Professional Documents
Culture Documents
Exit Exam Implementation Plan
Exit Exam Implementation Plan
ታህሳስ/2015 ዓ/ም
አሶሳ፣ኢትዮጵያ
ማዉጫ
1
1. መግቢያ …………………………………………………………………………………3
1. መግቢያ
በከፍፈተኛ ትምህርት ተቋማት ብቃትና ጥራት ያለዉ የሰዉ ኃይል ማፍራት ለአንድ ሀገር ኢኮኖሚያዊና ሁለተናዊ እድገት
ወሳኑን ድርሻ ይወስዳል፡፡ በተለይም አካባቢያዊ፤ሀገራዊና ዓለማቀፋዊ የሰዉ ሀይል ፍላጎትን ማዕከል ያደረገ ሥርዓተ-ትምህርት
2
ቀረጻ ተግባራዊ ማድረግ ወቅቱ የሚጠይቀዉ ዘመን ተሻጋሪ አሰራር ሁኗል፡፡ ሥርዓተ ትምህርቱን ከመቅረጽ ባለፈ ተማሪዎችን
በአግባቡና ዘመኑ የሚጠይቀዉን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ማስተማርና ዉጤታማ ማድረግን ይጠይቃል፡፡ ስለሆነም በስርዓተ
ትምህርቱ ዉስጥ የተመላከተዉን የምሩቃን ፕሮፋይል ምሩቃን እንዲጨብጡ ት በማድረግ ለገበያዉ ማቅረብ ያስፈልጋል፡፡
በሀገራችን የከፍተኛ ትምህርት ታሪክ ባለፉት 20 ዓመታት የትምህርት ጥራት ጉዳይ ትልቅ አጀንዳ ሆኖ ቆይቷል፡፡ ለትምህርት
ተደራሽነት የተሰጠዉን ትኩረት ያህል ለጥራቱም የገዘፈ ትኩረት ባለመሰጠቱ ምክንያት ምሩቃን የሚፈለገዉን ብቃት ያሟሉ
አለመሆናቸዉ ከቀጣሪ መ/ቤቶች ሳይቀር በየጊዜዉ ይነሳል፡፡
የምሩቃን በቃትን ለመመዘን ደግሞ ተቋማት በራሳቸዉ የሚሰጡት ብቃትን የማረጋገጥ ተግባር እንደተጠበቀ ሁኖ በአገር
አቀፍ ደረጃ ደግሞ ምሩቃን በስርዓተ ትምህርቱ ላይ የተቀመጠዉን ፕሮፋይል ማሟላቸዉን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡
መንግስት የመዉጫ ፈተናዉን አስፈላጊነት በመገንዘብ በህግ ትምህርት እና በተለያዩ የጤና ዘርፎች የሙጫ ፈተናን ተግባራዊ
ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ የምሩቃን ብቃትን በመመዘን ገበያዉ የሚያስፈልገዉን የሰዉ ሀይል ማቅረቡ እንደተጠበቀ ሁኖ
የተመራቂዎች ብቃት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ መጥቷል፡፡ ተማረዎችም በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሚኖራቸዉ ቆይታ
ፍሬያማ አድርጓቸዋል፡፡ ስለሆነም ይህን ተሞክሮ ከግንዛቤ በማስገባት መንግስት ከ 2015 ዓ/ም ጀምሮ የመዉጫ ፈተናን
በሁሉም የትምህርት መስኮች(ፕሮግራሞች) ተግራዊ ለማድረግ በተላላፈዉ ዉሳኔ መሰረት የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ የመዉጫ
ፈተናን ተግባራዊ ለማድረግ የትግበራ የድርጊት መረሐ ግብር አዘጋጅቷል፡፡
የመዉጫ ፈተናዉን ከ 2015 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ ለማድረግ መንግስት በወሰነዉ መሰረት ከወዲሁ በርካታ የቅድመ
ዝግጅት ሥራዎች መከናወን ይኖርባቸዋል፡፡ ስለሆነም በ 2015 ዓ/ም መጨረሻ ላይ ለሚሰጠዉ ፈተና የሚመለከታቸዉ
የዩኒቨርሲቲዉ አካላት ሚናቸዉን በመገንዘብ እንዲሁም ከወዲሁ የቅድመ የዝግጅት ሥራዎችን በመለየት የራሳቸዉን
የድርጊት መርሐ-ግብር አዘጋጅተዉ እንዲገብሩ ማድረግ አስፈላጊ ነዉ፡፡ በመሆኑም ይህ የመዉጫ ፈተና ዝግጅት ምዕራፍ
የድርጊት መርሐ-ግብር የሁሉንም ተሳትፎ በሚያረጋግጥ መልኩ ተዘጋጅቷል፡፡ ስለሆም በፈተናዉ ደርሻ ያላቸዉ አካዳሚክ
ዳይሬክቶሮች፣የተቋማዊ ጥራት ዳይሬከተር፣የኮሌጅ/ትም/ቤት ዲኖች፣አስተባባሪዎች፣ትምህርት ክፍል
ኃላፊዎች፣መምህራን፣ላብራቶሪ ቴክኒሽያን፣የተማሪዎች ህረት እና ተፈታኞች ሚናቸዉን በመለየት ለፈተናዉ
ዉጤታማነት ከወዲሁ አቅደዉ ወደ ተግባር ለማስገባት የድርጊት መርሐ-ግብሩ በዩኒቨርሲዉ በኩል ተዘጋጅቷል፡፡
በ 2015 ዓ/ም መጨረሻ ላይ የሚሰጠዉን የመዉጫ ፈተናን በተያዘለት ጊዜ ለመስጠት እንዲቻል የቅድመ
ዝግጅት ስራዎችን በዕድ መምራት ያስፈልጋል፡፡ ስለሆነም ፈተናዉ ግንቦትና ሰኔ ወራት ዉስጥ እንደሚሰጥ
3
ታሳቢ ተደርጎ ከታህሳስ 2015 ዓ/ም እስከ ሰኔ 30/2015 ዓ/ም ድረስ የሚከናወኑ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች
ተለይተዉ ታቅደዋል፡፡