You are on page 1of 25

የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ቅበላ እና

ምደባ ፖሊሲ

(Higher Education Students’ Admission and


Placement Policy)

A Transitional Policy

የካቲት 2013 ዓ.ም


አዲስ አበባ
ኢትዮጵያ
0
ማውጫ
ማውጫ ..................................................................................................... 1
የክቡር ሚኒስትሩ መልዕክት.............................................................. 2
1. መግቢያ .................................................................................................. 4
2. የፖሊሲው አስፈላጊነትና ዓላማ ........................................................... 5
2.1. የፖሊሲው አስፈላጊነት .......................................................... 5
2.2. የፖሊሲው ዓላማ .................................................................... 6
3. የተማሪዎች የቅበላና ምደባ መርሆዎች............................................... 8
4. የቅበላ እና ምደባ መስፈርቶች............................................................. 8
4.1 ለቅበላና ምደባ መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡- ................ 8
4.2. የተቋማት ምርጫ እና ምደባ................................................ 10
4.3. የትምህርት መስክ ምርጫ እና ምደባ ................................... 11
4.4. ልዩ ድጋፍ የሚደረግላቸው ተማሪዎች .................................. 12
5. የፖሊሲ ጉዳዮች፣ ግቦች እና ስትራቴጂዎች ..................................... 13
5.1. ሀገራዊ የኢኮኖሚ ፍላጎትን፤ የተማሪዎች ብቃትና ዝንባሌን
መሰረት ያደረገ የትምህርት መስክ ምደባ.......................... 13
5.2 ከተቋማት ልየታ ጋር የተሰናሰለ የተማሪዎች ቅበላ እና ምደባ
........................................................................................ 15
5.3 በቴክኖሎጂ የተደገፈ ፍትሐዊና ሚዛናዊ የተማሪዎች ቅበላና
ምደባ ............................................................................... 16
5.4 ብዝሐነትን ታሳቢ ያደረገ የተማሪዎች ቅበላና ምደባ ............. 17
5.5 የዓለም አቀፍ ተማሪዎች ቅበላ እና ምደባ ............................. 18
5.6 አመራር፤ አስተዳደርና የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ................ 19
6. የተፈጻሚነት ወሰን .............................................................................. 21
7. ፖሊሲውን ስራ ላይ ስለማዋል ......................................................... 21

1
የክቡር ሚኒስትሩ መልዕክት

የተከበራችሁ የሀገራችን ህዝቦች

የከፍተኛ ትምህርት በሀገራችን መሰጠት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ


በርካታ ለውጦች ተመዝግበዋል፡፡ በተለይም ባለፉት ሁለት
አስርት ዓመታት የቅበላ አቅማችን በከፍተኛ ሁኔታ አድጓል፡፡
ይሁን እንጅ የመቀበል አቅማችን ያደገውን ያህል በትምህርት
አግባብነትና ጥራት ላይ አመርቂ ውጤት አልተመዘገበም፡፡
በመሆኑም ጥራትና አግባብነቱ የተረጋገጠ የከፍተኛ ትምህርት
ለመስጠት ይቻል ዘንድ አገራዊ የተማሪዎች የቅበላና ምደባ
ስርዓት መዘርጋት ለነገ የሚተው ተግባር አይደለም፡፡ የተቋማትን
ስልጣንና ኃላፊነት ከግንዛቤ ያስገቡ መመሪያዎችን በማዘጋጀት
የከፍተኛ ትምህርት የተማሪዎች ቅበላና ምደባ ሲካሄድ ቆይቷል፡፡
በመመሪያ ያልተሸፈኑ ጉዳዮች ሲገጥሙ ደግሞ በሰሪኩላር
ወቅታዊ ምላሽ ሲሰጥባቸው ነበር፡፡ አሁን ግን የተማሪዎች
የቅበላና ምደባ ፖሊሲን በማዘጋጀትና በመተግበር ፍትሃዊ
የተማሪዎች ተሳትፎን ለማሳደግ፤ የትምህርት ጥራትና
አግባብነትን ለማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ ይህ ፖሊሲ
ተዘጋጅቷል፡፡ ስለሆነም ፖሊሲውን ተግባራዊ ለማድረግ ድርሻ
ያላችሁ አካላት የሚጠበቅባችሁን ሚና በአግባቡ እንድትወጡ
እያሳሰብኩ ወጥና አገራዊ የቅበላና ምደባ ስርዓት በማዘርጋት እና
2
ሀገሪቱ የምትፈልገውን የተማረ የሰው ኃይል በማፍራት
የሀገራችንን ብልጽግና እውን ለማድረግ ሁሉም የትምህርት
ማህበረሰብ በንቃት እንዲሳተፍ ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡

አመሰግናለሁ፡፡

ሳሙኤል ኡርቃቶ (ዶ/ር)

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር

3|የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ቅበላ እና ምደባ ፖሊሲ


1. መግቢያ
በሀገራችን የከፍተኛ ትምህርትን ለመምራት እንዲቻል የተለያዩ
የከፍተኛ ትምህርት አዋጆች በተለያየ ጊዜ ወጥተዋል፡፡ ከእነዚህም
ውስጥ አዋጅ ቁጥር 109/1977፣ የከፍተኛ ትምህርት አዋጅ ቁጥር
351/1995፣ አዋጅ ቁጥር 650/2001 እና አዋጅ ቁጥር1152/2011
ተጠቃሾች ናቸው። በተለይም እየተስፋፋ የመጣውን የከፍተኛ
ትምህርት ንዑስ ዘርፍን በተሻለ ደረጃ ለመምራት እንዲቻል
የኢፌዴሪ አስፈጸሚ አካላት ስልጣንና ተግባር ለመወሰን በወጣው
አዋጅ ቁጥር 1097/2011 መሰረት የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት
ሚኒስቴር በአዲስ መልክ ተቋቁሟል፡፡ ከላይ በተጠቀሱት የከፍተኛ
ትምህርት አዋጆች ውስጥ ሰለተማሪ ቅበላ እና ምደባ፣ የአካል
ጉዳተኛ ተማሪዎችን እና የታዳጊ ክልሎችን ከግንዛቤ ውስጥ
ያስገቡ አንቀፆች ይገኛሉ። ለምሳሌ አዋጅ ቁጥር 351/1995
በአንቀጽ 31 ከቁጥር 1-3፤ አዋጅ 650/2001 አንቀጽ 39 ከቁጥር
1-3 እና አንቀጽ 40 ከቁጥር 1-4 እንዲሁም አዋጅ ቁጥር
1152/2011 አንቀጽ 40 ከቁጥር1-7 እና አንቀጽ 41 ከቁጥር 1-5
የሚጠቀሱ ናቸው።

ወደ መንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚገቡ አዲስ ገቢ


የተማሪዎች ቅበላ እና ምደባ ስራ በመንግስት በኩል ሲከናወን
ቆይቷል። ይሁን እንጂ የቅበላ እና ምደባ ስራው ሲከናወን
የነበረው በተቋማት አዋጅ ላይ በመንተራስ እና የማስፈጸሚያ

4|የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ቅበላ እና ምደባ ፖሊሲ


መመሪያዎችን በማዘጋጀት ሲሆን ወጥ የቅበላ እና ምደባ ፖሊሲ
አልነበረም። ተማሪዎች በመረጡት የትምህርት መስክ የመማር
ዕድላቸው ዝቅተኛ መሆኑ፣ ቅበላ እና ምደባው ሀገር አቀፍ
የሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ፈተናን ብቻ መሰረት ያደረገ መሆኑ፣
በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጡ የትምህርት መስኮች
ከተማሪውና ከገበያው ፍላጎት ጋር የተመጣጠኑ አለመሆን፣ የቅበላ
እና ምደባ ሂደቱ በቅርቡ የተካሄደውን የከፍተኛ ትምህርት
ተቋማትን በተልዕኮና በትኩረት መስክ ልየታ እና የትኩረት
መስካቸውን ያገናዘበ አለመሆን እስካሁን በነበረው አፈጻጸም
የተስተዋሉ ችግሮች ናቸው። የቅበላ እና ምደባ መስፈርቶቹም
ተለዋዋጭና ዘላቂ ሁኔታዎችን ከግንዛቤ ውስጥ ያላስገቡ ሆነው
ይታያሉ። ይህ ሁኔታ ደግሞ በየጊዜው በተማሪዎች ቅበላ እና
ምደባ ዙሪያ በርካታ ችግሮች እንዲስተዋሉ አስተዋጽዖ አድርጓል።
ስለሆነም እነዚህንና ተዛማጅ ችግሮችን ሊፈታ የሚችል ወጥ
አገራዊ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች የቅበላ እና ምደባ ፖሊሲ
ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖ ስለተገኘ ይህ ፖሊሲ ተዘጋጅቷል።

2. የፖሊሲው አስፈላጊነትና ዓላማ

2.1. የፖሊሲው አስፈላጊነት

የከፍተኛ ትምህርት መሰጠት ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ


በኢትዮጵያ በርካታ የተማሪ ቅበላ እና ምደባ ስራዎች ተግባራዊ
ሆነዋል፡፡ ይሁን እንጂ ከዚህ በፊት የነበረው የተማሪዎች ቅበላ
5|የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ቅበላ እና ምደባ ፖሊሲ
እና ምደባ ብዙ ችግሮች የነበሩበት እንደሆነና አሁን ካለው ፈጣን
አገራዊ ለውጥና የተማሪዎች ፍላጎት ጋር አብሮ የሚሄድ ሆኖ
አልተገኘም፡፡ ስለዚህ እነዚህን ችግሮች ለመፍታት፣ ውጤታማ እና
የተማሪዎችን ፍላጎት ማስተናገድ የሚችል አዲስ የተማሪዎች ቅበላ
እና ምደባ ፖሊሲ ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኗል ፡፡

በመሆኑም ይህ የቅበላ እና ምደባ ፖሊሲ በዋናነት


የሚያስፈልገው፡-

x ጥራት ያለው፣ ጊዜና ወጪ ቆጣቢ (በቴክኖሎጂ የታገዘ)፣


ውጤታማ፣ ፍትሐዊ፣ የተማሪዎችን ፍላጎትና አቅም
ያገናዘበ የቅበላና ምድባ ስርዓት ለመዘርጋት፣
x የተማሪዎች ቅበላ እና ምደባ በዩኒቨርስቲዎች ተልዕኮ እና
የትኩረት መስክ ልየታ፣ አገራዊ የኢኮኖሚ ፍላጎትና
ወቅታዊ ሁኔታዎች ላይ የተመሰረተ ለማድረግ፣
በአጠቃላይ እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩትን ጉዳዮች በተገቢ ሁኔታ
ለመመለስ የተማሪዎችን ቅበላ እና ምደባ ፖሊሲ ማዘጋጀት
አስፈላጊ ሆኗል፡፡

2.2. የፖሊሲው ዓላማ

ይህ የቅበላ እና ምደባ ፖሊሲ የሚከተሉት ዋና ዓላማና ዝርዝር


ዓላማዎች አሉት።

6|የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ቅበላ እና ምደባ ፖሊሲ


ዋና ዓላማ

ሐገራዊ ኢኮኖሚን፤ የተቋማት የመቀበል አቅምንና የትከረት


መስክ ልየታን መሰረት ያደረገ፤ በተማሪዎች ብቃት፣ ፍላጎትና
ዝንባሌ ላይ የተመሰረተ፤ የትምህርት ጥራት መርህን ያገናዘበ፤
ግልጽ፣ ፍትሐዊና የውድድርን መርሕን የተከተለ እንዲሁም ልዩ
ድጋፍን ያካተተ የተማሪዎች ቅበላ እና ምደባ ስርዓት መዘርጋት
ነው፡፡

ዝርዝር ዓላማዎች፡-

x በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ግልጽ፣ ፍትሃዊ እና


ተዓማኒ የሆነ የተማሪዎች ቅበላ እና ምደባ ስርዓት
ለመዘርጋት፣
x በግልና በመንግስት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት
የተማሪዎች ምደባ እና ቅበላ ወጥነት ባለው የፖሊሲና
የአፈፃፀም አቅጣጫ ለመምራት፣
x የሀገሪቱን የከፍተኛ ትምህርት የተማሪዎች ቅበላ እና ምደባ
ሥርዓትን ከአህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ አካሄዶች ጋር
ተቀራራቢና በዘመናዊ ቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ፣
x በግል የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎችን ተሣትፎ
ለማበረታታትና ለማሳደግ፣

7|የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ቅበላ እና ምደባ ፖሊሲ


3. የተማሪዎች የቅበላና ምደባ መርሆዎች

የተማሪዎች የቅበላ እና ምደባ ፖሊሲ መሠረት የሚያደርጋቸው


ዋና ዋና መርሆዎች (Principles) ተደራሽነት፣ ፍትሐዊነት፣
ግልፅነት፣ ተጠያቂነት፣ ብዝሃነት፣ ተወዳዳሪነት፣ ዓለም አቀፋዊነት፣
አሳታፊነት እና ልህቀት የሚሉ ናቸው።

4. የቅበላ እና ምደባ መስፈርቶች

4.1 ለቅበላና ምደባ መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡-

የከፍተኛ ትምህርትን ለመከታተል ለቅበላ እና ምደባ መሟላት


የሚገባቸው መስፈርቶች፡-

1. የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አጠናቀው በቀጥታ ወደ ከፍተኛ


ትምህርት ተቋማት ለሚገቡ
x የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የማጠናቀቂያ ፈተና
ወስደው 50% እና ከዚያ በላይ ውጤት ያገኙ፤
x የመንግስት ተቋማት የመቀበል አቅምን በማገናዘብ
በሳይንስ ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የሚወሰነውን
የመቁረጫ (የማለፊያ) ነጥብ ያሟሉ፤
x የተማሪዎችን አጠቃላይ ብቃት ለመመዘን
የሚያስችለውን የችሎታ መመዘኛ ፈተና (Scholastic
Aptitude Test) የወሰዱ፤

8|የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ቅበላ እና ምደባ ፖሊሲ


2. የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና በድጋሜ
ለሚወስዱ ተማሪዎች
x የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት የማጠናቀቂያ ፈተና
ውጤታቸው 50% እና ከዚያ በላይ የሆነ፤
x በዘመኑ ለግል ተፈታኞች የሚወሰነውን የመቁረጫ
(የማለፊያ) ነጥብ ያሟሉና የችሎታ መመዘኛ ፈተና
(Scholastic Aptitude Test) የወሰዱ፤
3. ከኢትዮጵያ ውጪ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን
አጠናቀው በሀገር ውስጥ የከፍተኛ ትምህርት ለመማር
ለሚያመለክቱ ተማሪዎች የሚያቀርቡት ማስረጃ ከኢትዮጵያ
ሁለተኛ ደረጃ ማጠናቀቂያ ውጤት ጋር የአቻ ግምት
ማስረጃ የተሰጠውና በተቋማት የተዘጋጀውን የመግቢያ
ፈተና ያለፉ፣
4. የትምህርት ደረጃቸውን ለማሻሻል የሚፈልጉ አመልካቾች
x በዲፕሎማ ወይም በሰርቲፊኬት (ከደረጃ IV-V)
ዝግጅት ኖሯቸው የመጀመሪያ ዲግሪ ለመማር
ለሚፈልጉ ተማሪዎች ለደረጃው የሚሰጠውን የብቃት
ምዘና ማረጋገጫ ሰርተፊኬት የሚያቀርቡና
በተቋማት የሚሰጡ የመግቢያ ፈተና ወስደው
የማለፊያ ውጤት ያገኙ፣

9|የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ቅበላ እና ምደባ ፖሊሲ


5. የመጀመሪያ ዲግሪ ኖሯቸው በሌላ የትምህርት መስክ
መማር የሚፈልጉ ዜጎች ተቋማት የሚያስቀምጧቸውን
መስፈርቶችን ያሟሉ፣
6. የሁለተኛ ደረጃ ትምህርትን አጠናቀውና በስራ ዓለም
ቆይተው ወደ ከፍተኛ ትምህርት መግባት ለሚፈልጉ
በዲፕሎማ ወይም ሰርቲፊኬት መመረቅ ሳያስፈልጋቸው
የደረጃ IV ወይም V የብቃት ማረጋገጫ ምዘና ወስደው
ብቃታቸው የተረጋገጠላቸው፣
7. ልዩ ባህሪ ያላቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚሰጡትን
የመግቢያ ፈተና ወስደው የማለፊያ ነጥብ ያገኙ፤
8. እንግሊዝኛ ቋንቋ የትምህርት መስጫ ቋንቋ ካልሆኑ አገራት
የሚመጡ ተማሪዎች የእንግሊዝኛ ቋንቋ ብቃት ማረጋገጫ
ወይም የተማሩበት ቋንቋ በእንግሊዝኛ ቋንቋ መሆኑን
ማስረጃ ያላቸው፤

4.2. የተቋማት ምርጫ እና ምደባ

1. የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተልዕኮና በትኩረት


መስክ ልየታን መሰረት ያደረገ የተማሪዎች ቅበላ እና
ምደባ ይካሄዳል፡፡
2. ተማሪዎች በከፍተኛ ደረጃ ወደ ግል የከፍተኛ
ትምህርት ተቋማት እንዲገቡ ለማድረግ የተቋማቱን
ባህሪ ያገናዘበ የማበረታቻ ሥርዓት ይዘረጋል፡፡

10 | የ ከ ፍ ተ ኛ ት ም ህ ር ት ተ ማ ሪ ዎ ች ቅ በ ላ እ ና ም ደ ባ ፖ ሊ ሲ
3. ልዩ ፍላጎት ያላቸው፣ የተለየ የጤና እክል ያለባቸውና
የሚያጠቡ ተማሪዎች ለተቋማቱ የተቀመጡ
መስፈርቶችን ካሟሉ በምርጫቸው ይመደባሉ።
4. በሀገሪቱ ካሉት አስቸጋሪ የአየር ፀባይ ውስጥ የሚገኙና
ያልለሙ አካባቢዎች በሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት
ተቋማት ላይ በምርጫቸው የሚመደቡ ተማሪዎች ልዩ
ተጠቃሚ (Special Privilege) የሚሆኑበት ሥርዓት
ይዘረጋል።
5. በኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ት/ቤት የሚማሩ ተማሪዎች
በሀገር ውስጥ ለተማሩ ተማሪዎች በተዘጋጁ መስፈርቶች
መሰረት ይመደባሉ፡፡
6. በውጭ ሀገር ኮሙኒቲ ት/ቤቶች (በውጭ ስርዓተ
ትምህርት) የተማሩ ተማሪዎች በሀገር ውስጥ የከፍተኛ
ትምህርት ተቋማት ለመመደብ ጥያቄ ሲያቀርቡ
የሚስተናገዱበት ስርዓት ይዘረጋል፡፡

4.3. የትምህርት መስክ ምርጫ እና ምደባ

ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሲመደቡ በሁለተኛ


ደረጃ ትምህርት ቤት በተማሩበት መስክ (የተፈጥሮ ወይም
ማህበራዊ ሳይንስ) አንዲሁም የመምህርነት ሙያ በተፈጥሮ
ሳይንስና እና በማህበራዊ ሳይንስ በሚል በአራቱ መስኮች
እንዲመደቡ ይደረጋል፡፡

11 | የ ከ ፍ ተ ኛ ት ም ህ ር ት ተ ማ ሪ ዎ ች ቅ በ ላ እ ና ም ደ ባ ፖ ሊ ሲ
ሀ. መሟላት ያለባቸው ዋና ዋና መስፈርቶች

1. የአንደኛ ዓመት (Freshman Courses) አማካይ ውጤት


(CGPA)
2. እንደ ጥናት መስኮች ልዩ ባህሪ የትምህርት ክፍሎች
የሚሰጡት የመግቢያ ፈተና፤

ለ. እንደ ሁኔታው መሟላት ያለባቸው ተጨማሪ መስፈርቶች


1. ከትምህርት መስኮች ልዩ ባህሪ አንፃር ተቋማት
ተማሪዎችን ወደ ትምህርት መስኮች ለመመደብ
የመሸጋገሪያ ኮርሶች (Bridging Courses) ሊሰጡ ይችላሉ
2. አገር አቀፍ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና
ውጤት፤

4.4. ልዩ ድጋፍ የሚደረግላቸው ተማሪዎች

ከላይ በተ.ቁ. 4.2 እና 4.3 ላይ ከተጠቀሱት መስፈርቶች


በተጨማሪ በቅበላ እና ምደባ ወቅት ልዩ ድጋፍ የሚደረግላቸው
ተማሪዎች ትኩረት የሚሰጣቸው ይሆናል። በዚህ መሰረት

1. ለሴት ተማሪዎች፣ በልማት ተጠቃሚ ካልሆኑ የማህበረሰብ


ክፍሎች ለሚመጡ ተማሪዎች፣ ልዩ ፍላጎት እና የጤና
ዕክል ላለባቸው ተማሪዎች፣ በቅበላ ወቅት ለሚያጠቡ
ተማሪዎች በልዩ ሁኔታ የሚስተናገዱበት ስርዓት
ይዘረጋል።

12 | የ ከ ፍ ተ ኛ ት ም ህ ር ት ተ ማ ሪ ዎ ች ቅ በ ላ እ ና ም ደ ባ ፖ ሊ ሲ
2. ልዩ ተሰጥኦ ወይም የላቀ ችሎታ ላላቸው ተማሪዎች
መደበኛ የትምህርት የቆይታ ጊዜ መጠበቅ ሳይኖርባቸው
በልዩ ሁኔታ ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ገብተዉ
መማር የሚችሉበት አሰራር ይዘረጋል፡፡

5. የፖሊሲ ጉዳዮች፣ ግቦች እና ስትራቴጂዎች

በከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ የተማሪ ቅበላ እና ምደባን


በውጤታማነት ለማከናወን የሚያስችሉ ከፍተኛ ትኩረት
የሚያስፈልጋቸው የፖሊሲ ጉዳዮችን በመለየት ግብ፤ የፖሊሲ
አቅጣጫና የማስፈጸሚያ ስትራቴጂዎችን በመንደፍ ተግባዊ
ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ በመሆኑም ግቦች፣ የፖሊሲ አቅጣጫዎች
እና ስትራቴጂዎች እንደሚከተለው ተለይተዋል።

5.1. ሀገራዊ የኢኮኖሚ ፍላጎትን፤ የተማሪዎች ብቃትና ዝንባሌን


መሰረት ያደረገ የትምህርት መስክ ምደባ

5.1 .1 ግብ

x ሐገራዊ የኢኮኖሚ ፍላጎትን፤ የተማሪዎች ዝንባሌና


ብቃት መሰረት ያደረገ የከፍተኛ ትምህርት
የተማሪዎች ቅበላና ምደባን ማረጋገጥ፣

5.1.2 የፖሊሲ አቅጣጫ

x ሀገራዊና ዓለምአቀፋዊ የገበያ ፍላጎትን እንዲሁም


የተማሪዎች ብቃትና ዝንባሌን መሰረት ያደረገ
የቅበላና ምደባ ስርዓት ይረጋገጣል።
13 | የ ከ ፍ ተ ኛ ት ም ህ ር ት ተ ማ ሪ ዎ ች ቅ በ ላ እ ና ም ደ ባ ፖ ሊ ሲ
5.1.3 ስትራቴጂዎች

1. የተማሪዎች ቅበላና ምደባን ከገበያ ፍላጎት፤ ከተማሪዎች


ዝንባሌና ብቃት ጋር አስተሳስሮ የሚሰራ ጠንካራ
መዋቅር ይዘረጋል፡፡

2. ተማሪዎች ተገቢ የሆነ የቅድመ-ቅበላና ምደባ የምክር


አገልግሎት (Career Guidance and Career
Counseling) የሚያገኙበት ሥርዓት ይዘረጋል፡፡

3. የተማሪ ቅበላና ምደባ ከአገሪቱ/ዓለምአቀፍ የገበያ ፍላጎት


ጋር ለማጣጣም የሚያስችል የስራ ገበያ መረጃ ስርዓት
(Labor Market Information System) ይዘረጋል፡፡

4. ቅበላ እና ምደባው ሀገራዊ የልማት ግቦችንና ዓለምአቀፍ


የልማት አጀንዳዎችን ለሚያሳልጡ የትምህርት
ፕሮግራሞች ትኩረት ይሰጣል፡፡

5. በግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምደባ ለማግኘት


የሚሹ ብቃት ያላቸው ተማሪዎች ምርጫቸውን
እንዲያገኙ ለማድረግ ከሚመለከተው የመንግስት አካል
ጋር ተቀናጅተው የሚሠሩበት ማዕቀፍ ይዘጋጃል፡፡

6. በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎችን ተሳትፎ


የሚያሳድጉ የፋይናንስ አማራጮች ይመቻቻሉ፡፡

14 | የ ከ ፍ ተ ኛ ት ም ህ ር ት ተ ማ ሪ ዎ ች ቅ በ ላ እ ና ም ደ ባ ፖ ሊ ሲ
5.2 ከተቋማት ልየታ ጋር የተሰናሰለ የተማሪዎች ቅበላ እና ምደባ

5.2.1 ግብ
x በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ቅበላ እና
ምደባ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተልዕኮና
ትኩረት መስክ ልየታ ጋር እንዲመጋገብ ማድረግ፣
5.2.2 የፖሊሲ አቅጣጫ

x የተማሪዎች ቅበላ እና ምደባን ከዩኒቨርሲቲ


በተልዕኮና ትኩረት መስክ ልየታ (University
Differentiation) ጋር ተናብቦ እንዲፈጸም ይደረጋል።
5.2.3 ስትራቴጂዎች
1. የተማሪ ቅበላና ምደባው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት
ልየታን መሰረት ያደረገ ትግበራን በኃላፊነት ወስዶ
የሚሰራ አካል ይጠናከራል፡፡

2. የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከተለዩበት የተልዕኮና


ትኩረት መስክ አንጻር የቅበላ አቅማቸውን ወቅቱን
ጠብቀው የሚያሳውቁበት አሰራር ይዘረጋል፡፡

3. የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ልየታ፡ የተማሪ ቅበላና


ምደባ እንዲሁም የስራ ገበያ ፍላጎት ተሰናስለው
መሄዳቸውን በየጊዜው የሚፈተሽበት አሰራር ይዘረጋል።

15 | የ ከ ፍ ተ ኛ ት ም ህ ር ት ተ ማ ሪ ዎ ች ቅ በ ላ እ ና ም ደ ባ ፖ ሊ ሲ
5.3 በቴክኖሎጂ የተደገፈ ፍትሐዊና ሚዛናዊ የተማሪዎች ቅበላና
ምደባ

5.3.1. ግብ

x የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማስፋፋት በከፍተኛ


ትምህርት ዘርፍ የተማሪ ቅበላና ምደባን ፍትሐዊና
ሚዛናዊ ማድረግ፤

5.3.2. የፖሊሲ አቅጣጫ


x በቴክኖሎጂ የታገዘ ፍትሐዊ እና ሚዛናዊ የተማሪ
ቅበላና ምደባ ስርዓት እንዲጎለብት ይደረጋል፡፡

5.3.3 ስትራቴጂዎች

1. የተለያዩ አማራጭ ዘዴዎችን (በገጽ-ለገጽና በበይነ-


መረብ) በመጠቀም የከፍተኛ ትምህርት የተማሪዎች
ቅበላና ምደባ የሚቀላጠፍበት የአሰራር ስርዓት
ይዘረጋል፡፡
2. በልማት ተጠቃሚ ካልሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች
(Disadvantaged Groups) ለሚመጡ ተማሪዎች፤
ለሴቶችና ልዩ ድጋፍ (የአካል ጉዳት፤ የአዕምሮ ዕድገት
ውስንነት …ወዘተ ላለባቸው) ለሚያስፈልጋቸው
ተማሪዎች አዎንታዊ ድጋፍ ይደረጋል፡፡
16 | የ ከ ፍ ተ ኛ ት ም ህ ር ት ተ ማ ሪ ዎ ች ቅ በ ላ እ ና ም ደ ባ ፖ ሊ ሲ
3. በተለያየ ምክንያት በአንድ ጊዜ ፍተና ያልተሳካላቸው
ተማሪዎች በዳግም ምዘና ቅበላና ምደባ (Delayed
Admission & Placement) የሚያገኙበት አሰራር
ይዘረጋል፡፡
4. እጅግ የላቀ ችሎታ ያላቸው ተማሪዎች የተፋጠነ ቅበላና
ምደባ (Accelerated Admission & Placement)
የሚያገኙበት ስርዓት ይዘረጋል፡፡
5. በተለያዩ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አማራጮች የሚታገዝ
የቅበላ እና ምደባ ስርዓትን የሚመራና የሚያስተዳድር
ዘመናዊ የመረጃ አስተዳደር ሥርዓት ይፈጠራል፡፡

5.4 ብዝሐነትን ታሳቢ ያደረገ የተማሪዎች ቅበላና ምደባ


5.4.1 ግብ
x ብዝሐነትን መሰረት ያደረገ የከፍተኛ ትምህርት
ተቋማት የተማሪዎች ቅበላ እና ምደባ ስርዓትን
ማስፈን፣

5.4.2 የፖሊሲ አቅጣጫ


x የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ቅበላ እና
ምደባ ብዝሐነትን መሰረት ያደረገ እንዲሆን
ይደረጋል፡፡

17 | የ ከ ፍ ተ ኛ ት ም ህ ር ት ተ ማ ሪ ዎ ች ቅ በ ላ እ ና ም ደ ባ ፖ ሊ ሲ
5.4.3 ስትራቴጂዎች
1. ህብረ-ብሔራዊነትን እና አንድነትን የሚያጠናክር
የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች የቅበላ እና ምደባ
ሥርዓት ይዘረጋል፡፡
2. የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ማንነታቸውን፣
ባህላቸውን እና አመለካከታቸውን በነጻነት
የሚገልጹበትና የሚያሳድጉበት ግልጽ፣ ፍትሃዊ እና
ሚዛናዊ የቅበላ እና ምደባ ሥርዓት እንዲጠናከር
ይደረጋል፡፡
3. ህብረ-ብሄራዊነትን የሚጻረሩ አሰራሮችን በዘላቂነት
ለማስወገድ የሚያስችሉ የህግ ማዕቀፎች ይዘጋጃሉ፡፡

5.5 የዓለም አቀፍ ተማሪዎች ቅበላ እና ምደባ


5.5.1 ግብ፣
x በሀገር ውስጥ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የውጭ
ሀገር ተማሪዎችን ተሳትፎ የሚያሳድግ የቅበላ እና
ምደባ አሰራር ማጠናከር፣

5.5.2 የፖሊሲ አቅጣጫ፣


x የውጭ ሀገር የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች በሀገር
ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎ የሚያበረታታ የቅበላና
ምደባ አሰራር በትብብርና ትስስር ይደራጃል፡፡

18 | የ ከ ፍ ተ ኛ ት ም ህ ር ት ተ ማ ሪ ዎ ች ቅ በ ላ እ ና ም ደ ባ ፖ ሊ ሲ
5.5.3 ስትራቴጂዎች
1. በዓለምአቀፍ ተማሪዎች ቅበላና ምደባ ሚና ያላቸው
የባለድርሻ አካላት በትብብር እንዲሰሩ የሚያስችል
የተቀናጀ የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል፡፡
2. ከተለያዩ የዓለም ክፍሎች ወደ ሀገር ውስጥ ገብተው
መማር ለሚፈልጉ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች
የሚስተናገዱበት የቅበላ እና ምደባ ሥርዓት ይዘረጋል፡፡
3. ዓለም-አቀፍ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች ቅበላና
ምደባን የሚያስተዳድር በበጀት የተደገፈ አደረጃጀት
ይፈጠራል፡፡
4. የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከሌሎች መሰል በውጪ
ሀገር ከሚገኙ ተቋማት ጋር በተማሪዎች ቅይይር
ተግባራት ላይ በጋራ የሚሰሩበት አሰራር ይመቻቻል፡፡
5. በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ቅርንጫፍ ካምፓሶችን ለከፈቱ
የሀገር ውስጥ ተቋማት ኢትዮጵያውያንና ትውልደ
ኢትዮጵያውያን የሚስተናገዱበት በበጀት የሚደገፍ
የቅበላ እና ምደባ ስርዓት ይዘረጋል፡፡

5.6 አመራር፤ አስተዳደርና የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ


5.6.1 ግብ

x የባለድርሻ አካላት ተሳትፎን በማሳደግና ጠንካራ


አመራርና አስተዳደር በመገንባት ውጤታማ የከፍተኛ
ትምህርት የምደባና ቅበላ ስርዓት መዘርጋት፤
19 | የ ከ ፍ ተ ኛ ት ም ህ ር ት ተ ማ ሪ ዎ ች ቅ በ ላ እ ና ም ደ ባ ፖ ሊ ሲ
5.6.2 የፖሊሲ አቅጣጫ

x የባለድርሻ አካላት ተሳትፎን በማሳደግና


የአመራር/አስተዳደር ስራዎችን በማስረጽ ውጤታማ
የምደባና የቅበላ ስርዓት ይዘረጋል፡፡

5.6.3 ስትራቴጂዎች

1. የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች የቅበላ እና ምደባ


ስርዓቱን ውጤታማ የሚያደርግ የተቋማት ቅንጅታዊ
አሰራር ይዘረጋል፡፡
2. በተማሪዎች ቅበላ እና ምደባ ስራ ላይ የሚሳተፉ አካላት
የሚለዩበት፤ የተሳትፎ ደረጃቸውም በየደረጃው
የሚሻሻልበት የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል፡፡
3. በተማሪዎች የቅበላ እና ምደባ የአሰራር ሂደት የሚሳተፉ
ተቋማትና የሚኖራቸው ሚና በመመሪያ ይወሰናል፡፡
4. አገራዊና ተቋማዊ የማስፈጸም አቅም ግንባታ ስትራቴጂ
ተቀርጾ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡
5. የተማሪዎች ቅበላና ምደባ ስርዓቱ ለተቋማት እስከሚሰጥ
ድረስ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ስራውን
በበላይነት ይመራል፤ ያስተባብራል፤ ያስፈጽማል፡፡

20 | የ ከ ፍ ተ ኛ ት ም ህ ር ት ተ ማ ሪ ዎ ች ቅ በ ላ እ ና ም ደ ባ ፖ ሊ ሲ
6. የተፈጻሚነት ወሰን

ይህ ፖሊሲ ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ የሆኑ


ሁሉም የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፣ የግል ከፍተኛ
ትምህርት ተቋማት እና በዚህ ፖሊሲ ኃላፊነት የተጣለባቸው
አስፈጻሚ አካላት፤ የመንግስት፣ የኮሙኒቲ እና የግል ትምህርት
ቤቶች ላይ ተፈጻሚ ይሆናል። እንዲሁም የመጀመሪያ ዲግሪ
ትምህርት ለመማር በሚያመለክቱ ተማሪዎች ላይ ተፈጻሚነት
ይኖረዋል።

7. ፖሊሲውን ስራ ላይ ስለማዋል

ይህ ፖሊሲ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ከጸደቀበት


መጋቢት 01 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡

21 | የ ከ ፍ ተ ኛ ት ም ህ ር ት ተ ማ ሪ ዎ ች ቅ በ ላ እ ና ም ደ ባ ፖ ሊ ሲ
ምስጋና
ይህ የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች የምደባና ቅበላ ፖሊሲ በከፍተኛ
ትምህርት ስትራቴጂ ማዕከል አስተባባሪነት፣ በክቡር ዶ/ር ሳሙኤል
ኡርቃቶ፣ በክቡር ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ፣ በክቡር ዶ/ር ሳሙኤል
ክፍሌ በሳል አመራር እና በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከፍተኛ
ባለሙያዎች ቴክኒካዊ እገዛ የተዘጋጀ ነው፡፡ የከፍተኛ ትምህርት
ስትራቴጂ ማዕከል ባለሙያዎች በተለይም አቶ ሰይድ መሃመድ፣ አቶ
ሰራዊት ሀንዲሶ እና ሌሎችም ተመራማሪዎች ከፍተኛ ሙያዊ
አስተዋፅኦ ነበራቸው፡፡ ዶ/ር ተስፋዬ ሙህዬ፣ ዶ/ር አባተ ጌታሁን፣
ዶ/ር ጃይሉ ኡመር፣ እና አቶ ወንድወሰን ታምራት ለሰነዱ መሻሻል
ትልቅ ግብዓት ሰጥተዋል፡፡

ሰነዱን ከማሳተም ባለፈ የሽፋን ገፅ ዲዛይን በማሳመር ስራ ላይ


በትጋት ለተሳተፉት፣ በአዲስ አበባ እና በባህር ዳር በተደረጉት
ተከታታይ የምክክር መድረኮች ላይ ተገኘተው ፖሊሲውን ለማበልፀግ
ሀሳብ ለሰጡን ለሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒሰቴር ማናጅመንት
በሙሉ ማዕከሉ ምስጋናውን ያቀርባል፡፡ ሰነዱን ለማሻሻል በተደረጉት
የምክክር መድረኮች ተገኝተው ለገመገሙት ባለሙያዎች፣በተለያዩ
ስራዎች ውስጥ ለተሳተፉ የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና አግባብነት
ኤጀንሲ፣ አገር አቀፍ ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ፣ ለክልል ትምህርት
ቢሮዎች፣ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች ለሁሉም የዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ
አመራሮች የላቀ ምስጋና እናቀርባለን፡፡

ሀብታሙ ተካ (ዶ/ር)
የከፍተኛ ትምህርት ስትራቴጂ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር

22 | የ ከ ፍ ተ ኛ ት ም ህ ር ት ተ ማ ሪ ዎ ች ቅ በ ላ እ ና ም ደ ባ ፖ ሊ ሲ

You might also like