You are on page 1of 19

በፌ/ቴ/ሙ/ት/ሥ/ኤጀንሲ ምህንድስና ብቃት ማዕከል

የብሄራዊ ብየዳ ማሰሰልጠኛ ቡድን


2010 በጀት ዓመት ሚዛናዊ የውጤት ተኮር ዕቅድ

መጋቢት 2009
ዓ.ም
አዲስ አበባ

የብሄራዊ ብየዳ ማሰልጠኛ ቡድን የ 2010 በጀት ዓመት የሚዛናዊ የውጤት ተኮር ዕቅድ ገጽ - 1
ማውጫ

1. መግቢያ.........................................................................................................3

2. የዓመቱ ጠንካራ ጎኖች፣ ደካማ ጎኖችና፣ ትንተና ...........................................4

2.1 ጠንካራጎኖች....................................................................................4
2.2 ደ.ካማ ጎኖች......................................................................................4
2.3 የድክመቶች ትንተና..........................................................................5

3. በቀጣይ ትኩረት የሚደረግባቸው ተግባራት..................................................5

4. የብየዳ ማሰልጠኛ ማዕከል ዕቅድ ዓላማና፣ ዋና ዋና ግቦች.............................6

4.1 ዋና ዓላማ.......................................................................................6
4.2 ዝርዝር ላማዎች................................................................................6
4.3 ዋና ዋና ግቦች.....................................................................................7

5. የብየዳ ማሰልጠኛ ቡድን የሁለተኛው ዕ/ት/ ዕቅድ ግቦች...............................8

6. የብየዳ ስልጠና የመፈፀም አቅም...............................................................9

7. የብየዳ ማሰልጠኛ ቡድን የ 2010 ዓ.ም ዕቅድ ዋና ግቦችና ተግባራት.............10

8. የማስፈጸሚያ ስልቶች..........................................................................12

9. የ 2010 በጀት ዓመት ዕቅድ...................................................13

የብሄራዊ ብየዳ ማሰልጠኛ ቡድን የ 2010 በጀት ዓመት የሚዛናዊ የውጤት ተኮር ዕቅድ ገጽ - 2
1. መግቢያ

የብረታብረትና ኢንጅነሪንግ ንዑስ ዘርፍላይ በማኑፋክቸሪንግ እና ኮንስትራክሽን የብየዳ ሙያን ዓለም


በደረሰበት የክህሎት ደረጃ ለማድረስ ኤጀንሲው በምህንድስና ብቃት ማዕከል የብሄራዊ ብየዳ ማሰልጠኛ ቡድን
በማቋቋም በዓለም አቀፍ ደረጃ በብየዳ በክልልና ከተማ መስተዳድር ለሚመጡ መሪ አሰልጣኞች የአቅም
ግንባታ ስልጠና በመስጠት ላይ መሆኑ ይታወቃል፡፡

በብየዳ ማሰልጠኛ ማዕከሉ 13 ሰራተኞችን ያሟላ ሲሆን የብየዳ ማሰልጠኛ ማዕከሉ ከብረታ ብረትና
ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ጋር በመቀናጀት ከ 2004 ሚያዚያ ወር ጀምሮ 80 የኦሮሚያ ክልል
አሰልጣኞችን በመሰረታዊ የብየዳ ስልጠና ያሰለጠነ ሲሆን 415 ሙያተኞችን በመሰረታዊ ብየዳ ላይ
በማብቃት ወደ ህዳሴ ግድብ ተሰማርተው የሚጠበቅባቸውን አስተዋጽኦ እንዲያበረክቱ ማድረግ
ተችሏል፡፡

የብየዳ ማዕከሉ የወርክሾፕ አደረጃጀቱን በማጠናከርና በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ሰርቲፋይድ በሆኑ 4 የዌልዲንግ
ማስተሮቹ በመጠቀም 38 የሚሆኑ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት አሰልጣኞች እናየብረታ
ብረትና ኢንጅነሪንግ ኮርፖሬሽን ሙያተኞችበማሰልጠን በጀርመን ከፍተኛ ኤክስፐርቶች (መዛኞች)
ብቃታቸውን በማረጋጋጥ ሰርቲፋይድ ዌልደር እንዲሆኑ ማድረግ ተችሏል፣ ፡፡ እንዲሁም በ 2008
ዓ.ም 53 እና በ 2009 ዓ.ም 48 የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት አሰልጣኞች ስልጠናቸውን
ጨርሰው 65 ሰልጣኞች ተመዝነው ሙሉ በሙሉ አልፈዋል፡፡

በብየዳ አቅም ግንባታ በቀጣይ አሰልጠኞችን እስከ ብየዳ ኢንጂነር ደረጃ በማብቃት ማዕከሉን በዓለም
አቀፍ ደረጃ ዕውቅና እንዲያገኝ የማድረግና በተመረጡ ክልሎች ቅርንጫፍ ማዕከላትን የማደራጀትና
ወደ ሥራ እንዲገቡ የማድረግ፣ በብየዳ ሙያ ላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ ሰርቲፋይድ የሆኑ ብዛት
ያላቸውን ብቁ በያጆች (ዌልዲንግ ማስተሮችን/መሪ አሰልጣኞችንና ኢንጂነር ደረጃ) የማፍራት፣
ስራዎችን ተግባራዊ በማድረግ ማዕከሉ ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያለው ሰርቲፊኬት የመስጠት አቅም
እንዲኖረው ርብርብ ይደረጋል፡፡

2. የዓመቱ ጠንካራ ጎኖች፣ ደካማ ጎኖችና፣ ትንተና

2.1 ጠንካራ ጎኖች


 የቴክኖሎጂ ሰራዊት ግንባታ አደረጃጀት መፈጠሩና ግንባታው በተሻለ ሁኔታ መጀመሩ፣
 የብየዳ ስልጠና በታቀደው መሠረት ባልተሟላ ግብዓትና ሴፍትም ቢሆን መተግበሩ

የብሄራዊ ብየዳ ማሰልጠኛ ቡድን የ 2010 በጀት ዓመት የሚዛናዊ የውጤት ተኮር ዕቅድ ገጽ - 3
 የቅበላ አቅማችንን ተጨማሪ የመበየጃ ስቴሽኖችን በመስራት ከ 20 ወደ ሰላሳ ማሳደግ መቻሉ፣
 ጀርመን አገር ከሚገኘው SLV Mannheim የብየዳ ኢንስቲትዩት ጋር ተቋርጦ የነበረውን ግንኙነት
መጀመርና የመግባቢያ ሰነድ መፈራረም እና ወደ ሰርቲፊኬሽን መስመር እንዲገቡ በማድረግ 65
ስልጣኞችን በማስፈተን ሙሉ በሙሉ (Certified) ማድረግ ተችሏል

2.2 ደካማ ጎኖች

 የለውጥ መሳሪያዎችን በእምነት ይዞ በቁርጠኝነት አለመተግበር


 ለብየዳ የስልጠና ቡድን ለሰራተኛ የሚያስፈልጉና በግዢ ገቢ እንዲሆኑ የተጠየቁ የማሽን፣ ጥሬ እቃና
የሌሎች ግብዓቶች አቅርቦቶች ባለመግባታቸው ስራዎችን በታቀደው ጥራትና መጠን ለመተግበር
ማነቆ መሆኑና በሠራተኞች ዘንድ ቅሬታ መፍጠሩና በስልጠናው ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ መፍጠሩ፤
 የመንግስት ስራ ሰዓት መሸራረፍ
 የተግባራት ስታንዳርዶች ተሟልተው ባለመዘጋጀታቸው አፈጻጸሞችን ለመለካት ችግር መፍጠሩ፣
 በወርክሾፕ ውስጥ ባለው ጥገና ምክንያት የስልጠና ሂደት ላይ መቆራረጥ መፍጠሩ
 ከፍተኛ የውሃ እጥረት በመኖሩ በሰልጣኞችና ሰራተኛ ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታ መፍጠሩ

2.3 የድክመቶችትንተና፤

በአመለካከት
 የቴክኖሎጂ ሠራዊት መገንባት የሚያስችሉ የመተጋገሉ መንፈስ አነስተኛ መሆን፣
 የአጋር ድርጅቶች በገቡት ቃል መሠረት የሚጠበቀው ደረጃ ላይ ሳያደርሱ ባልታወቀ ሁኔታ
ማቋረጣቸውና ለዚህ ተገቢ ትኩረት አለመሰጠቱ፤
 የኪራይ ሰብሳቢነት አመለካከት (በሥራ ቦታ ከተገኙ በኋላ የመንግስትን የስራ ሰዓት መሸራረፍ፣ በተግባር
ያልሰሩትን ከፍተኛ ውጤት የመፈለግ፣ ግምገማን በጥሩ ጎኑ ተቀብሎ ድክመቶች ላይ ለመስራት አለመፈለግ፤

ግምገማን በአሉታዊ ነገር መፈረጅ ወዘተ…) የተጠበቀውን ያህል ቀንሶ አለመታየቱ፤

 የግምገማና ክትትል ማነስ፤


በክህሎት
 በለውጥ ስራዎች ትግባራ ላይ ክፍተት መኖሩ
 ፈጻሚዎች የተግባሮቻቸውን ስታንዳርድ የማዘጋጀት የክህሎት ክፍተት መኖሩ

የብሄራዊ ብየዳ ማሰልጠኛ ቡድን የ 2010 በጀት ዓመት የሚዛናዊ የውጤት ተኮር ዕቅድ ገጽ - 4
በግብዓት
 ለብየዳ ስልጠና የሚያገለግሉ ግብዓቶችን በግዢ ገቢ ለማድረግ ከፍተኛ ክትትልና ድጋፍ
ቢደረግም የሚጠበቀው ያህል ገቢ ማድረግ አለመቻሉ
በአደረጃጀት
 ማዕከሉ እንደ ማንኛውም የማሰልጠኛ ተቋም እራሱን ችሎ እና በደጋፊ ክፍል ባለመደራጀቱ
የስልጠና ሂደቱ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ መፍጠሩ

3. በቀጣይ ትኩረት የሚደረግባቸው ተግባራት

 የሰራዊት ግንባታ ስራዎች ያለመቆራረጥ እንዲሰሩ ማድረግ


 ያልተጠናቀቁ የፈጻሚ የአቅም ግንባታ ስራዎች ማከናወን
 ከትኩረት ዘርፎች መሪ መ/ቤቶችና ከሕዝብ ክንፍ ጋር ወደ ስራ መግባት
 በክልል አለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ የብየዳ ስልጠና እንዲሰጥ ድጋፍና ክትትል ማድረግ
 ከአውሮፓ የብየዳ ማህበር ጋር በቀጣይ የምንሰራበት ስልት በመቀየስና ግንኙነት መፍጠር
 የብየዳ ማሰልጠኛ ማዕከሉ ደረጃውን በጠበቀ መልኩ የማደራጀት ስራ መቀጠል
 በክልሎችተጨማሪ የብየዳ ማሰልጠኛ ማዕከላት እነዲቋቋሙ ድጋፍ ማድረግ
 ጀርመን አገር ከሚገኘው SLV Mannheim የብየዳ ኢንስቲትዩት ጋር የሰርቲፊኬሽን ስራ
ማከናወን
 የብየዳ ኢንጅነሪንግ ስልጠና ማሰጠት፡፡
 የብየዳ ማስተር ስልጠና መስጠት፡፡
 የአቅም ግንባታ ስራዎችን ማከናወን በውስጥ ስልጠና አቅም መገንባት፤
 በተለዩት የኪራይ ሰብሳቢነትና የመልካም አስተዳደር ችግሮች ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት፡፡
 የብየዳ ማሰልጠኛ ማዕከሉን መረጃ አያያዝ አጠናክሮ መቀጠል
 የግዢ ሂደቱ ላይ ክትትልና ድጋፍ ማድረግ

የብሄራዊ ብየዳ ማሰልጠኛ ቡድን የ 2010 በጀት ዓመት የሚዛናዊ የውጤት ተኮር ዕቅድ ገጽ - 5
4. የብየዳ ማሰልጠኛ ማዕከል ዕቅድ ዓላማና፣ ዋና ዋና ግቦች

4.1) ዋና ዓላማ

 በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ከፍተኛ ቴክኖሎጂዎችን የማምረት፣ አቅም የመፍጠርና በዘርፉ ለተሰማሩ አነስተኛ፣ መካከለኛና
ከፍተኛ ኢንተርፕራይዞች የብየዳ ስልጠና በመስጠት ገቢ ምርቶችን የመተካት አቅም በመገንባት በገበያ ተወዳዳሪነታቸውን
ማሳደግ፣

4.2) ዝርዝር ዓላማዎች

 በብረታ ብረት ዘርፍ ለተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች ዓለም አቀፍ ዕውቅና ያላቸው ብቁ የብየዳ ባለሙያዎች
ለማቅረብ እንዲችሉ የቴ/ሙ/ተቋማትንና የኢንዱስትሪ አሰልጣኞችን በብየዳ ቴክኖሎጂ ዓለም በደረሰበት
የክህሎት ደረጃ ለማድረስ አቅም መገንባት
 በሳታላይት የብየዳ ስልጠና እንዲሰጡ የተቋቋሙ የማሰልጠኛ ተቋማትን አቅም የመገንባትና ድጋፍና
ክትትል የማድረግ
 በኢንተርናሽና ደረጃ የብየዳ አሰልጣኞችን(Welding Specialist) ማፍራት

4.3) ዋና ዋና ግቦች

1. ብቁ በያጆችን (Certified Welders) ለማፍራትበክልሎች የተደራጁ 6 ተቋማት፣


2. በአለም አቀፍ ደረጃ የበቁ 4 ዌልዲንግ ኢንጂነሮች፣
3. በብየዳ አሰልጣኝነት በዓለም አቀፍ ደረጃ የበቁ 26 አሰልጣኞች (Certified Welding Teachers)፣
4. በዓለም አቀፍ ደረጃ ብቁ የሆኑ በማዕከል 120 በክልል ተቋማት 540 በያጆች (Certified Welders)፣

የብሄራዊ ብየዳ ማሰልጠኛ ቡድን የ 2010 በጀት ዓመት የሚዛናዊ የውጤት ተኮር ዕቅድ ገጽ - 6
5. የብየዳ ማሰልጠኛ ቡድን የሁለተኛው ዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ግቦች

መለ ኪያ መነሻ ግቦች
ተ. ቁ አመላካቾች ዓመት
2007 2008 2009 2010 2011 2012 2017
1. ብቁበያጆችንለማፍራትየተደራጁተቋማት(Welding Centers)፣ ቁጥር 1 1 4 6 7 8 13

2. በብየዳአሰልጣኝነትበዓለምአቀፍደረጃየበቁአሰልጣኞች (Certified Welding ቁጥር 0 20 40 55/26 80 105 210


Teachers)፣

3. በአለምአቀፍደረጃየበቁዌልዲንግኢንጂነሮች (Welding Engineers)፣ ቁጥር 0 0 4 4 4 4 15

4. በዓለምአቀፍደረጃብቁየሆኑበያጆች (Certified Welders)፣ ቁጥር 40 80 580 1600 2800 4,000 10,000

የብሄራዊ ብየዳ ማሰልጠኛ ቡድን የ 2010 በጀት ዓመት የሚዛናዊ የውጤት ተኮር ዕቅድ ገጽ - 7
6. የብየዳ ስልጠና የመፈፀም አቅም

በኢትዮጵያ በተደረገ ጥናት እስከ አስር አመት ድረስ ወደ 10000 (አስር ሽህ) በኢንተርናሽናል ደረጃ ሰርቲፋይድ ወይም ብቁ የሆነ በያጅ እንደሚያስፈልግ ተገልጧል፡፡
በዚህም መዘረት ከ 2008 ዓ/ም ጀምሮ በወጣው የ 2 ኛውና የ 3 ኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ውስጥ ይህንን አስር ሽህ ብቁ በያጅ እንዲፈራ በእቅድ
ተቀምጦ ስራ ተጀምሯል፡፡ ይህም እስከ 2012 ዓ/ም 4000 የሚሆነውን ሰርቲፋይድ በያጅ ማፍራት ሲሆን ቀሪውን ደግሚ እስከ 2017 ዓ/ም መፍራ እንዳለበት በእቅድ
ተይዟል፡፡

ይሁንና እስከ በኢንተርናሽናል ደረጃ የሚሰጠጥ ሰርቲፋይድ ወይም ብቁ በያጅ ለማፍራ የብየዳ ስልጠናው ስድስት ሞጁሎችን የሚይዝ ሲሆን ይህንን የብየዳ ስልጠና
ለመስጠት በህጉ መሰረት በትንሹ የብየዳ ስፔሻሊስት(Welding Specialist) ደረጃ ወይም የብየዳ ማስተር(Welding Teacher) መሆን እንዳለበት ተቀምጧል፡፡

ይሁን እንጂ በአሁኑ ሰዓት እዚህ ደረጃ ላይ ወይም የብየዳ ማስተር(Welding Teacher) ላይ የደረሱ በሀገሪቱ አራት የብየዳ አሰልጣኞች ብቻ ናቸው፡፡

የብየዳ ስልጠና ሂደቶችና የሚሰ,ወስዱት አማካኝ የስልጠና ሰዓት

ተ/ቁ የስልጠና በአርክ የብየዳ ሂደት ማግ የብየዳ ሂደት ቲግ የብየዳ ሂደት


ሞጁል
1 ሞጁል 1 90 ሰዓት 90 ሰዓት 50 ሰዓት
2 ሞጁል 2 50 ሰዓት 90 ሰዓት 50 ሰዓት
3 ሞጁል 3 75 ሰዓት 75 ሰዓት 50 ሰዓት
4 ሞጁል 4 75 ሰዓት 75 ሰዓት 50 ሰዓት
5 ሞጁል 5 75 ሰዓት 75 ሰዓት 50 ሰዓት
6 ሞጁል 6 75 ሰዓት 50 ሰዓት 50 ሰዓት
ድምር ሰዓት 440 ሰዓት(76 ቀን ወይም 455 ሰዓት(74 ቀን 300 ሰዓት (50 ቀን 9
16 ሳምንት) ወይም 14 ሳምንት) ሳምንት)

በአማካይ ይህንን የብየዳ ስልጠና ለመስጠት እንደ ስልጠና ሂደቱ የሚለያይ ሆኖ ከ 3 ወር እስከ አራት ወር ይወስዳል፡፡ ይህ ማለት በአመት እስከ ሶስት ዙር ድረስ እስከ
ሞጁል ስድስት ያለውን የብየዳ ስልጠና መስጠት የሚቻል ሲሆን የምዘና ጊዜን አያካትትም፡፡ ስልጠናው ስታንዳርድ አንድ ማሽን ለአንድ ሰው ነው ፡፡

እንደ ማዕከል ከዚህ መነሻ በመነሳት አሁን ያለውን 30 የብየዳ ስቴሽን ወደ አርባ በማሳደግ በአመት ሶስት ጊዜ ስልጠናውን መስጠት ቢቻል 120 ብቁ በያጆችን በአንድ
አመት ውስጥ ማፍራት ይቻላል፡፡

የብሄራዊ ብየዳ ማሰልጠኛ ቡድን የ 2010 በጀት ዓመት የሚዛናዊ የውጤት ተኮር ዕቅድ ገጽ - 8
በክልል ደረጃ ሁሉም ግብዓት ተማልቶ ወደ ስልጠና የሚገቡ ተቋማት ስድስት ቢሆኑ እና እያንዳንዳቸው በአንድ ዙር 30 ሰልጣኞችን ማፍራት የሚችሉበት ደረጃ ላይ
ደርሰዋል ቢባል አንድ የብየዳ ስልጠና ተቋም 90 ሰልጣኖችን ማፍራ ይችላል፡፡ ስድስት ተቋማት ደግሞ 540 ብቁ በያጆችን ማፍራት ይችላሉ፡፡ ይህ ደግሞ ወደ 660
ሰልጣኞችን እንደሃገር በአንድ አመት ማፍረት ይቻላል፡፡

ነገር ግን በክልሎች እንዳየነው የስልጠና ግብዓት የማሽነሪና የሰው ሃይል እጥረት እንዳለበቸው በአካል ተገኝተን ያረጋገጥነው ነው፡፡

ስለዚህ በቅርብ የሚሰጠው የሰርቲፊኬሽን ስራ ላይ የሚመዘኑ በሞጁል አራት ላይ ወደ 70 የሚጠጉ ሲሆን ቀሪዎች ወደ 25 የሚሆኑት በሞጁል ስድስት ምዘናቸውን
ያከናውናሉ፡፡

ስለዚህ ከላይ የተቀመጠው ከምዘና በኋላ እስከ ሞጁል ስድስት ያጠናቀቁትን ወደ ብየዳ ማስተር ስልጠና ማብቃትና በክልል የሚሰጠውን የብየዳ ስልጠና እንዲመሩ
ማስቻል ይጠይቃል፡፡ ቀሪዎችን ደግሞ በቀጣይ ዙር የፓይፕ ስልጠና እንዲወስዱ በማድረግ ብቃታቸውን እንዲያረጋግጡ በማድረግ እንደ ሃገር የተቀመጠውን ግብ
ማሳካት ይቻላል፡፡

በአጠቃላይ በዚህ የብየዳ ስልጠና ላይ ከላይ ባስቀመጥነው የመፈፀም አቅም መሰረት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅዱ ሚስተካከልበት ሁኔታ መፈጠር አለበት፡፡

7. የብየዳ ማሰልጠኛ ቡድን የ 2010 ዓ.ም ዕቅድ ዋና ግቦችና ተግባራት

ግብ 1. የዓለም አቀፍ የብቃት ደረጃ ያሟሉ ብቁ በያጆችን ማፍራት የሚችሉ 6 የብየዳ ማሰልጠኛ ተቋማትን (Welding Centers) ማደራጀት፣

 የዌልዲንግ ማሰልጠኛ ማዕከላት ማሟላት የሚገባቸውን መስፈርት (ISO 9606) በመጠቀም ማዕከላቱ እንዲደራጁ ድጋፍ ማድረግ፣
 የዓለም አቀፉን መመዘኛ ያሟሉ ማዕከላትን ገምግሞ በአለም አቀፍ የብቃት ደረጃ ሙያተኞችን ማፍራት የሚችሉ መሆናቸውን
በማረጋገጥ ስልጠና እንዲጀምሩ ማድረግ፣

ግብ 2. በብየዳ ቴክኖሎጂ ብቁ በያጆችን ማፍራት የሚችሉ የማዕከሉን ጨምሮ 30 አሰልጣኞች በዓለም አቀፍ ደረጃ ለዌልዲንግ አሰልጣኝነት (Certified
Welding Teachers) ማብቃት፣

 በአውሮፓ ብየዳ ፌዴሬሽን ጋይድላይን የተቀመጠውን የብየዳ አሰልጣኞች የብቃት ማዕቀፍ መነሻ በማድረግ የማዕከሉን የአሰልጣኞች
ብቃት ማዕቀፍ ማዘጋጀት፣
 ከማንሃይም ኢንስቲትዩት በሚደረግ ቴክኒክ ድጋፍ ቀድመው የሰለጠኑትን ጨምሮ 55 የአሰልጣኞችን ብቃት ማረጋገጥና ሰርቲፋይድ
እንዲሆኑ ማድረግ፣
ግብ 3. በዓለም አቀፍ ደረጃ ብቁ የሆኑ 4 ከፍተኛ የብየዳ ኢንጂነሮች (welding Engeeners)

የብሄራዊ ብየዳ ማሰልጠኛ ቡድን የ 2010 በጀት ዓመት የሚዛናዊ የውጤት ተኮር ዕቅድ ገጽ - 9
 በአውሮፓ ብየዳ ፌዴሬሽን ጋይድላይን የተቀመጠውን የብየዳ ኢንጂነሮች የብቃት ማዕቀፍ መነሻ በማድረግ የማዕከሉን አሰልጣኞች
ብቃት ማዕቀፍ ማዘጋጀት፣
 በጀርመኑ ኤስ ኤል ቪ ማንሃይም ኢንስቲትዩት ቴክኒክ ድጋፍ የማዕከሉን ዌልዲንግ ማስተሮች በስነማሰልጠን ዘዴ ማብቃት የሚችሉ
የአገር ውስጥ ዩኒቨርስቲዎችን መለየት፣
 በተዘጋጀው የአሰልጣኞች ብቃት ማዕቀፍ መሰረት ከተመረጠው ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር የአለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ማብቂያ
(ማሰልጠኛ) ካሪኩላ መቅረጽ፣
 የጋራ ስምምነት በመፈጸም የአሰልጣኞችን ስልጠና በሀገር ውስጥና በውጪ ማከናወን፣

ግብ 4 በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ዘርፍ ከኢንዱስትሪውና ከቴ/ሙ/ት/ስ/ ተቋማት የተውጣጡ 120 ሰልጠኞች በማዕክሉ 540/1600 ደግሞ በተመረጡ
የሳታላይ የብየዳ ስልጠና ተቋማት ብቁ በያጆችን (Certified Welders) ማፍራት፣

 ከዘርፉ መሪ ኢንዱስትሪ ጋር በመቀናጀት የአውሮፓ ብየዳ ፌዴሬሽን ጋይድላይን ቤንችማርክ በማድረግ የአገራችን የብየዳ ሙያ ደረጃ
እንዲዘጋጅ ማድረግ፣
 በተዘጋጀው ሙያ ደረጃ መሰረት የማሰልጠኛ ስርዓተ ስልጠናና ተያያዥ መርጃ መሳሪያዎች (ቢጋሮች፣ ማኑዋሎች፣ ስታንዳርዶች)
ማዘጋጀት፣
 ለስልጠናው የሚያስፈልጉ ግብዓቶች (ዎርክሾፕ አደረጃጀት፣ ማሽነሪዎች ጥገና፣ ጥሬ ዕቃዎች አቅርቦት፣ የደኅንነት መጠበቂያ
መሳሪያዎች) ማሟላት፣
 በቀጣይ በዘርፉ አቅም የሚገነቡ ሙያተኞችና አሰልጣኞች በዘርፉ ከተሰማሩ ኢንዱስትሪዎችና የቴ/ሙ/ት/ስ/ ተቋማት መለየት፣
 በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት ስልጠናውን ማከናወን፣
 በማጠናቀቂያ የሙያተኞችን ብቃት በዓለም አቀፉ ደረጃ መድረሱን በመመዘን ማረጋገጥ፣
 ብቃታቸው ለተረጋገጠ በያጆች የአለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና እንዲያገኙ ማድረግ፣

8. የማስፈጸሚያ ስልቶች

 የትኩረት ዘርፎች ባለድርሻ አካላት በፕሮጀክቱ ላይ ያላቸውን ሚና በማስገንዘብና በጋራ ዕቅድ በማሳተፍ የሚጠበቅባቸውን ሚና እንዲወጡ ማድረግ፣

የብሄራዊ ብየዳ ማሰልጠኛ ቡድን የ 2010 በጀት ዓመት የሚዛናዊ የውጤት ተኮር ዕቅድ ገጽ - 10
 ለብየዳ ስልጠናን አለም ዓቀፍ ደረጃ ሰርቲፊኬት በሀገር አቅም መስጠት እስክቻል ድረስ ፍቃደኛ ወይም በአጋር ድርጅቶች ድጋፍ በየውጪ ባለሙያዎች
እንዲያበቁ ማድረግ
 በክልልና ከተማ መስተዳድር የሚገኙትን የተመረጡት ቴ/ሙ/ት/ስ/ ተቋማት የብየዳ ማሰልጠኛ ተቋም እንዲያቋቁሙ በሚዘጋጁ መስፈርቶች መሰረት ፍተሻ
በማካሄድ መገምገምና መለየት፣
 የብየዳ ሥልጠናው የመጀመሪያው የትኩረት አቅጣጫ በምህንድስና ልህቀት ማዕከል በሚገኘው ብሔራዊ የብየዳ ማሠልጠኛ ኢንስቲትዩት አማካይነት ከየክልሉ
ቴ/ሙ/ት/ስ/ ተቋማትተመልምለውለሚመጡየማኑፋክቸሪንግመሪአሰልጣኞች የአሰልጣኞች /multipliers/ ሥልጠናመስጠትነው፡፡
 የብየዳ ቴክኖሎጂ በኢንዱስትሪው ዘርፍ ያለውን ሚናና አተገባበር የሚገልጽ የክልል የቴ/ሙ/ት/ስ/ አስፈጻሚ አካላት ወርክሾፕ በማዘጋጀት ክልሎች ለትግበራ
ዝግጁ የሚሆኑበትን ሥርዓትና ሃላፊነታቸው ምን መምሰል እንዳለበት ግንዛቤ በማስያዝ ከዝግጅት እስከ አፈፃፀም የሚኖራቸውን ሚና በመንደፍና የጋራ ዕቅድ
በማዘጋጀት ወደ ትግበራ የሚገባበት ስልት መንደፍ፣
 የብየዳ ቴክኖሎጂ ሥልጠናውን ለማከናወን በምህንድስና ልህቀት ማዕከል የተደራጀውን ብሔራዊ የብየዳ ማሠልጠኛ ኢንስቲትዩት አደረጃጀት መልካም ተሞክሮ
በተለይም የወርክሾፕ አደረጃጀትና ሌይአውት፣ የስልጠና ጋይድላይን፣ የማሰልጠኛ ማቴሪያሎች አደራጅቶ ለክልሎች በማድረስ በተመረጡ የብየዳ ማሰልጠኛ
ተቋማት እንዲተገበሩት ማድረግ፣
 ለብየዳ ቴክኖሎጂ ሥልጠናው የሚያስፈልጉ ግብዓቶች /Resource & consumables/ በዝርዝር በማዘጋጀትና ማሽነሪዎቹም በየደረጃው እንዲዘጋጁ በማድረግ
ስልጠናው ውጤታማ እንዲሆን ማድረግ፣ ለዚህም ዝርዝር መረጃዎች ለክልሎችና ሥልጠና ለሚሰጡ ተቋማት እንዲደርስ ማድረግ፡፡ እነዚህ ማሽነሪዎች ተቋማት
ካሉዋቸው በተጨማሪ የሚደራጁና ስታንዳርዱን እንዲጠብቁ የሚያስችሉ ይሆናል፤፤

የብሄራዊ ብየዳ ማሰልጠኛ ቡድን የ 2010 በጀት ዓመት የሚዛናዊ የውጤት ተኮር ዕቅድ ገጽ - 11
የአቶ አስመራው ቶሎሳ 2010 በጀት ዓመት ዕቅድ
የሚፈጸምበት ሩብ
ዓመት

የአፈጻጸም መነሻ

የ 2010 ዒላማ
የአፈጻጸም ስታንዳርዶች
ስትራቴጂክ

ለግቡና

መለኪያ
ተግባሩ ፈጻሚ
ግብ

የታቀዱ ተግባራት የተሰጠ የግብና ተግባር ውጤት


አካል
ክብደት 1ኛ 2ኛ 3 4ኛ መጠን ጥራት ጊዜ ወጪ

I. ተገልጋይ /ዜጋ (62%)

የተገልጋይ ዕርካታን ማሳደግ (የቴክኖሎጂና


3                      
ብየዳ አገልግሎት ተጠቃሚዎች)
የተገልጋይ እርካታን ማሳደግ

50 75 የብየዳ
1.1. በስታንዳርዱ መሰረት አገልግሎቱን በስታንዳርድ መሰረት የተሰጠ
1 መቶኛ 80 90 25 100 100 100 በአመት   ቡድን
መስጠት አገልግሎት

2 3
1.2. በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ግብረ መልስ
የተሰበሰበ ግብረ መልስ አስመራ
በማሰባሰብና በማደራጀት የተገልጋይ 1.5 በየሞጁሉ ማጠናቀቂያ
ቁጥር 1 4 1 4 4 100 በአመት  
እርካታ መለካት
የብየዳ
1.

1.3. ከተገልጋዮች በተገኘ ግብረ መልስ የተሸሻለ የአገልግሎት ቡድን


0.5 መቶኛ 100 50 100 2 100 ዓመት  
የአገልግሎት ስታንዳርዱን ማሻሻል ስታንዳርድ

ያደገ ብቁ የሰው ሃይል አቅርቦት 38                      


አቅርቦትን ማሳደግ

5 በዓለም አቀፍ ደረጃ ቁጥር 0 20 20 1 100 ዓመት አስመራ


ብቁ የሰው ሃይል

2.1. በብየዳ ስልጠና ብቁ በያጆችን ማፍራት


ብቃታቸው የተረጋገጠ
የሚችሉ የክልል ሳትላይት አሰልጣኞች የዌልዲንግ አሰልጣኞች
በዓለም አቀፍ ደረጃ ለዌልዲንግ
አሰልጣኝነት (Certified Welding
Teachers) ማብቃት፣
2.

የብሄራዊ ብየዳ ማሰልጠኛ ቡድን የ 2010 በጀት ዓመት የሚዛናዊ የውጤት ተኮር ዕቅድ ገጽ - 12
የሚፈጸምበት ሩብ
ዓመት

የአፈጻጸም መነሻ

የ 2010 ዒላማ
የአፈጻጸም ስታንዳርዶች
ስትራቴጂክ

ለግቡና

መለኪያ
ተግባሩ ፈጻሚ
ግብ

የታቀዱ ተግባራት የተሰጠ የግብና ተግባር ውጤት


አካል
ክብደት 1ኛ 2ኛ 3 4ኛ መጠን ጥራት ጊዜ ወጪ

2.2. በብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ዘርፍ 30 60


ከኢንዱስትሪውና ከቴ/ሙ/ት/ስ/
በዓለም አቀፍ ደረጃ የሰለጠኑ አስመራ
ተቋማት የተውጣጡ ሰልጠኞች በአለም 28 በያጆች
  48 120 90 120 4 100 ዓመት
አቀፍ ደረጃ ብቁ በያጆችን (Welders)
ማሰልጠን፣
135 270
2.3. በክልል ቴ/ሙ/ት/ስ/ ተቋማት የሚሰጡ በዓለም አቀፍ ደረጃ
ብቁ በያጆችን (Welders) ስልጠናን 3 እነዲሰለጥኑ የተደረገ ቁጥር 0 540 405 540 8 100 ዓመት
እንዲሰጥ መከታተልና መደገፍ ከትትልና ድጋፍ
የትምህርትና ስልጠና

የተሻሻለ የትምህርትና ስልጠና ውጤታማነት 11                    


ውጤታማነት

10 20
ማሻሻል

3.1. የብየዳ ማሰልጠኛ ማዕከሉ በ ISO


የብየዳ
ስታንዳርድ አለም አቀፍ አውቅና በአለም አቀፍ አውቅና
2 መቶኛ 0  50 35 50 1 100 ዓመት   ስልጠና
እንዲኖረው በማደራጀት 50% ደረጃ እንዲያገኝ የተደራጀ ተቋማ
ቡድን
እንዲደርስ ማድረግ
3.

የተሻሻለ የትምህርትና ስልጠና ፍትሓዊነት 1                      


ፍትሓዊነት ማሻሻል
ትምህርትና ስልጠና

4.1. በአለም አቀፍ ደረጃ ከሚሰለጥኑት


የብየዳ
በያጆች (Certified Welders) ውስጥ
1 የጨመረ የሴቶች ተሳትፎ መቶኛ 4 20 3 6 8 10 4 100 በዓመት   ስልጠና
የሴቶች በያጆችን ተሳትፎ 10 በመቶ ቡድን
ማድረስ
4.

የተሻሻለ የትምህርትና ሥልጠና ተደራሽነት 5                      


5.

የብሄራዊ ብየዳ ማሰልጠኛ ቡድን የ 2010 በጀት ዓመት የሚዛናዊ የውጤት ተኮር ዕቅድ ገጽ - 13
የሚፈጸምበት ሩብ
ዓመት

የአፈጻጸም መነሻ

የ 2010 ዒላማ
የአፈጻጸም ስታንዳርዶች
ስትራቴጂክ

ለግቡና

መለኪያ
ተግባሩ ፈጻሚ
ግብ

የታቀዱ ተግባራት የተሰጠ የግብና ተግባር ውጤት


አካል
ክብደት 1ኛ 2ኛ 3 4ኛ መጠን ጥራት ጊዜ ወጪ

ትምህርትና ሥልጠና ተደራሽነት

5.1. የዓለም አቀፍ የብቃት ደረጃ ያሟሉ


ብቁ በያጆችን ማፍራት የሚችሉ የብየዳ የብየዳ
የዓለም አቀፍ የብቃት ደረጃ
ማሰልጠኛ ተቋማትን (Welding 3 ያሟሉ ተቋማት
ቁጥር 1 6 1 2 3 4 4 100 ዓመት ስልጠና
Centers) መደራጀታቸውን ቡድን
በሱፐርቭዥን ማረጋገጥ
ማሻሻል

5.2. በማኑፋክቸሪንግ ሴክተር የብየዳ


ኢንድሰትሪዎች ለይ የብየዳ ቴክኖሎጂ 2 ቁጥር 0 1 1 100 ዓመት ስልጠና
1 ቡድን
ያለበትን ደርጃ የዳሰሳ ጥናት ማድረግ

ያደገ የህብረተሰብ ባለቤትነት 2                    


የህብረተሰብ ባለቤትነት

6.1. በብየዳ ስልጠና ቡድን ግቦችና ተግባራት የብየዳ


1
ዙሪያ ለህብረተሰቡ እና በሩብ ስልጠና
1 የተፈጠረ ግንዛቤ ቁጥር 1 1 1 100  
ለሚመለከታቸው አካላት ግንዛቤ ዓመት ቡድን
መፍጠር
ማሳደግ

6.2. የመንግስት ባለድርሻ መ/ቤቶች እና የብየዳ


የባለቤትነት ስሜት ስልጠና
ልማት ድርጅቶች አደረጃጀትን በሩብ
1 የተፈጠረለት የህብረተሰብ መቶኛ 50 85 75 85 85 100  
በመጠቀም የህብረተሰብ ባለቤትነትን ዓመት ቡድን
ክፍል
ማሳደግ፣
6.

የተሻሻለ የአጋሮችን ተሳትፎ 2                      


ተሳትፎማሻሻለ

50 የብየዳ
የአጋሮችን

8.1. የአጋሮችን አቅም አሟጦ በመጠቀም ስልጠና


አቅም የተገነባ ብየዳ ስልጠና
የብየዳ ማሰልጠኛ ማዕከል አካላት 2 ማዕከል
መቶኛ 40 100 100 2 100 ዓመት   ቡድን
አቅምን መገንባት፣
7.
8.

II. የፋይናንስ እይታ (8%)


ያደገ የሀብት ምንጮች 4                      
የ9.

የብሄራዊ ብየዳ ማሰልጠኛ ቡድን የ 2010 በጀት ዓመት የሚዛናዊ የውጤት ተኮር ዕቅድ ገጽ - 14
የሚፈጸምበት ሩብ
ዓመት

የአፈጻጸም መነሻ

የ 2010 ዒላማ
የአፈጻጸም ስታንዳርዶች
ስትራቴጂክ

ለግቡና

መለኪያ
ተግባሩ ፈጻሚ
ግብ

የታቀዱ ተግባራት የተሰጠ የግብና ተግባር ውጤት


አካል
ክብደት 1ኛ 2ኛ 3 4ኛ መጠን ጥራት ጊዜ ወጪ

9.1. የብየዳ ማሰልጠኛ ማዕከል አገልግሎት 1


ለአጋር ድርጅቶች ተነድፎ
ተደራሽነት ለሚሳተፉ አጋር ድርጅቶች 1.5 የፀደቀ ፕሮጀክት
በቁጥር 0 2 2 75 100 ዓመት  
የሃብት ማግኛ ፕሮጀክቶችን መንደፍ
ያደገ የሀብት አመዳደብ ፍትሐዊነት 1
ፍትሐዊነት ማሳደግ
የሀብት አመዳደብ

10.1. የተመደበውን
ሃብት በጊዜና በወቅቱ
የብየዳ
ለስልጠና እንዲውል ፕሮፖዛል ለዕቅድ እና በጀት ክፍል
2 ቁጥር 4 1 2 3 4 4 100 ዓመት  ስልጠና
በማዘጋጀት ለሚመለከተው ክፍል ገቢ የተደረገ ሪፖርት
ቡድን
ማድረግና መከታተል
10.
ውጤታማነት

የተሻሻለ የሀብት አጠቃቀም ውጤታማነት 3                    


አጠቃቀም

100 100 100 100


የሀብት

11.1. ከመንግስትና ከአጋሮች የተገኘውን ለታቀደለት ዓላማ የዋለ አስመራ


2 መቶኛ 100 100 100 ዓመት
ሀብት ለታቀደለት ዓላማ ማዋል ሃብት
11.

III. የውስጥ አሰራር እይታ(10%)

የተሻሻለ የሥራ ግንኙነት 2                    


ግንኙነትን ማሻሻል

የብየዳ
12.1. በዳይሬክቶሬቱ በሚገኙ ቡድኖችና
ስልጠና
ሰራተኞች መካከል የግንኙነት እቅድ/ 0.5 የተሻሻለ የግንኙነት ዕቅድ በቁትር - 1 1 1 1 100 ዓመት
ቡድን
ስልት ማሻሻል
12.2. በሌሎች ልማት ቡድኖችና 0.5 የተዘጋጀ የግንኙነት ስልት በቁጥር - 1 1 1 1 100 ዓመት የብየዳ
.የሥራ

በክልሎች መካከል የግንኙነት ስልት ስልጠና


ማዘጋጀት፣ ቡድን
12.

የብሄራዊ ብየዳ ማሰልጠኛ ቡድን የ 2010 በጀት ዓመት የሚዛናዊ የውጤት ተኮር ዕቅድ ገጽ - 15
የሚፈጸምበት ሩብ
ዓመት

የአፈጻጸም መነሻ

የ 2010 ዒላማ
የአፈጻጸም ስታንዳርዶች
ስትራቴጂክ

ለግቡና

መለኪያ
ተግባሩ ፈጻሚ
ግብ

የታቀዱ ተግባራት የተሰጠ የግብና ተግባር ውጤት


አካል
ክብደት 1ኛ 2ኛ 3 4ኛ መጠን ጥራት ጊዜ ወጪ

ዓመት የብየዳ
ስልጠና
12.3. የተዘጋጀውን ስልት በመተግበር ቡድን
የተሻሻሉ የውስጥና የውጭ
የውስጥና የውጭ የሥራ ግንኙነትን 1 የሥራ ግንኝነቶች
መቶኛ 86 100 100 100 100 100 100
ማሻሻል

የተሻሻለ የአገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍናና


3                    
ውጤታማነት
13.1. የአገልግሎት መስጫ ስታዳንዳርድ
(የዜጎች ቻርተር) እና የመልካም የተዘጋጀ የአገልግሎት መስጫ አስመራ
1 ቁጥር 2 2 1 2 2 100 አመት
አስተዳደር ዕቅድን በመከለስ የዜጎችን ስታዳንዳርድ እቅድ
ተገልጋይነት ማረጋገጥ፣
አስመራ
የአገልግሎት አሰጣጥ ቅልጥፍናና

13.2. የ QMS መተግበር 0.5 በመቶኛ 50 25 50 100 100 አመት


ውጤታማነት ማሻሻል

13.3. ካይዘንን ተግባራዊ በማድረግ በካይዘን ትግበራ ያደገ


መቶኛ
የአገልግሎት ቅልጥፍናን ማሳደግ የአገልግሎት ቅልጥፍና 100 100 100 100 100 100
1.5
አስመራ
100 ዓመት
13.

የጎለበተ የክትትል፣ ግምገማና ድጋፍ አሠራር 3                    


የክትትል፣ ግምገማና
ድጋፍ አሠራርን

14.1. በክልልና በቡድኑ ዋና ዋና ተግባራት በቸክልስቱ መሰረት


አተገባበር ላይ ቼክ ሊስት በማዘጋጀትና የተደረገ ክትትል፤ 24 6 6 6 24 100 12 ወር አስመራ
በተዘጋጀው መሰረት ክትትል፣ ግምገማና 2 በቁጥር 6
ድጋፍና ግምገማ
ድጋፍ መስጠት፣
14.2. በክልል ክትትልና ግምገማው ውጤት 1 የተሰጠ ግብረ መልስ ቡቀጥር 1 24 6 6 6 6 24 100 12 ወር አስመራ
መሠረት ግብረ መልስ መስጠት፣
14.

የብሄራዊ ብየዳ ማሰልጠኛ ቡድን የ 2010 በጀት ዓመት የሚዛናዊ የውጤት ተኮር ዕቅድ ገጽ - 16
የሚፈጸምበት ሩብ
ዓመት

የአፈጻጸም መነሻ

የ 2010 ዒላማ
የአፈጻጸም ስታንዳርዶች
ስትራቴጂክ

ለግቡና

መለኪያ
ተግባሩ ፈጻሚ
ግብ

የታቀዱ ተግባራት የተሰጠ የግብና ተግባር ውጤት


አካል
ክብደት 1ኛ 2ኛ 3 4ኛ መጠን ጥራት ጊዜ ወጪ

14.3. ምርጥ ተሞክሮዎችን መለየት፣ የተቀመረ ምርጥ


ማሰባሰብና መቀመር፣ 0.5 በቁጥር 1 - 1 100 100 6 ወር አስመራ
ተሞክሮ
ማጐልበት

14.4. የተቀመሩ ምርጥ ተሞክሮዎችን 0.5 የሰፋ ምርጥ ተሞክሮ በቁት 1 1 100 100 6 ወር አስመራ
በተለያዩ አማራጮች ማስፋት፣
14.5. የተከናወኑ ተግባራትን በወቅቱ የተደረገ የሪፖርት 12 በወ አስመራ
1 ቁጥር 0 24 6 6 6 6 24 100
በሪፖርት ማሳወቅ ብዛት ር

IV.የመማማርና እድገት እይታ(20%)

የተሻሻለ ተቋማዊ የአሰራር ስርዓት


4                    
መዘርጋት
የብየዳ
.ተቋማዊ የአሰራር ስርዓት ማሻሻል

15.1. የብየዳ ስልጠና ማዕከሉን ስልጠና


በኢንተርናሽናል ደረጃ እውቅና ቡድን
በቢቢአር መሰረት
እንዲሰጥ ለሚያደርግ የተለዩ ቦታዎችን
የተመረጡ የአሰራር
ቤንችማርክ (SLV/Asia & IIW 1.5 በቁጥር 2 2 1 100 ዓመት
ስራዓት ማሻሻያ
secretariat France) ጉብኝት
ስልቶች
በማድረግ የአሰራር ስርዓት መቅዳትና
ተግባራዊ ማድረግ

የብየዳ
15.2. በተዘረጉ የማዕከሉ የአሰራር በሰራ ላይ የዋሉ
ስልጠና
ስርዓት ስልቶች ስራ ላይ እንዲውሉ 0.5 የአሰራር ስርዓት በቁጥር 1 1 1 100 100 ዓመት
ቡድን
ማድረግ ማሻሻያ ስልቶች
15.

ያደገ የትምህርትና ስልጠና ልማት ሰራዊት 14                      


የትምህርት
ና ስልጠና

አቅም (የተሻሻለ የፈፃሚዎችን ዕውቀት፣


ክህሎትና አመለካከት)
16.

የብሄራዊ ብየዳ ማሰልጠኛ ቡድን የ 2010 በጀት ዓመት የሚዛናዊ የውጤት ተኮር ዕቅድ ገጽ - 17
የሚፈጸምበት ሩብ
ዓመት

የአፈጻጸም መነሻ

የ 2010 ዒላማ
የአፈጻጸም ስታንዳርዶች
ስትራቴጂክ

ለግቡና

መለኪያ
ተግባሩ ፈጻሚ
ግብ

የታቀዱ ተግባራት የተሰጠ የግብና ተግባር ውጤት


አካል
ክብደት 1ኛ 2ኛ 3 4ኛ መጠን ጥራት ጊዜ ወጪ

16.1. በአለም አቀፍ ደረጃ የበቁ በያጅ


አሰልጣኞችን(Certified Welding) በዓለም አቀፍ ደረጃ 1 1 1 1 አስመራ
ወደ ዌልዲንግ አሰልጣኝነት ብቃታቸው የተረጋገጠ ቁጥር 10 1 100 ዓመት
2 ዌልዲንግ ማስተሮች
(Certified Welding Teachers)
ደረጃ ማብቃት
16.2. ክፍተቱን ለመሙላትና ሠራዊት የተዘጋጀ የሠራዊት የብየዳ
1 ቁጥር 1 20 20 20 20 1 100 12 ወር
መገንባት የሚያስችል ዕቅድ ማዘጋጀትና ግንባታ ዕቅድና ተግበራ ስልጠና
መተግበር ቡድን
16.3. በልማት ሠራዊት ግንባታ መሟላት ሥልጠና ያገኙ የልማት የብየዳ
1 ቁጥር 10 12 10 - 12 10 100 12 ወር
ያልቻሉትን ክፍተቶች በተጨማሪ ሥልጠና ቡድኑ አባላት ስልጠና
መሟላታቸውን ማረጋገጥ፣ ቡድን
ብቃቱ ተፈትሾ
16.4. አዲስ ፈፃሚና አመራር በተዘጋጀው 1 የተቀላቀለ ፈፃሚና ቁጥር 22 - 5 5 - 22 100 4 ወር የብየዳ
የብቃት ማዕቀፍ መሠረት እየተፈተሸ ስልጠና
መቀላቀሉን ማረጋገጥ፣ አመራር ቡድን

በልማት ቡድኑ የተፈሩ የብየዳ


1 በቁጥር 15 - 5 5 - 15 100 12 ወር
ግንባር ቀደሞች ስልጠና
ልማት ሰራዊት አቅምን ማሳደግ

ቡድን
16.5. በተግባራዊ እንቅስቃሴያቸው ግንባር
ቀደሞችን የመለየትና የተደራጀ የልማት በግንባር ቀደሞች ተግባር
ሰራዊት ግንባታ ንቅናቄ ውስጥ ማስገባት፣ የብየዳ
1 የተለወጡ ሌሎች በቁጥር- 15 1 2 3 1 15 100 12 ወር
ስልጠና
ፈፃሚዎች ቡድን

በከይዘን ቦርድ
16.6. የሰራዊት መገንቢያ መሳሪያዎችን በመጠቀም የተገኘ የብየዳ
1 በቁጥር 3 40 20 10 40 3 100 12 ወር
አስተሳሰስሮ በመጠቀም ውጤታማነትን ውጤት እና በካይዘን ስልጠና
መጨመር የተደራጀ ቡድኖች ቡድን

የራስ ማብቂያ እና
16.7. ፈፃሚና አመራር ራሱን የሚያበቃበት 1 ውጤታማነት፤ዕቅድ፤ሪ በቁጥር 80 1 1 1 1 80 100 12 ወር አስመራ
እና ተጨባጭ ለውጥ እያየ ውጤታማ
እንዲሆን ማድረግ ፖርት፤ያደገ አመለካከት

የብሄራዊ ብየዳ ማሰልጠኛ ቡድን የ 2010 በጀት ዓመት የሚዛናዊ የውጤት ተኮር ዕቅድ ገጽ - 18
የሚፈጸምበት ሩብ
ዓመት

የአፈጻጸም መነሻ

የ 2010 ዒላማ
የአፈጻጸም ስታንዳርዶች
ስትራቴጂክ

ለግቡና

መለኪያ
ተግባሩ ፈጻሚ
ግብ

የታቀዱ ተግባራት የተሰጠ የግብና ተግባር ውጤት


አካል
ክብደት 1ኛ 2ኛ 3 4ኛ መጠን ጥራት ጊዜ ወጪ

ያደገ ተቋማዊ የቴክኖሎጂ አቅም 3                      


ተቋማዊ የቴክኖሎጂ አቅምን ማሳደግ

17.1. የብየዳ ስልጠና ማዕከሉን የብየዳ


አገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነት ስልጠና
ለማሳደግ የቴክኖሎጂ አቅም ቡድን
በቤንች ማርክ መሰረት የተለዩ
ክፍተቶችን በመለየት እንዲሞላ 2 የቴክኖሎጂ አቅም ክፍተቶች
መቶኛ 100 40 75 100 100 100 ዓመት
ማድረግ
 ጭስ ማስወጫ
 NDT & DT
17.2. የቴክኖሎጂ መረጃ ቋት (Data በተዘጋጀው መረጃ ቋት የብየዳ
Bank) በማዘጋጀት የብየዳ ስልጠናና ተደራሽ የሆነ የብየዳ ስልጠና
የትራክተር ፋብርኬሽን ስራዎችን መረጃ 1 አሰልጣኞችና ሰልጣኞች ቡድን
ማደራጀትና ለተጠቃሚዎች ተደራሽ መረጃ ሰነድ
ማድረግ፣
17.

ያዘጋጀው---------------------------------- ያፀደቀው----------------------------------

ፊርማ ------------------------------------ ፊርማ ------------------------------------

ቀን ----------------------------------------- ቀን-----------------------------------

የብሄራዊ ብየዳ ማሰልጠኛ ቡድን የ 2010 በጀት ዓመት የሚዛናዊ የውጤት ተኮር ዕቅድ ገጽ - 19

You might also like