You are on page 1of 4

በኢትዩጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የፌዴራል ኅብረት

ሥራ ኤጀንሲ

የሰው ሀብት አስተዳደርና ልማት ዳይሬክቶሬት

ከ 2014-2015 ዓ.ም በጀት ዓመት የፕሮግራም በጀት

የካቲት 2013 ዓ.ም


አዲስ አበባ
የሰው ሀብት አስተዳደርና ልማት ዳይሬክቶሬት ከ 2014-2015 ዓ.ም በጀት ዓመት የፕሮግራም በጀት ዕቅድ

መግቢያ
በአገር አቀፍ ወይም በኢትዮጽያን እየተካሄደ የሚገኘው ሀገራዊ የመደመር እሳቤ ሀገራዊ ለውጥን ለማሳካት
የ 2 ኛውን የትራንፎርሜሽን እቅድ ዘመን የመጨረሻ ዘመን እቅድ አፈጻጸማችንን መነሻነት ከኤጀንሲው ተልእኮ
አንጻር የሚፈለገውን ውጤት ማስመዝገብ የሚችል ብቁና በአመለካከቱ እና ልማታዊ የሆነ በቂ የሰው ሃብት
ማሟላትና ማልማት ሲቻል ብቻ በመሆኑ ከተቋሙ የተቀረፁ አምስት ስትራቴጂካዊ የትኩረት መስኮች ማለትም
የኅብረት ሥራ ማኅበራትን ማጠናከር፤የአግሮ-ፕሮሰሲንግና አግሮ-ሜካንይዜሽን በማስፋፋት፤ የላቀ ቁጠባና
ኢንቨስትመንት፤ከፍተኛ የገበያ ድርሻ ማሳደግ እና የኅብረት ሥራ ማኅበራት ደህንነታቸውንና ህጋዊነታቸውን
ለማስጠበቅ በውስጡ የተቀረፁ 17 ካስኬድ የተደረጉ ግቦች ለማሳካት የሥራ ሂደቱ የ 2 ዓመት የፕሮግራም በጀት
ዕቅድ ተዘጋጅቷል፡፡ የዕቅድ ሰንሰለቱን ተከትለን በበጀት ዓመቱ የኅብረት ሥራ ዘርፉን ስኬታማነት ከማስቀጠል
አንጻር አስፈላጊውን የሰው ሃብት ማሟላትና ያሉትንም የማስፈፀም አቅም በመገንባት ዓመታዊ ግባችንን
ለማሳካት ይቻል ዘንድ የተቋሙንና የሥራ ሂደቱን ስትራቴጂክ ዕቅድ የባለፈ ዓመት ዕቅድ አፈጻፀም ግምገማንና
ተቋማዊ አቅጣጫን መሠረት ያደረገ የሰው ሃብት አስተዳደርና ልማት ፋይሬክቶሬት ከ 2014-2015 ዓ.ም.
የፕሮግራም በጀት እንደሚከተለው ተዘጋጅቶ ቀርቧል፡፡

ዓላማ

በሰው ሃብት አስተዳደርና ልማት አዋጅ፤ደንብና፤ መመሪያ መሠረት በቅጥር፣ በዝውውርና በደረጃ ዕድገት ወዘተ
የኤጀንሲውን አደረጃጀት በማጥናት የሰው ሃይል ፍላጐት በማሟላት እና በማልማት የዘርፉን ውጤታማነት
ማስቀጠል፡፡

ዝርዝር ዓላማዎች

 የኤጀንሲውን አደረጃጀት በማጥናት የሥራ ሂደቶችን መፍጠር፤


 የኤጀንሲውን በቂና ተወዳዳሪ የሰው ኃይል ፍላጎት በወቅቱ ማሟላት፤
 የሰራተኞችን ልዩ ልዩ ህጋዊ ጥቅማ ጥቅሞችና መብቶችን ማስከበር፤
 የኤጀንሲውን የሰው ኃይል ልማትን በማጠናከር ብቁና ተወዳዳሪ ሰራተኞችን መቅጠር፤
 በበጀት ዓመቱ የተጣሉ ዋና ዋና ግቦችን ማሳካት፤

የአፈጻጸም ስምምነት ሰነዱ አስፈላጊነት

የዳይሬክቶሬቱ ዋና እና ዝርዝር ተግባራት ከኤጀንሲው የትኩረት አቅጣጫ ጋር በማዛመድ በዕቅድ ማዕቀፍ ውስጥ
ተካተው እያንዳንዱ ግብ ተኮር ተግባራት በዕቅድ እየተመሩ የሚከናወኑበትና የሚፈፀሙበት ሥርዓት ማዘጋጀት
አስፈላጊ በመሆኑ ይህ ከ 2014-2015 ዓ.ም በጀት ዓመት የ 2 ዓመት የሰው ሃብት አስተዳደርና ልማት ዳይሬክቶሬት
የፕሮግራም በጀት እቅድ እንዲዘጋጅ ተደርጓል፡፡
የፌደራል ኅብረትሥራ ኤጀንሲ ተልዕኮ፣ ራዕይ እና እሴቶች

ራዕይ፡-

በ 2028 ዓ.ም የአባላትን ኑሮ በላቀ ደረጃ የለወጡ እና በአገሪቱ ኢኮኖሚ ግንባታ የላቀ ሚና ያበረከቱ ጠንካራና ተወዳዳሪ
ኅብረት ሥራ ማኅበራት ተፈጥረው ማየት ነው፡፡
ተልዕኮ፣

በገጠርና በከተማ የሚኖረው ህብረተሰብ የአካባቢውን ሃብት መሰረት አድርጎ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግሩን ለመፍታት
በፈቃደኝነት ላይ ተመስርቶ በተለያየ አይነትና ደረጃ የኅብረት ስራ ማህበራትን በማደራጀት፣ በማጠናከርና፣ የኅብረት ሥራ
ኤክስቴንሽን በማስፋፋት፣ የመፈጸም እና የማስፈጸም አቅማቸውን በመገንባት፣ የአግሮ -ፕሮሰሲንግና አግሮ-ሜካንይዜሽን
በማስፋፋት፤ የግብይት ድርሻቸውን በማላቅ፤ የመቆጠብ ባህልና መጠንን በማሳደግ፤ ኢንቨስትመንትን በማስፋፋት፣
የአገልግሎት አሰጣጣቸውን በማዘመን፣ ደህንነት እና ህጋዊነታቸውን በማስጠበቅ፤ የአባላትን ተጠቃሚነት በዘላቂነት
ያረጋገጡ ጤናማ፣ ውጤታማና ተወዳዳሪ የኅብረት ሥራ ማህበራትን መፍጠር፡፡››
ዕሴቶች፣

 ቅንነት፣
 ወንድማማችነት፣
 መከባበር፣
 መተባበር፤
 መሰጠት፣
 በኅብረት ሥራ ወሳኝነት ማመን
 የግልና የጋራ ሃላፊነት መወጣት፣

ዓመታዊ ዕቅድ ሂደት

የሥራ ክፍሉ የውጤት ተኮር የአፈፃፀም ዕቅድ ከተቋሙ እስትራቴጃዊ ግቦችና ከሥራ ክፍሉ ግቦች ጋር በቀጥታም ሆነ
በተዘዋዋሪ በሚመጋገብበት አግባብ መዘጋጀት ያለበት በመሆኑ በየበጀት ዓመቱ ግብ ተኮር ተግባራት ማሳያ ቴምኘሌት
እንዲዘጋጅ የሚደረግ ሲሆን ቴምኘሌቱ የሚዘጋጀው፡-

3.1 ከተቋሙ የውጤት ተኮር የአፈፃፀም ዕቅድ የጥናት ሰነድ ላይ ከተለዩት 17 የተቋሙ ስትራቴጂያዊ ግቦች ውስጥ የሥራ
ክፍሉን የሚመለከቱ 4 የጋራ ስትራቴጂካያዊ ግቦችን (Shard Objective) ወደ ሥራ ክፍሉ እንዲወርድ (Cascade)
በማድረግ፣
3.2 ወደ ሥራ ክፍሉ የወረዱ ስትራቴጂያዊው ግቦች ከሥራ ክፍሉ ተግባርና ኃላፊነት (Functional Description) አንፃር 10
የሥራ ክፍሉ ግቦች በሥራ ክፍል ደረጃ ተመንዝረው እንዲቀረጽ በማድረግ፣
3.3 ከተቋሙ ወደ ሥራ ክፍሉ የወረዱ እስትራቴጂክ ግቦች እና በሥራ ክፍል ደረጃ ተመንዝረው የተቀረፁት ግቦች ከአራት
የእይታ መስኮች ማለትም ከተገልጋዩ፣ ከበጀት፣ ከውስጥ አሰራር እና ከመማርና ዕድገት ተለይተው እንዲቀመጡ
በማድረግ፣
3.4 ከእያንዳንድ ግብ የሚጠበቅ የግብ ውጤት፣ የግቡ ውጤት መለኪያ እና እንደ አግባብነቱ የግቦቹ ክብደት በመቶኛ ተሰልቶ
እንዲቀመጥ በማድረግ፣
3.5 ግቦቹን ለማሳካት በበጀት ዓመቱ የሚፈፀሙ ግብ ተኮር ተግባራት አጠቃላይ ዓመታዊ የዕቅድ መጠን በየሩብ ዓመቱ
በማከፋፈል የየሩብ ዓመቱ ግብ ተኮር ተግባራት መጠን በቁጥር ተለይተው እንዲቀመጡ በማድረግ፣የሥራ ክፍሉ
የ 2014 ዓም በጀት ዓመት ግብ ተኮር ተግባራት ማሳያ ቴምኘሌት የተቋሙን እስትራቴጂክ ግባችን መሠረት በማድረግ

3.6 ከላይ በተራ ቁጥር ከ 3.1 እስከ 3.5 ድረስ በተገለፀው መሠረት ከተዘጋጀው የሥራ ክፍሉ የዓመታዊ ግብ ተኮር ማሳያ
ቴምኘሌት ላይ የተለዩትን ግቦችና ግቦቹን ለማሳካት የሚከናወኑ ግብ ተኮር ተግባራት ለሥራ ክፍሉ ፈፃሚዎች
ከተመደቡበት የሥራ መደብና የሥራ ደረጃ አንፃር እንዲወርዱ በማድረግ የሥራ ክፍሉ ፈጻሚዎች የግለሰብ ግብ ተኮር
ስኮር ካርድ እንዲዘጋጅ በማድረግ ነው
ከ 2014 ዓ.ም እስከ 2015 ዓ.ም በጀት ዓመት በስራ ክፍሉ የተጣሉ ዋና ዋና ግቦች
1. የተገልጋይ እርካታን ማሳደግ፣
2. ውጤታማ የበጀት አጠቃቀምን ማሳደግ
3. አንድ ወጥ የውጤት ተኮር ዕቅድና የሥራ አፈጻፀም ምዘና የአሰራር ስርዓትን ማጐልበት
4. ቅንጅታዊ አሰራርን ማጠናከር
5. ወቅታዊ የሰው ሃብት መረጃና ዶክመንቴሽን ስርዓትን መዘርጋት፣
6. የተቋሙን የሰው ሃይል ፍላጐት ማሟላት፣
7. የኤጀንሲውን ሠራተኞች የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂን እና የመፈፀም ብቃታቸውን ማሳደግ፣
8. የሰው ሃብት የአሰራር ስርዓትን ማሳደግ፣
9. የለውጥ ሠራዊት አደረጃጀትና መልካም አስተዳርን ማጠናከር
10. ምርጥ ተሞክሮ ቅመራና ማስፋት፣

You might also like