You are on page 1of 5

አጠቃላይ ሪፖርት

የፕሮጄክት አጠቃላይ ሁኔታ

አምስት የተለያዩ ኮንትራክተሮች እንዳሉ ይታወቃል፤ እነርሱም

1. የባንትዋሉ
2. የታምራት ተመስገን
3. የሎዛ
4. የዮቴክ
5. የመንገድ ፕሮጄክቶች ናቸዉ
1. የባንትዋሉ ፕሮጄክት

ሁለት ብሎኮችን የያዘ ፕሮጄክት ሲሆን

አንደኛዉ/ ብ 1/ ያለበትን ደረጃ ለማሳየት ያህል

 የዉስጥ ልስን ገና ይቀረዋል


 የዉጭ ልስን ብዙ የቀረዉ
 የበር/የመስኮት/ ፍሬም ገጠማ በጅምር ላይ ይገኛል
 የሮቶ ማስቀመጫም እንዲሁ በጅምር ላይ ነዉ

ሁለተኛዉ ብሎክ / ብ 2/

 የዉስጥ ልስን ገና ይቀረዋል


 የዉጭ ልስን ብዙ የቀረዉ
 የበር/የመስኮት/ ፍሬም ገጠማ በጅምር ላይ ይገኛል፤የሮቶ ማስቀመጫም እንዲሁ በጅምር ነዉ
 የሁለቱም ብሎኮች አገልግሎት የዶርም አገልግሎት ነዉ

የሎዛ ኮንስትራክሽን
የፕሮጄክቱ ዉል ከተቁዋረጠ ወዲህ ምንም ዓይነት ሥራ አልተካሄደም ማለት ሌላ ኮንትራከተር አልቀረበም

በፕሮጄክቱ የተካተቱት ህንጻዎች


የኪችን /Kitchen/
 የካፌ
 የላዉንጅ
 የሠራተኞች መኖሪያ ሦስት ህንጻዎች ገና ብዙ የሚቀራቸዉ ናቸዉ፡፡ለሁሉም ብሎኮች የዉስጥ ቴራዞ
አልተነጠፈም፤ኮርኒስ አልገባም፤የፍሳሽ ማስወገጃ አልተሰራም፤ የበር/መስኮት/ ፍሬም ብቻ ተገጥሞአል፡፡

3.የታምራት ተመስገን ፕሮጄክት /የቀድሞዉ ዩናይትድ/


ሀ. የአስተዳደር ህንጻ

 የወለል ሥራ ተገባድዶአል
 የኮሪደር ቴራዞ ንጣፍ በጅምር የቀረ
 በር/መስኮት/ ፍሬም አልተገጠመም
 የኮርኒስ ሥራ በአብዛኛ ተሰርቶአል
 ሌሎች የፊኒሺንግ ሥራዎች ገና ናቸዉ

ለ. የሥልጠና ህንጻ

ጣሪያ ቢዋቀርም ጸሃይና ዝናብ እየተፈራረቀበት ስለሚገኝ ከጥቅም ዉጭ እየሆነ ይገኛል


የዉስጥና የዉጭ ልስኖች በጅምር የቀሩ
በር/መስኮት/ፍሬም አልተገጠመም

ሐ. ላይብረሪ

o የወለል ንጣፍ/ሊሾ/ የለዉም


o ኮርኒስ የለዉም
o የዉስጥ ልስን አላለቀም
o በር/መስኮት/ ፍሬም በጅምር ላይ ነዉ

4. የዮቴክ ፕሮጄክት

ሁለት ብሎኮች ያሉት ሲሆን፤

 ጊዜአዊ ርክክብ ከተደረገ ወዲህ ያለዉ እንከን /ግድፈት/ ያለተስተካከለ መሆኑን


 የተሰባበሩ ወይም ያልተገጠሙ መስኮቶች መኖራቸዉ
 የሚያፈስስ ጣሪያ መኖሩን
 ኮሪደሮች አካባቢ ኮርኖሱ የተበሳሳ መሆኑ

5.የመንገድ ግንባታ/ኮንስትራክሽን/

 ሥራዉ ከጅምሩ ሲታይ ከእስታንዳርድ በታች በመሆኑ ምክንያት ሙሉ በሙሉ መሠራት እንዳለበት ግንዛቤ
እንዲኖር

6. ከወሊሶ ከተማ አስተዳደር ጋር ሊሠሩ የታቀዱ ፕሮጄክቶች

6.1 የጎርፍ መዉረጃ /ዲች /


6.2 የመዋዕለ - ህጻናት ግንባታ
6.3 የዩኒቨርሲቲ ካምፓሱን ካርታ/የባለቤትነት ማረጋገጫ/ የማሠራት ዕቅድ ሲሆኑ፤

የጎርፍ መዉረጃዉ ግንባታ አልተጀመረም፤ ምክንያቱም የመሬት ባለይዞታዎቹ አርሶ አደሮች ካሳ


ስላልተከፈላቸዉ

የመዋዕለ - ህጻናት ግንባታዉም አልተካሄደም፤ ምክንያቱ ፕሮጄክቶች ሁሉ በሲሚንቶ ዋጋ መናር ሰበብ ሥራ ስላቆሙ
ነዉ፡፡ ማናቸዉም ኮንትራክተር ባሁኑ ጊዜ በሥራ ላይ የሉም፡፡

የዩኒቨርሲቲ ካምፓሱ ካርታ/የባለቤትነት ማረጋገጫ/ ተሠርቶ ተሠጥቶናል፡፡

7. ትምህርትና ሥልጠና
7.1 ትምህርት
ለቅዳሜና እሁድ የትምህርት መርሃ ግብር በአራት የትምህርት መስኮች !30 ዕጩዎች የመግቢያ ፈተና
ወስደዉ ዉጤታቸዉን እየተጠባበቁ ገኛሉ፡፡ የትምህርት መስኮቹም
7.1.1 project leadership and management
7.1.2 Environment and climate change management
7.1.3 Accounting and finance
7.1.4 Development management ናቸዉ፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ አስፈላጊዉ የቅድመ ዝግጅት ሥራ
ከወዲሁ መደረግ እንዳለበት መገንዘብ ያሻል፡፡
7.2 ሥልጠና

እስካሁን ድረስ ባጠቃላይ አራት የአጫጭር ሥልጠና ፕሮግራሞች የተካሄዱ ሲሆን


7.2.1 ለዞኑ አመራርና ለከተማዉ አመራር ሁለቴ /ዋና ዋና ርዕሶች ሀ. የአመራር ብቃትና ስኬት 2.የመሪ
ባህርይ 3. ስኬታማ አመራር
7.2.2 ለዉስጥ ሠራተኞች የአቅም ግንባታ ይረዳ ዘንድ ሁለቴ ተሰጥቶአል፡፡ ዋና ዋናዎቹ ርዕሶች

1.በሠራተኛ መብትና ግዴታ ዙሪያ

2. በዕቅድ አዘገጃጀት ዙሪያ ናቸዉ፡፡

8. የመሠረተ - ልማት ዝርጋታን በተመለከተ

8.1 የዉሃ መስመር ተዘርግቶ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል የግፊት ኃይል በማይፈልጉ የምድር ላይ
አገልግሎቶች ብቻ/
8.2 የሥልክ መስመር

የመደበኛ ስልክ አገልግሎትም ሆነ የገመድ ዓልባ ስልክ አገልግሎቶች አልተዘረጉም/የለም/


8.3 መብራት
ከአምቦ የደንበኞች ማስተባበሪያ ሪጅን ጋር በመተባበር በባለሙያ ጥናት ተደርጎና እስፔሲፊኬሽን
ቀርቦ 㙀 ሽፈላጕ ክፍያ የተጠናቀቀ ቢሆንም በትራንስፎርመር እጥረት/እጦት/ ሰበብ እስካሁን
ድረስ አገልግሎት ማግኘት አልተቻለም ፡፡
9. የግቢ ዉበትና የአረንጉዋዴ አሻራ መርሆ ትግበራ

የግቢ ዉበትንና የአረንጉዋዴ አሻራን መርሆ ትግበራ እዉን ለማድረግ የተከናወኑ ተግባራትን ቀጥሎ
ካለዉ ሠንጠረዥ መረዳት ይቻላል፡፡

ዓ.ም የተተከሉ ችግኞች የጸደቁ ምርመራ


ብዛት ችግኞች
በመቶኛ
2011 360 ( 12.5 ) በቂ ዝግጅት ስላልተደረገ
2012 120 (77.5 ) አትክልተኞች ስለተንከባከቡ
2013 500 (97.2 ) አትክልተኞች ስለተንከባከቡ
110 - እስካሁን የተተከሉ/ሰኔ ወር ዉስጥ/
2014 250 - ገና ወደ ፊት የሚተከሉ

10.አሁን ያሉ ሠራተኞች ብዛትና የሥራ መደቦቻቸዉ

ተ.ቁ የሥራ መደብ የሠራተኛ ብዛት ምርመራ


1 የካምፓስ ፖሊስ 13
2 የጽዳት ሠራተኞች 5
3 አትክልተኞች 2
4 የጉልበት ሠራተኞች 2
5 የንብረት ሃላፊ 1
6 ሴክሬተሪ 1
7 ድምር 24

10. መልካም የሆኑ ጅምሮች


 እስታፉን ለማብቃት በራስ አገዝም ሆነ በሌሎች አሰልጣኞች አማካይነት ሥልጠናዎች መሰጠታቸዉ
 ለግቢ ዉበት የተተከሉትን ችግኞች የመንከባከብና የማጽደቅ መጠኑ የሚበረታታ መሆኑ
 የሰብአዊም ሆነ የቁሳዊ ሃብት አያያዝና አስተዳደር ፈር እየያዘ መምጣቱ
 እስታፉ ማህበራዊ መስተጋብሩ ጤናማ እንዲሆንና ምቹ የሥራ አካባቢ እንዲፈጠር እየተደረገ ያለዉ
ዉህደት/መጣጣም/
 በትምህርትም ሆነ በሥልጠና የአካባቢዉን ህብረተሰብ ተደራሽ የሚያደርጉ ተግባራት መከናወናቸዉ

11. የአጋጠሙ ችግሮች

o እጅግ የተለጠጠ የግንባታዎች መዘግየት


o በመዋኛ ሥፍራ በታቆረዉ ኩሬ ዉሃ ሳቢያ የሰዉ ህይወት ማለፉ
o የመሠረተ - ልማቶች ዝርጋታ አለመሳካታቸዉ
12. ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች
 ግንባታዎቹን የማስቀጠል ሥራ
 የአጥር ጥገና
 ማዕከሉን ኮስት ሴንተር የማድረግ
 ለዊክ ኤንድ የትምህርት ፕሮግራም ቅድመ ዝግጅት ማድረግ
 አስፈላጊዉን የሰዉ ሃይል መሙላት
 የግቢዉ ስፋት ዉስን ስለሆነና የአፈሩም ባህርይ ልዩ ጥንቃቄ የሚሻ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ለዋና
/ / የታቀደዉ ሥፍራ ወደ ፍል ዉሃዉ መገኛ / / ወጣ ብሎ እንዲሠራ ሌላ ፕሮጄክት ቢቀረጽና
ተግባራዊ ቢደረግ
 የማዕከሉ መዋቅር በተቻለ ፍጥነት ቢጸድቅና ገቢራዊ ቢደረግ ተገቢዉን አገልግሎት በመስጠት
ጥሩና ተመራጭ ዩኒቨርሲቲ ካምፓስ መሆን ይቻላል፡፡

ሰኔ 2014 /ወሊሶ/

You might also like