You are on page 1of 54

የትምህርት ምዘናና ግምገማ

በቅድመ መደበኛ ትምህርት


ቤቶች

Epsy 242
ለቅድመ መደበኛ መምህራን ስልጠና የተዘጋጀ ሞጁዩል
ለመጀመሪያ ደረጃ መምህራን ለማሰልጠኛነት የተዘጃጀ ሞጁዩል

ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ


የስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል
2009 ዓ.ም
 

ምዘና እና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርትቤት ህጻናት


Assessment and Evaluation of Preschool  
Children
(AEPC-202)

i
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች

ምዘና እና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርትቤት ህጻናት


Assessment and Evaluation of Preschool
Children
(AEPC-202)

ለቅድመ መደበኛ መምህራን ስልጠና የተዘጋጀ ሞጁዩል


መጠነ ግብር፡ 2
አዘጋጆች፡
1. አቶ ታደለ ጌቴ እና
2. አቶ ዘላለም አዲስ

መጋቢት 2009 ዓ.ም


ደብረማርቆስ
 
ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል
ii
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች

መግቢያ.........................................................................................................................................................1
የትምህርቱ አላማዎች.....................................................................................................................................1
ክፍለ ትምህርት አንድ፡.....................................................................................................................................3
1. የትምህርት ምዘና እና ግምገማ መሰረታዊ ጽንሰ-ሃሳቦች...................................................................................3
1.1 የምዘና፤ልኬታና ግምገማ መሠረታዊ ጽንሰ-ሃሳቦች....................................................................................3
1.1.1. ምዘና፣ ልኬታ እና ግምገማ..............................................................................................................3
1.1.2. የድንገተኛ ሙከራ፣ ሙከራና ፈተና ንጽጽር.......................................................................................6
1.2 መማርን የመመዘንና የመገምገም ዓላማዎች.............................................................................................7
1.3 የመማር ምዘናና ግምገማ ትግበራ መርሆዎች/ Principles........................................................................11
1.4 የምዘና አይነቶች.................................................................................................................................12
1.4.1 ተከታታይ ምዘና (Continuous Assessment)..................................................................................12
1.4.2. የብቃት ምዘና (Authentic Assessment)......................................................................................14
1.5 ሂደታዊ ተከታታይ ምዘና የአተገባበር ችግሮች.................................................................................................15
የምዕራፉ ማጠቃለያ.................................................................................................................................16
የክፍለ ትምህርት አንድ ማጠቃለያ ጥያቄዎች...............................................................................................16
ክፍለ ትምፍርት ሁለት...................................................................................................................................17
2. የቅድመ መደበኛ ትምህርት ምዘና ባህርያት...................................................................................................17
2.1 ተከታታይ ምዘና..................................................................................................................................17
2.1.1. ሂደታዊ ተከታታይ ምዘና (ሂተም)...................................................................................................17
2.1.2 አጠቃላይ ተከታታይ ምዘና (አተም)................................................................................................18
2.1.3 የተከታታይ ምዘና አተገባበር መርሆዎች (ጠቃሚ ነጥቦች).................................................................19
የክፍለ ትምህርት ሁለት ማጠቃለያ ጥያቄዎች..............................................................................................23
ቀጥሎ በቀረቡት የመወያያ ጥያቄዎች ላይ ለ 20 ደቂቃ ያህል ውይይት በማድረግ ለክፍሉ ተማሪዎች በማብራራት
አቅርቡ....................................................................................................................................................23
ክፍለ ትምህርት ሶስት....................................................................................................................................24
3. የቅድመ መደበኛ ትምህርት ምዘና ስልቶች....................................................................................................24
3.1 መደበኛና መደበኛ ያልሆኑ የምዘና ስልቶች..................................................................................................24
3.2. የብቃት ምዘና ስልቶች (Tools of authentic assessment).....................................................................25
3.3 ግለ ምዘናና የአቻ ምዘና........................................................................................................................26
3.3.1. ግለ-ምዘና/ Self-Assessment.......................................................................................................26

ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል


iii
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች

3.3.2. የአቻ ምዘና/ Peer assessment.....................................................................................................27


ክፍለ-ትምህርት አራት...................................................................................................................................29
4. የቅድመ-መደበኛ ህጻናት የመዳበር ዘርፎችን የመመዘኛ ስልቶች.......................................................................29
የመማር ውጤቶች፡.......................................................................................................................................29
4.1. አካላዊና የአካላዊ እንቅስቃሴ የመዳበር ምንነትና የምዘና ስልቶች..............................................................29
4.2. አዕምሮአዊ መዳበርንና የቋንቋ ችሎታን የመመዘኛ ስልቶች......................................................................32
4.3 የማህበራዊና ስሜታዊ መዳበር መመዘኛ ስልቶች.....................................................................................36
የክፍለ ትምህርት ሶስት የማጠቃለያ ተግባራት..............................................................................................39
ክፍለ ትምህርት አምስት................................................................................................................................40
4. የጽሑፍ ፈተና አዘገጃጀት..........................................................................................................................40
5.1 የጽሁፍ ፈተናን ማቀድ.........................................................................................................................40
5.1.1 የፈተናዉን ዓላማ መወሰን.............................................................................................................41
5.1.2 የመማር ማስተማር አላማዎችን መምረጥ.......................................................................................42
5.1.3 ዝርዝር ሠንጠረዥ ማዘጋጀት.........................................................................................................42
5.1.4 የፈተና ጥያቄ አይነቶችን መምረጥ.................................................................................................44
5.1.5 የፈተና ጥያቄዎችን ማዘጋጀት.............................................................................................................45
5.3. ፈተና መፈተን ማረምና ዉጤቱን መመዝገብ..........................................................................................51
የክፍለ ትምህርት አምስት ማጠቃለያ ጥያቄዎች...........................................................................................53

ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል


iv
መግቢያ
ይህ ትምህርት ተገቢ መረጃን እና ድጋፍ አሰጣጥን በመጠቀም የህጻናትን መማር በማሻሻል ላይ ትኩረት
ይሰጣል፡፡ ተገቢ ከሆነ ውሳኔ ላይ ለመድረስ የሚረዳ መረጃ ለማግኘት ምዘና እንዴት ተግባራዊ ይደረጋል በሚሉ
ነጥቦች ላይ ያተኩራል፡፡ ስለሆነም የምዘና ትርጉም፣ የምዘና ስልቶችና መርሆዎች ምንነት፣ የምዘና ስልት
አይነት (ሂደታዊና አጠቃላይ)፣ የፈተና ጥያቄ አዘገጃጀትን፣ የማረምና ትርጉም መስጠትን፣ መረጃን
መጠቀምን የተመለከቱ ነጥቦች በትምህርቱ ትኩረት የሚሰጥባቸው ዋና ዋና ነጥቦች ናቸው፡፡ የዚህ ትምህርት
ዋና መርህ “ምዘና ለመማር” (assessment for learning) ፤ዋና ትኩረቱም በሂደታዊ የምዘና ስልቶች በተለይም
በምልከታ፣ ፖርትፎሊዮ፣ ግለ-ምዘና በአጠቃላይ በብቃት ምዘና ላይ ነው፡፡ በዚህ ትምህርት ሂደታዊ ተከታታይ
ምዘና ስልቶችን በመጠቀም የህጻናትን አእምሮአዊ፣ አካላዊ፣ ስሜታዊና ማህበራዊ የመዳበር ለውጦችን
ለማምጣት ምዘናን ተግባራዊ በማድረግ በመማር ዙሪያ ተገቢ ውሳኔን በማሳለፍ በመተግበር ላይ ትኩረት
ይሰጣል፡፡ ትምህርቱ ፋይዳ እንዲኖረው በምዘናው ሂደት ህጻናትን በማሳተፍ ላይ ያተኩራል፤ ኮርሱ የሚሰጥበት
አግባብም ከህጻናት የእድገት ደረጃ ጋር የተጣጣመ፣ ከቅድመ መደበኛ ትምህርት አሰጣጥ መርሆችን መሰረት
ያደረገ ይሆናል፡፡

ተከታታይ ምዘና በተገቢ መልኩ ተግባራዊ ሳይደረግ ሁሉም ህጻናት -ተማሪዎች እኩል የመማር እድል እንዲኖራቸው ማድረግ
አይቻልም፡፡ ስለሆነም ይህ ኮርስ የትምህርት ግቦቻችንን ዳር ለማድረስ እና የተሟላ ስብዕና የተላበሱ ዜጎችን ለማፍራት ተከታታይ
ምዘና የሚጫወተውን ሚና በጥልቀት የምንረዳበትና ይሆናል፡፡

የትምህርቱ አላማዎች
ትምህርቱን በሚገባ ተምረው ካጠናቀቁ በኋላ ሰልጣኞች፡
 የህጻናትን መማር ምዘናን የተመለከቱ ንድፈ ሃሳቦችን ይረዳሉ፤
 የተከታታይ ምዘና መረጃን በመጠቀም የህጻናት መማር እና መዳበር የተሻለ እንዲሆን ጥረት
ያደርጋሉ፣
 ተከታታይ ምዘናን በመጠቀም የህጻናትን የመማርና ሌሎች እገዛ የሚሹ ፍላጎቶችን ይለያሉ፣
 የተለያዩ የመማር ፍላጎት እና የመማር ስልት ላላቸዉ ህጻናት ተስማሚ የሆኑ የምዘና ስልቶችን
በመምረጥ ይጠቀማሉ፣
 ምዘናን ተከትሎ መማርና የህጻናት መዳበርን በተመለከተ ምን መስራት እንዳለባቸው ይለያሉ፣
 የህጻናትን መማርና የልጆች መዳበርን በመመዘን ሂደት መምህራን ሊከተሏቸው የሚገቡ የስነምግር
ደንቦችና መርሆዎችን ይረዳሉ፣
 ከህጻናቱ እና ከወላጆቻቸው/ አአሳዳጊዎቻቸው ጋር በምን መንገድ ግንኙነት መፍጠር እንዳለባቸው
ይረዳሉ፣

i
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች

 የሚከሰቱ አውንታዊ ለውጦች ቀጣይነት እንዲኖራቸው ልጆችንና ወላጆቻቸውን በየዎቅቱ


የማነቃቃት ክህሎትን ያዳብራሉ፣
 አጠቃላይ ተከታታይ ምዘናን በጥራት ተግባራዊ በማድረግ ጥራት ያለው መረጃን መያዝና ሪፖርት
ማድረግ ይችላሉ፡፡

ክፍለ ትምህርት አንድ፡


1. የትምህርት ምዘና እና ግምገማ መሰረታዊ ጽንሰ-ሃሳቦች
የክፍለ ትምህርቱ የመማር ዓላማዎች
ይህንን ክፍለ ትምህርት ከተማሩ በኋላ ሠልጣኞች፡
 የሙከራ፣ ምዘና፣ ልኬታና ግምገማን ትርጉም ይገልጻሉ፤
 የህጻናት ምዘናና ግምገማ ዓላማዎችን ያብራራሉ፤

ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል


ii
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች

 የህጻናትን መማር የተመለከተ ምዘናና ግምገማን መርሆዎችን ይለያሉ፤


 የህጻናትን መማር የመመዘንና የመገምገም አይነቶችን ያስረዳሉ፤
መግቢያ

ይህ ክፍለ ትምህርት የህጻናትን የመማር ሁኔታ በተመለከተ የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም መረጃ ማሰባሰብን፣ በመረጃው
መሰረት የህጻናትን መማር የተመለከቱ ውሣኔዎችን መወሰንና ድጋፍ መስጠትን የተመለከቱ ሃሳቦችን የምናይበት ነው፡፡ ውሳኔዎቹም
የመማር ማስተማሩን ሂደት ማሻሻል፤ የተማሪዎችን መሰረታዊ ክህሎቶች የማሳደግ፣ ወይም ብቃታቸውን ከማረጋገጥ ጋር
የተዛመዱ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ይህ ክፍለ ትምህርት ለትምህርቱ ቁልፍ የሆኑ ዋና ዋና ቃላቶችን ትርጉም፤ የተከታታይ ምዘና ባህሪያትንና
ግቦችን በጥልቀት የምንማርበት ነው፡፡

1.1 የምዘና፤ልኬታና ግምገማ መሠረታዊ ጽንሰ-ሃሳቦች


1.1.1. ምዘና፣ ልኬታ እና ግምገማ
የምዘና ጽንሰ-ሃሰብ (Assessment)፡- ምዘና ምንድነው? ምዘና ስለህጻናት መዳበር፣ መማር፣ ጤና፣ ባህርይ፣ የትምህርት
ግስጋሴ፣ የልዩ ድጋፍ ፍላጎት እና ስኬት የተመለከቱ መረጃዎችን የማሰባሰብ ሂደት ነው፡፡ ህጻናትን በተሻለ ለመረዳትና
ለመቅረጽ በማሰብ መረጃን የማሰባሰብ፣ የማደራጀት፣ የመተንተንና ትርጉም የመስጠት ሂደት ነው፡፡ በምዘና ሂደት የተለያዩ መደበኛ
(Formal)፣ መደበኛ ያልሆኑ (Informal) ወይም ሁለቱንም የመረጃ መሰብሰቢያ ስልቶች ተግባራዊ ማድረግ ይቻላል፡፡
የሚሰበሰበውም መረጃ መጠናዊ (quantitative)፣ አይነታዊ (qualitative) ወይም ሁለቱም ሊሆን ይችላል፡፡ ምዘና በተለያዩ
ደረጃዎች ተግባራዊ ሊደረግ ይችላል፡፡ ለምሳሌ በክፍል ዉስጥ በመምህራን ደረጃ፣ በትምህርት ቤት ደረጃ፣ ወይም ከዚያ
በላይ፤ ህጻናት በመማር ያመጡትን የባህርይ ለውጥ ለመረዳት፣ የተሻለ እንዲማሩ የእገዛ ሁኔታን ለማመቻቸት ታስቦ
ተግባራዊ ሊደረግ ይችላል፡፡ ለመማር ማስተማሩ ሂደት መሻሻል ትርጉም ያለዉ መረጃ የሚገኘዉ መምህራን
በየክፍላቸዉ ከሚያደርጉት ምዘና ነዉ፡፡

ተግባር፡- በሚከተለው ምስል የምታዩት የአንድ ተማሪን የባህርይ ለውጥን በተመለከተ በምን በምን የመረጃ መሰብሰቢያ
ዘዴዎች መረጃ እንደምናገኝ ነው፡፡
1. ሌሎች ተጨማሪ የምዘና ስልቶችን ጠቁሙ
2. የተጠቀሱትን እና ተጨማሪ ስልቶችን መደበኛና መደበኛ ያልሆኑ በማለት ፈርጁ፡፡

ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል


iii
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች

በክፍል መምህራን የሚደረግ ምዘና ከላይ በህጻን አልማዝ ላይ እንደተደረገዉ ሁሉ የተለያዩ የምዘና ስልቶችን በመጠቀም
መረጃ መሠብሰብ፣ መረጃዉን መተንተን እና ሁኔታዉን ሊያሻሽል የሚያስችል ዉሳኔ መስጠትን የሚያመለክት ጽንሰ
ሃሳብ ነዉ፡፡ ለምሳሌ ስለህጻኗ የሰበሰብነዉ መጠናዊና አይነታዊ መረጃ ጉብዝናዋን የሚያመላክት ከሆነ ዉሳኔያችን
አልማዝን ለሌሎች ጓደኞቿ የተማሪ አስተማሪ አድርጎ መመደብ አንዱ ሊሆን ይችላል፡፡

የልኬታ (measurement)፡- ልኬታ ወይም ሰፈራ ምንድነው? ልኬታ የህጻናትን እዕምሮአዊ፣ አመለካከታዊ ክህሎታዊ ለውጥ
የተመለከተ መረጃን በመጠን (በቁጥር) የማግኘት ሂደት ነው፡፡ ልኬታ መረጃን በመጠን ለመግለጽ የተወሰነ የአሰራር ህግን
ይጠቀማል፡፡ ለምሳሌ አንድ ህጻን የሩጫ ፍጥነቱን በተመለከተ በሰከንድ ምን ያህል ሜትር እንደሚሮጥ በመለካት መናገር ወይም
መረጃን መያዝ እንችላለን፡፡ የትምህርቱን አላማዎች መሰረት ተደርጎ የተዘጋጀ ሙከራን ወይም ሌላ የብቃት ምዘናን በመጠቀም
የህጻናትን እውቀት፣ ግንዛቤ ወይም ክህሎት በመጠን ወይም በቁጥር እንገልጻለን፡፡ ይኸውም ህጻኑ/ኗ 10 ከ 10፣ 8 ከ 10
ወይም ሌላ አመጣ/ች በማለት ሊገለጽ ይችላል፡፡ ልኬታ መረጃን ለመግለጽና ስርዓት ለማስያዝ ቁጥርን ይጠቀማል፡፡ ልኬታ
መረጃዎችን በአይነት አይገልጽም፤ በተጨማሪም ግምገማ ማድረግን አያካትትም፡፡ ልኬታ “ምን ያህል ነው?” የሚል ጥያቄን
በመመለስ ላይ ያተኩራል፡፡ ስለሆነም ልኬታን ብቻ በመጠቀም ሁሉንም የተማሪዎች የመማር ባህሪ መመዘን አይቻልም፡፡

የግምገማ (Evaluation)፡- ግምገማ ምንድነው? ግምገማ መረጃ በመሰብሰብ ለተሰበሰበው መረጃ ትርጉም የመስጠት
ሂደት ነው፡፡ ግምገማ ተማሪዎች የተነደፉ የትምህርቱ አላማዎችን በምን ያህል ከግብ እንዳደረሷቸው ለማወቅ የሚደረግ
ስልታዊ አካሄድ ነው፡፡

የአንድ/ዲት ህጻን በመማር የመለወጡ/ጧ ሁኔታ ተገምግሞ ከቀደመ የህጻኑ/ኗ የራስ ስራ ጋር (Self-referenced)፣
በቡድኑ ካሉ ሌሎች ህጻናት ስራ ጋር (Norm-referenced) ወይም ከትምህርቱ አላማ (ከመስፈርቱ) አንጻር (Criterion
referenced) ታይቶ/ ተወዳድሮ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ግምገማ የህጻናትን መማር ብቻ ሳይሆን፣ የትምህርት ፕሮግራሞች እና የመማር
ማስተማሩን ጥራት፣ ጠቃሚነትና አስፈላጊነት ላይም አስተያየት ለመስጠት ይረዳል፡፡

በአጠቃላይ አነጋገር ግምገማ፡-

ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል


iv
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች




 ስልታዊ አካሄድን ይከተላል ማለት ግብታዊ፣ ያለእቅድ የሚደረግ አካሄድን ያስዎግዳል፤ የውጤቱን ትክክለኛነት የሚያዛቡ
ተለዋዋጮችን ይቆጣጠራል፤
 የትምህርቱ አላማዎች ቀድመው በታወቁበት ሁኔታ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡ አላማዎች ቀድመው ሳይታዎቁ የተማሪዎችን መማርና
የጥራት ደረጃ መለካት አይቻልም፡፡

ግምገማ ‘በምን ያህል ጥራት?’ የሚል ጥያቄን ሲመልስ፣ ልኬታ ደግሞ ‘በምን ያህል መጠን?’ የሚል ጥያቄን ይመልሳል፡፡ ግምገማ
ከልኬታ በተሻለ አጠቃላይና ሁሉን አቀፍ ነው፡፡ ይኸውም መጠናዊ እና አይነታዊ መረጃዎችን በመጠቀም ውጤቱን መግለጽ ብቻ
ሳይሆን መረጃውን በመጠቀም ለባህሪው ትርጓሜ ይሰጣል፣ ያወዳድራል፤ ይፈርጃል፡፡ ይሁንና ግምገማና ልኬታ የማይለያዩ የአንድ
ሳንቲም ሁለት ገጽታዎች እንደሆኑ መረዳት ይቻላል፡፡ ልኬታ በባህሪው የተለመደ ግልጽ አካሄድን በመከተል መጠናዊ መረጃን
ያሰባስባል፤ ግምገማ በልኬታ የተገኘንና ሌሎች መረጃዎችን በመውሰድ ከትምህርቱ አላማዎች ጋር በማገናዘብ እንደ ሁኔታው
እያመዛዘነ በማየት ለባህሪው ደረጃ ያወጣል፣ ያወዳድራል ወይም በቅደም ተከተል ያስቀምጣል፡፡ ስለዚህ ግምገማ ባህሪን
በቁጥር እና በአይነት ከመግለጽ በተጨማሪ ስለስራዉ ጥራት አስተያየት መስጠትንም (Value judgement) ያካትታል፡፡

የመወያያ ጥያቄ
ሀ. -ልኬታ፣ ግምገማና ምዘና አንዱ በሌላው ስር ሊካተት ከመቻሉ አንጻር አይታችሁ ከምስሉ ከተለያዩ ክፍሎች ጋር አዛምዱ፡፡
ለተግባራችሁ ተገቢ ምክንያት ስጡ

ለ. የሚከተሉት ሃሳቦች እያንዳንዳቸው ምዘናን ወይም ግምገማን የቱን እንደሚያመለክቱ በመለየት መልሳችሁን
ለመምህራችሁ ተናገሩ!
1. በአመዛኙ የመማር- ማስተማርን ሂደት በማሻሻል ላይ ያተኩራል፤
2. ችግሮችን ከመለየት በበለጠ ነገሮችን በመፈረጅ ላይ ያተኩራል፤
3. ወጥ አሰራርን ከመከተል በበለጠ ሁኔታዎችን እንዳመጣጣቸው ለማየት ይረዳል፤
4. ከማፈካከር ይልቅ በህፃናቱ መካከል መተባበር እንዲኖር ያደርጋል፤
5. ህፃናቱ የሚሰማቸውን ስሜት አውጥተው እንዲያንጸባርቁት ያበረታታል

ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል


v
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች

1.1.2. የድንገተኛ ሙከራ፣ ሙከራና ፈተና ንጽጽር


ሀ. ሙከራ (Test)፡ ሙከራ ስልታዊ አካሄድን የሚከተል ህጻናት አንድን ጽንሰ-ሃሳብ፣ ርዕስ፣ ንዑስ-ርዕስ ከተማሩ በኋላ/
እየተማሩ እያለ/ በመማር ያገኙታል ተብሎ የሚጠበቅ የባህሪ ለውጥን (የእውቀት፣ የአመለካከት፣ የክህሎት) ለመለካት የሚረዳ
የናሙና ጥያቄዎች ስብስብ ነው፡፡ በሌላ አገላለጽ፣ ሙከራ በትምህርቱ ሂደት ቀድሞ በታዎቀ የጊዜ ፕሮግራም (በመደበኛ ፕሮግራም)
ለተማሪዎች የሚሰጥ የተማሪዎችን ውጤት ለመወሰን ወይም የመማር ማስተማሩን ሂደት ለማሻሻል ዓላማ ያለው፣ ከአንድ
አይነት በላይ የሆኑ ጥያቄዎች ስብስብ ነው፡፡

ተግባር፡-ለመሆኑ ከላይ በተሰጠው የሙከራ ትርጓሜ ውስጥ ስልታዊ አካሄድ፣ እና የተማሪዎች ባህሪ የሚሉት ሀረጋት ምን ማለት
እንደሆኑ ተረድታችኋል?

ለ. ድንገተኛ ሙከራ (Quiz)፡ ከሙከራ ወይም ከፈተና የተለየ ሆኖ አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ጥያቄዎችን የያዘ ለህጻናት ሳይታሰብ
የሚቀርብ የመማር ማስተማሩን ሂደት ለማሻሻል የሚረዳ መረጃን ለማሰባሰብ ታስቦ ተግባራዊ የሚደረግ ስልት ነው፡፡

ድንገተኛ ሙከራ ሳይታሰብ የሚቀርብ ነዉ ሲባል አስተማሪዉም ሆነ ተማሪዎች መቼ እና ከየት እንደሚመጣ


አያዉቁትም ማለት አይደለም! መምህራን መቼ እና ከየትኛዉ ይዘት ለምን ተግባር እንደሚጠቀሙበት ማወቅ
አለባቸዉ፡፡ ድንገተኛ ሙከራ ህጻናት ሁሌም ለትምህርታቸው ዝግጁ እንዲሆኑ ያበረታታል፣ የመማር ማስተማር ሂደትን
ለማሻሻል የሚረዳ መረጃ ለማግኘት ታስቦ የሚሰጥ ነዉ ሲባልም በድንገተኛ ሙከራ የሚገኝ ዉጤት ከ 100%
አጠቃላይ ዉጤት ጋር አይካተትም፡፡ ከዚያ ይልቅ በመማር ማስተማር ሂደት ልዩ ድጋፍ የሚፈልጉ ህጻናት ተማሪዎችን
ለመለየት፣ ቡድን ለማዋቀር፣ የትምህርት እቅድን ለማሻሻል፣ የማስተማር ስነ-ዘዴን ለመለወጥ/ ለማሻሻል፣
ትምህርቱን ይበልጥ ሳቢ ለማድረግ ወዘተ ቢያገለግል ይመረጣል፡፡ ድንገተኛ ሙከራ አጭር መደበኛ ያልሆነ በክፍለ ጊዜ
መጀመሪያ፣ ወይን መካከል ላይ ሊሰጥ ይችላል፡፡

ፈተና(Examination)፡ ፈተና ሰፋ ያለ ይዘትን የሚሸፍን በትምህርቱ ወይም በአመቱ መጨረሻ የሚሰጥ በዋናነት አላማው
የተማሪዎችን ውጤት መወሰን የሆነ በዛ ያሉ ጥያቄዎች የያዘ የምዘና ስልት ነዉ፡፡ ከፈተና የሚገኝ መረጃ ተማሪዎችን ከክፍል ወደ
ክፍል ለማዛወር (Promotion)፣ የምስክር ወረቀት (Certification) እና የሙያ ማስረጃ ለመስጠት (Licensing) እንዲሁም
የአንድን ስርዐተ-ትምህርት ዉጤታማነት ለመፈተሸ ያገለግላል፡፡ ፈተና በቅድመ መደበኛ ትምህርት ፕሮግራም ላይ ተግባራዊ ላይደረግ
ይችላል፡፡

የመወያያ ጥያቄ
1. ከዓላማ፣ ከትግበራ ጊዜ፣ ከጥያቄ ብዛትና አይነት አንጻር የድንገተኛ ሙከራን፣ የሙከራንና የፈተና አንድነትና
ልዩነትን አብራሩ፡፡
2. ሙከራ የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማሻሻል ወይም የአጠቃላይ ምዘና አካል የሚሆን ዉጤት ለመመዝገብ ታስቦ
ይሰጣል፡፡ ለሁለቱም አላማ የምናዘጋጀዉ የሙከራ ጥያቄ አንድ አይነት ይመስላችኋል? በቡድን በመወያየት
ማብራሪያ አቅርቡ፡፡

ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል


vi
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች

1.2 መማርን የመመዘንና የመገምገም ዓላማዎች


የትምህርት ምዘና ብዛት ላላቸው ዓላማዎች ተግባራዊ ይደረጋል፡፡ ዋና ዋናዎቹም፡
 ህፃናቱን የተሻለ እንዲማሩ ለማገዝ፤
 የህፃናቱን ጠንካራ ወይም ደካማ ጎኖች ለመለየት፤
 የመማር ማስተማር ሂደትን ውጤታማነት ለመመዘንና ለማሻሳል፤
 የትምህርት መርጃ መሳሪያዎችን እና የማስተማር ስልቶችን ውጤታማነት ለማየት፤
 የመምህራንን የማስተማር ተግባር ውጤታማነት ለመመዘንና ለማሻሻል፤
 ለትምህርት አመራር አካላት ስለመምህራን እና የትምህርቱን አካሄድ በተመለከተ የተሟላ መረጃ ለመስጠት፤
 ከተማሪ ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች ጋር በመረጃ የተደገፈ ግንኙነት ለመፍጠር፡፡

የትምህርት ምዘና አራት ዋና ዋና ዓላማዎች


ሀ. የቦታ ምደባ ምዘና (Assessment for Placement Purpose)
የምደባ ምዘና መማር ማስተማርን ለመጀመር ዝግጁነት መኖሩን ለማረጋገጥ እንዲረዳ የተማሪዎችን ቅድመ እውቀት/
ክህሎት ለመለካት ተግባራዊ የሚደረግ የመረጃ መሰብሰብና ከውሳኔ የመድረስ ሂደት ነው፡፡ የምደባ ምዘና ተግባራዊ
የሚሆነው በአብዛኛው ትምህርቱ ከመሰጠቱ በፊት ሲሆን ዓላማውም ለእቅድ ዝግጂት ግብዓት የሚሆን መረጃ
ለማግኘት ነው፡፡

በሌላ አባባል የምደባ ምዘና ወደፊት የሚማሩ ተማሪዎችን ለመማር ያላቸውን መነሳሳት፣ ጥንካሬና ድክመት በመለየት
ለነሱ የሚሆናቸውን የትምህርት ፕሮግራም ለይቶ ለማወቅ፤ ወይም ተማሪዎቹን በተለየ ቡድን ውስጥ በመመደብ
የተለየ ድጋፍ ካስፈለገ ለማመቻቸት የሚረዳ ውሳኔ ለማሳለፍ ነው፡፡

ለ. የሂደት ምዘና (Assessment for Formative Purpose)


በመማር ማስተማር ሂደት የሚደረግ ምዘና የተማሪዎች አዎንታዊ ልምዶች እንዲበረታቱ፤ መማርን የሚገድቡ ችግሮች
እንዲለዩና እንዲቀረፉ ወይም ተማሪዎች ፈጣን ግብረ-መልስ እንዲያገኙ እና እንዲታገዙ በአጠቃላይ ተማሪዎችና
መምሀራን ተገቢና ፈጣን ግብረ-መልስ እንዲያገኙ የሚረዳ ነው፡፡ እንዲህ አይነት ዓላማ ያለው ምዘና በአብዛኛው
መደበኛ ያልሆኑ የመረጃ መሰብሰቢያ ስልቶችን በመጠቀም ተግባራዊ የሚደረግ ይሆናል፡፡ መማር የተማሪዎች ተግባር
እንደመሆኑ በሂደታዊ ምዘና ተማሪዎች የራሳቸውን መማር በመመዘንና ግብረ-መልስ ለአቻዎቻቸው በመስጥና
ከአቻዎቻቸው በማግኘት ሂደት የነቃ ተሳትፍ ሊኖራቸው ይገባል፡፡

ሐ. የመማር ችግር መርማሪ ምዘና (Assessment for Diagnostic Purpose)


የመማር ችግር መርማሪ ምዘና (Diagnostic assessment) መማርን የሚወስኑ ወይም የሚያፋጥኑ መሰረታዊ
ሁኔታዎችን ለመለየት ማለትም የእያንዳንዱ/ዷን ህጻን/ ተማሪ ጥንካሬ፣ ድክመት፣ ልዩ ብቃት ወይም ግንዛቤ በትክክል
ለመረዳትና ቀጣይ እርምጃዎችን ለመውሰድ ተግባራዊ የሚደረግ ምዘና ነው፡፡ ሃኪሞች ለአንድ ህመምተኛ መዳህኒት

ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል


vii
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች

ለማዘዝ በሽታውን ቀድመው መለየት እንዳለባቸው፣ መምህራንም የአንድን ተማሪ/ ህጻን የመማር ወይም የእድገት
ሁኔታ ለማሻሻል የተማሪውን/ዋን ሁኔታ/ ጥንካሬ/ ችግር በትክክል ቀድመው መረዳት ይኖርባቸዋል፡፡

ተግባር፡ የሂደት ምዘና እና የችግር መርማሪ ምዘና ሁለቱም የህጻናቱን የመማር ችግር ያያሉ፡፡ ለመሆኑ ልዩነታቸው ምንድነው?

የመማር ችግር ምርመሪ ምዘና እና ሂደታዊ ምዘና ተመሳሳይነት ያላቸዉ ቢሆንም የችግር መርማሪ ምዘና ከበድ ባሉና ተደጋግመዉ
በሚከሰቱ የተማሪዎች መማር ችግሮች ላይ ያተኮረ ነዉ፡፡ ለምሳሌ ህጻናት አንድን ጨዋታ ለመጫዎት የአጨዋዎቱ ቅደም ተከተል
ቢጠፋቸው ችግሩ ቀላል የሚባል፤ አጨዋዎቱን ደግሞ በማሳየት እና እየተሳሳቱም ቢሆን ደጋግመው እንዲሞክሩት በማድረግ ሊፈታ
የሚችል ነው፡፡ ይህን አይነት ችግር በወቅቱ ለመለየት ታስቦ ተግባራዊ የሚደረግ ምዘና የሂደት ምዘና ይባላል፡፡

በአንጻሩ በመማር ማስተማር ሂደት የተግባቦት ችግር ያለበትና በቡድን ዉይይቶች ወቅት አዘዉትሮ ገለልተኛ የመሆን
ባህሪ ያለዉ ከሆነ ከባድ የመማር ችግር ነዉ፡፡ የዚህን አይነት ችግሮችና መንስኤዎቻቸውን ለመለየት ተግባራዊ የሚደረግ
ምዘና የመማር ችግር መርማሪ ምዘና ይባልል፡፡

ቀላል የመማር ችግሮች በጊዜዉ ካልታረሙ በሂደት ከባድ የመማር ችግሮችን ያስከትላሉ፡፡ ለምሳሌ ህጻናት
በእድሜአቸው እንዲያነቡ፣ እንዲጽፉ ካልተደረገ፣ ጥራት ያለው ትምህርት ሳያገኙ ከክፍል ክፍል እንዲዛዎሩ ከተደረገ
የኋላ ኋላ የመማር ችግር ያለባቸው፣ ትምህርት አይገባኝም የሚሉ በራሳቸው የማይተማመኑ ሰዎች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

መ. የማጠቃለያ ምዘና (Assessment for Summative Purpose)


የማጠቃለያ ምዘና ወይም ግምገማ ትኩረት የተማሪዎችን ውጤት በመወሰን፣ ለተማሪዎች መረጃ በመስጠት፣
ለሚመለከታቸው የትምህርት ባለድርሻ አካላት (ወላጆችን ይጨምራል) የተማሪዎችን መማር/ ውጤት የተመለከተ
የማጠቃለያ ሪፖርት በማቅረብ ላይ ነው፡፡ ይህ ተግባር ተጠያቄነትን ስለሚያስከትል፣ ለተማሪዎችና ወላጆቻቸው
የሚሰጠው የምዘና መረጃ ወይም ማስረጃ ትክክለኛና አስተማማኝ ሊሆን ይገባል፡፡

የተማሪዎችን ውጤት ከመወሰን ባሻገር ስርዐተ ትምህርቱንና የስርዓተ ትምህርቱን ማቴሪያሎች ውጤታማነት
እንዲሁም የመምህራንን የማስተማር ብቃት ለመገምገም ግብዓት የሚሆን መረጃ ከማጠቃለያ ምዘና ሊገኝ ይችላል፡፡

ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል


viii
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች

ተግባር፡- ከላይ ያሉትን አራቱን የግምገማ ምዘና አላማዎች /

ካነበባችሁ በኋላ የሚከተለውን ሠንጠረዥ


አሟሉ፡፡
ተግባራዊ የሚደረግበት ዓላማ ተግባራዊ የሚደረግበት የተከታታይ ምዘና ስልቶች
የምዘና አይነቶች ጊዜ /phase/
የምደባ ምዘና

የሂደት ምዘና

የመማር ችግር መርማሪ


ምዘና

የማጠቃለያ ምዘና

የምዘና አላማዎች ትግበራ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች


ምዘና ህጻናት አንድን የትምህርት ከመማራቸው በፊት፣ እየተማሩ እያለና ከተማሩ በኋላ ተግባራዊ እንደሚደረግ፣
አላማውም የተለያየ እንደሆነ ከላይ ከተሰጠው ማብራሪያ ተረድተናል፡፡ የቅድመ መደበኛ ትምህርት ውጤታማ
የሚሆነው እና ህፃናት ተገቢ ድጋፍ ማግኘት የሚችሉት ከላይ ያየናቸው የሂደት፣ የመማር ችግር ምርመራ፣ የማጠቃለያ ወይም
የምደባ ምዘናን በሚገባ በመለየት በመምህራን በወቅታቸው ተግባራዊ ሲደረጉ ነው፡፡ ለምሳሌ የመማር ችግር መርማሪ ምዘናን
ተግባራዊ ለማድረግ ገና ተማሪዎች ወደ ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች ሲመጡ ልዩ የትምህርት ፍላጎት ያላቸውን
ልጆች ማለትም የማየት፣ የመስማት፣ የማህበራዊ ግንኙነት፣ የአካል ጉድለት፣ የአእምሮ ዝግመት ወዘተ ችግር ያላቸውን
እና ፈጣን ተማሪዎችን ለይቶ ለማዎቅ በእቅድ የተለያዩ የመለያ ስልቶች በየትምህርት ቤቶች ተግባራዊ ሊደረጉ ይገባል፡፡
ተግባር፡-
1. ተማሪዎች እስቲ ይህን ማድረግ ጠቀሜታው ምን ይመስላችኋል? ፡
2. ልዩ የመማር ፍላጎቶች ያላቸውን ተማሪዎች ቀድሞ አለመለየት ተማሪዎችን እንዴት ሊጎዳ ይችላል?ጎን ለጎን
በጥንድ በመወያየት ለመምህራችሁ ግለጹ፡
ለቦታ ምደባ ምዘና ምሳሌ የሚሆነን ደግሞ የሚከተለውን እንመልከት፡፡ አንድ ትምህርት ቤት በማታ ፕሮግራም
ለእንግሊዘኛ ቋንቋ ትምህርት ፈላጊዎች ትምህርት ለማመቻቸት በቅድሚያ ለትምህርት ፈላጊ ተማሪዎች የመለያ
ሙከራ በመስጠት በሙከራው ውጤት መሠረት በጀማሪ፣ መካከለኛና ከፍተኛ ክፍል/ ምድብ ሰልጣኞችን በመመደብ
እንደየ ደረጃጀው/ ችሎታቸው በተለያየ ክፍል ስልጠና እንዲያገኙ ቢያመቻች ምዘናው የቦታ ምደባ ምዘና ይባላል፡፡

ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል


ix
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች

ተግባር፡- ከላይ ባየናቸው ሁለት ምሳሌዎች መሰረት በቅድመ መደበኛ ትምህርትቤቶች ተግባራዊ ሊደረጉ የሚችሉ
የመማር ችግር መርማሪ ምዘና፣ የቦታ ምደባ ምዘና፣ የሂደትና፣ የማጠቃለያ ምዘና ተግባራዊ ምሳሌዎችን በተጨማሪ በዝርዝር
በመጻፍ እና በማብራራት አቅርቡ፡፡

1.3 የመማር ምዘናና ግምገማ ትግበራ መርሆዎች/


Principles
በቅድመ መደበኛ የትምህርት አሰጣጥ ሂደት የትኛውም የምዘና አይነትንና ሁኔታ አራት መሰረታዊ መርሆዎችን አሟልቶ
መገኘት ይኖርበታል፡፡ ይኸውም፣ የምዘናው መሣሪያዎችና የምዘናው ሂደት ፍትሃዊ፣ ትክክለኛ፤ አስተማማኝ እና እንደ
ሁኔታው ተለዋዋጭ (Flexibility) ሊሆን ይገባል፡፡

ፍትሃዊነት: የምዘና ሂደትና መዛኙ ግለሰብ ተመዛኞችንና የእያንዳንዱን ተመዛኝ ጥቅም ከግምት ውስጥ የሚያስገቡ
መሆን አለባቸው፡፡ ስለሆነም ምዘና ፍትሃዊ ነው የምንለው ሁሉም ህጻናት-ተማሪዎች፡
 በምዘናው ሂደት እንዲፈጽሙት ስለሚጠበቅባቸውና ስለምዘናው አይነት የጠራ እውቀት ሲኖራቸው፣
 የብቃት መመዘኛ መስፈርቶችን ቀድመው ሲረዱ፣
 ሁሉም ተማሪውች በእኩል ሁኔታ ሊመዘኑ ሲችሉ፤
 ከመማር ዘይቤዎቻቸው (learning style) እና ልዩ ፍላጎቶቻቸው ጋር በተጣጣመ መልኩ እንዲመዘኑ
ሲደረግና፤
 የምዘናውን ውጤት ለማሻሻል እንዲችሉ ብቃታቸው እንደገና የሚታይበትና እንዲያሻሽሉ የሚጠይቁበት
እድል ሲሰጣቸው ነው፡፡
ተግባር፡የሚከተሉትን ጥያቄዎች በቡድን በመወያየት ለክፍሉ ተማሪዎች አቅርቡ፤
1. የተማሪዎች ልዩ ፍላጎቶችና የመማር ዘይቤዎች ምንድናቸው? ምዘናውን እንዴት ሊወስኑ
ይችላሉ?
2. ተማሪዎች ለምዘናው በተለያየ ምክንያት ሳይዘጋጁ ቀርተው ቢወድቁባችሁ ምን እርምጃ
ትወስዳላችሁ? ለምን?

ትክክለኛነት (Validity):- የምዘና ትክክለኛነት ምዘናው ሂደት ወይም መሣሪያው እንዲለካ የተፈለገውን ብቃት መለካት
የመቻል ሁኔታን ይመለከታል፡፡ ይህም እውን የሚሆነው፡
 ምዘናው ህጻናት-ተማሪዎች በደረጃቸው ከሚጠበቁ ብቃቶች (ዓላማዎች) ጋር የተጣጣመ መሆን
ይኖርበታል፤
 ህጻናት,ተማሪዎች የተማሩትን የሸፈነና በቂ ጥያቄዎችን የያዘ መሆን አለበት፤
 የሚሰበሰበው መረጃ ከህፃናት እድሜ የሚጠበቅ፣ ለወደፊት እድገታቸው ፋይዳ ያለው መሆን ይኖርበታል፤

ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል


x
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች

 በምዘናው ሂደት ተመዛኞች ስለሚለካው ብቃት በግልጽ ሊረዱ ይገባል፡


ተግባር፡-ምዘናው ትክክለኛ እንዲሆን የምዘና ጥያቄዎችን የሚያዘጋጅ አንድ መምህር በተጨባጭ ምን ተግባራትን
መፈጸም አለበት?

አስተማማኝነት (Reliability)፡-አስተማማኝነት የምዘናን ወጥነት ይመለከታል፡፡ በአንድ የመመዘኛ መሳሪያ ባህርይን


በተደጋጋሚ በመለካት የሚገኝን መረጃ/ ውጤት ተመሳሳይነት፣ ወጥነት ወይም ቋሚነትን የሚመለከት ጭብጥ
ነው፡፡ ምዘናችን አስተማማኝ እንዲሆን፡
 ስለሚመዘነው ብቃት ህጻናት-ተማሪዎች ቀድመው በሚገባ የተማሩት ሊሆን ይገባል፤
 የተለያዩ የምዘና ስልቶችን መጠቀም ያስፈልጋል፤
 መረጃዎችን በተለያየ ሁኔታና ጊዜ እንዲሰበሰቡ ማድረግ ሊያስፈልግ ይችላል፤
 ከአንድ በላይ መዛኞችን መጠቀም አስፈላጊ ሊሆን ይችላል፡፡

ተለዋዋጭነት(Flexibility)፡- የምዘና ተለዋዋጭነት የምዘናውን አይነት ከተመዛኞች ጋር በመነጋገርና በመስማማት


ከመወሰን ወይም ከመምረጥ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ አንድ ምዘና ተለዋዋጭነት አለው የምንለው ከጊዜ፣
ከምዘና ስልት፣ ከቦታና ምዘናው ከሚሸፍነው ይዘት አንጻር ምዘናው ለሁሉም ተመዛኞች አመች፣ በሁሉም
ተመዛኞች ተቀባይነት ያለው ሲሆን ነው፡፡

1.4 የምዘና አይነቶች


1.4.1 ተከታታይ ምዘና (Continuous Assessment)

ተከታታይ ምዘና ምንድነው? ምዘና አጠቃላይነት ያለው መረጃን ማሰባሰብን፣ መተንተንና መጠቀምን የሚመለከት ተግባር ሲሆን
ተከታታይ ምዘና በተለይ ከመማር ማስተማሩ ሂደት ጋር የተዛመደ፣ ቀጣይነት ያለውና በክፍል ውስጥ ትምህርቱን በሚያቀበው/
በምታቀርበው መምህር/ት ወይም በተማሪዎች ተግባራዊ የሚደረግ የዓላማውን ከግብ የመድረስ ሁኔታ ለመለየትና
የማሻሻያ እርምጃ ለመውሰድ የሚረዳ ተግባር ነው፡፡ ስለሆነም ተከታታይ ምዘና ህጻናት ወደ ስርዓተ ትምህርቱ የመማር
ውጤቶች (ዓላማዎች) የሚያደርጉትን ግስጋሴ በመመዘን ወይም በመለየት በየዕለቱ ተግባራዊ የሚደረግ የመረጃ ማሰባሰብ፣
ማደራጀት፣ መተንተንና ቀጣይ እርምጃን የመውሰድ ሂደት ነው፡፡

የተከታታይ ምዘና ጠቀሜታዎችና ተግባራዊ የሚደረግባቸው ደረጃዎች


በመማር ማስተማር ሂደት የሚተገበር ምዘና እንደ መማር ማስተማሩ ሂደት ቀጣይነት ያለው ሲሆን በተመሳሳይም በሶስት ደረጃዎች
ተከፍሎ ሊታይ ይችላል፡፡
ሀ. ትምህርቱ ከመሰጠቱ በፊት የሚደረግ ምዘና፤
ለ. ትምህርቱ በመሰጠት ላይ እያለ የሚደረግ ምዘና፤
ሐ. ትምህርቱ ከተሰጠ በኃላ የሚደረግ ምዘና፡ በሚሉ ሶስት ደረጃዎች ተከፍሎ ሊታይ ይችላል፡

ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል


xi
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች
ተግባር፡ የሚከተሉት የተከታታይ ምዘና ጠቀሜታዎች በየትኛው የምዘና ደረጃ ውስጥ ሊካተቱ የሚችሉ እንደሆኑ በመለየት
አዛምዱ፣ ለተግባራችሁ ምክንያት በመስጠት የተዛማጁን ፊደል (ደረጃውን የያዘውን ፊደል) በተሰጠው ክፍት ቦታ ላይ
አስፍሩ ፡፡
1. የእያንዳንዱን ተማሪ የመማር ፍላጎቶች ለመለየት፣ ____
2. መማርን የሚያሻሽል ግብረ-መልስ በወቅቱ ለተማሪዎች ለመስጠት፤ ____
3. ተማሪዎች ምን እንደሚያውቁ ወይም እንደሚችሉ ቀድሞ ለመረዳት፣ ____
4. የትምህርቱ አላማ በምን ያህል ከግብ እንደደረሰ ለመረዳት፤ ____
5. በየትኞቹ ይዘቶች ላይ ትኩረት መስጠት እንደሚያስፈልግ ለመለየት፤ ____
6. ተማሪዎች ትምህርቱን ለመማር ያላቸውን ተነሳሽነት ለመገንዘብ፣ ____
7. ተማሪዎች በምን ያህል መጠን ትምህርቱን በመከታተል ላይ እንዳሉ ለመለየት፤ ____
8. በእቅዱ አተገባባር ላይ ተገቢና ወቅታዊ የሆነ ለውጥ ለማድረግ፤ ____
9. የመማር ማስተማሩን ሂደት በመረጃ ለመምራት፣ ____
10. የተማሪዎችን መማር መዝኖ በመገምገም ለተማሪዎችና ወላጆቻቸው መረጃ ለመስጠት፣ ____
11. በትምህርታቸው ወደኋላ የቀሩትን ለማገዝና የተሻለ የሚማሩትን ለማበረታታት፤ የበለጠ የትምህርት
ፍላጎታቸውን ለማርካት፣ ____
12. የክፍሉን ተማሪዎች የጋራ የመማር ፍላጎቶች በመለየት እንደገና ማስተማር ሲያስፈልግ የማስተማር
ስነዘዴን በመቀየር ለማስተማር፤ ወደሌላ ርዕሰ ጉዳይ ለመሸጋገር ዝግጁ መሆናቸውን በመገምገም ከውሳኔ
ለመድረስ፣ ____

13. የተማሪዎችን የተሳሳቱ አመለካከቶች ለይቶ ለማዎቅ፣ ____


14. የተማሪዎችን ግላዊ ልምዶችና ዝንባሌዎቻቸውን ለመለየት፣ ____
15. መረጃዎችን በማሰባሰብና ከትምህርቱ አላማዎችና ከስርአተ-ትምህርቱ ይዘቶች ጋር በማዛመድ ተገቢ
የትምህርት እቅድ ለማዘጋጀት፤ ____
16. የተመረጡ ተማሪዎችን በማጠናከሪያ ወይም በላቀ ደረጃ ለመመደብ የሚያስችሉ መረጃዎችን ለማሰባሰብ፣
____
17.ተማሪዎች ለትምህርታቸው ውስጣዊ ትጋት/ተነሳስነት እንዲኖራቸው ለማድረግ፣ ____

1.4.2. የብቃት ምዘና (Authentic Assessment)


የብቃት ምዘና የተማሪዎችን ሰርቶ የማሳየት ክህሎቶች የመመዘን ሂደት ነው፡፡ የብቃት ምዘና የግንዛቤ መዳበርን፣ በድርጊት የመግለጽን፣
የተነሳሽነትን እና ችግር የመፍታትን ሁኔታዎች አጣምሮ በመመዘን ላይ ያተኩራል፡፡ አንዳንድ መምህራን ተማሪዎች በጽሁፍ ፈተናዎች
ያገኙትን ውጤት ትክክለኛነት ወይም መዛኝነት ለማረጋገጥ ተማሪዎች በተግባር ሰርተው የማሳየት ብቃታቸውን ለማየት ይሞክራሉ፡፡
በዚህም ምክንያት የብቃት ምዘና በሌላ ስም ተለዋጭ ምዘና ይባላል፡፡ የብቃት ምዘና ዋና ትኩረት ህጻናት ምን እንዳወቁ በማረጋገጥ
ላይ ሳይሆን ያወቁትን በተግባር መተርጎም መቻላቸውን በመለየት ላይ ነው፡፡ በመጨረሻም የብቃት ምዘና ዋና ዓላማ ተማሪዎች
በገሃዱ ዓለም ስራ ለመስራት ዝግጁ መሆን ወይም አለመሆናቸውን በምዘና በማረጋገጥና ለውጥ የሚያመጣ እርምጃ በመውሰድ ላይ
ነው፡፡ ለምሳሌ ህጻናት ሲያነቡ የንባብ ችሎታቸውን፣ ሲጽፉ የጽሁፋቸውን ጥራት፣ አካላዊ እንቅስቃሴዎችን ባዩት መሰረት
ሲያከናውኑ፣ የሂሳብ ስሌቶችን ተጠቅመው ተጨባጭ ችግሮችን ሲፈቱ ወዘተ መመዘን የብቃት ምዘና ይባላል፡፡

ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል


xii
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች

ተግባር፡-1. የብቃት ምዘና ሊባሉ የሚችሉ ሌሎች በአይነታቸው የተለያዩ ሶስት ምሳሌዎችን ስጡ
ሀ.__________________________________________________________
ለ.__________________________________________________________
ሐ.__________________________________________________________
2. የብቃት ምዘና ሊባል የማይችል አንድ ምሳሌ ስጡ ______________________

የብቃት ምዘና መገለጫ ባህሪያት፡

 ምዘናው የሚያተኩረው በቀጥታ በህጻናት ተግባር ላይ ነው፡፡ ስለሆነም በህጻናት የተሰሩ ናሙና ስራዎችን
(portfolio-exhibitions)፣ ቀጥታ የመስራት ሙከራዎችን (performances), የሰርቶ ማሳየት ሂደቶችን
(experiments)፣ ገለጻዎችን (presentations)፣ በመምህር/ት ምልከታዎች (observations) ላይ የሚያተኩር
ተግባር ነው፡፡
 የብቃት ምዘና የትምህርት አመቱን በሙሉ ቀጣይነት ያለው የምዘና ሂደት ነው፡፡ በዓመት መጨረሻ ላይ
የተማሪዎችን ውጤት ለመወሰን ተግባራዊ የሚደረግ ሙከራ/ ፈተና የብቃት ምዘና አይደለም፡፡
 የስርዓተ ትምህርቱ አንድ አካል ነው፡፡ ህጻናት በስርዓተ ትምህርቱ የተቀመጠውን ተግባር መስራት መቻላቸውን
የምንመዝንበት ሂደት ነው፡፡
 በተማሪዎች መካከል እና በመምህራንና ተማሪዎች መካከል መተጋገዝ ወይም መረዳዳት እንዲኖር
የሚያበረታታ የምዘና ተግባር ነው፡፡ ስለሆነም ከመምህር ተኮር ምዘና ባሻገር ሃጻናት በምዘና ሂደት እንዲሳተፉ
የሚፈቅድ ተግባር ነው፡፡
 ባለሙያዎችና ወላጆች ስለህጻናት የበለጠ እንዲማሩ በማገዝ ላይ ያነጣጠረ ነው፡፡ ስለሆነም የብቃት ምዘና
አንድ ውስን የህጻኑን/ኗን ባህርይ ለመለወጥ ሳይሆን ሁለንተናዊ የህጻናት መዳበርን ለማምጣት የሚረዳ ተግባር
ነው፣፣ ይህ ማለት የህጻኑን/ኗን ማህበራዊ፣ ስሜታዊ፣ አእምሮአዊ፣ አካላዊ እና የቋንቋ የመዳበር ሁኔታን
አጣምሮ ለመመዘን ያስችላል፡፡
 ከተቀመጠው መስፈርት አንጻር የአንድን ህጻን ብቃት በመመዘን ላይ ያነጣጥራል፡፡ አንድን ህጻን ከሌላ ጋር
ወይም ሃጻናትን ከሌሎች ህጻናት ጋር በማዎዳደር ላይ አያተኩርም፡፡
 ምዘናን የመማር አካል ያደርጋል፡፡ ለምሳሌ አንድ ህጻን አንድ ነገር ተመልክታና ሪፖርት ጽፋ ለክፍል ተማሪዎች
እንድታቀርብ በማድረግ የተማሪዋን ብቃት መመዘን በእግረ መንገድም እሷ፣ ሌሎችም ከተግባሩ እንዲማሩበት
ይረዳል፡፡ ማለትም የምዘናው ተግባር በቀጥታ ከተማሪዎች የመማር ተግባር ጋር እንዲያያዝ ያደርጋል፣
 ህጻናት ቀድመው ከተቀመጡላቸው አማራጮች ውስጥ እንዲመርጡ ሳይሆን አማራጭ መልስ እንዲሰጡ
ያበረታታል፣
 ተማሪዎች የላቀ አስተሳሰብ እንዲኖራቸው ይገፋፋል (ማለትም የመተንተን፣ የማደራጀት፣ የመገምገም)፣
 የተማሪዎችን ልዩነት ማለትም የመማር ዘይቤ፣ የቋንቋ ችሎታ፣ ባህል፣ ቅድመ እውቀት እና የክፍል ደረጃ
ልዩነቶች ከግንዛቤ ያስገባል፣

ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል


xiii
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች

1.5 ሂደታዊ ተከታታይ ምዘና የአተገባበር ችግሮች


ተከታታይ ምዘናን ተግባራዊ ለማድረግ አያጋጠሙ ያሉ መሰረታዊ ችግሮች፡-

 በአንድ ክፍል የሚማሩ ተማሪዎች ቁጥር መብዛት የተማሪዎችን የመማር ሁኔታ ለይቶ ለማዎቅ እና ለማገዝ የሚደረገውን
ጥረት አስቸጋሪ ያደርገዋል ተብሎ የሚታመን መሆኑ፤
 የመምህራን ተከታታይ ምዘናን የመተግበር ክህሎታቸው አናሳ መሆኑ፣
 የትምህርት ምዘና ከተገቢው በላይ ሊፈጸም የሚችል መሆኑ፣ ለምሳሌ የሁሉም የትምህርት አይነት መምህራን የቤት
ስራ በተደጋጋሚ ቢሰጡ ተማሪዎች ስራውን በጥራት ለመስራት በቂ ጊዜ ላያገኙ ይችላሉ፡፡ ይኸውም
የተማሪዎችን መማር ከላይ ከላይ የሚያደርግ መሆኑና፣ በወቅቱ አርሞ ተገቢ ግብረመልስ ለመስጠት
ለመምህሩ/ሯ አስቸጋሪ ሊሆን መቻሉ፡፡
 የተከታታይ ምዘናን ውጤት መዝግቦ መያዝ አስቸጋሪ ወይም ለብዙ መምህራን ከባድ መሆኑ፣
 ብዙ መምህራን ተከታታይ ምዘናን የስራቸው አካል ሳይሆን ከመደበኛ ስራቸው ተጨማሪ የመጣባቸው ጫና እንደሆነ
አድርገው የሚቆጥሩት መሆኑ፤
 ተከታታይ ምዘናን ተግባራዊ ለማድረግ እየሞከሩ ያሉ መምህራንም ቢሆን ትኩረታቸው በትውስታና ግንዛቤ ፈጠራ ላይ
ባተኮሩ የመማር ውጤቶች ላይ ብቻ መወሰኑ፡፡

ተግባር፡- ከላይ የተጠቀሱ የተከታታይ ምዘና የአተገባበር ችግሮች እንዴት ሊቃለሉ እንደሚችሉ በዝርዝር
በመወያየት ለክፍሉ ተማሪዎች በማብራራት አቅርቡ

የምዕራፉ ማጠቃለያ
ልኬታ የህጻናትን እዕምሮአዊ፣ አመለካከታዊ ክህሎታዊ ለውጥ የተመለከተ መረጃን በመጠን (በቁጥር) የመግለጽ ሂደት ነው፡፡
ምዘና ስለህጻናት መዳበር፣ መማር፣ ጤና፣ ባህርይ፣ የትምህርት ግስጋሴ፣ የልዩ ድጋፍ ፍላጎት እና ስኬት የተመለከቱ
መረጃዎችን የማሰባሰብ ሂደት ነው፡፡ የሚሰበሰበው መረጃ አይነታዊ ወይም መጠናዊ ሊሆን ይችላል፡፡ ግምገማ ዓላማን
መለየት፣ መረጃ የመሰብሰብ እና ለባህርይ ትርጉም የመስጠት ወይም የመፈርጅ ሂደት ነው፡፡ ግምገማ አይነታዊ ወይም
መጠናዊ መረጃ ወይም ሁለቱንም በመጠቀም ከዓላው ጋር በማገናዘብ ህጻናት ባሳዩት የባህርይ ለውጥ ላይ ፍረጃ
ማድረግን ያካትታል፡፡ በዚህ የግምገማ ትርጉም መረጃ መሰብሰብ የሚለው ምዘናን ይገልጻል፤ በመሆኑም በግምገማ
ውስጥ ምዘና ሊካተት ይችላል ማለት ነው፡፡ ምዘና መጠናዊ ወይም አይነታዊ መረጃን ያስገኛል ከሚለው ምዘና ውስጥ
ልኬታ መኖሩን ለማየት ያስችላል፡፡ ስለሆነም ልኬታ በምዘና፣ ምዘና በግምገማ ውስጥ መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል፡፡

በምዘና ሂደት መደበኛና መደበኛ ያልሆኑ የመረጃ ማሰባሰቢያ ስልቶችን ልንጠቀም እንችላለን፡፡
መደበኛ የመረጃ ማሰባሰቢያ ስልቶች የምንላቸው እንደ ፈተና፣ ሙከራ፣ ፕሮጀክት እና
የመሳሰሉት ሲሆኑ፤ መደበኛ ያልሆኑ የመረጃ ማሰባሰቢያ ስልቶች የምናላቸው እንደ ድንገተኛ
ሙከራ፣ የቃል ጥያቄ፣ ፅብረቃ፣ ምልከታ፣ ግለ-ምዘና፣ የአቻ-ምዘና እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡

የክፍለ ትምህርት አንድ ማጠቃለያ ጥያቄዎች


ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል
xiv
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች

ጥያቄ 1: ተከታታይ ምዘናን ተግባራዊ በማድረግ ሂደት (በምዘና እና ግብረ-መልስ በመስጠት) ተማሪዎችን ማሳተፍ ምን
አይነት ጠቀሜታ አለው?
ጥያቄ 2: የ”ሂተም” መረጃን መዝግቦ መያዝ ለመምህሩ/ሯ እና ተማሪዎች ምን ጠቀሜታ ይኖረዋል?

ጥያቄ 3: በክፍል ስራ እርማት የተገኘ መረጃ የ”ሂተም” ወይም የ”አተም” መረጃ ነው የሚባለው መቼ ነው?

ክፍለ ትምፍርት ሁለት

2. የቅድመ መደበኛ ትምህርት ምዘና ባህርያት

2.1 ተከታታይ ምዘና

ህጻናት ምን ቅድመ እውቀት እንዳላቸው ሳናረጋግጥ፣ ትምህርቱን እየተከታተሉ መሆኑን ወይም አለመሆኑን መረጃ
ሳይኖረን፣ በመማሩ ሂደት እያጋጠሟቸው ያሉ ችግሮች ሳናውቅ የመማር ማስተማሩን ሂደት ውጤታማ አያደርግም፡፡
የህጻናቱን መማር በተከታታይ መመዘን በራሱ የማስተማርን ሂደት ጥራት እንዲኖረው አያደርግም፡፡

ተከታታይ ምዘና መረጃ መሰብሰብን፣ ለተሰበሰበው መረጃ ትርጉም መስጠትን፣ እና እርምጃ መውሰድን በተከታታይነት የሚያካትት
ተግባር ነው፡፡ እርምጃ (Action) የህጻናትን የምዘና ውጤትና ግምገማን መሰረት በማድረግ ተግባራዊ የሚደረግ ክንውን
ነው፡፡ ይኸውም ግብረ-መልስ መስጠት፣ ማበረታታት፣ ግንዛቤ፣ እውቀትና ችሎታን ማጎልበት፣ ድጋፍ መስጠት፣ ወዘተ
ሊሆን ይችላል፡፡

2.1.1. ሂደታዊ ተከታታይ ምዘና (ሂተም)


በሚከተሉት ሂደታዊ ተከታታይ ምዘናን ሊገልጹ የሚችሉ ተምሳሌቶች (Models) ናቸው፡፡
የተከታታይ ምዘና ተምሳሌት 1

ለምሳሌ፡- ምዘና የአንድን ሰው ክብደትን እንደመለካት ብናየው፣ ግምገማ ክብደቱ ከሚገባው በላይ/በታች መሆኑና ለጤና አስጊ
መሆኑን/አለመሆኑን እንደመፈረጅ፤ እርምጃ አካላዊ እንቅስቃሴ ወይም ክብደት የሚቀንስ አመጋገብን እንደመጠቀም
ሊወሰድ ይችላል፡፡ ከእርምጃውም በኋላ እንደገና መረጃ መሰብሰብ ለውጡን መገምገምና የማስተካከያ ወይም ሌላ
እርምጃ መውሰድ እያለ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

ተግባር፡-እናንተ ከትምህርት ዘርፋችሁ አንድ ምሳሌ ተጠቅማችሁ እንዴት የምዘና፣ ግምገማና እርምጃን ተከታታይነትና
ተግባራዊነት ልታሳዩ ትችላላችሁ?
ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል
xv
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች

የተከታታይ ምዘና ተምሳሌት 2

ተግባር፡ የሚከተለው ምስል በተከታታይ ምዘና የተማሪዎችን የማብቃት ሂደትና የዳግም ምዘናን
አስፈላጊነት ሊያሳይ የሚችል ነው፡፡ ምስሉን በጥንቃቄ ተረድላችሁ በምሳሌ ለጓደኞቻችሁ
አስረዱ

ተግባር፡ 1. በዚህ ሂደታዊ ተከታታይ ምዘናን በሚገልጸው ንድፉ ውስጥ የሰፈሩ ነጥቦችን በመመርመር የምዘና፣ ግምገማ እና እርምጃን
ተግባራዊነት በመለየት ተንትናችሁ አስረዱ፡፡
2. ለማንሰራረሪያ፣ ማበልጸጊያና ዳግም ምዘና ትግጓሜ ስጡ

ተግባር፡- የሚከተሉት አባባሎች እውነት ወይም ሃሰት


መሆናቸውን ለዩ፤ ለመልሳችሁ በምሳሌ
የተደገፈ ምክንያት ስጡ፡፡
1. ሂደታዊ ተከታታይ ምዘና የመማር ማስተማሩ
ሂደት አንድ አካል ነው፡፡
2. ሂደታዊ ተከታታይ ምዘና ተማሪዎች በክፍል

ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል


xvi
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች

ውስጥ ሃሳብ እንዲለዋወጡ፣ እንዲጠያየቁ፣


በመረዳዳት ስሜት ግብረ-መልስ እንዲሰጣጡ
በማበረታታት የመማር ክፍተቶች እንዲሞሉ
የሚያደርግ ተግባር ነው፡፡
3. ለመማር ማስተማሩ ሂደት መሻሻል አስተዋጽኦ
የሌለው ምዘና ሂደታዊ ተከታታይ ምዘና
አይባልም፡፡
4. ሂደታዊ ተከታታይ ምዘና ኡደታዊ ነው፡፡
2.1.2 አጠቃላይ ተከታታይ ምዘና (አተም)
አጠቃላይ ተከታታይ ምዘና በአንድ በተወሰነ ጊዜ ውስጥ ህጻናት-ተማሪዎች ምን ያህል እንደተማሩ ለመወሰን ተግባራዊ
የሚደረግ የመረጃ ማሰባሰብ ሂደት ነው፡፡ ብዙውን ጊዜ ህጻናት አንድ ጭብጥ፣ ርዕስ ወይም ንዑስ ርዕስ ተምረው
ሲያጠናቅቁ ለአጠቃላይ ተከታታይ ምዘና አገልግሎት ምዘና ተግባራዊ እየተደረገ በየጊዜው የሚገኘው ውጤት
የሚመዘገብና የሚደመር ይሆናል፡፡

ከሂደታዊ ተከታታይ ምዘና በተመሳሳይ አጠቃላይ ተከታታይ ምዘና ሲታቀድ የሚከተሉት ከግንዛቤ መግባት ይኖርባቸዋል፡

 የመማር ውጤቶች ግልጽነት፡- የመማር ውጤቶች በግልጽ ሊነደፉ ይገባል፡፡ የሚጠበቁ የባህርይ ለውጦች
ማለትም የዕውቀት፣ የግንዛቤ፣ ክህሎት፣ ዝንባሌና መሰረታዊ እሴቶች በግልጽ ተብራርተው መታየት
ይኖርባቸዋል፡፡
 የመማር ተግባራት ተገቢነት፡- በመማር ማስተማሩ ሂደት የህጻናት ተሳትፎ መኖር የመማር ማስተማሩ ሂደት
ስኬታማ እንዲሆን ይረዳል፡፡ ለምሳሌ በገለጻ የማስተማር ስነ-ዘዴ ብቻ የተማሪዎችን ስብዕና፣ ክህሎታ
የመሳሰሉ አላማዎችን ከግብ ማድረስ አይቻልም፡፡ በገለጻ ስነዘዴን በመጠቀም ብቻ ካስተማርን የህጻናትን
በተግባር ሰርቶ የማሳየት ችሎታ ለመለካት አንሞክርም፣ ምክንያቱም ክህሎቱ እንዲጎለብት በማስተማር
ስልታችን አላደረግንምና፡፡
ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል
xvii








































ታ 
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች

የምዘና ስልቶች፡- ግልጽነት ያላቸው የመማር ውጤቶች የምዘናውን አካሄድ ቀላል ያደርጉታል፡፡ በሌላ አባባል
የምንመርጠው የምዘና ስልት ከትምህርቱ አላማ ጋር ሊሄድ የሚችል መሆን ይኖርበታል፡፡
በምዘና ሂደት የነዚህ ከላይ ያየናቸው ጭብጦች ሊዛመዱ ወይም ሊጣጣሙ ይገባል፡፡ የቅድመ መደበኛ ህጻናትን ውጤት
ለመወሰን በአብዛኘው የብቃት መመዘኛ ስልቶችን(ለምሳሌ፡ ሰርቶ ማሳየት፣ የክፍል ስራ፣ ምልከታ፣ የመሳሰሉትን)
እንድንጠቀም ይመከራል፡፡

2.1.3 የተከታታይ ምዘና አተገባበር መርሆዎች (ጠቃሚ ነጥቦች)


1. ተከታታይ ምዘና ማዛመድን (alignment) የሚጠይቅ ተግባር ነው፡፡ ማዛመድ በስርዓተ ትምህርቱ አላማዎች፣ በመማር
የማስተማር ስነዘዴዎችና ይዘቶች እንዲሁም ከምዘና ስልቶች ጋር የሚኖረውን የተያያዥነት መጠን የሚገልጽ ጭብጥ ነው፡፡
ትምህርት ጥራት እንዲኖረው የተጠቀሱትን ነጥቦች በማስተሳሰር መማር ማስተማሩን መምራትና የተማሪዎችን መማር
መመዘን አስፈላጊ ነው፡፡ የሚከተለው ሶስትዮሻዊ ትስስር ማዛመድን ያሳያል፡፡

ስለሆነም የምዘና ስልቶች እና የማስተማር መማር ተግባራት መመረጥ ያለባቸው ከትምህርቱ ዓላማዎች አንጻር ነው፡፡
አንድ የምዘና ስልት ወይም የመረጃ መሰብሰቢያ መሳሪያ በአንድ ቦታ ተገቢ/ የሚሰራ ሆኖ በሌላ ቦታ የማይሰራ/ የማይገባ
ሊሆን ይችላል፡፡ በሌላ አባባል የምዘና ስልት ከመምረጣችን በፊት ልናሳካ ላሰብነው ግብ ተስማሚ መሆኑን መመርመር
ይኖርብናል፡፡

ተግባር፡ ለሚከተሉት ዓላማዎች ተስማሚ የሚሆኑ የምዘና ስልቶችን ጠቁሙ!


የትምህርት አላማዎች
• እውቀት መያዝ
• ማገናዘብ መቻል
• መተግበር መቻል
• ጥልቀት ያለው አስተሳሰብ ማሳየት
• መተንተን መቻል
• የማደራጀት ችሎታ
• የመገምገም ብቃት
• የአካል ቅልጥፍና ማሳየት
ተስማሚ የምዘና ስልቶች (አስተያየት)

ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል


xviii
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች

• አውንታዊ አመለካከት መያዝ


• ሃሳብን መግለጽ መቻል
• የችግር ፈችነት ክህሎትን መላበስ
• የፈጠራ አስተሳሰብ መኖር

2. ምዘናችን ትክክለኛ እንዲሆን ከአንድ በላይ የምዘና ስልቶችን በመጠቀም መመዘን ያስፈልጋል (triangulation)፡፡
በተጨማሪም የሁሉንም የትምህርት አላማዎች ከግብ የመድረስ ሂደት ለማየት አንድ፣ ብቸኛና ተስማሚ የሆነ
የምዘና ስልት የሌለ መሆኑን መረዳት አስፈላጊ ነው፡፡

ተግባር 1:- የተማሪዎችን መማር ለመመዘን የተወሰኑትን ብቻ ሳይሆን የተለያዩ ወይም በዛ ያሉ የምዘና
ስልቶችን መጠቀም የሚያስፈልገው ለምንድነው?
1. ____________________________________________________
2. ____________________________________________________

3. የምዘና ስልቶችን በአግባቡ መጠቀም የእያንዳንዱን ስልት ድክመቶች፣ ጥንካሬዎችና ተገቢነት ጠንቅቆ ማወቅን
ይጠይቃል፡፡ ሁሉም የምዘና ስልቶች አንድ ወይም ከአንድ በላይ ችግሮች ይኖሯቸዋል፡፡

ተግባር፡-ለሚከተሉት የምዘና ስልቶች ቢያንስ አንድ ጠንካራና አንድ ደካማ ጎን ጥቀሱ


የተከታታይ ምዘና ስልት ጠንካራ ጎን ደካማ ጎን
1. ሙከራ/ፈተና
2. ምልከታ
3. የቡድን ስራ/ሪፖርት
4. የክፍል/የቤት ስራ
5. የቃል ጥያቄና መልስ
6. ፕሮጀክት/አሳይመንት
7. ፖርትፎሊዮ
8. የተግባር ስራን ማቅረብ
9. ቃለ-መጠይቅ
10. ግለ-ምዘና/የአቻ-ምዘና
11. ፅብረቃ

4. የተማሪዎችን መማር መመዘን በራሱ ግብ አይደለም፣ ከግብ የመድረሻ መንገድ እንጂ፡፡ ስለሆነም የማሳካው ዓላማ
ወይም ግብ ምንድነው? የሚል ጥያቄን ቀድሞ መመለስ ተገቢ ነው፡፡ በተጨማሪም ሊወሰዱ የሚገባቸውን
እርምጃዎች መለየት ያለብን መረጃ ማሰባሰቢያ መሳሪያው ከመመረጡ በፊት ነው፡፡

ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል


xix
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች

ተግባር፡-የተማሪዎችን መማር የምንመዝነው ለምንድነው?


የሚከተሉት ከምዘና በኋላ ሊወሰዱ የሚችሉ እርምጃዎች ናቸው፡፡ ለእያንዳንዱን ግልጽ ትርጓሜና
ምሳሌ/ዎችን በመስጠት አብራሩ፡፡
1. ማንሰራሪያ 5. ግብረ-መልስ መስጠት 9. መልሰው እንዲያነቡ ማድረግ
2. ማበልጸጊያ 6. እንደገና ማስተማር 10. የወላጆችን እገዛ መጠየቅ
3. ማበረታቻ/ማትጊያ 7. ውጤት መወሰን 11. የጥናት ቡድን ማደራጀት
4. ቱቶሪያል 8.ሚዲያዎችን መምረጥ 12. የምክር አገልግሎት መስጠት

5. በምዘና የተገኘን መረጃ በመጠቀም ወላጆች እና ማህበረሰቡ የህጻናትን መማር የሚያሻሽል ድጋፍ መስጠት እንዲችሉ መምህራን
እነዚህን አካላት የማሳተፍ፣ የማስተባበር ወይም የማነሳሳት በአጠቃላይ አብሮ የመስራት ሃላፊነት አለባቸው፡፡

ተግባር፡ የተማሪዎችን መማር በመመዘንና የምዘና መረጃን በመጠቀም ሂደት ወላጆችና መምህራን ሊፈጥሯቸው የሚችሉ
ቢያንስ ሶስት የግንኙነት ሁኔታዎችን በጥንድ በመወያየት ለክፍሉ አቅርቡ፡፡

6. የተማሪዎችን ባህርይ መመልከትና እውቀትና ችሎታቸውን የተመለከተ መረጃ መያዝ የቀን ተቀን ተግባር ሊሆን
ይገባል፡፡ መረጃ ሳንይዝ የተማሪዎችን መሻሻል ለማየት እርምጃ ለመውሰድ አንችልም፡፡ መረጃው ከግላዊ
አስተሳሰብና ጭፍን ጥላቻ የጸዳ ጠንካራ ጎኖችን፣ ድክመቶችን እና የተወሰዱ እርምጃዎችን የሚያሳይ ሊሆን
ይገባል፡፡ የተያዘውን መረጃ እንደአስፈላጊነቱ ወላጆችና ተማሪዎች እንዲያውቁት ይደረጋል፡፡ መረጃ የመያዝ
ተግባር የመምህራን ብቻ ሳይሆን የተማሪዎችም ተግባር ሊሆን ይችላል፡፡

ተግባር 1፡- የተማሪዎችን መማር የተመለከቱ መረጃዎች በሚከተለው መልኩ ተመዝግበው ሊያዙ ይችላሉ፤
ለእያንዳንዱ ግልጽ ትርጓሜና ምሳሌ/ዎች በመስጠት አስረዱ
 የተማሪዎችን መማር በተመለከተ የመምህሩ/ሯ እይታ/ግምገማ፣
 የተማሪዎች ግለ-ግምገማ ሪፖርቶች፤
 የመምህሩ/ሯ-ወላጆች-ተማሪዎች (ወተመ) የጋራ ውይይት ሪፖርት፤
 በተማሪዎች የተሰሩ የናሙና ስራዎች፤
 የአቻዎች ወይም ቡድናዊ አደረጃጀቶች የግምገማ ሪፖርት፤
 የተማሪው/ዋ ፖርትፎሊዮ፤
 በመምህሩ/ሯ የተሞሉ ቸክሊስቶች፣ ሬቲንግ ሰኬሎች፣ ሩብሪኮች
 የውጤት ማጠራቀሚያዎች(mark lists)፤ ሪፖርት ካርዶች
ተግባር 2፡ የምዘና መረጃን መዝግቦ መያዝ ሊያስገኛቸው ከሚችሉ ጠቀሜታዎች ቢያንስ ሁለቱን ጥቀሱ
1. _____________________________________________________________
2. _____________________________________________________________

ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል


xx
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች

7. የተሻለ ምዘና ተማሪዎች መልካም ስነምግባር እንዲያዳብሩ የሚረዳ ነው፡፡ መልካም ስነምግባርን መላበስ
ከመምህሩም፣ ከተማሪዎችም የሚጠበቅ እሴት ነው፡፡ ለምሳሌ ምዘናን ተግባራዊ ስናደርግ እያንዳንዱ ስራ
የተማሪዎች የራሳቸው መሆኑን ማረጋገጥና የሌላ ሰው ስራ ማቅረብን እንዲጠሉ ለማድረግ መጣር ይኖርብናል፡፡

ተግባር፡ በአንድ በተማሪ የተሰራ ስራ የተማሪው/ዋ የራሱ/ሷ መሆኑን ለማረጋገጥ ምን አይነት ስልቶችን ልንጠቀም
እንደምንችል በጥንድ በመወያየት ለክፍሉ ግለጹ፡፡
_________________________________________________________

8. የእያንዳንዱን ተማሪ የመማር ሁኔታ በመመዘን እና ተገቢ ግብረመልስ በመስጠት ተግባር ላይ ተማሪዎች ንቁ
ተሳታፊዎች ሊሆኑ ይገባል፡፡ ከዚህም አንጻር የምዘና ተሳታፊዎች መምህራን፣ ተማሪው /ዋ፣ አቻዎች ወይም
ቡድኖች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
ተግባር 1: የሚከተሉት በምዘና ሂደት ተማሪዎችን ማሳተፍ አስፈላጊ የሆነባቸው ምክንያቶች
ናቸው፡፡ እያንዳንዱን ነጥብ ካነበባችሁ በኋላ “እንዴት?” ብላችሁ ራሳችሁን በመጠየቅ
ለጥያቄዎቻችሁ በቂ መልስ ስጡ፡፡
1. ግለ-ምዘናና የአቻ ምዘና ተፈጥሮአዊ ናቸው፤
2. የመምህር ግምገማ ትክክለኛነትና አስተማማኝነት ሊጎለው ይችላል፤
3. ግለ-ምዘናና የአቻ ምዘና መማር ጥልቀት እንዲኖረው ይረዳል፤
4. ተማሪዎች መማርን የመመዘን ባህል እንዲኖራቸው ያደርጋል፤
5. ተማሪዎች የራሳቸውን መማር ራሳቸው እንዲመሩ ይረዳል፣
6. ተማሪዎች በትምህርታቸው በቂ ግብረ-መልስ እንዲያገኙ ያደርጋል፤

ተግባር 2፡-ተማሪዎች መረጃ የሚያገኙት


በግብረመልስ መልክ ነው፡፡ በቡድን በመሆን
የጥሩ ግብረመልስ ባህርያትን ዘርዝሩ
1. ___________________________________________
2. ___________________________________________
3. ___________________________________________
4. ___________________________________________
5. ___________________________________________

ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል


xxi
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች

ከግብ ወይም ከአላማ አንጻር ተከታታይ ምዘና በሁለት ዋና ዋና ምድቦች ተከፍሎ ሊታይ ይችላል፡፡ ሂደታዊ ተከታታይ ምዘና
(ሂተም) እና አጠቃላይ ተከታታይ ምዘና (አተም) በሚሉ፡፡

የሂደታዊ ተከታታይ ምዘና (ሂተም) ዋና ግብ የማስተማር መማር ሂደትን ማሻሻል ሲሆን የአጠቃላይ ተከታታይ ምዘና
(አተም) ዋና ግብ ደግሞ ፍትሃዊና ትክክለኛ በሆነ መልኩ የተማሪዎችን ውጤት መወሰን ነው፡፡

የክፍለ ትምህርት ሁለት ማጠቃለያ ጥያቄዎች


ቀጥሎ በቀረቡት የመወያያ ጥያቄዎች ላይ ለ 20 ደቂቃ ያህል ውይይት በማድረግ ለክፍሉ ተማሪዎች
በማብራራት አቅርቡ
1. የብቃት ምዘናን ከወረቀት ፈተና ጋር በማዎዳደር ልዩነታቸውን አሳዩ?
2. “ተከታታይ ምዘና ዑደታዊ ነው” ይባላል፡፡ ምን ለማለት ነው?
3. አንድ የቅድመ መደበኛ መምህርት የህጻናትን መማር ስትመዝን ከአንድ በላይ የምዘና ስልቶችን መጠቀም የሚያስፈልጋት
ለምድነው?
4. የምዘና መረጃን መዝግቦ መያዝ ለምን ያስፈልጋል?
5. የምዘና መረጃን መልሶ መጠቀም ማለት ምን ማለት ነው? ለምንስ ያስፈልጋል?

ክፍለ ትምህርት ሶስት

3. የቅድመ መደበኛ ትምህርት ምዘና ስልቶች

3.1 መደበኛና መደበኛ ያልሆኑ የምዘና ስልቶች

ከታች ካለው ምስል መረዳት እንደምትችሉት በአጠቃላይ የተከታታይ ምዘና ስልቶች መደበኛና መደበኛ ያልሆኑ በሚሉ ሁለት ምድቦች
ይመደባሉ፡፡ መደበኛ ያልሆኑት እንደገና ያልተደራጁና የተደራጁ በሚል በሁለት ይመደባሉ፡፡ መደበኛ የሆኑ የምዘና ስልቶች በጣም
የተደራጁ ናቸው፡፡ እነዚህን የምዘና ስልቶች በቅድመ መደበኛና በአንደኛ ደረጃ አንደኛ ሳይክል ትምህርትቤቶች የሚማሩ ተማሪዎችን
ውጤት ለመወሰን ተግባራዊ እንዲደረጉ አይመከርም፡፡ በዚህ ደረጃ የሚማሩ የህጻናትን ውጤት መደበኛ ያልሆኑ ነገር ግን የተደራጁ
የሚባሉ ስልቶችን በመጠቀም እንዲወሰን ይመከራል፡፡ እነዚህ የ ተደራጀ አካሄድ ያላቸው መደበኛ ያልሆኑ ስልቶች(ለምሳሌ
ትንሽ ሙከራ፣ የክፍል ስራ፣ የቤትስራ፣ የተግባርስራ፣ ወዘተ) በእቅድ ተግባራዊ የሚደረጉ ከሁሉም ህጻናት መረጃ
ለማግኘት በተመሳሳይ ለሁሉም ግብረመልስ ለመስጠትና መረጃን መዝግቦ ለመያዝ የሚመቹ ስልቶች ናቸው፡፡

ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል


xxii
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች

ተግባር፡- በመጀመሪያ መደበኛ ያልሆኑ የሂተም የመረጃ መሰብሰቢያ ስልት የሚባሉ ቢያንስ አምስት የተለያዩ ስልቶችን
በየግላችሁ ዘርዝሩ፤ በመቀጠል ጥንድ በመሆን የዘረዘራችሁትን አጠናክሩ፤ በመጨረሻ ሁለት ጥንዶች አንድ ቡድን (4
አባል) በመፍጠር ሁሉንም በተናጠል የታዩ የሂተም ስልቶችን አደራጅታችሁ የምዘና ስልቱ እንዴትና በምን ሁኔታ
ተግባራዊ እንደሚደረግ በማብራራት ለክፍሉ ተማሪዎች አቅርቡ፡፡

3.2. የብቃት ምዘና ስልቶች (Tools of authentic assessment)


ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆኑ የምልከታ ዘዴዎች በትምህርትቤቶች ተፈጥሮአዊ እየተደረጉ ያሉ ዋነኛ የብቃት መመዘኛ ስልቶች ናቸው፡፡
የሚከተሉት ዋና ዋና የብቃት ምዘና ስልት ምሳሌዎች ናቸው፡፡ የብቃት ምዘና ምሳሌዎች (examples of authentic
assessment)

ምዘና ማብራሪያ
ቃለ-መጠይቅ ተማሪዎችን ስለታሪካቸው፣ ስለሚያከናውኑት ተግባር፣ ስለአነቡትና ስለፍላጎቶቻቸው ወዘተ
(Interview) በመምህሩ/ሯ ለሚቀርብላቸው የተደራጀ መጠይቅ የተብራራ ምላሽ በቃል ይሰጣሉ፡፡
 ምልልሱ ያለማጨናነቅ፣ አዝናኝ ሆኖ ተግባራዊ ለደረግ ይገባል፣
 ከእያንዳንዱ ተማሪ ጋር ቃለ-መጠይቁ በተከታታይ ቀናት ተግባራዊ ይደረጋል፣
 በቃለ-መጠይቁ የሚገኘው መረጃ ተመዝግቦ (በአይነታዊ መረጃነት) የሚያዝ
ይሆናል፣
ታሪክ ማውራት ህጻናት በማዳመጥ ወይም በመስማት የተማሩትን ታሪክ መልሰው እንዲተርኩት/
/መተረክ እንዲናገሩት ማድረግ፣
(Story telling)  ህጻናት በቃል የሚተርኩትን ሪፖርት ያዘጋጃሉ፣
 የብቃት ምዘናው የተናገሩትን ፍሬ-ሃሳብ ወይም የቋንቋ አጠቃቀማቸውን መሰረት
በማድረግ ሊሆን ይችላል፣
 የመገምገሚያው መሳሪያው (መከታተያው) ሩብሪክ ወይም ሬቲንግ ስኬል ሊሆን
ይችላል፣
የተግባር ስራ /Project ህጻናት በተማሩት ይዘት ዙሪያ በተናጠል፣ በጥንድ ወይም በቡድን የተግባር ስራ ሰርተው
work ያቀርባሉ፣
 ህጻናት በቃል፣ በጽሁፍ ወይም በሁለቱም ስራዎቻቸውን ሊያቀርቡ ይችላሉ፣
 የህጻናትን የቃል እና የጽሁፍ ስራዎች እንዲሁም የአስተሳሰብ ብስለት ለማየት
ያስችላል፣
 የመከታተያ መሳሪያው ሩብሪክ ወይም ሬቲንግ ስኬል ሊሆን ይችላል፣
የመምህር/ት ምልከታ የህጻናት ባህርይ፣ አትኩሮት፣ ተነሳሽነት፣ ለትምህርት ተግባራት ያላቸው ምላሽ፣ ከሌሎች
Teacher Observation ተማሪዎች ጋር ያላቸውን ተግባቦት ወዘተ በመምህሯ/ሩ በቀጥታ ይታያል፣

ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል


xxiii
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች

 ምዘናው በመማር ላይ እያሉ ተግባራዊ ይደረጋል፣ ስለሆነም የሚወስደው ጊዜ


አጭር ነው፣
 እውነተኛ ባህርያቸውን እንዳይደብቁ፣ ወይም እንዳይደናገጡ ህጻናት በምልከታ ስር
እንደሆኑ ባያውቁ ይመረጣል፣
 የመከታተያ መሳሪያው የማረጋገጫ ዝርዝር፣ ደረጃ መመጠኛ ሰንጠረዥ ወይም
ሩብሪክ ሊሆን ይችላል
ፖርትፎሊዮ በአንድ ጭብጥ ላይ ትኩረት ያደረገ የህጻናትን በረጂም የጊዜ ሂደት መሻሻል የሚያሳይ
(Portfolios) የተጠራቀመ የህጻናቱ ስራ ነው፡፡
 ከተለያዩ ምንጮች የሚገኙ የምዘና መረጃዎችን (ከግለምዘና፣ ከአቻ፣ ከመምህር፣
ወላጆች) አጣምሮ ለማየት ያስችላል፤
 የህጻናትን መማርና መሻሻል ወይም መለወጥ በግልጽ ለማየት ያስችላል፣
 ህጻናት ቁርጠኞችና ንቁ ተሳታፊዎች እንዲሆኑ ያደርጋል፣
 ህጻናት የራሳቸውን መማር ራሳቸው የመመዘን ልምድን እንዲያዳብሩ ያደርጋል፣
ፅብረቃ (Reflection) ህጻናት የተረዱትን ጊዜ ሰጠው እንዲያስቡበት፣ ከውስጣቸው አውጥተው እንዲገልጹት ማድረግ
 የህጻናትን (በተናጠል ወይም የሁሉንም ህጻናት) የግናዛቤና የአስተሳሰብ ጥልቀት
በግልጽ ለማየት ያስችላል፤
የቡድን ውይይት ተማሪዎች በቡድን በመሆን ተወያይተው የተሰጣቸውን ተግባር እንዲሰሩ ማድረግ
ሪፖርት  የቡድን ውይይቱን ሂደት ወይም ውጤቱን መገምገም ይቻላል፤
 አንድን ቡድን ከሌላ ቡድን ጋር በማወዳደር ለሁሉም የአንድ ቡድን አባላት ተመሳሳይ ወይም በአንድ
ቡድን ውስጥ ያሉትን አባላት እርስ በእርስ በማወዳደር የተለያየ ውጤት እንዲያገኙ ማድረግ
ይቻላል

3.3 ግለ ምዘናና የአቻ ምዘና

3.3.1. ግለ-ምዘና/ Self-Assessment


ተግባር፡
1. ግለ ምዘና ምንድነው?
2. ግለ ምዘና ለምን ያስፈልጋል?
3. ግለ ምዘና መቼና እንዴት ተግባራዊ ይደረጋል?
ግለ-ምዘና ህጻናት የራሳቸውን መማር ከገመገሙ በኋላ የብቃት ደረጃቸውን የሚገልጹበት ሂደት ነው፡፡
ይህ ግምገማ የህጻኑን የእውቀት ደረጃ፣ አመለካከት፣ ክህሎትና የስሜት መዳበር ደረጃ የሚያካትት
ሊሆን ይችላል፡፡

ህጻናት ስለራሳቸው እና ስለመማራቸው ሁኔታ በግለ -ምዘና ግንዛቤን ይይዛሉ፡፡ ህጻናት ራሳቸውን
ገምግመው የሚገልጹበት ሁኔታ ምን ያህል በጥራት እየተማሩ መሆኑን ያመለክታል፡፡ ስለሆነም
የቅድመ መደበኛ መምህራን ህጻናት ራሳቸውን እንዲያዩ እድል ሊሰጧቸው ይገባል፡፡ ብዙውን ጊዜ
ህጻናት የመምህሩን ስራ ከራሳቸው ስራ ጋር በማነጻጸር ራሳቸውን ይገመግማሉ፡፡ በዚህ ሂደት ህጻናት
ከሰሯቸው ስራዎች መርጠው ለሌሎች እንዲያቀርቡ ሊበረታቱ ይገባል፡፡
ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል
xxiv
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች

ህጻናት ራሳቸውን ማየት እንዲችሉ መምህራን እንዴት ሊያግዟቸው ይችላሉ?


ህጻናት ራሳቸውን የማየት ክህሎትን ለማዳበር ጊዜ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ለዚህም መምህራን ለእያንዳንዱ
ህጻን በቂ ጊዜ በመመደብ የግለ-ምዘና ክህሎታቸውን እንዲያጎለብቱ ሊያግዟቸው ይገባል፡፡ ይህም
በሚከተለው መልክ ሊሆን ይችላል፡፡
የእገዛ ስልቶችም፡ (Helpful prompts include)፡
 መቼ ምን ሰራህ/ሽ …?
 እንዴት ሰራኸው/ሽው? ይኸንን ለመስራት ምን ተጠቀምህ/ሽ?
 ይኸንን በመስራትህ/ሽ ምን ሆነ?
 ይኸ ለምን የሆነ ይመስልሃል/ሻል?
 በዚም መንገድ ብታየው/ይው ምን የሚሆን ይመስልሃል/ሻል?
 በቀጣይ ምን መስራት አስበሃል/ሻል?
 ያንን እንዴት ልትሰራው/ሪው አሰብህ/ሽ?
 ይህንን ስትሰራ/ሪ የቀለለህ/ሽ የቱ ነው?
 ይህንን ስትሰራ/ስትሰሪ ያስቸገረህ/ሽ የቱ ነው?
 ከዚህ ምን ትማራለህ/ ሪያለሽ?
 እንደገና ብትሰራው/ሪው እንዴት ባለ በተለዬ ሁኔታ ትሞክረዋለህ/ሪዋለሽ?

3.3.2. የአቻ ምዘና/ Peer assessment


የአቻ ምዘናን ህጻናት በተመሳሳይ ደረጃ ያሉ አቻዎቻቸውን ስራ እንዲገመግሙ የማድረግ ሂደት ነው፡፡
የአቻ ምዘና ህጻናት እርስበርሳቸው እንዲማማሩ፣ ግብረመልስ መስጠትና መቀበል እንዲችሉ እድል
ይሰጣል፡፡ የአቻ ምዘና የመማሩን ሂደት ለማሻሻል የሚረዳ መረጃ ለማግኘት ብቻ ሳይሆን፣ ከተገቢ ስልጠና
በኋላና የቅርብ ክትትል በማድረግ የህጻናትን ውጤት ለመወሰንም ያስችላል፡፡

ከላይ ከገለጽናቸው በተጨማሪ የአቻ ምዘና ሌሎች በዛ ያሉ ጠቀሜታዎች ይኖረዋል:


 የአቻ ምዘና ሃጻናት ግብረመልስ እንዲያገኙ ይረዳል፡፡ አንዳንዴ ተማሪዎች ከመምህር
ግብረመልስ በተሻለ አሳማኝ የሆነ ግብረ-መልስ ሊያገኙ ይችላሉ፡፡
 የአቻ ምዘና ግብረመልስ ሰጭውንም ግብረመልስ ተቀባዩንም ይጠቅማል፡፡ ገንቢ ግብረመልስ
መስጠት በራሱ ተፈላጊ ክህሎት ነው፡፡ ይህን እውን ለማድረግ ህጻናት ግብረመልስ የመስጠት፣
ነገሮችን በጥልቀት የማየት፣ የማሳመን፣ የመከላከል ክህሎታቸውን ያጎለብታሉ፡፡
 ገንቢ ግብረመልስ መቀበል እንዲሁ ተፈላጊ ክህሎት ነው፡፡ ሃጻናት ነገሮችን የመቀበል
የማቻቻል ክህሎት ያዳብራሉ፡፡ ገንቢ አስተያየት የመቀበል ልምድ ይኖራቸዋል፡፡
ከመስፈርቶች አንጻር ራሳቸውን የሚያዩበት እድል ይፈጥራል፡፡

በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች ልጆች ገና ህጻናት በመሆናቸውና ስራዎችን ገምግመው አስተያየት
የመስጠት ክህሎት ያላጎለበቱ በመሆናቸው የአቻ ምዘና ብዙ አይዘዎተርም፡፡ መምህራን ህጻናትን በቀጥታ

ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል


xxv
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች

በመምራት ተግባሩን በብቃት እንዲፈጽሙት ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ ለምሳሌ ህጻናት የእንስሳትን ድምጽ
ሲያሰሙ፣ ሲደንሱ፣ ስዕል ሲስሉ፣ ሲዘፍኑ ወዘተ ምን ያህል ትክክል ነው /ናት በማለት አስተያየት እንዲሰጡ
የመምህሩ/ሯ ጥያቄ ለአቻ ምዘና ሊያበረታታ ይችላል፡፡ ተማሪዎች ለተሳሳቱና ትክክለኛ ምላሾች በምልክት
አስተያየት እንዲሰጡ ማድረግም ይቻላል፡፡

የክፍለ ትምህርት ሶስት ማጠቃለያ የውይይት ጥያቄዎች

ቀጥሎ በቀረቡ ጥያቄዎች ላይ ውይይት በማድረግ ለክፍሉ ተማሪዎች በማብራራት አቅርቡ፡፡

1. መደበኛና መደበኛ ያልሆኑ የምዘና ስልቶች አንድነትና ልዩነትን በምሳሌዎች በማስደገፍ እንዴት
ይገለጻሉ?
2. ዋና ዋና የብቃት ምዘና ስልቶችን በማሰልጠኛ ሞጁዬሉ ከቀረቡት በተጨማሪ በመዘርዘር በስፋት
በማብራራት አቅርቡ፡፡
3. ግለ-ምዘናና የአቻ-ምዘናን እንዴት ተግባራዊ ማድረግ እንደሚቻል በምሳሌዎች በማስደገፍ
አቅርቡ፡፡

ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል


xxvi
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች

ክፍለ-ትምህርት አራት

4. የቅድመ-መደበኛ ህጻናት የመዳበር ዘርፎችን የመመዘኛ ስልቶች

በዚህ ክፍለ ትምህርት ቀደም ሲል የተማርናቸውን የምዘና ስልቶች የህጻናት የመዳበር ደረጃዎችን ለመመዘን
ተግባራዊ የምናደርግባቸውን ስልቶች በምሳሌ አስደግፈን እናያለን፡፡ የህጻናት መዳበር ከሚከተሉት አራት
ደረጃዎች አንጻር ሊታይ ይገባል፡ አካላዊ መዳበር (የሰውነት የመጠን ለውጥና የአካል ቅልጥፍና መዳበር)፣
አእምሮአዊ እና የቋንቋ መዳበር (የማሰብ፣ ምክንያታዊነት፣ የማስታዎስ፣ ወዘተ እና የቋንቋ ችሎታ)፣ እና
ስነባህርያዊ-ማህበራዊ መዳበር (ከሌሎች ጋር የመግባባትና የስብዕና ለውጥ) ክህሎቶችን ይይዛል፡፡ ስለሆነም
በዚህ ሞጁል እነዚህን የመዳበር ዘርፎች የምንመዝንባቸውን ስልቶች እናያለን፡፡

የመማር ውጤቶች፡
ከዚህ ክፍለ ትምህርት በኋላ የቅድመ መደበኛ ዕጩ መምህራን:
 ልንመዝናቸው የሚገቡ የህጻናት መዳበር ዘርፎችን ይገነዘባሉ፣
 የተለያዩ የህጻናት መዳበር ዘርፎችን ለመመዘን የሚያስችሉ የተሻሉ ስልቶችን ይመርጣሉ፤
 የመረጡትን የምዘና ስልት በምክንያት ያስረዳሉ፤
 የህጻናትን መዳበር ዘርፎችን ለማቃናት የሚያስችል መረጃ ለማግኘት ምዘናን አዘጋጅተው
ይጠቀማሉ፡፡

4.1. አካላዊና የአካላዊ እንቅስቃሴ የመዳበር ምንነትና የምዘና ስልቶች

ተግባር፡-
1. አካለዊ መዳበር ምንድነው?

2. አካለዊ መዳበር እንዴት ይመዘናል?

አካላዊ መዳበር የህጻናት የክብደት፣ የቁመት እና የአካላዊ እንቅስቃሴ ክህሎት ለውጥን ይመለከታል፡፡ ወላጆችና
የቅድመ መደበኛ መምህራን የህጻናት መዳበር አይነቶች ይከሰቱባቸዋል ተብለው የሚጠበቁ ዋና ዋና ጊዜያትን
ለይተው ሊያውቋቸው ይገባል፡፡ የአካላዊ እንቅስቃሴ ክህሎት የህጻናትን የአካል ክፍሎች ለይቶ መረዳትን፣
የአካል ክፍሎችን ቅንጅትን፣ ሚዛን የመጠበቅ ሁኔታን፣ የእጅ ቅልጥፍናን፣ የአይንና የእጅ መስተጋብርን

ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል


xxvii
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች

ይመለከታል፡፡ የሚከተለው ደረጃ መመጠኛ ሰንጠረዥ የቅድመ መደበኛ ህጻናት የአካላዊ እንቅስቃሴ ክህሎት
እንዴት እንደሚመዘን ያሳያል፡፡
የአካላዊ እንቅስቃሴ ክህሎት መመዘኛ ደረጃ መመጠኛ ሰንጠረዥ
የህጻኑ/ኗ እድሜ: ____________________ምልከታው የተደረገበት ቀን ____________
ምልከታውን ያደረገው መምህር ስም: _______________________________________
ማውጫ፡ 4=እጂግ በጣም ጥሩ፣ 3=በጣም ጥሩ፣ 2=በቂ የሚባል፣ 1=ደካማ
1. የአካል ክፍሎችን ለይቶ መረዳት ሚዛን የተመዘነው ብቃት እና የተሰጠ ግብረ
Body Awareness 4 3 2 1 መልስ
ምሳሌ፡
 የአካል ክፍሎቻቸውን በስም መጥራት፣
 የአካል ክፍሎቻቸውን መስተጋብር መለየት፤
 በተለያየ መንገድ ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ መቻል፤
 በስልት መንቀሳቀስ፣ መደነስ፤
 እንቅስቃሴን በሚጠይቁ ተግባራትና ጨዋታዎች
መሳተፍ
2. የሰውነት ጡንቻዎችን ማቀናጀት መቻል ሚዛን የተመዘነው ብቃት እና የተሰጠ ግብረ
Muscle Coordination 4 3 2 1 መልስ
ምሳሌ፡
 በትንሽ መሰላል ወይም ደረጃዎች ላይ መውጣትና
መውረድ መቻል፣
 ክብ ቁሶችን ማሽከርከር መቻል፣
 ቁሳቁሶችን ማቀበል፣ መቀበል እና ኳስ መሰል ቁሶችን
መምታት መቻል፤
 ከፍተኛ አካላዊ እቅስቃሴን በቅልጥፍናና በቅንጂት
ማከናዎን መቻል
3. ሚዛንን የመጠበቅ ሁኔታ/ ሚዛን የተመዘነው ብቃት እና የተሰጠ ግብረ
Balance 4 3 2 1 መልስ
ምሳሌ:
 በአንድ እግር መቆምና መዝለል መቻል፣
 በእግር እጣቶች ረጂም ርቀት መጓዝ፤
 ሚዛን ጠብቆ በአግዳሚ ጣውላዎች ላይ መሄድ፤
 ወደኋላ መጓዝ መቻል
4.የእጅ ቅልጥፍናን/ ሚዛን የተመዘነው ብቃት እና የተሰጠ ግብረ
Manual Dexterity 4 3 2 1 መልስ
ምሳሌ:
 የመመገበያና መጠቀሚያ ቁሶችን ማጽዳትና በሚገባ መጠቀም
መቻል፤
 የመጫዎቻ ቁሳቁሶችን ከጭቃ (የተቦካ ወረቀት) በተለያዩ
ቅርጾች በማዘጋጀት መጫዎት መቻል፤

ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል


xxviii
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች

 ትናንሽ ቁሶችን መልቀም/ ከመሬት ማንሳት መቻል፤


 የመጻፊያ ቁሳቁሶችን በሁለት እጣቶች በሚገባ መያዝ መቻል፤
5. የአይንና የእጅ መስተጋብርን/ ሚዛን የተመዘነው ብቃት እና የተሰጠ ግብረ
Eye-Hand Coordination 4 3 2 1 መልስ
ምሳሌ፡
 በትናንሽ የግንባታ ቁሶች በቀላሉ መጫዎት መቻል፤
 ሊሽከረከሩ የሚችሉ ቁሶችን ማጦዝ መቻል፣
 በመቀስ መቁረጥ መቻል፤
 የአካል ክፍሎችን የለዬ ስዕል መሳል መቻል፣
 የፊደል አጣጣልን ማጥራት፣

በሌላ አነጋገር የቅድመ መደበኛ መምህራን የህጻናትን የመዳበር ሁኔታ ለመመዘን የሚያስችል የመገምገሚያ
መሳሪያን በእድሜአቸው ከህጻናት ከሚጠበቁ የመዳበር ለውጦች ጋር በማዛመድ ማዘጋጀት ይቻላል፡፡
ለምሳሌ፡
የአካላዊ መዳበር አመላካቾች/ Physical development indicators
የእድሜ ጠቅላላ እንቅስቃሴ አይነቶች/ ውስብስብ አካላዊ ብቃቶች/
ክልል Gross motor Fine motor
ከ 2-3  በቀላሉ መሮጥ፣ መታጠፍና በፍጥነት መቆም  ክብ ምስሎችን መስራት፤
ዓመት መቻል፤  የጠርሙስ እፊያዎችን መክፈትና መግጠም፤
 መሰላል መውጣትና መውረድ፣  ትናንሽ የመጫዎቻ ቁሶችን በተገቢ ቦታቸው ለይቶ
 በመንሸራተቻዎች ተንሸራቶ መውረድና ማስቀመጥ፤
ያለአጋዥ መልሶ መውጣት መቻል  የህጻናትን መጽሃፍ በአንድ ጊዜ አንድ ገጽ በመግለጽ
 ሁለት እግርን በአንድ ላይ በማድረግ ማየት መቻል፤
(እንደእንቁራሪት) መዝለል መቻል፤  በትናንሽ መቀሶች/ መቁረጫዎች ለመቁረጥ
 ለጥቂት ደቂቃዎች ያለድጋፍ በአንድ እግር መቆም መሞከር፤
መቻል፤  ስምንትና በላይ ኩቦችን በመደራረብ ማስቀመጥ
 ወደፊት በጀርባ መንከባለል (ሮል ማድረግ) መቻል፣
መቻል፤  እንደ አንድ ጎልማሳ ቾክ በእጅ በመያዝ መጻፍ
 ቁሶችን ተራምዶ ማለፍ መቻል መቻል
 ራስን ችሎ ደረጃዎችን መውጣትና መውረድ
መቻል
ከ 3-4  በሩጫ ጊዜ መንገድ ላይ ያሉ ቁሶችን/ እንቅፋቶችን  አግዳሚና ቋሚ መስመሮችን መሳል፣
ዓመት በመዝለል ማለፍ መቻል  ሙሉ ክብን መሳል/ ከሌላ አይቶ መሳል፤
 ባለሶስት ጎማ ብስክሌቶችን ማሽከርከር መቻል፤  በኩቦች የቤት፣ የድልድይ ወይም የመኪና ሞዴሎችን
 ያለድጋፍ በአንድ እግር መቆም መቻል መስራት፣
 በአንድ እግር ቢያንስ ሁለት ጊዜ ያለድጋፍ መዝለል  በመቀስ ወረቀቶችን አስተካክሎ መቁረጥ፣
መቻል  አቋራጭ የሆኑ ሁለት መስመሮችን መሳል፣
 ዘጠኝ እና በላይ ተገጣጣሚ መጫዎቻዎችን( puzzles)
በስልት ማስቀመጥ፣

ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል


xxix
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች

ከ 4-6  ያለድጋፍ በአንድ እግር በመዝለል ቁሶችን መዞር፣  ትርጉም ያለው ስዕል መሳል መቻል፤
ዓመት  ከሌላ ህጻን ጋር ሌባና ፖሊስ መጫዎት፤  አራቱ ማዕዘን በግልጽ የሚታይ ካሬ/ አራት ጎን
 ኳሶችን መወርዎርና መቅለብ መቻል፤ መስራት፤
 ንድፍን ተከትሎ ወረቀትን በመቀስ መቁረጥ መቻል፤
 ቢያንስ ሶስት ግልጽ ያካል ክፍል ያለው (ምሳሌ ራስ፣
እግር፣ እጅ ወይም ሌላ) ሙሉ የሰው ምስል መሳል
መቻል፤
 መስመር ሳያልፉ የምስሎችን ውስጥ ቀለም መቀባት
መቻል፤
 አቅዶና በስልት ስዕል መሳልና ቀለም መቀባት
መቻል፣

4.2. አዕምሮአዊ መዳበርንና የቋንቋ ችሎታን የመመዘኛ ስልቶች

ተግባር:
1. የአዕምሮአዊ እና ቋንቋ መዳበር ምንድን ናቸው? (ልዩነትና አንድነት)
2. የህጻናት የቋንቋ መዳበር እንዴት ይመዘናል?

አዕምሮአዊ መዳበር የአእምሮ ችሎታን ለምሳሌ የማሰብ፣ የማሳታዎስ፣ ችግር የመፍታት፣


ምክንያት የመስጠትና የመሳሰሉትን ችሎታዎች ይመለከታል፡፡ አዕምሮአዊ መዳበር በውስጡ
የቋንቋ መዳበርን ይይዛል፡፡ የቋንቋ መዳበር የተለያዩ ምልክቶችን በስርዓት በመጠቀም የተለያዩ
መልእክቶችን የማስተላለፍ ብቃትን ይመለከታል፡፡ ይኸውም የመናገር፣ የማንበብ፣ የማዳመጥ፣
እና የመጻፍ ችሎታዎችን ያካትታል፡፡ የሚከተለው ደረጃ መመጠኛ ሰንጠረዥ የቅድመ መደበኛ ህጻናት
የአእምሮአዊና የቋንቋ መዳበር እንዴት እንደሚመዘን ያሳያል፡፡

የቅድመ መደበኛ ህጻናትን አዕምሮአዊ መዳበር መመዘኛ ደረጃ መመጠኛ ሰንጠረዥ


የህጻኑ/ኗ እድሜ: ____________________ምልከታው የተደረገበት ቀን __________
ምልከታውን ያደረገው መምህር ስም: _______________________________________
ማውጫ፡ 4=እጂግ በጣም ጥሩ፣ 3=በጣም ጥሩ፣ 2=በቂ የሚባል፣ 1=ደካማ
1. የቁጥር ጽንሰ-ሃሳብ/ Number Concepts መመዘኛ ቁጥር የተመዘነው ብቃት እና የተሰጠ ግብረ
4 3 2 1 መልስ
ምሳሌ:
 አንድ ለአንድ በማጣመር ቁሶችን ይደረድራሉ፣
 ቁጥሮችን መለየት፣
 እስከ አምስት የሚደርሱ ቁሶችን መቁጠር፣

ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል


xxx
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች

 ቁጥሮችን ማዎዳደር፣
 መስፈር/ መለካት መቻል(ውሃ፣ አሸዋ ወዘተ)፣
2. ቅርጽን መለየት እና ቦታን መረዳት/ Shapes / Spatial Skills ሚዛን ቁጥር የተመዘነው ብቃት እና የተሰጠ ግብረ
4 3 2 1 መልስ
ምሳሌ:
 ቅርጾችን ማስታዎስ፣ መጥራትና መግለጽ መቻል፤
 ሚገጣጠሙ ቀላል መጫወቻዎችን መገጣጠም፤
 አቅጣጫን እና ቦታን መግለጽ፤
 ተመሳሳይ ቅርጽ ያላቸውን ቁሶች መመደብ፤
 የአንድ ነገር ክፍሎችን ከዋናው አካል ጋር ማዛመድ፤
3. በቅደም ተከተል/ በስርዓት ማስቀመጥ/ ሚዛን ቁጥር የተመዘነው ብቃት እና የተሰጠ ግብረ
Patterns/ Sequences 4 3 2 1 መልስ
ምሳሌ:
 ቀላል አሰላለፎችን (patterns) ማስታዎስና መልሶ
መስራት፤
 መሰረታዊ የጊዜ ሃሳቦችን መረዳት፤
 ቁሶችን/ ስእሎትን መቅደም ተከተላቸው ማስቀመጥ፤
 በአካባቢ የተከሰቱ ለውጦችን ማስታዎስ፤
4. መመደብ መቻል/ Classification ሚዛን ቁጥር የተመዘነው ብቃት እና የተሰጠ ግብረ
4 3 2 1 መልስ
ምሳሌ:
 የሚመሳሰሉ ቁሶችን ማዛመድ፣
 በቁሶች መካከል ያለ ልዩነትንና አንድነትን መግለጽ፣
 ቁሶችን በባህርያቸው (attributes) መምረጥ፣
 ግራፎችን በመስራትና በመጠቀም ሂደት ማገዝ፣
5. ችግር ፈችነት/ Problem Solving ሚዛን ቁጥር የተመዘነው ብቃት እና የተሰጠ ግብረ
4 3 2 1 መልስ
ምሳሌ:
 ችግሮችን ለመፍታት ምልከታ ማካሄድ፣
 ሳይንሳዊ የችግር መፍቻ ቁሶችን መጠቀም፣
 ምክንያትና ውጤትን ለመለየት መመራመር፣
 ከቀደመ ልምድ በመነሳት ውጤትን መተንበይ፣
 ሳይንሳዊ ቃላትና ሃረጋትን መጠቀም፡፡

የቅድመ መደበኛ ህጻናት የቋንቋ መዳበር መመዘኛ ደረጃ መጣን ሰንጠረዥ


የህጻኑ/ኗ እድሜ: ____________________ምልከታው የተደረገበት ቀን ____________
ምልከታውን ያደረገው መምህር ስም: _______________________________________
ማውጫ፡ 4=እጂግ በጣም ጥሩ፣ 3=በጣም ጥሩ፣ 2=በቂ የሚባል፣ 1=ደካማ
1. ማዳመጥ/ Listening ሚዛን ቁጥር የተመዘነው ብቃት እና የተሰጠ ግብረ

ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል


xxxi
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች

4 3 2 1 መልስ
ምሳሌ:
 ታሪክን ማዳመጥና ምላሽ መስጠት፣
 ለተጠየቁ ጥያቄዎች መልስ መስጠት መቻል፣
 ትዕዛዝ መቀበልና መፈጸም፣
 መረጃን መልሶ ማስታዎስ መቻል፣
2. መስማት/ Auditory ሚዛን ቁጥር የተመዘነው ብቃት እና የተሰጠ ግብረ
4 3 2 1 መልስ
ምሳሌ:
 ዜማዊ ቃላትን መለየት፣
 ፊደል ድምጾችን ከቅጾች ጋር ማዛመድ መቻል፣
 በመነሻ ድምጽ ቃላትን መለየት፣
 ድምጾችን በአናባቢዎቻቸው መክፈል መቻል፣
3. መናገር መቻል/ Speech Production ሚዛን ቁጥር የተመዘነው ብቃት እና የተሰጠ ግብረ
4 3 2 1 መልስ
ምሳሌ:
 አዳዲስ ቃላትን በንግግር ውስጥ መጠቀም መቻል፣
 ጥያቄ መጠየቅ መቻል፣
 ሙሉ አረፍተ ነገር በመስራት መናገር፣
 ፊደላትን በትክክል መጥራት፣
4. ማንበብ መቻል/ Reading ሚዛን ቁጥር የተመዘነው ብቃት እና የተሰጠ ግብረ
4 3 2 1 መልስ
ምሳሌ:
 ለራስና ለሌሎች አንብቦ ለማሳየት መሞከር፣
 ምልክቶችን ከአካባቢያዊ ሁኔታዎች ጋር ማዛመድ መቻል፤
 አነባበብን (ከግራ ወደቀኝ እና ከላይ ወደታች እንደ ሚነበብ)
ማዎቅ፣
 ፊደላትን እና የተለመዱ ቃላትን መገንዘብ፤
5. መጻፍ መቻል/ Writing ሚዛን ቁጥር የተመዘነው ብቃት እና የተሰጠ ግብረ
4 3 2 1 መልስ
ምሳሌ:
 ቀላል ቅርጾችን አስመስሎ መሳል ወይም መኮረጅ መቻል፣
 የሰዎችን አጻጻፍ አስመስሎ መጻፍ፣
 ጽፎ ለማሳየት (ለጎልማሶች) ቁርጠኛ መሆን፣
 የሰሙትን ፊደላትና የተለመዱ ቃላትን መጻፍ መቻል፣

የቅድመ መደበኛ ህጻናትን የአዕምሮአዊና የቋንቋ መዳበርን ለመመዘን የሚከተሉትን የባህርይ ጠቋሚዎች
በማገናዘብ መጠቀም ይኖርብናል
የአእምሮአዊና የቋንቋ መዳበር ጠቋሚዎች /indicators ሚዛን ቁጥር
ምርመራ
3 2 1
ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል
xxxii
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች

 የምርምር ፍላጎትን ማሳየት/ Engages in inquiry

 ችግሮችን መፍታት/ Solving Problems


 ቁሶችን መመደብ/ Sort Objects
 ቅርጾችን መስራት/ Makes patterns
 ማዎዳደርና በቅደም ተከተል ማሳቀመጥ/ Compares and orders
 በቁጥር መግለጽ/ Quantifies
 ቦታን መረዳት/ Shows spatial awareness
 አረፍተ ነገር መጠቀም/ Uses sentences
 ቃለ-ምልልሶችን መረዳት/ Understands conversations
 ታሪክን መረዳት/ Understands stories
 መጽሃፍትን መረዳት/ Understands books
 ድምጾችን ማስታዎስ/ Recognizes sounds
 ቃላትን መለየት/ Identifies words
 ትርጉሞችን መጻፍ/ Writes for meaning

4.3 የማህበራዊና ስሜታዊ መዳበር መመዘኛ ስልቶች


ማህበራዊ መዳበር ማለት በልጆች የአካላዊና የእድሜ የእድገት ሂደት ከሰዎችና ከማህበረሰቡ ጋር ያላቸው ግንኙነት
የመፍጠር ሁኔታ ነው፡፡ ስሜታዊ መዳበር ስንል ደግሞ ህጻናት ስሜታቸውን ለመረዳትና ለመቆጣጠር የሚያስችላቸውን
ልምድ ወይም ችሎታ እየጨመረ መሄድ ማለት ነው፡፡ በመሰረቱ ስሜታዊ መዳበር ብቻውን ሳይሆን ከአእምሮአዊ፣
ማህበራዊ፣ ባህርያዊ መዳበሮች ጋር አብሮ ሚከሰት ነው፡፡ ማህበራዊና ስሜታዊ መዳበሮች የማይነጣጠሉ ናቸው፡፡
ማህበራዊና ስሜታዊ መዳበሮች በምልከታ፣ እና ሌሎች ስልቶች ሊመዘኑ ይችላሉ፡፡

የማህበራዊ መዳበር መመዘኛ ደረጃ መመጠኛ ሰንጠረዥ


የህጻኑ/ኗ እድሜ: ____________________ምልከታው የተደረገበት ቀን __________
ምልከታውን ያደረገው መምህር ስም: _______________________________________
ማውጫ፡ 4=እጂግ በጣም ጥሩ፣ 3=በጣም ጥሩ፣ 2=በቂ የሚባል፣ 1=ደካማ
1. ተግባቦት/ Communication ሚዛን ቁጥር የተመዘነው ብቃት እና የተሰጠ ግብረ
4 3 2 1 መልስ
ምሳሌ:
 ስሜትን በቃላትና በቃላ አልባ ዘዴዎች መግለጽ፣
 ግለሰባዊ ሁኔታዎችን በንግግር መግለጽ፣
 በቡድን ውይይቶች መሳተፍ፣
 በንግግርና ማዳመጥ ሂደት ለሌሎች ተራ መስጠት፣
2. መተባበር መቻል/ Cooperation ሚዛን ቁጥር የተመዘነው ብቃት እና የተሰጠ ግብረ
4 3 2 1 መልስ
ምሳሌ:
 ከሌሎች ጋር በሚገባ መስራትና መጫዎት መቻል፣
ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል
xxxiii
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች

 ለሌሎት አስተያየት ምላሽ መስጠት፣


 መካፈልና ድርሻን መውሰድ መቻል፣
 ከሌሎች ጋር መደራረር መቻል፣
3. ሃላፊነትን የመቀበል ብቃት/ Respectfulness ሚዛን ቁጥር የተመዘነው ብቃት እና የተሰጠ ግብረ
4 3 2 1 መልስ
ምሳሌ:
 የአክብሮት ቃላትን መጠቀም፣
 ለሌሎች ሰዎችና ለንብረቶች ክብር መስጠት፣
 ለልዩነቶች አውንታዊ ምላሽ መስጠት፣
 የሌሎችን ንግግሮች ማዳመጥ፡
4. የሌሎችን ስሜት መረዳትና መጋራት/ Empathy ሚዛን ቁጥር የተመዘነው ብቃት እና የተሰጠ ግብረ
4 3 2 1 መልስ
ምሳሌ:
 የሌሎችን ስሜት ለመግለጽ ምልክትን መጠቀም፣
 የሰዎችን ስሜት ለማስረዳት ሙከራ ማድረግ፤
 ለሌሎች እገዛ ማድረግ፣
 ሌሎች ምን እንደሚፈልጉ መገመት መቻል፣
 ነገሮችን/ ችግሮችን ከሌሎች አንጻር ማየት መቻል፣
5. ማህበረሰባዊ ተሳትፎ/ Community ሚዛን ቁጥር የተመዘነው ብቃት እና የተሰጠ ግብረ
4 3 2 1 መልስ
ምሳሌ:
 ለመማሪያ ክፍሎችና ለቁሳቁሶች መጠንቀቅ፣
 በክፍል ውስጥ ስራዎች መሳተፍ፣
 በቡድን እንደ አንድ አባል በንቃት መሳተፍ፤
 በማህበረሰብ ውስጥ የሰዎችን ሚና መረዳት፡፡

በተጨማሪም አንድ/ዲት የቅድመ መደበኛ መምህር/ት የሚከተሉትን የማህበራዊና ስሜታዊ መዳበር


ጠቋሚዎች በመጠቀም የቃለ መጠይቅ፣ ደረጃ መመጠኛ ሰንጠረዥ፣ ማረጋገጫ ዝርዝር ወይም ሩብሪክ
ማዘጋጀትና መጠቀም ይችላል/ትችላለች፡፡ ስለሆነም የሚከተሉት ዋና ዋና መነሻ የማህበራዊና ስሜታዊ
መዳበር ጠቋሚዎች ናቸው፡፡

 ያለችግር ከሌሎች ጋር ውስብስም የተግባቦት ጫዋታዎችን መድረግ መቻል፣


 ጠንካራና ፈጣን ጨዋታን መልመድና ማዘውተር(ለወንዶች)
 ትብብራዊ ጨዋታን (cooperative play) መምረጥ፣
 ጎናዊ ጨዋታን (parallel play) በቡድናዊ ጨዋታ (group play) መተካት፣
 ከብቻ ይልቅ ከሌሎች ጋር መጫዎትን መምረጥ፣
 ሃሳብና ስሜትን መግለጽ መቻል፣
 የሌሎችን ስሜት መረዳት መቻል፣

ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል


xxxiv
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች

 ፍርሃትና ተስፋ መቁረጥን መቋቋም፣


 በራስ የመተማመን ስሜትን ማሳየት፣

የህጻናትን ማህበራዊ-ስሜታዊ መዳበር ለመመዘን መምህራን ሊጠይቋቸው የሚገቡ ሌሎች ተጨማሪ


ጥያቄዎች

 ከሌሎች ህጻናት ጋር በመሆን የማውራት፣ የመሳቅ እና የመጫዎት ሁኔታው/ታዋ ምን


ይመስላል?
 ህጻኑ/ኗ በቀላል ህጎች የሚመሩ ጫዎታዎችን በቡድን ይጫዎታል/ትጫዎታለችን?
 ህጻኑ/ኗ የሌሎችን ስሜት ለመጠበቅ ይጥራል/ትጥራለችን?
 ህጻኑ/ኗ ሊሎችን ይቀርባል/ትቀርባለችን?
 ህጻኑ/ኗ የሌሎችን መስተጋብር የማነሳሳት ልምድ አለው/አላትን?
 ህጻኑ/ኗ ተግባቢ፤ ግልጽና በሌሎች ዘንድ ተፈላጊ ነውን/ናትን?
 ነገሮችን መግፋትና መሳብ ይችላል/ትችላለችን?
 ህጻኑ/ኗ ራዕይ ያለው/ላት እና ለማሳዎቅ የሚጥር ነውን/ናትን?
 ከሌሎች ህጻናትን ባህርይ የማስተናገድ ሁኔታው ምን ይመስላል (ማፈግፈግ፣ መሳተፍ፣
መጋፈጥ)?
 ግጭቶችን እንዴት ይፈታል/ ለመፍታት ይሞክራል?
 ህጻኑ/ኗ ስለሌሎች ህጻናት ምን አይነት ሰሜት ይታይበታል?
 ልዩ ችግሮች ይታይበታል/ባታልን (ለምሳሌ፡ ትግስት ማጣት፣ መማታት፣ መበሳጨት፣
አለመናገር፣ አብዝቶ የመምህርን ድጋፍ መሻት)?
 ህጻኑ/ኗ በቡድን ውስጥ የቱን ይመስላል (መሪ፣ ተከታይ ወይስ በጥባጭ)?
 ህጻኑ/ኗ በሌሎች ህጻናት ዘንድ ተመራጭ ነው/ ናትን?

የስብዕና መዳበር መመዘኛ ደረጃ መመጠኛ ሰንጠረዥ

የህጻኑ/ኗ እድሜ: ______________________ምልከታው የተደረገበት ቀን ________


ምልከታውን ያደረገው መምህር ስም: _________________________________
ማውጫ፡ 4=እጂግ በጣም ጥሩ፣ 3=በጣም ጥሩ፣ 2=በቂ የሚባል፣ 1=ደካማ
1. በራስ መተማመን/ Confidence ሚዛን ቁጥር የተመዘነው ብቃት እና የተሰጠ ግብረ መልስ
4 3 2 1
ምሳሌ:
 በአዲስ ሁኔታዎች ራስን ማላመድ
 በራስ ስራ መኩራት

ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል


xxxv
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች

 ፅናት (ጀምሮ መጨረስ)


 ማቀድና ግብ መጣል
 አዲስ ነገር መጀመር
2. የሃላፊነት ስሜት/ Responsibility ሚዛን ቁጥር የተመዘነው ብቃት እና የተሰጠ ግብረ መልስ
4 3 2 1
ምሳሌ:
 የራስን ስሜት መረዳትና መቆጣጠር፣
 የራስ ንብረት በጥንቃቄ መያዝ፣
 የክፍል የመተዳደሪያ ደንብን መከተል፣
 የግል መረጃን ማዎቅ (ሙሉ ስም፣ እድሜ፣
ስልክ ቁጥር፣ አድራሻ)
3. ራስን መቻል/ Independence ሚዛን ቁጥር የተመዘነው ብቃት እና የተሰጠ ግብረ መልስ
4 3 2 1
ምሳሌ:
 ለአላማ መጽናትን በተግባር ማሳየት፣
 ፍላጎትን መግለጽ፣
 ክህሎትን በራስ ጥረት ማዳበር፣
 በመረጃ የተመሰረተ ምርጫ መያዝ
4. የፈጠራ ችሎታ/ Creativity ሚዛን ቁጥር የተመዘነው ብቃት እና የተሰጠ ግብረ መልስ
4 3 2 1
ምሳሌ:
 ወጥ ስራ መፍጠር፣
 የነገሮችን ወካይ በስዕል ወይም በቅርጽ
መስራት፣
 ሚና ጨዋታን መሳተፍ፣
 በቁሶችና ነገሮች ላይ እምነት መጣል፣
5. ራስን መጠበቅ/ Health and Safety ሚዛን ቁጥር የተመዘነው ብቃት እና የተሰጠ ግብረ መልስ
4 3 2 1
ምሳሌ:
 ለጤና ተስማሚ የሆኑ ምግቦችን መለየትና
መምረጥ መቻል፣
 ጤናን የሚጠብቁ ልምዶችን ማዘውተር፣
 የእንቅስቃሴን እና የረፍትን አስፈላጊነት
መረዳት፣
 ሰላማዊ ባህርይን መረዳትና ተግባራዊ ማድረግ

የክፍለ ትምህርት ሶስት የማጠቃለያ ተግባራት


የሚከተሉትን ጥያቄዎች መልሱ
1. መዳበር ምንድነው?

ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል


xxxvi
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች

2. የቅድመ-መደበኛ መምህር የሚመዝናቸውን የመዳበር ደረጃዎች ምን ምን ናቸው?


3. የተለያዩ የመዳበር አይነቶች እንዴት ይመዘናሉ?
4. በአእምሮአዊና የቋንቋ መዳበር እንዴት ይዛመዳል?
5. የቋንቋ መዳበር እንዴት ይመዘናል?

ክፍለ ትምህርት አምስት


4. የጽሑፍ ፈተና አዘገጃጀት
የህጻናትን መማር ለመረዳት ወይም ህጻናትን ለመመደብ ከምንጠቀምባቸዉ የምዘና ስልቶች መካከል አንዱ የጽሁፍ
ፈተና ሊሆን ይችላል፡፡ የጽሑፍ ፈተና ምንም እንኳ አዕምሮታዊ የመማር ዘርፍን (Cognitive domain) ብቻ የሚለካ
ቢሆንም መምህራን የአዘገጃጀት ደረጃዎችንና መርሆዎቹን ጠብቀዉ በጥንቃቄ ማዘጋጀት ከቻሉ የህጻናትን መማር
በመለካት ረገድ የጎላ ድርሻ ይኖረዋል፡፡ ምንም እንኳ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤት የህጻናትን ውጤት ለመወሰን
የጽሁፍ ፈተና መስጠት የሚመከር ባይሆንም መምህራን የምዘና ስልቶችን አውቀው መገኘታቸው ስለምዘና ሙሉ
ያደርጋቸዋል፡፡ በመሆኑም በዚህ ክፍለ ትምህርት የጽሁፍ ፈተና ስናዘጋጅ ልንከተላቸዉ ስለሚገቡ ቅደም ተከተሎችና
በየደረጃዎቹ ስለምናከናዉናቸዉ ተግባራት ማብራሪያዎች ይሰጣሉ፡፡ በተጨማሪም የጥሩ የጽሑፍ ፈተና ተፈላጊ
ባህሪያት በወፍ በረር ይቃኛሉ፡፡

የክፍለ ትምህርቱ ዓላማዎች

የቅድመ መደበኛ እጩ መምህራን ይህንን ምዕራፍ ካጠናቀቁ በኋላ


 የጽሑፍ ፈተና አዘገጃጀት ሂደቶችን ይገነዘባሉ፣
 የጽሑፍ ፈተና አይነቶችን ያዉቃሉ፣
 የተለያዩ ፈተና አይነቶችን ድክመትና ጥንካሬ ይረዳሉ፣
 የመማር ማስተማር ባህሪያት ሊለኩባቸዉ ከሚችሉ የፈተና አይነቶች ጋር ያዛምዳሉ፣
 የጽሑፍ ፈተና ያዘጋጃሉ፣
 የሚያዘጋጃቸዉን የጽሑፍ ፈተናዎች የጥራት ደረጃ መፈተሻ ስልቶችን ያዉቃሉ፣
 የጽሑፍ ፈተና የተማሪዎችን መማር በመለካት ረገድ ያለዉን ፋይዳ ይገነዘባሉ፣
 የጽሐፍ ፈተና ልዩ ባህሪያትን ይገነዘባሉ፣
5.1 የጽሁፍ ፈተናን ማቀድ

የመወያያ ጥያቄዎች (በቡድን በመወያየት መልሦቻችሁን ለመምህራችሁ ተናገሩ)


1. ፈተናን ማቀድ ሲባል ምን ማለት ነዉ?
2. ፈተናን ማቀድ ለፈተና ጥያቄዎች ጥራት ያለዉ ፋይዳ ምንድን ነዉ?
3. እናንተ በኮሌጅ ቆይታችሁ በተፈተናችኋቸዉ የፈተና ጥያቄዎች ምንምን ስህተቶችን አስተዋላችሁ? እነዚህ

ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል


xxxvii
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች

ስህተቶች በምን ምክንያት የተፈጠሩ ይመስላችኋል?

በጽሑፍ ፈተና አዘገጃጀት ላይ ጥናት ያደረጉ ምሁራን እንደሚሉት ጥራት ያላቸዉ የፈተና ጥያቄዎች በዘፈቀደ የሚጻፉ
ሳይሆኑ ጥብቅ ህግጋትን በመከተል በጥንቃቄ የሚዘጋጁ ናቸዉ፡፡ በመሆኑም በፈተና አዘገጃጀት ሂደት የመጀመሪያዉ
ተግባር ማቀድ ነዉ፡፡ ፈተናን በማቀድ የጽሑፍ ፈተና አዘገጃጀት እርከን የሚከተሉት ንዑሳን ቅደም ተከተሎች
ይካተታሉ፡፡
1. የፈተናዉን አላማ መወሰን፣
2. ዝርዝር የመማር ማስተማር አላማዎችን መምረጥ፣
3. የጥያቄ ብዛት መወሰን፣
4. ዝርዝር ሠንጠረዥ ማዘጋጀትና፣
5. የፈተና ጥያቄ አይነቶችን መምረጥ፡፡

5.1.1 የፈተናዉን ዓላማ መወሰን


የጽሁፍ ፈተናን መምህራን ለተለያየ አላማ ሊያዘጋጁ ይችላሉ፡፡ለቦታ ምደባ፣ የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማሻሻል
የሚጠቅም መረጃ ለማግኘት፣ ከበድ ያሉ የመማር ችግሮችን ለመለየትና ለመፍታት እና የተለያዩ አስተዳደራዊ
ዉሳኔዎችን ለመወሰን ለምሳሌ ከክፍል ክፍል ዝዉዉር ለመስራት፣ የደረጃ ማጠናቀቂያ ሰርቲፊኬት ለመስጠት፣ የብቃት
ማረጋገጫ ለመስጠት…ወዘተ /እነዚህን የምዘና አይነቶች በበለጠ ለመረዳት በምዕራፍ አንድ ላይ የተማራችሁትን
ከልሱ/፡፡

መምህራን የሚያዘጋጁት የፈተና ጥያቄ ባህሪ ለምሳሌ ቅለትና ክብደት፣ የሚሸፍነዉ የይዘት ስፋት …ወዘተ ጥያቄዉ
የሚዘጋጅበትን አላማ መሰረት በማድረግ ይወሰናል፡፡ ለግንዛቤ እንዲረዳችሁ የሚከተለዉን ሠንጠረዥ ተመልከቱ፡፡

የፈተና ዓላማ የይዘት ስፋት የክብደት ደረጃ


የቦታ ምደባ ፈተና በርካታ ይዘቶችና ያካትታል፣ የሚለካዉ አጠቃላይ እዉቀትን
ሲያስፈልግም ከአንድ የክፍል ደረጃ በመሆኑ የክብደት ደረጃዉ እምብዛም
በላይ ይዘት ሊያካትት ይችላል፡፡ ለተፈታኞች አስቸጋሪ አይደለም፡፡
ይህ ግን ሁል ጊዜ ላይጠበቅ ይችላል፡፡
የሂደት ፍተሻ ፈተና የፈተና ጥያቄዎች የሚዘጋጁት የጥያቄዎቹ ክብደት ተመሳሳይና
በጣም ዉስን ከሆነ ይዘት ላይ ነዉ፡፡ አብዛናዉ ተማሪ ሊመልሳቸዉ
የሚችሉ ናቸዉ
የመማር ችግር መለያ ፈተና
የማጠቃለያ ፈተና

መምህራን ፈተና ለማዘጋጀት ሲነሱ ፈተናዉን ለምን አላማ እንደሚያዘጋጁት መረዳት ተቀዳሚ ተግባራቸዉ ነዉ፡፡
ምክንያቱም ከላይ ከቀረበዉ ሠንጠረዥ እንደምንረዳዉ የፈተናዉ ባህሪ የሚወሰነዉ ፈተናዉ ከሚዘጋጅበት አላማ
አንጻር በመሆኑ ነዉ፡፡

5.1.2 የመማር ማስተማር አላማዎችን መምረጥ

ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል


xxxviii
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች

ፈተና ሁሉንም አይነት የባህሪ ገጽታዎች አይለካም፡፡ ለምሳሌ ተማሪዎች በመማር ማስተማር ሂደት ያዳበሩትን ክህሎት
(Psychomotor domain) ወይም ያዳበሩትን ፍላጎት፣ የዝንባሌ፣ የአመለካከት (Affective domain) ለዉጥ በጽሑፍ
ፈተና ጥያቄዎች መለካት ያስቸግራል፡፡ የጽሑፍ ፈተና ሊለካ የሚችለዉ የተማሪዎችን የማስታወስ፣ የመገንዘብ፣
የመተግበር፣ የመተንተን፣ የማቀናበርና የመገምገም በአጠቃላይ አዕምሮአዊ (Cognitive domain) ችሎታን ነዉ፡፡
ስለሆነም በሴሚስተሩ ከተተኮረባቸው የመማር ማስተማር ዝርዝር አላማዎች ዉስጥ በፈተና ሊለኩ የሚችሉ
ባህሪያትን መለየት በሁለተኛነት የሚመጣ የፈተና ዕቅድ ክፍል ነዉ፡፡

የተግባር ስራ፡ይህንን ተግባር በይበልጥ ለመረዳት ኮርሱን ከሚያስተምራችሁ መምህር ጋር በመሆን


1. ሁኔታ፣ መስፈርትና ድርጊት ያካተቱ ዝርዝር የመማር ማስተማር ዓላማዎችን ጻፉ
2. ከእያንዳንዱ የመማር ማስተማር አላማ ሁኔታና ድርጊት ጋር ትስስር ያለዉ አንድ የፈተና ጥያቄ አዘጋጁ፡፡

5.1.3 ዝርዝር ሠንጠረዥ ማዘጋጀት

የፈተና ዝርዝር ሠንጠረዥ (Table of Test Specification or Test Blue Print) ዝርዝር የመማር ማስተማር
አላማዎችን በፈተናዉ ልናካትታቸዉ ካሰብናዉ ይዘቶች ጋር የምናዛምድበት ሠንጠረዥ ነዉ:: ብያኔዉን በይበልጥ
ለመረዳት የሚከተለዉን ምሳሌ ተመልከቱ፡፡

ዝርዝር የመማር ማስተማር አላማዎች ምድብ ጠቅላላ የጥያቄ


ይዘት የተመደበ ማስታወ መገንዘብ መተግበር መተንተን ማቀናበር መገምገም ብዛት
ክ/ጊዜ ስ
የምዘና 40 ×10
መሠረታዊ ጽንሠ 10 4 3 1 1 0 0
=9
45
ሃሳብ
የገሃዱ አለም 12 4 3 2 1 1 0 40 ×12
ምዘና
=11
45
የጽሑፍ ፈተና 16 6 4 2 0 1 1 40 ×16
አረገጃጀት
=14
45
የምዘና 7 3 2 1 0 0 0 40 ×7
ስነምግባር
=6
45
ጠቅላላ ድምር 45 17 12 6 2 2 1 40

የፈተና ዝርዝር ሠንጠረዥ ስናዘጋጅ የሚከተሉትን ቅ/ተከተሎች መከተል ያስፈልጋል፡፡


 በፈተናችን የሚካተቱ ዝርዝር የመማር ማስተማር ዓላማዎችን መምረጥ፣
 ፈተናችን የሚያተኩርባቸዉን ዋና ዋና ይዘቶች መለየት፣
 እያንዳንዱን ይዘት ለማስተማር የምንጠቀመዉን ክ/ጊዜ ማስላት፣
 የፈተና ጥያቄዎችን ብዛት መወሰን፣
 በፈተናችን የሚካተቱ ዝርዝር አላማዎች የሚለኩትን የማሰብ ደረጃ (ማስታወስ፣ መገንዘብ፣ መተግባር፣
መተንተን፣ ማቀናርና መገምገም) መለየት፣

ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል


xxxix
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች

 ዝርዝር ሠንጠረዥ ማዘጋጀት፣

ከእያንዳንዱ ይዘት ውስጥ በፈተናችን ልናካትተዉ የምንፈልገዉን የጥያቄ ብዛት የምንወስነዉ በዋናነት ይዘቱን
ለማስተማር የተጠቀምንበትን የክ/ጊዜ ብዛት መሠረት አድርገን በሚከተለዉ መንገድ በማስላት ነዉ፡፡

ቀx ወ ወ፡ እያንዳንዱን ይዘት ለማስተማር የተጠቀምነዉ ክ/ጊዜ ብዛት


ሸ ቀ፡ በፈተናችን የሚያካትተዉ አጠቃላይ የጥያቄ ብዛት
ሸ፡ በፈተናዉ የተካተቱ ሁሉንም ይዘቶች ለማስተማር የተጠቀምንበት የክ/ጊዜ መጠን

ነገር ግን ከሂሳባዊ ስሌቱ በተጨማሪ መምህራን አንደኛዉ ይዘት/ የመማር ማስተማር ዓላማ ከሌላኛዉ ይልቅ
ለተማሪዎች ቀጣይ ህይወት አስፈላጊ ነዉ ብለዉ ካሰቡ የራሳቸዉን ግምገማ በማካሄድ (Using Personal Judgement)
ከእያንዳንዱ ይዘት የሚያዘጋጁትን የጥያቄ ብዛት ማመጣጠን ይችላሉ፡፡

በእያንዳንዱ የማሰብ ደረጃ (Process objective) አንጻር የሚካተት የጥያቄ ብዛትን ደግሞ የመማር ማስተማር ዝርዝር
አላማ ባህሪን ግምት ዉስጥ በማስገባት የጥያቄዎችን ብዛት ማመጣጠን ይቻላል፡፡

የተግባር ስራ
ከዚህ በታች የሰፈሩት የመማር ማስተማር አላማዎች የተጻፉባቸዉን ድርጊት አመልካች ግሶች በመመልከት በየትኛዉ የማሰብ
ደረጃ ላይ ጥያቄዉ ሊካተት እንደሚችል ለክፍል ጓደኞቻችሁ ተናገሩ፡፡ የፈተና አረገጃጀት ደረጃዎችን ከተማሩ በኋላ
ሠልጣኞች፡
1. የጽሑፍ ፈተና አዘገጃጀት ደረጃዎችን በቅደም ተከተሎች ይዘረዝራሉ፣
2. በመጀመሪያ ደረጃ መምህራን የተዘጋጁ ጥያቄዎችን ጥንካሬና ድክመት ይገመግማሉ፣
3. ዝርዝር ሠንጠረዥ ማዘጋጀት ለፈተናችን ጥራት ያለዉን ፋይዳ ያብራራሉ
4. የጽሑፍ ፈተና አዘገጃጀት ህግጋትን ጠብቀዉ 2 የምርጫ ጥያቄዎችን ይጽፋሉ፣
5. የተለያዩ የፈተና ጥያቄ አይነቶችን ደካማና ጠንካራ ጎን ይተነትናሉ፣
6. በመረጡት አንድ የትምህርት አይነት ላይ ዝርዝር ሠንጠረዥ ያዘጋጃሉ፣
…. መምህር እባክዎ ሌሎችንም ምሳሌዎች በመጨመር ይህን ተግባር ያለማምዷቸዉ!

ተማሪዎች! ዝርዝር ሠንጠረዥ ማዘጋጀት ለምን ያስፈልጋል? የተለያዩ የመስኩ ምሁራን እንደገለጹት ዝርዝር
ሠንጠረዥ ማዘጋጀት የሚከተሉት ጠቀሜታዎች አሉት፡፡
 የይዘት ትክክለኛነትን (Content Validity) ለማረጋገጥ ይጠቅማል፣
 ተማሪዎች ለፈተና የሚዘጋጁበትን አግባብና አቅጣጫ ለመጠቆም ያግዛል፣
 መምህራን ፈተናቸዉን ሲያዘጋጁ እንደ ካርታ ሆኖ ያገለግላቸዋል፣
 የመማር ማስተማርን ተግባርን ከምዘና ተግባር ጋር ለማስተሳሰር ጉልህ አስተዋጾ አለዉ
ተማሪዎች! እያንዳንዱ ጠቀሜታ ምን ማለት እንደሆነ በቡድን በመወያየት ጽብረቃ አቅርቡ፡፡

5.1.4 የፈተና ጥያቄ አይነቶችን መምረጥ

ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል


xl
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች

ተማሪዎች! በኮሌጅ ቆይታችሁ ምን ምን አይነት የፈተና ጥያቄዎችን ተፈትናችሁ ታዉቃላችሁ? እዉነት/ሐሰት፣


ማዛመድ፣ አጭር መልስ ስጥ/ጭ ወይም ባዶ ቦታ መሙላት፣ የምርጫ ጥያቄ፣ የማብራራት ጥያቄዎች… !
መምህራሮቻችሁ ለምን እነዚህን ሁሉ አይነት ጥያቄዎች በፈተና እንደሚያካትቱስ ምክንያቱን ታዉቃላችሁ?
የፈተና ጥያቄ አይነቶችን በተለያዩ ምድቦች ከፋፍሎ ማየት ይቻላል፡፡ በእርግጥ ይህንን ምደባ ለመስራት የተለያዩ
መስፈርቶች ቢኖሩም ለዚህ ኮርስ ፍጆታ ግን ዉስን መልስ የሚሹ (Objective items) እና የማብራራት ጥያቄዎች
(Subjective items) ተብለዉ በሁለት ምድብ ተከፍለዋል፡፡ ዉስን ምላሽ የሚሹ ጥያቄዎችም አጭር መልስ የሚሹ
(Supply type items) እና አማራጭ ያላቸዉ ጥያቄዎች (Selection type items) ተብለዉ ይመደባሉ፡፡

ዉስን መልስ የሚሹ የማብራራት ጥያቄዎች


አጭር መልስ መስጠት የሚሹ Supply type አማራጭ ያላቸዉ  የተገደቡ የማብራራት
items Selection type items ጥያቄዎች
 ባዶ ቦታ መሙላት/Completion  እዉነት/ሐሰት  ያልተገደቡ የማብራራት
 አጭር መልስ መስጠት /Short  ማዛመድ ጥያቄዎች
answer/  ባለ ብዙ ምርጫ

በአንድ የጥያቄ አይነት ሁሉንም የመማር ባህሪያት መለካት ያስቸግራል፡፡ መምህራን የተለያዩ ጥያቄ አይነቶችን
በፈተናቸዉ የሚያካትቱት የተለያዩ የመማር ባህሪያትን ለመለካት ነዉ፡፡ ለግንዛቤ እንዲሆናችሁ የሚከተለዉን
ሠንጠረዥ ተመልከቱ፡፡

የጽሁፍ ፈተና ጥያቄ አይነቶችና የሚለኩት የመማር ባህሪ ትስስር

የጥያቄ አይነት ሊለካ የሚችለዉ የባህሪ


ገጽታ ደረጃ የሚለካዉ ዝርዝር የባህሪ ገጽታ
እዉነት/ሐሰት ማስታወስ ነባራዊ ሐቆችን፣ መርሆዎችን፣ በተማሪዎች ዘንድ የተዛቡ
ግንዛቤዎችን (Popular misconceptions) ማስታወስ፣
አጭር መልስ ወይም ማስታወስ ቀንን፣ ክስተትን፣ ብያኔን፣ ቀመርን፣ቃልን፣ ሐረግን ወይም
ባዶ ቦታ አጫጭር ዝርዝር ጉዳዮችን ማስታወስ፣
ማዛመድ ማስታወስ በሁለት ጉዳዮች መካከል ለምሳሌ ህጎችና አፍላቂዎቻቸዉ፣
በቃላትና ተመሳሳዮቻቸዉ… ወዘተ መካከል ያለዉን
ዝምድና ማስታወስ

ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል


xli
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች

ባለ ብዙ ምርጫ ማስታዎስን፣ ግንዛቤን እና የተማሪዎችን የማስታወስ፣ የመገንዘብ፣ የመተግባር፣ ችሎታ


ትግበራን
የማብራራት ጥያቄ መገንዘብ፣ መተግበር፣ ከፍተኛ የማሰብ ደረጃ የሚጠይቁ የመማር ማስተማር
መተንተን፣ ማቀናበር፣ ባህሪያትን ለምሳሌ የመተንተን፣ የማቀናበርና የመገምገም
መገምገም ችሎታን ይለካሉ

ቀጣዩ ተግባር የሚሆነዉ ከላይ የቀረቡትን የተለያዩ የፈተና ጥያቄ አይነቶች መሠረት በማድረግ የሚከተለዉን የፈተና
አይነት ዝርዝር ሠንጠረዥ ማዘጋጀት ነዉ፡፡

5.1.5 የፈተና ጥያቄዎችን ማዘጋጀት


የጽህፍ ፈተና ጥያቄዎችን ማዘጋጀት ሰፊ ጊዜ የሚፈልግና አስቸጋሪ ተግባር እንደሆነ የመስኩ ምሁራን ይናገራሉ፡፡
የፈተና ጥያቄዎችን ስናዘጋጅ በዋናነት የምንጠቀምባቸዉ የመማር ማስተማር ማቴሪያሎች፡ የፈተና ዝርዝር
ሠንጠረዥ፣ እለታዊና አመታዊ የመማር ማስተማር ዕቅዶች፣ የተማሪዉ መማሪያ መጽሐፍ ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

የተግባር ስራ፡- ቀጣዩን ክፍል ከማንበባችሁ በፊት ከክፍል ጓደኞቻችሁ ጋር በመወያየት ማብራሪያ ስጡ
1. መምህራን የፈተና ጥያቄዎችን ሲያዘጋጁ ሊከተሏቸዉ የሚገቡ አጠቃላይ እና ዝርዝርዝ መርሆዎች ምን ምን ናቸዉ?
2. እነዚህን አጠቃላይና ዝርዝር መርሆዎች በጽሁፍ ፈተና ዝግጅት ወቅት ተግባራዊ ማድረግ መምህራን ለሚያዘጋጁት
የፈተና ጥያቄ ጥራት ያለዉ ፋይዳ ምንድን ነዉ?
3. የእያንዳንዱ የጥያቄ አይነት ጠንካራና ደካማ ጎኖች ምን ምን ናቸዉ?
4. የተለያዩ የፈተና ጥያቄ አይነቶች የትኛዉን የመማር ባህሪ እንደሚለኩ ማብራሪያ ስጡ

አጠቃላይ መመሪያዎች /General Guidelines/


 የፈተና ትዕዛዞችን ግልጽና የማያሻሙ ማድረግ፣
 የቋንቋ አጠቃቀማችንን ቀላልና ግልጽ ማድረግ፣
 ሁሉንም የጥያቄ አይነቶች ማካተት፣
 ተጨማሪ መጠባበቂያ ጥያቄዎችን ማዘጋጀት፣
 የሁሉንም ተማሪዎች ችሎታ ያገናዘበ ጥያቄ ማዘጋጀት፣
 ጥያቄዎች ከቀላል ወደ ከባድ መደርደራቸዉን ማረጋገጥ፣
 አንድ ግልጽ የመማር ማስተማር አላማ መለካት መቻሉን ማረጋገጥ፣
 የትክክለኛ መልሶችን ምጥጥን መጠበቅና የመልሶችን አደራደር ማዘበራረቅ፣
 በመማር ማስተማር ሂደት የተተኮረባቸዉን ይዘቶች ፍታዊ በሆነ መንገድ ማካተት መቻሉን ማረጋገጥ፣
 ቋንቋን መሠረት ያደረገ ማሳሳቻን (trick) አለመጠቀም፣
 ለተማሪዎች መማር የማይጠቅሙ (trivial) የተለመዱ ወይም ያለ በቂ ዝግጅት ሊመለሱ የሚችሉ (Obvious
questions) ጥያቄዎችን አለማካተት፣
 እርስ በርስ ትስስር ያላቸዉን ጥያቄዎች (interrelated items) አለማካተት፣

ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል


xlii
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች

 ትክክለኛዉን መልስ ሊያመለክቱ የሚችሉ ፍንጮችን ማስወገድ፣


 ተራ ሽምደዳ (Simple recalling) የሚጠይቁ ጥያቄዎች ላይ በብዛት አለማተኮር፣
 ዉስን መልስ ለሚሹ ጥያቄዎች አንድ ትክክለኛ መልስ መኖር መቻሉን ማረጋገጥ፣
 ጥያቄዎችን ወይም ሙሉ አረፍተ ነገሩን ከመማሪያ መጽሐፍ ላይ እንዳለ አለመገልበጥ፤
ዝርዘር መመሪያዎች (Specific Guidelines)
ሀ. ባለሁለት አማራጭ ጥያቄዎች /Alternative Response Items/
ይህ የፈተና ጥያቄ አይነት ምንም እንኳ ብዙ ቅርጽ /Form/ ያለዉ ቢሆንም “እዉነት/ሐሰት” የሚለዉ በመምህራን ዘንድ
የተለመደ አጠያየቅ ነዉ፡፡ የእዉነት/ሐሰት ጥያቄ የማስታወስ ችሎታን፣ በተማሪዎች ዘንድ ይኖራል ተብሎ የሚገመት
የተሳሳተ ግንዛቤን እና ሁለት አማራጭ ብቻ ያላቸዉን ቀላል የመማር ባሪያት ለመለካት ምቹ ነዉ፡፡

የእዉነት/ሐሰት ጥያቄዎች ጠንካራና ደካማ ጎኖች

ጠንካራ ጎን ደካማ ጎን
 ለማረም ቀላል ነዉ  ለግምት የተጋለጠ ነዉ /50%/
 ለማዘጋጀት አይከብድም  የመለየት አቅሙ /discrimination power/ ደካማ ነዉ
 በርካታ ይዘቶችን ለመሸፈን ያስችላል  ከፍተኛ የማሰብ ደረጃን አይለካም
 ተማሪዎች በፍጥነት መመለስ ይችላሉ  አስተማማኝነቱ (Test reliability) ዝቅተኛ ነዉ

እዉነት/ሐሰት ጥያቄዎችን ስናዘጋጅ የምንከተላቸዉ ዝርዝር ህጎች


 ሁለት አሉታዊ ቃላትን በአንድ ዓ/ነገር አለመጠቀም፣
 የዓ/ነገሮችን ርዝመት ማመሳሰል እና መመጠን፣
 እንደ “ሁሉም፣ ብቻ፣ ምንም፣ በአብዛኛዉ፣ እንዳንድ ጊዜ፣ አልፎ አልፎ..ወዘተ” ያሉ ፍጹም ወይም ጥቅል ሃሳብ
/መልስ አመልካች/ ቃላትን አለመጠቀም፣
 በአንድ ጥያቄ አንድ ሐሳብ ብቻ መጠየቅ
 የጥያቄዉ መልስ በትክክል እዉነት ወይም ሐሰት መሆኑን ማረጋገጥ፣
 የምንጠይቀዉ የመማር ባህሪ በእዉነት/ሐሰት ሊለካ የሚችል መሆኑን ማረጋገጥ፣

ለ. የማዛመድ ጥያቄዎች

የማዛመድ ጥያቄዎች ተማሪዎች ተዛምዶ ያላቸዉን የትምህርት ይዘቶች ዝምድናቸዉን እንዲያስታዉሱ


የምንጠይቅበት የፈተና ጥያቄ አይነት ነዉ፡፡ለምሳሌ ቃላት ከትርጉሞቻቸዉ፣ መንስዔዎች ከዉጤቶቻቸዉ፣ ቀመሮች
ከመግለጫዎቻቸዉ፣ ቦታን ከክህስተት፣ የፈጠራ ዉጤቶችን ከፈጣሪዎቻቸዉ… ..ወዘተ ጋር ያላቸዉን ዝምድና
ልንጠይቅበት እንችላለን፡፡ የማዛመድ ጥያቄዎች የራሳቸዉ የሆነ ጠንካራና ደካማ ጎኖች አላቸዉ፡፡

የማዛመድ ጥያቄዎች ጠንካራና ደካማ ጎኖች

ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል


xliii
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች
ጠንካራ ጎን ደካማ ጎን
 ለማዘጋጀት አያስቸግርም፣  ተማሪዎች ምላሽ ሲሰጡ ጊዜ ሊወስድባቸዉ ይችላል፣
 በትቂት ቦታ ሰፊ ይዘት ለመሸፈን ያስችላል፣  ከማስታወስ በላይ ያሉ የመማር ባህሪትን ለመለካት ያስቸግራል፣
 ለማረም ቀላል ነዉ፣  ተመሳስሎ ያላቸዉን ርዕሰ ጉዳዮች ለማግኘት ያስቸግራል፣

የማዛመድ ጥያቄዎችን ስናዘጋጅ የምንከተላቸዉ ህጎች


 ሁሉንም ጥያቄዎች በአንድ ገጽ ላይ ማጠቃለል፣
 ተማሪዎች ምንን ከምን እንደሚያዛምዱ በትዕዛዙ ላይ በግልጽ ማስቀመጥ፣
 ተመሳስሎ ያላቸዉን ርዕሰ ጉዳዮች (homogenous material) ብቻ ማካተት፣
 ለአምስት የማዛመድ ጥያቄዎች ከ 2-3 የሚደርሱ አሳሳች ምላሾችን (Responses) መጠቀም፣
 በ “ለ” ክፍል የምናካትታቸዉን ምላሾች በቅ/ተከተል /በፊደል ተራ፣ በዓ.ም …/ መደርደር፣
 በ “ለ” አምድ ስር የምናካትታቸዉን ምላሾች በ “ሀ” አምድ ከምናካትታቸዉ አጫጭር ማድረግ፣

ሐ. የአጭር መልስ የሚሹ ጥያቄዎች


እነዚህ አይነት ጥያቄዎች ተማሪዎች ሃቆችን፣ ብያኔዎችን፣ ምልክቶችን፣ ቀመሮችን ቀናትን፣ ክህስተትን… ወዘተ
ማስታወስ መቻላቸዉን ለመፈተሸ የምንጠቀምባቸዉ ናቸዉ፡፡

አጭር መልስ የሚሹ ጥያቄዎች ጠንካራና ደካማ ጎኖች

ጠንካራ ጎን ደካማ ጎን
 ለማዘጋጀት በጣም ቀላል ነዉ  በብዛት ከተጠቀምንበት ተራ ሽምደዳን ያበረታታል
 መልሱን በግምት የማግኘት እድልን ይቀንሳል  ከሌሎች ዉስን መልስ ካላቸዉ ጥያቄዎች ለማረም አስቸጋ ነዉ
 ምን፣ማን፣የት፣መቼ አይነት ይዘቶችን ለመጠየቅ ምቹ  በጥንቃቄ ካልተዘጋጁ አንድ ዉስን መልስ ላይኖራቸዉ ይችላል
ነዉ
 የተማሪዎች የአጠናን ስልት እንዲሻሻል ያደርጋል፣

የአጭር መልስ የሚሹ ጥያቄዎችን ስናዘጋጅ የምንከተላቸዉ ህጎች


 ካልተሟሉ አ/ነገሮች ይልቅ ጥያቄያዊ አ/ነገሮችን መጠቀም፣
 ባዶ ቦታዎችን በጥያቄዉ መጨረሻ ማስቀመጥ፣
 ህጻናት ጠቃሚ ነጥቦችን ብቻ እንዲያስታዉሱ መጠየቅ፣
 በአንድ ጥያቄ ብዙ ባዶ ቦታዎችን እንዲሞሉ አለመጠየቅ፣
 ጥያቄዉን አንድ ትክክለኛ መልስ እንዲኖረዉ አድርጎ መጻፍ፣
 ተማሪዎች ዝርዝርና ረጃጅም ነገሮችን እንዲያስታዉሱ አለመጠየቅ፤ለምሳሌ የዝርዝር ሠንጠረዥን ትርጉም
እንዲያስታዉሱ ከመጠየቅ ይልቅ ትርጉሙን በመስቀመጥ ቃሉን/ዝርዝር ሠንጠረዥን/ እንዲያስታዉሱ
መጠየቅ፣

ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል


xliv
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች

 መለኪያዎች ለሚያስፈልጓቸዉ የመማር ማስተማር ዉጤቶች ለምሳሌ የራስ ዳሽን ተራራ ርዝመት መለኪያ
አሃዱን ጨምሮ መግለጽ፣

መ. የባለብዙ ምርጫ ጥያቄዎች


የባለ ብዙ ምርጫ ጥያቄዎች የማስታዎስን፣ የመገንዘብና የመተግበር ችሎታን ለመመዘን የሚችል በመሆኑ ሁለገብ
(Versatile) ሊባል ይችላል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ምንም እንኳ የራሳቸዉ የሆነ ደካማ ጎን ቢኖራቸዉም የባለ ብዙ
ምርጫ ጥያቄዎች የሌሎች ጥያቄ አይነቶችን ደካማ ጎኖች መሸፈን ይችላሉ፡፡

ባለብዙ ምርጫ ጥያቄዎች ጠንካራና ደካማ ጎኖች

ጠንካራ ጎን ደካማ ጎን
 የተለያዩ የመማር ዉጤቶችን ለመለካት ያስችል/Versatile/  ከሁሉም የጥያቄ አይነቶች ለማዘጋጀት ከባድ
 የተማሪዎችን መማር ለመለካት ዉጤታማ ነዉ/Effective/ ነዉ
 በርካታ ይዘቶችን ለመመዘን ያስችል  ተመሳሳይ አሳሳቾችን ለማግኘት ያስችግራል
 ለማረም ቀላል ነዉ

የባለብዙ ምርጫ ጥያቄዎችን ስናዘጋጅ የምንከተላቸዉ ህጎች

 የጥያቄዉ ግንድ አንድ ሐሳብ ብቻ የያዘ፣ የተሟላ፣ ግልጽና ትክክለኛዉን መልስ ከሚጠቁሙ አመልካቾች የጸዳ
መሆን አለበት፣
 ተማሪዎች በከፊል እዉቀት መልሱን ማግኘት እንዳይችሉ “ሁሉም መልስ ነዉ” የሚል አማራጭ አለመጠቀም፣
 “መልስ የለም” የሚለዉን አማራጭ ሲያስፈልግ ብቻና በጥንቃቄ መጠቀም፣
 አሳሳቾችን (Distractors) ከትክክለኛዉ መልስ ጋር የተቀራረቡ ማድረግ (Plausible)
 አማራጮችን እርስበርስ የሚጋጩ ወይም ተመሳሳይ ሃሳብ የሚያስተላልፉ አለማድረግ፣
 ሁለት አሉታዊ ቃላትን በአንድ ላይ አለመጠቀም፣ከተቻለ ጥያቄዉን አወንታዊ በሆነ መንገድ ብቻ መጻፍ፣የግድ
ካስፈለገ ደግሞ አሉታዊ ቃላትን/ሃረጋትን ማስመር፣ማድመቅ ወይም ሌላ የትኩረት መሳቢያ መንገድ መጠቀም፣
 አማራጮችን ስርዓት ባለዉ መንገድ መደርደር፤ለምሳሌ አማራጮቹ ዓ.ም ከሆኑ ከበፊቱ ወደአሁኑ ወይም
ከአሁኑ ወደቀደምቱ፣ ቁጥር ከሁኑ ከትንሹ ወደትልቁ ወይም ከትልቁ ወደ ትንሹ…ወዘተ መደርደር፣
 ትክክለኛ ምላሾችን በተመጣጠነ እና በተዘበራረቀ መንገድ መደርደር፣
 እያንዳንዱ ጥያቄ አንድ ዉስን የመማር ማስተማር ዓላማ እንዲለካ ማድረግ፣
 አማራጮችን በራሳቸዉ አዲስ መስመር ላይ መደርደር
 የአንድ ጥያቄ ግንድም ሆነ አማራጮች በአንድ ገጽ ላይ እንዲሰፍሩ ማድረግ፣
 ቢያንስ ሦስት ራሳቸዉን የቻሉ (independent) አማራጮችን መጠቀም፣አራት ቢሆኑ ይመረጣል

ሠ. የማብራራት/ Essay/ ሠርተህ/ሽ አሳይ /workout/ ጥያቄዎች

ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል


xlv
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች

እነዚህ አይነት ጥያቄዎች ከላይ ባየናቸዉ ዉስን መልስ ባላቸዉ (Objective items) ጥያቄዎች ለመለካት ያልቻልናቸዉን
የመማር ዉጤቶች ለመለካት ስንፈልግ የምንጠቀምባቸዉ ናቸዉ፡፡ ለምሳሌ ከፍተኛ የማሰብ ደረጃን የሚጠይቁ እንደ
መተግበር፣ መተንተን፤ ማቀናበር እና መገምገም ያሉ የመማር ዉጤቶችን በዚህ መንገድ መለካት እንችላልን፡፡ነገር ግን
ለማረም አመቺ ባለመሆናቸዉ የመጀመሪያ ደረጃ መምህራን ከላይ ያየናቸዉን የጥያቄ አይነቶች ያህል ሲጠቀሙባቸዉ
አይታዩም፡፡

የማብራራት/ሠርተህ አሳይ ጥያቄዎች ጠንካራና ደካማ ጎኖች

ጠንካራ ጎን ደካማ ጎን
 ለግምት የተጋለጠ አይደለም  ለማረም በጣም አስቸጋሪ ነዉ
 ለማዘጋጀት በጣም ቀላል ነዉ  ሠፊ ይዘት ለመሸፈን ያስቸግራል
 ተማሪዎች የተሻለ የአጠናን ስልት እንዲኖራቸዉ  በእርማት ወቅት ለተመሳሳይ ስራ የተለያየ ዉጤት
ያበረታታል ልንሰጥ እንችላለን
 ከፍተኛ የአዕምሮ ደረጃ የሚጠይቁ የመማር ዉጤቶችን  ለሁለት የሚታረም ከሆነም በአራሚዎች መካክል
ለመለካት ምቹ ነዉ መመሳሰል ላይኖር ይችላል
 ተማሪዎች ሐሳባቸዉን በነጻነት በጽሑፍ እንዲገልጹ
እድል ይሠጣል

የማብራራት/ሠርተህ አሳይ ጥያቄዎችን ስናዘጋጅ የምንከተላቸዉ ህጎች

 ለተማሪዎች በቂ ጊዜ መስጠት፣
 ተማሪዎች የተለያዩ ጥያቄዎችን እንዲሰሩ አለመፍቀድ፣
 የጥያቄዉ አቀራረብ ተማሪዎች ምን መስራት እንዳለባቸዉ በግልጽ የሚያመለከት መሆን ይኖርበታል/ማብራራት
ከሆነ እንዲያብራሩ፣ማወዳደር ከሆነም እንዲያወዳድሩ…./

5.2. ፈተናዉን መከለስ

የተለያዩ የመስኩ ምሁራን መምህራን ያዘጋጁትን የፈተና ጥያቄዎች ለተማሪዎቻቸዉ ከመፈተናቸዉ በፊት ራሳቸዉ
መፈተን አለባቸዉ ይላሉ፡፡ ለምን አንደዚህ እንደሚሉ ከጓደኞቻችሁ ጋር በመወያየት ምላሽ ስጡ፡፡

የፈተና ክለሳ ትኩረት የሚያደርገዉ በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ነዉ


 የፈተናዉ አጠቃላይ ትዕዛዝ/ዝርዝር ትዕዛዛት በትክክል ተጽፈዋል?
 የጥያቄ አይነቶችና ዝርዝር ጥያቄዎች ከቀላል ወደከባድ ተደርድረዋል?

ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል


xlvi
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች

 እያንዳንዱ ጥያቄ መጠየቅ የፈለግነዉን የመማር ማስተማር ዉጤት መጠይቅ ችሏል?


 ፊደላት፣ቃላትና ሃረጋት ያለስተት በትክክል ተጽፈዋል?
 እያንዳንዱ ጥያቄ ከቋንቋ ስህተቶች ነጻ ነዉ?
 ለፈተናዉ የሰጠነዉ ጊዜ ተመጣጣኝ ነዉ?
 የትክክለኛ መልሶች አደራደር ትክክል ነዉ?

የፈተና ጥያቄዎች አደራደር ከቀላል ወደ ከባድ በሆኑን ማረጋገጥ ሁለተኛዉ የክለሳ የትኩረት ነጥብ ነዉ፡፡ በዚህም
መሠረት የፈተና ጥያቄ አይነቶች በሚከተለዉ ቅ/ተከተል ቢቀመጡ ለተማሪዎች ምቹ እንደሚሆን በርካታ የመስኩ
ምሁራን ይስማሙበታል፡፡
 የእዉነት/ሐሰት ጥያቄዎች
 የማዛመድ ጥያቄዎች
 የአጭር መልስ መስጠት/ባዶ ቦታ መሙላት ጥያቄዎች
 የባለብዙ ምርጫ ጥያቄዎች
 የማብራራት/ሠርተህ/ሽ አሳይ ጥያቄዎች
በእያንዳንዱ የጥያቄ አይነት ስር ያሉ ዝርዘር ጥያቄዎችም ከቀላል ወደ ከባድ መደርደራቸዉን ማረጋገጥ በክለሳ ወቅት
የምናረጋግጠዉ ተግባር ነዉ፡፡

በአጠቃላይ መምህራን ምንም እንኳ የፈተና ጥያቄወቻቸዉን ከላይ የሰፈሩ የፈተና አዘገጃጀት ህግጋትን መሠረት
አድርገዉ ቢያዘገጇቸዉም ፈተናዉን ከመፈተናቸዉ በፊት ራሳቸዉ እንደተማሪዎች ሆነዉ መልሱን
ማዉጣት/መፈተናቸዉ በፈተና ጥያቄዎቻቸዉ ዉስጥ ጉልህ ስህተት እንዳይኖር ያደርጋል፡፡ ጥያቄዉ ይህን ደረጃ ካለፈ
በኋላ በፈተና ወቅት በየክፍሉ በመዘዋወር ማስተካከያ /Correction/ መስጠት የፈተና አዘገጃጀት ህግጋትን የሚቃረን
ተግባር ነዉ፡፡

5.3. ፈተና መፈተን ማረምና ዉጤቱን መመዝገብ


የጽሑፍ ፈተና አፈታተን
መምህራን የፈተና ጥያቄዎችን ሲያዘጋጁ የቱንም ያህል ጥንቃቄ አድርገዉ ቢያዘጋጁት በፈተና ወቅት የሚከሰቱ
ችግሮችን መቆጣጠር ካልቻሉ ፈተናዉ የተፈለገዉን የመማር ባህሪ መለካት አይችልም፡፡ ተማሪዎች! እናንተ ለፈተናዉ
በጣም ተዘጋጅታችሁ በአፈታተን ሂደት በተከሰተ ችግር ምክንያት ያሰባችሁትን ዉጤት ያላመጣችሁበት ጊዜ አለ?
ምንም ሳትዘጋጁ ቀርታችሁስ ያልጠበቃችሁትን ዉጤት ያመጣችሁበት ጊዜ አለ? በጉዳዩ ላይ በጥንድ በጥንድ ሆናችሁ
ተወያዩ፡፡

ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል


xlvii
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች

ስለዚህ መምህራን ፈተናዎችን በሚፈትኑበት ጊዜ አካባቢያዊ እና ስነልቦናዊ ተግዳሮቶችን መቆጣጠር አለባቸዉ፡፡


አካባቢያዊ ተግዳሮቶች ስነልቦናዊ ተግዳሮቶች
 የክፍሉ ሁኔታ ለምሳሌ የብርሃን ሁኔታ፣ጸጥታ፣  የተፈታኞች የተጋነነ የፈተና ፍርሃት
የሙቀት መጠን፣  የፈታኙ ባህሪ ለምሳሌ ቁጡነት፣ ነጭናጫነት፣ ግልፍተኝነት፣
 የመቀመጫ ወንበሮች፣ ማስደገፊያ ጠረጴዛዎች፣  በጊዜ እጥረት ምክንያት የሚከሰት መደናገጥ፣
ወዘተ ምቹነት፣  የተፈታኞች በፈተና ወቅት ሚያጋጥም ድብርትወይም
 የፈተና ጥያቄዎች ተነባቢነት..ወዘተ አለመነቃቃት

ከፈተናዉ በፊት ተፈታኞች ፈተናዉ ስለሚያካትተዉ የጥያቄ አይነት፣ ስለሚሸፍነዉ ይዘትና የትኩረት አካባቢ፣ በፈተና
ወቅት ስለሚያስፈልጉ ቁሳቁሶች፣ ስለፈተናዉ ቦታና ቀን መረጃ ሊኖሯቸዉ ይገባል፡፡

ፈተና ማረም
በዚህ ምዕራፍ ክፍል 3.1.2 እንደተመለከትነዉ የጽሑፍ ፈተና ጥያቄዎች ዉስን መልስ ያላቸዉና የማብራራት/ሠርቶ
የማሳየት ጥያቄዎች ተብለዉ ይከፈላሉ፡፡ በፈተና እርማት ሂደት ዉስን መልስ ያላቸዉ ለምሳሌ የእዉነት/ሐሰት፣
የማዛመድ፣ የአጭር መልስ መስጠት፣ የባለብዙ ምርጫ ጥያቄዎች ለማረም ብዙም የማያስቸግሩ ናቸዉ፡፡ ነገር ግን
የማብራራት ጥያቄዎች ተማሪዎች የፈለጉትን ሃሳብ እንዲጽፉ እድል ስለሚሰጡ እና እያንዳንዱ ተማሪ ጥያቄዉን
በተረዳበት አግባብ ዝርዝር ትንታኔ ስለሚሰጥ ለማረም በጣም አስቸጋሪ ናቸዉ፡፡

ዉስን መልስ የሚሹ ጥያቄዎችን ለማረም መምህራን መጀመሪያ የራሳቸዉን ትክክለኛ መልስ (Answer key) ማዘጋጀት
አለባቸዉ፡፡ ይህንን የመልስ ወረቀት መሠረት በማድረግም የተማሪዎቻቸዉን ስራ በፍጥነት ማረም ይችላሉ፡፡ አንዳንድ
ጊዜ የማረሚያ ስቴንስል (Scoring stencil) በመጠቀም የፈተና ወረቀቶች ይታረማሉ፡፡
የማብራራት/ሠርቶ የማሳየት ጥያቄዎችን ለማረም ግን ሁለት አይነት አስተራረሞችን ይጠቀማሉ፡፡
ሀ. አንጻራዊ መንገድ (Relative scoring)፡- የሁሉንም ተማሪዎች ምላሽ በማንበብ የስራዉን የጥራት ደረጃ መሠረት
አድርጎ በተለያዩ ምድቦች መመደብ፤ በዚህ ሂደት ተመሳሳይ መልሶች በአንድ ቡድን ዉስጥ ይመደባሉ፡፡ በመጨረሻም
የሌሎች ቡድኖችን ስራ ለማረም ጥያቄዉን የተሻለ የሞከሩትን ተማሪዎች (ምድብ አንድ) ስራ እንደ ትክክለኛ መልስ
በመቁጠር የሌሎች ምድቦች ስራ ይታረማል፡፡
ለ. ፍጹማዊ መንገድ (Absolute scoring) ፡ ይኸኛዉ የማረሚያ መንገድ ደግሞ የፈተና        ወረቀቶችን ከማንበባችን
በፊት ትክክለኛ መልሶችን እናዘጋጃለን፡፡ በመቀጠል        የእያንዳንዱን ተማሪ ስራ በቅድሚያ ከአዘጋጀነዉ መልስ ጋር
በማወዳደር ዉጤት        እንሰጣለን፡፡
ዉጤት መመዝገብ
ከእርማት ቀጥሎ የሚመጣዉ ተግባር ዉጤት መመዝገብ ይሆናል፡፡ ከጽሑፍ ፈተና የሚገኘዉ ዉጤት አብዛኛዉን ጊዜ
የአጠቃላይ ተከታታይ ምዘና ተግባር በመሆኑ የተለያዩ አስተዳደራዊ ዉሳኔዎችን ለምሳሌ ከክፍል ክፍል ዝዉዉርን
ለመስራት ስለሚያገለግል አመዘጋገቡም በዚሁ አግባብ ይሆናል፡፡ ተማሪዎች! እናንተ በአቅራቢያችሁ በሚገኙ ት/ቤቶች

ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል


xlviii
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች

በመሄድ መምህራን የጽሑፍ ፈተና ዉጤትን እንዴት እንደሚመዘግቡ መረጃ ይዛችሁ በመምጣት ለክፍል ጓደኞቻችሁ
አንጸባርቁ፡፡ ለበለጠ መረጃ መጽሐፍትን አንብቡ፡፡

የክፍለ ትምህርት አምስት ማጠቃለያ ጥያቄዎች

ትዕዛዝ 1. በ’ለ’ረድፍ ያሉትን የተለያዩ የጥያቄ አይነቶች ጠንካራና ደካማ ጎኖች፣ በ”ሀ” ስር ከተዘረዘሩ የጥያቄ አይነቶች
ጋር በማዛመድ፣ ተዛማጁን የያዘውን ፊደል ከአዛማጁ በግራ ባለው ክፍት ቦታ ላይ ጻፍ/ፊ፡፡ አንድ ተዛማጅ
ሁለት ጊዜ ሊመረጥ (መልስ ሆኖ ሊጻፍ) ይችላል፡፡
ረድፍ-ሀ ረድፍ-ለ
_____1. ጥያቄዎችን ለማዘጋጀት ተመሳሳይ ጉዳዮች ማግኘት የግድ ይላል፤ ሀ. ማዛመድ
_____2. ሰፊ ይዘትን የሚሸፍኑ በብዛት ጥያቄዎችን ለማካተት አያስችልም፤ ለ. ማብራራት
_____3. ለአንድ አይነት ምላሾች የተለያየ ውጤት እንድንሰጥ ያደርጋል፣ ሐ. እውነት ሀሰት
_____4. መልስ ለመስጠት ተማሪዎች የሚፈጅባቸውን ጊዜ ይቆጥባል፣ መ. ባለብዙ ምርጫ
_____5. በማደራጀት ተማሪዎች በነጻነት ሃሳብ እንዲሰጡ ያበረታታል፣ ሰ. አጭር መልስ መስጠት
_____6. አማራጮች ተመሳሳዮች ካልሆኑ ጥያቄው ቀላል ይሆናል፣
_____7. በብዛት ስንጠቀምበት ተራ ሽምደዳን ያበረታታል፣
_____8. ከሌሎች በተሻለ ከፍተኛ የማሰብ ደረጃን ይለካል፣
_____9. በትንሽ ቦታ ሰፊ ይዘትን ለመሸፈን ያስችላል፤
_____10. ለማዘጋጀት ረጂም ጊዜን ይጠይቃል፣
ትዕዛዝ 2. እያንዳንዱን ጥያቄ በሚገባ ካነበባችሁ በኋላ የተብራራ መልስ ስጡ!
ጥያቄ 11: የሚከተሉትን ተግባራት ከቀዳሚው ወደ መጨረሻው የፊደል ተራውን በቅደም ተከተል አስተካክላችሁ አስቀምጡ፡
ሀ. ፈተና ማረም ረ. የፈተናውን ጥያቄዎች ጥራት መፈተሽ
ለ. ፈተና መፈተን ሸ. የፈተና ጥያቄዎችን ማዘጋጀት
ሐ. የፈተና ጥያቄዎችን መከለስ ቀ. የፈተና አይነትና ጥያቄዎችን ከቀላል ወደ ከባድ ማደራጀት
መ. የፈተና እቅድ ሰንጠረዥ ማዘጋጀት በ. የትምህርቱን ዓላማና ይዘት በዝርዝር መለየት
ሠ. የጥያቄውን አይነት መምረጥ
ጥያቄ 12፡ የሂሳብ መምህር የሆነው አያሌው ለሚያስተምረው ትምህርት አምስት ዋና ዋና ርዕሶች እንዳሉት በማረጋገጥ
በየርዕሶች ስር ያሉትን የትምህርቱን ዓላማዎች ከመርሃ ስርዐተ ትምህርቱ በዝርዝር ከለዬ በኋላ ትምህርቱን
አስተምሮ ሲጨርስ 50 ጥያቄዎችን የያዘ ፈተና በማዘጋጀት የተማሪዎችን መማር ለመመዘን ወስኗል፡፡
ፈተናውን ለማዘጋጀት እንዲረዳው የትምህርቱን ዓላማዎች ማስታዎስን፣ ማገናዘብን፤ እና መተግበርን
የሚመለከቱ በማለት በሶስት መድቧቸዋል፡፡ በተጨማሪም አምስት ዋና ዋና የትምህርቱን ርዕሶች (ሙሉ
ቁጥሮች፣ ክፍልፋዮችና አስርዮሾች፣ ልኬቶች፤ የጠለል ምስሎች እና ጠጣር ምስሎችን) ለማስተማር በቅደም-
ተከተል 12፤ 20፣ 16፣ 10 እና 8 በድምሩ 66 ክፍለ ጊዜያት እንደተመደበላቸው መርሃ-ስርዐተ-ትምህርቱን

ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል


xlix
የትምህርት ምዘናና ግምገማ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች

በማየት አረጋግጧል፡፡ የተሰጠውን መረጃ መሰረት በማድረግ አያልው ሊያዘጋጀው የሚችለውን ዝርዝር
ሰንጠረዥ በሚከተለው ሰንጠረዥ ያሉትን ክፍት ቦታዎች በመሙላት አሳዩ
የአላማዎች አይነት/ፍረጃና ብዛት
ማስታዎስ ማገናዘብ ትግበራ
1 ሙሉ ቁጥሮች
2 ክፍልፋዮችና አስርዮሾች
3 ልኬቶች
4 የጠለል ምስሎች
5 ጠጣር ምስሎች
ድምር
ጥያቄ 13: የግለጹ ጥያቄዎች ከአማራጭ ሰጭ ጥያቄዎች በተሻለ ተመራጭ የሚሆኑት መቼ ነው?
ጥያቄ 14፡ የፈተና ጥያቄዎች ዝርዝር ሠንጠረዢን (Table of test specification) የማዘጋጀት ዋና ዋና ጠቀሜታዎች ምን ምን
ናቸው?

ደብረማርቆስ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ/ ስነ-ትምህርት ትምህርት ክፍል


l

You might also like