You are on page 1of 14

የመ/ሜዳ ቴ/ሙያ ኮሌጅ

2014ዓ.ም አመታዊ የእቅድ አፈፃፀም አጭር ሪፖርት


ተልእኮ

 ጥራት ያለው የሙያ ስልጠና በመስጠት ብቃቱ የተረጋገጠ በአነስተኛና በመካከለኛ ደረጃ የሰለጠና በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪና ብቁ
የሆነ የሰው ኃይል ማፍራትና የጥቃቅን አነስተኛ ኢንተ/ዞች በስፋት እንዲቋቋሙ በማድረግ የስራ ዕድል መፍጠርና ለኢንተ/ዞች
የኢ/ኤ/አገልግሎት በመስጠት በገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ማድረግ ነው፡

I ቁልፍ ተግባር--- የልማት ሠራዊት እንቅስቃሴ

ኮሌጁ የበጀት ዓመቱን እቅድ በተገቢው ሁኔታ ለመፈፀም የኮሌጁን የሠው ኃይል በተለያዩ አደረጃጀቶች የማደራጀት ስራ ተሰርቶ ተግባራዎ
እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል፡፡
ይኸውም -100 የሚሆኑ የኮሌጁን መ/ራንና ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች በ5 የል/ቡድንና በ17 የ1ለ5 የማደራጀት ስራ ተሰርቷል፡፡
- 1060 ሰልጣኞችን ደግሞ በ32 የል/ቡድንና በ130 የ1ለ5 የማደራጀት ስራ ተሰርቷል ፡፡
• ሁሉም አደረጃጀቶች የራሳቸውን እቅድ አዘጋጅተው በእቅዳቸው መሰረት በል/ቡድን በየ15 ቀኑ እና በ1ለ5 ደግሞ በየሳምንቱ የእቅድ

አፈፃፀማቸውን ይገመገማሉ፡፡ ይወያያሉ

• በአፈፃፀም ያጋጠማቸውን ችግሮችን በወቅቱ እንደፈቱ ያደርጋሉ በዚህም የስራ አፈፃፀም ወይይት በአብዛኛው የኮሌጁ አደረጃጀቶች

በተቀመጠላቸው

• የመወያያ ጊዜ የሚወያዩ ሲሆን የተወሰኑት ደግሞ በማቋራረጥ የሚወያዩ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡

• በውይይት የመጡ ለውጦች


- የሚሰራና የማይሰራውን ለመለየት የተሻለውን የማበረታታትና ወደ ኋላ የቀረውን ድጋፍና ክትትል ማድረግ
- ርስ በርስ የመተጋገልና የኮሌጁን እቅድ በጋራ ለመፈፀም የስራ ተነሳሽነት ተፈጥሯል፡፡
- የጠባቂነት ስሜት ማሰቀረት
- ሰልጠኞች በስልጠና ዙሪያ የርስበርስ ለመረዳዳት ችለዋል
- የተሰጠን ኃላፊነት በውል ተገንዘቦ ለመስራት ረድቷል፡፡
- መመሪያዎችን አሰራሮችን አውቆ ለመስራት ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡
II አብይት ተግባራት --ትም/ትና ስልጠና

የዚህ ዓመት የመደበኛ የሰልጣኝ ቅበላ

----ነባር እቅድ 667 ክንውን 815 አፈፃፀም 122.5%

----አዲስ እቅድ 315 ክንውን 245 አፈፃፀም 77.8%

በድምሩ እቅድ 982 ክንውን 1060 አፈፃፀም 107.9%

የነባር ሰልጣኞች የተሻለ አፈፃፀም ያለው ሲሆን በተሻሻለው መመሪያ መሰረት በርካታ ሰልጣኞችን በመልሶ ቅበላ

የተቀበልን ስለሆነ ነዉ፡፡ በሌላ በኩል የአዲስ ሰልጣኞች ቅበላ የእቅዱን 77.8% ብቻ ነው ይህውም በሁለት ዙር/ጥቅምት

እና ግንቦት ወር/ የተደረገ ቅበላ አፈፃፀም ነው፡፡

 
መደበኛ ባልሆነ አጫጭር ስልጠና

• በኢንተርፕሪነር እቅድ 6159 ክንውን 5490 አፈፃፀም 89.1%

• በቴክኒካል እቅድ 1832 ክንውን 2148 አፈጻጸም 117.2%

• አ/አደር እቅድ 115 ክንውን 100 አፈፃፀም 86.9% የመንዝ ቀያ ገብረኤል ወረዳ ብቻ

• ከሰለጠኑት ዉስጥ ቀሚና ጊዜያዊ የስራ እድል የተፈጠረላቸዉ ወ 2408 ሴ 2299 ድ 4707 ያህሉ ናቸዉ ፡፡አፈፃፀም 85.7
ፐርሰንት ነዉ፡፡
• የአጫጭር ስልጠና ከ3ቱ ወረዳ ጽ/ቤቶች ጋር የካቲት ወር ላይ የጋራ ውይይት ከተደረገ በኋላ የተሻለ እንቅስቃሴ ቢኖርም አሁንም ከእቅድ አፈፃፀም
አኳያ ሲታይ የሚቀር ተግባር ነው፡፡

• የምሩቃን ሁኔታ በ2013 እና ከዚህ በፊት ከኮሌጁ የተመረቁ ከ360 በላይ የተመረቁ ሲሆን እስከ አሁን ባለን መረጃ መሰረት ከ335 በላይ የሚሆኑ ወይም
93.1% ምሩቃን የሚሆኑት በቋሚና በጊዜያዊ ስራ ወደ ስራ የገቡ እንደሆነ መረጃ የተያዘ ቢሆንም አሁንም ወደ ስራም ያለገቡ ምሩቃን አሉና በሁሉም
ወረዳዎች ትኩረት ተሰጥቶ ሊሰራ ይገባል
• በ2014 አ.ም ስልጠናቸዉን ካጠናቀቁ ሰልጣኞች ዉሰጥ የቴክስታይልና ጋርመንት እንድሁም የአይቲ ምሩቃን ወደ ስራ እየገቡ ነዉ
የትብብር ስልጠና አፈፃፀም ለሰልጣኞች የትብብር ስልጠና ሊሰጡ የሚችሉ 77 የትብብር መስጫ ድርጅቶች ተለይተውና ውለታ ተፈርሞ

ወደ ተግባር የተገባ ሲሆን እስከ አሁን ድረስ ከ1060 ሰልጣኞች ውስጥ 1048 የሚሆኑ ሰልጣኞች ለትብብር ስልጠና እንዲሳተፉ ተደርጓል፡፡

የቀሩት በዚህ አካባቢ የትብብር መስጫ ድርጅት የሌለ ስለሆነ ነዉ፡፡

 የሙያ ብቃት ምዘና

የሙያ ብቃት ምዘና ቤደረጃውና በየሙያ ዓይነቱ የሚደረግ ሲሆን በዚህ በጀት ዓመት 2 ጊዜ ብቻ ምዘና የተደረገ ሲሆን የምዘና ስራ

ለማካሄድ የግብዓትና የመኪና ችግር በመኖሩ የተፈለገውን ያህል የምዘና ስራን ለማኬሄድ አልተቻለም፡፡ይሁን እንጂ በ2ዙር ምዘና የደረጃ

ደረጃ 204 ተመዛኞች የተመዘኑ ሲሆን በምዘናው ብቁ የሆኑ ደግሞ 165 ሲሆኑ አፈፃፀሙ 80.3.% ያህል ነው፡፡ የተመራቂ ምዘና ደግሞ 320

ተመዝነዉ 266 በምዘናዉ ብቁ የሆኑ ሲሆን አፈፃፀሙ 83.2.% ያህል ነዉ

በኮሌጃትን የአጫጭር ስልጠና በልብስ ስፌት፣ በመሰረታዊ ህንፃ ግንባታ እና በኮብልስቶን ስልጠና ወስደውና የሙያብቃት ምዘና በድምሩ

114 ተመዝነው 112 ተመዛኞች ብቁ ሆነዋል አፈፃፀሙ 98.2% ያህል ነው፡፡


• የሰልጣኝ ቁጠባ

• የቴ/ሙያ ሰልጣኝ ሁሉም የፕሮጀክቱን 20% እና በላይ መቆጠብ አለባቸው፡፡

• ምክንያቱም ነገ ከስልጠና ማግስት ተመርቆ ሲወጣ ወደ ስራ ሊገባ የሚችለው ገንዘብ ሲኖረው ነውና
ለቴ/ሙያ ሰልጣኝ ቁጠባ የውዴታ ግዴታ ነው፡፡ አሰልጣኝ መ/ራንና የገንዘብ ተቋማትም ግንዛቤ እየፈጠሩ
ማስቆጠብ አለባቸዉ ፡፡ሰው ስላለው ሳይሆን ተቸግሮም መቆጠብ እንዳለበት ሰፊ ግንዛቤ በመፍጠር
እያንዳንዱ ሰልጣኝ በየወሩ ቢያንስ ከ50 ብር በላይ እንዲቆጥቡ መደረግ አለበት፡፡ የዚህ አመት የሰልጣኝ
ቁጠባ እቅድ አፈፃፀም ስንመለከት እቅድ 392000 ክንውን 196180 ሲሆን አፈፃፀም 50.4% ያህል ነዉ
፡፡.
III የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ኤክ/አገ/ተግባር
የኢንዱስትሪ ኤ/ድጋፍ በሦስት ወረዳ ላሉ ኢንተ/ዞችንና አንቀሳቃሾችን በአራቱ የድጋፍ ማዕቀፍ እየተደረገ ያለ
ድጋፍ ሲሆን
እቅድ ክንውን አፈፃፀም
ለነባር ኢ/ፕራይዝ 217 195 89.8%
ለአዲስ ኢንተ/ዝ 27 10 37.3%
ለነባር ኢንተ/ዞች የተደረገው ድጋፍ በማንፋክቸሪንግ በግብረና እና በአገልግሎት ዘርፈ ብቻ ሲሆን በኮንስትራክሽን
ዘርፍ ወደ ስራ የገቡ ኢንተ/ዞች አነስተኛ በመሆናቸዉ የተፈለገዉን ያህል ድጋፍ መስጠት አልተቻለም፡፡

አዲስ ኢንተ/ዞችም በየወረዳው በበቂ ሁኔታ ተፈጥረው ስላልተሰጡን በብዛት መደገፍ አልተቻለም፡፡

.የካይዘን አሰራርን ያስቀጠሉ ነባር ኢንተ/ዞች በገጠርና በከተማ እቅድ 175 ክንውን 175 አፈፃፀም 100%

.በአዲስ ካይዘን የተገበሩ በገጠርና በከተማ ኢንተ/ዞች እቅድ 95 ክንውን 90 አፈፃ 94.8%
መረጃና ምክር ያገኑ ኢንተ/ዞች በከተማና በገጠር እቅድ 175 ክንወን 202 አፈፃፀም 115.4 %

ሞዴል ኢንተ/ዝ ፈጠራ በከተማና በገጠር እቅድ 7 ክንውን 12 አፈፃፀም 130%

የቴ/ሎጂ ልየታ በብዛት በከተማና በገጠር እቅድ 33 ውንውን 36 አፈፃፀም 109.7%

የተሸጋገረ ቴ/ሎጂ በዓይነት በገጠርና በከተማ እቅድ 3 ክንውን 20 አፈፃፀም 433.3%

የተሸጋገረ ቴ/ሎጂ በዓይነት በገጠርና በከተማ እቅድ 3 ክንውን 20 አፈፃፀም 433.3%

የተሸጋገረ ቴ/ሎጂ ብዛት በገጠርና በከተማ እቅድ 33 ክንውን 36 አፈፃፀም 109.7%

አብዥ ኢንተ/ዝ ፈጠራ እቅድ 4 ክንውን 3 አፈፃፀም 75%

በተሸጋገሪ ቴ/ሎጂ የፈራ ሀብት እቅድ 146812 ክንውን 112190 አፈፃፀም 76.9%
IV የተቋሙ አቅም ግንባታ ፡- የኮሌጁን የሰው ኃይል አቅም በመገንባት ረገድ ለ9 መ/ራን የረጀም ጊዜ ስልጠና ለ5 መ/ራን
የአጭር ጊዜ ስልጠና እና የልምድ ልውውጥ በማድረግ የመፈፀም አቅም ግንባታ ለመስራት ተሞክሯል .

.በሌላ በኩል የኮሌጁ መ/ራንና ድገፍ ሰጪ ሰራተኞች በመማማር መድረክ በየወሩ በእቅዳቸው መሰረት ውይይት በማድረግ
የመፈፀም አቅማቸውን ለማጎልበት ጥረት እየተደረገ ነው ፡፡

ሆኖም ለድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች የረጅም ሆነ የአጭር ጊዜ ስልጠና አለመሰጠቱ በእጥረት የሚጠቀስ ነው፡፡

የኮሌጁን ገፅታ ግንባታ በተመለከተ ፡-

- የኮሌጁን የወጪ በርና የኮለን ስራን ደረጃዉን በጠበቀና በጥራት እንዲሰራ ተደርጓል፡፡
- የኮሌጁን ዙሪያ አጥር በግንባታና በጋቢዮን ሽቦ የማጠር ስራ ተሰርቷል፡፡
- የኮሌጁን ግንባታ የቀለም ቅብ ብዙ ጊዜ ስለሆነው የተላላጠ ስለነበር በአዲስ በቀለም ቅብ የማደስ ስራ ተሰርቷል
- የኮሌጁን የፋይንንስ ስራዎች ፈጣንና ቀልጣፋ እንዲሆን በባንኮች እንዲሆን ተደርጓል፡፡
- አጠቃላይ ግቢውንና ሾፖዎችን በካይዘን አሰራር በማደራጀት ስራ ምቹ የማድረግ ስራ ተሰርቷል፡፡

 
የጥገና ስራ ፡
በኮሌጁ ያሉ የተለያዩ ማሽኖችንና የማሰልጠኛ ቁሳቁሶችን በመ/ራንና የመጠገን ስራ ተሰርቷል ፡፡

5 የእንጨት ስራ ማሽን 9 የልብስ ስፌት ማሽን 15 ኮምፒውተሮች 38 የተማሪ መቀመጫ ወንበሮችን እና የህውሐት
አሸባሪ ቡድን የሰባበራቸውን በርካታ በሮችን መስኮቶችንና ቁልፎችን በመ/ራን አማካይነት በመጠገን ወደ ነበረበት
ለመመለስ ጥረት ተደርጓል፡፡

በሌላም በኩል ከመ/ራን አቅም በላይ የሆኑ አንድ ፎቶ ኮፒ ማሽንና ሁለት ፕሪንተር ጨረታ በማዉጣት በባለሞያ
የማስጠገን ስራ ተሰርተል፡፡
• የተቋሙ አቅም በአሸባሪው የህውሐት ቡድን በከፍተኛ ደረጃ እንደተጎዳ የሚታወቅ ነው፡፡ ይህውም ለማሰልጠኛ የሚሆኑ
በርካታ ማሽኖችንና የእጅ መሰሪያዎችን የቢሮ ቁሳቁሶችን የኮሌጁን መኪና ጭምር ግምቱ ከ8 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት
የማሰልጠኛ ማቴሪያሎችን በመዝረፍና በመሰባበር የኮሌጁን አቅም በከፍተኛ ደረጃ አዳክሟል ፡፡ ይህን ተከትሎ የጉዳት መጠን
መረጃውን ለሚመለከተው አካል ለማድረስ የተሞከረ ቢሆንም እስከ አሁን በመንግስት በኩል የተደረገ /የተገኘ /ድጋፍ የለም
ማለት ይቻላል ፡፡ በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ከአልማዝ በም ፖሊ ቴ/ሙያ ኮሌጅ የተለያዩ ቁሳቁሶች ግምታቸው 35 ሺህ በላይና
ከዶ/ር ካል ቴ/ሙያ ኮሌጅ ግምታቸው 3ሺህ ብር በላይ የሚሆኑ ከመ/ሜዳ ከተማ አስተዳደር 50 የፕላስቲክ ወንበሮች የተገኙ
ሲሆን

• በግል ጥረት በተደረገ ሀብት የማፈላለግ ስራ ለንደን ሀገር ከሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጲያዊ ዜጋ አቶ ተፈሪ እሸቱ ከሚባሉ በጎ
አድራጊ ግለሰብ ከብዙ ውጣ ወረድና እንግልት ቡኋላ 23 ኮምፒውተሮች አንድ ፕሪንተርና አንድ ኔትወርክ ስዊች ድጋፍ
ተገኝቶ ወደ ኮሌጁ ገቢ ሆነዋል፡፡ ይህም በገንዘብ ሲተመን ከ480 ሺህ ብር በላይ የሚያወጡ የማሰልጠኛ ማቴሪያሎች ናቸው፡፡
ይህም ሆኖ ኮሌጁ ስልጠና የመስጠት ተግባሩን የአለውን ሀብትና ንብረት እንዲሁም በግዥ የማሰልጠኛ ማቴሪያሎች ለማሟላት ጥረት
በማድረግ ስልጠና ብዙም ሳያቋረጥና /ሳይጓተት/ ስልጠነውን በወቅቱ በማስጀመር ወደ ስራ ተገብቷል፡፡

የኮሌጁን ማህበረሰብ የስነ-ልቦና ጫና ለማቃለል ተደጋጋሚ ወይይትና የሻይ ቡና ፕሮግራም ጭምር በማዘጋጀት በጦርነቱ የደረሰብንን
የስነ- ልቦና ጫና በማቃለል መደበኛ ስራ እንዲቀጥል መደረጉ በጥሩ ጎን የሚጠቀስ ሲሆን ከተወሰዱት ንብረቶች ከ2 ኮምፒውተሮች
በስተቀር ሌላው ሊገኝ /ሊመለስ / ባለመቻሉ ሌላው በእጥረት የሚገለፅ ነው፡፡

የበጀት አፈፃፀም

እቅድ ክንዉን አፈፃፀም

መደበኛ በጀት 9 605 651 8 796 854 90.5 %

የውስጥ በጀት 6 186 273 3 360 567.83 50.6%


V.ዘርፍ ብዙ ጉዳዮች ፡-
--የሴቶችን ተጠቃሚነትና ተሳትፎ 50% ለማድረስ እቅድ ተይዞ 52.3 % ለማድረስ
ተችላል ፡፡

--ለ12 የአካል ጉዳተኛ ሰልጣኞች የመደገፍ ስራ ተሰርተል ፡፡

--ኤች አይቪ ፀረ -ኤድስ እና ኮሮናን ለመከላከል የግንዛቤ ፈጠራ ስራ ተሰርተል ፡፡

--የኢኮኖሚ ችግር ላለባቸው ከ20 በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች እና ለህልውና ዘማች


ቤተሰቦች ነፃ የትም/ት እድል ተሰጥቷል፡፡
--የአፍሪካ የህፃናት ቀን በወረዳ ደረጃ በሚከበርበት ወቅት የኢኮኖሚ ችግር ላለባቸው
ከ65 በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች የተለያዩ አልባሳት ከኮሌጁ በድጋፍ ተሰጥቷል፡፡
ያጋጠሙ ዋና ዋና ችግሮች

- 133412 ብር የ3ዓመት የ3 ፌዝ ቆጣሪ ክፍያ


- የአውቶና ሰርቨይንግ ዲ/ት የተግባር ማሰልጠኛ ማቴሪያል አለመኖሩ
- ኢንዱስትሪያል የልብስ ስፌት እጥረት
- ለአጥር ስራና ቆርቆሮ በቆርቆሮ የመማሪያ ክፍል ወደ ህንፃ ለመቀየር የበጀት እጥረት
ኮሌጁን ወደ ፖሊ ቴ/ሙያ ኮሌጅ ለማሳደግ
- ለምዘናም ሆነ ድጋፍ ለማሰባሰብ የመኪነና ችግር
- የወቅቱ ገበያ ባለመረጋጋቱ ምክንያት የማሰልጠኛ ማቴሪያል በተፈለገው ልክ በግዥ
ማሟላት አለመቻሉ
 

You might also like