You are on page 1of 4

ቁጥር አጠ/ትም 1190/01/02

ቀን 23/01/2015

ለምስ/ጎጃም ዞን ትም/ት መምሪያ

የአጠ/ትም/ኢን/ክ/ግ/ቡድን፣

ደ/ማርቆስ፣

ጉዳዩ፡- የመስከረም ወር ሪፖርት ሰርቶ ስለመላክ፣

ከላይ በጉዳዩ ለመግለፅ እንደተሞከረው በአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን ክትትልና ግም ገማ ቡድን በመስከረም ወር
ውስጥ የተከናወኑ ተግባራትን በተላከልን የሪፖርት ቢጋር መሰረት በማዘጋጀት ከዚህ ሸኝ ድበዳቤ ጋር 3 ገጽ አባሪ
በማድረግ ሰርተን የላክን መሆኑን በአክብሮት እናሳውቃለን፡፡

“ከሠላምታ ጋር”

ግልባጭ//

 ለቢ/ወ/ትም/ፅ/ቤት ኃላፊ

ድጎጽዮን፣
1. ከዞን ትምህርት መምሪያ በተሰጠን እቅድ መሰረት ከጥቅምት ወር ጀምሮ እስከ ሰኔ 2015/ ዓ.ም ድረስ በየፕሮግራሙ
ኢንስፔክሽን የሚሰራላቸውን የት/ት ተቋማት በመለየት መረጃውን ለሚመለከተው አካል ማለትም፡- ለዞን
አጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን ቡድን በወቅቱ መላክ ተችሏል፡፡
2. በየደረጃው ለሚገኙ ምክር ቤቶች /ሁሉም ት/ቤቶች በኢንስፔክሽን ጊዜ የተሰጡ አስተያየቶችን ለቀበሌ ምክር ቤት
እንዲሁም በወረዳ ደረጃ የስራ ቡድኑ አጠቃላይ ወረዳው ውስጥ ያሉ የመጀመሪያና የ 2 ኛ ደረጃ ት/ቤቶችን
የተጠቃለለ የኢንስፔክሽን ግኝት ለወረዳ ምክር ቤቱ እና በፅ/ቤቱ ስር ላሉ ሁሉም የስራ ቡድኖች ሪፖርት በማቅረብ
በሚታዩ ችግሮች ላይ እንዲመከርባቸውና አቅጫጣ እንዲቀመጥባቸው የማድረግ ስራ ተሰርቷል፡፡
3. በ 2015 ዓ.ም በሁሉም ፕሮግራሞች የኢንስፔክሽን አገልግሎት የሚያገኙ የት/ት ተቋማትን ዞኑ በላከልን መነሻ እቅድ
መሰረት ከወረዳው ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማጣጣምና በማቀድ መረጃውን በዞን አጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን
የስራ ቡድን ሪፖርት ማድረግ ተችሏል፡፡
4. በሁሉም ፕሮግራሞች በ 2015 ዓ.ም የኢንስፔክሽን ሱፐርቪዥን አገልግሎት የሚሰራላቸውን የት/ት ተቋማት
በመለየት መረጃውንም በወቅቱ ለዞን መላክ ተችሏል፡፡
5. የትምህርት ተቋማት በ 2015 ዓ.ም ትምህርት ሲጀምሩ በተለይም ከግብዓት ማሟላት አንጻር በኢንስፔክሽን የተለዩ
ክፍተቶችን በመለየትና የእቅድ አካል በማድረግ ለመማር ማስተማሩ እንቅስቃሴ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር
እንዳለባቸው በቂ መግባባት በመያዝ በበርካታ ት/ቤቶች የተሰሩ ግብዓቶችን የመስክ ስምሪት በመያዝ የማረጋገጥ ስራ
ተሰርቷል፡፡ ከተሰሩ ስራዎችም ለአብነት፡-
 መሃል ሜዳ ት/ቤት፡-
 4 የመማሪያ ክፍሎችን ሙሉ በሙሉ የግርፍና የሊሾ ስራ መስራት ተችሏል፡፡
 የት/ቤት አጥር የመጠገን ስራ ተሰርቷል፡፡
 በርካታ ችግኞችን በአይነት የመትከል ስራ ተሰርቷል፡፡
 አየር ት/ቤት፡-
 4 የመማሪያ ክፍሎች ሙሉ በሙሉ የምርግና የልስን ስራ ተሰርቷል፡፡
 ከ 10,000 በ ላይ የባህርዛፍ ችግኝ የመትከል ስራ ተሰርቷል፡፡
 የወንበር፣ የአጥርና ብላክ ቦርድ ጥገና ስራ ተሰርቷል፡፡
 ኩችት ት/ቤት፡-
 4 መማሪያ ክፍሎችን የውሃ ልክ ስራ ተሰርቷል፡፡
 4 መማሪያ ክፍሎችን በውስጥና በውጭ የምርግ ስራ ተሰርቷል፡፡
 ከበሴ ት/ቤት፡-
 4 የመማሪያ ክፍል የልስን ስራ ተሰርቷል፡፡
 100 ሜትር በአዲስ የአጥር ስራ ተሰርቷል፡፡
 ገነቱ ት/ቤት፡-
 የ 11 መ/ራን የመጠለያ ግንባታ ስራ ለመስራት ከ 500 በላይ የግምስ ዝግጅት ስራ ተጠናቋል፡፡
 ብርሃነ ጊዮርጊስ ት/ቤት፡-
 2 ክፍል የመምህራን መጠለያ ግንባታ ስራ ተሰርቷል፡፡
 ገነተ ማሪያም ት/ቤት፡-
 4 የመማሪያ ክፍል በውስጥና በውጭ የምርግ ስራ ተሰርቷል፡፡
 ደብረ ሲና ማሪያም ት/ቤት፡-
 4 የመማሪያ ክፍሎችን የውሃ ልክ ስራ ተሰርቷል፡፡
 አዲስ አምባ ት/ቤት፡-
 14 መማሪያ ክፍሎች
 በሬቤት ት/ቤት፡-
 2 መማሪያ ክፍሎችን በውስጥና በውጭ የምርግ ስራ ተሰርቷል፡፡
 እድገት ት/ቤት፡-
 2 መማሪያ ክፍል በአዲስ ስራ ተሰርቷል፡፡
 125 ሜትር የአጥር ጥገና ስራ ተሰርቷል፡፡
 4 መማሪያ ክፍል በር ጥገና ስራ ተሰርቷል፡፡
 6 መማሪያ ክፍል ጥገና ስራ ተሰርቷል፡፡
6. በ 2015 ዓ.ም በአዲስ የሚከፈቱና ደረጃቸውን የሚያሳድጉ ተቋማትን በተመለከተ እስካሁን ድረስ እንደ ወረዳችን፡-
- በአዲስ ይከፈትልን የቀረበ ጥያቄ - የለም፡፡
- ደረጃ ይደግልን የቀረበ ጥያቄ - የለም፡፡
7. በስራ ቡድናችን የስራ እንቅስቃሴያችንም ሆነ የአግልግሎት አሰጣጥ ሂደቱ በምን ልክ እንደሆነ ለመረዳት በየሩብ
ዓመቱ የዳሰሳ ጥናት ማድረግ እንዳለብን በእቅዱ በማካተት ወደ ስራ ተገብቷል፡፡ ከዚህም ተግባር አኳያ
የመጀመሪያውን ሩብ ዓመት በቡድኑ የአገልግሎት አሰጣጥ ርካታ የሚያሳይ የዳሰሳ ጥናት መስራት ተችሏል፡፡
8. ለ 2015 ዓ.ም ከዞን በወረደው መነሻ እቅድ መሰረት እንደ ወረዳው ተጨባጭ ሁኔታ በመቃኘት የስራ ቡድኑን
አመታዊ እቅድ አሳታፊ በሆነ መንገድ በማቀድ ለዞን አጠቃላይ ትም/ት ኢንስፔክሽን ቡድ ማሳወቅ ተችሏል፡፡
9. ስልጠና ያልወሰዱን በአዲስ ወደ ቡድኑ የተቀላቀለ ባለሙያ - የለም፡፡ ከዚህ ቀደም በተሠጡ የአቅም ማጎልበቻ
ስልጠናዎች ላይ ሁሉም የቡድኑ ባለሙያዎች መሳተፍ በመቻላቸው በአገኘነው ስልጠና መሰረት ተጨማሪ የዕርስ
በዕርስ መማማር ዕቅድ በማቀድ በተለያ ርዕሠ ጉዳዮች ላይ በመመማር እየተበቃቃን ያለንበት ሂደት ተፈጥሯል፡፡
10. የይዞታ ማረጋገጫ ድብተር የሌላቸው ት/ቤቶች እንደ ወረዳችን ካሉት 45 የመጀመሪያና 2 ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ውስጥ
2 ቶች የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤቶች /ድጎ-ፅዮንና ነጭ ሳር/ የላቸውም፡፡ በቀጣይም ደብተር እንዲኖራቸው ለማድረግ
እየተሰራ ያለ ስራ በትምህርት ንቅናቄ መድረኩ ላይ ከመሪ መዘጋጃ ፅ/ቤቱ ጋር በመሆን ስራ በመስራት የይዞታ
ማረጋገጫ ደብተር እንዲኖራቸው መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡
11. የአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን አገልግሎት ያገኙ ተቋማት በየፕሮግራሙ በመለየት ከ 2006 ዓ.ም ጀምሮ
ያላቸውን ደረጃና ውጤት በግልጽ በንፅፅር በሚያሳይ አግባብ በሃርድ ኮፒና በሶችት ኮፒ በማደራጀት ለተለያዩ
ባለድርሻ አካላት የማሳወቅ ስራዎችን መስራት ተችሏል፡፡ በቡድን ደረጃም መረጃውን በአግባቡ መያዝ ተችሏል፡፡
ከዚህ ተግባር አኳያም፡-
 ተቋማት በምን አይነት ደረጃ ላይ እንደሚገኙ እና ደረጃቸው ወደ ኋላ የተመለሱ የት/ት ተቋማትን በ 2014 ዓ.ም
የትምህርት ስራ የእቅድ አፈጻፀም ግምገማና የ 2015 ዓ.ም የእቅድ ትውውቅ ላይ ሪፖርት በማቅረብ ውይይት
የተደረገበት አግባብ መኖሩና በቀጣም የት/ቤቶችን ደረጃ ማሻሻል ላይ በልዩ ትኩረት መስራት እንደሚገባ
ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡
12. ከሌሎች ተግባራት አኳያ ፡-
 በጽ/ቤቱ በኩል የሚሰጡ ተልዕኮዎችን ሙሉ በሙሉ በመያዝ ለትምህርት ተቋማት የድጋፍና ክትትል ስራዎችን
መስራት ተችሏል፡፡
 ተቋማት በክረምት ወራት የተከሉትን የአረንጓዴ ልማት ተግባር እንክብካቤ /ኩትኳቶ፣ አረም/ እንዲያደርጉ ሰፊ
የሆነ የክትትል ስራዎችን መስራት ተችሏል፡፡

You might also like