KG Checklist

You might also like

You are on page 1of 7

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር

የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን

የትምህርትና ስልጠና ጥራት ማረጋገጥና ምርምር ዳይሬክቶሬት

በኢንስፔክሽን ግብረ-መልስ መሰረት የተከናወኑ የማሻሻያ ስራዎች ላይ

ክትትልና ቁጥጥር ለማድረግና ተጠያቂነትን ለማስፈን የተዘጋጀ

የቅድመ አንደኛ ደረጃ ት/ቤቶች ቼክሊስት

ጥቅምት 2016 ዓ.ም


አዲስ አበባ
ዓላማው፡-

የክትትልና ቁጥጥር ኢንስፔክሽን ዋነኛው ዓላማው የትምህርት ተቋማት የኢንስፔክሽን አገልግሎት ባገኙበት ቀጣይ
አመታት ውስጥ የሚተገበር እንደመሆኑ ት/ቤቶች ከስታንዳርድ ኢንስፔክሽን ትግበራ በተሰጣቸው ግብረመልስ
መሰረት በትምህርት ተቋማቸው ውስጥ በኢንስፔክሽን በእጥረት የተለዩት ችግሮች ላይ ትኩረት በማድረግ
የተከናወኑትን ተግባራትና የታየውን ለውጥ ለመፈተሸና ለመቆጣጠር እንዲሁም ተጠያቂነትን ለማስፈን ነው፡፡

በዚሁ መሰረት ት/ቤቶች ባለፈው አመት ከተሰራላቸው የስታንዳርድ ኢንስፔክሽን ግብረመልስ በመነሳት
በትምህርት ተቋሙ የታየውን ለውጥ ለመቆጣጠር ያመች ዘንድ ይህ ቼክሊስት ተዘጋጅቷል፡፡

የትምህርት ቤቱ አጠቃላይ መረጃ


1. የትም/ቤቱ ስም፡- የቤት ቁጥር፡- መለያ ቁጥር .
የትም/ቤቱ ዓይነት፡- እርከን፡- የመማሪያ ክፍል ብዛት .

Page | 1
ት/ቤቱ የሚገኝበት ቦታ፡- ክፍለ ከተማ፡ ወረዳ፡ ልዩ ቦታ .
2. የትም/ቤቱ ዋና ር/መምህር/ት ስም፡ ጾታ፡ የትምህርት ደረጃ፡
የተመረቀበት የት/ዓይነት
3. የመምህራን ብዛት፡- ወንድ፡ ሴት፡ ድምር፡
4. የመምህራን ብዛት በትምህርት ደረጃ፡-
 ከዲፕሎማ በታች፡ ወ ሴ ድ
 ዲፕሎማ፡- ወ ሴ ድ
 የመጀ/ዲግሪ፡- ወ ሴ ድ
 ማስተርስና በላይ፡- ወ ሴ ድ
7. የተማሪዎች ብዛት፡- ወንድ ሴት ድምር
8. የት/ቤቱ አድራሻ፡- ስልክ፡ ተንቀሳቃሽ ስልክ(የር/መር/ርት)
ፋክስ፡ ኢሜይል፡ የት/ቤቱ ድረ ገጽ፡
9. የክትትል እና ቀጥጥር ኢንስፔክሽን የተካሄደበት፡- ከቀን / /አስከ / / 2016 ዓ.ም

ክፍል 1፡-
1. የመደበኛው ት/ቤት አመራሮች የኢንስፔክሽንን ግብረ መልስ መሰረት አድርገው የታዩ ክፍተቶችን ለመቅረፍ በተጨባጭ
የሰሯቸዉ ስራዎች ስለመኖራቸዉ (ለመንግስት ት/ቤቶች)፡-

2. የወረዳ ት/ጽ/ቤት አመራሮችና ባለሙያዎች የኢንስፔክሽንን ግብረ መልስ መሰረት አድርገው የታዩ ክፍተቶችን ለመቅረፍ
በተጨባጭ የሰሯቸዉ ስራዎች ስለመኖራቸዉ

3. ለት/ቤቱ በተሰጠዉ ግብረ መልስ መሰረት አመራሩ ለባለድርሻ አካላት በወቅቱ በማቅረብ የጋራ ግንዛቤ ስለመፍጠሩ እና
የተገኘ ተጨባጭ ውጤት

4. የት/ቤቱ የጉድኝት ማእከል ሱፐርቫይዘር በክፍተት የተሰጡ የኢንስፔክሽን ግብረ መልሶችን መሰረት በማድረግ ችግሮችን
እንደ ክብደታቸዉ በቅደም ተከተል በመለየት ለበጀት ዓመቱ ባቀደዉ እቅድ ዉስጥ አካቶ ለት/ቤቱ ክትትል እና ድጋፍ
ስለማድረጉ

Page | 2
5. ት/ቤቱ የዓመቱን የዉስጥ ኢንስፔክሽን በተመለከተ በኢንስፔክሽን መመሪያው መሰረት ተገቢነት ያላቸውን
ባለድርሻ አካላት ያካተተ ኮሚቴ በማደራጀትና አሰራርን በመከተል መረጃዎችን በማሰባሰብና በደረጃ
በመፈረጅ መረጃውን አደራጅቶ ስለመያዙ

6. ት/ቤቱ የኢንስፔክሽን መረጃዎችና ግብረ መልሶችን አደራጅቶ ስለመያዙ (መመሪያዎች፣ ቼክሊስቶች፣


ስታንዳርዶች፣ ደብዳቤዎች፣ የደረጃ ፍረጃ ሰርቲፊኬት)

7. የትምህርት ጥራት ማረጋገጥ ባለሙያዎች የሰጡት የስታንዳርድ ኢንሰፔክሽን ግብረ መልስ የት/ቤቱ ችግር እንዲፈታ
አስተዋጽኦ ስለማድረጉ፡-

ክፍል ሁለት

8. በግብዓት
8.1. ትምህርት ቤቱ ግብረ መልስ ከተሰጠዉ በኋላ የት/ቤቱን ምድረ ግቢ እና ህንጻዎች ምቹ እና ሳቢ ለማድረግ የተሰሩ
ስራዎች (ስታ 1 እና 4)

8.2. ትምህርት ቤቱ ግብረ መልስ ከተሰጠዉ በኋላ የልዩ ልዩ አገልግሎት መስጫ ክፍሎች (ስታ 1 እና 4)
 ስታንዳርድ ለማስጠበቅ የተሰሩ ስራዎች

 ያልነበሩና በአዲስ ግንባታ በመገንባት የተሟሉ

8.3. ትምህርት ቤቱ ግብረ መልስ ከተሰጠዉ በኋላ በስታንዳርዱ መሰረት የተሟላ የሰው ኃይል (ስታ 2)
 መምህራን (ከትምህርት ዝግጅት አንጻር)

 የአስተዳደር ሰራተኞች (ርዕሰ መምህራን ጨምሮ)

8.4. የት/ቤቱ ዓመታዊ እቅድ ሲዘጋጅ የኢንስፔክሽን ግብረ መልስን ያካተተ እና የቅድሚያ ትኩረት ነጥቦችን የለየ ስለመሆኑ (ስታ
7)

Page | 3
9. በሂደት
9.1 በዉጭ ኢንስፔክሽን በተሰጠዉ ግብረ-መልስ መሰረት ለመምህራን ተግባራዊ ጥናትና ምርምር እንዲያከናውኑ የቅድመ
ዝግጅት ስራዎች ስለ መሰራታቸዉ (ስልጠና፣ የጥናትና ምርምር ማንዋል፣ በት/ቤቱ ዕቅድ መካተቱ ፣ የጥናት ርዕሶች
ስለመለየታቸዉና መምህራን እንዲያዉቁት ስለመደረጉ፣ የተሰሩ ጥናትና ምርምሮች መኖራቸውና ተግባራዊ በመደረጋቸው
የታየ ለውጥ (ስታ. 12)

9.2. በት/ቤቱ የልዩ ፍላጎት ተማሪዎች ተለይተው ድጋፍ ስለመደረጉና ያሳዩት ለዉጥ ስለመገምገሙ (ስታ 14)

9.3. የትምህርት ቤቱ አመራር፣ መምህራንና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች በልማት ሠራዊት ተደራጅተዉ በቡድን ስሜት እየሰሩ
ስለመሆኑ እና በአደረጃጀቶቹ የተከናወኑ ተግባራትና የተገኙ ተጨባጭ ውጤት (ሰታ 15)
 በመምህራን አደረጃጀት

 በሰራተኞች አደረጃጀት

9.4. የትምህርት ቤቱ አመራር በስራ ክፍሎች የተዘጋጁ ልዩ ልዩ እቅዶች በአግባቡ መታቀዳቸውንና መከናወናቸውን
ስለመከታተሉና ላጋጠሙ ችግሮች መፍትሄ እየሰጠ መሄዱ (ስታ 15)

9.5. ት/ቤቱ ግብረ መልስ ከደረሰዉ በኋላ መምህራንን የማስተማር ክህሎት ለማሳደግ የወሰዳቸዉ እርምጃዎች ስለመኖራቸዉ
እና የተከናወኑ ተጨባጭ ተግባራት (ስታ 16 እና 17)

9.6. ወላጆች በወላጅ መምህር ህብረት (ወመህ) ሲደራጁ በመመሪያዉ መሰረት መሆኑና ንቁ ተሳትፎ ስለማድረጋቸው
(በት/ት አመራርና አስተዳደር ዉሳኔዎች ላይ፣ በመማር-ማስተማር ሂደት ላይ፣ በት/ት ሀብት አሰባሰብና
አጠቃቀም፣ በወላጆች የምክክር መድረክ ላይ) (ስታ 19)
 በወመህ አደረጃጀት የተከናወኑ ተግባራት

Page | 4
 በአጠቃላይ ወላጆች የተከናወኑ ተግባራት

10. በውጤት፡
10.1. ትምህርት ቤቱ ከወላጆች፣ ከአካባቢው ማህበረሰብና አጋር ድርጅቶች ጋር ጠንካራ ግንኙነት በመፍጠር በዕቅድ
የተደገፈ በገንዘብ፣ በዓይነትና በጉልበት ድጋፍ ስለማግኘቱ (ለመንግስት ት/ቤቶች) (ስታ 23)

ክፍል 3፡-

በውጭ ኢንስፔክሽን ደረጃ/ውሳኔ አሰጣጥ በተሰጠው ግብረመልስ መሰረት፡-


 በትምህርት ቤቱ የታዩ መሻሻሎች፡-

 መሻሻል ያልታየባቸው ጉዳዮች

Page | 5
 የኢንስፔክተሮች አጠቃላይ አስተያየት

 የት/ቤቱ ር/መምህር አስተያየት

የኢንስፔክተሮች ስም፡ 1 ፊርማ ቀን


2 ፊርማ ቀን
3 ፊርማ ቀን

የትምህርት ቤቱ ር/መምህር/ርት
ስም
ፊርማ
ቀን

የት/ቤቱ ማህተም

Page | 6

You might also like