You are on page 1of 12

ቀን፡- 05/02/2015 ዓ.

በ 2015 ዓ.ም በመስከረም ወር በአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን ቡድን በወረዳ ደረጃ እንዲከናወኑ
በቼክሊስት ከወረዱትና ከተከናወኑት ተግባራት አኳያ የተዘጋጀ ግብረ መልስ

ግብረ መልስ ቁጥር 3

1. ከዞን ትምህርት መምሪያ በተሰጠው እቅድ መሰረት ከጥቅምት ወር ጀምሮ እስከ ሰኔ ወር/2015 ዓ.ም

ድረስ በየፕሮግራሙ ኢንስፔክሽን የሚሠራላቸውን ተቋማት ብዛት በዝርዝር በመለየት ለዞን

ትምህርት መምሪያ ከማሳወቅ አኳያ፣

በጥንካሬ

 የኢንስፔክሽን ዕቅዱ በየፕሮግራሙ እና በሚከናወኑበት ጊዜ በሠንጠረዥ በሚገባ ተዘጋጅቶ

በሪፖርቱ ላይ የተገለፀ መሆኑ፣ እነብሴ፣ እነማይ፣ ጎዛምን፣ ሞጣ፣ ደባይ

 የኢንስፔክሽን ዕቅዱ የጊዜ ሠሌዳ ራሱን በቻለ ደብዳቤ በየፕሮግራሙና በሚከናወኑበት ጊዜ

ለዞን የተላከ መሆኑ በሪፖርቱ መገለፁ፣ ሰዴ፣ ባሶሊበን፣ ሁለት እጁ፣ አዋበል፣ ደ/ኤልያስ፣

ቢቡኝ፣ እናርጅ፣ ሸበል፣ አነደድ፣ ማቻክል፣

በዕጥረት

 የኢንስፔክሽን ፕሮግራሙ ኢንስፔክት የሚደረጉ ተቋማትን ዕቅድ ከማሳወቅ ባሻገር

የኢንስፔክሽን ስራው የሚካሔድበት የጊዜ ሠሌዳ በመስከረም ወር ሪፖርቱ ላይ አለመካተቱ

ወይም ራሱን ችሎ ስለመላኩ አለመገለፁ፣ ደጀን፣ ጎንቻ

2. በየደረጃው ለሚገኙ ምክር ቤቶች /ትምህርት ቤቶች ለቀበሌ ምክር ቤት ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት

/የስራ ቡድኑ/ ደግሞ ለወረዳ ምክር ቤቶች የተጠቃለለ ሪፖርት ከማቅረብና በሚታዩ ችግሮች ላይ

እንዲመከርባቸውና አቅጣጫ እንዲቀመጥባቸው የማድረግ ስራ ከመስራት አኳያ፣

በጥንካሬ
 በየጉድኝቱ የሚገኙ ሁሉም ት/ቤቶች በቀበሌ ደረጃ ችግሮቻቸውን ለም/ቤቶች በማቅረብ

እየፈቱ መሆኑ፣ ደጀን

 በሁሉም ቀበሌዎች አጠቃላይ ከትምህርት አጀማመርና ከግብዓት ማሟላት ጋር በተያያዘና

በ 2015 ዓ.ም ትምህርት ጥራትን ማስጠበቅ እንዴት እንደሚቻል በም/ቤቶች ውይይት

እንዲደረግ አቅጣጫ በማውረድ የተሰራ ሲሆን በወረዳ ደረጃም መስከረም 12/2015 ዓ.ም

በተደረገ የ 1 ኛው ሩብ ዓመት ጉባዔ የስራ ቡድኑን ሪፖርት ማቅረብ የተቻለ ሲሆን

በመጨረሻም ለስራ ቡድኑ የ 2015 ዓ.ም ስራ ማስኬጃ በጀት በም/ቤቱ ማስፀደቅ መቻሉ፣

ጎንቻ

 አዲስ ስራ በሚጀምረው ግራራም 2 ኛ ደረጃና በጎዛምን 2 ኛ ደረጃ ት/ቤቶች አስፈላጊ

ጉዳዮችን በማንሳት ከም/ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ ጋር መወያየት መቻሉ፣ ጎዛምን

 የኢንስፔክሽን ግኝቶችን ለቀበሌ ም/ቤቶች ሪፖርት ያቀረቡ ት/ቤቶች በቁጥር የተገለፁ

መሆኑ፣ እነብሴ (78 ት/ቤት)፣ እነማይ (18 ት/ቤቶች)፣

 በወረዳ ኢንስፔክሽን ቡድን ለወረዳ ም/ቤቶች ሪፖርት የቀረበ መሆኑና የተካተቱ ዋና ዋና

ነጥቦችም መካተታቸው፣ እነብሴ፣ እነማይ፣ ማቻክል

 በወረዳ ም/ቤት የሚፈቱ ችግሮችን በመለየት የ 37 ት/ቤቶችን ሪፖርት ማቅረብ መቻላቸው፣

ሸበል

 ለወረዳና ለቀበሌ ም/ቤት ሪፖርት የቀረበ መሆኑ መገለፁ፣ ሰዴ፣ ሁለት እጁ፣ ቢቡኝ፣ እናርጅ

 የ 2 ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የግብዓት ችግሮች ተለይተው ለወረዳ አፈ ጉባዔ እና ለሌሎችም ወሳኝ

ባለድርሻ አካላት የተላከ መሆኑ መገለፁ፣ አዋበል

 የ 5 ት/ቤቶች ኢንስፔክሽን ግኝት ለትኩረት ሲባል ለወረዳ ም/ቤት በፅሑፍ ሪፖርት የደረሰ

መሆኑና በዚህም ተጨባጭ ለውጦች እየታዩ መሆኑ መገለፁ፣ሞጣ

 የወረዳውን የኢንስፔክሽን ግኝት ለወረዳ ም/ቤት ለማቅረብ በደብዳቤ አሳውቀው ም/ቤቱን

መሠብሠብ በመጠባበቅ ላይ የሚገኙ መሆናቸው፣ ደ/ኤልያስ


በዕጥረት

 በኢንስፔክሽን የተገኙ ግኝቶችን ት/ቤቶች ለቀበሌው ም/ቤት እንዲያቀርቡ አቅጣጫ ወርዶ

ት/ቤቶች ግኝቶችን ለም/ቤቶች ለማቅረብ ጥረት ቢያደርጉም ከተወሰኑ ቀበሌዎች በስተቀር

ም/ቤቱ መሠብሠብ ባለመቻሉ የቀረበ አለመሆኑ፣ ደ/ኤልያስ

 በወረዳም ሆነ በቀበሌ ም/ቤቶች ምን ያህል ተቋማት ሪፖርት እንደቀረበ በቁጥር የተገለፀ ነገር

አለመኖሩ፣ ሰዴ፣ ሁለት እጁ

 ለቀበሌ ም/ቤት ሪፖርት መቅረቡ ከመገለፁ ውጭ ምን ያህል ት/ቤቶች ሪፖርት እንዳቀረቡ

በሪፖርቱ ላይ የተገለፀ አለመሆኑ፣ ደጀን

 ከዚህ በፊት ኢንስፔክሽን ሪፖርቶች በወቅቱ በየደረጃው ለሚገኙ ም/ቤቶች ሲቀርቡ የነበረ

መሆኑን በመጥቅስ አሁን ላይ ግን ቀጣይ ኢንስፔክሽን ሲጀመር የሚቀርብ እንጅ በዚህ ሠዓት

የቀረበ ሪፖርት አለመኖሩ መገለፁ፣ ደባይ

 በ 2 2 ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ዙሪያ ከቋሚ ኮሚቴ ጋር ከመነጋገር ባሻገር በም/ቤ ደረጃ የቀረበ ነገር

ስለመኖሩ አለመገለፁ፣ ጎዛምን

 በወረዳ ም/ቤት ደረጃ ሪፖርት ስለመቅረብ አለመቅረቡ ምንም የተገለፀ ነገር አለመኖሩ፣ ደጀን

 በኢንስፔክሽን የተለዩ ችግሮችን ር/መምህራንና ሱፐርቫይዘሮች ለቀበሌ ም/ቤት

እንዲያቀርቡ በደብዳቤ ቢያሳውቁም እስካሁን ስለመቅረቡ ሪፖርት ያደረገ ት/ቤት አለመኖሩ፣

ሸበል

 በየደረጃው ለሚገኙ ም/ቤቶች ሪፖርት ያልቀረበ መሆኑ መገለፁ፣ ባሶሊበን፣ አነደድ

 በየደረጃው ለሚገኙ ም/ቤቶች የ 2 ኛ ደረጃ ት/ቤቶችን የግብዓት ችግር በደብዳቤ ከመግለፅ

ውጭ በአካል ሪፖርት ስለመቅረቡ የተገለፀ አለመሆኑ፣ አዋበል

3. በ 2015 ዓ.ም ከዞን የስራ ቡድኑ በወረደው መነሻ እቅድ መሰረት በሁሉም ፕሮግራሞች የኢንስፔክሽን

አገልግሎት የሚያገኙ ተቋማትን ከወረዳው ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማጣጣም ከማቀድና ለዞን

የአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን ቡድን ሪፖርት ከማድረግ አኳያ፣


በጥንካሬ

 ኢንስፔክት የሚደረጉ ተቋማት ዕቅድ በቁጥር የተገለፀ መሆኑ፣ ደጀን፣ ጎንቻ፣ እነብሴ፣

እነማይ፣ ሰዴ፣ ባሶሊበን፣ ሁለት እጁ፣ አዋበል፣ ደ/ኤልያስ፣ እናርጅ፣ ጎዛምን፣ ሸበል፣ ሞጣ፣

ደባይ፣ አነደድ፣ ማቻክል

በዕጥረት

 ኢንስፔክት የሚደረጉ ተቋማት ዕቅድ በዞኑ መነሻ ዕቅድ መሠረት ታቅዶ የተላከ መሆኑ

ቢገለፅም ቁጥሩ በሪፖርቱ ላይ አለመገለፁ፣ ቢቡኝ

 ኢንስፔክት የሚደረጉ ተቋማት በጥቅል የተቀመጠ መሆኑና በየፕሮግራሙ አለመለየቱ፣ ደጀን

4. በሁሉም ፕሮግራሞች የኢንስፔክሽን ሱፐርቪዥን አገልግሎት የሚሰራላቸውን ተቋማት ከወረዳው

ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማገናዘብ ከፕሮግራም አንጻር እቅድ ከማቀድና ለዞን አጠቃላይ ትምህርት

ኢንስፔክሽን ቡድን ሪፖርት ከማድረግ አኳያ፣

በጥንካሬ

 የኢንስፔክሽን ሱፐርቪዥን የሚሠራላቸውን ተቋማት ዕቅድ በቁጥር ማስቀመጥ መቻሉ፣

ደጀን፣ ጎንቻ፣ እነብሴ፣ አነማይ (በስም ዝርዝር ጭምር)፣ ሰዴ፣ ባሶሊበን፣ ሁለት እጁ፣ አዋበል፣

ደ/ኤልያስ፣ እናርጅ፣ ጎዛምን፣ ሸበል፣ ሞጣ (በስም ዝርዝር)፣ ደባይ፣ አነደድ፣ ማቻክል

በዕጥረት

 የኢንስፔክሽን ሱፐርቪዥን የሚሠራላቸው ተቋማት የተላከ መሆኑ ከመጠቀሱ ውጭ ዕቅዱ

በዚህ ሪፖርት አለመካተቱ፣ ቢቡኝ

5. የትምህርት ተቋማት በአዲስ ዓመት ትምህርት ሲጀምሩ በተለይ ከግብዓት አንጻር በኢንስፔክሽን

የተለዩ ክፍተቶች ማሟላታቸውንና ለመማር ማስተማር ምቹ መሆናቸውን ፍተሻ ከማድረግ አኳያ፣


በጥንካሬ

 ለተቋማት ግብዓት ለማሟላት ጥረት ሲደረግ መቆየቱና በዚህም በርካታ ስራዎች የተሠሩ

መሆኑና ማሳያዎችም መገለፃቸው፣ ደጀን፣ ጎንቻ፣ እነብሴ፣ እነማይ፣ ሰዴ፣ ባሶሊበን፣ ሁለት

እጁ፣ አዋበል፣ ደ/ኤልያስ፣ ቢቡኝ፣ እናርጅ፣ጎዛምን፣ ሸበል፣ ሞጣ፣ ደባይ፣ ማቻክል

 በወረዳው የሚገኙ 3 የግል አፀደ ህጻናትን የቡድኑ ባለሙያዎች በጋራ ሆነው ምልከታ

በማካሔድ ያልተሟሉ ግብዓቶችንና የአሠራር ክፍተቶችን በመለየት ግብረ መልስና የከፋ

ችግር ያለባቸውን ደግሞ ጠንከር ያለ ማስጠንቀቂያ መስጠት መቻላቸው፣ ጎንቻ

በዕጥረት

 ከግብዓት ማሟላት አኳያ በሪፖርቱ ላይ በግልፅ የተቀመጠ አለመሆኑ፣ አነደድ

6. በ 2015 ዓ.ም በአዲስ የሚከፈቱና ደረጃቸውን የሚያሳድጉ የመጀመሪያና 2 ኛ ደረጃ ትምህርት

ቤቶችን መረጃ ከመሰብሰብና ለመምሪያው በፍጥነት ማስተላለፍ አኳያ፣

በጥንካሬ

 በአዲስ የተከፈተ 2 ኛ ደረጃ ት/ቤት መኖሩ መገለፁ፣ ጎንቻ (ባርጃኖ 2 ኛ ደረጃ ት/ቤት)፣

ጎዛምን (ግራራም 2 ኛ ደረጃ ት/ቤት)

 በአዲስ የተከፈተ 1 ኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት መኖሩ፣ ሞጣ (1)፣ አነደድ (1)

 ባለፈው ዓመት ስራ እንዲጀምር ከተፈቀደለት በኋላ በግብዓት ችግር ምክንያት ስራ

ሳይጀምር ከርሞ በዚህ ዓመት በአዲስ ስራ የጀመረ ተቋም መኖሩ፣ አዋበል (ፅድ ማርያም 2 ኛ

ደረጃ ት/ቤት)

 በዚህ ዓመት በአዲስ የተከፈተ ተቋም አለመኖሩ መገለፁ፣ ሰዴ፣ ሁለት እጁ፣ ደ/ኤልያስ፣

ቢቡኝ፣ እናርጅ፣ ሸበል፣ ደባይ


 በአዲስ የተከፈተ አፀደ ህጻናት መኖሩ፣ እነብሴ (1)፣ እነማይ (2)፣ ሞጣ (1)

 ከ 1-6 ነበረ ት/ቤት ወደ ከ 1-8 እንዲያድግ የተደረገ መሆኑ፣ ደጀን(1)፣ ባሶሊበን (1)፣ አነደድ
(1)
 በወረዳው ደረጃ ያሳደገ ተቋም አለመኖሩ መገለፁ፣ ጎንቻ፣ ሰዴ፣ ሁለት እጁ፣ አዋበል፣

ደ/ኤልያስ፣ ቢቡኝ፣ እናርጅ፣ ጎዛምን፣ ሸበል፣ ደባይ

 የክፍል ማስፋፋት ያደረጉ ት/ቤቶች መኖራቸው መገለጹ፣ እነማይ (የቀበሃና 2 ኛ ደረጃ ት/ቤት

ከ 9-10 የነበረው 11 ኛ ክፍል ማስጀመሩ፣ ደ/ኤልያስ (ጎፍጭማ 2 ኛ ደረጃ ት/ቤት ከ 9-10

የነበረው 11 ኛ ክፍል ማስጀመሩ)፣ ጎዛምን (ገጠር ፋና 2 ኛ ደረጃ ት/ቤት ከ 9-10 የነበረው

11 ኛ ክፍል ማስጀመሩ)

በዕጥረት

 ከ 1-4 የነበሩ ተቋማት ወደ ከ 1-6 ከፍ ሲሉ እንደ ደረጃ ማሳደግ የመቁጠር ሁኔታ መስተዋሉ፣

በተወሰኑ ወረዳዎች

 በአዲስ ስለተከፈቱም ሆነ ደረጃ ስላሳደጉ ተቋማት በሪፖርቱ ላይ በግልፅ የተቀመጠ ነገር

አለመኖሩ፣ ማቻክል

7. በስራ ቡድኑ የስራ እንቅስቃሴውን አስመልክቶ የደንበኞችን ርካታ ለመለካትና ማሻሻያ ለማድረግ

የዳሰሳ ጥናት ከማድረግ አኳያ፣

በጥንካሬ

 የዳሰሳ ጥናት የተደረገ መሆኑና የተሠራው የዳሠሳ ጥናት ኮፒ ለዞን መላኩ፣ እነብሴ (1)፣

ሁለት እጁ (1)፣ ሞጣ (1)

 በስራ ቡድኑ የዳሰሳ ጥናት የተካሔደ መሆኑ መገለፁ፣ ጎንቻ (1)፣ እነማይ (1)፣ ቢቡኝ (1)፣

ጎዛምን (1)
 በስራ ቡድኑ ያለውን የአገልግሎት አሠጣጥ እና የኢንስፔክሽን አሠራር ሒደትን በተመለከተ

የዳሠሳ ጥናት በማካሔድ የርካታ ደረጃቸው 87.87% መሆኑን ማረጋገጥ መቻላቸው፣

ደ/ኤልያስ

 የዳሠሳ ጥናት ለማካሔድ መጠይቅ በማዘጋጀት ሒደት ላይ መሆናቸው፣ ደጀን፣ ሰዴ፣ እናርጅ

በዕጥረት

 የተደረገው የዳሰሳ ጥናት ኮፒ ለዞን አለመላኩ፣ ጎንቻ፣ ቢቡኝ፣ እነማይ፣ ጎዛምን

 የዳሰሳ ጥናት ያልተደረገ መሆኑ መገለፁ፣ ባሶሊበን፣ ሸበል፣ ደባይ

 ስለ ዳሰሳ ጥናት በሪፖርቱ ላይ የተባለ ነገር አለመኖሩ፣ አዋበል፣ ማቻክል

 ዳሰሳ ጥናት ለማድረግ ስለተመረጠው ርዕስ ከመግለፅ ባሻገር ጥናቱ ስለመደረግ አለመደረጉ

በሪፖርቱ የተባለ ነገር አለመኖሩ፣ አነደድ

8. ለ 2015 ዓ.ም በወረደው መነሻ እቅድ መሰረት እንደ ወረዳው ተጨባጭ ሁኔታ በመቃኘት የስራ

ቡድኑን እቅድ አሳታፊ በሆነ መንገድ ከማቀድ አኳያ፣

በጥንካሬ

 የስራ ቡድኑ ልዩ ልዩ ዕቅዶች ታቀዱ መሆኑ፣ በሁሉም ወረዳዎች

በዕጥረት

9. ስልጠና ያልወሰዱና በአዲስ ወደ ስራ ሂደቱ የተቀላቀሉ ባለሙያዎችን መለየትና ለመምሪያ ከማሳወቅ

እንዲሁም ለአዲስ ሙያተኞች የስራ መግቢያ ስልጠና በመስጠት ወደ ስራ ስምሪት ከማስገባት

አኳያ፣

በጥንካሬ

 በስራ ቡድኑ አዲስ ባለሙያዎች ያሉ ሲሆን የስራ ትውውቅ ስልጠና በወረዳው የስራ ቡድን

መሰጠቱና ዝርዝራቸውን ለዞን የማሳወቅ ስራ መሠራቱ፣ ሁለት እጁ (1)፣ ደ/ኤልያስ (1)፣

ጎንቻ (1) ደጀን፣ ጎዛምን (3)፣ ሸበል (1)፣ ሞጣ (1)


 አዲስ ባለሙያ በስራ ቡድኑ አለመኖሩ መገለፁ፣ እነብሴ፣ እነማይ፣ ሰዴ፣ ባሶሊበን፣ አዋበል፣

ቢቡኝ፣ እናርጅ፣ ደባይ

 ለ 5 አዲስ ር/መምህራንና ለ 2 ሱፐርቫይዘሮች የስራ መግቢያ ስልጠና በኢንስፔክሽን ቡድን

የተሠጠ መሆኑ፣ እነብሴ

በዕጥረት

 ምን ያህል አዲስ ባለሙያ እንዳለ በሪፖርቱ ላይ በግልፅ አለመቀመጡ፣ ደጀን

 ስለአዲስ ባለሙያዎች በሪፖርቱ ላይ በግልፅ የተቀመጠ ነገር አለመኖሩ፣ ማቻክል፣ አነደድ

10. የይዞታ ማረጋገጫ ካርታና ፕላን የሌላቸው ትምህርት ተቋማት የይዞታ ማረጋገጫ እንዲኖራቸው

ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ርብርብ ከማድረግ አንፃር፣

በጥንካሬ

 በወረዳ ደረጃ ይዞታ ማረጋገጫ ካርታ የሌላቸው ተቋማት መረጃቸው ተለይቶ ችግሩን

ለመቅረፍ እየሠራ መሆኑ መገለፁ፣ ጎንቻ (9 መጀ/ደረጃ ት/ቤት እና 3 2 ኛ ደረጃ

ት/ቤቶች)፣ደጀን (3 ት/ቤቶች)፣ እነማይ (5 ት/ቤቶች)፣ ሰዴ (ከ 12 ቱ ት/ቤቶች የ 8 ቱ ችግሩ

መፈታቱ)፣ ሁለት እጁ (11 ት/ቤቶች)፣ ደ/ኤልያስ (1 የመጀ/ደረጃና 2 የ 2 ኛ ደረጃ)፣ ቢቡኝ

(2 የመጀ/ደረጃ ት/ቤቶች)፣ እናርጅ (5 2 ኛ ደረጃና 9 የመጀ/ደረጃ ት/ቤቶች)፣ጎዛምን (2

የመጀ/ ደረጃና 1 2 ኛ ደረጃ ት/ቤቶች)፣ ደባይ (10 ት/ቤቶች)፣ አነደድ (1 ት/ቤት)

 ከከንቲባ ጽ/ቤት ጋር በመፃፃፍ ለ 2 ት/ቤቶች ማለትም ለመርጡለ ማርያምና ለአብርሃ

ወአፅብሃ 1 ኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤቶች ካርታ እንዲሰራላቸው ማድረግ መቻላቸው

እንዲሁም ለ 18 የገጠር ት/ቤቶች ደብተር እንዲሠራላቸው በደብዳቤ አሣውቀው መሬት

አስተዳደር መረጃ እየለቀሙ የሚገኙና በጥሩ ሒደት ላይ የሚገኝ መሆኑ መገለፁ፤ እነብሴ

 በወረዳው ከሚገኙ 55 ት/ቤቶች 47 መሬት ማረጋገጫ ደብተር ላቸው ሲሆን ተቋማት

የሌላቸው በመሆኑ በአሁኑ ሰዓት በወረዳው መሬትን በዘመናዊ መንገድ መረጃ መያዝ

በማስፈለጉ ከክልል የካዳስተር ባለሙያዎች መጥተው ስራውን እየሰሩ መሆኑና ት/ቤት


አመራሮች ከባለሙያዎቹ ጋር በመቀራረብ ት/ቤታቸውን መሬት መረጃ በመስጠት አዲስ

ደብተር እንዲያወጡ ክትትልና ድጋፍ መደረጉ፣ ሸበል

በዕጥረት

 የይዞታ ማረጋገጫ የሌላቸው ተቋማት ያሉ ሲሆን ችግሩን ለመቅረፍ ስለተሠራው ስራ

በሪፖርቱ ግልፅ አለመደረጉ፣ ባሶሊበን

 በዚህ ወር ስለይዞታ ማረጋገጫ የተሠራ ስራ አለመኖሩ መገለፁ ፣ አዋበል

 የይዞታ ማረጋገጫ የሌላቸው ተቋማት ቁጥር በግልፅ አለመቀመጡ፣ ማቻክል፣ ሞጣ

11. በአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን የኢንስፔክሽን አገልግሎት ያገኙ ተቋማት በየፕሮግራሙ

በመለየት በየዓመተ ምህረቱ በመለየትና በማጠቃለል በሶፍት እና በሃርድ ኮፒ ከማደራጀት አኳያ፣

በጥንካሬ

 የኢንስፔክሽን መረጃዎች በሶፍትና በሃርድ ኮፒ የተያዘ መሆኑ፣ በሁሉም ወረዳዎች

12. ሌሎች ወቅታዊና ደራሽ ስራዎችን ከመስራት አኳያ፣

በጥንካሬ

 ደራሽ ስራዎች በአግባቡ እየተከናወኑ መሆኑ፣ በሁሉም ወረዳዎች

ከዚህ በታች ለቼክሊስቱ ቀደም ብሎ በተሠጠው ነጥብ መሠረት የወረዳዎች ደረጃ የወጣ ሲሆን የስናን ወረዳ

ግብረ መልሱ እስከተጠናቀረበት ሠዓት ድረስ ሪፖርቱ መድረስ ባለመቻሉ በደረጃው ሊካተት አልቻለም፡
የወረዳዎች ደረጃ
የደረጃ ሠንጠረዥ

የትምህርት ተቋማትን የግብዓት ክፍተት

ከማድረግና ለዞን ከማሳወቅ አንፃር (10%)


የሚያሳድጉ ተቋማትን በተመለከተ (5%)

መረጃን በሶፍትና በሃርድ ኮፒ ከመያዝ

ወቅታዊና ደራሽ ስራዎችን መፈፀም


ለአዲስ ባለሙያዎች የስራ ትውውቅ
ለም/ቤቶች ሪፖርት ከማቅረብ አኳያ

ልዩ ልዩ የስራ ቡድኑን ዕቅድ ከማቀድ


የኢንስፔክሽን ሱፐርቪዥን ዕቅድን
የኢንስፔክሽን ፕሮግራም በግልፅ

በግልፅ ከማስቀመጥ አንፃር (10%)

የዳሰሳ ጥናትን በተመለከተ (5%)


አዲስ የሚከፈቱና ደረጃቸውን

የተቋማትን የይዞታ ማረጋገጫ


የኢንስፔክሽን ዕቅድን በግልፅ
ከማስቀመጥ አንፃር (10%)

ከመፈተሸ አንፃር (10%)

በተመለከተ (10%)

ጠቅላላ ድምር
መቀመጡ (5%)

አንፃር (10%)

አንፃር (5%)

ደረጃ
(10%)

(10%)
ቁ ወረዳ
1 ጎዛምን 5 4 10 10 10 5 4.5 10 10 7.5 5 7.5 88.5 7

2 አነደድ 5 0 10 10 7 5 1 10 5 7.5 5 7.5 73 16

3 ባሶሊበን 5 0 10 10 10 5 0 10 10 0 5 7.5 72.5 17

4 ማቻክል 5 5 10 10 10 2.5 0 10 5 6 5 7.5 76 14

5 ደ/ኤልያስ 5 3 10 10 10 5 4.5 10 10 7.5 5 7.5 87.5 9

6 አዋበል 5 2.5 10 10 10 5 0 10 10 0 5 7.5 75 15

7 ደጀን 4 4 9.5 10 10 5 3.5 10 8 7.5 5 7.5 84 12

8 እነማይ 5 7 10 10 10 5 4.5 10 10 7.5 5 7.5 91.5 3

9 ሸበል 5 5 10 10 10 5 0 10 10 7.5 5 7.5 85 11

10 ደባይ 5 0 10 10 10 5 0 10 10 7.5 5 7.5 80 13

11 እናርጅ 5 8 10 10 10 5 3.5 10 10 7.5 5 7.5 91.5 3

12 ጎንቻ 4 5 10 10 10 5 4.5 10 10 7.5 5 7.5 88.5 7

13 እነብሴ 5 8 10 10 10 5 5 10 10 7.5 5 7.5 93 1


14 ሞጣ 5 2.5 10 10 10 5 5 10 10 6 5 7.5 86 10

15 ሁለት እጁ 5 7 10 10 10 5 5 10 10 7.5 5 7.5 92 2

16 ሰዴ 5 7 10 10 10 5 3.5 10 10 7.5 5 7.5 90፣5 6

17 ቢቡኝ 5 7 9 9 10 5 4.5 10 10 7.5 5 7.5 89.5 5

You might also like