You are on page 1of 14

መልካምዘር፤ሲሳይና ጓደኞቻቸው

የአካባቢ ብክለት ክትትልና ቁጥጥር

ጀማሪ አማካሪ የህ/ሽ/ማህበር

በኮ/ቀ/ክ/ከተማ በወረዳ ፣ ፤
13 14 15

አስተዳደር ስር በአነስተኛና ጥቃቅን

የስራ ዕድል ፈጠራ

1
ኢንተርፕራይዝና በአዲስ አበባ

የአካባቢ ጥበቃና አረንጓዴ ልማት

ኮሚሽን አማካኝነት የተቐቐመ

ማህበር የጥር የካቲትና መጋቢት

ዕቅድ፡፡

2
ጥር 2013 ዓ.ም
1.መግቢያ

የአካባቢ ጉዳይ ላለፉት አስርት አመታት የፕላኔታችን ቁልፍ ግን ትኩረት ያላገኘ ጉዳይ የነበረ ሲሆን በአሁኑ ወቅት
የአለም አቀፉ ህብረተሰብ የሁኔታውን አሳሰቢነትና በአካባቢ ላይ እየደረሰ ያለውን ጉዳት በመረዳት ልማትና አካባቢ
ተጠጣጥመው እንዲሄዱ በማድረግ የእድገት ቀጣይነትን ለማረጋገጥ እንዲያስችል በአገራት መካከል በርካታ አለም አቀፍ
ስምምነቶች ተደርገዋል፡፡

ኢትዮጵያም አብዛኞቹን ስምምነቶች የተቀበለች ስትሆን ይህንን መሰረት በማድረግ የአካባቢ ፖሊሲ፣ ስረትራቴጂዎች፣
የህግ ማእቅፎች እንዲወጡ የተደረገ ሲሆን ኪዚህም ጋር ተያይዞ በፌደራል ፣ ክልልና በከተማ አስተዳደሮች አስፈጻሚ
መስሪያ ቤት እንዲቋቋሙ ተደርጓል፡፡
በከተማ ደረጃ የአካባቢ ጉዳይ በይበልጥ ትኩረት የሚሻው በከተማ መስፋፋት፣ ከፍተኛ የመሰረተ ልማት ግንባታዎችና
የልማት እንቅስቃሴዎች የተነሳ በከተማ አካባቢ ላይ በተለይም በስርአተ ምህዳር፣ ብዝሃ ህይወት ላይ የሚደርሰው
ጥፋትና የአካባቢ ብክለት የከፋ ከመሆኑ ባሻገር እለት ተእለት የሚታየውን ከፍተኛ የሙቀት መጠን መጨመር የከተሞች
ልዩ መገለጫ እየሆነ መጥቷል፡፡
በታህሳስ 2013 ዓ/ም የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአካባቢ ጥበቃና አረንጓዲ ልማት ኮሚሽን በወጣው መረጃ መሰረት
በስፋት እንደገለፀው የተፈጥሮ ሃብት ልማትና እንክብካቤ ጋር ተያይዞ በአረንጓዴ ቦታዎች ልማትና አጠባበቅ እንዲሁም
ከአካባቢ ብክለት በተለይም በከተማው ውስጥ ባሉ የብክለት ምንጭ የሆኑ ትላልቅ ተቐማት የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ
አያዝዝን በተመለከተ በመንግስትና በህብረተሰቡ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ መሆኑን ያስገነዝባል፡፡
በዚህም መሰረት መልካምዘር፤ሲሳይና ጓደኞቻቸው የአካባቢ ብክለት ቁጥጥርና ክትትል ጀማሪ አማካሪ ህ/ሽ/ማ
በኮ/ቀ/ክ/ከ ስር በሚገኙት በወረዳ 13፤14፤15 ላይ የሚደርሰውን የአካባቢ ብክለትና የተፈጥሮ ሃብት መመናመንን
ለመከላከል የሚያስችል እቅድ ማዘጋጀት አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

3
2. የወረዳ 13፤14፤15 ነባራዊ ሁኔታ
2.1 አካባቢ ጥበቃና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት

የአለማችንን የአካባቢ ሁኔታ ከጊዜ ወደ ጊዜ አሳሳቢ እየሆነ የመጣ ሲሆን በተለይ ከዓለም ሙቀት መጨመርና ከአየር

ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ የአለማችን ቀዳሚ አጀንዳ እየሆነ ነው፡፡ የሚሊንየሙ የልማት ግቦች ላይም የአካባቢያዊ

ዘለቄታዊነትን ማረጋገጥ የሚለው አብይ ግብ በርካታ ስልቶችና የልማት አመልካቾችን አስፍሯል፡፡

በአገራችን 1984 ዓ.ም ወዲህ ለአካባቢ ጥበቃ ትኩረት ተሰጥቶት የአካባቢ ሥራዎች እንቅስቃሴ ከተጀመረበት ጊዜ

አንስቶ በአዲስ አበባ ከተማም በክልልና በክፍለ ከተማ የአካባቢ ጥበቃ ተቋቁሞ ሥራዎች ሲከናወኑ ቆይተዋል፡፡

ከ 2 ዐዐ 1 ዓ.ም ጀምሮ በ BPR ጥናት ሰነድ መሠረት የአካባቢ ጥበቃ ጉዳይ ከማዕከል እስከ ወረዳ መዋቅር ተዘርግቶለት

እንዲሁም በክ/ከተሞች በጽ/ቤት ደረጃ እንዲቋቋም ተደርጐ በሥራ ላይ ይገኛል፡፡ ይህም መንግስት ለአካባቢ የሰጠው

ትኩረት ያመለክታል፡፡

የወረዳ 13፤14፤15 አስተዳደርም ለአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች ተግባራዊነት የተለያዩ ዕቅዶችን ነድፎ በእንቅስቃሴ ላይ

ሲገኝ ከዘርፈ ብዙ የአካባቢ ችግሮች አኳያ የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች የባለድርሻ አካላትንና የህብረተሰቡን ተሳትፎ የሚሹ

ለመሆናቸው ሊሰመርበት ይገባል ፡፡

ወረዳዎቹ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ የሚኖርበት ሰፊ የኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ፣ የንግድ እንቅስቃሴዎች እና መኖርያ

ቤቶች የሚገኙበት እንደመሆኑ መጠን በርካታ የአካባቢ ችግሮች የሚስተዋሉበት ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ጥቂቶቹን

ለመጥቀስ ያክል፡-
 ከሚመነጨው ደረቅ ቆሻሻ 20% የሚሆነው የማይሰበሰብና አግባብ ባልሆነ አያያዝና አወጋገድ በየቦታው

የሚጣል ነው፡፡
 የቆሻሻ ገንዳዎቹም ደረጃውን በጠበቀ ቦታ የማይቀመጡ፣ ከልጆችና ከእንሳሳት ንክኪ እንዳይኖራቸው

ያልተከለሉና ወቅቱን ጠብቀው የማይነሱ በመሆናቸው ለአካባቢ መበከል አስተዋፅኦ ማድረጋቸው፡፡


 የሚመነጨው የፍሳሽ ቆሻሻ ደረጃውን በጠበቀ የፍሳሽ መስመር ወደ ማጣሪያ የሚገባው በጣም አነስተኛ

መሆኑ፡፡
 መኖሪያ ቤቶች የመፀዳጃ አገልግሎት ያላቸው ውስን ከመሆናቸው በተጨማሪ በተለያዩ ወረዳዎች የህዝብ

መፀዳጃ አገልግሎት የሚሰጡ ቤቶች ስርጭታቸው አነስተኛ ነው፡፡

4
 የማምረቻና አገልግሎት ሰጭ ተቋማት፣ እንዲስትሪዎች፣ ጋራዦች፣ ሆቴሎች፣ ሆስፒታሎች ወዘተ

ቆሻሻዎችን ወደ ወንዞች የጐርፍ ማስወገጃ ቱቦዎች፣ ቦዮች እና ሌሎች አካባቢዎች መልቀቃቸው ሌላው

ብክለትን ከሚያባብሱ መካከል የሚጠቀሱ ናቸው፡፡


ማህበሩ በትስስር መሥራት የሚገባቸው ሴክተር መሥሪያ ቤቶች ውስጥ

ከአካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት፤ ከንግድ ጽ/ቤት ፣ ከሥራ አስኪያጅ፣ ከጤና ጽ/ቤት ፣ከወጣቶችና በጎፍቃደኞች ጽ/ቤት፤ ሰላምና
ጸጥታ ጽ/ቤት ፣ ከባህልና ቱሪዝም ጽ/ቤት ፣ ከፍትህጽ/ቤት ጋር በትስስር በመሥራት ተልዕኮውን ማሳካት ይችላል

3. የማህበሩ ራዕይ ተልእኮ እና እሴቶች


3.1 ራዕይ
አዲስ አበባ ከተማ 2017 ዓ.ም ከአካባቢ ብክለትና ከተፈጥሮ ሃብት መራቆት ተጠብቃ ከአካባቢ ጋር
የተጣጣመ ልማት የሚካሄድባትና በዓለም አቀፍ ደረጃ በተምሳሌትነት ከሚታዩ 15 ከተሞች አንዷ
ማድረግ

3.2. ተልዕኮ
አዲስ አበባ ከተማን ከብክለትና ከተፈጥሮ ሃብት መራቆት ለመከላከልና ልማትን ከአካባቢ ጋር
ለማጣጣም በጥናትና በምርምር የታገዘ ክትትልና ቁጥጥር እንዲሁም በህዝብ ተሳትፎ የአካባቢና
የተፈጥሮ ሃብት እንክብካቤ በማካሄድ የከተማዋ ነዋሪ በንፅሑና ጤናማ አካባቢ የመኖር መብቱ
እንዲጠበቅ ማድረግና ዘለቄታዊ ልማትና የተፈጥሮ ሃብት አጠቃቀምን ማረጋገጥ ፡፡

3.3. እሴቶች
 ተጠያቂነት
 ግልፅነት
 የላቀ አገልግሎት መስጠት
 ለለውጥ ዝግጁነት
 በዕውቀትና በዕምነት መመራት/መሥራት
 አካባቢ የሕይወት መሰረት መሆኑን ማመን
 ከአካባቢ ጋር የተጣጣመ ልማት ለዘላቂ ዕድገት መሰረት እንዲሆን መስራት
 በአካባቢ ጉዳዮች ላይ ሕብረተሰቡን ማሳተፍ ናቸው

4. የማህበሩ የጥር የካቲትና መጋቢት 2013 ዓ.ም ዕቅድ


4.1 የትኩረት አቅጣጫዎች
 በየወረዳው የባለድርሻ አካላትን መለየትና ማደራጀት ለዕድሮች፤ለነዋሪዎች ህብረት፤መንግስታዊና መንግስታዊ
ያልሆኑ ተቐማት፤በጎ ፍቃደኞች፤ወዘተ
 የግንዛቢ መፍጠሪያ ሰነድ ማዘጋጀት

5
 ውይይትና የጋራ ግንዛቤ መፍጠር ለዕድሮች፤ለነዋሪዎች ህብረት፤መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቐማት፤በጎ
ፍቃደኞች፤ወዘተ
 የጋራ ዕቅድ ማዘጋጀት
 ግንዛቤ መፍጠር-ለማህበረሰብ፤የብክለት ምንጭ ለሆኑ ተቐማት፤ወዘተ
 ከፍተኛ ብክለት እያስከተሉ ያሉ አምራችና አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን መለየት
 በተዘጋጀው የመረጃ መሰብሰቢያ ፎርማት መሰረት መረጃ መሰብሰብ መጀመር
 በሂደቱ ከብክለት ምንጭነት ያልታቀቡ ተቐማትን ለኮሚሽኑ ማሳወቅ

4.2. የማስፈፀሚያ እስትራቴጂዎች

 ህብረተሰቡንና ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ የአካባቢ ልማትና እንክብካቤ ስራዎችን መስራት


 ሕጎች፣ደንቦችና፣የአፈፃፀም መመሪያና ማኑዋል መተግበር
 የክትትልና ግምገማ ስራዎችን መስራት
 መጠነ ሰፊ ግንዛቤ የመፍጠርና የማስጨበጥ ስራ መስራት
 በወረዳዎች ውስጥ ያሉትን ባለድርሻ አካላትን በማጠናከር የአካባቢን ጉዳይ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ

5. ስጋቶች

 ስራ ማስኬጃ በጀት በተፈለገው ጊዜ አለመጽደቅ


 የግብአት ችግር
 ከአንዳንድ ተቋማት ተቀናጅቶ ለመሰራት አለመቻላቸው
 አመራሮች ለአካባቢ የሚሰጡት ትኩረት አነስተኛ መሆን
 የጀማሪ አማካሪ ማህበሩ የተለያዩ ስራዎች ለመስራት ቢሮ በጊዜው አለማግኘት

6. የክትትልና ድጋፍ ስርዓት


6.1. የሪፖርት ስርዓት
 በየሳምንቱ ፣በወር እና የሶስት ወር የስራ አፈፃፀም ሪፖርት እንዲቀርብ ክትትል ማድረግ
 በሚቀርበው ሪፖርት እና በመስክ በሚደረግ ቅኝት የመደበኛ ስራዎችን በመከታተል ጥሩ የሰሩትን
እንዲቀጥሉበት ደከም ያሉትን የሚደገፉበትን ስልት በመነደፍ ተግባራዊ ማድረግ
 በአፈፃፀም ዝቅተኛ ደረጃ ያላቸውን የማህበሩን አባላት ከሚመለከታቸው አካባቢ ጥበቃ ባለሙያዎች ጋር
በመነጋገር ስልጠና እንዲሰጣቸው በማድረግ የአፈፃፀም አቅማቸውን ማሳደግ

6.2. የሱፐርቪዥንና ግብረ መልስ አሠራር

 በየሳምንቱ፣ በየወሩ እና የሶስት ወር ሪፖርቶች ላይ በመመስረት እያንዳንዱ የስራ ክፍል ምን ያህል እንዳከናወነ
ይገመገማል

6
 በሪፖርቶቹ ላይ በመንተራስ በአፈፃፀም የታዩ ጉድለቶች የእርምት እርምጃ እንዲወሰድባቸው ግብረመልስ
ይሰጥባቸዋል
 በተለያዩ መድረኮች ስራዎች ይገመገማሉ የማስተካከያ አቅጣጫም ይወሰዳል፡፡

7. ማጠቃለያ

በአካባቢ ላይ መጠነ ሰፊ ግንዛቤ የሚፈጥሩና የሚያስጨብጡ ስራዎችን በመስራት የህብረተሰቡንና የባለድርሻ አካላትን
ያሳተፈ የአካባቢ ልማትና እንክብካቤ ስራዎችን መስራት፣ የአካባቢ ሕጎች፣ ደንቦችና የአፈፃፀም መመሪያ እንዲተገበሩ
በማድረግ የክትትልና ግምገማ ስራዎችን በመስራትና እንዲተገበሩ በማድረግ ማህበሩ የበኩሉን አስተዋፅኦ ይደረጋል ፡፡

ዋና ዋና ዓላማዎች

ዓላማ፡- 1- በኮ/ቀ/ክ/ከ በወ-13፤14፤15 ያለውን የአካባቢ ብክለት መከላከልና መቀነስ፣

ቁልፍ ተግባር

 ሶስቱን አቅሞች (የመንግስት፣ የሕዝብ፣ የድርጅት) በመጠቀም እቅድን በመጠቀም በጊዜና በጥራት
መፈፀም
 ሞርኒንግ ብሪፊንግ መልሶ በማደራጀት የክትትል ድጋፍና ግምገማ ሥርዓት መዘርጋት
ዓበይት ተግባራት

በኮ/ቀ/ክ/ከ በወ-13፤14፤15 እየተከሰተ ያለውን የአካባቢ ብክለትና የሕግ ማዕቀፎችን ለመተግበር እንዲያስችል
የሕብረተሰቡ ግንዛቤ በማሳደግና የተቀናጀ የቁጥጥር ስርዓት በመዘርጋት የአካባቢ ብክለት መከላከል፡፡

በማህበሩ የአካባቢ ብክለት ክትትልና ቁጥጥር ጀማሪ አማካሪ ቡድን አባላት የሚከናወኑ አበይት ተግባራት

ዓለማ 1፡ በኮ/ቀ/ክ/ከ በወ-13፤14፤15 የሚደርሰውን የአካባቢ ብክለትን በመከላከልና በመቆጣጠር ለነዋሪዎቿ ንጹህና

ጤናማ አካባቢ መፍጠር፡፡

ግብ 1፡ በኮ/ቀ/ክ/ከ በወ-13፤14፤15 ልማትና አካባቢ ተጣጥመው እንዲሄዱ ለ 6 አዳዲስ አገልግሎት ሰጭና ማምረቻ
ተቋማት/ፕሮጀክቶች ከአካባቢ አንጻር እንዲገመገሙ ማድረግ ፡፡
1.1. ይሁንታ እንዲሰጣቸው የሚፈልጉ ተቋማትን ጥያቄ መቀበል
1.2. የመስክ መረጃ መሰብሰብ ፤ሙያዊ ትንታኔ ማድርግና ምላሽ መስጠት
1.3. በአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ያለፉ ፕሮጀክቶችን አተገባበር መከታተልና መቆጣጠር

7
1.4. የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ አሰራርን ከየወረዳዎች አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ጋር እየተገናኙ መገምገምና
ድጋፍ ማድረግ
1.5. ከሚመለከታቸው ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጋር ትስስር መፍጠር
1.6. በአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ዘርፍ የባለሙያውንና የባለድርሻ አካላትን አቅም ማሳደግ
ግብ 2፡ በኮ/ቀ/ክ/ከ በወ-13፤14፤15 የአካባቢ ብክለትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል አሰራርን በመዘርጋት በ 70
አገልግሎት ሰጭና ማምረቻ ተቋማት ላይ ክትትልና ቁጥጥር ማድረግ ፡፡
2.1. መረሀ-ግብር ማዘጋጀት
2.2. የተቋሙን ማኔጅመንት ማናገር፤ ስለስራው ማሳወቅና የተቋሙን የአካባቢ ሁኔታ መገምገም
2.3. የግምገማውን ውጤት መተንተን ማሳወቅና የመፍትሄ እርምጃ ማመላከት
2.4. የአካባቢ ብክለትን ለመከላከል የሚረዱ ስልቶችን ነድፎ በተቋማት መካከል የውድድር መንፈስ
መፍጠር
ግብ 3፡ በኮ/ቀ/ክ/ከ በወ-13፤14፤15 የብክለት ይወገድልኝ አቤቱታዎችን ማስተናገድ
ግብ 3.1 ፡ 6 የድምጽ ብክለት ይወገድልኝ አቤቱታዎችን መቀበል፣ ማስተናገድና ምላሽ የመስጠት ስራ መስራት ፡፡
3.1.1 ቅሬታዎችንና ጥቆማዎችን መቀበል
3.1.2 የመስክ መረጃ ማሰባሰብ፤ ሙያዊ ትንታኔ ማዘጋጀትና ምላሽ መስጠት
3.1.3 የማስተካካያ እርምጃ እንዲወሰድ ማድረግና መከታተል
ግብ 3.2፡ 10 የፍሳሽ ውኃ ብክለት ይወገድልኝ አቤቱታዎችን መቀበል፣ ማስተናገድና ምላሽ የመስጠት ስራ መስራት ፡፡
3.2.1 ቅሬታዎችንና ጥቆማዎችን መቀበል
3.2.2 የመስክ መረጃ ማሰባሰብ፤ ሙያዊ ትንታኔ ማዘጋጀትና ምላሽ መስጠት
3.2.3 የማስተካካያ እርምጃ እንዲወሰድ ማድረግና መከታተል
ግብ 3.3፡ 3 የአየር ብክለት (የብናኝ፣ የሽታ፣ የጭስ፣ ወዘተ) ይወገድልኝ አቤቱታዎችን መቀበል፣ ማስተናገድና ምላሽ
የመስጠት ስራ መስራት ፡፡
3.3.1 ቅሬታዎችንና ጥቆማዎችን መቀበል
3.3.2 የመስክ መረጃ ማሰባሰብ፤ ሙያዊ ትንታኔ ማዘጋጀትና ምላሽ መስጠት
3.3.3 የማስተካካያ እርምጃ እንዲወሰድ ማድረግና መከታተል
ግብ 4፡ በኮ/ቀ/ክ/ከ በወ-13፤14፤15 ብክለት ባደረሱ 6 ተቋማትና ድርጅቶች ላይ አስተዳደራዊና ሕጋዊ እርምጃ
እንዲወሰድ ለኮ/ቀ/ክ/ከተማ ለወረዳ 13፤14፤15 አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት ማሳወቅና እርምጃ መወሰዱን መከታተል ፡፡
4.1 የአካባቢ ብክለትን ለመቆጣጠር የሚያስችል ስርአትን መዘርጋት
4.2 ከህጉ ውጭ ብክለትን በሚያደርሱ ተቋማት ላይ አስተዳደራዊና ህጋዊ እርምጃ እንዲወሰድ ለየወረዳዎቹ
ማሳወቅ
4.3 የተወሰደውን እርምጃ አፈጻጸም መከታተል
ግብ 5. በኮ/ቀ/ክ/ከ በወ-13፤14፤15 የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ይሁንታ ያገኙ ፕሮጀክቶችን አተገባበር መከታተልና
መቆጣጠር

8
ተግባር 1. የፕሮጀክቱን ተጽእኖ ግምገማ ዶክመንቱና የአሉታዊ ተፅዕኖ የአካባቢ አያያዝ ዕቅድ በማነጻጸር ለግምገማ የሚሆን
ቼክሊሰት ማዘጋጀት፣ መስክ በመሄድ ዶክመንቶች በተሰጠቸው ይሁንታ መሠረት እየተሰራ ያለውን ስራ በቼክሊስቱ መሰረት
መገምገም
ተግባር 2. ግብረመልስ ለሚመለከተው አካል/ለተቋማቱ ማቅረብ፣ የጎላ ግድፈት በታየባቸው ፕሮጀክቶች እንዲያስተካክሉ
አስተደደራዊ እርምጃ እንዲወሰድባቸው ለየወረዳዎቹ ማሳወቅ

ግብ 6፡ በኮ/ቀ/ክ/ከ በወ-13፤14፤15 ውስጥ በ 2 መድረኮች በአካባቢ ብክለት ችግሮችና መፍትሄዎች ላይ ለ 60 ለተለያዩ


አገልግሎት ሰጪ ተቐማት የግንዛቤ ማስጨበቻ ስራ መስራት ፡፡
6.1 በአካባቢ ችግሮችና መፍትሄዎቻቸው ላይ ለባለድርሻ አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ አውዴጥናቶችንና
ስልጠናዎችን መስጠት
6.2 ለተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቐማት የሚደርሱና በተለያየ አካባቢ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ 60 ብሮሸሮችን
በማዘጋጀት ማሰራጨት
ግብ 7፡ በኮ/ቀ/ክ/ከ በወ-13፤14፤15 1 ምርጥ ተሞክሮዎችን የመቀመርና የማስፋት ስራ መስራትና ለተቐማዊ ለውጥ መስራት ፡፡

7.1 ምርጥ ተሞክሮ የሚቀሰምባቸውን ተቋማት መለየት


7.1 የመንግስት የስራ ሰዓት ማክበር
7.2 የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ በመመሪያው መሰረት ይሁንታ ለሚገባቸው ድርጅቶች መስጠት

9
10
ሂደት ዝርዝር መርሀ-ግብር

የክንውን ጊዜ
ዓላማዎች
ግቦችና ዝርዘዝር ተግባራት
(goals)
(objectives and መለኪያ ከጥር-
activities) የካቲተ ጥር የካቲት መጋቢት ምርመራ
ኢላማ

ግብ 1፡ በኮ/ቀክ/ከ በወ-13፤14፤15 በቁጥር


ዓለማ 1፡ ልማትና አካባቢ ተጣጥመው እንዲሄዱ 3 3
በኮ/ቀ/ክ/ከ በወ- ለ6 አዳዲስ አገልግሎት ሰጭና
13፤14፤15 ተቋማት/ፕሮጀክቶች ከአካባቢ አንጻር
የሚደርሰውን እንዲገመገሙ ማድረግ ፡፡
1.1 ይሁንታ እንዲሰጣቸው የሚፈልጉ   
የአካባቢ ብክለትን
በመከላከልና ተቋማትን ጥያቄ መቀበል

በመቆጣጠር 1.2 የመስክ መረጃ መሰብሰብ ፤ሙያዊ   


ለነዋሪዎቿ ትንታኔ ማድርግና ምላሽ መስጠት
ንጹህና ጤናማ
1.3 በአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ያለፉ   
አካባቢ መፍጠር፡፡
ፕሮጀክቶችን አተገባበር
መከታተልና መቆጣጠር

1.4 የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ አሰራርን   


ከየወረዳዎች ጋር እየተገናኙ
መገምገምና ድጋፍ ማድረግ

1.5 ከሚመለከታቸው ሴክተር መስሪያ   


ቤቶች ጋር ትስስር መፍጠር

1.6 በአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ ዘርፍ   


የባለሙያውንና የባለድርሻ አካላትን
አቅም ማሳደግ

ግብ 2፡ በኮ/ቀ/ክ/ከ በወ-13፤14፤15 በቁጥር 70 10 30 30


የአካባቢ ብክለትን ለመከላከልና
ለመቆጣጠር የሚያስችል አሰራርን
በመዘርጋት በ 70 አገልግሎት ሰጭና
ማምረቻ ተቋማት ላይ ክትትልና
ቁጥጥር ማድረግ ፡፡
2.1 መረሀ-ግብር ማዘጋጀት

2.2 የተቋሙን ማኔጅመንት ማናገር፤  


ስለስራው ማሳወቅና የተቋሙን የአካባቢ
ሁኔታ መገምገም

11
2.3 የግምገማውን ውጤት መተንተን  
ማሳወቅና የመፍትሄ እርምጃ
ማመላከት የአካባቢ ብክለትን
ለመከላከል የሚረዱ ስልቶችን
ነድፎ በተቋማት መካከል የውድድር
መንፈስ መፍጠር

ግብ 3፡ በኮ/ቀ/ክ/ከ በወ-13፤14፤15 በቁጥር 100%


የብክለት ይወገድልኝ አቤቱታዎችን
ማስተናገድ
ግብ 3.1፡- 10 የድምጽ ብክለት በቁጥር 6 3 3
ይወገድልኝ አቤቱታዎችን መቀበል፣
ማስተናገድና ምላሽ የመስጠት ስራ
መስራት ፡፡
3.1.1 ቅሬታዎችንና ጥቆማዎችን   
መቀበል

3.1.2 የመስክ መረጃ ማሰባሰብ፤  


ሙያዊ ትንታኔ ማዘጋጀትና
ምላሽ መስጠት

3.1.3 የማስተካካያ እርምጃ  


እንዲወሰድ ማድረግና
መከታተል

ግብ 3.2፡ 6 የፍሳሽ ውኃ ብክለት በቁጥር 6 3 3


ይወገድልኝ አቤቱታዎችን መቀበል፣
ማስተናገድና ምላሽ የመስጠት ስራ
መስራት ፡፡
3.2.1 ቅሬታዎችንና ጥቆማዎችን  
መቀበል

3.2.2 የመስክ መረጃ ማሰባሰብ፤  


ሙያዊ ትንታኔ ማዘጋጀትና
ምላሽ መስጠት

3.2.3 የማስተካካያ እርምጃ እንዲወሰድ 


ማድረግና መከታተል
ግብ 3.3 ፡ 1 የአየር ብክለት (የብናኝ፣ በቁጥር 1 1
የሽታ፣ የጭስ፣ ወዘተ) ይወገድልኝ
አቤቱታዎችን መቀበል፣ ማስተናገድና
ምላሽ የመስጠት ስራ መስራት ፡፡
3.3.1 ቅሬታዎችንና ጥቆማዎችን   
መቀበል

3.3.2 የመስክ መረጃ ማሰባሰብ፤  


ሙያዊ ትንታኔ ማዘጋጀትና
ምላሽ መስጠት

12
3.3.3 የማስተካካያ እርምጃ  
እንዲወሰድ ማድረግና
መከታተል

ግብ 4፡ በኮ/ቀ/ክ/ከ በወ-13፤14፤15 ውስጥ በቁጥር 6 6


ብክለት ባደረሱ 6 ተቋማትና ድርጅቶች
ላይ አስተዳደራዊና ሕጋዊ እርምጃ
እንዲወሰድ ለኮ/ቀ/ክ/ከ ለወረዳ
13፤14፤15 አካባቢ ጥበቃ ጽ/ቤት
ማሳወቅና እርምጃ መወሰዱን
መከታተል፡፡
4.1 የአካባቢ ብክለትን ለመቆጣጠር   
የሚያስችል ስርአትን መዘርጋት

4.2 ከህጉ ውጭ ብክለትን በሚያደርሱ   


ተቋማት ላይ አስተዳደራዊና ህጋዊ
እርምጃ እንዲወሰድ ለየወረዳዎቹ
ማሳወቅ

4.3 የተወሰደውን እርምጃ አፈጻጸም 


መከታተል

ግብ 5፡በኮ/ቀ/ክ/ከ በወረዳ 13፤14፤15 በቁጥር 60 30 30


ውስጥ በ 2 መድረኮች በአካባቢ ብክለት
ችግሮችና መፍትሄዎች ላይ ለ 60
ለተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቐማት
የግንዛቤ ማስጨበቻ ስራ መስራት ፡፡
5.1 በአካባቢ ችግሮችና  
መፍትሄዎቻቸው ላይ ለባለድርሻ
አካላት የግንዛቤ ማስጨበጫ
አውዴጥናቶችንና ስልጠናዎችን
መስጠት

5.2 ለተለያዩ አገልግሎት ሰጪ ተቐማት 


የሚደርሱና በተለያየ አካባቢ
ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ 60
ብሮሸሮችን፤

ግብ 6፡ በኮ/ቀ/ክ/ከ በወረዳ 13፤14፤15 በቁጥር 1 1


ውስጥ 1 ምርጥ ተሞክሮዎችን የመቀመርና
የማስፋት ስራ መስራትና ለተቐማዊ ለውጥ
መስራት ፡፡
6.1 ምርጥ ተሞክሮ የሚቀሰምባቸውን 
ተቋማት መለየት

13
6.2 የመንግስት የስራ ሰዓት ማክበር   

6.3 የአካባቢ ተጽዕኖ ግምገማ በመመሪያው  


መሰረት ይሁንታ ለሚገባቸው ድርጅቶች
መስጠት

14

You might also like