You are on page 1of 7

1

የ 2016 በጀት አመት የተደረገ የስምምነት ቻርተር

በቦሌ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች


ጽ/ቤት

ኮንትራት አስተዳር ቡድን

እና

በቡድኑ ፈፃሚዎች መካከል

የተደረገ የስምምነት ቻርተር

ነሀሴ 2015 ዓ.ም


2
የ 2016 በጀት አመት የተደረገ የስምምነት ቻርተር

መግቢያ፡-
የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስፈፃሚ አካላትን እንደገና ለማቋቋም በወጣው አዋጅ
መሰረት ከተቋቋሙት የተለያዩ ቢሮዎች አንዱ ሲሆን ቢሮው ከተመሰረተበት ጊዜ ጀምሮ የአምስት አመት ስትራቴጂክና አመታዊ
ዕቅድ በማዘጋጀት፣ በቢሮው ስር የሚገኙት መ/ቤቶችን በማስተባበር መሰረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥና የሚዛናዊ ሥራ አመራርና
ውጤት ምዘና ጥናት በማጥናት ፣ እንዲሁም በየበጀት ዓመቱ የታቀዱ ሥራዎች አፈፃፀም በመከታተልና ውጤታማ እንዲሆን
ለማድረግ የበኩሉን ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

በዚህም መሠረት በቢሮው ሥር ከተደራጁት ተቋማት አንዱ የሆነው የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ በክ/ከተማ የዲዛይንና
ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ከላይ በተጠቀሰው አዋጅ የተሠጡ ሥልጣንና ተግባራትን በብቃት ለመወጣት እንዲያስችለው ተናባቢ
የሆነ ዕቅድ በየደረጃው በማዘጋጀት ለተግባራዊነቱ ከፍተኛ የሥራ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡

የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ የከተማዋን ልማትና ሁለንተናዊ ዕድገት በማፋጠን ረገድ ከተሰጡት ተልዕኮዎች መካከል
በዋነኛነት በከተማዋ የሚገነቡ የመንግስት የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ግንባታዎች ጥራትና ደረጃቸውን የጠበቁና
ደህንነታቸው አስተማማኝ ሆነው እንዲገነቡ እና በወቅቱ ተጠናቅቀው ለአገልግሎት ብቁ እንዲሆኑ ቢሮዉ የኮንስትራክሽን
አመራር አቅም በመገንባት ተገቢውን የቁጥጥርና ክትትል በማድረግ በማእከል እና በክፍለ ከተማ ስር ላሉ የሥራ ሂደቶች ድጋፍ
ማድረግ ዋና ዋና ተግባሮቹ ናቸው፡፡

ስትራቴጂዎቻችንን በመተግበር የልማትና መልካም አስተዳደር ተልዕኮዎቻችን እንዲሳኩ የባላንስድ ስኮር ካርድ ማለትም
ሚዛናዊ የሥራ አመራርና ውጤት ምዘና ጥናት በስትራቴጂ ለመመራትና የተግባር እንቅስቃሴዎቻችንን በውጤት ለመለካት
የሚያስችለን በመሆኑ የተጀመረውን ለውጥ ለማስቀጠል ወሳኝ ድርሻ ይኖረዋል፡፡ የልማት ቀጣይነትን በማረጋገጥ መልካም
አስተዳደርን ለማስፈን በሚደረገው ጥረት ውስጥ ቢሮዉ የራሱን ድርሻ እንዲወጣ በዘርፉ በየደረጃው የልማት ሠራዊትን
በመፍጠርና በማጠናከር የልማትና የለውጥ ማነቆዎችንና ችግሮችን በማስወገድ ሥራን በተጨባጭ ውጤት እየተለካ መቀጠል
አስፈላጊ ይሆናል፡፡ በመሆኑም የአመራሩና የሠራተኛው የአመለካከት፣ የክህሎትና የግብዓት ችግሮችን በመፍታት የልማት
ዕቅዶቻችን በተሟላ መልኩ ለማሳካት የተጠናከረ ሥራ ይጠበቃል፡፡ የልማት ሥራዎችን ለማፋጠን፣ቀጣይነታቸውን ለማረጋገጥና
ፍትሀዊ የሕዝብ ተጠቃሚነትን ለማስፈን ሥራዎቹ በጠንካራ የልማት ሠራዊት እንዲተገበሩ ማድረግና የሪፎርም ስራዎቻችንን
ተከታታይነት ባለው መንገድ መስራት ያስፈልጋል፡፡

የልማትና መልካም አስተዳደር የማይለያዩ ገጽታዎች እንደመሆናቸው መጠን በልማቱ የሚገኘው ውጤት የህዝቡን የመልካም
አስተዳደር ጥያቄዎች ይፈታል፡፡ ለህዝቡ በምንሰጠው አገልግሎትና የልማት ፕሮግራም ከኪራይ ሰብሳቢነት የጸዳ፣ግልጽነትን፣
ተጠያቂነትንና ፍትሃዊነትን ማዕከል በማድረግ ልማቱን ማስቀጠል ይገባል፡፡

የልማት ዕቅዶቻችንን ተግባራዊ ለማድረግ መሠረታዊው ነገር የማስፈፀም አቅም ግንባታ በመሆኑ በ BSC ጥናት ትኩረት
እንዲሰጠው ተደርጓል፡፡ አቅማችንን በመገንባትና በውስጥ የሥራ ሂደቶቻችን /Internal Business Process/ በርካታ
ሥራዎችን በማከናወን ለልማት ሥራችን የሚውሉ ሃብቶቻችንን በተገቢው በመምራት የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር
ፍላጐቶች ማርካት የስትራቴጂያችን ዋና ግብ ይሆናል፡፡ በመሠረታዊ የሥራ ሂደት የተገኙ ተሞክሮዎችን ከማስፋት ጐን ለጐን
የለውጡን አደናቃፊ ችግሮች በዋናነትም የኪራይ ሰብሳቢነትን አመለካከትና ተግባር በመናድ የልማታዊ አመለካከትና ተግባር
3
የ 2016 በጀት አመት የተደረገ የስምምነት ቻርተር

የበላይነት እንዲሰፍን ማድረግ ካልተቻለ የለውጡ ቀጣይነት ዋስትና አይኖረውም፡፡ የ BSC ጥናት ተግባራዊነትም ታሳቢ
የሚያደርገው ልማታዊ እና ዲሞክራሲያዊ አስተሳሰብና ተግባርን በመገንባት ላይ ነው፡፡

የኮንትራት አስተዳደር ቡድን ካለው ነባራዊ መነሻ ተነስቶ የ 2016 በጀት አመት እቅድ አቅዶ በዝግጀት ምእራፍ ላይ ይገኛል፡፡
ስለሆነም ከላይ የተጠቀሱትን ዓላማዎች ለማሳካት እንዲቻል ይህ የስምምነት ቻርተር /CHARTER/ እንዲዘጋጅ ተደርጓል፡፡

የቻርተሩ ትርጉም

ሚዛናዊ የሆነ የሥራ አመራርና ውጤት ምዘና ሥርአት የስምምነት ሰነድ /CHARTER/ ማለት ተቋማት፣የሥራ
ሂደቶች፣ንዑሳን የሥራ ሂደቶች፣ኬዝ ቲሞችና እና ፈፃሚዎች ተቋማዊ የቢኤስሲ ጥናትና በጥናቱ መሠረት የተዘጋጀውን ስኮር
ካርድ ተግባራዊ ለማድረግ፤እንዲሁም በየደረጃው የተቀመጡ ግቦችንና ዒላማዎችን ለማሳካት እንዲቻል የግልጸኝነትንና
የተጠያቂነት መርህን መሠረት በማድረግ በየተዋረዱ የሚያደርጉት የፁሁፍ ስምምነት ነው፡፡

የቻርተሩ ዓላማ

በጽ/ቤቱ የተቀመጡትን የጋራ ራዕይና ተልዕኮዎችን በማሳካት የጋራ አስተሳሰብና መግባባት በመፍጠር ውጤታማነትንና
ቀልጣፋነትን በማረጋገጥ በልማትና በመልካም አስተዳደር ተጨባጭ ውጤት በማስመዝገብ ህዝቡን ተጠቃሚ ማድረግ ፡፡

የቻርተሩ አስፈላጊነት

 በውል ሰጪና በውል ተቀባይ መካከል በጊዜ የተገደበ የስራ እቅድና ክንውን በግልፅ ተግባር ቆጥሮ ተግባርን
በውጤት በመቀበል ሁሉም አካላት የበኩላቸውን ሀላፊነት እንዲወጡ ያደርጋል፡፡
 ተጠያቂነትንም ከማስፈኑ በተጨማሪ ሁሉም የድርሻውን በመወጣት በልማትና በመልካም አስተዳደር ስራዎች
ሁሉም ተጠቃሚ እንዲሆን ያደርጋል፡፡

የቻርተሩ ወሰን

በቦሌ ክፍለ ከተማ በዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት እና በኮንትራት አስተዳደር ቡድን መሪ የተፈራረመ ውል ሲሆን የቡድኑ
መሪ በስሩ ባለሙያዎች በተገቢው መንገድ ይከታተላል፤ ይደግፋል፤ የራሳቸውን ቻርተርከ ፈፃሚዎች ጋር የሚፈራረሙ
ይሆናል፡፡

 የቻርተሩ አፈፃፀም መርሆዎች


 ግልፅነትና ተጠያቂነት ያለው አሰራርን መከተል
 በተዘጋጀው ስኮር ካርድና በተቀመጠው ስታንዳርድ መሰረት አገልግሎት በመስጠትና ተግባራትን በማከናወን
ውጤትን ማምጣት
 ስምምነቱን ተግባራዊ የማድረግ ግዴታ
4
የ 2016 በጀት አመት የተደረገ የስምምነት ቻርተር

 ተከታታይና ውጤታማ ስርዓተ-ተግባቦት በመዘርጋት የሚመለከታቸውን አካላት እንዲያውቁትና እንዲረዱት


ማድረግ
 ወቅቱን የጠበቀ የማስተካከያ እርምት እርምጃ መውሰድ
 ግልፅና ተደራሽ እንዲሁም የተሟላ መረጃን መያዝ
 ተጠቃሚውን ህብረተሰብና ባለድርሻ አካላትን ማሳተፍ

በቦሌ ክፍለ ከተማ የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ጽ/ቤት ራዕይ፣ተልዕኮ፣እሴቶች፣ስትራቴጂያዊ የትኩረት


መስኮችና ውጤቶች

 ራዕይ /Vision/
አዲስ አበባ ከተማ በ 2 ዐ 17 ዓ.ም መካከለኛ ገቢ ካላቸው ከተሞች ጋር ተወዳዳሪ እንድትሆን ጥራትና ደረጃቸዉን የጠበቁ
የመንግስት የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት የተሟሉላት ማድረግ፡፡

 ተልዕኮ /Mission/
በቦሌ ክፍለ ከተማከተማ ያለዉን የመንግስት ማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ችግር ለመቅረፍ
 በመንግስት ሚገነቡ የማህበራዊ ተቋማት ሽፋን በማሳደግ ከመንግስት የልማት ስትራቴጂ ጋር እንዲቀናጅ
ማድረግ፣
 በክፍለ ከተማዋ ዉስጥ የሚከናወኑ የመንግስት ማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ፍላጎትን መሰረት ያደረገ
ጥናትና ዲዛይን በመስራትና እንዲሰሩ በማድረግ ግንባታዎች ጥራትና ደረጃቸዉን የጠበቁ እንዲሆኑ እና ለአገልግሎት
ብቁ እንዲሆኑ ማድረግ ነዉ፡፡

 ዕሴቶች /Values/
 ግልጽነት
 ተጠያቂነት
 የላቀ አገልግሎት መስጠት
 በእውቀትና በእምነት መምራት/መሥራት
 ለለውጥ ዝግጁነት
 ጥራትና ወጭ ቆጣቢነት
 ፍትሃዊነት

 ስትራቴጂያዊ የትኩረት መስኮች (Strategic Themes) እና ውጤቶች


 የማስፈጸም አቅም ግንባታና መልካም አስተዳደር (capacity building and good governance)
 ብቃት ያለው የሰው ሀይል፣አደረጃጀትና አሰራር በመፍጠር ልማትና መልካም አስተዳደር ያሰፍናል
5
የ 2016 በጀት አመት የተደረገ የስምምነት ቻርተር

 ሰፊ የማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማት ግንባታ


 የማህበራዊ ተቋማት አቅርቦትና ተደራሽነት ይጨምራል፣ማሕበራዊ ችግሮች ይቀረፋሉ፣

 የዲዛይን እና ኮንትራት ማኔጅመንት ቡድን ተግባር


 የቡድኑን ሥራ ማቀድ፣ መምራትና ማስተባበር፤
 በ 2015 ለ 9 ነባር እና ለ 27 ፕሮጀክቶች የኮንትራት አስተዳደር ስራ ማከናወን
 በ 2014 ለ 11 አማካሪዎች በቼክ ሊስት መሰረት ክትትል እና ድጋፍ ማድረግ
 በ 2014 ለ 35 የተለያዩ ግንባታዎች የመጨረሻ ርክክብ መፈጸም
 የቡድኑን የሥራ ክንውን ሪፖርት በየወቅቱ በማዘጋጀት ለቅርብ የሥራ ኃላፊው ያቀርባል፣
ክትትልና ድጋፍ
ቡድኑ በስሩ ያሉት ባለሙያዎች ያስቀመጧቸውን ግቦችና ዒላማዎች ከማሳካት አንጻር ዕቅዶቻቸውን በአግባቡ
እየተገበሩ መሆናቸውን ለማወቅና በትግበራ ሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮችን እየለዩ ወቅታዊ የመፍትሄ እርምጃ ለመውሰድ
ውጤታማ አፈጻጸምን ለማረጋገጥ ጠንካራ የክትትል ሥርዓት ሊዘረጉ ይገባል፡፡ ውጤታማ ስራን በማከናወን ግብን
ለማሳካት የክትትልና ግምገማ ውጤቶችን መሰረት አድርጎ ተከታታይነት ያለው በሰው ኃይል፤ በማቴሪያልና በበጀት ድጋፍ
ማድረግ ከክትትል ጎን ለጎን ማከናወን ያስፈልጋል፡፡

የክትትልና ድጋፍ ስራ ባልተቋረጠ መልኩ የሚከናወን ቢሆንም ቡድኖች የየክፍላቸውን ተጨባጭ ሁኔታ ከግምት ውሰጥ
አስገብተው ለስራቸው አመቺ የሆነ የክትትልና ድጋፍ መርሀ-ግብር አዘጋጅተው ወደ ተግባር መግባት ይጠበቅባቸዋል፡፡

ግምገማ
ቡድኑ በዕቅዶቻቸው መስረት ስራቸውን እያከናወኑ መሆናቸውንና ግባቸውን እና ዒላማቸውን በተሟላ መልኩ ለማሳካት
በሚያስችላቸው የአፈጻጻም ደረጃ ላይ መሆናቸውን በየጊዜው መገምገም ይጠበቅባቸዋል፡፡

በዚህም መሰረት
 የኮንትራት አስተዳር ቡድን በስሩ ከሚገኙ ጋር በየሳምንቱ ሐሙስ ከሰዓት ከ 8፡30 ሠዓት ጀምሮ የአፈፃፀም ግምገማ
ያካሂዳል፡፡
 የዲዛይን እና ግንባታ ስራዎች ፅ/ቤት ከቡድኑ ጋር በየአስራ አምስት ቀን አርብ ጧት ከ 4፡00 ሠዓት ጀምሮ የአፈፃፀም
ግምገማ ያካሂዳል፡፡
 የጽ/ቤቱ ፕሮሰስ ካውንስል በየሳምንቱ ሰኞ ጧት ከ 4፡30 ሠዓት ጀምሮ የአፈፃፀም ግምገማ ያካሂዳል፡፡
ሪፖርትና ግብረ-መልስ፤
ቡድኑ የስትራቴጂያዊ ዕቅድ አፈጻጸማቸውን፤ በትግበራ ሂደት ያጋጠሟቸውን ችግሮች፤ ችግሮችን ለመፍታት የወሰዱትን
እርምጃዎች፤እና የተገኘ ትምህርትን በተወሰነ የጊዜ ሠሌዳ መሠረት ሪፖርት ማዘጋጀትና በሪፖርቱ ላይ ከፈጻሚዎች፣
ከአስፈጻሚዎችና ከባለድርሻ አካላት ጋር መወያየት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ሪፖርቶች ስትራቴጂያዊ ግቦችንና ዒላማዎችን ከማሳካት
አኳያ ያለውን አፈፃፀም በማሳየት የቀጣይ ስራዎችን አስመልክቶ ለሚተላለፉ ውሳኔዎች ወሳኝ ግብዓቶች ስለሆኑ ወቅታቸውን
ጠብቀው በጥንቃቄ መዘጋጀት ይኖርባቸዋል፡፡ ከክትትል፤ድጋፍና ግምገማ የሚገኙ መረጃዎች ለሪፖርት ዝግጅት ወሳኝ ግብዓቶች
6
የ 2016 በጀት አመት የተደረገ የስምምነት ቻርተር

ስለሆኑ እነዚህ መረጃዎች በአግባቡ ሊያዙና በሪፖርቱ ሊካተቱ ይገባል፡፡ ቡድኖች የሚያደርጉት ክትትል፤ ድጋፍና ግምገማ
መሰረት አድርገው በአፈጻጸም የታዩ ጠንካራ ጎኖችን የበለጠ አጠናክሮ ለማስቀጠል፤ የታዩ ጉድለቶችን ደግሞ መፍትሄ በመስጠት
ለማሻሻል የሚያስችል የግብረ-መልስ ሥርዓት ሊኖራቸው ይገባል፡፡

በዚህም አግባብ

 የሪፖርቶች አቀራረብ የተቋማዊ ዕቅድ አፈፃፀምን በማጣመር በዕቅዱ ላይ የተቀመጡትን ግቦችና ዋና ዋና ተግባራትን
መሠረት ያደረገ ሆኖ ውጤቶች ላይ ያተኮረ መሆን ይኖርበታል፣
 ወርሃዊ ሪፖርት በየግቡ ሥር እየተከናወኑ ባሉ ዋና ዋና ሥራዎች ላይ በማተኮር የተዘጋጀ አጭር ሪፖርት ወሩ
በተጠናቀቀ በመጀመሪያው ሳምንት ባሉ 2 ቀናት ውስጥ ይሆናል፣
 የሩብ ዓመት፣የግማሽ ዓመት ፣የዘጠኝ ወራት እና ዓመታዊ ሪፖርት ዘርዝር ያሉ የአፈፃፀም ሪፖርቶች ከነማብሪራያው
በመያዝ የየሩብ የግማሽ ዓመቱ ወይም የዕቅድ ወሩ ሳይጠናቀቅ በወሩ ከ 18-21 ቀናት ውስጥ ተዘጋጅቶ መቅረብ
ይኖርበታል፣
 በየደረጃው ተግምግሞ በመጨረሻ መልኩ የሚወጣው የቡድኑ የዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በየወሩ ለኤጄንሲዉ እና
ለሌሎች ለሚመለከታቸው አካላት ይሰራጫል፡፡
 ግብረ-መልስ በየሩብ ዓመቱ በየደረጃው መሰጠት ይኖርበታል፡፡

ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች
ስምምነቱ ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ

ይህ ስምምነት በሁለቱ ተፈራራሚ አካላት (ተዋዋይ ወገኖች) ከተፈረመበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ሰኔ 30/2016 ዓ.ም ድረስ ጸንቶ
ይቆያል፡፡ ሆኖም በሁለቱ ተዋዋዮች ስምምነት ሊሻሻል ይችላል፡፡

1.1. ይህ የስምምነት ሠነድ በተሟላ ሁኔታ ተግባራዊ መደረግ ያለበት ሲሆን ከውሉ ውጪ ወቅታዊና ለዋናው ግብ
አስፈላጊ የሆኑ ተግባራት ሲያጋጥሙ በጋራ ውይይት የስምምነቱ አካል ይሆናሉ፡፡ በተጨማሪም የተቋማት
እቅድ አፈፃፀም ምዘና እና ግብረ-መልስ መመሪያ የዚሁ ውል አካል ይሆናል፡፡
1.2. የቡድን መሪ ዕቅድ እና የቢኤስሲ ዕቅድ ወደ ንዑሳን ኬዝ ቲሞች በመዘርዘር ፤ ክብደት በመስጠት ከተዋረድ
የሥራ ሂደት እና የኬዝ ቲም አስተባባሪዎች እስከ ግለሰብ ዕቅድ ለማውረድና ሪፖርት ለማቅረብ ውል ተቀባይ
በወቅቱ ተስማምቷል፡፡

ውል ተቀባይ
የዲዛየን እና ኮንትራት ማኔጅመንት ቡድን ፈጻሚዎች
ከላይ የተዘረዘሩትን ስራዎች ለማከናወን ቆጥሬ ተረክቤአለሁ ፡፡
የቻርተሩ ውል ተቀባይ፡-

ስም ፊርማ ቀን
1. ወ/ሪት ሰላማዊት ጌታነህ ……………… 18/12/2014 ዓ.ም
2. አቶ ሰለሞን አለማየሁ ……………… 18/12/2014 ዓ.ም
3. ወ/ሮ ህሊና በቀለ ……………… 18/12/2014 ዓ.ም
4. አቶ አሸናፊ ሀይለ ማርያም ……………… 18/12/2014 ዓ.ም
5. አቶ አቤል አስፋው ……………… 18/12/2014 ዓ.ም
7
የ 2016 በጀት አመት የተደረገ የስምምነት ቻርተር

6. ወ/ሮ ህይወት ዘርጋ ……………… 18/12/2014 ዓ.ም


7. አቶ እስክንድር ተስፋዬ ……………… 18/12/2014 ዓ.ም
8. አቶ ብርሃኑ በቀለ ……………… 18/12/2014 ዓ.ም
9. አቶ ነጋ አስፋ ……………… 18/12/2014 ዓ.ም
10. አቶ ሳዲቅ ኢሳ ……………… 18/12/2014 ዓ.ም
11. ወ/ሮ ሄቫና ሲሳይ ……………… 18/12/2014 ዓ.ም
12. አቶ ሙሉጌታ ተስፋዬ ……………… 18/12/2014 ዓ.ም
13. ወ/ሮ አለም በለጠ ……………… 18/12/2014 ዓ.ም
14. ወ/ሮ አለምነሽ ንጉሴ ……………… 18/12/2014 ዓ.ም

ውል ሰጪ፡-
የኮንትራት አስተዳር ቡድን መሪ /ተወካይ/

የቻርተሩ ውል ሰጪ /ቻርተሩን ያፀደቀው ሀላፊ

ስም-------------------------------------
ፊርማ---------------------------------
ቀን-------------------------------------

You might also like