You are on page 1of 76

የከተማ መጠጥ ውኃና ፍሳሽ

አገልግሎት ጽ/ቤቶችን የሂሳብ


አያያዝ ስርዓት ለማጠናከር
የተዘጋጀ የስልጠና ማንዋል
ጥር/2015 ዓ.ም
መግቢያ
• በአማራ ብሄራዊ ክልዊ መንግስት የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎቶችን እንደገና
ለማደራጀት የወጣውን አዋጅ ማስፈጸሚያ ደንብ ቁጥር 94/2004 ዓ.ምን
ተከትሎ የወጡ የፋይናንስ ፣የንብረት ፣የግዥ እና ልዩልዩ ገቢ መሰብሰቢያ
መመሪያዋችን አጣምሮ የያዘ ዘመናዊ/ድርብ/ የሂሳብ አያያዝ ስርዐት በሁሉም
ውሃ አገልግሎቶች ተመሳሳይ አፈጻጸም እንዲኖር ለማስቻል የተዘጋጀ የስልጠና
ማንዋል ሲሆን ዋና አላመው የከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎቶችን የሂሳብ
አያያዝ እና የፋይናንስ አስተዳደር የዕለት ከዕለት ተግባር አጋዥ እንዲሆን በማሰብ
እና ይህን የሂሳብ አያያዝ ስርአት መተግበር የውስጥ ቁጥጥር ስርአትን ለማጠናከር
እና የበላይ አመራሮች የተቋሙን ወቅታዊ እንቅስቃሴ ሪፖርቶችን በማየት በቀላሉ
ገምግመው ውሳኔ እንዲያሳልፉ ለማድረግም ከፍተኛ ሚና የሚጫወት ይሆናል፡፡
ዓላማዉ
•የሂሳብ አያያዝ ስርዐቱን ዘመናዊ ለማድረግ፤
•የውስጥ ቁጥጥርን ለማጠናከር፤
•የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዐትን ለማሻሻል፤
•የተሟሉ ወቅታዊ የሂሳብ ሪፖርቶችን
ለማዘጋጀት፤
የገለጻ ትንታኔ
• የሂሳብ አያያዙን ለመተግበር የሚያስችሉ ሁኔታዋች
 አሰራሩን ለመተግበር አመች በሆነ መልኩ የአዋጅ እና የደንብ
ማሻሻያ ተደርጓል ፤
 የተሻሻለውን ደንብ ለማስፈጸም እና አሰራሩን ለመተግበር
የሚያስችሉ መመሪያዋች ቅጻቅጽ እና
መዛግብትን/ቮውቸሮችን/ አካተው ወጥተዋል፤
 የገቢ፣ግዥ፣ፋይናንስና ንብ/አስ የስራ ሂደት አደረጃጀት
ለደንበኞች አገልግሎት አሰጣጥ ምቹ ፣ፈጣን እና አስተማማኝ
እንዲሆን ተደርጓል፤
 የሂደቱ ሰራተኞች ዝርዝር ተግባር እና ሀላፊነት እስከ መወሰን
ስልጣን ከተጠያቂነት ጋር ተሰጥቷል፤
የሂሳብ መዝገብ አያያዝ / Book-Keeping /
•ማንኛውም ድርጅት የሂሳብ ልውውጦችን በሂሳብ
አያያዝና አሰራር ደንቦችና መመሪያዎች መሰረት አግባብ
ባላቸው ሰነዶችና መዛግብት ስርአት ባለው ሁኔታ
የሚመዘግብበትና የሂሳብ መረጃዎችንም የሚይዝበት
የአሰራር ጥበብ የሂሳብ መዝገብ አያያዝ ይባላል፡፡
•የሂሳብ መዝገብ አያያዝ ማለት በአጭሩ የሂሳብ
ክስተቶችን በሂሳብ ሰነዶችና መዝገቦች ላይ መመዝገብ
ማለት ነዉ፡፡
የሂሳብ አያያዝ /Accounting/
•የሂሳብ አያያዝ ማለት በማንኛውም የኢኮኖሚ ተቋም ውስጥ
የሚገኙትን የኢኮኖሚ መረጃዎች ለመመዝገብ፣ ለማብራራትና
ለተጠቃሚው ክፍል ለማስተላለፍ የሚያገለግል የንግድ ዓለም
ቋንቋ ነው፡፡ ስለሆነም የሂሳብ አያያዝ የሚያከናውናቸው
ተግባሮች ሰፊ በመሆናቸው አንድ ወጥ ትርጉም ለመስጠት
ቢያዳግትም የሂሳብ አያያዝን ጠቅለል ባለ መልኩ
እንደሚከተለው መተርጎም ይቻላል፡፡
• በሂሳብ መዝገብ አያያዝ የተከናወኑና የሚከናወኑ ተግባራት ወቅታዊና
አስተማማኝነት የማረጋገጥና የመቆጣጠር እንዲሁም የሂሳብ አያያዝ
ህጎች፣ ደንቦችና መመሪያዎች ተከትሎ የሂሳብ መረጃዎችን በማቀነባበር
የስራ እንቅስቃሴ ውጤት በትክክል የሚገልፁ የሂሳብ መግለጫዎችንና
ሪፖርቶችን የማዘጋጀት፣ የመተንተን፣ የመተርጎምና ለሚመለከታቸው
ክፍሎችም እንዲደርሱ የማድረግ ተግባራት የሚከናወንበት የሂሳብ
አሰራር ስርዓት የሂሳብ አያያዝ ወይም /Accounting/
ይባላል፡፡

• የሂሳብ አያያዝ (Accounting) የገበያ ልውውጥ


/ክስተቶች /የመመዝገብ፣
የመለየት፣የማቀናጀት፣የመተርጎም፣የመተንተና መረጃውን
ለሚያስፈልጋቸው አካላት ሪፖርት የማድረግ ሂደት ነው፡፡
• የሂሳብ አያያዝ አይነቶች
የሂሳብ አያያዝ አይነቶች ሁለት ሲሆኑ

1.በእጅ የሚሰራ የሂሳብ አያያዝ /manual


accounting/
2. በኮምፒተር /computerized
accounting / የሚሰራ የሂሳብ አያያዝ
ናቸው።
የሂሳብ አያያዝ ስርዓቶች/Methods of accounting
1) accounting is the language of business. Various
transactions are communicated through accounting.
there are many parties –owners, creditors ,
government ,employees etc .the accounting shows
areal & true position of the firm or the business.

2) Methods of accounting :

A. single entry/ ነጠላ የሂሳብ አሰራር ስርዓት/ : it is incomplete system


of recording business transaction. the business
organization maintains only cash book.

B. Double entry/ ጥምር የሂሳብ አሰራር ስርዓት : is an accounting


system that records the effects of transactions & other
events in at least two accounts with equal debits &
credits
Advantages of double entry system:

1. Scientific system

2. Complete record of transactions

3. A check on the accuracy of accounts

4. Ascertainment of profit or loss

5. Knowledge of the financial position of the business

6. Full details for purpose of control

7. Helps management in decision making

8. No scope for fraud


• Basis of accounting/የሂሳብ አያያዝ ስርዓት
1. ጥሬ ገንዘብን መሰረት ያደረገ/Cash basis /፡-ይህ የሂሳብ አያያዝ ስርአት የሂሳብ
እንቅስቃሴዋች በሙሉ ጥሬ ገንዘብ ላይ ብቻ የተመሰረቱ ናቸው ፡፡
2. አክሩዎል /accrual basis /:- ይህ የሂሳብ አያያዝ ስርዐት ጥሬ ገንዘብ
እና ጥሬ ገንዘብ ነክ ያልሆኑ የሂሳብ እንቅስቃሴዋችን አጣምሮ የያዘ ሂሳብ አያያዝ
ስርዐት ሲሆን ይህ የስልጠና ማንዋልም የተዘጋጀው በሚታወቁት የሂሳብ አያያዝ
መርሆች/GAAP/መሰረት ሲሆን የያዘው የሂሳብ አያያዝ ድርብ ሂሳብ
አመዘጋገብ ማለትም ጥሬ ገንዘብ እና ጥሬ ገንዘብ ነክ ያልሆኑ የሂሳብ
እንቅስቃሴዋችን ያጠቃለለ ነው ።
3. modified cash base accounting/ በጥሬ ገንዘብ እንቅስቃሴ ላይ
የተመሰረተ የተሻሻለ የሂሳብ አያያዝ
Cont….

ምሳሌ

•አቶ አወል ከX ድርጅት የ10000 ብር የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች ገዙና


5000 ብር ከፍለው ቀሪውን በ2 ወር ውስጥ ሊከፍሉ ተስማሙ ፡፡የአቶ
አወል መ/ቤት ሂሳባቸውን የሚይዙት ጥሬ ገንዘብን መሰረት አድርገው
ሲሆን ምዝገባቸውን አስቀምጡ?
Cont…..

1. Cash basis of accounting :a business recognizes


revenue when cash is received ,& expense when cash
is paid.
•ጥሬ ገንዘብን መሠረት ያደረገ የሂሣብ አያያዝ ስርዓት የጥሬ ገንዝብ እንቅስቃሴዎችን ብቻ
መሰረት አድርጎ የሚሰራ ሲሆን ጥሬ ገንዘብ ነክ ያልሆኑ የሂሳብ እንቅስቃሴዎችን አያካትትም
•ወጪ መጽደቅ (መመዝገብ) ያለበት ክፍያ ሲፈፀም እንዲሁም ገቢ መመዝገብ ያለበት ገንዘቡ
ገቢ ሲደረግ ነው፡፡ በዚህ ሂሳብ አያያዝ ዘዴ ተሰብሳቢ እና ተከፋይ ሂሳቦች አይኖሩም ፡፡
ማንኛውም ሂሳብ ምዝገባ የሚከናወነው (ዕውቅና የሚሰጠው) የጥሬ ገንዘብ እንቅስቃሴ ሲኖር
ብቻ መሆን እንዳለበት ያሳውቃል ፡፡

•በመሆኑም ለተከፋይና እና ለተሰብሳቢ እውቅና የለውም ፡፡


ምሳሌ

•አቶ አወል ከX ድርጅት የ10000 ብር የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች


ገዙና 5000 ብር ከፍለው ቀሪውን በ2 ወር ውስጥ ሊከፍሉ
ተስማሙ ፡፡የአቶ አወል መ/ቤት ሂሳባቸውን የሚይዙት ጥሬ
ገንዘብን መሰረት አድርገው ሲሆን ምዝገባቸውን አስቀምጡ
Cont…

ዝርዝር መግለጫ ዴቢትክሬዲት

 
የቢሮ መገልገያ ዕቃዎች 5000

 
ጥሬ ገንዘብ (ሳጥን/ባንክ ዩኒ) 5000
2. ጥሬ ገንዘብን መሰረት ያላደረገ /accrual base/
•ጥሬ ገንዘብ ስራ ላይ ባይውልም ( ክፍያ ባይፈፀም እና ገቢ ባይሰበሰብም) ስራዎች

በጥሬ ገንዘብ እንደተከናወኑ የሚቆጥር የሂሳብ አያያዝ ነው ፡

•በዚህ የሂሳብ አያያዝ ለተከፋይ እና ተሰብሳቢ ሂሳቦች ዕውቅና ይሰጣል ፡፡

•ክፍያሳይፈፀም ለሚገዛ ዕቃ ወጪ ተብሎ እንዲያዝ፤

•በዱቤ ለሚሸጥ ዕቃ እንደ ገቢ እንዲያዝ የሚያደርግ


Conti

ምሳሌ
አቶ አወል ከX ድርጅት የ10000 ብር የቢሮ
መገልገያ ዕቃዎች ገዙና 5000 ብር ከፍለው ቀሪውን
በ2 ወር ውስጥ ሊከፍሉ ተስማሙ ፡፡የአቶ አወል
መ/ቤት ሂሳባቸውን የሚይዙት ጥሬ ገንዘብን
መሰረት ያላደረገ ሲሆን ምዝገባቸውን አስቀምጡ?
Conti……

በአቶ አወል በኩል ሲመዘገብ


Cont…

3. በጥሬ ገንዘብ እንቅስቃሴ ላይ የተመሰረተና የተሻሻለ የጥንድ ሂሳብ


(modified cash base
•ጥሬ ገንዘብን መሠረት ያደረገ የተሻሻለ የሂሣብ አያያዝ ስርዓት የጥሬ ገንዝብ እንቅስቃሴዎችንና ጥሬ
ገንዘብ ነክ ያልሆኑ የሂሳብ እንቅስቃሴዎችን ያካትታል፡፡

•ጥሬ ገንዘብን መሠረት ያደረገ የተሻሻለ የሂሣብ አያያዝ በአብዛኛው በጥሬ ገንዘብ ላይ የተመሠረተ
ሲሆን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ጥሬ ገንዘብ ነክ ያልሆኑ የተወሰኑ የሂሣብ እቅስቃሴዎችን ዕውቅና
መስጠትን ያካትታል፣

1.ወጪ እውቅና የሚሰጠው፣

 የደመወዝ መክፈያ ዝርዝር ሲዘጋጅ፣

 ዕቃዎች ገቢ ሲሆኑና አገልግሎቱ ሲገኝ


Conti……

2. በዓይነት ዕርዳታ ሲገኝ

3. የውኃ ቢሮ በተዋረድ ያሉ የውኃ አገልግሎት ተቋማትን በመወከል ክፍያ


ሲፈጸምና ለተቋማቱ ምዝገባ እንዲያደርጉ ሲያሳውቅ፣

4. በ የውኃ አገልግሎት መ/ቤቶች መካከል የሚደረጉ የገንዘብ ዝውውሮች ያለ ጥሬ


ገንዘብ እንቅስቃሴ ዕውቅና መስጠት፣

5. የተሰብሳቢና የተከፋይ ሂሳቦች ያለ ጥሬ ገንዘብ እንቅስቃሴ እውቅና መስጠት፣


ዋና ዋና የሂሳብ አያያዝ መርሆዎች
1. የሂሳብ መዝገብ አያያዝ የሂሳብ የጊዜ ዑደት
• የፋይናንስ ለውጦች /እንቅስቃሴዎች/ ሪፖርት የሚደረጉት ለውስን ጊዜ ሆኖ
በሂሳብ መግለጫዎች አማካኝነት ይሆናል፡፡ይህም ማለት
ሪፖርቶች/መግለጫዎች/ የሚዘጋጁት በየወሩ ፣ በየ3 ወሩ እና በዓመቱ ሲሆን
የሂሳብ መግለጫዎች ማለት

– ትርፍ እና ኪሳራ መግለጫ/income statement/


– የካፒታል መግለጫ /capital statmenet/ እና
– የሀብት እዳ እና መግለጫ/balance sheet/ ወ.ዘ.ተ ናቸው፡፡
2. ግልፅነት ፡-
 የሂሳብ መግለጫዎች /financial statement /አስፈላጊ
መረጃዎችን ያካተቱ እና የሚመለከተው አካል የመ/ቤቱን የገንዘብ
አቋም እንዲረዳ የሚያደርጉ መሆን አለባቸው፡፡
3. ቀጣይነት/consistency/ ፡-
የሂሳብ መግለጫዎች/ financial statement /የሚዘጋጁት መ/ቤቱ
ቀጣይነት ይኖረዋል በሚል አስተሳሰብ ነው፡፡
4. ገቢና ወጭን ማገናዘብ /matching/ ፡-
 የተገኘ ገቢ ከወጣው ወጭ ጋር ተገናዝቦ በሂሳብ መዝገብ አያያዝ ይመዘገባል፡፡
5. አስተማማኝ የሰነድ ማስረጃ ፡-
እያንዳንዱ የሂሳብ እንቅስቃሴ ማስረጃ የሚሆን እና እንቅስቃሴው ለመካሄዱ
ማረጋገጫ አስተማማኝ የሰነድ ማስረጃ ነው፡፡
6. ገቢ መቼ እንደ ገቢ እንደሚቆጠር/revenue recognize/ ፡-
በስራ እንቅስቃሴ ወቅት ገቢ እንደ ገቢ የሚመዝገበው ገቢ ሲገባ እና ገቢ ባይገባም
አስቀድሞ አገልግሎት እንደተሰጡ ነው፡፡
• የሂሳብ አመዘጋገቡ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን
የሂሳብ እንቅስቃሴዋች በዋናነት ያካትታል

 በመረጃ የተደገፈ አገልግሎት እስከተሰጠ ድረስ ገንዘብ


ባይሰበሰበም እንደ ዘመኑ ገቢ እውቅና ተሰጥቶ ይመዘገባል፡፡

 መ/ቤቱ ወደፊት አገልግሎት ለመስጠት ዉል ገብቶ ከሌላ


ወገን ገንዘብ ሲቀበል እንደ ገቢ ወይም እንደ እዳ እውቅና
ተሰጥቶ ይመዘገባል።
 ንብረቶች በስጦታም ሆነ በግዥ ወደ መ/ቤቱ ገቢ ሲሆኑ እንደ
ሀብት ተመዝግበው አገልግሎት ላይ ሲውሉ በወጪ ይመዘገባሉ
እንዲሁም የተሸጡ ካሉ በማጠቃለያ ይመዘገባል ፡፡እንዲሁም
ለቋሚ እቃዋች የእርጅና ቅናሽ ማስተካከያ እየተደረገ በወጪ
ይመዘገባል ፡፡
 በመረጃ የተደገፈ አገልግሎት/ግዥ/ እስካገኘን ድረስ
ለተከፋይ ሂሳቦች እውቅና ተሰጥቶ ይመዘገባሉ።
 አገልግሎቱን ወደፊት ለማግኘት ለሌላ ወገን የተከፈሉ ቅድሚያ
ክፍያዋች አገልግሎት እስከሚሰጡ ድረስ እንደ ወጪ ወይም
እንደ ሀብት/ቅድሚያ ክፍያ/ እውቅና ተሰጥቶ ይመዘገባሉ
፡፡
• መሰረታዊ የሂብ አያያዝ መጠየቅ /Accounting
equation/

ሀብት = ጠቅላላ እዳ + የተጣራ ሀብት/ካፒታል/ ነው ።

• በዚህ ክስተት አመዘጋገብ ቢያንስ ሁለት እና ከዚያ


በላይ የሂሳብ መደቦች /accounts/ ሁልግዜ
ታሳቢ ይደረጋሉ ። ለዚያም ነው ሁለት እና ከዚያ በላይ
የሂሳብ መደቦችን ስለሚይዝ ድርብ የሂሳብ አያያዝ
ሊያስብለው የቻለው ።
የድርብ ሂሳብ አያያዝ ህግ
Increased Decreased Decreased Increased
with DEBITS with CREDITS with DEBITS with CREDITS

LIABILITIE
ASSETS & S,
REVENUE
EXPENSES S&
capital

Normal Balance is DEBIT Normal Balance is CREDIT


የሂሳብ መዛግብቶች እና አገልግሎታቸው
1.የገንዘብ መቀበያ ደረሰኝ/cash receipt
voucher/ ፡-ማለት ከስሙ መረዳት እንደሚቻለው
ገንዘብ ስንቀበል ብቻ የሚዘጋጅ ገቢ ለመሰብሰባችን ማስረጃ
የሚሆን ሰነድ ነው ።
2.የጥቃቅን ወጪ ማስመስከሪያ/petty cash
payment voucher/ ፡- ማለት በጥቃቅን ወጪ
መክፈል እስከሚቻለው ድረስ ላሉ ጥቃቅን ወጭዋችን ስንከፍል
የሚዘጋጅ እና በጥቃቅን ወጪማስመስከሪያ ለመክፈላችን
ማስረጃ የሚሆን ሰነድ ነው ።
የሂሳብ መዛግብቶች እና አገልግሎታቸው
3.የባንክ ወጪ ማስመስከሪያ/check payment
voucher/ ፡- ማለት በጥቃቅን ወጪ መክፈል ከሚቻለው በላይ
ለሆኑ ማንኛውም በቸክ የሚከፈሉ ክፍያዋችን ስንከፍል የሚዘጋጅ በቸክ
ለመክፈላችን ማስረጃ የሚሆን ሰነድ ነው።
4. የሂሳብ ምዝገባ ማዘዣ/journal voucher/ ፡- ማለት ከዚህ
በላይ በተብራሩት ሰነዶች/vouchrs/ሊሰሩ ያልቻሉ ወይም ጥሬ
ገንዘበብ ነክ ያልሆኑ ማንኛውንም የሂሳብ እንቅስቃሴዋች ምዝገባ
የምናከናውንበት የሂሳብ ምዝገባ ማዘዣ ሰነድ ሲሆን
• ለምሳሌ፡- የደመወዝ ወጭ ፣ ተከፋይ ሂሳቦች ፣ ተሰብሳቢ ሂሳቦች ፣የባንክ
ዝውውር ፣የወለድ ገቢ፣ከካዘና ወደ ባንክ ገቢ ሲሆን፣የሂሳብ ማስተካከያ
፣የሂሳብ መዝጊያ ወ.ዘ.ተ
• ማሳሰቢያ ፡- ሁሉም ሰነዶች/ቨውቸሮች/ ሲዘጋጁ በድርብ የሂሳብ አሰራር
መርህ መሰረት ሁኖ ደጋፊ ሰነዳቸው መሟላታቸው እና ማጽደቅ በሚገባው
አካል እየጸዸቁ መሆን አለበት ።
5. የሂሳብ እንቅስቃሴ መዝገብ/transaction rigister/ ፡ ማለት
ከዚህ በላይ ከተራ ቁጥር 1-4 በተቀመጡት ሰነዶች/vouchers/
የተሰሩ የሂሳብ እንቅስቃሴዋችን የምንመዘግብበት የመጀመሪያ መዝገብ ሲሆን
ወደ ሌጀሮች ለማወራረስ በመነሻነት ያገለግላል፡፡
6. የሂሳብ ሌጀር ካርድ/ledger card/ ፡-ማለት በሂሳብ እንቅስቃሴ
መዝገብ ውስጥ የሰፈረውን እያንዳንዱን የሂሳብ ልውውጥ በየ ሂሳብ አርዕስቱ
የሚቀመጥበት ነው፡፡
-petty cash payment voucher
-check payment voucher
-cash receipt voucher
-journal voucher

-Trial balance /የሂሳብ ሚዛን ሙከራ/ Ledger /


-Income statement /ትርፍና ኪሳራ መግለጫ/ የሂሳብ
ቋቶች/
-Capital statement /ካፒታል መግለጫ/
-Balance sheet /ሀብት እና ዕዳ መግለጫ/
የሂሳብ መዝገብ አያያዝ አጀማመር

የሂሳብ መዝገብ አያያዝን ተግባራዊ ለማድረግ የሂብ መግለጫዎችን ማዘጋጀት


ለአንድ መስሪያ ቤት መረጃዎች አስፈላጊዎች ናቸው፡፡በዚህ መሰረት አንድ ወሃና
ፍሳሽ አገ/ጽ/ቤት ወደ ድርብ የሂሳብ አያያዝ ስርዐት ለመግባት በመጀመሪያ
መነሻ ሀብት እና ዕዳ መግለጫ ማለትም ሀብትን ፣እዳን እና ካፒታሉን ማወቅ
የሚያስፈልገው ሲሆን በዚህም መሰረት ለስልጠናው አመች ይሆን ዘንድ የመነሻ
ሀብት እና እዳ መግለጫ አዘጋጅተን እያንዳንዱን የሂሳብ አያያዝ ከማብራሪያ ጋር
እስከ ሪፖርት አዘገጃጀት ድረስ እናያለን ።
የሀብት እና ዕዳ መግለጫ
ሀምሌ 1/2014 ዓ.ም
Asset
Current asset
•Petty cash...................................1250.00
•Cash at bank/CBE/.....................950000.00
•Cash at bank/ACSI/...................540000.00
•Staff debtor/አሊ/.......................9500.00
•Staff debtor/ሞገስ/......................10250.00
•Fitting.........................................250000.00
•Chemical......................................10000.00
•Stationery & office supply............32000.00
•Printing & duplication ..................19000.00
Fixed assets.
•Computer & software ...................84500.00
•Office furniture &equipment..........90000.00
Total assets................................................1,996,500.00
የሀብት እና ዕዳ መግለጫ
ሀምሌ 1/2014 ዓ.ም
Liabilities & capital
•Liability
•Income tax payable.............. 12150.00
•Pension contribution payable....... 13560.00
•Total liabilities......................25710.00
Capital
•የXY wsss, capital............. 1970790.00
•Total liabilities & capital................. 1996500.00
• ሀብት/asset/ ፡- ማለት ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያለው ጽንስ ሀሳብ ሁኖ ገቢ
በገንዘብ መልክ ወደ ውስጥ እንዲፈስ እና የወጭ ፍሰት እንዲቀንስ ለማስቻል
ያገለግላል።ምዝገባን በተመለከተ ሀብት ሲጨምር ዴቢት ሲቀንስ ደግሞ ክሬዲት
ይመዘገባል ።
• ሀብት ሁለት ክፍሎች ሲኖሩት እንደሚከተለው ተቀምጠዋል፡-
ከረት አሴት እና ፊክሲድ አሴት
1./current asset/ ፡-በአጭር ጊዜ ውስጥ በቀላሉ ወደ ገንዘብ የሚቀየሩ
ሀብቶች ሲሆኑ ከነዚህም ውስጥ ጥሬ ገንዘብ ፣ተሰብሳቢ ፣ኢንቨንተሪ፣ ቅድሚያ ክፍያ
ወ.ዘ.ተ..የመሳሰሉት የሚጠቀሱት ናቸው ።
1.1. ጥሬ ገንዘብ ፡-ወዲያው ስራ ላይ የሚ ውል ሀብት ውስጥ የመጀመሪያውን ደረጃ
ይይዛል ። ( ምሳሌ በካዝና ያለ እና በባንክ ያለ ገንዘብ
 ታህሳስ 1 የ የXY ከተማ ውሃ አገ/ጽቤት የሰኔ ወር 2007ዓ.ም የስልክ
ፍጆታብር 1000.00 እንዲከፍል ቢጠየቅ ጥሬ ገንዘቡ ሲከፈል አመዘጋገቡ በጥሬ
ገንዘብ መክፈያ ሰነድ እንደሚከተለው ይመዘገባል፡-PCPV-000
የስልክ ወጭ/……….1000.00
ጥቃቅን ክፍያዋች ገንዘብ .......1000.00

ታህሳስ 2 ለጥቃቅን ወጪዋች የሚሆን ጥሬ ገንዘብ ብር 4750.00 እንዲተካ


ሲጠየቅ የባንክ ወጪ ማስመስከሪያ በማዘጋጀት የሚከተለው የምዝገባ ሂደት ይከናወናል
፡-CPV-51

ጥቃቅን ክፍያ ገንዘብ ......4750.00


ባኔክ ያለ ገንዘብ………................4750.00

1.2. ተሰብሳቢዋች፡- የከተማው መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገ/ጽቤት ከሌላ ወገን


ገንዘብ እስከሚሰበስብ ድረስ ወይም ተገቢው ስራ ተከናውኖ ወደ ሀብትነት/ወጭነት/
እስከሚቀየር ድረስ በተሰብሳቢ አካውንት ስር ተመዝግቦ የሚቆይ ማለት ሲሆን ብዙ
አይነት ተሰብሳብዋችን እንደሚከተለው እናያለን ፡-
• ታህሳስ 3፡- ቢል ተሰብሳቢ….......75700.00
መኖሪያቤት....................32500.00
መኖሪያ ቤት ያልሆኑ…….....35200.00
ቆጣሪ ኪራይ ...................8000.00

• ታህሳስ 4 ከውሃ ፍጆታ የተሰበሰበ ብር 39000.00 ወደ ባንክ ገቢ ቢሆን በሂሳብ


ምዝገባ ማዘዣ ምዝገባው ይከናወናል ።JV-102
ባንክ ያለ ገንዘብ ...............39000.00
ቢል ተሰብሳብ.................39000.00
• ታህሳስ 5 ከውሃ ፍጆታ የተሰበሰበ ብር 10000.00 ወደ ካዘና ገቢ ቢሆን በጥሬ
ገንዘብ መቀበያ ደረሰኝ ምዝገባው ይከናወናል ።CRV-1001
ካዘና ያለ ገንዘብ ...........10000.00
ቢል ተሰብሳቢ ...............10000.00
• ታህሳስ 6 ጽ/ቤቱ ከውሃ ፍጆታ ተሰብስቦ ሀምሌ 5 ወደ ካዘና ገቢ የሆነው ብር
10000.00 ወደ ባንክ ገቢ በሚሆንበት ወቅት የሂሳብ ምዝገባው በሂሳብ ምዝገባ
ማዘዣ ይከናወናል። JV-103

ታህሳስ 6፡-ባንክ ያለ ገንዘብ ...........10000.00


ካዘና ያለ ገንዘብ……..............10000.00

• ታህሳስ 7 ከውሃ ፍጆታ የተሰበሰበ ብር 246400.00 ወደ አ.ብ.ቁ.ተ ገቢ ቢሆን


በሂሳብ ምዝገባ ማዘዣ ምዝገባው ይከናወናል ።JV-104

ሃምሌ7፡- አ.ብ.ቁ.ተ ያለ ገንዘብ......24640.00


ቢል ተሰብሳብ ………………........24640.00
•ሀምሌ 8 ለቢል ሽያጭ ሰራተኛ እንዲሸጥ ከተላለፈው ቢል ውስጥ በንባብ
ስህተት እና ሌሎች ችግሮች ምክኒያት መኖሪያ ቤት ብር 500.00 ፣መኖሪያ
ቤት ካልሆኑ ብር 1500.00 እና ቆጣሪ ኪራይ ብር 60.00 የያዘ ቢል
ለቢል ዝግጅት ተመላሽ ቢደረግ መጀመሪያ እንደ ገቢ ተመዝግቦ ስለነበረ የሂሳብ
ማስተካከያ መስራት አስፈላጊ ይሆናል ። ምዝገባውም በሂሳብ ምዝገባ ማዘዣ
የሚሰራ ይሆናል ፡-JV-105
ሀምሌ 8- መኖሪያ ቤት …….......500.00
መኖሪያ ቤት ያልሆኑ ..... 1500.00
ቆጣሪ ኪራይ ... ...........60.00
ቢል ተሰብሳቢ.............................2060.00
• የመ/ቤቱ ባልደረባ አቶ Moges የደመወዝ ብድር ብር 1250.00 ቢወስድ
የሂሳብ ምዝገባው በጥሬ ገንዘብ መክፈያ ሰነድ እንደሚከተለው ይመዘገባል፡- PCPV-
0002
የሰራተኛ ብድር.........1250.00
ጥቃቅን ክፍያዋች ገንዘብ …..........1250.00
• የመ/ቤቱ ባልደረባ የሆነው አቶ Moges ያለበትን የደመወዝ ብር 9500.00
ባንክ ገቢ አድርጎ እዳው እንዲሰረዝለት በሚጠይቅበት ወቅት የሂሳብ ምዝገባው በሂሳብ
ምዝገባ ማዘዣ የሚከናወን ይሆናል፡-JV-106
ባንክ ያለ ገንዘብ......................9500.00
ሰራተኛ ብድር………............................9500.00
• የመስሪያ ቤቱ ባልደረባ አቶ አበበ ፣ ትዕግሰት እና አለሙ ለስራ ወደ አ/አ ሲሄዱ የውሎ
አበል ለእያንዳዳቸው ብር 2000.00 ቅድሚያ ተከፈላቸው በዚህ ጊዜ የሂሳብ
ምዝገባው በባንክ ወጭ ማስመስከሪያ የሚከናወን ይሆናል፡-CPV-52 ,53 &54

• የሰራተኛ ብድር/አበበ/................2000.00
ባንክ ያለ ገንዘብ ………….......................2000.00

• የሰራተኛ ብድር/ትዕግስት/.................2000.00
ባንክ ያለ ገንዘብ……...............................2000.00

• የሰራተኛ ብድር/አለሙ/.................2000.00
ባንክ ያለ ገንዘብ………...........................2000.00
• ታህሳስ 12 አ/አ ለስራ የሄዱት ሰራተኞች ስራቸውን አጠናቀው ሲመለሱ አበላቸው
ሲወራረድ አቶ አበበ ከወሰደው አበል ተጨማሪ ብር 200.00፣ አቶ አለሙ ከወሰደው
ተመላሽ ብር 120.00 እና ወ/ሮ ትዕግስት ቀደው ብሰዱት ልክ አወራረዱ በዚሁ
መሰረት የሂሳብ ምዝገባው በሂሳብ ምዝገባ ማዘዣ፣በጥሬ ገንዘብ መክፈያ እና ገንዘብ
መቀበያ ደረሰኝ እንደሚከተለው የሚመዘገብ ይሆናል፡-JV-
107,108,&109,PCPV-0003 &CRV-1002
• አቶ አበበ
የጥቃቅን ወጭ ማስመስከሪያ
–ውሎ አበል ወጭ/…...........2200.00
ሰራተኛ ብድር/አበበ)……...................2000.00
ጥቃቅን ክፍያዋች ገንዘብ……..…...............200.00
አቶ አለሙ
በሂሳብ ምዝገባ ማዘዣ
ውሎ አበል ወጭ ………......................1880.00
ካዘና ያለ ገንንዘብ/አበልተመላሽ/...............120
ሰራተኛ ብድር/አለሙ/.................................2000.00
ወ/ሮ ትግስት
ሂሳብ ምዝገባ ማዘዣ
ውሎ አበል ወጭ..........2000.00
ሰራተኛ ብድር/ትዕግስት/.................2000.00
• ታህስስ13 የXY ከተማ ውሃ አገ/ጽቤት የህዳር ወር 2015 ዓ.ም የውሃ ማምረቻ
ፓምፖች የመብራት ፍጆታ ብር 7000.00 እንዲከፍል ቢጠየቅ ጥሬ ገንዘቡ ከባንክ
ሲወጣ አመዘጋገቡ በቸክ መክፈያ ሰነድ እንደሚከተለው ይመዘገባል፡-CPV-55
• ቅድሚያ ክፍያ/ ...............7000.00
ባንክ ያለ ገንዘብ……..................7000.00

• ታህሳስ 14-ክፍያው ተከናውኖ ክፍያ የተፈጸመበት ሰነድ ሲቀርብ በሂሳብ ምዝገባ ማዘዣ
በሚከተለው መልኩ ይመዘገባል፡-JV-110

• የመብራት ወጪ..............7000.00
ቅድሚያ ክፍያ....................7000.00
የጥቃቅን ክፍያዋች የመጀመሪያ ምስረታ ምዝገባ
/establishment of petty cash fund/

•ታህሳስ 15-የጥቃቅን ወጭ መጠን ፋይናንስ መመሪያው ላይ በተቀመጠው


መሰረት ሁኖ እንዴት ፒቲ ካሽ እንደሚመሰረት ለማየት ለጥቃቅን ግዥዋች
የሚሆን ፒቲ ካሽ ብር 15000.00 በግዥ ሰራተኛው ሲመሰረት
እንደሚከተለው ሲሆን ምዝገባው በባንክ ወጪ ማስመስከሪያ ይከናወናል ፡-
CPV-56

•ጥቃቅን ግዥ ክፍያ ገንዘብ......15000.00


ባንክ ያለ ገንዘብ……….............15000.00
• ታህሳስ 16 የXY ከተማ ውሃ አገ/ጽቤት የሰኔ ወር 2014 ዓ.ም የስልክ ፍጆታ ብር
1500.00፣ለፖስታ አመታዊ ኪራይ እና የመላኪያ አገልግሎት ብር 200.00 እና
ለቢሮ አገልግሎት የሚውል የመብራት ፍጆታ ብር 1500.00 እንዲከፍል ቢጠየቅ
ክፍያው በሚከፈልበት ወቅት በጥቃቅን ወጪ መክፈያ ሰነድ እንደሚከተለው
ይመዘገባል፡-PCPV-0004 & 0005

• የመብራት ወጭ..................1500.00
የግዥ ጥቃቅን ክፍያ ገንዘብ……….........1500.00

• የስልክ ወጭ …..................1500.00
• የፖስታ ወጭ …………...........200.00
የግዥ ጥቃቅን ክፍያ ገንዘብ..................1700.00
• ታህሳስ 17-ለመ/ቤቱ የሚያገለግሉ የተለያዩ መገጣጠሚያዋች እንዲገዙ ለግዥ
ሰራተኛው ብር 60000.00 ወጪ ተደርጎ ሲሰጠው የሂሳብ ምዝገባው በባንክ ወጪ
ማስመስከሪያ የሚከናወን ይሆናል ፡-CPV-57
• የግዥ ቅድሚያ ክፍያ ...........60000.00
ባንክ ያለ ገንዘብ …...................60000.00
• ታህሳስ 18-ከላይ እንዲገዛ ከታዘዛቸው መገጣጠሚያወች ውስጥ የ 50000.00
ገዝቶ ገቢ ቢያደርግ እና የተረፈውን ሲመልስ የሂሳብ ምዝገባው በሂሳብ ምዝገባ ማዘዣ
እንደሚከተለው ይመዘገባል ፡-JV-111
• መገጣጠሚያ ............50000.00
• ባንክ…………............10000.00
ግዥ ቅድሚያ ክፍያ ..............60000.00
• አቶ አወል የዱቤ ውሃ መስመር ሲያዘረጉ ከእቃ ሽያጪ 850.00 ከቴ/አገልግሎት
780.00 ከእ/አገልግሎት 255.00 ከተቀማጪ 200.00 ውል ካርድ
20.00 ግምት እና ፈቃድ 40.00 ማስቆፈሪያ 240.00 በዱቤ ለመክፈል ግዴታ
ሲገቡ የሂሳብ ምዝገባ በሂሳብ ምዝገባ ማዘዣ ይመዘገባል ፡-JV-112
• ዱቤ ተሰብሳቢ/አወል/........2385.0
• ግምትና ፈቃድ……………..……..........40.00
• እቃ ሽያጪ....................................850.00
• ከቴ/አገልግሎት...............................780.00
• ከእ/አገልግሎት................................255.0
• ተቀማጭ……...................................200.00
• ውል ካርድ. ………………….……….......20.00
• ማስቆፈሪያ.......................................240.00
• ዱቤ የወሰዱት አቶ አወል 500.00 ብር ገቢ ሲያደርጉ የሂሳብ ምዝገባው
በጥሬ ገንዘብ መቀበያ ይመዘገባል ፡-CRV-1003

• ካዘና ................500.00
• ዱቤ ተሰብሳቢ……..............500.00

• ቅድሚያ ክፍያ ፡- ማለት አገልግሎቱን ወደፊት ለመጠቀም


በማሰብ የሚከፈሉ ቅድሚያ ክፍያዋች ናቸው ። ለምሳሌ ያህል ፡-
የቤት ኪራይ ፣ የማስታወቂያ ፣ የኢንሹራንስ ወ.ዘ.ተ
• ታህሳስ መ/ቤቱ የአንድ አመት ቅድሚያ ክፍያ ማለትም ለመኪና ኢንሹራንስ
5400.00 ፣ለሞተር 2200.00 እና ለቤት ኪራይ 24000.00 ቅድሚያ
ሲከፍል እና ክፍያው በባንክ ዝውውር ቢፈፀም የሂሳብ ምዝገባው እንደሚከተለው
ይከናወናል ፡-JV-113

• የመኪና ኢንሹራንስ ቅድሚያ ክፍያ......5400.00


• የሞተር ኢንሹራንስ ቅድሚያ ክፍያ.....2200.00
• ለቢሮ ኪራይ ………....................24000.00
ባንክ …………..…………..........................31600.00
=1999.75 የአንድ ጠረጴዛ የአንድ አመት የእርጅና ቅናሽ ወጪ የሚኖረው
ሲሆን የ4 ጠረጴዛ የሶስት አመት የእርጅና ቅናሽ 23997 አመዘጋገብ እንደሚከተለው ይሆናል
፡-JV-115
የእርጅና ቅናሽ ወጭ -ጠረጴዛ/6003-1004/............23997
የተጠራቀመ እርጅና ቅናሽ-ጠረጴዛ /1504-0001/........233997
• ታህሳስ 26-ቋሚ ንብረቶችን ማስወገድ ፡-ቋሚ ንብረቶች በተለያየ ምክንያት ለመ/ቤቱ አገልግሎት
የማይሰጡበት ሁኔታ ይፈጠራል በዚህም ምክኒያት የተለያዩ የንብረት ማስወገጃ ዘዴዋችን ተጠቅመን
እናስወግዳቸዋለን ንብረቶች እንዴት መወገድ እንዳለባቸው ንብረት አስተዳደር መመሪያው ላይ ያለ
በመሆኑ ሲወገዱ የሂሳብ ምዝገባው እንዴት መከናወን እንዳለበት እናያለን ፡-
• ዋጋው 8000.00 የሆነ ጠረጴዛ እርጅና ተቀናንሶለት ብር 2000.75 ቀሪ ዋጋ ቢኖረው እና
በብልሽት ምክኒያት በመጣል እንዲወገድ ቢደረግ አመዘጋገቡ እንደሚከተለው ይሆናለ ፡-JV-116

• የተጠራቀመ እርጅና.........................5999.25
• እቃውን በማስወገድ የመጣ ኪሳራ .........2000.75
ጠረጴዛ ……...........................................8000.00
• ዋጋው 8000.00 የሆነ ጠረጴዛ እርጅና ተቀናንሶለት ብር 2000.75 ቀሪ ዋጋ ቢኖረው እና
1500.75 በመሸጥ እንዲወገድ ቢደረግ አመዘጋገቡ እንደሚከተለው ይሆናለ ፡-JV-117

• የተጠራቀመ እርጅና/.......................5999.25
• እቃውን በማስወገድ የመጣ ኪሳራ ........500.00
ባንክ ……………………………..……1500.75
ጠረጴዛ ……………….........................................8000.00
• ዋጋው 8000.00 የሆነ ጠረጴዛ እርጅና ተቀናንሶለት ብር 2000.75 ቀሪ ዋጋ ቢኖረው እና
2500.75 በመሸጥ እንዲወገድ ቢደረግ አመዘጋገቡ እንደሚከተለው ይሆናለ ፡-JV-118

• የተጠራቀመ እርጅና.........................5999.25
• ጥሬ ገንዘብ /bank.........................2500.75
እቃውን በማስወገድ የመጣ ትርፍ........................500.00
ጠረጴዛ ……...............................................8000.00

• ዋጋው 8000.00 የሆነ ጠረጴዛ እርጅና ተቀናንሶለት ብር 2000.75 ቀሪ ዋጋ ቢኖረው እና


2000.75 በመሸጥ እንዲወገድ ቢደረግ አመዘጋገቡ እንደሚከተለው ይሆናለ ፡-JV-119

• የተጠራቀመ እርጅና...........................5999.25
• ጥሬ ገንዘብ /bank.........................2000.75
ጠረጴዛ ..................................................8000.00
 23 ታህሳስ መ/ቤቱ ቢሮ ለማስገንባት ሻትን ጨምሮ 115000.00 ዉል ቢዋዋልና ቅድሚያ ክፍያ
30 ፐርሰንት ተከፍሎት ግንባታ ሲጀምር ምዝገባዉ እንደሚከተለዉ በባንክ ወጪ ማስመስከሪያ
ይመዘገባል ፡-
ቅድመ ግንባታ ክፍያ / ………………. 345000.00
ባንክ / …………………..……………………. 345000.00
 ታህሳስ በባለሙያ ሥራዉ ተረጋግጦ የመጀመሪያ ዙር 40 ፐርሰንት ክፍያ ሲፈጸም በባንክ ወጪ
ማስመስከሪያ ምዝገባዉ ይከናወናል ፡-
ኮንስትራክሸን ኢን ፕሮግረስ.…………….. 460000.00
40ፐርሰንት ቅድመ ግንባታ ክፍያ ……………..… 138000.00
5ፕርሰንት ሪቴንሽን …………………………..….. 23000.00
2ፐርሰንት ቅድመ ግብር …………………………. 8000.00
ባንክ ………………………………………………. 291000.00
ታህሳስ በባለሙያ ሥራዉ ተረጋግጦ የሁተኛ ዙር 40 ፐርሰንት ክፍያ ሲፈጸም በባንክ ወጪ ማስመስከሪያ ምዝገባዉ
ይከናወናል ፡-
ኮንስትራክሸን ኢን ፕሮግረስ /…………….. 460000.00
40ፐርሰንት ቅድመ ግንባታ ክፍያ ……………..… 138000.00
5ፕርሰንት ሪቴንሽን/ …………………………..….. 23000.00
2ፐርሰንት ቅድመ ግብር/ …………………………. 8000.00
ባንክ ………………………………………………. 291000.00
 ታህሳስ በባለሙያ ሥራዉ ተረጋግጦ ሦስተኛው ዙር 20 ፐርሰንት ክፍያ ሲፈጸም በባንክ ወጪ
ማስመስከሪያ ምዝገባዉ ይከናወናል ፡-
ኮንስትራክሸን ኢን ፕሮግረስ …………….. 230000.00
20ፐርሰንት ቅድመ ግንባታ ክፍያ ……….……………… 69000.00
5ፕርሰንት ሪቴንሽን …………………………..……….. 11500.00
2ፐርሰንት ቅድመ ግብር ……………….…………………. 4000.00
ባንክ ………………………………………..…………… 145500.00

 ታህሳስ የግንባታ ርክክብ ተፈጽሞ ምንም ችግር እንደሌለበት በባለሙያ ሲረጋገጥ እና 2.5ፕርሰንት እንዲለቀቅለት
ጠይቆ ሲፈቀድ እን ክፎያ ሲፈጸም በባንክ ወጪ ማስመስከሪያ ምዝገባዉ እንደሚከተለዉ ይመዘገባል ፡-

2.5ፕርሰንት ሪቴንሽን ……………….. 28750.00


ባንክ ………………………..…………………. 28750.00

ታህሳስ ዉሃ አግልግሎቱ ከከተማ አስተዳደር ለማስፋፊያ የሚሆን ገንዘብ 1500000.00 በርዳታ ሲሰጠዉ የሂሳብ ምዝገባ
ማዘዣዉ እንደሚከተለዉ ይከናወናል
ባንክ ……………….. 1500000.00
እርዳታ በጥሬ ገንዘብ ………………………. 1500000.00
• እዳ ፡- ማለት በሁለት ቦታ ተከፍሎ ሊታይ ይችላል ፡፡ ይህም ወቅታዊ
/የአጭር ጊዜ እዳና ለረጅም ጊዜ የሚቆይ እዳ ተብሎ በጊዜ ማዕቀፍ ሊከፈል
ይችላል ።
• ካፒታል ፡- ማለት የአመቱ ካፒታል/capital/ መጠን እና ከተጣራ
ወደ ካፒታል የዞረ የተጣራ ትርፍ/retained earinings/
ድምር ነው ።
• ገቢ ፡- ገቢን ስለመመዝገብ ፡- የከተማ መጠጥ ውሃና ፍሣሽ አገልግሎት
ገቢን እንደገቢ ለመመዝገብ ሁለት ቅድመ ሁኔታዎች መሟላት አለባቸው፡፡
– ሀ) አገልግሎት ለደንበኛ የተሰጠ መሆን ይኖርበታል::
– ለ) በተሰጠው የአገልግሎት መጠን ገንዘብ ገቢ መደረግ ይኖርበታሌ፡፡
– የከተማ መጠጥ ውሃና ፍሣሽ አገልግልት አክሩዋል የሂሣብ አያያዝ
ሥርአትን የሚከተሉ በመሆኑ ገቢ የሚመዘገበው ገቢው እንደተገኘ ወይም
ገንዘቡ ገቢ ባይደረግም አገልግሎቱ እንደተሰጠ ይሆናል ፡፡
በአክሩዋሌ አሠራር ወጪን ስለመመዝገብ
•በአክሩዋል የሂሣብ አያያዝ ሥርአት መሠረት ወጭ የሚመዘገበው ወጪ እንደተደረገ
እንጂ የግድ ወጪው በጥሬ ገንዘብ ሲወጣ ብቻ መሆን የለበትም ፡፡ በመሠረታዊ የሂሳብ
አያያዝ መርሆዎች መሠረት ገቢና ወጪን የማዛመድ መርህ ለመጠበቅ እንዲቻል አክሩ
ያደረገው ወጪ ምዝገባ በተመሳሳይ ወቅት አክሩ ካደረገው ገቢ ምዝገባ ጋር በተዘመደ መልኩ
ይሆናል፡፡ ይህም ማለት የማዛመድ መርሁ የሚገለጸው ከተመዘገበው ወጪ ጋር ተያይዞ
በተመሳሳይ ወቅት የተገኘውን ገቢ መመዝገብ ማለት ነው ።
የበጀት ሥርአት ፡-
•በጀት የፋይናንስን ሥራ ለማከናወን የሚያስችል ለተወሰነ ጊዜ የሚሠራ
አጠቃላይ የማኔጅመንት ዕቅድ ሲሆን የወጪ ግምትና የፋይናንስ ወጪ
አደራረግ ሥራዓትን ያካትታል፡፡ ይህ ማንዋል የከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ
አገሌግልት በጀትን በአመት አንድ ጊዜ እንደሚዘጋጅ ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡
ሆኖም የከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገሌግልት አስፈሊጊ ሆኖ ሲያገኝ
አመታዊ በጀቱን በሩብ አመት እና በወርሀዊ ዕቅድ ሊተነተን ይችላል፡፡
ወቅታዊ ሪፖርት ሲቀርብ ወርሀዊ ወይም የሩብ አመት ዕቅድ ከተመሳሳይ
ወቅት አፈፃፀም ጋር በማነፃፀር ልዩነቱ በተገቢው አምድ ይቀመጣል፡፡ በጀቱ
በከተማ ውሃ ቦርድና ማኔጅመንት ከታመነበት በማንኛውም ጊዜ ሊከለስ
ይችላል፡፡
 የበጀት ዝግጅት በዋናነት የዕቅድና ቁጥጥር መሣሪያ ነው፡፡ በጥንቃቄ
የተዘጋጀ በጀት የውሀ ማምረትን፣ የውሀ ሥርጭትን፣ ሽያጭንና ሌሎች
አስተዳደራዊ ሥራዎችን አቀናጅቶ ለመምራት ያገለግላል፡፡ የበጀት ዋና
ዋና አላማዎች፡-
 በከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ለታቀደለት ሥራዎች
ተገቢውን ገንዘብ ለማቅረብ፣
 የከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት የሚሠራቸውን ሥራዎች
በማቀናጀት ውጤታማ የሀብት አጠቃቀም እንዲኖር ለማስቻል፣
 ከዕቅድ ውጪ እንዳይሆን መቆጣጠር የሚስችል ኃላፊነትን
የሚወስንና የእርምት እርምጃ እንዱወሰድ ለማኔጅመንት ተገቢውን
መረጃ ለመሥጠት፡፡
የበጀት አይነቶች
•የከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ሁለት የበጀት አይነቶች ሲኖሩት እነርሱም፡-
1. መደበኛ በጀት (The Recurrent Budget)
•ይህ አይነቱ በጀት በአብዛኛው ለአንድ አመት ጊዜ የከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት መደበኛ
ሥራዎችን ለማከናወን እንዲያስችል የሚዘጋጅ ነው፡፡ ይህ በጀት ለደመወዝ፣ለቢሮ ውስጥ መገልገያ
ዕቃዎች ፣ ለውሀ ማጣሪያ ኬሚካሎች፣ ለውሀ ቆጣሪ መግዣ፣ ለቧንቧ እና መገጣጠሚያዎች ግዥ፣ ለጥገና
እና እድሳት ሥራዎች፣ ወዘተ ወጪ መሸፈኛ የሚያገለግል ነው፡፡

2.ካፒታል በጀት
•የከተማ መጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ለረጅም ጊዜ የታቀደ የካፒታል ማሳደጊያ መርሀ ግብርን ተከትሎ
የሚዘጋጅ በጀት ሲሆን የገንዘብ ምንጩንም መሠረት የሚያደርገው ለረጅም ጊዜ የካፒታል ፍላጎት
ለማሟላት ለኦፕሬሽን ገቢ፣ እርዳታ እና ሌሎች የካፒታል ማሻሻያ ፈንዶች ነው፡፡ በሌላ አገላለፅ ይህ
በጀት ለካፒታል እቃዎች ግዥ የሚውል ሲሆን የሚገዙት የካፒታል ዕቃዎችም ለከተማ መጠጥ ውሃና
ፍሳሽ አገልግሎት ለበርካታ አመታት የሚያገለግሉ መሆናቸውን በማመነን ነው፡፡ የካፒታል በጀት ለቢሮ
ግንባታ፣ ለተሽከርካሪዎችና ሞተር ሳይክልች ግዢ፣ ጀነሬተሮች፣ የውሀ ሥርጭት ሥርአት ማሻሻያዎችና
መስፋፊያዎች፣ ለመሣሪዎች ማሻሻያ ወይም ግዢ፣' ለቢሮ መገልገያ መሣሪያዎች ወዘተ ግዢ የሚውል
ነው፡፡
ታህሳስ የሰራተኞች ደመወዝ ለመክፈል ፔሮል በሚዘጋጅበት ወቅት ክፍያው እና
ክፍያው በባንክ ሲከፈል ምዝገባው በሂሳብ ምዝገባ ማዘዣ እንደሚከተለው
ይመዘገባል ;-JV-120
•ቋሚ ሰራተኛ ደመወዝ ……........73817.00
•ኩንትራት ሰራተኛ ደመወዝ …..…...500.00
•ትርፍ ሰዐት ክፍያ …………........3580.88
•የወንበር አበል ………….............420.00
•የካዘና መጠባበቂያ ………........... 80.00
•11% ጡረታ …………… ........8119.87
የተጠራቀመ ደመወዝ …………............55731.83
ስራ ግብር/....................................13218.93
18% ጡረታ…………………..............13287.06
አልማ ...........................................90.00
ደመወዝ ብድር …………...................4189.93
• የስራ ግብር ብር 25368.93 ፣18% ጡረታ ብር 26847.06 እና
ለአልማ ብር 90 ለሚመለከታቸው አካላት ክፍያ ቢፈጸም እና ክፍው ከባንክ
በዝውውር የተፈጸመ ቢሆን ምዝገባው በሂሳብ ምዝገባ ማዘዣ ይመዘገባል :-
JV-121

ስራ ግብር.............25368.93
18% ጡረታ ........26847.06
አልማ/......................90.00
ባንክ....................52305.99
የሂሳብ ማስተካከያ ማድረግ (Adjustments)
•የከተማ ውሃ አቅርቦት አገልግሎት የሂሳብ ሠራተኞች የውስጥ
ትራንዛክሽኖችን ለመመዝገብ ሪፖርት ማድረጊያ የመጨረሻዎቹ
ወቅቶች ላይ የሂሳብ ማስተካከያዎች ዘዴዎችን መጠቀም
አለባቸው፡፡ ማስተካከያ የሚደረግባቸው የሂሳብ መደቦች
አገልግሎት ሰጥተው ወደ ወጭ ያልተቀየሩ ዋጋዋችን
(unexpired cost)ገንዘብ ቢሰበሰብም አገልግሎት
ባለመሰጠቱ እንደ እዳ ተመዝግበው ያሉ (Unearned
Income) ሂሳቦች እና የተጠራቀሙ ሂሳቦች
(Accruals) ናቸው፡፡
ቅድሚያ የተሰበሰበ ገቢ
•ያልተመዘገበ ገቢ ወይም ወደፊት የተሸጋገረ ገቢ
(unearned or Differed Revenue) ማለት
አገልግሎቱ ሳይሰጥ ገንዘብን መቀበል ማለት ነው፡፡ በሌላ አባባል
አገልግሎት ወይም የዕቃ አቅርቦት ለወደፊት
ለማቅረብ/ለመስጠት ግዴታ ውስጥ በመግባት የተቀመጠውን
ክፍያ አስቀድሞ መቀበል ማለት ነው፡፡
• ታህሳስ 30,በጥቅም ላይ የዋለ ኬሎሪን ብር 5000.00፣ አላቂ
እቃዋች ብር 8000.000 እና ህትመት ደግሞ 1000.00
ማስተካከያ ሲደረግ የሂሳብ ምዝገባ ማዘዣ እንደሚከተለው
ይመዘገባል ፡-JV-122

• ክሎሪን ወጭ .......................5000.00
• አላቂ እቃ ..........................8000.00
• ህትመት ............................1000.00
• ክሎሪን ወጭ ……….........5000.00
• አላቂ እቃ......................8000.00
• ህትመት ……......................1000.00
• ታህሳስ ቅድሚያ ከተከፈሉ ክፍያዋች ውስጥ ለመኪና ኢንሹራንስ ብር
450.00 ለሞተር ኢንሹራንስ ብር 183.33 እና ለቢሮ ኪራይ
ብር 2000.00 አገልግሎት ስለሰጡ የማስተካከያ ሂሳብ ምዝገባ
እንደሚከተለው ይሆናል ፡-JV-123

• ለኢንሹራንስ ወጭ .......633.33
• ኪራይ ................2000.00
– የመኪና ኢንሹራንስ ቅድሚያ ክፍያ............450.00
– የሞተር ኢንሹራንስ ቅድሚያ ክፍያ ...........183.33
– ለቢሮ ኪራይ ………..............................2000.00
• ታህሳስ 30-ለቢል ሽያጭ ሰራተኛ ከመኖሪያ ቤት 40000.00 መኖሪያ ቤት ካልሆኑ
35000.00 ቆጣሪ ኪራይ 10000.00 የያዘ ቢል ለሽያጭ ሲተላለፍ የሂሳብ ምዝገባው
እንደሚከተለው ይሆናል ፡-JV-124

• ቢል ተሰብሳቢ ..........85000.00
– መኖሪያቤት.............................40000.00
– መኖሪያ ቤት ያልሆኑ...................35000.00
– ቆጣሪ ኪራይ…….......................10000.00
• ታህሳስ መ/ቤቱ አብቁተ ከተቀመጠ የቁጠባ ሂሳብ 2587.93 ወለድ ገቢ ሲያገኝ
የሂሳብ ምዝገባው እንደሚከተለው ይሆናል ፡-
ባንክ……………2587.93
ወለድ…..………………..2587.93
• የቁጥጥር ስርዐት
– የጥሬ ገንዘብ ቁጥጥር
– አዘጋጁን ፣ ተቀባዩን/ከፋይን/ እና ሂሳቡን የሚመዘግበውን
የተለያዩ ማድረግ
– ጥሬ ገንዘብ ቆጠራ ማካሄድ
– ባነከ ማስታረቂያ/bank reconcilation/ መስራት
• የንብረት ቁጥጥር
– በተጠቃሚዋች ያለ ቋሚ ንብረት መቆጣጠሪያ ካርደ ላይ
መመዝገብ ፣ኢንቨተሪዋችን በቢን ካርድ እና በስቶክ ካርድ
በማቀናነስ የንብረት ቆጠራ ማካሄድ ፡
የባንክ ሂሳብ ማስታረቂያ ዝጅት እና መነሻ ሰነዶች
• የባንክ ሂሳብ ማስታረቂያ ለማዘጋጀት መነሻ ሠነዶች
የሚሆኑት ከዚህ በታች የተመለከቱት ናቸው፡፡
ከባንክ የተቀበልነው የባንክ ሂሳብ መግለጫ፣
የሂሳብ እንቅስቃሴ መዝገብ/አጠቃላይ የሂሳብ ሌጀር
ካርድ፣
ከባንክ ሂሳብ መግለጫ ጋር አባሪ ተደርገው በሚደርሱት
ሠነዶች በጉርድ ቼክ ውስጥ ያለው ዝርዝር መረጃ፣
የባንክ ሂሰብ ማስታረቂያ በሚዘጋጅበት ወቅት የሚከናወኑ ቅደም ተከተሎች
- የባንክ ሂሳብ መግለጫ/Bank statement ከባንክ በምናገኝበት ወቅት
በባለፈው ወር ማስታረቂያ ወቅት ያልተመዘገቡ ሂሳቦች መመዝገባቸውን
ማጣራት፣
– የባንክ ሂሳብ መግለጫ ላይ የተመዘገበው መለያ ቁጥር በሂሳብ እንቅስቃሴ
መዝገብ ከተመዘገበው ጋር በመናበብ ስህተቶችና ከባንክ ገንዘብ ወጪ
ያልተደረገባቸው ቼኮች ካሉ መለየት፣
– የባንክ ሂሳብ መግለጫ ላይ ገቢ የተደረጉ ሂሳቦች በሂሳብ እንቅስቃሴ መዝገብ
ከተመዘገበው ጋር ልዩነት አለመኖሩን ማጣራት፣
– በባንክ የሂሳብ መግለጫም ሆነ በሂሳብ መዝገብ /ሌጀር ላይ ተመዝግበው
በሌላኛው ያልተመዘገቡ ሂሳቦችን መለየት፣
– የባንክ ማስታረቂያ ማዘጋጀት፣
የባንክ ሂሳብ ማስታረቂያ ቅፅ የሚከተለውን ይመስላል ፡-
የXY ከተማ ውሃ አገ/ጽቤት
Bank Recouncilation
For the month of ……/2015
የባንክ ከወጪ ቀሪ በባንክ መግለጫ መሰረት ………………………………………xxxx
ሲደመር ፡-ባንክ ገቢ ሁኖ በባንክ መግለጫ ያልታ………….xxxx
- ባንክ ስህተት…………………….……………xxxx
የባነከ ስህተት …………………………………………....... xxxx
ድምር………………………………………………………..xxxx
ሲቀነስ ፡-ባንክ ያልደረሱ ቸኮች
-ቸክ ቁጥር ……………………….xxxx
-ቸክ ቁጥር ………………………xxxxx
- ባንክ ስህተት…………………….……………xxxx
ድምር………………………………………………………..xxxx
የተስተካከለ የባንክ ሚዛን…………………………………………………..xxxxxx

የመዝገብ ከወጪ ቀሪ በሂሳብ ሌጀር መሰረት…………………………..xxxxx


ሲደመር ፡-በባንክ በኩል የተሰበሰበ ገቢ……………………..……….xxxxx
- ስህተት………………………….....………..….……..xxx
ድምር………………………..……....…………...…..xxxxxxx
ሲቀነስ ፡-የባንክ አገልግሎት…………………..xxxx
-ተመላሽ ቸክ…………………………xxxx
ስህተት…………....………..….……..xxx
የተስተካከለ የመዝገብ ሚዛን………………………………………………xxxxxxx
ለምሳሌ ፤-ስንሰራቸው ከቆዩት የሂሳብ እንቅ ስቃሴዋች ተነስተን
እንደሚከተለው እናያለን ፡-
የመ/ቤቱ ሂሳብ ባለሙያ የባንክ ሂሳብ ማስታረቂያ ለመስራት ሰነዶችን ሲመለከት
የባንክ መግለጫ /bank statement/ ከወጪ ቀሪ 314,910.08
የመ/ቤቱ ሌጀር ከወጪ ቀሪ 709,560.08 የሚያሳይ ሲሆን ሌጀር እና
የባንክ መግለጫውን ሲያገናዝባቸው የሚከተሉትን ክስተቶች አገኘ ፡-
-ባንክ ገቢ ሁኖ በባንክ መግለጫ ያልታየ 1,500,000.00
-ከቦኖ ማደያ ተሰብስቦ ገቢ የሆነ 5,000.00
-ብር 52,305.99 እንዲከፈል የታዘዘ ክፍያ በባንኩ ሲመዘገብ 53,205.99
ተብሎ መመዝገቡን
-ባንክ ያልደረሱ ቸኮች ድምር 1,101,250.00 መኖሩን አረጋገጠ ከዚያ
ማስታረቂያውን እና ማስተካከያ የሂሳብ ምዝገባውን እንደሚከተለው የሚሰራ
ይሆናል ፡፡
የXY ከተማ ውሃ አገ/ጽቤት
Bank Recouncilation
For the month of ……/2015

 የባንክ ከወጪ ቀሪ በባንክ መግለጫ መሰረት ………………………………………314,910.08


ሲደመር ፡-ባንክ ገቢ ሁኖ በባንክ መግለጫ ያልታየ…………1500,000.00
- ባንክ ስህተት……………………………………900.00
ድምር……………………………………………………………..…..1,815,810.08
ሲቀነስ ፡-ባንክ ያልደረሱ ቸኮች…………………..1101250.00
ድምር………………………………………………..……………………..….. 1,101,250.00

Adjusted/የተስተካከለ የባንክ ሚዛን………………….………………………………..714,560.08

 የመዝገብ ከወጪ ቀሪ በሂሳብ ሌጀር መሰረት…………………………………..709,560.08


ሲደመር ፡-በባንክ በኩል የተሰበሰበ ገቢ……………………..……….5,000.00

ድምር………………………..…………...…………...…..714,560.08
ሲቀነስ ፡-የባንክ አገልግሎት…………………..0
-ተመላሽ ቸክ…………………………0
Adjusted/የተስተካከለ የመዝገብ ሚዛን………………………………………………714,560.08
የማስተካከያ ምዝገባ
ባንክ..........................5000.00
ቦኖ ማደያ ገቢ……………………………5000.00
Thank You
Mohamed
Yimer

You might also like