፈጸም አቅሙ በቀጣይነት

ለመገንባት የሚያስችል በእቅድ አፈጻጸም ላይ መሰረት ያደረገ ችግር ፈች የድጋፍና ክትትል ስርአት

በመዘርጋት ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል ::

በመሆኑም ኤጀንሲዉ የ 2010 በጀት አመት እቅዱን በስኬት ለማጠናቀቅ በዝግጅት ምእራፍ ፣ በተግባር

ምእራፍ እና በማጠቃለያ ምእራፍ ላይ በእቅድ ዝግጅት ፣ በድጋፍና ክትትል፣ በእቅድ አፈጻጸም

ግምገማ እና ግብረ መልስ ስርአቱን አጠናክሮ ለመፈጸም የሚያስችሉ ተግባራትን በመለየት እና

የሚፈጸሙበትን መርሃ ግብር በግልጽ ለማመላከት ጥረት ተደርጓል፡፡

5.1 በዝግጅት ምእራፍ


ኤጀንሲዉ በ 2010 በጀት አመት እቅድ በመፈጸም ረገድ በዝግጅት ምእራፍ በክልል ፣ በማኔጅመንት ፣

በስራ ሂደትና በቡድን ደረጃ ሊከናወኑ የሚገባቸዉ ተግባራት ከዚህ በታች ቀርበዋል፡፡

5.1.1 በክልል እና ከተማ አስተዳደር ደረጃ ፡-

 ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በ 2010 በጀት አመት በእቅድ የተያዙ ተግባራትን

በዉጤታማነት እንዲፈጽሙ ለማድረግ በዝግጅት ምእራፍ ወቅት የክልልና ከተማ አስተዳደር

አመራሮችና ባለሙያዎች ዝርዝር ኦረንቴሽን በመስጠት በእቅዱ ላይ የጋራ መግባባት

እንዲፈጥሩ የማድረግ ስራ ትኩረት ተሰጥቶት የሚሰራ ይሆናል፡፡

 በእቅድ ኦረንቴሽን መድረኩ ላይ የተገኙ ግብአቶችን በተደራጀ አግባብ በእቅዱ ዉስጥ

እንዲካተቱ በማድረግ እና እቅዱን በማዳበር ለክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች ፣ እንዲደርስ

የማድረግ ስራ ይሰራል፡፡

44
5.1.2 በማኔጅመንት ደረጃ ፡-

 የኤጀንሲዉ ማኔጅመንት አካል በ 2010 በእቅድ የተያዙ ተግባራትን ዉጤታማ ለማድረግ

እንዲቻል በዝግጅት ምእራፍ ወቅት የኤጀንሲዉን ዓመታዊ እቅድ እንዲዘጋጅ በማድረግ እና

በተዘጋጀዉ እቅድ ዙሪያ በየደረጃዉ የሚገኙ የኤጀንሲዉ አመራሮች እና ፈጻሚ አካላት ፣

የክልል እና ከተማ አስተዳደር አመራሮችና ባለሙያዎች እንዲሁም እቅዱን በመፈጸም ረገድ

ወሳኝ ድርሻ ላላቸዉ የኤጀንሲዉ ባለድርሻ አካላት ዝርዝር ኦረንቴሽን በመስጠት በእቅዱ ላይ

የጋራ መግባባት እንዲፈጥሩ የማድረግ ስራ ትኩረት ተሰጥቶት የሚሰራ ይሆናል፡፡

 በእቅድ ኦረንቴሽን መድረኩ ላይ የተገኙ ግብአቶችን በተደራጀ አግባብ በእቅዱ ዉስጥ

እንዲካተቱ በማድረግ እና እቅዱን በማዳበር በየደረጃዉ ለሚገኙ ክልሎች እና ከተማ

አስተዳደሮች ፣ የኤጀንሲዉ ዳይሬክቶሬቶች እና ባለድርሻ አካላት እንዲደርስ የማድረግ ስራ

ይሰራል፡፡

 ሌላዉ በዝግጅት ምእራፍ ወቅት ትኩረት የሚሰጠዉ ጉዳይ በእቅድ የተያዙ ተግባራት

አፈጻጸም የሚያሳይ ወቅታዊ ሪፖርት በየደረጃዉ ከሚገኙ አካላት እንዲደርስ በማድረግ

ተቋማዊ ሪፖርት የማዘጋጀት እና ለሚመለከታቸዉ አካላት በወቅቱ እንዲደርስ ማድረግ ነዉ፡፡

በዚህ መሰረት የኤጀንሲዉ ማኔጅመንት አካል ዳይሬክቶሬቶች የ 15 ቀን ፣ ወርሃዊ እና የሩብ

አመት ሪፖርታቸዉን የሚልኩበት ወጥ የሆነ የሪፖርት ፎርማት በማዘጋጀት እና

እንዲደርሳቸዉ በማድረግ 15 ቀን፣ ወሩና ሩብ አመቱ እንደተጠናቀቀ ለኤጀንሲዉ እንዲልኩ

በማድረግ የማድረግ ስራ በትኩረት የሚሰራ ይሆናል፡፡

5.1.3 በዳይሬክቶሬት ደረጃ ፡-

 የኤጀንሲዉ ዳይሬክቶሬቶች በተቋም ደረጃ በበጀት አመቱ በእቅድ የተያዙ ተግባራትን ዉጤታማ

ለማድረግ እንዲቻል በዝግጅት ምእራፍ ወቅት የዳይሬክቶሬቱን ዓመታዊ እቅድ እንዲዘጋጅ

በማድረግ እና በተዘጋጀዉ እቅድ ዙሪያ በየደረጃዉ የሚገኙ የዳይሬክቶሬቱ ፈጻሚ አካላት ዝርዝር

45
ኦረንቴሽን በመስጠት በእቅዱ ላይ የጋራ መግባባት እንዲፈጥሩ የማድረግ ስራ ትኩረት በመስጠት

የሚሰሩ ሲሆን በእቅድ ኦረንቴሽን መድረኩ ላይ የተገኙ ግብአቶችን በተደራጀ አግባብ በእቅዱ

ዉስጥ እንዲካተቱ በማድረግ እና እቅዱን በማዳበር ለኤጀንሲዉ እና በየደረጃዉ ለሚገኙ ቡድኖች

እና ፈጻሚ አካላት እንዲደርስ የማድረግ ስራ መስራት ይኖርባቸዋል፡፡

 በእቅድ አፈጻጸም ወቅት የነበሩ ጠንካራ አፈጻጸሞችን ፣ ደካማ አፈጻጸሞችን እና በአፈጻጸም ወቅት

ያጋጠሙ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን የሚያመላክት ዝርዝር ግብረ

መልስ በሁለት ቀናት ዉስጥ በማዘጋጀት ለለዉጥ ቡድኖች እና የ 1 ለ 5 አደረጃጀቶች እንዲደርስ

ያደርጋል፡፡

 ዳይሬክቶሬቶች በእቅድ የተያዙ ተግባራት አፈጻጸም የሚያሳይ ወቅታዊ ሪፖርት ከለዉጥ ቡድኖች

እና ከ 1 ለ 5 አደረጃጀቶች እንዲደርስ በማድረግ የዳይሬክቶሬቱን ሪፖርት በማዘጋጀት ለኤጀንሲዉ

15 ቀን፣ ወርና ሩብ አመቱ እንደተጠናቀቀ በ 3 ቀናት ዉስጥ ለኤጀንሲዉ እንዲልኩ የማድረግ ስራ

የሚሰራ ይሆናል፡፡

5.1.4 በቡድን ደረጃ ፣

 በዳይሬክቶሬት ደረጃ የሚገኙ ቡድኖች በስራ ሂደቱ በእቅድ የተያዙ ተግባራትን ለማሳካት

እንዲቻል በዝግጅት ምእራፍ ወቅት የቡድኑን እቅድ እንዲዘጋጅ በማድረግ እና በተዘጋጀዉ እቅድ

ዙሪያ ለቡድኑ ፈጻሚዎች ኦረንቴሽን በመስጠት በእቅዱ ላይ የጋራ መግባባት እንዲፈጥሩ

የማድረግ ስራ የሚሰራ ሲሆን በኦረንቴሽን መድረኩ ላይ የተገኙ ግብአቶችን በእቅዱ ዉስጥ

እንዲካተቱ በማድረግ እና እቅዱን በማዳበር ለዳይሬክቶሬቱ እንዲደርስ የማድረግ ስራ መስራት

ይኖርባቸዋል፡፡

 ቡድኑ በእቅድ አፈጻጸም ወቅት የነበሩ ጠንካራ አፈጻጸሞችን ፣ ደካማ አፈጻጸሞችን እና በአፈጻጸም

ወቅት ያጋጠሙ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን የሚያመላክት ግብረ-

መልስ በማዘጋጀት በአንድ ቀን ዉስጥ ለ 1 ለ 5 አደረጃጀቶች እንዲደርስ ያደርጋል፡፡

46
 ቡድኖች በእቅድ የተያዙ ተግባራት አፈጻጸም የሚያሳይ ወቅታዊ ሪፖርት ከ 1 ለ 5 አደረጃጀቶች

እንዲላክ በማድረግና ሪፖርት በማዘጋጀት ለዳይሬክቶሬቱ በየሳምንቱ እንዲልኩ የማድረግ ስራ

የሚሰራ ይሆናል፡፡

5.2 በተግባር ምእራፍ


ኤጀንሲዉ በ 2010 በጀት አመት በእቅድ የተያዙ ተግባራትን በመፈጸም ረገድ በተግባር ምእራፍ

በክልል፣ በማኔጅመንት ፣ በስራ ሂደት እና በቡድን ደረጃ የሚከናወኑ ተግባራት ከዚህ በታች ቀርበዋል፡፡

5.2.1 በክልል ደረጃ ፡-

 ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች በተግባር ምእራፍ ወቅት በእቅድ የተያዙ ተግባራትን

ዉጤታማ በሆነ ሁኔታ እንዲፈጽሙ ለማድረግ እንዲቻል በሚያቀርቡት ሪፖርት ላይ


በመመስረት በየሩብ አመቱ ድጋፍ የመስጠት እና በአፈጻጸም ወቅት ያጋጠሙ ችግሮችን ለይቶ

የመፍትሄ አቅጣጫ ያስቀምጣል፡፡

 በእቅድ አፈጻጸም ወቅት የነበሩ ጠንካራ አፈጻጸሞችን ፣ ደካማ አፈጻጸሞችን እና በአፈጻጸም

ወቅት ያጋጠሙ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን የሚያመላክት

ዝርዝር ግብረ መልስ በማዘጋጀት እንዲደርስ ይደርጋል፡፡

5.2.2 በማኔጅመንት ደረጃ ፡-

 የኤጀንሲዉ ማኔጅመንት አካል በተግባር ምእራፍ ወቅት በእቅድ የተያዙ ተግባራት ወሳኝ

በመሆናቸዉ የእቅዱን ዉጤታማነት ለማረጋገጥ አፈጻጸሙን ዳይሬክቶሬቶች በሚያቀርቡት


ሪፖርት ላይ በመመስረት ድጋፍ የመስጠት እና በአፈጻጸም ወቅት ያጋጠሙ ችግሮችን ለይቶ

የመፍትሄ አቅጣጫ ያስቀምጣል፡፡

47
 በእቅድ አፈጻጸም ወቅት የነበሩ ጠንካራ አፈጻጸሞችን ፣ ደካማ አፈጻጸሞችን እና በአፈጻጸም

ወቅት ያጋጠሙ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን የሚያመላክት

ዝርዝር ግብረ መልስ በማዘጋጀት ለኤጀንሲዉ ዳይሬክቶሬቶች እንዲደርስ ያደርጋል፡፡

5.2.3 በዳይሬክቶሬት ደረጃ ፡


 የኤጀንሲዉ ዳይሬክቶሬቶች የተግባር ምእራፍ ተግባራትን አፈጻጸም የለዉጥ ቡድን እና

የ 1 ለ 5 አደረጃጀቶች በሚያቀርቡት ሪፖርት ላይ በመመስረት ድጋፍ የመስጠት እና በአፈጻጸም


ወቅት ያጋጠሙ ችግሮችን ለይቶ የመፍትሄ አቅጣጫ ያስቀምጣል፡፡

 በእቅድ አፈጻጸም ወቅት የነበሩ ጠንካራ አፈጻጸሞችን ፣ ደካማ አፈጻጸሞችን እና በአፈጻጸም

ወቅት ያጋጠሙ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን የሚያመላክት

ዝርዝር ግብረ መልስ በሁለት ቀናት ዉስጥ በማዘጋጀት ለለዉጥ ቡድኖች እና የ 1 ለ 5

አደረጃጀቶች እንዲደርስ ያደርጋል፡፡

 ዳይሬክቶሬቶች በእቅድ የተያዙ ተግባራት አፈጻጸም የሚያሳይ ወቅታዊ ሪፖርት ከለዉጥ

ቡድኖች እና ከ 1 ለ 5 አደረጃጀቶች እንዲደርስ በማድረግ የዳይሬክቶሬቱን ሪፖርት በማዘጋጀት

ለኤጀንሲዉ 15 ቀን፣ ወርና ሩብ አመቱ እንደተጠናቀቀ በ 3 ቀናት ዉስጥ ለኤጀንሲዉ

እንዲልኩ የማድረግ ስራ የሚሰራ ይሆናል፡፡

5.2.4 በቡድን ደረጃ ፣

 ቡድኖች የተግባር ምእራፍ ተግባራትን አፈጻጸም የ 1 ለ 5 አደረጃጀቶች በሚያቀርቡት ሪፖርት


ላይ በመመስረት ድጋፍ የመስጠት እና በአፈጻጸም ወቅት ያጋጠሙ ችግሮችን ለይቶ የመፍትሄ

አቅጣጫ ያስቀምጣሉ፡፡

 ቡድኑ በእቅድ አፈጻጸም ወቅት የነበሩ ጠንካራ አፈጻጸሞችን ፣ ደካማ አፈጻጸሞችን እና

በአፈጻጸም ወቅት ያጋጠሙ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን

የሚያመላክት ግብረ-መልስ በማዘጋጀት በአንድ ቀን ዉስጥ ለ 1 ለ 5 አደረጃጀቶች እንዲደርስ

ያደርጋል፡፡

48
 ቡድኖች በእቅድ የተያዙ ተግባራት አፈጻጸም የሚያሳይ ወቅታዊ ሪፖርት ከ 1 ለ 5 አደረጃጀቶች

እንዲላክ በማድረግና ሪፖርት በማዘጋጀት ለዳይሬክቶሬቱ በየሳምንቱ እንዲልኩ የማድረግ

ስራ የሚሰራ ይሆናል፡፡

5.3 በማጠቃለያ ምእራፍ


ኤጀንሲዉ በ 2010 በጀት አመት በእቅድ የተያዙ ተግባራትን በመፈጸም ረገድ በማጠቃለያ ምእራፍ

በክልል፣ በማኔጅመንት ፣ በስራ ሂደት እና በቡድን ሊከናወኑ የሚገባቸዉ ተግባራት ከዚህ በታች

ቀርበዋል፡፡

5.3.1 በክልል ደረጃ ፡-

 ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በሚያቀርቡት ሪፖርት ላይ በመመስረት በየሩብ አመቱ


አፈጻጸማቸዉን በመገመገም በአፈጻጸም ወቅት ያጋጠሙ ችግሮችን ለይቶ የመፍትሄ አቅጣጫ

ያስቀምጣል፡፡

 በእቅድ አፈጻጸም ወቅት የነበሩ ጠንካራ አፈጻጸሞችን ፣ ደካማ አፈጻጸሞችን እና በአፈጻጸም

ወቅት ያጋጠሙ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን የሚያመላክት

ዝርዝር ግብረ መልስ የግምገማ መድረኮቹ በተጠናቀቁ በ 10 ቀናት ዉስጥ በማዘጋጀት

ለኤጀንሲዉ ዳይሬክቶሬቶች እንዲደርስ ያደርጋል፡፡

5.3.2 በማኔጅመንት ደረጃ ፡-

 የኤጀንሲዉ ማኔጅመንት አካል በማጠቃለያ ምእራፍ የተቋማዊ እቅዱን ዉጤታማነት

ለማረጋገጥ አፈጻጸሙን ዳይሬክቶሬቶች በሚያቀርቡት ሪፖርት ላይ በመመስረት በ 15 እና በወር


በማኔጅመንት ደረጃ በሩብ አመቱ መጨረሻ ላይ ደግሞ በአጠቃላይ ሰራተኛ ደረጃ በመገመገም

በአፈጻጸም ወቅት ያጋጠሙ ችግሮችን ለይቶ የመፍትሄ አቅጣጫ ያስቀምጣል፡፡

 በእቅድ አፈጻጸም ወቅት የነበሩ ጠንካራ አፈጻጸሞችን ፣ ደካማ አፈጻጸሞችን እና በአፈጻጸም

ወቅት ያጋጠሙ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን የሚያመላክት

ዝርዝር ግብረ መልስ የግምገማ መድረኮቹ በተጠናቀቁ በሶስት ቀናት ዉስጥ በማዘጋጀት

ለኤጀንሲዉ ዳይሬክቶሬቶች እንዲደርስ ያደርጋል፡፡


49
 በእቅድ የተያዙ ተግባራት አፈጻጸም የሚያሳይ ወቅታዊ ሪፖርት በማዘጋጀትና

ለሚመለከታቸዉ አካላት በወቅቱ እንዲደርስ በማድረግ ረገድ የኤጀንሲዉ ማኔጅመንት አካል

ዳይሬክቶሬቶች የ 15 ቀን ፣ ወርሃዊ እና የሩብ አመት ሪፖርታቸዉን የሚልኩበት ወጥ የሆነ

የሪፖርት ፎርማት በማዘጋጀት እና እንዲደርሳቸዉ በማድረግ 15 ቀን፣ ወሩና ሩብ አመቱ

እንደተጠናቀቀ ለኤጀንሲዉ እንዲልኩ የማድረግ ስራ በትኩረት የሚሰራ ይሆናል፡፡

 ማኔጅመንቱ ከዳይሬክቶሬቶች የተላከዉን ሪፖርት በማኔጅመንት ደረጃ በመገምገም እና

የኤጀንሲዉ ሪፖርት እንዲዘጋጅ በማድረግ ወሩና እና ሩብ አመቱ እንደተጠናቀቀ በ 5 ቀናት

ዉስጥ ለሚመለከታቸዉ አካላት ተቋማዊ ሪፖርቱ እንዲላክ ይደረጋል፡፡

5.3.3 በዳይሬክቶሬት ደረጃ ፡


 የኤጀንሲዉ ዳይሬክቶሬቶች በእቅድ የተያዙ ተግባራትን አፈጻጸም የለዉጥ ቡድን እና የ 1 ለ 5

አደረጃጀቶች በሚያቀርቡት ሪፖርት ላይ በመመስረት በሳምንት ፣ በ 15 ቀን ፣ በወር እና በሩብ


አመት በመገመገም በአፈጻጸም ወቅት ያጋጠሙ ችግሮችን ለይቶ የመፍትሄ አቅጣጫ

ያስቀምጣል፡፡

 በእቅድ አፈጻጸም ወቅት የነበሩ ጠንካራ አፈጻጸሞችን ፣ ደካማ አፈጻጸሞችን እና በአፈጻጸም

ወቅት ያጋጠሙ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን የሚያመላክት

ዝርዝር ግብረ መልስ የግምገማ መድረኮቹ በተጠናቀቁ በሁለት ቀናት ዉስጥ በማዘጋጀት ለለዉጥ

ቡድኖች እና የ 1 ለ 5 አደረጃጀቶች እንዲደርስ ያደርጋል፡፡

 ዳይሬክቶሬቶች በእቅድ የተያዙ ተግባራት አፈጻጸም የሚያሳይ ወቅታዊ ሪፖርት ከለዉጥ

ቡድኖች እና ከ 1 ለ 5 አደረጃጀቶች እንዲደርስ በማድረግ የዳይሬክቶሬቱን ሪፖርት በማዘጋጀት

ለኤጀንሲዉ 15 ቀን፣ ወርና ሩብ አመቱ እንደተጠናቀቀ በ 3 ቀናት ዉስጥ ለኤጀንሲዉ

እንዲልኩ የማድረግ ስራ የሚሰራ ይሆናል፡፡

5.3.4 በቡድን ደረጃ ፣

50
 ቡድኖች የእቅድ አፈጻጸማቸዉን የ 1 ለ 5 አደረጃጀቶች በሚያቀርቡት ሪፖርት ላይ በመመስረት

በየሳምንቱ በመገመገም በአፈጻጸም ወቅት ያጋጠሙ ችግሮችን ለይቶ የመፍትሄ አቅጣጫ

ያስቀምጣሉ፡፡

 ቡድኑ በእቅድ አፈጻጸም ወቅት የነበሩ ጠንካራ አፈጻጸሞችን ፣ ደካማ አፈጻጸሞችን እና

በአፈጻጸም ወቅት ያጋጠሙ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን

የሚያመላክት ግብረ-መልስ በማዘጋጀት ከግምገማ መድረኮቹ በኋላ በአንድ ቀን ዉስጥ ለ 1 ለ 5

አደረጃጀቶች እንዲደርስ ያደርጋል፡፡

 ቡድኖች በእቅድ የተያዙ ተግባራት አፈጻጸም የሚያሳይ ወቅታዊ ሪፖርት ከ 1 ለ 5 አደረጃጀቶች

እንዲላክ በማድረግና ሪፖርት በማዘጋጀት ለዳይሬክቶሬቱ በየሳምንቱ እንዲልኩ የማድረግ

ስራ የሚሰራ ይሆናል፡፡

ክፍል ስድስት፡- በአፈጻጸም ወቅት የሚያጋጥሙ ችግሮች፣ መፍትሔዎች እና


የቀጣይ አቅጣጫ
6.1 በአፈጻጸም ወቅት የሚያጋጥሙ ችግሮች
 ኤጀንሲዉ አዲስ የተቋቋመ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የለዉጥ ስራዎችን በመፈጸም ረገድ አመራሩና

ፈጻሚዉ የአመለካከት እና የክህሎት ችግር መኖር ½

 በእቅድ የተያዙ ተግባራትን በዉጤታማነት ለመፈጸም የሚያስችል ቀጣይነት ያለው የቅርብ

አመራር ለመስጠት በእቅድ ያልተያዙ ደራሽ ስራዎች መበራከት፣

 ከተቋሙ ተልእኮ ጋር ተያያ™ነት ያለዉ ባለሙያ በገበያ ላይ አለመኖር እና የተሻለ ልምድ ያላቸው

ባለሙያዎች ከተቋሙ መልቀቅ፣

 ኤጀንሲዉ ተልእኮዉን በብቃት እንዲወጣ ከማድረግ አንጻር የግብዓት አቅርቦት ማነቆ በተሟላ

ሁኔታ አለመፈታት፣

6.2 መፍትሄዎች
 የለዉጥ ስራዎችን ተግባራዊ ለማድረግ በአመለካከት ለውጥ ለማምጣት በዕቅድና ግምገማ ሪፖርት

ዝግጅት ትኩረት እንዲሰጠዉ ማድረግ እና የሁሉም አጀንዳ እንዲሆን ጥረት ማደረግ፣

51
 በእቅድ የተያዙ ተግባራትን እና በተለያየ ጊዜ ከእቅድ ዉጭ የሚመጡ ተግባራትን ከዋናዉ እቅድ ጋር

በማጣጣም የመፈጸም ስትራቴጅ ተግባራዊ ማድረግ ፣

 በተቋሙ ያሉ ክፍት የስራ መደቦችን በሰዉ ሃይል እንዲሟሉ ለማድረግ የሚታዩ ክፍተቶችን

በመገምገም የሰዉ ሃይል ለማሟላት የሚያሰችል ስልት ነድፎ ተግባራዊ ማድረግ ፣

 በተቋም ደረጃ ያለዉ የሰዉ ሃይል ለረ™ም ጊዜ እንዲያገለግል የስራ አካባቢዉ ምቹ እና ሳቢ እንዲሆን

ለማድረግ ጥረት የሚደረግ ይሆናል ½

 በቀጣይ ዓመት የግብዓት ችግር ለመፍታት በዋና ዋና የግብዓት ችግሮች መነሻ ጥናት በማድረግ

ለመፍታት በዕቅድ የተያዘ መሆኑ፣

6.3 የአፈጻጸም አቅጣጫ

በኤጀንሲ ደረጃ የታቀደው የዉጤት ተኮር እቅድ በሚፈለገው መልኩ ተፈፃሚ እንዲሆን ለማስቻል በየደረጃዉ

የሚገኘዉ አመራር እና ፈጻሚ አካል ግልጽ የአፈፃፀም አቅጣጫ በማስቀመጥ በተቀመጠለት አቅጣጫ መሰረት

እንዲመራ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት የ 2010 በጀት አመት የኤጀንሲው የውጤት ተኮር እቅድ

የአፈፃፀም አቅጣጫ እንደሚከተለው ቀርቧል::

 ኤጀንሲው በ 2010 በጀት አመት በእቅድ የተያዙ ግቦችን እና ተግባራትን ዉጤታማ በሆነ ሁኔታ ለመፈጸም

እንዲቻል እቅዱን በየደረጃዉ ለሚገኙ ፈጸሚ አካላት በማዉረድ ተግባራዊ እንዲያደርጓቸዉ የጋራ መግባባት

መፍጠር፣

 በኤጀንሲ ደረጃ በእቅድ የተያዙ ተግባራትን ዉጤታማ ለማድረግ በእቅድ የታዘዉ የውጤት ተኮር እቅድ

በተቀመጠው የአፈፃፀም ደረጃ ተግባራዊ እንዲደረግ በየደረጃዉ የሚገኘዉ አመራር ስራዎችን በየወቅቱ

እየገመገመ እና የአፈፃፀም አቅጣጫ እያስቀመጠ የውጤት ተኮር እቅዱ ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ ½

 በተቋም ደረጃ በእቅድ የተያዙ ግቦችን እና ተግባራትን ዉጤታማነት ለማረጋገጥ ተቋሙ ለእያንዳንዱ የስራ

ሂደት ፣ የስራ ሂደቶች ለቡድኖች ፣ ቡድኖች ለፈፃሚዎች ተከታታይነት ያለው እና በእቅድ አፈጻጸም ላይ

መሰረት ያደረገ የግብረ መልስ ስርዓት ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ ½

 ተቋማዊ የውጤት ተኮር እቅዱ ተግባራዊ ሲደረግ ከእቅድ ጀምሮ እስከ ምዝና ባለዉ ሂደት አጠቃላይ

ክፍተትን የለየ ½ ቀጣይነት ያለዉና ችግር ፈቺ የሆነ የድጋፍ አግባብን ተከትሎ ተግባራዊ እንዲሆን

ማድረግ ½

52
 በተቋም በስራ ሂደት እና በቡድን ደረጃ የተቀረጸዉ የውጤት ተኮር እቅድ በየደረጃዉ የሚገኘዉን ፈጻሚ

አካል በላቀ ደረጃ ተሳታፊ እንዲሆን በማድረግ የእቅዱን ዉጤታማነት ማረጋገጥ ½

 ተቋማዊ እቅዱን በመፈጸም ረገድ በተቋም ½ በሂደትና በፈጻሚ ደረጃ የሚታዩ የአፈጻጸም ጉድለቶችንና

በአፈጻጸም ወቅት የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመቅረፍ የሚያስችል የተቀናጀ እና የተናበበ የአሰራር መርህን

ተግባራዊ ማድረግ፣

 በተቋም ½ በስራ ሂደት ½ በቡድን እና በፈጻሚ ደረጃ በእቅድ የተያዙ ተግባራትን ዉጤታማነት ለማረጋገጥ

በውጤት ተኮር እቅድ መሰረት የእርስ በእርስ አቅም መገንቢያ ስልቶችን በላቀ የቡድንና የባለቤትነት መንፈስ

ተግባራዊ እንዲሆን ማድረግ ½

 ተቋማዊ የዉጤት ተኮር እቅዱን ስኬታማ ለማድረግ ከሁሉም ባለድርሻ እና አጋር አካላት ጠንካራ ትስስር

በመፍጠር ለውጤት ተኮር እቅዱ አስተዋጽኦ ስኬት የበኩላቸዉን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ማስቻል ½

53

You might also like