Professional Documents
Culture Documents
2010
2010
መግቢያ
መንግስት የህብረተሰቡንና የሲቪል ሰርቫንቱን ኖሩ ለማሻሻል በኪራይ ሰብሳቢነት ዙሪያ በርካታ ስራወችን
ከክልል እስከ ዞን ከዞን እስከ ወረዳና ከወረዳ እስከ ቀበሌ ድረስ በርካታ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል፡፡
በዚህ መሰረት የመ/ወ/ትም/ት ጽ/ቤት ተቋሙ ካልዉ ራዕይና ተልዕኮ አካያ ተቋሙ ከተቋቋመበት ጊዜ ጀምሮ
በተቋሙ ዋና ዋና የኪራይ መስብሰቢያ አዝማሚ ናቸዉ ከሚባሉት የመንግስት ስራ ሰዓት
አለማክበር፣ቅጥር፣ዝዉዉር፣የደረጃ እድገት፣ የዲስፕሊን ክስ ላይ የሚገባዉን ዉሳኔ ካለመስጠት፤ የት/ቤት
አመራሮች በጀትን ለልታለመለት አላማ ማዋል፤ ወ.ዘ.ተ የመሳሰሉት የሚታዩ የኪራይ ሰብሳቢነት
አዝማሚያዉች ሲሆኑ እነዚህን ተግባራት ከመታገል አንፃር በርካታ ስራዎችን አከናዉኗል፡፡ ይህን ችግር
በዘላቂነት በመቅረፍ የት/ቤቱን አገልግሎት ፈልገዉ ለሚመጡ ደንበኞች ፈጣንና ቀልጣፋ የአገልግሎት አሰጣጥ
በመዘርጋት በተቋሙ ላይ የተሻለ አመኔታ እንዲኖራቸዉ የማድረግ ስራ ተሰርቷል፡፡
ስለዚህ በ 2010 ዓ.ም የፀረ-ኪራይ ሰብሳቢነት ማድረቂያ እቅድ ስናዘጋጅ በ 2009 ዓ.ም የታዩ ጉድለቶችን
በማስዉግድ የነበሩትን ጠንካራ ተግባራት ደግሞ የበለጠ አጠናክረን ለማስቀጠል ይህን መነሻ እቅድ
አዘጋጅተናል፡፡
/
የመተማ ወረዳ ትምህርት ጽ ቤት ተልዕኮ፣ ራዕይና እሴቶች
ተልዕኮ
በትምህርትና ስልጠና ውጤታማና ብቁ ዜጋ ማፍራት፤
ራዕይ 2012
ትምህርትና ስልጠናን በስፋት በማዳረስ ስብዕናው የተሟላ የስራ ባህልን ያሳደገ ብቁ ዜጋ ተፈጥሮ ማየት፤
እሴቶች
ለዉጥ ናፋቂና አራማጅ እንሆናለን፣
የስራ ፍቅር፣ ከበሬታና መልካም ስነ-ምግባር መለያችን ይሆናል፣
ከተገልጋዮች/ዜጎች ፍላጎት ቅድሚያ መስጠት የመፈጠራችን ምክንያት መሆኑን
እንረዳለን፣
ግልጽነትና ተጠያቂነትን እናሰፍናለን፣
ሁሌም ተማሪና አስተማሪ መሆን እንደሚገባ እንገነዘባለን፣
ቅልጥፍናና ዉጤታማነትን ማረጋገጥ የጥረታችን ሁሉ መቋጫ መሆኑን እናምናለን፣
ዓላማ
የፀረ-ኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከትና አዝማሚያ ተግባርን በመታግል በሰነ- ምግባሩ የታነፀ ሙያተኛ
፣ደንበኛና ማህበረሰብ በመፈጠር ኪራይ ሰብሳቢነትን የሚፀየፍና የሚጠላ የህብረተሰብ ክፍል
ማፈራት ነዉ፡፡
የሁኔታ ትንተና
በጥንካሬ
የፀ-ኪራይ ሰብሳቢነት ማትጊያ መድረኮችን ፈጥሮ በማታገል የተሻለ መሆኑ፤
ሙያተኛዉ እና የት/ቤት መርሱወች በየዓመቱ ራሱን በሚያሳይ ሁኔታ 2 ጊዜና ሲቀጥልም
እንደአስፈላጊነቱ ሂስና ግለ-ሂስ ማድረጉና ችግሮችን እየለየ ማሻሻል መቻሉ፤
በመሰረታዊነት የሚታዩ ችግሮችን ከተገልጋዮች ጋርና በጽ/ቤቱ አደረጃጀቶች እንዲፈቱ ጅምር
ተግባር መኖሩ፤
ኪራይ ሰብሳቢነት አዝማሚያ ያላቸዉን ባለሙያዎች በመለየት በህግና በሲ/ሰ መመሪያ እንዲጠየቁ
መደረጉ፤
በድክመት
ሙያተኛዉ እና መርሱወች የሚያሳዩቸዉ የትግል ሁኔታ ከአድርባይነት የተላቀቀ አለመሆኑ፤
በሂስና ግለ-ሂስ ወቅት ከተወሰኑ ባለሙያዎች ዉጭ ሂስን ከመቀበል ይልቅ የማኩረፍ ሁኔታ መኖሩ፤
በሂስና ግለ-ሂስ ወቅት ሁሉም ባለሙያ በምን አለብኝነት ዝምታን የመምረጥ ሁኔታ መኖሩ፤
የኪራይ መሰብሰቢያ ምንጭች
1. ሙያተኛዉ እና መርሱወች የመንግስትን የመዉጫና የመግቢያ የስራ ስዓት በትክክል አለመጠቀም
2. በመርሱ ቅጥር ወቅት ከተፈታኞች የማይገባ ጥቅም መፈለግ፤
3. በቅጥር ወቅት ተፈታኞችን በኩል እይታ ያለማየት ችግር ማለትም ተፈታኝ ዘመድ ካለ ለዘመድና
ለሚያዉቁት ማዳላት እና የት/ቤት ምደባም ያለአግባብ መስራት፤
4. የት/ቤት ት/ቤት ዝዉዉር ሲሰራ ከደንብና መመሪያ ዉጭ መፈፀም፤
5. በዲስፕሊን ክስ ወቅት በተከሳሾች ላይ ያላግባብ መመስከር፣ ያላጠፋዉን ጥፋት እንደ ጥፋተኛ ነጥብ
ይዞ መቅረብ፤ መጠየቅ ያለበትን መርሱ ደግሞ አደፋፍኖ ማለፍ እና ከጥፋቱ ጋር ያልተመጣጠነ ዉሳኔ
መወሰን፤
6. ባልተሰራ ስራ ላይ አበል መጠየቅ፤
7. የት/ቤት አመራሮች የት/ቤት በጀትን ለግል ጥቅም የማዋል አዝማሚያወች፤
8. በጽ/ቤቱ ዉስጥ የምንጠቀምባቸዉን እስክብሪቶ፣ወረቀትና ማቴሪያሎችን በአግባቡ አለመጠቀም
ወ.ዘ.ተ የመሳሰሉት ዋና ዋና የኪራይ መሰብሰቢያ ምንጮች ናቸዉ፡፡