You are on page 1of 4

የአርባምንጭ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ የፀረ-

ኤች/አ/ኤ/ሜ/ደ/ስ/ሂደት የ 2015 ዓ.ም


የ 1 ኛ ሩብ ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት
1. የ 2015 ዓ/ም የዕቅድ ዝግጅት በተመለከተ

የ 2015 ዓ/ም የስራ ሂደቱን የፊዚካል እቅድ እና የበጀት ፍላጎት እቅድ በማዘጋጀት በኮሌጁ

ለሚመለከታቸው የስራ ሂደቶችና ለክልል ትም/ቢሮ እንዲደርስ ተደርጓል፡፡

1.1 የእቅድ አፈጻጸም ሪፖርት በተመለከተ


በሩብ ዓመቱ የተከናወኑ ስራዎች ዝርዝር ሪፖርት በማዘጋጀት በኮሌጁ ለሚመለከታቸው የስራ
ሂደቶችና ለክልል ትም/ቢሮ እንዲደርስ ተደርጓል፡፡

1. የ 0.5%በፍቃደኝነት ፈንድ አገልግሎት መዋጮበተመለከተ

በኮሌጁ ከሚገኙ መምህራንና አስ/ር ሠራተኞች መካከል የፈንዱ ዓባል የሆኑ

 መምህራን፡- ወንድ 156 ሴት 20 ድምር 176


 አስ/ሠራተኛ፡- ወንድ 71 ሴት 63 ድምር 135
 አጠቃላይ ድምር፡- 310 ሲሆን ሁሉም በፈቃደኝነት የፈንዱ አባል ሆነው
ከደመወዛቸው በየወሩ 0.5 % ይቆረጣል፡፡

በ 2015 ዓ/ም ከሁሉም የፈንድ አባል ከሆኑ መምህራንና አስተዳደር ሰራተኞች ከደመወዛቸው
0.5% በ 1 ኛ ሩብ ዓመት ለመሰብሰብ የታቀደው ብር 35526.72 (ሠላሳ አምስት ሺህ አምስት
መቶ ሀያ ስድስት ብር ከሰባ ሁለት ሳንቲም) ሲሆን በሩብ ዓመቱ የተሰበሰበ ብር 35526.72
(ሠላሳ አምስት ሺህ አምስት መቶ ሀያ ስድስት ብር ከሰባ ሁለት ሳንቲም)ነው፡፡
በዓመቱ 0.5% ለመሰብሰብ የታቀደው ብር 142106.88 /አንድ መቶ አርባ ሁለት ሺ አንድ
መቶ ስድስት ብር ከሰማንያ ስምንት ሳንትም / ታቅዶ ከሐምሌ እስከ መስከረም 20115
ዓ/ም 0.5% ለፈንድ የተቆረጠው ገንዘብ መጠን ብር 35526.72 (ሠላሳ አምስት ሺህ አምስት
መቶ ሀያ ስድስት ብር ከሰባ ሁለት ሳንቲም) ሲሆን የተሰበሰበውን ገንዘብ የጋሞ ዞን ፋይ/ኢ/ል/
መምሪያ ለዚሁ በከፈተው አካውንት ገቢ እየተደረገ ይገኛል፡፡ ከሩብ ዓመቱ እቅድ አንጻር
አፈፃጸሙም በፐርሰንት ሲሰላ 100% ነው፡፡ ከዓመቱ ዕቅድ አንጻር አፈፃጸሙ በፐርሰንት ሲሰላ
100% ነው፡፡

3.የድጋፍና እንክብካቤ ተግባራትን በሚመለከት፡-

የኤች አይ ቪ ኤድስ ቫይረስ በደማቸው ውስጥ ያላቸውና ራሳቸውን በግልጽ


ያሳወቁ 7/ሰባት/ ሰራተኞች የፈንዱ ተጠቃሚ ሲሆኑ ለልጆቻቸው ለትምህርት ቤት
ምዝገባና ለትምህርት ግባዓት አገልግሎት እንዲሆንና ለአድስ አመት በዓል መዋያ
መደጎሚያ ድጋፍ የሚሆን በማነጅመንት በማስወሰን ለስሰባቱም ግለሰቦች
ለእያንዳንዳቸው ብር 2000 የተሰጣቸው ሲሆን በድምሩ 14000/አስራ አራት ሺህ
ብር/ ድጋፍ ተደርጎላቸዋል፡፡
በተጨማርም የኮሌጃችን ሠራተኛ የሆኑት አቶ ታመነ ታደለ ባቀረቡት የሕክምና
ማስረጃ መሠረት የ 0.5 ፈንድ ከሐምሌ ወር ጀምሮ ተጠቃም እንድሆኑ ተደርጓል፡፡

4. የመምህራን ፤አ/ሰራተኞች እና የከረምት ተማሪዎች የማህበረሰብ


ውይይት በሚመለከት፡-
የሰራተኞች መምህራንና የተማሪዎች ዉይይት ለማካሄድ እቅድ ቢያዝም ዉይይት
ለማድረግ በተከሰተው ኮብድ-19 ምክንያት መምራኑና ሠራተኛው በሙሉ በስራ
ላይ ባለመኖሩ የታቀዱ ተግባራት አልተፈ™ሙም፡፡
5. የኮንዶም ስርጭትን በተመለከተ

በኮሌጁ በተመረጡ አምስት ቦታዎች ላይ በተቀመጡ ሳጥን በ 2015 ዓ/ም


ለማሰራጨት የታቀደው እቅድ የኮንደም ብዛት 2000 ሲሆን ለ 1 ኛ ሩብ ዓመት
የክረምት ተማሪዎች 1000 ኮንዶም ለማሰራጨት እቅድ ተይዞ ክንውን 500
ተጠቃሚዎች በአግባቡ እንዲጠቀሙ የማድረግ ስራ ተሰርቷል፡፡ በፐርሰንት ሲሰላ
የሩብ ዓመት አፈጻጸም 50 % ሲሆን ከዓመቱ እቅድ ጋር ሲነጻጸር አፈጻጸም
በፐርሰንት ሲሰላ 50% ነው፡፡
6. 2% በጀት አመዳደብ በተመለከተ፣-
ለ 2015 ዓ/ም የስራ ሂደቱን እቅድ ለማሳካት እንዲመደብ በእቅድ ደረጃ የተያዘ በጀት

59,658,454.00 ሲሆን ነገር ግን የ 2014 ዓ/ም የኮሌጁ ስራ ማስካሄጃ በጀት የተፈቀደው


ብር 235,525,0 ሲሆን የዚህ 2% መመደብ ያለበት ብር 465,862.58 በጀት
መመደብ ሲገባው በግልፅ የተመደበ በጀት አለመኖሩ በእቅዱ መሰረት ስራዎች ለማከናወን
አልተቻለም ፡፡ ሆኖም በሩብ ዓመቱ ቫይረሱ በደማቸዉ ያለባቸዉ የኮሌጁ አስተዳደር

ሰራተኞች ድጋፍና እንክብካቤ የሚሆን 14000 ብር ለድጋፍ ውሏል፡፡

1. የአመቱ የዕቅድ ክንውን እና ሽፋን መግለጫ ሰንጠረዥ

ተ.ቁ በአመቱ የተከናወኑ ተግባራት ዝርዝር የዓመቱ የ 1 ሩብ ዓመቱ ሽፋን ምርመራ


ዕቅድ ክንውን በፐርሰንት
1 0.5% ፈንድ መዋጮ የሚሰበሰብ ብር 105592.2 35197.4 50%
2 2% የተመደብ በጀትብር --- 10000 %
6 ቫይረሱበደማቸው የተገኘባቸውን መምህራንና አስ/ር 3 1 100%
ሰራተኞችን መደገፍ በዙር
7 ድጋፍየተደረገላቸው ቫይረሱ በደማቸዉ 14000 3800 40%
ያለባቸዉ የኮሌጁ አስተዳደርሰራተኞች በብር

8 ድጋፍና እንክብካቤ የሚየስፈልጋቸው የክረምት - - -


ተማሪዎች መከታተልና ድጋፍ እዲያገኙ ማድረግ
9 ኮንዶም ማሰራጨት 2000 500 50%
14 የስራ ሂደቱን አመታዊ ዕቅድ እና የውጤት ተኮር እቅድ 2 2 100%
ማዘጋጀትና ለሚመለከተው ክፍል ማቅረብ
15 የስራ ሂደቱን አመታዊ የዕቅድ ክንውን ሪፖርት በየሩብ 4 1 100%
ዓመቱ ማዘጋጀት

8.ያጋጠሙ ችግሮች
 መመሪያው በግልፅ ለስራ ሂደቱ ከስራ ማስካሄጃ በጀት 2% የሚመደብ መሆኑን እየታወቀ
በግልፅ በጀት አለመመደብ
 የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ስለኤች አይቪ ኤድስ ስርጭት እና ወረሽኝ መሆኑን ያላቸው
አመለካከትና ግንዛቤ መቀዛቀዝ /መቀነስ/
 የኤድስ መረጃ ማዕከል ያለበት ግልጽ ቦታ ላይ አለመሆን፡፡
 በክፍሉ የሚገኙ ዕቃዎች አብዛኞቹ አገልግሎት የማይሰጡ ስለሆኑ ከማዕከሉ ማግኘት
የሚገባቸውን መረጃና ዕውቀት ተማሪዎች አለማገኘት
 በተከሰተው ወረርሽኝ ምክንያት በተገብው ሁኔታ መንቀሳቀስ አለመቻል

You might also like