You are on page 1of 4

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ጽ ቤት /

የፋይናንስ ቡድን

የ 2016 በጀት ዓመት

የልምድ ልውውጥ እቅድ

ሐምሌ/2015 ዓ.ም

መግቢያ
በቡድናችን እየተመዘገበ ያለውን አበረታች የእድገትና፣የልማትና የመልካም አስተዳደር እንቅስቃሴ አጠናክሮ
ለማስቀጠል የቡድኑ ሰራተኛ የመፈጸም አቅም ማሳደግና በልማት ሰራዊት አቋም እንዲገኝ ማድረግ ወሳኝ
ነው፡፡

በአሁኑ ጊዜ እየተካሄደ ያለው ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴ ውጤታማ በሆነ መንገድ ለማስቀጠል በተለይ 2016
በጀት አመት ለመጀመር ውጤታማ የሆኑ ልምዶችን በመለየት የመቀመርና ከማስፋት ባሻገር እንኝህ
ተሞክሮዎች እንዴት ውጤታማ እንደሆኑ በቦታው በመገኘት ልምድና ተሞክሮ መቅሰም ከዚያም የራስን
ተጨባጭ ሁኔታ ገምግሞ በልምድ ልውውጥ የታየውን ተሞክሮ ከራስ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር አዛምዶ ተግባራዊ
ማድረግ ተገቢ ነው፡፡

ከዚህ አንጻር በተለይ የዋና ስራ አስፈጻሚ ፋይናንስ ቡድን ቀጣዩን የልምድ ልውውጥ እቅድ አቅዷል፡

በአዲስ ከተማ ከፍለ ከተማ የዋና ስራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ራዕይ፣ ተልዕኮና እሴቶች

ራዕይ (VISION)
ራዕይ

መልካም አስተዳደር ወጪ ቆጣቢ የሆነ ውጤታማ እና ብቃት ያለው የሀብት አጠቃቀም


ተጠያቂነት እና ኃላፊነት ያለው ከምዝበራና ከብከነት የፀዳ ዘመናዊ የክፍያ ሥርዓት ሰፍኖ ማየት
ነው፡፡

ተልዕኮ
በክፍለ ከተማው ውስጥ የገቢ አሰባሰቡ፣ የወጪ አፈፃፀምና በጀት አያያዝና አጠቃቀም
ደንብና መመሪያ የተከተለ መሆኑን የንብረት አያያዝና አጠቃቀም በቁጠባና ውጤታማ
መሆኑን እንዲሁም የወጪና የክፍያ ሥርዓቱ የተጠናከረ እንዲሆን በማጣራትና በማረጋገጥ
ከማሻሻያ ሃሣብ ጋር በማቅረብ የማስተካከና የእርምት እርምጃ እንዲወሰድ ማድረግ፡፡

እሴቶች (VALUES)
 ታማኝነትና ተአማኒነት

 ግልጽነትና ተጠያቂነት

 ለህግ ለበላይ መገዛት

 ውጠየታማነት

 ያለእድልኦ ህዝብንና ዜጋውን ማገልግለ

 በቁርጠኝነት፤በብቃትና በተነሳሽነት መስረት

 ስራ ሁሉ በክብር ነው፡፡ ማገልገልም ክብር ነው፤፤

ኢላማ
በቡድኑ የለውጥ ስራውን አጠናክረው በመተግበር ውጤታማ ለመሆን ልምድና ተሞክሮ ለመለዋወጥ እና ያለን
ክፍተት መሙላት ማስቻል፡፡

በልምድ ልውውጥ ተሳተፊዎች

የልምድ ልውውጥ፡
1. የፋይናንስ ቡድን ባለሙያዎች
የልምድ ልውውጥ የሚካሄደባቸው ቦታዎች
የልምድ ልውውጡ የተሻለ ልምድና ተሞክሮ ይገኝባቸዋል ተብለውና በአፈጻጸማቸው ተሻለ ደረጃ ላይ ያሉ
የከተማ አስተዳደሩ እና ወረዳዎች የመረጠዉ ቦታ ልምድ ልውውጥ ማድረግ

በልምድ ልውውጥ የሚታዩ ዋና ዋና ፍሬ ሃሳቦች


1. የመረጃ አያያዝና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ስርአታቸው
2. የለውጥ ስራ ያለበት ደረጃ
3. IBEX አጠቃቀም
4. ውጤታማ መምረጥና ምርጥ ተሞክሮ የመቀመርና የማሳተፍ ሂደት ያለበት ደረጃ
5. የባለሙያዎች ቅንጂታዊ ስራ
6. የአገልግሎት አሰጣጥ ሀሁ………. አጠቃቀም
7. የህዝብ እርካታ ሁኔታ መለየት መለካት
8. የሰነድ አያያዝ
በልምድ ልውውጥ የሚሳተፉ ባለሙያዎች ብዛት

 ከጽ/ቤት
1. በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት የፋይናንስ ቡድን አጠቃላይ

ሰራተኛ

ማጠቃለያ

በአጠቃላይ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ ጽ/ቤት የፋይናንስ ቡድን ለማገልገል

የሚችል ተቋም ለመፍጠር ብቃት ያለው እቅድ በማቀድ አገልግሎት አሰጣጥ ስርአቱን ቀልጣፋ እና ውጤታማ

ለማድረግ የሚያስችል ነባራዊ ሁኔታ ከሌሎች ውጤታማ ቡድኖች ልምድ በመውሰድ በራሳችን ወረዳ

በተገቢው የተሻለውን ነገር መተግበር

You might also like