Professional Documents
Culture Documents
2015 1st Quarter Report
2015 1st Quarter Report
መግቢያ
የአስተዳደርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ዲን ጽ/ቤት በ 2015 ዓ.ም የአስተዳደር፤ የፋይናንስ፤ የልማትና ማህበረሰብ
አገልገሎት ተግባራትን ለማከናወን ሰፊ ዕቅድ በማቀድ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡ ከዕቅዶቹም መካከል በዋናነት
የኮሌጁ ማህበረሰብ የዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ የማድረግ፤ ለትምህርትና ስልጠና የሚያስፈልጉ
ግብአቶች በጥራትና በወቅቱ እንዲቀርቡ የማድረግ፤ የቤተመጻህት፤ የሳይንስ ቤተሙከራዎች፤ የአይሲቲ ላቦራቶሪዎች፤
የአይ አር ሲ እና የማባዣና ፎቶ ኮፒ ክፍሎች ተገቢዉን አገልግሎት ቀልጣፋና በቂ በሆነ ሁኔታ እንዲሰጡ የማመቻቸት፤
የኮሌጁን የፋይናንስ ፍሰት መመሪያን ጠብቆ እንዲሄድ መከታተልና መደገፍ፤ ድጋፍ ለሚስፈለጋቸዉ የኮሌጅ ዉስጥና
ለዉጭ ማህበረሰብ ድጋችን ማድረግ እንዲሁም የካፒታል ፕሮጀክቶችን የመከታተልና ሌሎችንም በርካታ ሥራዎች
መስራት ይጠበቅበታል፡፡
2
በዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ምክንያት ከአርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ወደ ዉጭ እንዲወጡ ለተደረጉ ተማሪዎች
በኮሌጃችን ግቢ ማደሪያ ቦታ በማዘጋጀት የማስጠለል ስራ ተሰርቷል፡፡
7. የመሰረተ-ልማት ስራዎች
የተቋረጠዉን የ G+2 መማሪ ህንጻ ግንባታ ክትትልና ድጋፍ በማድረግ እንዲጠናቀቅ ተደርጓል፡፡
1.2 ኮሌጁን በመወከል መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ አካላትና መዋቅር ጋር አስፈላጊዉ ግንኙነት
ተደርጓል፡፡
1.3 የአገልግሎት ክፊያዎች (የቴሌ፤ መብራትና፤ ዉሃ፤ የጋዜጣና መጽሔት) በወቅቱ እንዲከፈሉ ተደርጓል፡፡
1.4 የዉስጥ ገቢ ማስገኛ ስራዎችን በተመለከተ የመመረቂያ ገዋን በማከራዬት ገቢ የማስገኘት ስራ ተሰርቷል፡፡
1.5 በማኔጅመንት ጉዳዮች ላይ መሳተፍ አስፈላጊዉን አስተያዬትና ዉሳኔ የመስጠት ስራ ተሰርቷል፡፡
1.6 ዕቅድና ሪፖርት ዝግጅት በተመለከተ
በስራ ሂደቱ ስር የሚገኙ ሁሉም ፈጻሚዎች ሳምንታዊ ዕቅድ አዘጋጅተዉ በዕቅዱ መሰረት እየተገበሩ
ይገኛሉ፡፡
የ 2015 ዓ.ም እቅድ ለሚመለከተዉ አካል በወቅቱ ቀርቧል፡፡
የ 2014 ዓ.ም እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለሚመለከተዉ አካል በወቅቱ ቀርቧል፡፡
3
9. የትምህርትና ሥልጠና ግብአት አቅርቦትና ሥርጭትን በማሻሻል የሠልጣኞችን ውጤታማነትና ተጠቃሚነትን
ከማሳደግ አንጻር
በ 2013 ዓ.ም በተደራጀ መልኩ አዳዲስ ሞጁሎችን ማዘጋጀት ፤ ክለሳ የሚያስፈልጋቸዉን መከለስ ፤በወቅቱ
ሞጁሎችን መጠረዝና ማደራጀት እንዲሁም ጥምርታን በማሻሻል 1 ለ 1 ለተማሪዎች ለማሰራጨት
ዝግጅት ተደርጓል፡፡ የጎደሉ እና የተበላሹ ሞጁሎችን እንደገና የማባዛትና የጥረዛ፣ ለቀማ ሥራም ተከናዉኗል፡፡
በግዥ የሚቀርቡ ግዓቶችን በተመለከተ የኮቪድ መከላከያ ቁሳቁሶች ግዥ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ
ተከናዉኗል፡፡
የአይ ሲቲ ላቦራቶሪዎችን በበቂ የቴክኖሎጂ ቁሳቁስና 1 ለ 2 የተማሪ ኮምፒዉተር ጥምርታ የማደራጀት ስራ
ተከናዉኗል፡፡
1.2 የቅድመ ስራ ስልጠና ከመስጠት አንጻር የተከናወኑ የግብአት አቅርቦት ስራዎችና ስልጠናዉን ዉጤታማ ለማድረግ
የተከናወኑ ተግባራት
የተማሪዎች መረጃን መሰረት በማድረግ ሞጁሎችን የማዘጋጀት፤ የማባዛት ስራ ተሰርቷል፡፡
10. አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን በማስረጽ አሠራርን በማቀላጠፍ የደንበኞችን ፍላጎ ማርካትን በተመለከተ
በኮሌጁ ግቢ በየትኛዉም አከባቢና በሁሉም የስራ ክፍሎች ባለገመድና የገመድ አልባ የኢንተርኔት አገልግሎት
በተለያዩ ቦታዎች የመስጠት ስራ ታቅዶ ተከናዉኗል፡፡
የኮሌጁን የኢንተርነት አቅም ከ 30 ሜጋ ባይት ወደ 50 ሜጋ ባይት የማሳደግ ስራ ተሰርቷል፡፡
በአይሲቲ ዳታ ሰንተር በጊዜያዊነት ባለሙያ በመመደብ አገልግሎቱ እንዳይቋረጥ ተደርጓል፡፡
4
ቀላል የኤሌክትሮኒክስ ጥገናዎች በኮሌጁ የ ICT ባለሙያዎች ለተለያዩ የራ ክፍሎች
የመስጠት ስራ ተሰርቷል፡፡
ለመምህራን የኢንተርነት ክፍል እንዲደራጅ ተደርጓል፡፡
በኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ የሚያገለግሉ ስፔስፊከሽን ስራ ተሰርቷል፡፡
የተቋረጠዉን የ G+2 መማሪ ህንጻ ግንባታ በተመለከተ ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር በድጋሚ በመወያዬትና
አቅጣጫ በማስቀመጥ ግንባታዉ እንድቀጥል የማድረግና የመከታተል ስራ ተሰርቷል፡፡
አስቀድሞ አዲስ የ G+2 ላቦራቶሪ ህንጻ ዲዛይን ተሰርቶና በጀት ተፈቅዶ የነበረዉን ወደ ግንባታ የማስገባትና
የመከታተል ስራ ተሰርቷል፡፡
13. ሌሎች የአስተዳደራዊ ስራዎች
1.7 የድስፕልን ጥሰት በታየባቸዉ የስራ መደቦች ግለሰቦቹ በድስፕልን እንዲጠየቁ የማድረግ ስራ ተሰርቷል፡፡
1.8 የመልካም አስተዳደር ስራዎች አፈጻጸም በተመለከተ፡ በትምህርት መሳሪያዎች አቅርቦት ስርጭትና
የቴክኖሎጅ ስርፀት ዋና ስራ ሂደት የመልካም አስተዳደር ችግር በዋናነት በሚታይባቸው የስራ ክፍሎችና
አገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ዉይይት ተደርጎ ወደ ስራ ተገብቷል፡፡
1.9 ሌሎች በስራ ክፍሉ የተከናወኑ ተግባራትን በተመለከተ
ሀ) በማኔጅመንት ጉዳዮች ላይ መሳተፍ በተመለከተ አንደ አንድ ዋና የስራ ሂደት የማኔጅመንት ዉሳኔ ለሚፈልጉ ጉዳዮች
በማኔጅመንት ዉይይቶች በመሳተፍ አስፈላጊዉን አስተያዬትና ዉሳኔ የመስጠት ስራ ተሰርቷል፡፡
ከሁሉም ስራ ክፍል ፈጻሚዎች ጋር የክልሉን ዕቅድ መነሻ በማድረግ የግብ ስምምነት በመፈራረም ወደ
ስራ ተገብቷል፡፡
በስራ ሂደቱ ስር የሚገኙ ሁሉም ፈጻሚዎች ሳምንታዊ ዕቅድ አዘጋጅተዉ በዕቅዱ መሰረት እየተገበሩ
ይገኛሉ፡፡
የ 2012 ዓ.ም እቅድ አፈጻጸም ሪፖርት ለሚመለከተዉ አካል በወቅቱ ቀርቧል፡፡