You are on page 1of 9

ዉጫሌ-17 አጠ/የከፍ/ትም/መሰ/2 ኛ ደረጃ ት/ቤት

በዉጫሌ-17 አጠ/የከፍ/ትም/መሰ/2 ኛ ደረጃ ት/ቤት የ 2012 ዓ.ም 12 ኛ ክፍል ተማሪዎችን በቴክኖሎጂ


ተደግፈዉ የተቋረጠባቸዉን ትምህርት እንዲቀጥሉ በማድረግ ከኃምሌ 29፣ 2012 ዓ.ም እስከ ቀጣይ
ጥቅምት/ህዳር 2013 ዓ.ም ለሚካሄደዉ ሃገር አቀፍ የ 12 ኛ ክፍል ፈተና ማዘጋጀት

ፐሮጀክት አመልካች /Name of the Applicants:


የዉጫሌ-17 አጠ/የከፍ/ትም/መሰ/2 ኛ ደረጃ ት/ቤት ሱፐርቫይዘር ፣ ም/ዕረሰ መምህር እንዲሁም መምህራን

11/23/2012 ዓ.ም
ማዉጫ
1. መግቢያ.................................................................................................................................................... ①
2. የፕሮጀክቱ ዓላማዎች.................................................................................................................................. ②
2.1. የፕሮጀክቱ አብይ ዓላማ............................................................................................................................②
2.2. የፕሮጀክቱ ንዑስ ዓላማ...........................................................................................................................②
3. ፕሮጀክት ተጠቃሚዎች............................................................................................................................... ②
4. ዋና ዋና የፕሮጀክት አስፈፃሚዎች/ተግባሪዎች.................................................................................................②
5. ፕሮጀክት ተሳታፊዎች................................................................................................................................. ③
6. ፕሮጀክት አተገባበር METHODOLOGY (STRATEGIES)....................................................................................③
7. ፕሮጀከቱን ለመተግበር የሚያስፈልጉ ግብአቶች..............................................................................................④
8. የድርጊት መርሃግብር/ACTION PLAN............................................................................................................ ④
9. ፕሮጀክት በጀት.......................................................................................................................................... ⑥
10. CONTACT PERSONS:............................................................................................................................. ⑥
1. መግቢያ
የኮሮና ቫይረስ በሽታ በቻይና ሃገር ከታየ ጀምሮ አፍሪካን ጨምሮ ወደ በርካታ የዓለም ሃገራት በመስፋፋቱ

ምክንያት በአለማችን ያሉ ትምህርት ቤቶች የተለመደዉን የመማር ማስተማረ ካቋረጡ ወራቶች

ተቆጥረዋል፡፡ ወረረሽኙ ከሚየደረሰዉ ጉዳት ባልተናነሰ የነገ አገር ተረካቢ ተማሪዎች ከትምህርት

ገበታቸዉ ሲለዩ በተማሪዎች፤ በወላጆች ፣ በመንግስት ብሎም በአገራት የወደፊት የእደገት ተሰፋ ላይ

ከፍተኛ የሆነ አሉታዊ ተፅኖ እንደሚኖረዉ ብዙ ሙሁራን ይስማማሉ፡፡ ይህንን ችግሩን ለመቅረፍ የብዙ

አገራ መንግስታት ፣ የትምህርት ተቆማት ወይም ትምህርት ቤቶች ፣ ወላጆች እና መምህራን እስከዛሬ

ከተለመደዉ የመማር ማስተማር ዘዴ በተለየ መልኩ የተለያዩ ዘዴዎችን በመተግበር ተማሪዎች በኮሮና

ቫይረስ ተጋላጭ በማይሆኑበት መልኩ ለማስተማረ በአገራችን ኢትዮጵያም ጭምር ጥረት በመደረግ ላይ

ይገኛል፡፡ ከነዚህ ዋና ዋና ተግባራት መካከል ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂን ተጠቅሞ በችግር ዉስጥም ቢኮን

ተማሪዎችን ማስተማር እንደሚቻል በብዙ የአገራችን ዋና ዋና ከተሞች በሚገኙ ትምህርት ቤቶች

ታይቷል፡፡ ስለሄነም የዉጫሌ-17 አጠ/የከፍ/ትም/መሰ/2 ኛ ደረጃ ት/ቤት የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል

ከሚያደርገዉ ጥረት ጎን ለጎን በት/ቤቱ ሚገኙ የኮምፒዉተር ቴክኖሎጂ እና በቅርቡ ከ አዲስ አበባ

ባስመጣነዉ የቪዲዎ ሌክቸር ተጠቅሞመን ፣ ለኮሮና ተጋላጭ በማያደርግ መልኩ የ 12 ኛ ክፍል

ተማሪዎችን በቀጣይ ጥቅምት/ህዳር 2013 ዓ.ም ለሚካሄደዉ ሃገር አቀፍ የ 12 ኛ ክፍል ፈተና ለማዘጋጀት

አስበናል፡፡ ስራዉን በብቃት መፈፀም የሚያስችል ዋና ዋና ግብአቶች እና የሰለጠነ የሰዉ ሀብት የለን

ቢሆንም ስራዉ በክረምት እና ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ አንዳንድ ግብአቶችን በማሟላት ከሓምሌ 20፣

2012 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 2013 ማስተማር እንድንችል አምስት ሺ ብር ስለሚያስፈልግ እንዲሁም

በሽታዉን ለመከላከል ኮማንድ ፖስት የተቋቋመ በመሆኑ ይህን አጭር ፕሮጀክት ማዘጋጀት አስፈልጓል፡፡

1
2. የፕሮጀክቱ ዓላማዎች
2.1.የፕሮጀክቱ አብይ ዓላማ
 ዉጫሌ-17 አጠ/የከፍ/ትም/መሰ/2 ኛ ደረጃ ት/ቤት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት
ትምህርታቸዉ የተቋረጠባቸዉ የ 2012 ዓ.ም 12 ኛ ክፍል ተማሪዎችን ለኮሮና ቫይረስ
ተጋላጭ በማይሆኑበት መልኩ ኮምፒዉተር ተጠቅሞ በመጪዉ ጥቅምት/ህዳር
2013 ዓ.ም ለሚሰጠዉ አገራ አቀፍ የ 12 ኛ ክፍል ፈተና ለማአጋጀት ነወ፡፡

2.2. የፕሮጀክቱ ንዑስ ዓላማ


 የ 2012 ዓ.ም ትምህርት በመቋረጡ ያልተሸፈኑ የአመቱን ትምህርቶች መሸፈን
 በኮሮና ምክንያት የተዳከመዉን የተማሪዎች የመማር እና የንባብ ፍላጎት ማነቃቃት
 ተማሪዎች የአመቱን ትምህርቶች እንዳይረሦቸዉ መከለስ እንዲችሉ ለማድረግ

3. ፕሮጀክት ተጠቃሚዎች
 የ 12 ኛ ክፍል ተማሪዎች እና ወላጆች
 የዉጫሌ-17 አጠ/የከፍ/ትም/መሰ/2 ኛ ደረጃ ት/ቤት መምህራን
 ዉጫሌ-17 አጠ/የከፍ/ትም/መሰ/2 ኛ ደረጃ ት/ቤት ማህበረሰብ
 የዉጫሌ ከተማ ማህበረሰብ
 የአምባሰል ወረዳ ት/ጽ ቤት፣ እንዲሁም
 የአምባሰል ወረዳ ህዝብ እና መንግስት

4. ዋና ዋና የፕሮጀክት አስፈፃሚዎች/ተግባሪዎች
1. ተስፋያ ሁሴን፡- በአምባሰል ወረዳ አጠ/የከፍ/ትም/መሰ/2 ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ሱፐርቫይዘር
2. በላይ ተፈራ፡- በዉጫሌ-17 አጠ/የከፍ/ትም/መሰ/2 ኛ ደረጃ ት/ቤት ም/ዕ/መ
3. ሳሙኤል በዜ፡- በዉጫሌ-17 አጠ/የከፍ/ትም/መሰ/2 ኛ ደረጃ ት/ቤት ICT መምህር
4. አባተ ይመር፡- በዉጫሌ-17 አጠ/የከፍ/ትም/መሰ/2 ኛ ደረጃ ት/ቤት ICT መምህር
5. ቴዎድሮስ ሽመልስ፡- በዉጫሌ-17 አጠ/የከፍ/ትም/መሰ/2 ኛ ደረጃ ት/ቤት ታሪክ መምህር
6. የ 12 ኛ ክፍል ተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች
7. የ 12 ኛ ክፍል ማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች

2
5. ፕሮጀክት ተሳታፊዎች
1. በዉጫሌ-17 አጠ/የከፍ/ትም/መሰ/2 ኛ ደረጃ ት/ቤት የ 12 ኛ ክፍል የተፈጥሮ እና ማህበራዊ
ሳ ንስ ተማሪዎች
2. በዉጫሌ-17 አጠ/የከፍ/ትም/መሰ/2 ኛ ደረጃ ት/ቤት በጎ ፈቃደኛ መምህራን
3. በዉጫሌ-17 አጠ/የከፍ/ትም/መሰ/2 ኛ ደረጃ ት/ቤት ምክትል እረሰ መምህር እና
ሱፐርቫይዘር
4. በዉጫሌ-17 አጠ/የከፍ/ትም/መሰ/2 ኛ ደረጃ ት/ቤት ፍቃደኛ መምህራን
5. የአምባሰል ወረዳ ት/ፅ ቤት
6. በአምባሰል ወረዳ የኮሮና ቫይረስ መከላከል ኮማንድ ፖስት

6. ፕሮጀክት አተገባበር Methodology (strategies)

የኮሮና ቫይረስ በሽታ በመከሰቱ ምክንያት እስከዛሬ ከተለመደዉ የመማር ማስተማር ዘዴ በተለየ መልኩ
ዘመናዊ ቴክኖሎጂን በመተግበር ተማሪዎች በኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ በማይሆኑበት መልኩ ለማስተማረ
በአገራችን ኢትዮጵያም ጭምር በሚገኙ አንዳንድ ተምህርት ቤቶች ጥረት በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡
የዉጫሌ-17 አጠ/የከፍ/ትም/መሰ/2 ኛ ደረጃ ት/ቤት የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ከሚያደርገዉ ጥረት ጎን
ለጎን በት/ቤቱ ሚገኙ የኮምፒዉተር ቴክኖሎጂ እና በቅርቡ ከ አዲስ አበባ ባስመጣነዉ የቪዲዎ ሌክቸር
ተጠቅሞመን ፣ ለኮሮና ተጋላጭ በማያደርግ መልኩ የ 12 ኛ ክፍል ተማሪዎችን በቀጣይ ጥቅምት/ህዳር
2013 ዓ.ም ለሚካሄደዉ ሃገር አቀፍ የ 12 ኛ ክፍል ፈተና ማዘጋጀት እንችላለን፡፡ስራዉን በብቃት
መፈፀም የሚያስችል ዋና ዋና ግብአቶች እና የሰለጠነ የሰዉ ሀብት የለን ቢሆንም ስራዉ በክረምት እና
ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ምክንያት ከዘህ በታች የተዘረዘሩ ወና ዋና ደንቦችን ተግባራዊ በማድረግ
ይከናወናል፡-

 ለመማራ ፍቃደኛ የሆኑ ተማሪወችን ብቻ በመመዝገብ በአንድ ክፍል ከ 15


ያልበለጡ ተማሪዎችን ከሰኞ እስከ አርብ ፕሮግራም በማዉጣት እንዲማሩ
ማድረግ

3
 ኮምፒዉተሮችን በ 2 ሜትር እርቀት በማስቀመጠ አንድ ኮምፒዉተር ላይ አንድ
ተማሪ ብቻ ሁልጊዜ እንዲገለገልበት በማድረግ፣
 ሁሉም ተማሪ የኮሮናን ቨይረስን መከላከል የሚያስችሉትን አራት የመ ህጎችን
እንዲተገብሩ በማድረግ፣
 ተማሪወች ኮምፒዉተሩ ላይ የተጫነዉን ቪዲዮ ሌክቸር እንደየፍላጎታቸዉ
ከፍተዉ የድምፅ ማዳመጫ ጆሮአቸዉ ላይ በማድረግ እንዲማሩ ማድረግ ፣
 ተማሪዎች ወደ መማርያ ክፍል ሲገቡ ሳኒታይዘር እንዲጠቀሙ ማድረግ እንዲሁም
የአፍ መሸፈኛ መልበሳቸዉን በማረጋገጥ፣

በአጠቃላይ ከላይ ከተዘረዘሩት ተግባራት በተጨማሪ ተማሪዎች ለኮሮና ቫይረስ ተጋላጭ በማይሆኑበት
መልኩ መማር ማስተማሩን የተሸለ ለማድረግ ከተማሪዎች፣ መምህራን እና ሌሎች ባለድርሻ
አካላት ጋር መስተካከል ያለበትን ለማስተካከል ተከታታይ ዉይይቶችን እናደርጋለን፡፡

7. ፕሮጀከቱን ለመተግበር የሚያስፈልጉ ግብአቶች


1. በኮምፒዉተር ክላስ ዉስጥ በ 2 ሜትር እርቀት የተደረደሩ 15 ኮምፒዉተሮች
2. ኤርፎን የድምፅ ማዳመጫ
3. ከ 9-12 ያሉ ሁሉም ትምህርቶች ያሉበት የቪዲዮ ሌክቸር
4. ወደ መማርያ ክላስ ሲገቡ ተማሪዎች እሚታጠቡበት የዉሃ ማጠራቀሚያ
በርሚል/ጀሪካ እና ሳሙና
5. ለኮምፒዉተር ማፅጃ የሚሆን 5 ሌትር አልኮል/ሳኒታዘር
6. 20 ሌትር ጀኔሬተር
7. 1 ደስታ ወረቀት

8. የድርጊት መርሃግብር/Action plan


ተ.ቁ የሚተገበሩ ዋና ዋና ተግባራት/ስራዎች ስራዉን የሚተገብረዉ አካል የሚከናወንበት ምርመራ
የጊዜ ሰሌዳ

4
1st  ከዉጫሌ-17
አጠ/የከፍ/ትም/መሰ/2 ኛ ደረጃ
ት/ቤት ባለድርሻ አካላት ጋራ
አጠቃላይ አሰራሩን
በተመለከተ ዉይይት ማድረግ

2nd  ተማሪወችን መመዝገብ እና


ስለ ትምህርት አሰጣጡ
ግንዛቤ መፍጠርየ
3rd  የኮምፒዉተር መማርያ
ክፍልን ኮሮናን መከላከል
በሚያስችል መልኩ ማዘጋጀት
እና መሟላት የለበትን
ማተርያሎች ማሟላት

4th  ከአምባሰል ወረዳ ት/ፅ ቤት ጋራ


በትምህርት አሰጣጡ ዙሪያ
መወያየት
5th  በአምባሰል ወረዳ የኮሮና ቫይረስ
መከላከል ኮማንድ ፖስት ጋራ
በትምህርት አሰጣጡ ዙሪያ
በመወያየት ፍቃድ ማግኘት

6th ትምህርት ለመጀመር የሚያስችሉ


ቁሳቁሶች ማለትም የድምፅ
ማዳመጫ፣ ነዳጅ ዘይት፣ አልኮል፣
ሳኒታይዘር እና ሌሎች ቁሳቁሶች
መሟላታቸዉን ማረጋገጥ
7th ተማሪዎችን ማሟላት ያለባቸዉን

5
ቅድመ ሁኔታ በመጥቀስ
ተማሪዎችን በማስታዎቂያ
መጥራት
8th ሁሉም ተማሪ ማሟላት
ያለባቸዉን አሟልተዉ ስማቸዉ
በተለጠፈበት ከምፒዉተር
እንዲቀመጡ በማድረግ
ስለኮምፒዉተር አጠቃቀሙ
ስልጠና መስጠት
9th ሁሉም ተማሪ በየለቱ መምጣቱን
ማረጋገጥ
10t በትምህርት አሰጣጡ ዙርያ
h መስተካከል ያለበትን ለማስተካከል
ተከታታይ ግምገማ ወይም ሀሳብ
መስጠት
11t
h

9. ፕሮጀክት በጀት
ተ. የሚያስፈልግ ቁሳቁስ ብዛ መለኪ የአን ጠቅላላ ምርመራ
ቁ ት ያ ዱ ድምር
ዋጋ
1 ኤርፎን (ድምፅ ማዳመጫ) 40 #
2 ወረቀት 1 ደስታ
3 በየለቱ ተማሪዉች የሚጠቀሙት ሳኒታይዘር 10 ሌትር
4 የኮምፒዉተር ማፅጃ አልኮል 5 ሌትር
5 መብራት ሲጠፋ ለጀነሬተር የሚሆን ነዳጅ ዘይት 20 ሌትር
6 የፅዳት ሰራተኛ 1 #
7
8
9

6
10. Contact Persons:
 ተስፋያ ሁሴን፡- በአምባሰል ወረዳ አጠ/የከፍ/ትም/መሰ/2 ኛ ደረጃ ት/ቤቶች ሱፐርቫይዘር፣
phone: +2519__________________ Email: _______________________________

 በላይ ተፈራ፡- በዉጫሌ-17 አጠ/የከፍ/ትም/መሰ/2 ኛ ደረጃ ት/ቤት ም/ዕ/መ phone:


+2519__________________ Email: _______________________________

You might also like