You are on page 1of 35

በሐረሪ ክልል ትምህርት ቢሮ የትምህርት ቤት

መሻሻል ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት

የትምህርት ቤቶችን መሠረተ-ልማት


ለማሻሻል
ለትምህርት ቤት አመራሮችና የተማሪ
ወላጆች ማህበር የተዘጋጀ
ንቅናቄ ሰነድ
ግንቦት 2015 ዓ.ም
መግቢያ

 በዘርፉ የተደረጉ ጥናቶች የትምህርት ጥራት አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን አመላክተዋል፡፡


የተለዩት የትምህርት ጥራት ችግሮች ውስጥ
 የሥርዓተ-ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ከምርትና ከተግባር ጋር የተያያዘ አለመሆን፣
 የመምህራን ብቃትና ተነሳሽነት ችግር፣
 ትምህርት ቤቶች ለመማር ማስተማር ምቹ አለመሆናቸው በዋናነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡

 ባለፉት አመታት የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል የትምህርት ቤት ደረጃ መሻሻያ ስትራቴጂና አጋርነትና
ትብብር ሞዴል ተዘጋጅቶ ወደ ስራ ተገብቷል።

 ትምህርት ቤቶች ለመማር ማስተማር ምቹ አለመሆን የብዙ አካላትን ተሣትፎ የሚጠይቅ ነው፡፡

 እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ክልል አብዛኛው ትምህርት ቤቶች ለመማር ማስተማሩ አስፈላጊ የሆነ መሠረተ-
ልማት የሌላቸው በመሆኑ ተማሪዎች በተጓደለ የትምህርት ከባቢ ውስጥ እንዲማሩ ተገደዋል፡፡

 ይህ ደግሞ በትምህርት ጥራት ላይ ያስከተለው አሉታዊ ተጽእኖ በየደረጃው ያሉ ተማሪዎች የሚጠበቅባቸውን


እውቀት፣ ክህሎትና የባህሪ ለውጥ ማምጣት አለማቻላቸው በግልጽ ታይቷል፡፡

 ይህን ችግር ለማሻሻል እና ዘላቂ መፍትሔ ለማበጀት የማበረሰብና የልዩ ልዩ የትምህርት ባለድርሻ አካላት
ቀጥተኛ ተሣትፎን ያማከለ ንቅናቄ ማድረግ እጅግ ወሳኝ ሆኖ ተገኝቷል፡፡
 ስለሆነም በሚቀጥሉት ሶስት ወራት ከሰኔ 1/2015 እስከ ነሐሴ 30/2015 ዓ.ም
በንቅናቄው የሚሳተፉ አካላት እነማን ናቸው
 ንቅናቄው በየደረጃው ያለውን የአካባቢ ማህበረሰብ፣
 ከየአካባቢው ተምረው የወጡ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሚኖሩ
ተወላጆችን፣
 ባለሀብቶችን፣
 ታዋቂ ግለሰቦችን፣
 ማህበራትን፣
 የግልና የመንግሥት ተቋማትን፣
 የልማት አጋሮችን፣
 በየደረጃ ያሉ የመንግሥት አካላትን፣ ወዘተ. ንቁ ተሳታፊ ማድረግ
የሚያስችል የትምህርት ቤቶችን መሠረተ-ልማት ማሻሻል ክልላዊ ንቅናቄ
ዘላቂነት ባለው መልኩ የሚቀጥልበት ሥርአት መፍጠር አስፈልጓል፡፡
 በመሆኑም ንቅናቄው በየደረጃው በውጤታማነት መምራትና መፈፀም
እንዲቻል ይህ የንቅናቄ ሰነድ ተዘጋጅቷል፡፡
የክልላዊ ንቅናቄው ዓላማ

 በየደረጃው ባለው ማህበረሰብና ልዩ ልዩ አካላት ተሳትፎ የትምህርት ቤቶችን


መሠረተ-ልማት
 ንጹሕ ውሃ፣
 መፀዳጃ ክፍሎች፣
 በቂ መማሪያ ክፍሎች፣
 ወንበር፣ ጠረጴዛ፤
 የስፖርት ሜዳ፣
 መጻሕፍት፣
 የኤሌትሪክ አገልግሎት፣
 ቤተ-መጻሕፍት፣
 ቤተ-ሙከራ፣ ወዘተ.) ለማሻሻል የአሠራር ሥርአት መዘርጋት
 ማህበረሰቡ በትምህርት ሥርአት ውስጥ በመሠረተ-ልማት መሻሻል ሳይወሰን
የመማር ማስተማሩን ሂደት በዘላቂነት በባለቤትነት እንዲደግፍ ለማስቻል ነው፡፡
የሚጠበቅ ውጤት

 የማህበረሰቡ ድጋፍና ልዩ ልዩ አካላት የትምህርት ተሣትፎና ድጋፍ


ያረጋገጠ የተጠናከረ የአሠራር ሥርአት፤
 በዘላቂነት የቀጠለና የተረጋገጠ የማህበረሰብና የልዩ ልዩ አካላት

የትምህርት ድጋፍና ተሣትፎ፤


 በማህበረሰብና በልዩ ልዩ አካላት አስተዋጽኦና ጥረት እያደጉ የመጡ

መሠረተ-ልማቶች
 (ንጹሕ ውሃ፣ መፀዳጃ ክፍሎች፣ መማሪያ ክፍሎች፣ ወንበር፣

ጠረጴዛ፤ የስፖርት ሜዳ፣ መጻሕፍት፣ የኤሌትሪክ አገልግሎት፣


ቤተ-መጻሕፍት፣ ቤተ-ሙከራ፣ ወዘተ.) ያሻሻሉ ትምህርት ቤቶች
ብዛት፤
4. የሐረሪ ክልል ትምህርት ቤቶች ያሉበት ነባራዊ ሁኔታ

በክልላችን ያሉን የመንግስት ትምህርት ቤቶች


 64 ኦ ክፍሎች
 69 አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች
 10 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች

 በ2013-2015 የትምህርት ዘመን በተካሄደው ኢንስፔክሽን


ከታዩ 80 የመጀመርያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መካከል
 14(17%) ፤ ደረጃ 1 ከስታንደርድ በታች
 48(63%) ደረጃ 2 በመሻሻል ላይ ያለ
 18(23%) ደረጃ 3 ወይንም ስታንዳርድ ያሟሉ ናቸው።
ሀረሪ ክልል 1ኛ ደረጃ ከግብአት አንጻር
ከግብዓት ዝቅተኛ አፈጻጸም
 በክልል ደረጃ የመጀመርያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አማካይ የግብዓት አፈጻጸም ከመቶ ሲሰላ 60%
ነው።
 ከግብአት ስታንዳርዶች መካከል እንደ ክልል በዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ስታንዳርዶች መካከል
 ስታንዳርድ1 (59%) ሲሆን
 ስታንዳርድ2(59%)
ስታንዳርድ 3 (54%) ናቸው።
ስታንዳርድ 1.ትምህርት ቤቱ ለደረጃው በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት የመማሪያ እና
የመገልገያ ህንፃዎች፣ ፋሲሊቲዎች እና የማስተማሪያ መርጃ መሳሪያዎች (Learning
Resources) አሟልቷል፡፡
 ትምህርት ቤቱ በስታንዳርዱ መሠረት በቤተ-መጽሃፍት፣ በቤተ-ሙከራ፣ በትምህርት

ማበልጸጊያ ማዕከል እና በስፖርት ሜዳ መሟላት የሚገባቸው ፋሲሊቲዎች


በተመለከተ፣
 የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ፣ አገራዊና ክልላዊ ፕሮግራሞችና ማእቀፎች እንዲሁም

ተያያዥነት ያላቸው መመሪያዎችና መተዳደሪያ ደንብ ተሟልተው ስለመገኘታቸው፣


4.1. መሰረተ ልማት

 የትምህርት ቤት መሰረተ ልማት ለመማር ማስተማር ስራው ዋናውና


ቁልፉ ጉዳይ መሆኑ ሃቅ ነው።
 በትምህርት ቤት ውስጥ የሚካሄደውን የተማሪዎች መማር ከማሳለጥ

ባሻገር ለትምህርት ጥራት መሻሻል ከፍተኛውን ሚና ይጫወታል።


 የትምህርት ቤት መሰረተ ልማት ስንል
 ለመማር ማስተማር ስራ አገልግሎት የሚውሉ ህንፃዎች፣
 የስፖርት ሜዳዎች፣
 የውስጥ ለውስጥ መንገዶች፣
 የትምህርት ክፍሎችና የተለያዩ ኮሚቴዎች ቢሮዎች፣
 የመፀዳጃ ቤቶች፣
 የኤሌክትሪክ መስመሮች እና
 የውሃ አቅርቦቶች የመሳሰሉት ናቸው።
የቀጠለ…
 የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል የትምህርት ቤት መሰረተ ልማቶች
ከፍተኛ ፋይዳ ያላቸው መሆኑ ግልጽ ነው።
 የትምህርት ቤቶችን ያሏቸው መሰረተ ልማቶች ከተቀመጠው

ስታንዳርድ አንፃር ሲታዩ በጣም በዝቅተኛ ደረጃ የሚታዩ ናቸው።


 ማሳያ የአጠቃላይ ትምህርት ኢንስፔክሽን አመታዊ ሪፖርትና

የትምህርት መረጃ አመታዊ መጽሄት ማየት በቂ ይሆናል።


 የትምህርት ቤቶች የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን ስንመለከት
 ልዩ የትምህርት ፍላጎት ያላቸው ዜጎች ወደ ትምህርት ቤት

እንዲመጡ የማይጋብዙ ናቸው፤


 በችግሩ ውስጥም ሆነው ለመማር ወደ ትምህርት ቤት የመጡትን

ጥራት ያለው አገልግሎት እንዳያገኙ የሚገድቡ መሆናቸውን


መረጃዎች ያሳያሉ።
የቀጠለ….
 የንፁህ መጠጥ ውሃ እና መጸዳጃ ቤት አገልግሎት በትምህርት
ቤቶች መኖር ፋይዳው የተማሪዎችን የትምህርት አቀባበል
ማሳደግ ብቻ ሳይሆን፤
 ቁጥራቸው ቀላል የማይባሉ ተማሪዎች እንዳያቋርጡ
ከማድረግ አንፃር አዎንታዊ ተጽእኖ እንዳለው በርካታ ጥናቶች
ያሳያሉ፡፡
 ትምህርት ቤቶች የንጹህ መጠጥ ውሃና የመፀዳጃ ቤት

አገልግሎት እንዲያገኙ ባለፉት አመታት በርካታ ስራዎች


የተሰሩ ቢሆንም
 አሁንም አገልግሎቱን በጥራትና በስታንዳርዱ መሰረት
ከመስጠት አንፃር ያልተሻገርነው ችግር ነው።
የቀጠለ….

 የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት በአንጻራዊነት መሻሻሎች የታዩ


ቢሆንም እንደ
 44% አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች
 95% ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ብቻ ናቸው የንጹህ

መጠጥ ውሃ አገልግሎት አላቸው።


የመፀዳጃ ቤት አገልግሎትን ስንመለከት
 95 % አንደኛና መካከለኛ ደረጃ እና
 100% ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የመፀዳጃ አገልግሎት

የሚሰጡ መሆኑን መረጃው ያሳያል።


 በቁጥር ደረጃ ትምህርት ቤቶች አሉን ያሉት የውሃ እና የመጸዳጃ

ቤት አገልግሎት ቀላል የማይባል ቢሆንም ከጥራትና ከተማሪዎች


ቁጥር አንፃር ሲታይ በቂ እንዳልሆኑ ያሳያል።
 ስለሆነም በቀጣይ ሁሉም ትምህርት ቤቶች በስታንዳርዱ መሰረት

በጾታ የተለየ የመፀዳጃ ቤትና የውሃ አገልግሎት ተጠቃሚ እንዲሆኑ


በትኩረት መስራት ያስፈልጋል።
የኤሌክትሪክ አገልግሎት በተመለከተ

 ሁሉም ትምህርት ቤቶች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን


እንዳለባቸው በትምህርት ቤት ስታንዳርድ ላይ የተቀመጠ ቢሆንም
 አሁን ባለው ሁኔታ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆን የቻሉት
 **% አንደኛ እና መካከለኛ
 100% ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ናቸው።
 ይህ የሚያመላክተው በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች
 በቴክኖሎጂ የተደገፈ የ21ኛው ክፍለ ዘመን የትምህርት ክህሎትን
ለመስጠት፤
 ቴክኖሎጂ ተኮር የሆኑ የትምህርት ዓይቶች (አይ.ቲ) በአግባቡ ለመስጠት
 በሬዲዮ የተደገፈ ትምህርት ለማቅረብ ተግዳሮት ይሆናል፤
 ስለሆነም ትምህርት ቤቶች ደረጃቸውን ያልጠበቁና በስታንዳርዱ
መሰረት ያልተሟሉ መሰረተ ልማቶች ሳይኖራቸው ከተማሪዎች የተሻለ
ውጤትና ስነምግባር መጠበቅ ተገቢም አይደለም፡፡
የመማሪያ ክፍሎች ሁኔታ
 የመማሪያ ክፍሎችና ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ቢሮዎችን ስናይ አብዛኛዎቹ
ትምህርት ቤቶች በስታንዳርዱ መሰረት የተገነቡ የመማሪያና አገልግሎት መስጫ
ክፍሎች የሌሏቸው መሆኑን የኢንስፔክሽን ሪፖርት ያመላክታል።
 አብዛኛዎቹ የመማሪያ ክፍሎች ለመማር ማስተማር ምቹ ያልሆኑ ተማሪዎችን
ለመማር የማያነቃቁ መሆናቸውን መረጃዎች ያሳያሉ።
 በተመሳሳይ መልኩ ከቁጥር አንፃርም ቢሆን በቂ እንዳልሆኑ እና በተለይ ደግሞ
የአገልግሎት መስጫ ከፍሎች ከፍተኛ እጥረት ያለባቸው መሆኑን መረጃዎች
ያመላክታሉ።
 የመማሪያ ክፍሎች በቂ ወንበርና ጠረጴዛ ባለመኖሩ በአንድ ኮምባይድ ዴስክ ላይ
በአንድ አንድ ትምህርት ቤቶች እስከ ስድስት ተማሪዎች የሚቀመጡበት
አጋጣሚ ሁሉ መኖሩ የመማር ማስተማር ስራውን በእጅጉ ጎድቶታል።
 ይህ ደግሞ ተማሪዎች በክፍል ውስጥ የሚማሩትን ትምህርት ኖት ለመውሰድ፣
የቤት ስራዎችን ለመስራትና የክፍል ምዘናዎችን በቀላሉ ለማድረግ አስቸጋሪ
በመሆኑ የመማር ማስተማር ስራውን በእጅጉ ጎድቶታል።
 በቀጣይ የተማሪዎችን ወንበር እና ጠረጰዛ በአጭር ጊዜ ለማሟላት የርብርብ
ማዕከል ሊሆን ይገባል።
ስፖርት ሜዳ

 ስፖርት ለትምህርት ጥራቱ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑ ይታወቃል።


 ነገር ግን አብዛኛዎቹ ትምህርት ቤቶች የስፖርት ሜዳ የሌላቸው በመሆኑ ልጆችን ከዚህ
ተጠቃሚ መሆን አልቻሉም።
 ይህም የሆነው ትምህርት ቤቶች ሲስፋፉ ስታንዳርዱን መሰረት ባላደረገ መልኩ በመሆኑ
ነው።
 በቀጣይ የትምህርት ቤቶችን ስታንዳርድ ማስጠበቅ ላይ ልዩ ትኩረት ሊደረግ ይገባል።
 
 በአጠቃላይ የትምህርት ቤት መሰረተ ልማት ለትምህርት ያለውን ፋይዳ ተረድቶ
 ሁሉንም የትምህርት ባለድርሻ አካላት በማሳተፍ መፍታት ካልተቻለ ትምህርት ቤቶች
የተማሪዎች መማሪያ ማዕክል ከመሆን ይልቅ መዋያ ብቻ ይሆናሉ።

 ይህ ደግሞ የትምህርት ስርዓቱን ምን ያህል እንደጎዳይ የ2014 ዓ.ም የተማሪዎችን


የ12ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ማየት ብቻ በቂ ነው።

 ስለሆነም የተለያዩ አማራጮችን በመፈተሽ የትምህርት ቤት መሰረተ ልማቶችን


በስታንዳርዱ መሰረት ለማሟላት በቀጣይ የርብርብ ማዕከል መሆን ይኖርበታል።
4.2. የትምህርት ፋሲሊቲና ግብዓቶች በተመለከተ

 የትምህርት ቤት መሻሻል ዋና አላማው ትምህርት ቤቶች


ከአራቱ አበይት ጉዳዮች አንፃር በመገምገም ችግሮችን በቅደም
ተከተል በማስቀመጥ ትምህርት ቤቶች ያላባቸውን ክፍተቶች
በመፍታት የተማሪዎችን ውጤትና ስነምግባር ማሻሻል ነው።
 እስካሁን ባለው ጥረት የትምህርት ቤቶችን ቁጥር ከማሳደግ

አንፃር የሚያበረታታ ስራ ተሰርቷል።


 የትምህርት ቤት ቁጥር መጨመር በራሱ የትምህርት ጥራትን

ለማሻሻል ያለው አስተዋጽኦ እንደተጠበቀ ሆኖ ትምህርት


ቤቶቹ ስታንዳርዱን ጠብቀው እንዲመሰረቱ ከማድረግ አንፃር
ሰፊ ክፍተት ያለ በመሆኑ ከግብዓት አንፃር መሰረታዊ የሚባል
ክፍተት አለባቸው።
ከመማር ማስተማሪያ መፃህፍት
 ከመማር ማስተማሪያ መፃህፍት አንፃር ምንም እንኳን የተማሪ
መፃህፍት ጥምርታ አንድ ለአንድ መሆን እንዳለበት ይታመናል፤
 የተማሪ መፃህፍት አንድ ለአንድ እንዳልሆነና የተማሪ መፃህፍት

ጥምርታ ከት/ቤት ት/ቤት የሚለያይ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ።


 ይህም በመፃሕፍት ህትመትና ስርጭት፤ ማነጀሜንቱ የሚታዩን

ችግር መፍታት ያስፈልጋል።


 ይህ ደግሞ አሁን የትምህርት ጥራትን ለማምጣት በሚደረገው

ጥረት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ያሳድራል።


 ስለሆነም በቀጣይ የተማሪ መፃህፍትን ለማሟላት አንዱ የርብርብ

ማዕከል ሊሆን ይገባል።


የቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት በተመለከተ

በክፍል ውስጥ ከሚሰጣቸው ትምህርት በተጨማሪ የተማሩትን ትምህርት በተሻለ ደረጃ
ተማሪዎች
እንዲገነዘቡና እንዲመራመሩ በስታንዳርዱ መሰረት የቤተ-መጻሕፍት አገልግሎት ማግኘት
እንዳለባቸው ይታመናል።
 ሆኖም ግን ትምህርት ቤቶች በስታንዳርድ መሰረት ሁሉም ትምህርት ቤቶች በግብዓት የተሟላ

ስታንዳርዱን የጠበቀ የቤተ መፃህፍት አገልግሎት የላቸውም።


 ያላቸውም ቢሆኑ በስታንዳርዱ መሰረት በግብዓት የተሟሉ አይደሉም።
 ለምሳሌ ካሉን አንደኛና መካከለኛ ትምህርት ቤቶች ውስጥ
 45 % የሚሆኑት ብቻ ቤተ-መፃሕፍት ቤት አላቸው።
 ነገር ግን የተሟላ አገልግሎትና በበቂ ግብዓት የተደራጁ አለመሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ።
 በተመሳሳይ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን 100% የሚሆኑት ብቻ የቤተ መፃህፍት ቤት

እንዳላቸው መረጃዎች ቢያሳዩም

 በስታንዳርዱ መሰረት ወንበር፣ ጠረጴዛ፣ የመፀህፍት መደርደሪያ፣ አጋዥ መፃኅፍትና ማጣቃሻ


መፃህፍት ባለመኖሩ የተሟላ አገልግሎት እየሰጡ አይደለም።
 ተማሪዎች መምህራን በሚሰጧቸው እውቀትና ባልተሟላ መልኩ ባገኙት የመማሪያ መፃኅፍት ላይ

ብቻ ስለሚወሰን በውጤታቸው ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ያሳድራል።

 ስለሆነም በቀጣይ የተማሪዎችን ውጤትና ስነምግባር ለማሻሻል የተማሪዎችን አጋዥና ማጣቀሻ


መፃህፍትን ለማሟላት ሁሉንም ባለድርሻ አካላት በማሳተፍ በቀጣይ ርብርብ ማድረግ ይገባል። 
የቤተ-ሙከራ አገልግሎት
 ተማሪዎች በንድፈ ሀሳብ የተማሩትን ትምህርት
 በተሻለ መልኩ እንዲረዱት የቤተ-ሙከራ አገልግሎት ከማገዙም በተጨማሪ
 የተማሪዎችን የፈጠራ ችሎታ የማገዝ፣
 ንድፈ ሀሳቦችን የመገምገምና የመተንተን ችሎታቸውን የሚያበለጽግ በመሆኑ
 ለቀጣይ የትምህርት እርከኖች የተዘጋጁ ተማሪዎች እንዲኖሩ ከማድረግ አንጻር ፋይዳው
ከፍተኛ ነው፡፡
 በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ስታንዳርድ ውስጥ ለትምህርት እርከኑ አስፈላጊ የሆኑ
ቁሳቁሶችን ያሟሉ ቤተ-ሙከራዎች እንዲኖሩ የሚጠበቅ ነው፡፡
 መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ግን አስፈላጊውን አገልግሎት ሊሰጡ የሚያስላቸውን
ቁሳቁሶች አሟልተው የተገኙ ቤተ-ሙከራዎች ያሏቸው
 50% አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና
 95% ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ብቻ ናቸው።
 ምንም እንኳን የቤተ ሙከራ አገልግሎት እንደሚሰጡ መረጃው ቢያመላክትም
በስታንዳርዱ መሰረት የተሟላ ግብዓት ባለመኖሩ ተማሪዎች ከሳይንስ ትምህርት
ማግኘት ያለባቸውን እውቀት እና ክህሎት ማግኘት እንዳልቻሉ
 የዚህ አመት የ12ኛ ክፍል ቢሄራዊ ፈተና ውጤት ያመላክታል።
የትምህርት ማበልፀጊያ ማዕከላት በተመለከተ
 የትምህርት ማበልፀጊያ ማዕከላት መምህራን በሚያስምሩት የትምህርት ዓይነት የትምህርት
መርጃ መሳሪያ የሚያዘጋጁበትና ትምህርት ቤቱም ከአካባቢ ቁሳቁስ ከሚሰሩ አጋዥ የመማሪያ
ማስተማሪያ ቁሳቁሶች በተጨማሪ የፋብሪካ ምርቶችን በመግዛት የሚያደራጁበት ማእከል
ሲሆን
 መምህራን ከማእከሉ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎችን እየተዋሱ የሚስተምሩትን ትምህርት
ይበልጥ ተጨባጭ በማድረግ የተማሪዎችን የትምህርት አቀባበል ለማሳደግ የሚገለገሉበት ነው፡፡
 ከዚህ አንጻር ከ60% በላይ የአንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትህርት ቤቶች እና
 93% የሚሆኑ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የትምህርት ማበልፀጊያ ማዕከላት አላቸው።
 ምንም እንኳን መረጃው የትምህርት ማበልጸጊያ ማዕከል ትምህርት ቤቶች እንዳላቸው
ቢያሳይም በተለያዩ ጊዜያት የተደረጉ የሱፐርቪዥን ስራዎችና የኢንስፔክሽን ሪፖርቶች
እንደሚያመላክቱት ትምህርት ቤቶች
 በስታንዳርዱ መሰረት የማምረቻ፣ የማዘጋጃና የማዋሻ ክፍሎች የሌላቸው መሆኑንና
 መምህራንም በቂ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎችን እያመረቱ እንዳልሆነ፣ በችግር ውስጥ ተሁኖ
የተመረቱትንም ቢሆን በአግባቡ መጠቀም ላይ ክፍተት ያለ መሆኑን ያሳያሉ።
 ስለሆነም ሁሉም ትምህርት ቤቶች በስታንዳርዱ መሰረት የተሟላ የትምህርት ማበልጸጊያ
ማዕካለት እንዲኖራቸው ማድረግ ያስፈልጋል።
ኢንስፔክሽን ሪፖርት ስለ ትምህርት ቤቶች መሰረተ-ልማትና ፋሲሊትዎች

 የመምህራን ማረፊያ ክፍል


 የመጀመሪያ እርዳታ መስጫ ክፍል
 ዕቃ ግምጃ ቤት /ስቶር/
 የጽዳት ሠራተኛ ክፍል
 የትምህርት መረጃ መሳርያዎች ማዘጋጃ ማዕከል
 የትምህርት መረጃ መሳሪያዎች ማዋሻ ክፍል
 ዴስክ /ለመቀመጫ /ለሁለት ተማሪ አንድ መቀመጫ /ዴስክ/ (ከ1-4)
 ዴስክ /ለመቀመጫ /ለሁለት ተማሪ አንድ መቀመጫ /ዴስክ/ (ከ5-8)
 ጠረጴዛ /ለመምህሩ/ርቷ
 ወንበር /ለመምህሩ/ርቷ
 ጥቁር ሰሌዳ
 የማስታወቂያ ሰሌዳ
 የስፖርት ሜዳ/ሁለገብ/
ስታንዳርድ 2 -ትምህርት ቤቱ የመማር ማስተማሩን ሂደት ለማሻሻል
ላቀዳቸውና ቅድሚያ ለሰጣቸው ተግባራት ማስፈፀሚያ የሚያገለግል
የፋይናንስ ሃብት ስለማሟላቱ፡፡/4%/
 በገንዘብ ለማሳባሰብ የታቀደ
 በአይነት /በቁሳቁስ/ ለማግኘት የታቀደ
 የጉልበት ድጋፍ ለማግኘት የታቀደ
 የእውቀት ድጋፍ ለማግኘት የታቀደ
 መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ለማሳባሰብ የታቀደ
 ከግለሰቦች ለማሳባሰብ የታቀደ
 ከቀድሞ ተማሪዎች ለማሳባሰብ የታቀደ
 ከአካባቢው ተወላጆች ለማሳባሰብ የታቀደ
የቀጠለ…
 በአጠቃላይ ከላይ የተጠቀሱት የመሰረተ ልማት እና የፋሲሊቲ
ችግሮች በአንድ ጊዜ የተፈጠሩ ሳይሆን ለረጅም ጊዜ ሲንከባለሉ
የመጡ የትምህርት ስርዓታችን ችግሮች መሆናቸውን የሚያሳዩ
ናቸው፡፡
 በስታንዳርዱ መሰረት መሟላት ያለባቸውን መሰረተ ልማቶች

እና ፋሲሊቲሮች አሟልተው ትምህርት ቤቶችን ከመክፈት ይልቅ


ትምህርትን ተደራሽ ለማድረግ ሲባል ስታንዳርዱን ያላሟሉ
ትምህርት ቤቶች በመክፈት አገልግሎት እንዲሰጡ በመደረጉ እና
ችግሮቹ በሂደት እየተቀረፉ ባለመምጣታቸው የተፈጠረ መሆኑ
ይታወቃል፡፡
 ስለዚህ በቀጣይ መሰረታዊ በሆኑ ችግሮች ላይ በማተኮር እና

ሁሉንም የትምህርት ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ የትምህርት


ቤቶችን ደረጃ ማሻሻል ይቻላል።
የክልላዊ ንቅናቄው ዋና ዋና ተግባራት

 ክልላዊ ዊ ንቅናቄውን በውጤታማነት ለመምራት የሚያስችል በክልል ት/ቢሮ ደረጃ አደረጃጀት


መፍጠር፤ ለእያንዳንዱ አደረጃጀት ተግባርና ኃላፊነት መስጠት፣ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፣
 የክልላዊ ንቅናቄ ሰነድና የተግባቦት ስልት ማዘጋጀት፤ ማስተዋወቅና መተግበር፤
 ከቢሮ እስከ ትምህርት ቤት የሚደርስ አደረጃጀት መፍጠር፤ ተግባርና ኃላፊት በመስጠት ወደ ትግበራ
ማስገባት፤ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፣
 ለክልላዊ ንቅናቄ የሚያስፈልጉ ግብአቶችን (የፋይናንስና የሎጂስቲክስ) በመለየት በሚመለከተው
አካል ፀድቆ ወደ ተግባር እንዲገባ ማድረግ፣
 በየደረጃው ባለው ማህበረሰብና ልዩ ልዩ አካላት ተሳትፎ የትምህርት ቤቶችን መሠረተ-ልማት
ማሻሻል፤
 የትምህርት ቤት መሠረተ-ልማት የማሻሻል ሥራ የአሠራር ሥርአት ተዘርግቶለት በዘላቂነት
እንዲቀጥል ማድረግ፣
 ማህበረሰቡ በትምህርት ሥርአት ውስጥ በመሠረተ-ልማት መሻሻል ሳይወሰን የመማር ማስተማሩን
ሂደት በባለቤትነት እንዲደግፍ ማድረግ፣
 የትምህርት ቤቶችን መረጃ በፖርታል በተደገፈ ሥርአት መሰነድና ለሁሉም ተደራሽ ማድረግ፣
 በሙያቸው፣ በእውቀታቸውና በችሎታቸው በበጐ ፍቃድ ሊያግዙ የሚችሉ ባለሙያዎችን በማፈላለግ
በመርሃ-ግብሩን እንዲያግዙ ማድረግ፣
 ክልላዊ የንቅናቄ ማስጀመሪያ መድረክ ማካሄድ፣ በየደረጃው ተመሳሳይ መድረኮች መካሄዳቸውን
ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፣
 ሁሉም ተግባራት በእቅዱ መሠረት መፈፀማቸውን ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፣
ማስፈፀሚያ ስልቶች

 የማህበራዊ ሚዲያን ጨምሮ በቴሌቭዥንና ራዲዮ በመጠቀም ለባለድርሻ አካላት


የግንዛቤ ማስጨበጫ ዘመቻ ማካሄድ፣
 የተለያዩ ተዋንያኖችን አቅም ልየታና ማፒንግ በማዘጋጀት እንዲሳተፉ ማድረግ፣
 የህብረተሰቡ ተሳትፎና አስተዋፅዖ በጉልበት፣ በአገር ውስጥ የሚገኙ ቁሳቁሶችን
(እንደ አሸዋና ጠጠር ወዘተ) መጠቀም እና የባለቤትነት ስሜት በመፍጠር ከጅምሩ
እስከ መዝጊያው ድረስ ለዘመቻው ስኬት ሀገር በቀል ዕውቀትን መጠቀም፣
 ለዘመቻው ፈጣን ትግበራ ከግል፣ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ ባለድርሻ
አካላት ጋር በግብአት ማሰባሰብ ላይ ውጤታማ ትብብርና ትስስር መፍጠር፣

 ለትምህርት ቤቶቹ እድሳትና ፅዳት ከመንግስት የተለያዩ ሴክተር ፕሮግራሞች


(የውሃ፣ መስኖና ኤሌክትሪክ ቢሮ፣ ከተማ ልማት፣ የጤና ጥበቃ እና ወዘተ)
በየደረጃው ተቀናጅተው እንዲሰሩ ማድረግ፣ለዘመቻው ማስፈፀሚያ ያለውን
መዋቅር በመጠቀም በየደረጃው አስተባባሪ ኮሚቴ ማቋቋም፣
 ወረዳዎችና ትምህርት ቤቶች የዘመቻ ትግበራ ሂደቶችን፣ መልካም ተሞክሮዎችን
መቀመር፣ መማር እና መጋራት፣ 
በክልል ትምህርት ቢሮ ደረጃ

አብይ ኮሚቴ አባላት


1. ቢሮ ኃላፊ ሰብሳቢ
2. የመማር ማስተማር ምክትል ቢሮ ኃላፊ ም/ሰብሳቢ
3. ሁሉም ምክትል ቢሮ ኃላፊዎች አባላት
4. የት/ቤት መሻሻል ፕሮግራም ዳይክቶሬት ዳይሬክተር አባልና ፀሐፊ
5. የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አባል
6. የወላጆች ሕብረት ተወካይ አባል
7. የመምህራን ማህበር ተወካይ አባል
8. እንደአስፈላጊነቱ ሌሎች አባላትን መጨመር
ተግባርና ኃላፊነት

 የትምህርት ቤት መሰረተ ልማት ማሻሻል ንኡስ ኮሚቴ የሚመራበት እቅድ ማዘጋጀት፣


 ከክልል እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የትምህርት ቤት መሰረተ ልማት መሻሻል ኮሚቴ ማደራጀት

እና አፈፃፀሙን መከታተል፣
 የንቅናቄ ሰነዱን ለዞንችችና ለባለድርሻ አካላት ማስተዋወቅ፣
 ባለድርሻ አካላትን ልየታ ማካሄድና ሚናቸውን መለየት፤
 የትምህርት ቤቶች መሠረተ-ልማት ነባራዊ ሁኔታ የሚገልጹ መረጃዎችን መለየት፣
 የተጠናከረ የክትትልና የግምገማ ሥርዓት በማዘጋጀት መተግበር፣
 ትምህርት ቤቶች ጉድለታቸውን የሚለዩበትን ግለ ግምገማ ቴምፕሌት ማዘጋጀት
 ትምህርት ቤቶች የአካባቢያቸውን ፀጋ ተጠቅመው መሰረተ ልማትን ማሻሻል የሚያስችል ስልት

እንዲያዘጋጁ ማድረግ፣
 የንቅናቄ ስራውን የሚያሳይ የመልካም ተሞክሮ ሰነድ ማዘጋጀት፣
 ለንቅናቄና ለድጋፍ ስራዎች የሚያስፈልግ ግብዓት እና በጀት መለየት እና አፈፃፀሙን መከታተል፣
 የሚከናወኑ ተግባራትን በአህዝቦት ስራ እንዲታጀብ ማድረግ፣
 የትምህርት መሰረተ ልማት ማስፈጸሚያ ስልት ማዘጋጀት፣ መተግበር፣ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፣
 እንደአስፈላጊነቱ ንኡሳን ኮሚቴዎችን ማቋቋም፣
 አፈጻጸሙን ለትምህርት ሚኒስቴር በየሣምንቱ መላከ፣
በወረዳ ደረጃ ያሉ አባላት

1. የወረዳ ትምህርት ኃላፊ ሰብሳቢ


2. የመማር ማስተማር ም/መምሪያ ኃላፊ ም/ሰብሳቢ
3. ሁሉም ም/መምሪያ ኃላፊዎች አባላት
4. የት/ቤት መሻሻል ፕሮግራም ቡድን መሪ አባልናፀሐፊ
5. የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አባል
6. የወላጆች ሕብረት ተወካይ አባል
7. የመምህራን ማህበር ተወካይ አባል
8. እንደአስፈላጊነቱ ሌሎች አባላት መጨመር አባል
ተግባርና ኃላፊነት

 የትምህርት ቤት መሰረተ ልማት ማሻሻል ንኡስ ኮሚቴ የሚመራበት እቅድ ማዘጋጀት፣


 እስከ ትምህርት ቤት ድረስ የትምህርት ቤት መሰረተ ልማት መሻሻል ኮሚቴ ማደራጀት እና
አፈፃፀሙን መከታተል፣
 የንቅናቄ ሰነዱን ለባለድርሻ አካላት ማስተዋወቅ፣
 ባለድርሻ አካላትን ልየታ ማካሄድና ሚናቸውን መለየት፤
 የትምህርት ቤቶች መሠረተ-ልማት ነባራዊ ሁኔታ የሚገልጹ መረጃዎችን መለየት፣
 የተጠናከረ የክትትልና የግምገማ ሥርዓት በማዘጋጀት መተግበር፣
 ትምህርት ቤቶች ጉድለታቸውን የሚለዩበትን ግለ ግምገማ ቴምፕሌት ማዘጋጀት
 ትምህርት ቤቶች የአካባቢያቸውን ፀጋ ተጠቅመው መሰረተ ልማትን ማሻሻል የሚያስችል ስልት
እንዲያዘጋጁ ማድረግ፣
 የንቅናቄ ስራውን የሚያሳይ የመልካም ተሞክሮ ሰነድ ማዘጋጀት፣
 ለንቅናቄና ለድጋፍ ስራዎች የሚያስፈልግ ግብዓት እና በጀት መለየት እና አፈፃፀሙን መከታተል፣
 የሚከናወኑ ተግባራትን በአህዝቦት ስራ እንዲታጀብ ማድረግ፣
 የትምህርት መሰረተ ልማት ማስፈጸሚያ ስልት ማዘጋጀት፣ መተግበር፣ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፣
 እንደአስፈላጊነቱ ንኡሳን ኮሚቴዎችን ማቋቋም፣
 አፈጻጸሙን ለክልል ትምህርት ቢሮ በየሣምንቱ መላከ፣
በትምህርት ቤት ደረጃ

አባላት
1. የወላጅ፣ ተማሪ፣ መምህር ህብረት ሰብሳቢ
2. የትምህርት ቤቱ ር/መምህር ም/ሰብሳቢ
3. የትምህርት ቤት መሻሻል ኮሚቴ ሰብሳቢ አባል እና ፀሐፊ
4. የትምህርት ቤቱ ም/ር/መምህር አባል
5. የመሰረታዊ የመምህራን ማህበር ሊቀመንበር አባል
6. የተማሪዎች ተወካይ አባል
7. የበጎ ፈቃድ ክበብ ተወካይ አባል
8. የቀድሞ የት/ቤቱ ተማሪዎች ተወካይ አባል
9. ከተዋቂ ግለሰቦች ተወካይ አባል
10. እንደአስፈላጊነቱ ሌሎች አባላትን መጨመር
ተግባርና ኃላፊነት

 የትምህርት ቤቱን መሰረተ ልማት ለማሻሻል ከክልል/ዞን/ወረዳ በሚላከውን


የንቅናቄ ሰነድ መሠረት ያደረገና የትምህርት ቤቱን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘበ
የንቅናቄ ሰነድ ማዘጋጀት፣
 ለባለደርሻ አካለት የንቅናቄ ሰነዱ ላይ ግንዛቤ መፍጠር፣
 የትምህርት ቤት መሰረተ ልማት ችሮችን መለየት፣
 ወላጆች የትምህርት ቤቶች ችግሮች ተረድተው ግብአቶችን እንዲያሟሉ፤
እንዲያሻሽሉ፤ ትርጉም ያለው ተሣትፎ የሚያደርጉበትን ዝርዝር የአፈጻጸም
ስልት በማዘጋጀት መተግበር፤
 የትምህርት ቤት መሰረተ ልማት የሚሻሻልበት ስልት መቀየስ፣ ተግባራዊነቱን
መከታተል፣
 በአካባቢያቸው ያለውን ጸጋ በመጠቀም እና ባለሀብቶችን በማስተባበር
የትምህርት ቤቱን መሰረተ ልማትን ማሻሻል፣
 የተጠናከረ የክትትል፣ ግምገማ እና ድጋፍ ስርዓት መዘርጋት፤ ተግባራዊ ማድረግ፣
 የሚከናወኑ ተግባራትን በአሕዝቦት ሥራ እንዲደገፉ ማድረግ፣
 እንደአስፈላጊነቱ ንኡሳን ኮሚቴዎችን ማቋቋም፣
 በየሣምንቱ በወረዳው ስለንናቄው አፈጻጸም ሪፖርት መላክ፣
 
የክትትልና ግምገማ ስርዓት

 ክክልል እስከ ትምህርት ቤት ድረስ ሳምንታዊ እቅድ፥


የአፈፃፀም ሪፖርትና ግብረ መልስ ስርዓት ይዘረጋል፡፡
 ከየወረ የተጠቃለለ የሳምንት ሪፖርት ይቀርባል፤ በየአስራ

አምስት ቀኑ ከቢሮ ግብረ ሃይል መልስ ተዘጋጅቶ ለውይይት


ይቀርባል፡፡
 የመስክ ምልከታ በተመረጡ ትምህርት ቤቶች በቢሮ ከፍተኛ

አመራሮችና ማነጅሜንት ይካሄዳል፡፡


ማሳሰቢያ
 ሁሉም ትምህርት ቤት እስከ ግንቦት 20/2015 የትምህርት
ቤት መሰረተ ልማት መረጃውን ለቢሮ ሞልቶ መላኪ
ይጠበቅባቹዋል።
 መረጃውን በተባለበት ጊዜ ያላከ ትምህርት ቤት ድጋፍም ፤

ማበረታቻም አያገኝም ፤እርምጃ ይወሰድበታል።


 8ኛ ክፍል ፈተና ሰኔ 19 እና 20/2015 ዓ.ም (ደብዳቤ

ይውሰዱ)
 የ8ኛ ክፍል ምዝገባ የተማሪዎች ዳታ ያላስገቡ ት/ቤቶች

የመጨረሻ ቀን ግንቦት 8/2015 ዓ.ም


 4ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 13-14/2015 ይሰጣል
እናመሰግናለን!

You might also like