You are on page 1of 8

"ህብረ ብሄራዊ አንድነታችን ለዘላቂ ሰላማችን"

የ 17 ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን


በዓል አከባበር መሪ እቅድ
በአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የተዘጋጀ

ነሃሴ/2014 ዓ.ም

ባህር ዳር

1. መግቢያ

0
"ህብረ ብሄራዊ አንድነታችን ለዘላቂ ሰላማችን"
የኢፌዲሪ ሕገ መንግሥት የፀደቀበትን ህዳር 29 ቀን ለመዘከር እለቱ በየዓመቱ የብሔረሰቦች ቀን ሆኖ እንዲከበር
በኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ሚያዚያ 21 ቀን 1998 ዓ.ም መወሰኑ ይታወቃል፡፡ ከዚህ ውሳኔ በኋላ እለቱ
ላለፉት አስራ ስድስት አመታት በመከበሩ ህብረተሰቡን በበርካታ ዘርፎች ተጠቃሚ ማድረግ ተችሏል፡፡ በዓሉ
በተለያዩ ዝግጅቶች በየዓመቱ በመከበሩ በክልላችን የሚገኙ የተለያዩ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ማንነት
በሚገባ እንዲታይና እንዲታወቅ በማድረግ ረገድ የላቀ አስተዋፅኦ አበርክቷል፡፡ በተለይም የክልሉ ህዝብ ከሌሎች
ክልሎች ብሔሮች ጋር የእርስ በእርስ ግንኙነት እንዲጠናከርና ባህላቸው፣ አልባሳቶቻቸው፣ እሴቶቻቸውን
በማስተዋወቅ የእርስ በእርስ ግንኙነት እንዲፈጠር በማድረግ ረገድ የበዓሉ ሚና የላቀ ነው፡፡ ከዚህ ባሻገር የበዓሉ
መከበር ዋነኛ ፋይዳ በአገራችን ሕገ መንግስትና ሕገ መንግሥታዊ ስርዓት ዙሪያ ህብረተሰቡ የተሻለ ግንዛቤ
እንዲያገኝ ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል፡፡

በዚህ መሰረት እስካሁን ሲከበር የቆየው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ሁሉም የአገራችን
ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ማንነታቸው እንዲከበርና በቀጣይ ለፍትህ፣ ነፃነትና ለዲሞክራሲ ስርዓት መከበርና
መረጋገጥ በጋራ ጠንክረው እንዲሰሩ የሚነሱበትን መሰረት የጣለ ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል፡፡

በኢፌዲሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔ መነሻነት በ 1999 ዓ.ም ሕዳር 29 ጀምሮ መከበር የጀመረው የኢትዮጵያ
ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል ላለፉት 16 ዓመታት ሲከበር በዓሉን በባለቤትነት በማስተባበር እንደ
ክልል ምክር ቤት ኃላፊነቱን ሲወጣ ቆይቷል፡፡

በ 2014 ዓ.ም ደግሞ “ወንድማማችነት ለሕብረብሔራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል 16 ኛው የኢትዮጵያ


ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በክልና በሁሉም የክልሉ ከተሞች ሲከበር በተለያዩ ሁነቶችና ፍፃሜዎች
ተከብሯል፡፡ በዓሉ በውጤቱ ከፍተኛ ተሞክሮ የተገኘበት ከመሆኑም በላይ ወቅታዊ አገራዊ ሁኔታን ግምት ውስጥ
በማስገባት በዓሉ በደም ልገሳ ፣የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል በመሰብሰብ ፣ በጦርነት የተጎዱ ወገኖችን በመጎብኘት
አብሮ ቡና የመጠጣት፣ ማዕድ የማጋራት፣ የተጀመረውን የስንቅ ዝግጅት ሥራ አጠናክሮ በመቀጠል ዘርፈ
ብዙ ስራ መስራት ተችሏል፡፡ በተለይም ደግሞ የአሸባሪ የህወሓት ሃይል የከፈተብንን አማራን የማዋረድና አገርን
የማፍረስ ድርጊት የኢትዮጵያ ብሄሮች፣ብሄረሰቦችና ህዝቦች በጋራ በመመከት ያሳዩትን ትግል በማስታወስ ቀጣይ
በሚደረገው አገርን የማዳን ተጋድሎ ደግሞ በጋራ እንድንቆም መነሳሳት በመፍጠር አንድ አቋም ይዘን የወጣንበት
ነው፡፡

ስለሆነም የ 17 ኛው በዓል አከባበር ከዚህ ቀደም የተከበሩ በዓላት ልምዶችን ውስንነቶችንና ድክመቶች በማረም
በሲዳማ ክልል አስተናጋጅነት በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት እንዲከበር በፌደሬሽን ምክር ቤት ተወስኗል፡፡ በዚህ
መሠረት በአሉ “ህብረ ብሄራዊ አንድነታችን ለዘላቂ ሰላማችን” በሚል መሪ ቃል ይከበራል፡፡ የኢፌዴሪ
ፌዴሬሽን ምክር ቤት የላከውን እቅድም መነሻ በማድረግ በአማራ ክልል የበዓሉን አከባበር በተመለከተ ይህ
ክልላዊ መሪ እቅድ ተዘጋጅቷል፡፡

2. የእቅዱ መነሻዎች

1
"ህብረ ብሄራዊ አንድነታችን ለዘላቂ ሰላማችን"
2.1. ሕገ መንግስታችን የፀደቀበትን ቀን በመዘከር የምክር ቤቱ ውሳኔ እንደ ዕቅድ መነሻ

ለኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች መብት መከበር ሕገ መንግሥታዊ ዋስትና ያረጋገጠው የኢ.ፌ.ዲ.ሪ
ሕገ መንግሥት የፀደቀበትን ህዳር 29 ቀን 1987 ዓ.ም ለመዘከር የፌዴሬሽን ምክር ቤት በወሰነው ውሳኔ መሠረት
እለቱ ከህዳር 29 ቀን 1999 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት እየተከበረ ይገኛል፡፡ የአገራችን ብሔሮች፣
ብሔረሰቦችና ህዝቦች በሚገኙበት በዚህ በዓል የጋራ መድረክ በመፍጠር ልምዳቸውን፣ ተሞክሮቻቸውን፣
ባህላቸውንና ማህበራዊ አኗኗራቸውን በማሳየት ያለውን ብዝሃነትና ህብር በሚገባ ጐልቶ እንዲወጣና
ኢትዮጵያዊነት የሁሉም ህብራዊነት መሆኑን የሚረጋግጥበት ነው፡፡ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን መከበሩ
ሁሉም ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ማንነታቸው እንዲከበርና በቀጣይ ለፍትህ ነፃነት ለዲሞክራሲ ስርዓት
መከበርና መረጋገጥ በጋራ ጠንክረው እንዲሰሩ የሚነሱበት ሆኗል፡፡ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የብሔሮች፣
ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ምክር ቤት በመሆኑ በጉዳዩ ባለቤትነት የሁሉንም ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ማንነት
ጐልቶ እንዲወጣ እያደረገ ይገኛል፡፡

በዚህ ረገድ የምክር ቤቱን ውሳኔ በመተግበር ላለፉት 16 ዓመታት በበዓሉ የተገኙት ውጤታማ ተግባራት በተለይም
ህዝባዊ ተጠቃሚነትን በማረጋገጥ የታየው መነቃቃት ቀላል ባለመሆኑ የፌዴሬሽን ምክር ቤት እለቱ በየዓመቱ
እንዲዘከር መወሰኑ እንደመነሻ ተይዟል፡፡

2.2. የ 17 ኛዉ የኢትዩጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ዓል አከባበር እንደመነሻ

የ 16 ኛው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል “ወንድማማችነት ለሕብረብሔራዊ


አንድነት" በሚል መሪ ሃሳብ እንደ ሃገር በድሬዳዋ ከተማና በክልላችንም ተከብሯል ፡፡ በአሉን ለማከበር
ባለንበት የዋዜማ ዝግጅት ላይ በዉጭና በዉስጥ የሚገኙ የጠላት ሃይል በተለይም የአሸባሪው የሕወሃት

ቡድን ክልላችን ብሎም አገራችን አደጋ ላይ በመጣል የኢትዩጵያን ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦችን
ለመበታተን በከፈተዉ የሕልውና አደጋ ለመመከት ሁሉም ኢትዩጵያዉያን በአንድ የቆሙበት ወቅት መሆኑ
በአሉን ለማክበር የራሱ የሆነ ተግዳሮትና መልካም አጋጣሚዎች የነበሩ ቢሆንም ተግዳሮቱን ወደ መልካም
አጋጣሚ በመቀየር የበዓሉን አከባበር ከሕልውና ማስከበር ዘመቻው ጋር በሚመጋገብ ሁኔታ እቅዱን
በመከለስ በዓሉ የሕዝቦችን አንድነትና ወንድማማችነትን የበልጥ ሊያጎለብት በሚችል አግባብ ተከብሯል፡፡

ለዚህም ማሳያ ተደርጎ የሚወሰደዉ የህልዉና ዘመቻዉን ለመደገፍ በዓሉን አስመልክቶ በተደረጉ የንቅናቄ
ስራዎች በደም ልገሳ 9,510 ዩኒት ደም ለማሰባሰብ ተችሏል ፣ የዘማች ቤተሰቦችን ከመደገፍ አኳያ ለ 120

ዘማች ቤተሰቦች ነጻ የትምህርት ዕድል ተሰጥቷል፤ በወራሪው የትግራይ


ቡድን ለተፈናቀሉ ለ 3‚747 ተፈናቃዮች የአልባሳት ድጋፍ ተደርጓል፤
2
"ህብረ ብሄራዊ አንድነታችን ለዘላቂ ሰላማችን"
በጦርነት የተጎዱ ወገኖችን በመጎብኘት አብሮ ቡና የመጠጣት፣ ማዕድ የማጋራት፣ የተጀመረውን የስንቅ
ዝግጅት ሥራ አጠናክሮ በመቀጠል የተሰሩ ስራዎች እንዲሁም የበዓሉ መከበር በዉስጥና በዉጭ ላሉ
የሀገራችንን መበታተን ለሚፈልጉና ለሚመኙ የፌዴራል ሰርዓቱ እንዳይጠናከር ለሚሰሩ የጠላት ሃይሎች
ተሰፋ ያስቆረጠ ከመሆኑ ባሻገር ለዉስጣዊ አንድነታችን መጠናከር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱ
እንደመነሻ ሁኔታ ተወስዷል፡፡

3. የበዓሉ ዓላማ

4. በክልል ደረጃ በትምህርት ሴክተሮች ኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የእርስ በእርስ ትስስር
በማጠናከር በብዝኃነት ላይ የተመሰረተ ሕብረብሔራዊ አንድነትን ሥር እንዲሰድ ለማድረግ የገቡትን ቃል
ኪዳን በማደስ በአዲስ መንፈስ እንዲነሳሱ ማድረግ ነው፡፡

5. የበዓሉ ግብ

በክልል ደረጃ በትምህርት ሴክተሮች የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን በዓል አከባበር አገራዊ
አንድነትን በሚያጠናክር መልኩ ይከናወናል፡፡

6. የበዓሉ መሪ ቃል

በ 2015 ዓ.ም ህዳር ወር ላይ የሚከበረው 17 ኛው ኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል ወቅታዊ
እና አገራዊ ሁኔታዎችን ከግምት በማስገባት ከአገራዊ የምክክር ሂደቱ ጋር በሚመጋገብ መልኩ ማክበር ያስፈልጋል፡፡
ስለሆነም በዓሉ ኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች የሚያቀራርቡ፣ የሚያስተሳስሩ እና በብዝሃነት ላይ
የተመሰረተ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት ስር እንዲሰድ እና እንዲዳብር በሚያደርጉ ተግባራት እና ኩነቶች ላይ
የሚያጠነጥን ለማድረግ ከፌደረሽን ምክር ቤት በተላከው መነሻ መሰረት የበአሉ መሪ ቃል “ህብረ ብሄራዊ
አንድነታችን ለዘላቂ ሰላማችን” ነው፡፡

7. የትምህርት ተቋማት በዓል አስተባባሪ ን/ንዑስ ኮሚቴ

በዚህ ኮሚቴ ስር የተቋማትን የበዓል አከባበር ሁኔታ የሚያስተባብሩ የሚከተሉት አባላት ይኖሩታል፡

 የትምህርት መምሪያ ኃላፊ…………………ሰብሳቢ


 የዞን ምክር ቤት የሚወከል…………………………….……………..ም/ሰብሳቢ
 የሙያ ቴክኒክ ኢንተርፕራይዝ መምሪያ ኃላፊ……………………..…አባል
 የከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ኃላፊ…………………………..…አባል
 ከዞን ምክር ቤት ጽ/ቤት የሚወከሉ 2 ሰዎች………………………..…አባል
6.1 የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

3
"ህብረ ብሄራዊ አንድነታችን ለዘላቂ ሰላማችን"
6.1.1 በቅድመ ዝግጅት የሚከናወኑ ተግባራት
 የክልል ትምህርት ቢሮ እቅድን መነሻ በማድረግ ዞናዊ መሪ እቅድ ማዘጋጀት፣
 የዞኑ አብይ ኮሚቴ በእቅዱ ላይ ዉይይት በማድረግ ማጸደቅ
 በአብይ ኮሚቴዉ እቅድ መነሻ ልዩ ልዩ ኮሚቴዎችን አደራጅቶ ወደ ስራ ማስገባት፤
 ከክልል ትምህርት ቢሮ የሚላከውን ርእስ መነሻ በማድረግ ለሲምፖዚየም እና በየደረጃዉ ለሚደረጉ

ዉይይቶች የሚሆኑ ርእስ መምረጥ፣


 ለሚዲያ አካላትና ለሚቋቋሙ ኮሚቴዎች እቅዱን መነሻ በማድረግ የበአሉን አስፈላጊነት እና ዓላማ ላይ ግልጽነት
በመፍጠር መግባባት ላይ መድረስ

በክልል ትምህርት ቢሮ የተመረጡ የዉይይት ርዕስ

 የሕብረብሔራዊ ፌዴራላዊ ስርዓት ምንነት፣ ባህሪያት እና አፈጻጸም በኢትዮጵያ የሚል ነዉ

6.1.2 በተግባር ምዕራፍ የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

 የትምህርት ተቋማት በዓል አስተባባሪ ን/ንዑስ ኮሚቴ ተግባርና ኃላፊነት

 በትምህርት ተቋማት ስለሚኖረው የበዓል አከባበር ዝግጅቶች የበዓሉን መሪ ዕቅድ ተከትሎ ያስፈጽማል፡፡
 አደረጃጀታቸውን ተከትለው በጋራና በተናጠል በዓሉን ስለሚያከብሩበት ሁኔታ ዕቅድ ያዘጋጃል ያስፈጽማል፡፡
 ለትምህርት ተቋማት የሚውሉ የመወያያ ጽሁፍ ያዘጋጃል፣
 እያንዳንዱ ተቋም ለበዓል አከባበር የሚያስፈልገውን ወጭ እንዲሸፍን ያደርጋል፡
 በ 1 ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ፣ በ 2 ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና የመምህራን ትምህርት ኮሌጆች ስለሚኖረው
የበዓል አከባበር ዝግጅቶች በበዓሉን መሪ ዕቅድ መሰረት እቅድ ያዘጋጃል፤ ያስፈጽማል፡፡
 የስራዎቹን ሪፖርት ለአብይ ኮሚቴው ያቀርባል፤

6.1.4 የትምህር ተቋማት በዓል አስተባባሪ ንኡስ ኮሚቴ


 የትምህርትቤቱ ር/መምህር------------------------ሰብሳቢ
 የወመህ ሊቀመንበር------------------------------- ም/ሰብሳቢ
 የትምህርት ቤቱ ም/ር/መምህር-------------------- ፅሐፊ
 የስነ-ዜጋና ስነ-ምግባር መምህር-------------------------- አባል
 የትምህርት ክፍል ሐላፊዎች---------------------------አባል

6.1.5 የትምህር ተቋማት በዓል አስተባባሪ ንኡስ ኮሚቴ ተግባርና ሀላፊነት


4
"ህብረ ብሄራዊ አንድነታችን ለዘላቂ ሰላማችን"

 የትምህርት ተቋማት ማሕበረሰብ (አጠቃላይ እና ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት) በዓሉን

በልዩ ልዩ ኩነቶችና የውይይት መድረኮች እንዲካሄዱ የማስተባበር ሥራ ይሰራል፤

ሕብረብሔራዊ አንድነትንና ዘላቂ ሰላምን የሚያጎለብቱ የውይይት መድረኮች ማካሄድ፤


የመምህራንና የተማሪዎች የደም ልገሳ ፕሮግራም ማዘጋጀት
በትምህርት ተቋማት የተተከሉ ችግኞችን መንከባከብ
የስነፅሁፍ ዝግጅት ማቅረብ
የጥያቄና መልስ ዉድድር
የብሄር ብሄረሰቦች ባህልና ትዉፊት ማሳየት
የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መስራት

7. የሚዲያ እና ኮሚኒኬሽን ሥራዎችን በተመለከተ፤

 ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ የዞኑን የሚዲያ አካላት በቂ ኦሬንቴሽን በመስጠት በተለያዩ ፕሮግራሞች
የአስተምህሮ ስራ እንዲሰሩ ማድረግ፣ (ወጣቶችን ሴቶች ወ.ዘ.ተ መድረኮች)
 ሁሉም የሚዘጋጁ ሁነቶች እና ውይይቶች በልዩ ሁኔታ የዜና ሽፋንና ፕሮግራሞችን እንዲሰሩ ከሚዲያ
አካላት ጋር አስቀድሞ ስምምነት ላይ በመድረስ የሚዲያ ሽፋን በትኩረት ይሰራል፤
 በክልል ትምህርት ቢሮ የሚላኩ የበዓሉን መልዕክት የሚያስተላልፍ ልዩልዩ ህትመቶችን የማሰራጨት
ሥራ ይሰራል፤
 ጋዜጣዊ መግለጫዎች እንዲሰጡ ማመቻቸት

8. የክትትልና ድጋፍ አግባብ

 የበዓሉ አስተባባሪ ኮሚቴ በየጊዜው እየተገናኘ ስራዎችን ይገመግማል፣ ይከታተላል፣ ድጋፍ ይሰጣል፤
 የዞኑ ምክር ቤት የበዓል አከባበሩን እቅድ እሰከታች አደረጃጀት በማውረድ ድጋፍና ክትትል ያደርጋል፤
 እቅዱ ወደስራ መግባቱን በግብረ-መልስ፣ በስልክና በአካል ድጋፍ ያደርጋል፤

9. ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮችና መፍትሔዎች


9.1 ሊያጋጥሙ የሚችሉ ችግሮች
 በአንዳንድ ዞኖች ባለዉ ወቅታዊ ሁኔታ በሁሉም ወረዳዎች እና ትምህርት ቤቶች በዓሉን በተሟላ መልኩ
ለማክበር ያለመቻል፤
 ከእቅዱ ጀምሮ ለስራው ትኩረት ያለመስጠት
 የስራ መደራረብና በዓሉን አቅሎ ማየት
 በቅንጅት ተናቦ ያለመስራት/የኮሚቴ አለመሟላት፤

5
"ህብረ ብሄራዊ አንድነታችን ለዘላቂ ሰላማችን"
 እያንዳንዱ የኮሚቴ አባል የሚጠበቅበትን ያለመወጣት፤

9.2 የመፍትሔዎች እርምጃዎች

 በተሻለ የጸጥታ ሁኔታ ውስጥ ባሉ ወረዳዎች እና ትምህርት ቤቶች በትኩረት ተግባራት እንዲፈጸሙ
ማድረግ፤
 ሁሉም ባለድርሻ አካላትን ከእቅድ ጀምሮ ማሳተፍ፤
 በየወቅቱ መረጃዎችን መለዋወጥ፤
 ጠንካራ ድጋፍና ክትትል ማድረግ፤
 ግብረመልስ መስጠትና ያልተተገበረውን በግምገማ ማስተካከል

o የሚከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት

 የፅዳት ዘመቻ
o የስፖርት ዉድድር ማካሄድ

15. የድርጊት መርሃ ግብር


ተ.ቁ. ዋና ዋና ተግባራት የክንውን ጊዜ
1. የበዓሉ መሪ እቅድ በአብይ ኮሚቴ እንዲጸድቅ ማድረግ፣ እስከ ጥቅምት 10/2015
1. የደም ልገሳ እና የወጣቶች የበጎ ፈቃደኝነት አገልግሎት ይጀመራል ከህዳር 1/2015 ጀምሮ
2. የውይይት ሰነዶችን ለወረዳና ለትምህርት ቤቶች ማስራጨት ከህዳር 15/2015 ጀምሮ
የባህል ትርዒት ተሳታፊዎችን መለየት ከህዳር 1/2015 ጀምሮ
3.
የባህል ትርዒት ማሳየት ህዳር 29/2015
4.

6
"ህብረ ብሄራዊ አንድነታችን ለዘላቂ ሰላማችን"
ተ.ቁ. ዋና ዋና ተግባራት የክንውን ጊዜ
በግቢዉ የተተከሉ ችግኞችን መንከባከብ ከጥቅምት 8-ህዳር 30/2015
5.
የጥያቄና መልስ ዉድድር እና የስነ ፅሁፍ ዝግጅት ማቅረብ እስከ ህዳር 15/2015
6.
7. የአብይ ኮሚቴ አባል የሆኑ የክልል ቢሮዎች የአፈጻጸም ሪፖርት ይቀርባል፤ እስከ ታህሳስ 15/2014
8. የዞኖች የአፈጻጸም ሪፖርት ይቀርባል እስከ ታህሳስ 10/2015
የበዓሉ ክንውን የሚያሳይ አጠቃላይ ሪፖርት በክልሉ አብይ ኮሚቴ ይገመገማል፣ እስከ ታህሳስ 20/2015
9.
ለቀጣይ ዓመት ትምህርት በሚወሰድባቸው ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ ይቀመጣል

You might also like