You are on page 1of 23

ማውጫ

ይዘት ገጽ
መግቢያ
ክፍል አንድ፡- የሁኔታ ትንተና 1
1.1 የቅድመ መደበኛ ትምህርት ፕሮግራም አፈፃፀም ……….……………….………….……. 2
1.2 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ፕሮግራም አፈፃፀም ……….………….……….…………… 2
1.2.1. የአንደኛ ክፍል ንጥር ቅበላ አፈፃፀም ……..….…………………………………… 2
1.2.2. የመጀመሪያ ደረጃ አንደኛው ሣይክል (1 ኛ-4 ኛ ክፍል) አፈፃፀም ……..…………… 2
1.2.3. የመጀመሪያ ደረጃ ሁለተኛው ሣይክል (5 ኛ-8 ኛ ክፍል) አፈፃፀም ……....………… 3
1.2.4. የመጀመሪያ ደረጃ (1 ኛ-8 ኛ ክፍል) አፈፃፀም ………………………....…………… 4
1.3 የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ፕሮግራም አፈፃፀም ………………..……………..…..……… 4
1.3.1. የአጠቃላይ 2 ኛ ደረጃ (9 ኛ-10 ኛ ክፍል) አፈፃፀም ……..………………..………… 4
1.3.2. የከፍተኛ ትምህርት መሠናዶ 2 ኛ ደረጃ (11 ኛ-12 ኛ ክፍል) አፈፃፀም ……..…… 5
1.4 የተቀናጀ ተግባር ተኮር የጎልማሶች ትምህርትፕሮግራም አፈፃፀም ……….…….……...… 5
1.5 የልዩ ፍላጎት ትምህርት ፕሮግራም አፈፃፀም ………….……………………..…..……… 6
1.5.1. የመጀመሪያ ደረጃ ልዩ ፍላጎት ትምህርት ፕሮግራም አፈፃፀም ………………… 6
1.5.2. የሁለተኛ ደረጃ ልዩ ፍላጎት ትምህርት ፕሮግራም አፈፃፀም ………….………… 6
1.6 ማጠቃለያ …………..………………………………………….…..……………….…….. 6
1.6.1. የ 2011 የትምህርት ዘመን ተማሪ ምዝገባና ተሣትፎ ለምን አልተሣካም? ………. 7
1.6.2. የዘመኑ ዕቅድ አለመሣካት እንደምታዎቹ ምንድን ናቸው? ………………………. 9
1.6.2.1. የሁለተኛውን የእድገትና ትራንስፎሜሽን እቅድ ማሣካት አለመቻል ….. 9
1.6.2.2. የየደረጃው ትምህርት ተሣትፎ፣ ብቃትና ጥራት አለመሣካት ………… 9
1.7 ወደፊት ምን ማድረግ ይገባል?……..…………………………………..………………… 9
1.7.1. በክረምት ወራት መከናወን ያለባቸው የቅድመ ዝግጅት ተግባራት……………… 10
1.7.2. ት/ቤቶች ከተከፈቱ በኋላ የሚከናወኑ ተግባራት……………..………………….. 10

ክፍል ሁለት፡- የ 2012 የትምህርት ዘመን እቅድ 11


2.1 የዕቅድ መነሻ ሁኔታዎች ……..………………………….………………………..……… 11
2.1.1. የድህረ 2015 ዘላቂ የልማት ግቦች እንደ መነሻ፤…………………………………. 11
2.1.2. የትምህርት ለሁሉም ግቦች እንደ መነሻ፤………………………….………………. 12
2.2.3. የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ የመካከለኛ ዘመን ግምገማ እንደመነሻ፣ ……… 12
2.2 የዕቅዱ ዓላማና ግቦች…………………………………………………………………. 12
2.3 የተማሪዎችን ትወራ ለማከናወን ታሣቢዎችና ዝርዝር እቅድ …………………… 13
2.3.1. የቅድመ መደበኛ ትምህርት ፕሮግራም ተማሪዎች………………..……… 13
2.3.2. የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ፕሮግራም ተማሪዎች……………………… 14
2.3.3. የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ፕሮግራም ተማሪዎች………..……..………… 15
2.3.4. የልዩ ፍላጎት ትምህርት ፕሮግራም ተማሪዎች………………..………… 16

አባሪዎች 22

መግቢያ

0
ትምህርት ለቴክኖሎጂ መሻሻል፣ ለማህበራዊ ለውጥና ለኢኮኖሚ ዕድገት መሠረት ነው፡፡ ሁልጊዜም ቢሆን የአገሮች
እድገትና ትምህርት የጠበቀ ትስስር አላቸው፡፡ ስለሆነም ትምህርት ለሰው ልጆች እድገት ቀጣይ መሆን አንዱ ቁልፍ መሣሪያ
ነው፡፡በ 1986 ዓ.ም. የወጣውን የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ ረዥም ዘመናት ተሻጋሪ የመሆን ባህሪ ያለው በመሆኑ ወደ ተግባር
የሚመነዘረው በየአምስት ዓመቱ በሚነደፍ መርሃ ግብሮችና መርሃ ግብሩን ተከትሎ በሚዘጋጁ ዓመታዊ እቅዶች አማካኝነት
መሆኑ ግልጽ ነው፡፡

በመሆኑም በአገር አቀፍ ደረጃ የተቀመጡትን የትምህርት ዘርፍ ልማት መርሃ ግብር ግቦች በተሟላ መልኩ ለመፈፀም
በየአምስት ዓመቱ የተከፋፈለ የትምህርት ልማት ዘርፍ ልማት መርሃ ግብር በማዘጋጀትና ተግባራዊ በማድረግ ለማሳካት
መሰረተ ሰፊ በሆነው የሁለተኛው አምስት ዓመት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ (2008-2012) ማዕቀፍ ውስጥ በመሆን
በየበጀት ዓመቱ ከክልሉ ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር የተቃኙ ትላልቅ ዕቅዶችን በማዘጋጀት ወደ አፈጻጸም ማሸጋገር ችለናል።

በእነዚህ የዕቅድ ዓመታት የተቀመጡ ዓላማዎችን ለማሳካት በአመራሩ አመራር ሰጪነት የባለሙያዎችንና የህዝብን አቅም
በማቀናጀት በሁሉም የልማትና መልካም አስተዳደር መስኮች መሰረታዊ ግቦችን በማሳካት የህዝቡን ተሳትፎና ተጠቃሚነት
ለማሳደግ ሰፊ ርብርብ ሲደረግ ቆይቷል። በዚህም በትምህርት ጥራት፣ ተገቢነት፣ ብቃትና ፍትሃዊነት ማሻሻል እንዲሁም
የትምህርት ተሣትፎን ማሣደግ በኩል አበረታች ውጤት ማስመዝገብ የተቻለ ቢሆንም በቀጣይ በሁሉም መስክ ሰፊና
የተጠናከረ ስራ መስራት የሚጠይቅ ይሆናል።

የህዳሴውን ጉዞ ሊያረጋግጥ በሚችል የረጀም ጊዜ ስትራቴጂ ማዕቀፍ በየአምስት ዓመቱ ተዘጋጅቶ ወደ አፈጻጸም
እንዲሸጋገር የተደረገው የሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን የመካከለኛው ዘመን ተጠናቅቆ በቀሪው የዕቅድ
ዘመን የሚከናወኑ ተግባራትን በውጤታማነት ለመፈፀም ያላሰለስ ጥረት በመደረግ ላይ ይገኛል። በትምህርት ዘርፍ በዝግጅት
ምእራፍ ከሚከናወኑ ተግባራት መካከል አንዱ ጥራት ያለው እቅድ ማዘጋጀትና በየደረጃው ካሉ አካላት ጋር መግባባት መፍጠር
ነው፡፡ ከዚህ አኳያም የ 2012 በጀት ዓመት በየደረጃው የሚማሩ ተማሪዎችን እቅድ የያዘ ሰነድ ተዘጋጅቷል፡፡

ይህ ሰነድ በዋናነት የቅድመ መደበኛ፣ የመጀመሪያ ደረጃ፣ ሁለተኛ ደረጃ፣ የተቀናጀ ተግባር ተኮር የጎልማሶች ትምህርት፣
የልዩ ፍላጎት ትምህርት የተማሪዎች ትወራ የያዘ ሲሆን እያንዳንዱ ዞን ትምህርት መምሪያ ከነባራዊ ሁኔታ በመነሣት ዝርዝር
እቅድ እና የአፈፃፀም ስልት በመንደፍ ወደ ተግባር መሸጋገር ይጠበቅበታል፡፡

1
ክፍል አንድ፡- የሁኔታ ትንተና
ትምህርት አገራችን ላቀደችው የመካከለኛ ገቢ ኢኮኖሚ ራዕይ መሣካት በዋነኛነት ጉልህ ድርሻ ያለውና በመካከለኛና
በከፍተኛ ደረጃ የሚፈለግ የሰለጠነ የሰው ሃይል ልማት መሠረት በመሆኑ በዞናችን መንግሥት ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት
በመከናወን ላይ የሚገኝ ሲሆን በዘመኑ ያለው አፈፃፀም እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

1.1. የቅድመ መደበኛ ትምህርት ፕሮግራም፣

የቅድመ መደበኛ ትምህርት ፕሮግራም ህፃናት ለተስተካከለ የአካልና የአእምሮ፣ የስሜትና የማህበራዊ ግንኙነት እድገት
በማዳበር ለመደበኛው ትምህርት እንዲዘጋጁ የሚያመቻች እንዲሁም በየደረጃው አካባቢያቸውን እንዲገነዘቡና እንዲያውቁ
የሚያደርግ ነው፡፡ይህንን አገልግሎት ለማስፋፋት መንግሥት ልዩ ትኩረት በመስጠት የመደበኛው አፀደ ህፃናት አገልግሎት
እንደተጠበቀ ሆኖ ሌሎች አማራጮች ማለትም የ”ኦ“ ክፍል እና የተፋጠነ የትምህርት ዝግጁነት በመጠቀም በስፋት በማዳረስ
ላይ ይገኛል፡፡

በ 2011 የትምህርት ዘመን 22160 (ወ 10944፣ ሴ 11,216) መዝግቦ በማስተማር ታቅዶ በትምህርት ዘመኑ መጀመሪያ
ላይ በአደረጃጀት አማካይነት 9596(ወ 4645፣ ሴ 4651) ህፃናትን በመመዝገብ አፈፃፀሙ 43.3%(42.44% ወ፣ 41.47% ሴ)
ማድረስ ተችሎ ነበር፡፡ የ 2011 የትምህርት ዘመን የቅድመ መደበኛ ትምህርት ጥቅል የትምህርት ተሣትፎ 45.16% (46.91%
ወ፣ 43.43% ሴ) ደርሷል፡፡ ስለሆነም በጥቅል የትምህርት ተሣትፎ ፆታዊ ክፍተት 3.48 ሲሆን ይህም የሴት ተማሪዎች
ተሣትፎ ከወንዶች ያነሰ መሆኑን ያስገነዝባል፡፡

በዘመኑ በዓመቱ መጀመሪያ ላይ ለመማር ከተመዘገቡት 10637 (ወንድ 5470፣ ሴት 5167) መካከል በሦስተኛው ሩብ
ዓመት መጨረሻ ላይ በመማር ላይ ያሉት 10080 (ወ 5176፣ ሴ 4904) ናቸው፡፡ በመሆኑም ለመማር ከተመዘገቡት መካከል
ያቋረጡት 557 (ወ 294፣ ሴ 263) ወይም 5.24% (ወ 5.37%፣ ሴ 5.09%) ናቸው፡፡

1.2. የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ፕሮግራም አፈፃፀም፣

የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት በስምንት ዓመት የሚጠናቀቅ ሆኖ፣ በመሠረታዊና አጠቃላይ ትምህርት ለሚቀጥለው
የትምህርት ደረጃ የሚያዘጋጅና በሂደት የሚዳብር መሠረታዊ ችሎታ ያላቸውን ዜጎች የሚያፈራ ነው፡፡ ይህ ፕሮግራም
መሠረታዊ ትምህርትን (ማንበብ፣ መፃፍ፣ ሃሣብን በቃል መግለጽ፣ መሠረታዊ ስሌትና ችግሮችን መፍታት መቻልን)
ለተማሪዎች የሚያስጨብጥና ህፃናትን ለቀጣይ አጠቃላይ ትምህርትና ስልጠና የሚያዘጋጅ በመሆኑ አንገብጋቢ የሆነውን
የትምህርት እድል መፍጠሪያ ሆኖ ተወስዷል፡፡ በመሆኑም ጥራት ያለው የመጀመሪያ ደረጃ ፍትሃዊነቱን በጠበቀ መልኩ
ለማስፋፋት ትኩረት ተሰጥቶት የተከናወኑ ሲሆን በሦስተኛው ሩብ ዓመት መጨረሻ ላይ ያለው አፈፃፀም እንደሚከተለው
ቀርቧል፡፡

1.2.1. የአንደኛ ክፍል ንጥር ቅበላ ዕቅድ አፈፃፀም

በዘመኑ በዞናችን 10556 (ወንድ 5268፣ ሴት 5288) ተማሪዎችን በመመዝገብ ንጥር ቅበላ ምጣኔውን 100% ለማድረስ
ታቅዶ በትምህርት ዘመኑ መጀመሪያ ላይ 9041(ወንድ 4559፣ ሴት 4482) ተማሪዎችን ምዝገባ በማከናወን አፈፃፀሙ
85.65% (86.54% ወ፣ 84.76% ሴ) ሆኗል፡፡ ስለሆነም በንጥር ቅበላ ፆታዊ ክፍተት 1.78 ሲሆን ይህም የሴቶች ተሣትፎ
ከወንዶች የበለጠ መሆኑን ያስገነዝባል፡፡
2
1.2.2. የመጀመሪያ ደረጃ አንደኛው ሣይክል (1 ኛ-4 ኛ ክፍል) አፈፃፀም

በዘመኑ በዞናችን በመጀመሪያ ደረጃ አንደኛው ሣይክል (1 ኛ-4 ኛ ክፍል) በዘመኑ 49743 (ወንድ 25762፣ ሴት 23961)
ነባርና አዲስ ገቢ ተማሪዎችን በመመዝገብ ጥቅል የትምህርት ተሳትፎ ምጣኔ 100% ለማድረስ ታቅዶ በዓመቱ መጀመሪያ
ላይ ወደ ት/ቤት መጥተው የተመዘገቡት 47864 (ወ 24874፣ ሴ 22990) ሲሆኑ በዚህ መሠረት የእቅድ አፈፃፀሙ 96.2%
(96.55% ወ፣ 95.95% ሴ) ሆኗል፡፡ ስለሆነም በጥቅል ተሣትፎ የፆታዊ ክፍተት 0.6 ሲሆን ይህም ወንዶች ከሴቶች የበለጠ
እና ፆታዊ ክፍተት ያለ መሆኑን ያስገነዝባል፡፡

በዘመኑ በመጀመሪያ ደረጃ 1 ኛው ሣይክል በዓመቱ መጀመሪያ ለመማር ከተመዘገቡት 47864 (ወ 24874፣ ሴ 22990)
ተማሪዎች መካከል በሦስተኛው ሩብ ዓመት መጨረሻ ላይ በት/ቤት ውስጥ ያሉት 43851 (ወንድ 22643፣ ሴት 21208)
ናቸው፡፡ በመሆኑም በዓመቱ መጀመሪያ ላይ ከተመዘገቡት መካከል ያቋረጡት 4013 (ወንድ 2231፣ ሴት 1782) ናቸው፡፡
በመሆኑም የሩብ ዓመቱ የተማሪዎች የማቋረጥ ምጣኔ 8.38% (8.97% ወንድ፣ 7.75% ሴት) ሆኗል፡፡

1.2.3. የመጀመሪያ ደረጃ ሁለተኛው ሣይክል (5 ኛ-8 ኛ ክፍል) አፈፃፀም

በመጀመሪያ ደረጃ ሁለተኛው ሣይክል (5 ኛ-8 ኛ ክፍል) በዘመኑ 31245 (ወንድ 15013፣ ሴት 16232) ነባር ተማሪዎችን
በመመዝገብ ለማድረስ ታቅዶ በዓመቱ መጀመሪያ ላይ አደረጃጀቶችን በመጠቀም ወደ ት/ቤት መጥተው የተመዘገቡት
28128(ወንድ 13339፣ ሴት 14789) ሲሆኑ በዚህ መሠረት የእቅድ አፈፃፀሙ 90.02% (88.85% ወንድ፣ 91.11% ሴት)
ሆኗል፡፡ ስለሆነም በጥቅል ተሣትፎ የፆታዊ ክፍተት 2.26 ሲሆን ይህም ሴቶች ከወንዶች የበለጠ መሆኑን ያስገነዝባል፡፡

በዘመኑ በመጀመሪያ ደረጃ 2 ኛው ሣይክል በዓመቱ መጀመሪያ ላይ ለመማር ከተመዘገቡት 28128 (ወንድ 13339፣ ሴት
14789) ተማሪዎችን መካከል በሦስተኛው ሩብ ዓመት መጨረሻ ላይ በት/ቤት ውስጥ ያሉት 26034 (ወንድ 12163፣ ሴት
13871) ናቸው፡፡ በመሆኑም በዓመቱ መጀመሪያ ላይ ከተመዘገቡት መካከል ያቋረጡት 2094 (ወንድ 1176፣ ሴት 918)
ናቸው፡፡ በመሆኑም የሩብ ዓመቱ የተማሪዎች የማቋረጥ ምጣኔ 7.44% (8.82% ወንድ፣ 6.21% ሴት) ሆኗል፡፡

1.2.4. የመጀመሪያ ደረጃ (1 ኛ-8 ኛ ክፍል) ጥቅል ተሣትፎ አፈፃፀም፣

በመጀመሪያ ደረጃ ሁለተኛው ሣይክል (1 ኛ-8 ኛ ክፍል) በዘመኑ ወ 40775 ሴ 40213 ድ 80988 ነባር ተማሪዎችን
በመመዝገብ ለማድረስ ታቅዶ በዓመቱ መጀመሪያ ላይ አደረጃጀቶችን በመጠቀም ወደ ት/ቤት መጥተው የተመዘገቡት ወ
38213 ሴ 37779 ድ 75992 ሲሆኑ በዚህ መሠረት የእቅድ አፈፃፀሙ 93.83% (ወ 93.71%፣ሴ 93.95%)ሆኗል፡፡
ስለሆነም በጥቅል ተሣትፎ የፆታዊ ክፍተት 0.24 ሲሆን ይህም ሴቶች ከወንዶች የበለጠ መሆኑን ያስገነዝባል፡፡

በዘመኑ በመጀመሪያ ደረጃ በዓመቱ መጀመሪያ ላይ ለመማር ከተመዘገቡት ወ 38213 ሴ 37779 ድ 75992 ተማሪዎችን
መካከል በሦስተኛው ሩብ ዓመት መጨረሻ ላይ በት/ቤት ውስጥ ያሉት 62326 (ወንድ 30762፣ ሴት 31564) ናቸው፡፡
በመሆኑም በዓመቱ መጀመሪያ ላይ ከተመዘገቡት መካከል ያቋረጡት 13666 (ወንድ 7451፣ ሴት 6215) ናቸው፡፡ በመሆኑም
የሩብ ዓመቱ የተማሪዎች የማቋረጥ ምጣኔ 17.98% (19.5% ወንድ፣ 16.45% ሴት) ሆኗል፡፡

1.3. የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ፕሮግራም አፈፃፀም፣

3
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ዓላማ በመካከለኛ ደረጃ የተማረ የሰው ሃይል ማፍራትና ወጣቶችን ለከፍተኛ ትምህርት
ማዘጋጀት ሲሆን በ 2 ኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን ጥራቱን በጠበቀ ሁኔታ ለማስፋፋት ትኩረት ተሰጥቷል፡፡
ምክንያቱም የአገራችን ኢኮኖሚ በተከታታይ እያደገና እየሰፋ በመምጣቱ ኢኮኖሚው የሚፈልገውን በመካከለኛና በከፍተኛ
ደረጃ የሰለጠነ የሰው ኃይል ለማዘጋጀት ዜጎቻችንን የሁለተኛ ደረጃ የመጀመሪያ ሳይክል (9 ኛ-10 ኛ ክፍሎች) ትምህርት
ማስተማር የግድ ስለሚል ነው። ተሣትፎን ከማሣደግ አንፃር ያለው ሁኔታ በየእርከኑ ተከፍሎ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

1.3.1. አጠቃላይ 2 ኛ ደረጃ ትምህርት ፕሮግራም፣

በዘመኑ በዞናችን 7200(ወንድ 3,168፣ ሴት 4,032) የሚሆኑ ነባርና አዲስ ገቢ ተማሪዎችን በመመዝገብ ለማድረስ ታቅዶ
በትምህርት ዘመኑ መጀመሪያ ላይ 5752(ወንድ 2613፣ ሴት 3139) በመመዝገብ አፈፃፀሙ 79.9% (82.48% ወንድ፣ 77.85%
ሴት) ደርሷል፡፡

የ 2011 የትምህርት ዘመን የአጠቃላይ 2 ኛ ደረጃ ትምህርት ጥቅል የትምህርት ተሣትፎ 79.9% (82.48% ወንድ፣
77.85% ሴት) ሆኗል፡፡ ስለሆነም በጥቅል የትምህርት ተሣትፎ ፆታዊ ክፍተት 4.63 ሲሆን ይህም የወንዶች ጥቅል የትምህርት
ተሣትፎ ከሴቶች የበለጠ መሆኑን ያሣያል፡፡

በዓመቱ መጀመሪያ ላይ ለመማር ከተመዘገቡት 5752 (ወንድ 2613፣ ሴት 3139)ነባርና አዲስ ገቢ ተማሪዎችን መካከል
በሦስተኛው ሩብ ዓመት መጨረሻ ድረስ በት/ቤት ውስጥ ያሉት 4807(ወንድ 2111፣ ሴት 2696) ናቸው፡፡ በመሆኑም በዓመቱ
መጀመሪያ ላይ ከተመዘገቡት መካከል ያቋረጡት 945 (ወንድ 502፣ ሴት 443) ናቸው፡፡ በመሆኑም የሩብ ዓመቱ የተማሪዎች
የማቋረጥ ምጣኔ 16.43% (19.21% ወንድ፣ 14.11% ሴት) ይሆናል፡፡

1.3.2. ከፍተኛ ትምህርት መሠናዶ 2 ኛ ደረጃ ትምህርት ፕሮግራም

በዘመኑ በዞናችን 1610(ወንድ 784፣ ሴት 826) ተማሪዎችን በማስተማር ጥቅል የትምህርት ተሣትፎውን ለማድረስ ታቅዶ
በትምህርት ዘመኑ መጀመሪያ ላይ 1440 (ወንድ 749፣ ሴት 691) ተማሪዎችን በመመዝገብ የእቅድ አፈፃፀሙ 89.4%
(95.53% ወንድ፣ 83.66% ሴት) ሆኗል፡፡

የ 2011 የትምህርት ዘመን የከፍተኛ ትምህርት መሠናዶ 2 ኛ ደረጃ ትምህርት ጥቅል የትምህርት ተሣትፎ 89.4% (95.53%
ወንድ፣ 83.66% ሴት) ሆኗል፡፡ ስለሆነም በጥቅል የትምህርት ተሣትፎ ፆታዊ ክፍተት 11.87 ሲሆን የወንዶች ጥቅል
የትምህርት ተሣትፎ ከሴቶች የበለጠ መሆኑን ያሣያል፡፡

በዓመቱ መጀመሪያ ላይ ለመማር ከተመዘገቡት 1440 (ወንድ 749፣ ሴት 691) ነባርና አዲስ ገቢ ተማሪዎችን መካከል
በሦስተኛው ሩብ ዓመት መጨረሻ ድረስ በት/ቤት ውስጥ ያሉት 1290 (ወንድ 686፣ ሴት 604) ናቸው፡፡ በመሆኑም በዓመቱ
መጀመሪያ ላይ ከተመዘገቡት መካከል ያቋረጡት 150 (ወንድ 63፣ ሴት 87) ናቸው፡፡ በመሆኑም የሩብ ዓመቱ የተማሪዎች
የማቋረጥ ምጣኔ 10.42% (8.41% ወንድ፣ 12.59% ሴት) ይሆናል፡፡

1.4. የተቀናጀ ተግባር ተኮር የጎልማሶች ትምህርት የፕሮግራም አፈፃፀም፣

በዘመኑ በዞናችን 24940(ወንድ 12453፣ ሴት 12487) ነባርና አዲስ ጎልማሶችን ለማሣተፍ ታቅዶ በትምህርት ዘመኑ
መጀመሪያ ላይ 14006 (ወንድ 7954፣ ሴት 6052) በመመዝገብ አፈፃፀሙ 56.16% (63.87% ወንድ፣ 48.47% ሴት) ሆኗል፡፡

4
በዘመኑ በዞናችን በትምህርት ዘመኑ መጀመሪያ ላይ ለመማር የተመዘገቡት 14006 (ወንድ 7954፣ ሴት 6052) ነባርና አዲስ
ጎልማሶችን ሲሆን ከእነዚህ መካከልም እስከ ሦስተኛው ሩብ ዓመት መጨረሻ ድረስ በ 180 የመማማሪያ ጣቢያዎችና 193
(ወንድ 53፣ ሴት 140)አመቻቾች አማካይነት 6721 (ወንድ 3912፣ ሴት 2849) ጎልማሶች በመማር ላይ ይገኛሉ፡፡ ስለሆነም
በዓመቱ መጀመሪያ ላይ ለመማር ከተመዘገቡት መካከል በመማር ላይ ያሉት አፈፃፀም 27.28% (31.33% ወንድ፣ 22.81%
ሴት) ይሆናል፡፡

1.5. የልዩ ፍላጎት ትምህርት ፕሮግራም አፈፃፀም


1.5.1. የመጀመሪያ ደረጃ ልዩ ፍላጎት ትምህርት ፕሮግራም አፈፃፀም

በዘመኑ 291 (ወንድ 153፣ ሴት 138) የሚሆኑ የልዩ ፍላጎት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎችን በማስተማር ጥቅል
የትምህርት ተሣትፎውን ለማድረስ ታቅዶ በአደረጃጀት የተመዘገቡት 236 (ወንድ 115፣ ሴት 121) ተማሪዎችን መመዝገብ
የተቻለ ሲሆን በዚህ መሠረት የምዝገባ እቅድ አፈፃፀሙ 81.1% (ወንድ 75.16%፣ ሴት 87.68%) ሆኗል፡፡

የ 2011 የትምህርት ዘመን የመጀመሪያ ደረጃ የልዩ ፍላጎት ጥቅል የትምህርት ተሣትፎ 81.1% (ወንድ 75.16%፣ ሴት
87.68%) ሆኗል፡፡ ስለሆነም በጥቅል የትምህርት ተሣትፎ ፆታዊ ክፍተት 12.52 ሲሆን ይህም የሴቶች ጥቅል የትምህርት
ተሣትፎ ከወንዶች የበለጠ መሆኑን ይገልጻል፡፡

በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ፕሮግራም በዘመኑ በዓመቱ መጀመሪያ ላይ ለመማር ከተመዘገቡት 236 (ወንድ 115፣ ሴት
121)መካከል በሦስተኛው ሩብ ዓመት መጨረሻ ላይ ት/ቤት ተገኝተው በመማር ላይ ያሉት 207 (ወንድ 114፣ ሴት 93)
ናቸው፡፡ በመሆኑም በዓመቱ መጀመሪያ ላይ ለመማር ከተመዘገቡት መካከል ያቋረጡት 29 (ወንድ 1፣ ሴት 28) ወይም
12.28% (0.87% ወንድ፣ 23.14% ሴት) ናቸው፡፡

1.5.2. የሁለተኛ ደረጃ ልዩ ፍላጎት ትምህርት ፕሮግራም አፈፃፀም

በዘመኑ 13 (ወንድ 7፣ ሴት 6) የልዩ ፍላጎት የሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎችን ለማስተማር ታቅዶ በአደረጃጀት
የተመዘገቡት 2 (ወንድ 2፣ ሴት 0) ተማሪዎችን መመዝገብ የተቻለ ሲሆን በዚህ መሠረት የምዝገባ እቅድ አፈፃፀሙ 15.38%
(ወንድ 28.57%፣ ሴት 0%) ሆኗል፡፡

የ 2011 የትምህርት ዘመን የሁለተኛ ደረጃ የልዩ ፍላጎት ጥቅል የትምህርት ተሣትፎ 15.38% (ወንድ 28.57%፣ ሴት 0%)
ሆኗል፡፡ ስለሆነም በጥቅል የትምህርት ተሣትፎ ፆታዊ ክፍተት 28.57 ሲሆን ይህም የሴቶች ጥቅል የትምህርት ተሣትፎ ዜሮ
መሆኑን ያመለክታል፡፡

በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ፕሮግራም በዓመቱ መጀመሪያ ላይ ለመማር ከተመዘገቡት 2 (ወንድ 2፣ ሴት 0) መካከል
በሦስተኛው ሩብ ዓመት መጨረሻ ላይ በመማር ላይ ያሉት 2 (ወንድ 2፣ ሴት 0) ናቸው፡፡ በመሆኑም ለመማር ከተመዘገቡት
ያቋረጡት የሉም ፡፡

1.6. ማጠቃለያ

የ 2011 በጀት የተማሪዎች ምዝገባ በውጤታማነት ለማከናወን በቅድሚያ የ 2010 ትምህርት ዘመን የትምህርት ስራ
አፈፃፀም በመፈተሽና ከእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አንፃር በ 2011 ሊደረስበት የታሰበውን ውጤት መሠረት በማድረግ
የ 2011 ዓ/ም ዓመታዊ እቅድ ከመዘጋጀቱ ጎን ለጎን የዚህ ማስፈፀሚያ የሚሆን የክረምት ስራዎች ዕቅድ እና የ 2011 ዓ/ም
የተማሪዎች ምዝገባ ማስፈፀሚያ ዝርዝር እቅድ በወረዳ ደረጃ ተሸንሽኖ በማዘጋጀት እንዲሠራጭ ተደርጓል፡፡
5
ከዚያም በመቀጠል በ 2010 ዓ/ም የክረምት ወቅት ላይ በዞንደረጃ የወረዳ ቁልፍ አመራሮች እንዲሁም የህዝብ ክንፍ
የተሣተፉበት መድረክ በማዘጋጀት የ 2010 አፈፃፀም በጋራ እንዲገመገምና የ 2011 ዕቅድ አቅጣጫዎች ላይ ኦሪንቴሽን
እንዲሰጥ ተደርጓል፡፡ ተመሣሣይ መድረኮች በወረዳ፣ በቀበሌና በመንደር ወይም በጎጥ ደረጃ ተከናውነዋል፡፡ ከዞን እስከ መንደር
/ት/ቤት/ በተካሄዱ የንቅናቄ መድረኮች በ 2010 ዓ/ም የትም/ዘመን በሁሉም የትምህርት ኘሮግራሞች የነበሩ ጠንካራ
አፈፃፀሞችና ያልተሻገርናቸው ማነቆዎች፣ ለክፍተቶች መንስኤ የሆኑት ጉዳዮች እየተነሱ በስፋትና በጥልቀት በመወያየት
በየመድረኮች የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡

በመቀጠልም የክረምት ሥራዎች አፈፃፀም ለመደገፍ በሁሉም ወረዳዎች በሚገኙ የትምህርት ተቋማት የመስክ ክትትል
በማድረግ የታዩ ጠንካራ ጎኖችና መሻሻል ባለባቸው ጉዳዩች ዙሪያ ግብረ መልስ ተዘጋጅቶ እንዲደርሣቸው ተደርጓል፡፡ ከዚህ
ባሻገር በየእለቱ የተመዘገቡ ተማሪዎችን መረጃ በማደራጀትና በመተንተን እያንዳንዱ ወረዳዎች የደረሰበትን ደረጃ ለማሣወቅ
ጥረቶች ተደርገዋል፡፡

በዚህም የተነሣ የዘመኑ የመደበኛ ትምህርት የተማሪዎች ምዝገባና ተሣትፎ ካለፈው ዓመት ከነበረው አፈፃፀም አንፃር
ሲመዘን መቀነስ ታይቷል፡፡ በ 2010 ዓ/ም በዞናችን በመማር ላይ የነበሩት 90762 (ቅደመ መደበኛ 11561፣ የመጀመሪያ ደረጃ
74318 እና ሁለተኛ ደረጃ 4883) ነበሩ፡፡ ይህም መጨመር በማሣየት በ 2011 ዓ/ም 93827 (ቅደመ መደበኛ 10643፣
የመጀመሪያ ደረጃ 75992 እና ሁለተኛ ደረጃ 7192) ደርሷል፡፡ በተጨማሪም በዘመኑ የተመዘገቡ ተማሪዎች በእድገትና
ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ላይ ከተቀመጠው ዒላማ ጋር ሲነፃፀር አፈፃፀሙ መካከለኛ ነው፡፡

1.6.1. የ 2011 የትምህርት ዘመን ተማሪ ምዝገባና ተሣትፎ ለምን አልተሣካም?

በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ላይ በ 2011 ዓ/ም ለማሣካት ካስቀመጥነው ግብ አንፃር ሲታይ የዘመኑ የተማሪዎች
ምዝገባና ተሣትፎ ግቡን አልመታም፡፡ እንዲሁም በ 2010 በጀት ከተመዘገበው ጋር ሲነፃፀር አፈፃፀሙ የተሻለ ነው፡፡ በ 2010
ዓ/ም በመማር ላይ የነበሩ ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ወደ ት/ቤት አለመምጣትና አዲስ ገቢ ተማሪዎችን መመዝገብ አለመቻል
ለዕቅዱ አለመሣካት በምክንያቱም ይጠቀሣሉ፡፡

ተማሪዎች ወደ ት/ቤት ያልመጡበት ቁልፉ ችግር በእቅድ ላይ በቂ መተማማን አለመፈጠሩ፣ የአጎራባች ወረዳና ቀበሌ፣
ት/ቤት ተማሪዎችን አሟጥጦ አለመመዝገብ፣ የቦታ አቀማመጡ ለህፃናት አመቺ አለመሆኑ፣ በየደረጃው ያለው መዋቅር
ለምዝገባ ስራው ትኩረት አለመስጠት፣ በዞን ደረጃ መግባባት ከተደረሰበት አቅጣጫ ውጭ መፈፀም እና ከተመዘገቡት መካከል
ሁሉም በትምህርት ቤት መጥተው መማር አለመቻላቸው ናቸው፡፡

በዘመኑ እንደ ቀደሙት ዓመታት ሁሉ ከዞን እስከ ት/ቤት ድረስ የታቀደው የተማሪዎችን ብዛት ወጥ የሆነና ተመጋጋቢ
መሆን ይገባዋል፡፡ ነገር ግን በወረዳና በት/ቤት ደረጃ የታቀደው እቅድ የማይናበብና ልዩነት ያለው ነው፡፡ ለልዩነት መከሰት ዋናው
ችግር አመራሩ በየት/ቤቶች ለታቀደው እቅድ ተገቢውን ግንዛቤ ጉዳዩ ለሚመለከታቸው አካላት መፍጠር አለመቻሉ ነው፡፡
በዚህም የተነሣ በወረዳና በት/ቤት ደረጃ እቅዱ የተጋነነ ወይም በጣም የተለጠጠ በመሆኑ ማሣካት አይቻልም የሚል ጫፍ
የወጣ አስተሣሰብ በመያዙ ነው፡፡ በተለይም በት/ቤት ደረጃ ያለው አመራርና መምህራን የትምህርት ቤት ወላጅ ግንኙነት
በጣም ዝቅተኛ በሆነበት የታቀደውን እቅደ ለማሳከት አይቻልም የሚል አመለካከት መያዙና ይህንንም ለማስተካከል
የተከናወኑ ተግባራት ውስኑንት ያለባቸው በመሆኑ ተግባሩ እንዳይሣካ መሠናክል ሆነዋል፡፡

እንደሚታወቀው ሁሉ የ 2011 ዓ/ም የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች ዕቅድ ሲዘጋጅ ታሣቢ የተደረገው የ 2010 ዓ/ም ከ 1 ኛ
ክፍል እስከ 7 ኛ ክፍል የነበሩ ሁሉም ነባር ተማሪዎች እና በ 2011 ዓ/ም የስነ ህዝብ ትንበያ መሠረት በማድረግ የአዲስ ገቢ
ወይም የአንደኛ ክፍል አዲስ ገቢ ተማሪዎች ቅበላ ነው፡፡ በዚህ መሠረት በ 2010 በጀት ዓመት የነበሩና በ 2011 በጀት ዓመት

6
መማር ያለባቸው ነባር የመጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች 80889 ሲሆኑ ከእነዚህ መካከል ት/ቤት መጥተው ለመማር የተመዘገቡት
75992 ወይም 93.83% ናቸው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ በዘመኑ 10772 አዲስ አንደኛ ክፍል የሚገቡ ተማሪዎችን መዝግቦ
ለማስተማር ታቅዶ ወደ ት/ቤት መጥተው ለመማር የተመዘገቡት 9041 (83.93%) ናቸው፡፡ የህዝብ ብዛት ትንበያው መሠረት
ያደረገው በዞናችን ያለውን አማካይ የመውለድ ምጣኔ እና የሞት ምጣኔ ነው፡፡ በመሆኑ ይህ ከእውነታው ጋር ብዙም ለውጥ
ይኖረዋል ተብሎ አይጠበቅም፡፡ ስለሆነም ይህንን ከወረዳው ነባራዊ ሁኔታ አንፃር በመረጃ ላይ ተመስርቶ በመተንተን
መተማማመን መድረስ ሲገባ ዕቅድ በጣም የተለጠጠ በመሆኑ ልናሣካው አንችልም በማለት ዕቅድን ማሣካት አልተቻለም፡፡

ሁለተኛው ችግር የአጎራባች ወረዳና ቀበሌ፣ ት/ቤት ተማሪዎችን አሟጥጦ አለመመዝገብ ነው፡፡ በአንዳንድ አካባቢዎች
በቀበሌው ያለው ት/ቤት ለሌላ ቀበሌ ቅርብ የሚሆንበት አጋጣሚዎች አሉ፡፡ ይህ ክስተት ሲፈጠር በቀበሌው ያለው
የመንግሥት አደረጃጀት ተማሪዎችን ቀስቅሶ በአጎራባች ቀበሌው ለሚገኘው ት/ቤት መላክና መመዝገባቸውን ማረጋገጥ ሲገባ
በቸልታ የማለፍ ሁኔታ ታይቷል፡፡ ተመሣሣይ ሁኔታም በአጎራባች ወረዳዎችተከስቷል፡፡ ይህንን ፈጥኖ እንዲስተካከል ጥረቶች
ቢደረጉም በአንዳንድ አካባቢዎች በተሟላ ሁኔታ ባለመፈፀም የተማሪዎች ምዝገባ እንዳይሣካ መሠናክል ሆኗል፡፡

ሦስተኛው ችግር የቦታ አቀማመጡ ለህፃናት አመቺ አለመሆኑ ነው፡፡ በአዳንድወረዳዎች የመሬቱ አቀማመጥ ተራራማና
ወጣ ገብ የበዛበት በመሆኑ ተማሪዎች በቀላሉ ወደ ት/ቤት መምጣት አልቻሉም፡፡ ይህንን ችግር ለመፍታት በአብዛኛው
አካባቢዎች ሣተላይት የመማሪያ ክፍሎች የተከፈቱ ቢሆንም ችግሩ ሙሉ በሙሉ መቅረፍ ባለመቻሉ የተማሪዎችን ምዝገባ
ውጤታማ እንዳይሆን አድርጎታል፡፡

አራተኛው ችግር በየደረጃው ያለው መዋቅር ለምዝገባ ስራው ትኩረት አለመስጠት ነው፡፡ በዘመኑ የተማሪዎችን ምዝገባ
በሠራዊት አግባብ ለመፈፀም በቅድሚያ የተማሪ ልየታ ስራውን በአደረጃጀት ማከናወን፣ በመቀጠልም የፓይለት ምዝገባ
ማካሄድና አፈፃፀሙን መገምገም በመጨረሻም አደረጃጀትን ተጠቅሞ በአንድ ቀን ውስጥ የተማሪዎችን ምዝገባ ማጠናቀቅ
በሚሉት የአሠራር ስርዓት ላይ ስምምነት ተደርሶ ነበር፡፡ ይሁን እንጂ በተግባራዊ ሂደት በሁሉም አካባቢዎች በተቀመጠው
አቅጣጫ መሠረት አልተፈፀመም፡፡ በበርካታ ት/ቤቶች በ 2011 በበጋው ወቅት የተለየውን የአዲስና የነባር ተማሪዎችን መረጃ
በስም፣ በቀበሌ እና በጎጥ ለይቶ ለቀበሌ አደረጃጀት መሪዎች በመስጠት የምዝገባ ስራው እንዲከናወን ተደርጓል፡፡ በሌላ በኩል
ደግሞ አንዳንድ ት/ቤቶች ለአደረጃጀቶች ምንም አይነት መረጃ ያልሰጡ ሲሆን ይህም ችግሩ በወቅቱ ለማረም ጥረቶች
ተደርገዋል፡፡ ከተማሪ ልየታ በመቀጠልም የተማሪዎች ምዝገባ በተቻለ መጠን በአንድ ቀን ውስጥ ማጠናቀቅ ካልሆነ በሦስት
ቀን ውስጥ ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ በቅድሚያ በሁሉም ት/ቤት ከመጀመሩ በፊት የምዝገባ የሙከራ ስራ (pilot) በመጠቀም
የሙከራ ስራው በጥንካሬ እና በድክመት ተገምግሞ ለሁሉም ቀበሌዎችና ት/ቤቶች በማድረስ በንቅናቄ ማስመዝገብ የሚል
አቅጣጫ የተቀመጠ ቢሆንም አፈፃፀሙ የተዥጎረገረና በሁሉም አካባቢ በተመሣሣይ ሁኔታ አልተፈፀመም፡፡ ከዚህ በተጨማሪ
ተሞክሮዎቹን ቀምሮ በማስፋት ረገድም የተሄደበት ርቀት ውስንነት ያለበት ነው፡፡ በአጠቃላይ በየደረጃው ያለው አመራር
የተማሪዎችን ምዝገባ በክልል ከተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት በጥብቅ ዲስፒሊን መፈፀም ባለመቻሉ ግቡን ማሣካት
አልተቻለም፡፡

በአደረጃጀት የተመዘገቡት ሁሉም ተማሪዎች ወደ ት/ቤት መጥተው ትምህርት መጀመር አለመቻላቸው ሌላው
አምስተኛው ችግር ነው፡፡ በአደረጃጀት የተለዩ ተማሪዎች በስም ዝርዝር ከተለዩ በኋላ ወደ ት/ቤት መጥተው ትምህርት
አልጀመሩም፡፡

1.6.2. የዘመኑ ዕቅድ አለመሣካት እንደምታዎቹ ምንድን ናቸው?

የተመዘገበው የዚህ አፈፃፀም ሲታይ ይህ ከሌሎች ክልሎች ጋር ሲነፃፀር እጅግ አነስተኛ ነው፡፡ ይህም የሚከተሉት
እንደምታዎች አሉት፡፡

7
1.7. ወደፊት ምን ማድረግ ይገባል?

በሁሉም አካባቢዎች በየደረጃው ያለው አካል ለተማሪዎች ምዝገባ ውድቀት ዝርዝር ግምገማ በማድረግ ችግሩን፣ የችግሩን
ምንጭና መንስኤ ከለየ በኋላ አካባቢያዊ የመፍትሄ ሃሣብ ማስቀመጥ እንደተጠበቀ ሆኖ የሚከተሉት ጉዳዩች ልዩ ትኩረት
ተሰጥቷቸው የሚፈፀሙ ይሆናሉ፡፡

1.7.1. በክረምት ወራት መከናወን ያለባቸው የቅድመ ዝግጅት ተግባራት

በክረምት ወራት የሚከናወኑት ተግባራት የ 2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በተሳካ ሁኔታ ለማካሄድ እንዲቻል የሚረዱ
ናቸው፡፡ የ 2012 ዓ.ም የትምህርት ዘመንን በበቂ ዝግጅት መቀበል ይቻል ዘንድ መምህራን ከነሃሴ ወር 2011 ዓ/ም መጨረሻ
ሣምንት ጀምሮ በት/ቤት ተገኘተው አስፈላጊ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን እንዲያከናውኑ ለዕረፍት ት/ቤት ከመዘጋቱ በፊት
በስብሰባና በማስታወቂያ መግለጽ፣ መምህራን በት/ቤት ሲገኙ በተናጠልና በቡድን ተደራጅተው የሚሰሯቸውን ተግባራት
አደራጅቶ መጠበቅና ማሰማራት ያስፈልጋል፡፡ በዚህ በተጨማሪም ት/ቤቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ተግባራት ከራሳቸው
ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማገናዘብ ይፈጽማሉ፡፡

1.7.1.1. መረጃዎችን የማጥራት ስራ ትኩረት በመስጠት ማከናወ

በየአካባቢው ያሉ ነባርና አዲስ ተማሪዎችን መረጃ የማጥራትና ይህንንም ወደ ት/ቤት እንዲመጡ ለማድረግ የሚያስችል
የጋራ መግባባት መፍጠር ቅድሚያ ትኩረት ተሰጥቶት የሚከናወን ተግባር ይሆናል፡፡ በዚህ መሠረት የሚከናወኑ ዝርዝር
ተግባራት እንደሚከተለው ቀርበዋል፡፡
 ከክፍል ክፍል መዛወር የሚያስችላቸው ነጥብ ሳያገኙ በስህተት ወደ ተከታዩ ክፍል የሚገቡ ተማሪዎች እንዳይኖሩ
ክትትል ማድረግ፣ ሮስተሮችን መመርመርና በትክክል የተዛወሩና ደጋሚ ተማሪዎችን መለየት፣
 የነባር ተማሪዎች ልየታ ከተጠናቀቀ በኋላ በየክፍሉ በመደልደል ተማሪዎች እንዲያውቁት መለጠፍ እና ነባር
ተማሪዎችን የሚመዘግብ አደረጃጀት በመፍጠር ከተገቢው ኦሬንቴሽን ጋር መረጃውን መስጠት፣
 ሁሉንም ነባር አና አዲስ ተማሪዎች የሚመጡበትን ጎጥ በመለየት ከቀበሌው አመራር ጋር በመሆን እነዚህ ተማሪዎች
መቼ መምጣት እንዳለባቸው የጋራ ስምምነት ላይ መድረስ፣ ምናልባትም የክልሉ ፕላን ኮሚሽን የህዝብ ትንበያ
መረጃ መሠረት እድሚያቸው 7 ዓመት የሞላቸው ህፃናት በየጎጡና ቀበሌው የሌሉ ከሆነ መረጃውን የቤት ለቤት
ቆጠራ በማድረግ የማጥራት ስራ መስራት እና ማረጋገጥ ይገባል፡፡ ይህም ተልእኮ በ 2011 በጀት ዓመት ት/ቤቶች
ከመዘጋታቸው በፊት ማጠናቀቀ ይገባል፡፡ ከሁሉም በላይ አስቀድሞ ህፃናት በየጎጡና መንደሩ የሉም የሚለውን
አስተሣሰብ መዋጋት ይገባል፡፡
1.7.1.2. ተማሪዎችን ማስተናገድ የሚያስችል በቂ ግብአት መኖሩን ማረጋገጥ

 የሦስት አመት ስትራቴጅክ ዕቅድና ከዚሁ የተቀዳ የትምህርት ቤት ማሻሻያ የ 2012 ዓ.ም ዕቅድ ከት/ቢሮ ከወረደው
ዕቅድ ጋር በተገናዘበ መልኩ ማደራጀት፣
 የመደበኛ ት/ቤት በአቅራቢያቸው ለማያገኙ ህፃናት ሣተላይት ክፍል መክፈት እና በተገቢው ግብአት እንዲሟላላቸው
የማድረግ ስራ ማከናወን ይገባል፡፡ የቦታ አቀማመጡ ለህፃናት አመቺ ባልሆነባቸው አካባቢዎች ህፃናት ረጀም ርቀት
ተጉዘው ወደ መደበኛ ት/ቤት ለመምጣት ይቸገራሉ፡፡ ስለሆነም በአቅራቢያቸው ከመደበኛው ት/ቤት ጋር የተያያዙ
የመማሪያ ክፍሎችን በመክፈት ህፃናት በአቅራቢያቸው የሚማሩበት ምቹ ሁኔታ መፍጠር ይገባል፡፡ ከሁሉም በላይ
የኦ ክፍል ህፃናትን ለማስተናገድ በቂ ክፍል ከሌለ በክረምት ወቅት እንዲሟላ ማድረግ ይገባል፡፡
 በት/ቤቱ ያሉ የመማሪያ ክፍሎች፣ መምህራንና መጽሀፍት በዕቅድ ላይ የተቀመጠውን የተማሪ ቁጥር ለማስተናገድ
በቂ መሆናቸውን በመፈተሽ በእጥረት የሚታይ ካለ የሚሟላበትን በክረምት ወቅት አስቀድሞ ከሚመለከታቸው ጋር
በመሆን እንዲሟላ ማድረግ፣
8
 ጥገናናዕድሳትየሚያስፈልጋቸውንየመማሪያናየአገልግሎትመስጫክፍሎችእንዲሁምጠረጴዛዎች፣ወንበሮችናጥቁርሰሌዳዎችመጠገንናማ
ደስ፣ተጀምረውያልተጠናቀቁ የማስፋፋት ስራዎች ካሉ ተጠናቀው ለ 2012 የትም ዘመን አገልግሎት ዝግጁ እንደሆኑ
ማድረግ፣
 ተማሪዎች ወደ ት/ቤት ከመምጣታቸው በፊት ወላጆችንና ሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎችን በማስተባበር የት/ቤቱን
ምድረ ግቢ ለመማር ማስተማሩ ሂደት ምቹ ማድረግ፣
1.7.2. ት/ቤቶች ከተከፈቱ በኋላ የሚከናወኑ ተግባራት

የ 2012 የትምህርት ዘመን ት/ቤቶች የሚፈከፈቱት በነሐሴ ወር 2011 ዓ/ም መጨረሻ ሣምንት ላይ ሲሆን በእነዚህ
ጊዚያት የሚከናወኑ ተግባራት የሚከተሉት ይሆናሉ፡፡

1.7.2.1. የነባር እና አዲስ ተማሪዎችን ምዝገባ ማከናወን

በየአካባቢው የተለዩት ሁሉም ህፃናት ወደ ት/ቤት እንዲመጡ ለማድረግ የሚያስችል ዝርዝር አሠራር ቀይሶ ት/ቤቶች
ሲከፈቱ የተማሪዎችን ምዝገባ የሚከናወን ይሆናል፡፡ በመሆኑም፣

 የተማሪዎች ምዝገባ በውጤታማነት ለመፈፀም የወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት ዝርዝር የማስፈፀሚያ ዕቅድ
አዘጋጅቶና በዞን ትምህርት መምሪያ ይሁንታ ማግኘት ይገባዋል፡፡፡ በመቀጠልም ከነሐሴ ወር ጀምሮ ሁሉም የት/ቤት
አመራሮችና መምህራን በተገኙበት የተማሪዎች ምዝገባ ስራ የሚከናወን ይሆናል፡፡
 የምዝገባው አካሄድ በተመለከተ በቅድሚያ ሁሉም ነባር እና አዲስ ተማሪዎችየሚመጡበትን ጎጥ በመለየት
ከቀበሌው አመራር ጋር በመሆን እነዚህ ተማሪዎች ወደ መቼ መምጣት እንዳለባቸው የጋራ ስምምነት ላይ መድረስ
ያስፈልጋል፡፡ ምናልባትም የክልሉ ፕላን ኮሚሽን የህዝብ ትንበያ መረጃ መሠረት እድሚያቸው 7 ዓመት የሞላቸው
ህፃናት በየጎጡና ቀበሌው የሌሉ ከሆነ መረጃውን የቤት ለቤት ቆጠራ በማድረግ የማጥራት ስራ መስራት እና
ማረጋገጥ ይገባል፡፡ ይህም ተልእኮ በ 2011 በጀት ዓመት ት/ቤቶች ከመዘጋታቸው በፊት ማጠናቀቀ ይገባል፡፡ ከሁሉም
በላይ አስቀድሞ ህፃናት በየጎጡና መንደሩ የሉም የሚለውን አስተሣሰብ መዋጋት ይገባል፡፡

1.7.2.2. ጠንካራ ክትትልና ድጋፍ ስርዓት መዘርጋትና ተግባራዊ ማድረግ

የተማሪዎችን ምዝገባ በውጤታማነት መፈፀሙን ለመከታተልና ለመደገፍ አመራሩ የተለዩ ድጋፍ በሚያስፈልጋቸው
አካባቢዎች በመስክ ሱፐርቪዥን ለመደገፍ የሚያደርገው ጥረት እንደተጠበቀ ሆኖ የዞኑን ወይም ወረዳውን በቀጠና
በመከፋፈልና የባለሙያ ምደባ በማድረግ እለታዊ ክትትልና ግምገማ ያደርጋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በየደረጃው ኮማንድ
ፖስት በማደራጀት በየእለቱ ወደ ት/ቤት የመጡ ተማሪዎችንና በየደረጃው የሚታየውን አዝማሚያ በመገምገም የጽሁፍ
መረጃ መላክ ለበላይ አካል ይገባዋል፡፡ መረጃው የደረሰው አካልም በመተንተንና ደረጃ በማውጣት ግብረ መልስ አዘጋጅቶ
ይሰጣል፡፡ ቀጥሎ ለሚገኘው አካልም ሪፖርት ይልካል፡፡ ይህ አሠራር ስርዓት የምዝገባ ስራው ተጀምሮ እስከ ሚጠናቀቅበት
ጊዜ በትኩረት የሚፈፀም ጉዳይ ይሆናል፡፡

1.7.2.3. ምርጥ ተሞክሮ መቀመርና ማስፋት

የተማሪዎችን ምዝገባ አስመልክቶ በየደረጃው ኮማንድ ፖስት በማደራጀት በየአካባቢው የተገኙ ምርጥ ተሞክሮዎችን
መቀመርና ማስፋት ትኩረት የሚሰጡው አንዱ ተግባር ይሆናል፡፡

9
ክፍል ሁለት፡- የ 2012 የትምህርት ዘመን ዕቅድ

2.1. የእቅዱ መነሻ ሁኔታዎች


በየደረጃው የትምህርት ተደራሽነትና ተሣትፎን ለማሣደግ በርካታ ጉዳዮችን ከግምት ማስገባት አስፈላጊ በመሆኑ የ 2012 በጀት
ዓመት የተማሪዎች ተሣትፎ ዕቅድ ዝግጅት መነሻዎችና ታሣቢዎች በዝርዝር እንደሚከተለው ቀርበዋል።

2.1.1. የድህረ 2015 ዘላቂ የልማት ግቦች እንደ መነሻ፤

የ 2012 በጀት ዓመት ዕቅድ ሲዘጋጅ የዘላቂ የልማት ግቦችን በተለይም ከትምህርት ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸውን ግብ
አራት (Provide equitable and inclusive quality education and life-long learning opportunities for all) እና ግብ
አምስት (Attain gender equality, empower women and girls everywhere) ማሳካት እንደ አንድ መነሻ ተወስደው
ከአገራችን ብሎም ከክልላችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር በማዛማድ እንዲቀመጡ ተደርገዋል።

2.1.2. የትምህርት ለሁሉም ግቦች እንደ መነሻ፤

ትምህርት በሁሉም የዕድሜ ደረጃና በየትኛውም የዓለም ክፍል የሚገኙ ሰዎች ሁሉ የወንዶችንም የሴቶችም መሠረታዊ መብት
መሆኑ በመገንዘብ እስከ አሁን የመጣውን ለውጥ በመገምገም እና በቀሪው ጊዜያት ሊከናወኑ የሚገባቸውን ተግባራት በመመዘን
በዕቅዱ ውስጥ ታሣቢ ተደርጓል።

2.1.3. የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ የመካከለኛ ዘመን ግምገማ እንደመነሻ፣

የአጠቃላይ ትምህርት ለሀገራችን የ 2017 ዓ.ም የመጀመሪያ ደረጃ መካከለኛ ገቢ ኢኮኖሚ ራዕይ መሳካትና ከዚህ ግብ እውን
መሆን ጋር ለሚከሰተው ሁለንተናዊ የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ሽግግር ውጤታማነት ከፍተኛ ድርሻ አለው። በመሆኑም
የሀገራችንን የህዝብ እድገት ታሳቢ ያደረገና ይህን እድገት ከብዛት ወደ ሰለጠነ የሰው ሀብትነት ለመቀየር በእድገትና
ትራንስፎርሜሽን እቅድ ላይ የተቀመጡትን የትምህርት ዘርፍ ዋና ዋና ግቦች አፈፃፀም በጥልቀት በመገምገም በቀጣይ መከናወን
ያለባቸውን አቅጣጫዎች በዚህ ዕቅድ ዝግጅት ወቅት በመነሻነት ተወስደዋል፡፡

2.2. የዕቅዱ ዓላማና ግቦች


የ 2012 ዓ/ም የትምህርት ተሣትፎና ተደራሽንነት ዓላማ ሁሉም ተማሪዎች ተደራሽ የሆኑ የትምህርት ተቋማት እንዲያገኙ
በማድረግ ህፃናት ለደረጃው የተቀመጠውን የቅድመ መደበኛ፣ የመጀመሪያ ደረጃና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት እንዲያጠናቅቁ
ማስቻል ነው። ይህንን ዓላማ ለማሣካት የሚከተሉት ግቦች ተነድፈዋል፤
 የቅድመ መደበኛ ትምህርት ጥቅል የትምህርት ተሳትፎ ምጣኔ በ 2011 ዓ.ም ከነበረበት 45.16% (46.91% ወ፣
43.43% ሴ) በ 2012 ዓ.ም ወደ 50% (ወንድ 50.00%፣ 50.00% ሴት) ደርሷል።
 የአንደኛ ክፍል ንጥር ቅበላን በ 2011 ዓ/ም ከነበረበት 85.65% (86.54% ወ፣ 84.76% ሴ) በ 2012 ዓ.ም ወደ 100%
(ወንድ 100%፣ 100% ሴት) ደርሷል፡፡
 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ጥቅል የትምህርት ተሣትፎ ምጣኔ በ 2011 ዓ/ም ከነበረበት 93.83% (ወ 93.71%፣ሴ
93.95%) በ 2012 ዓ.ም ወደ 95.31% (ወንድ 94.15%፣ ሴት 95.85%) ደርሷል፡፡
 የአጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ጥቅል ተሳትፎ ምጣኔ በ 2011 ዓ/ም ከነበረበት 79.9% (82.48% ወንድ፣ 77.85% ሴት)
በ 2012 ዓ.ም ወደ 80.52% (ወንድ 80.22%፣ 79.78% ሴት) ደርሷል፡፡

10
 የከፍተኛ ትምህርት መሠናዶ ሁለተኛ ደረጃ ጥቅል ተሳትፎ ምጣኔ በ 2011 ዓ/ም ከነበረበት 89.4% (95.53%
ወንድ፣ 83.66% ሴት) በ 2012 ዓ.ም ወደ 90.5% (ወንድ 94.53%፣ 85.47% ሴት) ደርሷል፡፡
 በ 2011 የትምህርት ዘመን በመማር ላይ የነበሩት ጎልማሶች 14006 (ወንድ 7954፣ ሴት 6052) ሲሆን በ 2012
የትምህርት ዘመን ወደ 1,6400 (9460 ወንድ፣ 6940 ሴት) (9845 በደረጃ አንድና 6555 በደረጃ ሁለት) እንዲሳተፉ
ተደርጓል፡፡

2.3. የተማሪዎች ትወራ ታሣቢዎችና ዝርዝር አሃዛዊ ዕቅዶች፣


የ 2012 የትምህርት ዘመን የተማሪዎች ትወራ በዋናነት ታሣቢ ያደረገው የዘላቂ የልማት ግብ የማሣካት ግቦች፣ የትምህርት
ለሁሉም ግቦች፣ አገር አቀፍ አምስተኛው ዙር የትምህርት ዘርፍ ልማት መርሃ ግብር ግቦች፣ የክልላችን የ 2011 በጀት ዓመት
እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ናቸው፡፡ ይህንን በመመርኮዝ ዝርዝር ትወራው ሲዘጋጅ ታሣቢ የተደረጉ መሠረታዊ ጉዳዩች
የሚከተሉት ናቸው፡፡

2.3.1. የቅድመ መደበኛ ትምህርት ፕሮግራም ተማሪዎች

ይህ ፕሮግራም እድሜያቸው 4-6 የሆነ ህፃናትን የተስተካከለ የአካልና የአእምሮ፣ የስሜትና የማህበራዊ ግንኙነት እድገትና
ለመደበኛ ትምህርት የሚዘጋጁበት ሲሆን በ 2012 የትምህርት ዘመን በጠቅላላው 16443 (ወንድ 8172፣ ሴት 8271)
ተማሪዎችን በማስተማር ጥቅል የትምህርት ተሣትፎውን 50.00% (ወንድ 50.00%፣ 50.00% ሴት) ለማድረስ ታቅዷል፡፡
ይህም የሚከተሉትን ታሣቢ ያደረገ ነው፡፡

ሀ) ነባር ተማሪዎች

በ 2012 የትምህርት ዘመን በዞኑ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ፕሮግራም ይማራሉ ተብለው የታቀዱ ነባር ተማሪዎች
10643(ወ 5478፣ ሴ 5165) ሲሆኑ ይህም የተሠላው በሚከተለው አኳኋን ነው፡፡

 በመደበኛ የቅድመ መደበኛ ት/ቤቶች በ 2011 ዓ/ም እድሚያቸው 5 እና በታች የሆኑት 695 (ወንድ 355፣ ሴት 340)
ህፃናት በ 2012 ዓ/ም በመዋእለ ህፃናት ትምህርታቸውን የሚከታተሉ ይሆናሉ፡፡
 ከመንግሥት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቶች ጋር ተያይዘው በተከፈቱ የኦ ክፍል በ 2011 ዓ/ም እድሚያቸው አምስት
ዓመትና በታች የሆናቸው 6282 (ወንድ 3212፣ ሴት 3070) ህፃናት በ 2012 ዓ/ም በነበሩበት ት/ቤት
ትምህርታቸውን ይከታተላሉ ተብሎ ታሣቢ ተደርጓል፡፡

ለ) አዲስ ገቢ ተማሪዎች

በ 2012 ዓ/ም በቅድመ መደበኛ ትምህርት ፕሮግራም የታቀደውን ግብ ለማሣካት 16443 (ወንድ 8172፣ ሴት 8271) አዲስ
ገቢ ህፃናት ወደ ት/ቤት ይመጣሉ ተብሎ ታሣቢ ተደርጓል፡፡ ይህም የሚከተሉትን ታሣቢ ያደረገ ነው፡፡

 በመደበኛ የቅድመ መደበኛ ት/ቤቶች (KG) ባለፉት ዓመታት የነበረውን አማካይ የአዲስ ተማሪዎች ቅበላ ዓመታዊ
እድገት መነሻ በማድረግ በ 2012 የትምህርት ዘመን 942 (ወንድ 483፣ ሴት 459) አዲስ ገቢ ተማሪዎች ይኖራሎ
ተብሎ ታሣቢ ተደርጓል፡፡

11
 ከመንግሥት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቶች ጋር ተያይዘው በተከፈቱ የኦ ክፍሎች (0 class) በ 2012 ዓ/ም 15501
(ወንድ 7689፣ ሴት 7812) አዲስ ገቢ ተማሪዎች ይኖራሉ ተብሎ ታሣቢ ተደርጓል፡፡ የአዲስ ገቢ ተማሪዎች ዕቅድ
የተለጠጠ ቢመስልም ባለፉት ዓመታት ከነበረው አፈፃፀም አንፃር ማሣካት ይቻላል፡፡

2.3.2. የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ፕሮግራም ተማሪዎች

ይህ ፕሮግራም እድሜያቸው 7-14 የሆነ ህፃናትን በመሠረታዊና አጠቃላይ ትምህርት ለሚቀጥለው የትምህርት ደረጃ
የሚያዘጋጅና በሂደትም የሚዳብር መሠረታዊ ችሎታ ያላቸውን ዜጎች የሚያፈራ ሲሆን በ 2012 የትምህርት ዘመን በአንደኛ
ክፍል ቅበላ፣ በጥቅል ተሣትፎና በንጥር ተሣትፎ ያለው እቅድ የሚከተውን ታሣቢ ያደረገ ነው፡፡

ሀ) የአንደኛ ክፍል ተማሪዎች ቅበላ

በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ የ 2012 የትምህርት ዘመን የአንደኛ ክፍል ንጥር ቅበላን 100% እና ጥቅል
ቅበላ ደግሞ 115% ለማድረስ ታቅዷል፡፡ በመሆኑም ዝርዝር የተማሪዎች ትወራ የሚከተሉትን ታሣቢ በማድረግ ተሰልቷል፡፡

 በክልሉ ፕላን ኮሚሽን ትንበያ መሠረት በ 2012 ዓ/ም በዞኑ እድሚያቸው 7 ዓመት የሆናቸው ሁሉም 12515 (ወንድ
6154፣ ሴት 6361) ህፃናት ምንም ሣይንጠባጠቡ አንደኛ ክፍል በማስገባት ንጥር ተሣትፎው 100% የሚደርስ
ይሆናል፡፡
 በእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ 2012 ዓ/ም የአንደኛ ክፍል ጥቅል ቅበላ ምጣኔ 115% ለማድረስ 742,165
(ወንድ 6482፣ ሴት 6643) አዲስ አንደኛ ክፍል ተማሪዎች ተመዝግበው ይማራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ለ) የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ጥቅል ተሣትፎ

በ 2012 የትምህርት ዘመን ከ 1 ኛ-8 ኛ ክፍል ጠቅላላ 87671 (44118 ወንድ፣ 43553 ሴት) ተማሪዎችን ለማስተማር
የታቀደ ሲሆን ከእነዚህ መካከል 16862 (ወንድ 8244፣ ሴት 8618) አንደኛ ክፍል አዲስ ገቢ ተማሪዎች ሲሆኑ ቀሪዎቹ 70809
(ወንድ 35874፣ ሴት 34935) ደግሞ ከ 1 ኛ-8 ኛ ክፍል በ 2011 ዓ/ም ትምህርት ሲከታተሉ የነበሩ ነባር ተማሪዎች ናቸው፡፡
በ 2012 ዓ/ም በጠቅላላው የሚኖሩ ተማሪዎችን ብዛት የተሰላው የሚከተለውን ታሣቢ ተደርጎ ነው፡፡

 በ 2011 የትምህርት ዘመን ከ 1 ኛ-7 ኛ ክፍል በመማር ላይ ከነበሩት ተማሪዎች መካከል 70809 (ወንድ 35874፣ ሴት
34935) ተማሪዎች ወይም 96% ወደ ቀጣዩ የክፍል ደረጃ ተሸጋግረዋል ተብሎ ታሣቢ ተደርጓል፡፡
 በ 2011 ዓ/ም ከ 1 ኛ-7 ኛ ክፍል ይደግማሉ ወይም ትምህርት ያቋርጣሉ ተብለው ታሣቢ የተደረጉት 4% ተማሪዎች
ወይም 2832 (1435 ወንድ፣ 1397 ሴት) በነበሩበት ክፍል ገብተው እንዲማሩ ይደረጋል ተብሎ እሣቤ ተወስዷል፡፡
 በ 2011 ዓ/ም 8 ኛ ክፍል ይደግማሉ ተብለው ታሣቢ ከተደረጉት 208 (94 ወንድ፣ 114 ሴት) በነበሩበት 8 ኛ ክፍል
ገብተው እንዲማሩ ይደረጋል ተብሎ እሣቤ ተወስዷል፡፡
 በ 2012 ዓ/ም 16862 (ወንድ 8244፣ ሴት 8618) አዲስ የአንደኛ ክፍል ተማሪዎች ይኖራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

2.3.3. የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ፕሮግራም ተማሪዎች

ሀ) የአጠቃላይ 2 ኛ ደረጃ ትምህርት ፕሮግራም ተማሪዎች

12
የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት በሁለት ሣይክል የሚጠናቀቅ ሆኖ በመጀመሪያው ሣይክል (9 ኛ-10 ኛ ክፍል) የሚሰጠው
አጠቃላይ ትምህርት ተማሪዎች ተሰጥኦቸውን፣ ችሎታቸውን መርምረው የሚስማማቸውን የሙያ ዘርፍ ለመምረጥና
ለቀጣየዩ ትምህርትና ስልጠና፣ እንዲሁም በመጠነኛ ሥልጠና ወደ ምርት ተግባር ለመግባት የሚያስችላቸው ሆኖ የአጠቃላይ
2 ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ይሆናል፡፡ በዚህ ፕሮግራም በ 2012 የትምህርት ዘመን ለማስተማር የታቀደው 9422 (4301
ወንድ፣ 5121 ሴት) ተማሪዎችን ሲሆን ይህም የሚከተለውን ታሣቢ አድርጎ የተሰላ ነው፡፡

 በ 2011 የትምህርት ዘመን ከዞኖች በተሰበሰበው መረጃ መሠረት 9 ኛ ክፍል በመማር ላይ ከነበሩት 3718 (1676
ወንድ፣ 2042 ሴት) ተማሪዎች መካከል በሠራዊት ግንባታ አደረጃጀት መሠረት ስራዎችን በማከናወናችን የተነሣ
3569 (1609 ወንድ፣ 1960 ሴት) ተማሪዎች ወይም 96% ወደ ቀጣዩ የክፍል ደረጃ ተሸጋግረዋል ተብሎ ታሣቢ
ተደርጓል፡፡
 በ 2011 ዓ/ም በተለያዩ ምክንያቶች 9 ኛ ክፍል ይደግማሉ ወይም ትምህርት ያቋርጣሉ ተብለው ታሣቢ የተደረጉት
4% ወይም 149 (67 ወንድ፣ 82 ሴት) ተማሪዎች በ 2012 ዓ/ም ተመልሰው በድጋሚ ክፍል ገብተው እንዲማሩ
ይደረጋል ተብሎ እሣቤ ተወስዷል፡፡
 በ 2011 ዓ/ም የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ከወሰዱት 4591(ወንድ 2055፣ ሴት 2536) መደበኛ
ተማሪዎች መካከል 3902 (ወንድ 1747፣ ሴት 2155) ተማሪዎች ወይም 85% ወደ 9 ኛ ክፍል ይሸጋገራሉ ተብሎ
ይጠበቃል፡፡

ለ) የከፍተኛ ትምህርት መሠናዶ 2 ኛ ደረጃ ትምህርት ፕሮግራም ተማሪዎች

ይህ ፕሮግራም ተማሪዎች ከአጠቃላይ ትምህርት ጋር ተዛምዶ በሰለጠኑበት የሙያ ዘርፍ በቂ ችሎታና ክህሎች ኖሯቸው
በእርሻ፣ በምርት ቴክኖሎጂ፣ በኑሮ ዘዴ ሣይንስና በንግድ ሥራ በመሣሰሉት መሥራት እንዲችሉና ለከፍተኛ ትምህርት በብቃት
እንዲዘጋጁ ለማድረግ የተዘረጋ ነው፡፡ በዚህ ፕሮግራም በ 2012 የትምህርት ዘመን ለማስተማር የታቀደው 1722(868 ወንድ፣
854 ሴት) ተማሪዎችን ሲሆን ይህም የሚከተለውን ታሣቢ አድርጎ የተሰላ ነው፡፡

 በ 2011 ዓ/ም በመማር ላይ የነበሩ ሁሉም 649 (351 ወንድ፣ 298 ሴት) የ 11 ኛ ክፍል ተማሪዎች ወደ 12 ኛ ክፍል
ይሸጋገራሉ ተብሎ ታሣቢ ተደርጓል፡፡
 በ 2011 ዓ/ም የአጠቃለያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ አገር አቀፍ ፈተና ከወሰዱት 1738 (ወንድ 787፣
ሴት 951) መደበኛ ተማሪዎች መካከል 782 (ወንድ 354፣ ሴት 428) ተማሪዎች ወይም 45% ወደ 11 ኛ ክፍል
ይሸጋገራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

2.3.4. የልዩ ፍላጎት ትምህርት ፕሮግራም ተማሪዎች

በዚህ ፕሮግራም በ 2012 የትምህርት ዘመን ለማስተማር የታቀደው 216 (117 ወንድ፣ 99 ሴት) ተማሪዎች ሲሆኑ ዝርዝሩ
እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

ሀ) የመጀመሪያ ደረጃ ልዩ ፍላጎት ተማሪዎች

በ 2012 የትምህርት ዘመን በልዩ ፍላጎት ዩኒቶች ለማስተማር የታቀደው 214 (115 ወንድ፣ 99 ሴት) ተማሪዎችን ነው፡፡
ይህም የሚከተሉትን ታሣቢ ያደረገ ነው፡፡
13
 በ 2012 የትምህርት ዘመን እድሚያቸው ለመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት (1 ኛ-8 ኛ ክፍል) ትምህርት ከደረሱት 87671
(44118 ወንድ፣ 43553 ሴት) ህፃናት መካከል የልዩ ፍላጎት ትምህርት ፈላጊዎች 13151 (6618 ወንድ፣ 6533 ሴት)
ህፃናት ወይም 15% ናቸው ተብሎ ታሣቢ ተደርጓል፡፡
 በ 2011 የትምህርት ዘመን በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች (1 ኛ-8 ኛ ክፍል) በመማር ላይ ከነበሩት የልዩ ፍላጎት
ነባር ተማሪዎች መካከል 164(91 ወንድ፣ 73 ሴት) ትምህርታቸውን ይቀጥላሉ ተብሎ ታሣቢ ተደርጓል፡፡
 በ 2012 የትምህርት ዘመን እድሚያቸው ለመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት (1 ኛ-8 ኛ ክፍል) ከደረሱት የልዩ ፍላጎት
ህፃናት መካከል 50(24 ወንድ፣ 26 ሴት) አዲስ ገቢ ተማሪዎችን በመመዝገብ ለማስተማር ታቅዷል፡፡

ለ) የሁለተኛ ደረጃ ልዩ ፍላጎት ተማሪዎች

በ 2012 የትምህርት ዘመን 2 (ወንድ 2፣ ሴት 0) የልዩ ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎችን በዞናችን በሚገኙ ሁለተኛ ደረጃ
ት/ቤቶች ለማስተማር ታቅዷል፡፡ ዝርዝሩ እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

 በ 2012 የትምህርት ዘመን እድሚያቸው ለሁለተኛ ደረጃ (9 ኛ-12 ኛ ክፍል) ትምህርት ከደረሱት 11144 (5169
ወንድ፣ 5975 ሴት) ህፃናት መካከል የልዩ ፍላጎት ትምህርት ፈላጊዎች 1672 (776 ወንድ፣ 896 ሴት) ህፃናት ወይም
15% ናቸው ተብሎ ታሣቢ ተደርጓል፡፡
 በ 2012 የትምህርት ዘመን እድሚያቸው ለሁለተኛ ደረጃ (9 ኛ-12 ኛ ክፍል) ከደረሱት የልዩ ፍላጎት ህፃናት መካከል 2
(ወንድ 2፣ ሴት 0) ለማስተማር ታቅዷል፡፡

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በምዕራብ AMHARA NATIONAL REGIONAL STATE


ጎንደር ዞን አስተዳደርማህበራዊ ልማት መምሪያ WESTE GONDAR ZONE ADIMNSETERATION
የትምህርት ጉዳዮች ክትትል ዋና የስራ ሂደት
SOCIAL DEVELOPMENT DEPARETEMNET
EDUCATIONAL AFFAIRS KORE PROCESE

ቁጥር ምዕ/ጎን/ ት/ት/ ጉ/1223/35


ቀን 07/10/2011 ዓ.ም

ለመተማ ወረዳ ት/ጽ/ቤት


ለቋራ ወረዳ ት/ጽ/ቤት
ለም/አርማጭሆ ወረዳ ት/ጽ/ቤት
ለአዳኝአገር ጫቆ ወረዳ ት/ጽ/ቤት
ለገንዳ-ውኃ ከተማ አሰተዳደር ት/ጽ/ቤት
ገንዳውኃ
14
ጉዳዩ፡- የ 2012 በእየርከኑ የሚማሩ ተማሪዎች ረቂቅ ዕቅድ መላክን ይመለከታል
ከላይ በርዕሱ እንደተገለፀው በምዕ/ጎንደር ዞን ስር በሚገኙ ወረዳዎች የመደበኛ፣ የቅድመ መደበኛ ና
የጎልማሳ አዲስና ነባር ተማሪዎች ረቂቅ ዕቅድ ክልል ት/ቢሮ በላከልን መሰርት አደራጅተን 24 ገጽ የላክን
መሆኑን እንገልፃለን፡፡

//ከሰላምታ ጋር;//

ቅጅ
ለእቅድ ዝግጅትና ግምገማ ባለሙያ
ገንዳ-ውኃ

ጥራት ያለው ትምህርት ለሁሉም!! ኤች ኤይ ቪ/ኤድስን እንግታ!!


QULITY EDUCATION FOR ALL!! STOP HIV/AIDS!!

15
ሰኔ/2012 ዓ.ም

ገንዳ-ውኃ

16
አባሪ አንድ፣ በ 2012 ዓ/ም በአፀደ ህፃናት ተቋማት የሚማሩ ተማሪዎች ዕቅድ
የመዋእለ ህፃናት ተማሪዎች ጠቅላላ የቅድመ መደበኛ ተማሪዎች
ብዛት የኦ ክፍል ተማሪዎች ብዛት ብዛት
  ተ.ቁ ወረዳ ወንድ ሴት ድምር ወንድ ሴት ድምር ወንድ ሴት ድምር
1 Adagne Ager Chako 208 223 431 208 223 431
2 Gende wuha 179 166 345 332 351 683 511 517 1,028
3 Metema 250 246 496 2,779 2,761 5,540 3,029 3,007 6,036
4 Mirab Armachiho 1,639 1,682 3,321 1,639 1,682 3,321
5 Negade Bahir
6 Quara 54 47 101 2,731 2,795 5,526 2,785 2,842 5,627
Mirab Gonder 483 459 942 7,689 7,812 15,501 8,172 8,271 16,443

አባሪ ሁለት፣ በ 2012 ዓ/ም እድሚያቸው 7 ዓመት የሞላቸው አንደኛ ክፍል አዲስ ገቢ (ንጥር ቅበላ) ተማሪዎች ዕቅድ
የአንደኛ ክፍል ንጥር ቅበላ
  ተ.ቁ ወረዳ ወንድ ሴት ድምር
1 Adagne Ager Chako 661 861 1,522
2 Gende wuha 374 246 620
3 Metema 2,236 2,268 4,504
4 Mirab Armachiho 1,018 885 1,903
5 Negade Bahir
6 Quara 1,865 2,101 3,966
Mirab Gonder 6,154 6,361 12,515

አባሪ ሦስት፣ በ 2012 ዓ/ም ከ 1 ኛ-4 ኛ ክፍል መማር የሚገባቸው ተማሪዎች ዕቅድ
1 ኛ ክፍል 2 ኛ ክፍል 3 ኛ ክፍል 4 ኛ ክፍል ጠቅላላ 1 ኛ-4 ኛ ክፍል
 ተ.ቁ ወረዳ ወንድ ሴት ወንድ ሴት ድምር ወንድ ሴት ድምር ወንድ ሴት ድምር
1 Adagne Ager Chako 688 883 676 544 432 413 227 309 2,023 2,149 4,172
2 Gende wuha 387 258 320 296 275 287 207 237 1,189 1,078 2,267
3 Metema 2,372 2,381 3,361 2,824 2,896 2,511 2,250 2,202 10,879 9,918 20,797
4 Mirab Armachiho 1,051 917 828 793 795 734 637 645 3,311 3,089 6,400
5 Negade Bahir 24 21 596 511 449 388 264 261 1,334 1,180 2,514
6 Quara 1,984 2,204 2,973 2,582 2,888 2,701 2,291 2,209 10,136 9,696 19,832
Mirab Gonder 6,482 6,643 8,158 7,039 7,286 6,646 5,612 5,602 27,538 25,930 53,468

17
አባሪ አራት፣ በ 2012 ዓ/ም ከ 5 ኛ-8 ኛ ክፍል መማር የሚገባቸው ተማሪዎች ዕቅድ
5 ኛ ክፍል 6 ኛ ክፍል 7 ኛ ክፍል 8 ኛ ክፍል ጠቅላላ 5 ኛ-8 ኛ ክፍል
 ተ.ቁ ወረዳ ወንድ ሴት ወንድ ሴት ወንድ ሴት ወንድ ሴት ወንድ ሴት ድምር
1 Adagne Ager Chako 177 230 111 147 80 135 42 99 410 611 1,021
2 Gende wuha 235 230 258 272 221 243 200 221 914 965 1,879
3 Metema 2,083 1,998 1,781 1,940 1,343 1,597 1,101 1,286 6,309 6,821 13,130
4 Mirab Armachiho 818 708 825 772 641 594 542 534 2,826 2,607 5,433
5 Negade Bahir 212 206 157 190 120 176 81 136 570 708 1,278
6 Quara 2,126 2,189 1,706 1,738 1,299 1,510 990 1,183 6,122 6,619 12,741
Mirab Gonder 5,439 5,355 4,681 4,869 3,585 4,078 2,875 3,323 16,580 17,623 34,203

አባሪአምስት፣በ 2012 ዓ/ምከ 1 ኛ-8 ኛክፍልመማርየሚገባቸውተማሪዎችዕቅድ


ከ 1 ኛ-4 ኛክፍል ከ 5 ኛ-8 ኛክፍል ጠቅላላከ 1 ኛ-8 ኛክፍል
 ተ.ቁ ወረዳ ወንድ ሴት ወንድ ሴት ወንድ ሴት ወንድ ሴት ድምር
1 Adagne Ager Chako 2,023 2,149 4,172 410 611 1,021 2,433 2,760 5,193
2 Gende wuha 1,189 1,078 2,267 914 965 1,879 2,103 2,043 4,146
3 Metema 10,879 9,918 20,797 6,309 6,821 13,130 17,188 16,739 33,927
4 Mirab Armachiho 3,311 3,089 6,400 2,826 2,607 5,433 6,137 5,696 11,833
5 Negade Bahir 1,334 1,180 2,514 570 708 1,278 1,904 1,888 3,792
6 Quara 10,136 9,696 19,832 6,122 6,619 12,741 16,258 16,315 32,573
Mirab Gonder 27,538 25,930 53,468 16,580 17,623 34,203 44,118 43,553 87,671

አባሪ ስድስት፣ የ 2012 የትምህርት ዘመን የልዩ ፍላጎት የተማሪዎች ዕቅድ


የመጀመሪያ ደረጃ ልዩ ፍላጎት
ተማሪዎች የ 2 ኛ ደረጃ የልዩ ፍላጎት ተማሪዎች
 ተ.ቁ ወረዳ ወንድ ሴት ወንድ ሴት ወንድ ሴት
1 Adagne Ager Chako 3 3 6
2 Gende wuha 4 5 9 2 0 2
3 Metema 59 50 109 0 0 0
4 Mirab Armachiho 36 26 62 0 0 0
5 Negade Bahir
6 Quara 13 15 28 0 0 0
Mirab Gonder 115 99 214 2 0 2

አባሪ ሰባት፣ በ 2012 ዓ/ም ከ 9 ኛ-10 ኛ ክፍል መማር የሚገባቸው ተማሪዎች ዕቅድ
18
9 ኛ ክፍል 10 ኛ ክፍል ጠቅላላ ከ 9 ኛ-10 ኛ ክፍል
ተ.ቁ ወረዳ ወንድ ሴት ወንድ ሴት ወንድ ሴት ድምር
1 Adagne Ager Chako - - - - - - -
2 Gende wuha 231 285 479 604 710 889 1,599
3 Metema 727 864 425 351 1,152 1,215 2,367
4 Mirab Armachiho 409 395 204 226 613 621 1,234
5 Negade Bahir 409 395 204 226 613 621 1,234
6 Quara 709 963 504 812 1,213 1,775 2,988
Mirab Gonder 2,485 2,902 1,816 2,219 4,301 5,121 9,422

አባሪ ስምንት፣ በ 2012 ዓ/ም ከ 11 ኛ-12 ኛ ክፍል መማር የሚገባቸው ተማሪዎች ዕቅድ
11 ኛ ክፍል 12 ኛ ክፍል ጠቅላላ 11 ኛ-12 ኛ ክፍል
ተ.ቁ ወረዳ ወንድ ሴት ወንድ ሴት ወንድ ሴት ድምር
1 Adagne Ager Chako - - - - - - -
2 Gende wuha 98 101 123 105 221 206 427
3 Metema 112 130 31 16 143 146 289
4 Mirab Armachiho 90 95 125 99 215 194 409
5 Negade Bahir 29 21 80 51 109 72 181
6 Quara 109 168 71 68 180 236 416
Mirab Gonder 438 515 430 339 868 854 1,722

አባሪ ዘጠኝ፣ የ 2012 የትምህርት ዘመን የተቀናጀ ተግባር ተኮር የጎልማሶች የተሣታፊዎች ዕቅድ
የአንደኛ አመት ተሣታፊዎች የሁለተኛ አመት
የኮንትራት
እቅድ ተሣታፊዎች እቅድ አንደኛና ሁለተኛ አመት እቅድ
የጣቢያ አመቻቾች
ተ.ቁ ወረዳ ዕቅድ ዕቅድ ወንድ ሴት ወንድ ሴት ወንድ ሴት ድምር
1 Adagne Ager Chako 67 30 1,506 888 2,394
2 Gende wuha 8 7 15 58 11 40 26 98 124
3 Metema 135 135 1241 1004 807 558 2048 1562 3610
4 Mirab Armachiho 48 28 1072 1288 1418 1405 2490 2693 5183
5 Negade Bahir 0 0 0
6 Quara 70 118 1825 938 1565 761 3390 1699 5089
Mirab Gonder 328 318 4153 3288 3801 2764 9460 6940 16400

19
አባሪ አስር፣ በ 2012 ዓ/ም እድሚያቸው ከ 4-6 ዓመት የሆናቸው ህፃናት ብዛት
ተ.ቁ ወረዳ ወንድ ሴት ድምር
1 Adagne Ager Chako 2,107 2,088 4,195
2 Gende wuha 913 1,350 2,263
3 Metema 6,863 6,957 13,820
4 Mirab Armachiho 3,053 3,026 6,079
5 Negade Bahir
6 Quara 6,571 6,973 13,544
Mirab Gonder 19,507 20,394 39,901

አባሪ አስራ አንድ፣ በ 2012 ዓ/ም እድሚያቸው 7 ዓመት የሆናቸው ህፃናት ብዛት
ተ.ቁ ወረዳ ወንድ ሴት ድምር
1 Adagne Ager Chako 661 861 1,522
2 Gende wuha 374 246 620
3 Metema 2,236 2,268 4,504
4 Mirab Armachiho 1,018 885 1,903
5 Negade Bahir
6 Quara 1,865 2,101 3,966
Mirab Gonder 6,154 6,361 12,515

አባሪ አስራ ሁለት፣ በ 2012 ዓ/ም እድሚያቸው 7-10 ዓመት የሆናቸው ህፃናት ብዛት
ተ.ቁ ወረዳ ወንድ ሴት ድምር
1 Adagne Ager Chako 2,959 2,915 5,874
2 Gende wuha 1,320 1,362 2,682
3 Metema 8,248 8,347 16,595
4 Mirab Armachiho 3,295 3,625 6,920
5 Negade Bahir
6 Quara 7,819 8,499 16,318
Mirab Gonder 23,641 24,748 48,389

20
አባሪ አስራ ሦስት፣ በ 2012 ዓ/ም እድሚያቸው 11-14 ዓመት የሆናቸው ህፃናት ብዛት
ተ.ቁ ወረዳ ወንድ ሴት ድምር
1 Adagne Ager Chako 2,820 2,474 5,294
2 Gende wuha 1,038 616 1,654
3 Metema 7,284 6,104 13,388
4 Mirab Armachiho 2,677 1,797 4,474
5 Negade Bahir
6 Quara 7,735 6,562 14,297
Mirab Gonder 21,554 17,553 39,107

አባሪ አስራ አራት፣ በ 2012 ዓ/ም እድሚያቸው 7-14 ዓመት የሆናቸው ህፃናት ብዛት
ተ.ቁ ወረዳ ወንድ ሴት ድምር
1 Adagne Ager Chako 5,779 5,389 11,168
2 Gende wuha 2,358 1,978 4,336
3 Metema 15,532 14,451 29,983
4 Mirab Armachiho 5,972 5,422 11,394
5 Negade Bahir
6 Quara 15,554 15,061 30,615
Mirab Gonder 45,195 42,301 87,496

አባሪ አስራ አምስት፣ በ 2012 ዓ/ም እድሚያቸው 15-16 ዓመት የሆናቸው ህፃናት ብዛት
ተ.
ቁ ወረዳ ወንድ ሴት ድምር
1 Adagne Ager Chako 1,355 1,185 2,540
2 Gende wuha 420 830 1,250
3 Metema 3,104 3,699 6,803
4 Mirab Armachiho 1,214 1,286 2,500
5 Negade Bahir
6 Quara 3,488 3,834 7,322
Mirab Gonder 9,581 10,834 20,415

አባሪ አስራ ሰባት፣ በ 2012 ዓ/ም እድሚያቸው 4-6 ዓመት የሆናቸው የልዩ ፍላጎት ያላቸው የቅድመ መደበኛ ትምህርት ፕሮግራም አገልግሎት ፈላጊ ህፃናት ብዛት

21
ተ.ቁ ወረዳ ወንድ ሴት ድምር
1 Adagne Ager Chako 316 313 629
2 Gende wuha 137 202 339
3 Metema 1,030 1,044 2,074
4 Mirab Armachiho 458 454 912
5 Negade Bahir
6 Quara 986 1,046 2,032
Mirab Gonder 2,927 3,059 5,986

አባሪ አስራ ስምንት፣ በ 2012 ዓ/ም እድሚያቸው 7-14 ዓመት የሆናቸው የልዩ ፍላጎት ያላቸው የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ፕሮግራም አገልግሎት ፈላጊ ህፃናት ብዛት
ተ.ቁ ወረዳ ወንድ ሴት ድምር
1 Adagne Ager Chako 1,217 1,285 2,502
2 Gende wuha 379 900 1,279
3 Metema 3,475 4,343 7,818
4 Mirab Armachiho 1,576 2,271 3,847
5 Negade Bahir
6 Quara 3,830 3,210 7,040
Mirab Gonder 10,477 12,009 22,486

አባሪ አስራ ዘጠኝ፣ በ 2012 ዓ/ም እድሚያቸው 15-18 ዓመት የሆናቸው የልዩ ፍላጎት ያላቸው የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ፕሮግራም አገልግሎት ፈላጊ ህፃናት ብዛት
ተ.ቁ ወረዳ ወንድ ሴት ድምር
1 Adagne Ager Chako 386 371 757
2 Gende wuha 120 260 380
3 Metema 987 1,206 2,193
4 Mirab Armachiho 419 534 953
5 Negade Bahir
6 Quara 1,098 1,057 2,155
Mirab Gonder 3,010 3,428 6,438

22

You might also like