You are on page 1of 23

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን

የኮርፖሬሽኑን የቅርንጫፍ ቢሮዎች ለመክፈት የተደረገ የትግበራ ስትራቴጂክ ሰነድ

የመስክ ጥናትሪፖርት

አዲስ አበባ

1
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን

ማውጫ

ክፍል አንድ

1. መግቢያ

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በአሁኑ ወቅት ሁለት ቅርንጫፎች (አንድማዕከላዊ ልዩ ቅርንጫፍ በዋናው መ/ቤት እና አንድ
በጁቡቲ የሚገኝ ቅርንጫፍ) ያሉት ሲሆን፣ ነገር ግን ኮርፖሬሽኑ ካሉት ፖሮጀክቶች ብዛትና ዓይነት እንዲሁም ሌሎች በተልዕኮ ከተሰጠው
የቢዝነስ ሥራዎች ስፋት አንጻር በዋናው መ/ቤት እና ባሉት ሁለት ቅርንጫፎች ብቻ ሥራዎችን መምራት አስቸጋሪ መሆኑ ስለታመነበት
ቅርንጫፎችን በመክፈት የተነሳበት ዓላማ ከግብ ማድረስ ያስችላል፡፡

በመሆኑም የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን የመንግስት የልማት ድርጅት እንደመሆኑ መጠን፣ በራሱ ገቢ
የሚተዳደር ተቋም ነው፡፡ ስለዚህም ኮርፖሬሽኑ ወጪ ቆጣቢ እና ውጤታማ በሆኑ የስራ መስኮች ላይ በመሰማራት ትርፋማ
በመሆን ከሌሎች መሰል የአገር ውስጥና አለም አቀፍ ተቋማት ጋር ተወዳዳሪ መሆን ይጠበቅበታል፡፡ ስለሆነም ወጪ
ለመቆጠብና ውጤታማ ለመሆን እንዲቻል በአራቱም አቅጣጫዎች ቢሮዎችን መክፍት ዋንኛ መንገድ ነው፡፡

በመሆኑም በአገሪቱ በአራቱም አቅጣጫዎች ማለትም በጅግጅጋ ጅማ.ኮምቦልቻ እና አርባምንጭን በመምረጥ የኮርፕሬሽኑን የስራ አድማስ
ላመስፋት አስፈላጊ መረጃ በመሰብሰብ ወደ ትግበራ ለመግባት ይህ ጥናት እንዲዘጋጅ ተደርጎዋል ስለሆነም ጥናቱን እንዲያጠኑት ከተዋቀሩት
ቡድኖች ደቡብ ምዕራብና ምስራቅ ኢትዮፕያን የሚያካትት የመስክ ጥናት እንደሚከተላው ቀርቦዋል፡፡

1.1 ዋና ዓላማ

የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በአገራችን


በሚገኙ በአራት የተለያዩ ከተሞች ማለትም ኮምቦልቻ፣
ጂማ፣ ጂጂጋ እና አርባ ምንጭ ከተሞች ላይ ቅርንጫፍ
ጽ/ቤቶችን ለመክፈት የአደረጃጀትና የከተሞች ልየታ
ጥናት ተከናውኖ በስትራቴጂክ ማኔጅመንቱ ተቀባይነት
አግኝቷል፡፡ በመሆኑም የዘህ ሰነድ ዋና ዓላማ በአገራችን
2
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን

ከላይ ከተጠቀሱት በምስራክና ደቡብ ኢትዮፕያ


አካባቢዎች ቅርንጫፎችን ለመክፈት የተከናወነውን
የአደረጃጀት ተግባራዊ ጥናት መረጃ መሰብሰብና
መተንተን፡፡
1.2 ዝርዝር ዓላማ

 በክልሎቸና በዞኖቹ የኮንስትራክሽን ሥራዎች እንቅስቃሴ፣የኮንስትራክሽን አይነቶች፣እና የግብዓት አቅርቦት በመለየት


ኮርፖሬሽኑ የበለጠ ምርታማ እንዲሆን የሚያግዙ አዋጪ ስራዎችን ለይቶ ገቢ ሊያመነጭ እንደሚችል መረጃ
መሰብሰብ፤
 በአካባቢው ምን ዓይነት ለኮንስትራክሽን ጥሬ ዕቃ ግብዓት ሊሆኑ የሚችሉ ማዕድናት እንደሚገኙ መረጃ መሰብሰብ እና
መተንተን
 ኮርፖሬሽኑ በከተማው የቅርንጫፍ ጽ/ቤት ቢሮ ለመክፈት የሚያስችለውን ምቹ ቦታ አፈላልጎ ማግኘት

1.3 የጥናት ስልት

ጥናቱን ለማካሄድ የመጀመሪያና ሁለተኛ ደረጃ የመረጃ ምንጮችን በመጠቀም መረጃዎችን የማሰባሰብ ስራዎች

ተሰርተዋል፡፡ የመጀመሪያ ደረጃ የመረጃ ምንጭ ቁልፍ የመረጃ ምንጭ የሆኑ የስራ አላፊዎችንና ሞያተኞችን ቃለ
መጠይቅ ማድረግ ፣የጋራ የቡድን ውይይት መድረኮችን በመጠቀም የሌሎች መስራቤቶችን ተሞክሮና ቤንች ማርክ
ውሰድ፣ መጠይቅ ማዘጋጀት፣ቃለመጠይቅ በማድረግ ሲሆን ሁለተኛ መረጃ የልዩ ልዩ መስራ ቤቶችን አላፈነትና

ተግባር የሚግፁ በሶፍት እና በአርድ ኮፒ መረጃዎችን ማሰባሰብ የተቻለ ሲሆን የተሰበሰቡ መረጃዎችን በማደራጀት

ገላጭ በሆነ መልኩ ለመተንተን ተችሏል፡፡

1.4 ወሰን (Scope)

ይህ ጥናት በኮርፖሬሽኑ የቅርንጫፍ ቢሮዎች ለመክፈት በደቡብ ምዕራብ አትየጵያ(ጅማ እና አካባቢው) እና

መስራቅ ኢትዮጵያ( ጅግጅጋ፣ድሬደዋ፣ሐረር) ላይ ብቻ መረጃ በሰብሰብና ለመተንተን የተዘጋጀ የመስክ ጥናት

ነው፡፡

3
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን

1.5 የጥናቱ ውስንነቶች (Limitations)

ይህ ጥናት ምንም እንኳ የኮርፖሬሽኑ ስራ መብዛት እና ተደራሽነት ለማስፋት የቅርንጫፎች እጥረት ላይ የሚታዩ

ችግሮችን እና ኮርፕሬሽኑ በተለያዩ የአገራቸን ክልሎች ቢሮዎች ሊያስከፍት የሚያስችል የቢዝነስ አማራጮችንና

የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች ጥገና እና የኮንትራክሽን ግብዓት ምርቶችን ስራ ለማግኘት በበአጭር ጊዜ ለመዳሰስ

የተሞከረ ቢሆንም ጥናቱን በተፈለገው ልክ ለማከናወን የመረጃ ውስንነት ብሎም አላፊዎችን በወቅቱ

አለማግኘት፣የተጠናከረ እና የተደራጀ መረጃ አለማግኘት፣መረጃን በጊዜው አለመላክ ችግር ነበር፡፡ ይሁን እንጂ

በተቻል መጠን መረጃውን በመሰብሰብ ለመተንተነት ተሞክሮዋል

4
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን

ክፍል ሁለት

2 በመስክ ላይ የተሰበሰቡ መረጃ


2.2 ጅማ

1. ፐሮፋይል

2.1.1 የጅማ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት (ፎቶ)

በከንቲባ ፅ/ቤት በኩል በተዘገጀው የውውይት መድረክ ስለ ኮርፕሬሽናቸን አስፈላጊውን መረጃ


ከሰጠን በዋላ እንዲሁም የኮርፕሬሽኑን የሚሰራውን ስራ ጨምረን የመጣንበትን ዋና ዓላማ በሰፊ
ማብራሪያን ተወያይተናል፡፡የከንቲባው ጽ/ቤት የመጣንበትን ዓላማ ሀሳብ በሚገባ በመረዳት
ደስተኛ መሆናቸውንና ለምንስራቸው ማንኛውን ስራ ተገቢውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ በመግለስፅ
ከሚመለከታቸው የስራ ክፍሎቸ ማለትም ከኮንስትራራክሽን ቢሮ፣ ከማዕድን ቢሮ፣ ከመሬት
አስተዳደር ቢሮ፣ከግብር፣ ከኢንቨትመንትና ንግድ ቢሮ ተወካዮች ጋር ክቡር ከንቲባው በተገኙብት
ሰፊ የውይይት መድረክ እነደሚያዘጋጁ ለጠየቅናቸው ጥቄዎች በሙሉ በሚመለከታቸው የስራ
ክፍሎች ምላሽ እነደምናገኝ ተስፋ በማድረግ ሰኞ ሐምሌ 17 ከጠሮ እንደሚይዙልን ቃል በመግባት
ስብሰባችንን ጨርሰናል፡፡

2.1.2 የጅማ ከተማ አስተዳደር የእቅድና በጀት አፈፃፀም ቢሮ(ፎቶ)

ከአቶ ካሚል ሲፊያን ሽፋ ጋር በነበረን ሰፋ ያለ ውይይት የመጣንበት ዓላማ ከጅማ ከተማ ፍላጎት
ጋር የሚስማማና የመንግስት ፕሮጅክቶችን ሊያግዝ የሚችል አካል በማግኘታቸው በመደሰት

5
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን

በከተማዋ የኮንስትራክሽን ስራ ትልቁ ችግር ከጎናቸው ሆኖ የሚያማክር የአማካሪ ድርጅት


ባለማግኘታቸው ለፕሮጅክቶች መጓተት ትልቅ ችግር እንደሆነ ገልፀው ኮርፕሬሽኑ በአማካሪ ስራ
ቢሳተፍ ትልቅ ፍላጎት እንዳላቸው ገልፀዋል፡፡በተጨማሪም ይህ የማማክር ችግር ስላለባቸው ጅማ
ዩኒቨርስቲን ቀጥረው በማሰራት ላይ እንዳሉ እና በእነሱ ብቻ ችግሮች እንደማይቀረፉ ገልፀዋል፡፡
ይህ በእንዲ እንዳለ የከተማውን የ 2016 ዓ.ም ዕቅድ እንደሚልኩልን ቃል ገብተዋል፡፡

ሰንጠረዥ 2፡1 የጅማ ከተማ 2015-2017 የከተማ ኮንስትራክሽን እቅድ

Table 11. Summary of Three Year Rolling CIP for 2015 - 2017 by IBEX Urban Investment Components
No Urban Investment Component EFY 2015 EFY 2016 EFY 2017 Total

001 Road - - - -
002 Rehabilitation of Roads - 28,000,000.00 38,000,000.00 66,000,000.00
003 Integrated multiple infrastructure and land services - - - -

004 Sanitation (Liquid waste) including vacuum trucks etc.


- - - -
005 Solid waste management - - - -
006 Urban Drainage - 25,820,665.00 57,000,000.00 82,820,665.00
007 Urban Disaster Risk Management - 183,997,526.30 66,997,526.30 250,995,052.60
008 Built facilities - - 25,000,000.00 25,000,000.00
009 Urban Green Infrastructure - - - -
Consultancy serv. for designs and Contract
0010
management - - - -
0011 Capacity Building - - - -
Total - 237,818,191.30 186,997,526.30 424,815,717.60

especial Projects
1 Boye Park By Prime minister offive 924,000,000
2 Aba Jifar Park 430,000,000
3 New aspalt road 250,000,000

Total 1,841,818,191.30

2.1.3 የጅማ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት

ከጽ/ቤቱ ኃላፉ ጋር በመገናኘት የኮርፕሬሽናችንን የስራ እንቅስቃሴ በጥልቀት በማስረዳት


እንዲሁም የመጣንበትን ዋና አላማ በሚገባ በመግለፅ ሰፊ ውይይት አካሄደናል፡፡ በምላቸውም
በአሳባችን የተስማሙና መደሰታቸውን በመግለጽ ከጎናችን በመሆን አስፈላጊውን የስራ ትብብር
በማድረግ ከፍተኛ ተነሳሽነት እንዳላቸሀው አረጋግጠዋል፡፡በተጨማሪም በስራቸው ላሉ የስራ

6
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን

ክፍሎች በእጅ ስልካቸው በመደውል አስፈላጊውን መረጃ እንድናገኝ እገዛ አድርገውልናል በዚህ
መሰረት

ከዞኑ ማዕድን ቢሮ፣ኮንስተራክሸን ቢሮ እንዲሁም ከኢንቨስትመንት በየቢሮዋቸው ጋር በመገኘት


አስፈላጊውንን ውይይት አድርገናል፡፡የ 2016 እቅድ አፈፃፀም ሪፓርት ማግኘት መቻላችንን
በጥያቄ ብናቀርብም በሄድንበት ወቅት እቅዱ ፀድቆ እንዳልደረሳቸውና ሲድርሳቸሀው እንደሚልኩ
ግልፀውልናል፡፡

2.1.4 የጅማ ዞን አስተዳደር ም/ኃላፊ ጽ/ቤት (ፎቶ)

ከጅማ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት ም/ኃላፊ ከወ/ሮ ረሂማ ጋሊ ጋር በነበረን ውይይት ሰፋ ያለ


የኮርፕሬሽናችንን የስራ ዕድል ካሳወቅናቸው በኋላ በዞኑ የሚገኙ የኮንስታረክሽን ኳሪ ሳይቶች
በጠይቅናቸው መሰረት በዞኑ በኪ. ሜ ርቀት የሚገኙ የተለዩ የኳሪ ሳይቶች መኖራቸውንና
እነዚህም፡-

በ 20 ኪ.ሜ የሚገኝበት አካባቢ በ 50 ኪ.ሜ የሚገኝበት


የሚገኙ የሚገኙ ወረዳዎች አካባቢ
ወረዳዎች

ዴዶ ኮይሻ በሚወስደው ፒስታ ሸቤ ሰንቦ ጅማ ሚዛን ቴፒ


መንገድ አስፓልት መንገድ

ሰቃ ጨቆርሳ ጅማ ሚዛን ቴፒ አስፓልት

7
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን

መንገድ

ማና ወደ አጋሮ የሚወስደው
አስፓልት መንገድ

ቀርሳ ከጅማ ወደ አዲስ አባባ


የሚወስደው መንገድ

1.ማዕድን ቢሮ

በዞኑ ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ እንቅስቃሳ መኑሩን በመግለፅ ከፍተኛ የመዐድን ክምቸት መኖሩንና
በኢትዮጵያ ጂሎጂካል ሰርቬ መስራ ቤት በኩል ጥናት እየተካሄደ መሆኑንና አስፈላጊ መረጃ
በእጃቸው ሲገባ መረጃውን ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ነገር ግን በቢሮዋቸው በኩል
ያለውን የማዕድን ክምችት መረጃ በሁለት ቀን ውስጥ መረጃውን እነደሚሰጡን ቃል
ገብተውልናል፡፡ በተጨማሪም ከእኛ ፍላጎት በመነሳት በእኛ በኩል ዝግጅነቱ ካለ ለሲምንቶ
የሚሆን የድንጋይ ከሰል እንዲሁም አይረን የማምረት ስራ መስራት እንደሚቻልና የክልሉን
መንግስት መመሪያ በመጠቀም ማምረት እነደሚቻል ግልጸዋል፡፤ በተጨማሪም ለኮንስትራክሽን
ሚሆን የኮንስትራክሽን ኳሪ መኖሩን እንዲሁምና የእምነበረድና የግራናይት ግብዓት እንዳለ በቂ
ጥናት አለመኖሩን ገልጸውልናል፡፡ለዚህም ዋናው ችግር ብለው የገለፁት የመንገድ እና የበጀት ችግር
ናቸው፡፡በማጠቃለያቸው እንደተናገሩት ቢሮ ከከፈታቸሁ በኋላ በየወረዳው ወርድን በጋራ
እንሰራለን ብለው ቃል ግብተዋል፡፡

8
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን

2.ኢንቨስትመንት ቢሮ

ይዘን በመጣነው ሀሳብ ደስተኛ መሆናቸውንና አበረታቸው መሆኑን ገልፀውልን፡፡ በመቀጠልም


የዞኑ የኢንቨስትምንት በጋራ ለመስራት የአግሮ ኢዱስትሪ ምርቶች ቅድሚያ የሚሰጣቸውና የዞኑ
ከፍተኛ ፍላጎት መሆኑን በመግለፅ ለምሳሌም ያህል የሳሙና ፋብሪካ፣ የብስኩት ፋብሪካ ፍላጎት
እናለ፡፡በመጨረሻም የሳሙና ማምረቻ አቅርቦት እነዳለ ገልጸው እርሻን በተመለከተ በቂ እና ብቁ
አርሶ አደር መኖሩን ገልተዋል ስለሆነም የገበሬው አቅርቦት በቂ መሆኑን ግልፀዋል፡፡

3.ኮንስትራክሽን ቢሮ

ከዞኑ የኮንስትራከሽን ቢሮ አላፊ ጋር በመገናት ስለ ኮርፕሬሽኑ ሰፋ ያለ ውይይይት በማድረግ


በዋናነት የመጣንበትን አላማ በማስረዳት ሳባችንን የገለፅን ሲሆን አላፊዋ በአሳቡ እደተደሰቱና
በጋራ ለመስራት ፍቃደኛ መሆናቸሀውን በመግለጽ በአብዛኛውበዞኑ የሚሰሩ የኮንስትራክስን
ስራዎች በ ማይክሮ ፋይናንስ የሚከናወኑና ከእዛ ባለፈ በኦሮሚያ ኮንስትራክሽን ኮርፕሬሽን
የሚሰሩ መሆኑን ግልፀዋል፡፡በመሆኑም ከኮንስትራክሽን ግብዓት ከሲሚንቶ ማቅረብ ችግር
በስተቀር በሌሎቹ የኮንሰትራክስን ግብዓት ይህን ያህል እጥረት አለመኖሩን ገልፀው ሲሚንቶ
ማምረት ከተቻለ ሰፊ ገበያ መኖሩን ገልጸዋል፡፡ቢሮ ከተከፈተ በኋላ ብዙ ስራዎችን እነደምንሰራ
ቃል የገቡልን ሲሆን የ 2016 እቅድ ጸድቆ አለመምጣቱን ግልጠዋል፡፡

2.1.5 ከታቀደው ወይም ከሄድንበት አላማ ውጪ ያገኘናቸው ጠቃሚ ሀሳቦች

ከታቀደው የጥናት ስራ ውጪ የጥናት ስራውን አስፍቶ የቢዝነስ እድሎችን ለማግኘት በጅማ


ከተማ ከሚገኘው የኢትጵያ የመንገዶች አስተዳደር ዲስትሪክትና ከመንገድ ፕሮጀክት አስተዳደር

9
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን

ፅ/ቤቶች ጋር ሁለት ቀን የፈጀ የፎከስ ግሩፕ ዲስክሽን እና በመጠይቅ ለጥናት አላማ የሚጠቅሙ
አስፈላጊ መረጃዎችን መሰብሰብ የተቻለ ሲሆን ዋና ዋና አሳቦች እንዲሚከተለው ቀርበዋል፡፡

1.የኢትጵያ የመንገዶች አስተዳደር ዲስትሪክት

1.የተገኙ ጥሩ ጎኖች

በሄድንበት ወቅት የኢትዮፕያ መንገዶች ባለስልጣን ከኮርፕሬሽኑ ጋር ለመስራት ደስተኛ


በመሆናቸው መረጃውን ለመስጠት በመልካም ፍቃደኝነት በመተባበር ሳባችንን በመቀበል ለማገዝ
ዝግጁ መሆናቸውን ገልፀውልናል በተጨማሪም ጊዜያቸውን በመስጠት ስራችንን ትኩረት
ስለሰጡት ሚበረታታ ሀሳብ መሆኑን እንገልፃለን

1.1 ከኮንስትራክን ግብዓት አቅርቦት አንፃር

የራሳቸው የሆነ የተለያየ ኳሪ ሳይቶች መኖራቸውን የገለፁልን ሲሆን ተገቢውን ፕላንት ወይም
ስቶን ክሬሸር ለመትከል በጋራ ለመስራት ፍላጎት እንዳላቸው ሆኖም ግን ጠጠር መፍጨት ብቻ
ሳይሆን ለመንገዱ የሚረዱ የቢቱሚኒየስ ማቴሪያል ማቅረብ ካልተቻለ ከባድ ስለሚሆን
እንዲሁም ፈንጂ አቅርቦ ስራውን በጋራ ለመስራት መስማማታቸው ተገፀዋል፡፡

ኮንስትራክን ማነሽነሪን በተመለከተ በዋናናነት የአስፓልት ሚክሲንግ ፕላንት ከፍተኛ የፍላጎት


እጥረት እንዳለና በዚህ ጉዳይ ላይ ኮርፕሬሽኑ ካለምንም ቅድምመ ሁኔታ አብሮ ለመስራት
ፍቃደኝነት እንዳላቸው ተግልፀዋል፡፡በተጨማሪም በ 2015 የነበረ የአስፓለት ፍላጎት ባይሟላም
በ 2016 ላይ ግን ችግሮችን ለመፍታታ በታቀደው መሰረት ቢቲሙኑላይ እቅድ ስልተያዛ
ኮርፕራሽኑ ይህን መልካም አጋጣሚ እነዲጠቀም አቅጣጫ ተቀምጣል ስለሆነም ይህ ጉዳይ
የሚሳካ ከሆነ በቀጥታ ፕላንት በመትከል ጠጠር ማምረት ስራ ላይ መሰማራት እንደምንችል
ተገጻል፡፡

1.2 ከስትራክሽን ማሽነሪ ጥገና እና ስፔር ፓርት አቅርቦት አንፃር

10
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን

ከኮርፕሬሽናችን ጋር በጋራ ለመስራት ከፍተኛ ፍላጎት ያለ መሆኑንና በስፔር ፓርት ችግር ጥገና
ባለማግኛት በርከት ያሉ ማሽኖች የቆሙ እና የማይሰሩ ስለሆነ በኮርፕሬሽናችን በኩል የጥገና እና
መለዋወጫ አቅርቦት ቢቀርብ ብዙ ስራዎችን በጋራ መስራት እንደሚቻል በውይይታችን ላይ
ተረድተናል፡፡

በዚሁ መሰረት ከዲስትሪክቱ በተገኛ መረጃ መሰረት በ 21016 የኮንስትራክሽን እቅድ


እናንደሚከተለው ተቀምጧል ከዚህ እቅድ በመነሳት በራሳቸው አቅም ብቻ ማሟላት የሚቸገሩ
እና የኮርፕሬሸናችንን እገዛ በእጅጉ እንደሚፈልጉ ተረድተናል

 ቴብል(2016

ለፅ/ቤት ሚሆን ቦሮ ለመክፈት

ፅ/ቤቱን በአጭር ጊዜ ለክፈት ፍላጎት ስላል በራስ አቅም ለመክፈት ከያዝነው ዓላማ ገር በቂ ግዜ
ስለሌልን በዲስትሪክታቹ ግቢ ውስጥ ጊዜዊ ቢሮ ማግኛት እንድንችል ባነሳነው ጥያቄ መሰረት
ዲስትሪክቱ የኛን ስራ መጀምር ከፍተኛ ፍላጎት መኖሩን ሳቡን ተቀብሎ ለተፈፃሚነት በኩል
በሀየር ሌቭል ንግግር እንዲኖር ተነግሮናል፡፡

 በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የጅማ አካባቢ ፕሮጀክት አስተዳደር ፅ/ቤቶች

11
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን

በኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር የጅማ አካባቢ ፕሮጀክት አስተዳደር በኩል በስሩ 6 ፕሮጅክቶች
ሲኖሩ 5 የውጪ (የቻይና) መንገድ ስራ ተቋራጭ ሲሆን የቀረው 1 ድግሞ የግል ድርጅት
በማሰራየክልሉን መንገድ ግንባታ ያሰስተዳድራል፡፡ ስለሆነም ከጥናት ዓላማ ጋር አጋዥ የሚሆን
ከፅ/ቤቱ ያገኘነው መረጃ እንደሚከተለው በቴብል ተቀምጧል፡፡

ሰንጠረዥ

ከፅ/ቤቱ በተደረገ ውይይት በ 6 ቱም ፕሮጅክቶች ላይ የስራ ተቋራጮቹ በራሳቸው አቅም


የኮንስትራክሽን ግብዐዓቶችን እነደሚያመርቱ የተገለፀ ቢሆንም እንኳን ካለው ከፍተኛ
የኮንስትራክሽን ግብዓት አቅርቦት በቂ እንዳልሆነና ኮርፕሬሽናችን በዚህ ግብዓት ማምረት ስራ ላይ
ገብቶ እንዲሰራ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለ ነገር ግን በቀላሉ የገበያ እድሎችን ለማግኘት የባለቤቱን
ፍቃድ ማግኘትነትነ በንዑስ ተቋራጮቹ ከኮርፕሬሽናችን ጋር ግዢ ለመፈጸም አስፈላጊ አቅጣጫ
መኖር እንዳለበት ተቀምጧል፡፡

2.2 ድሬደዋ

ፕሮፋይል

2.2.1 የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ጽ/ቤት እና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ

ከአቶ ገበየሁ ጥላሁን የመጣንበትን ጉዳና የኮርፕሬሽኑነን አሁን ያለበትን አቋም በሚገባ
በማስረዳት እንዲሁም በድሬደዋ ከተማ ለመስራት ያሰበንቻውን ስራዎች በዝርዝር በመግለፅ
በምላሹም ደስተኛ መሆናቸውን እና መረጃ የሚገኝበትን ቦታ የስራ ትዕዛዝ/ደብዳቤ በመምራት
የሚያስፍለጉ መረጃዎችን ሰብስበናል፡

12
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን

2.2.2 ለድሬደዋ አስተዳደር ገንዘብ ኢኮኖሚና ልማት ቢሮ

ከቢሮ አላፊ ተወካይ አቶ ኃይለማሪም ዳዲ ጋር ሰፋ ያለ ውይይት በማድረግ ኮርፖሬሽናችን


በአሁን ሰዓት ያለብትን ትልቅ የኮንስትራክሽን አቅም በአገር ውስጥም በውጪም
የሚያከናውናቸውን የኮንስትራክሽን ስራዎች በዝርዝር በማስረዳ የመጣንበት አላማ በትክክል
እንዲገነዘቡ አድርግናል፡፡እስቸውም ዓላማውን በመረዳት በሰጡት አስተያየት ለድሬደዋ ከተማ
የሚጠቅም መሆኑን በማስረዳት በአሁኑ ሳዓት በድሬደዋ ከተማ የሚከናወኑ የኮንስትራክሽን
ስረዎችን በዝርዝር በማስረዳት የከተማውን የስራ ፍላጎትና የ 2016 እቅድ በሚቀጥለው
ሰንጠረዥ ሰተውናል

ሰንጠረዝ 1.1

በአጠቃላይ ግብዓት በተመለከተ ይህ ነው የሚባል ችግር እንደሌለና ነገርግን የሲሚንቶ እና የብረት


አቅርቦት ላይ አቅሙ ካለ ብታግዙን የሚል ዓሳብ ሰተውናል ሆኖም ግን ለፕጅክቶቹ መዘግየት
የአማካሪ መዐንዲስ ችግር፣ዲዛይን ሳያልቅ ወደ ስራ መግናትና፣የፕሮጅክት አዋጭነት ጥነናት
አለመኖር እንደችግር ተቀመጦዋል፡፡

2.2.3 ለድሬደዋ አስተዳደር ንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ

ኢንቨስትምነት በተመለከተ በድሬደዋ ከተማ እና አካባቢው ለግንባታ ግብዓት የሚሆኑ የማዐድን


ሀብት በስፋት የሚገኝ ሲሆን በተለየ መልኩ ምንም እንኳን በድሬደዋ ከተማ የሴሜንቶ ፋብሪካ
ቢኖርም ካለው ከፍተኛ የሲሚንቶ ፍላጎት አንፃር ኮርፕሬሽናችን ፋብሪካ የሚገነባበትን ሁሜታ
ቢያመቻች የድሬደዋ ከተማ አስተዳደር አስፈላጊውን እገዛ በማድረግ በጋራ ለመስራት ዝግጁ
መሆናቸውን ገልፀውልናል፡፡በአሁኑ ሰዓት በጥናት የተለዩ ለጠጠርና ለግንባታ የሚውሉ ካባዎች
ስላሉ የክሩሸር ፕላንቶችን በመትከል ማምረት እንደሚቻል እና ለተለያ የኮንስትራክሽነን
ፕሮጀክቶች ገልፀውልናል፡፡

13
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን

2.2.4.ለድሬደዋ አስተዳደር ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ

ከኮንስትራክሽን ቢሮ አላፊ አቶ አለሌ አሰን ጋር በነበረን ጥሩ የውይይት መድረክ የኮርፕሬሽኑን


ዘርፈ ብዙ የስራ እንቅስቃሴ በማስረዳትና የኮርፕሬሽኑን ፍላጎት ሰፊ ማብራሪያ ካቀረብን በዋላ
ከመጣንበት የስራ እቅድ ጋር አስፈላጊ የሚሆን መረጃ ምናገኝበት ቦታ ማለትም ለድሬደዋ ህንፃ
ሹምና ለመንግስት ግንባታና ኮንትራክት አስተዳደር ኤጀንሲ ክፍል መርተውናል

2.2.4.1 ድሬደዋ ከተማ ህንፃ ሹም

ከአቶ ኤፍሬም ግርማይ ጋር በነበረን ውይይት የመጣንበትን ዓላማ በመረዳት እንዲሁም


የኮርፕሬሽኑ ያለበትን ደረጃ በማበረታታትና በቅርቡ በኮርፕሬሽኑ ተዘጋጀውን የኢግዚብሽን
ኢቨንት ተካፍለው እንደነበረና ደስተና መሆናቸውን ገልፀው ለመጣንበት አላማ ድሬደዋ የግብዓት
አቅርቦት ችግር እንደሌለባቸውና የሚሰሩት ኮንትራክተሮች የአቅርቦት ችግር አለመኖሩንና ከበድ
ያለ ስራ ካለ ለቻይና ድርጅት እንደሚሰጡ በተጨማሪም ኮንስትራክሽኑን እራሳቸው ቁጥጥር
እንደሚያደርጉ እና የግብዓት ችግር የሲሚኒቶ ችግርና የብረት አቅርቦት ቢኖርም በየጊዜው
ሚቀያየረው የዋጋ ንረት ችግር እነዳለ እና ኮርፕሬሽኑ በእነዚህ ሁለት የኮንስትራክሽን ግብዓት
አቅርቦት ላይ ትኩረት እንዲያደርግ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡

2.2..4.2 የመንግስት ግንባታና ኮንትራክት አስተዳደር ኤጀንሲና የከተማ ኮንስትራክሽን ቢሮ

አቶ ደራራ ኢብራይም የቢሮ አላፊና በኮንስትራክሽን ቢሮ ምክትል አላፊ ጋር በነበረን ቆይታ


የግብዓት እና የአቅርቦትበተላይም የጠጠር፣አሸዋ ድንጋይ ችግር አለመኖሩን ገልፀው በተጨማሪም
የውስጥ አግም ግንባታ የኮንስትራክሽን ኮንትራት አስተዳደር ፣ፕሮጅክት ማኔጅመንት ከዘመናዊ
ቴክኖሎጂ የዲዛይን ስልጠና በመስጠት ለሰራተኞች የአቅም ግንባታ ቢደረግ ድሬደዋን እንደ
አገርአግ ማሳደግ እነደሚቻል በመግለጥ ኮርፕሬሽኑ ባቋቋመው የስልጠና ማዕከል እንዲያገኑኙ

14
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን

በመገልፀ ኮርፕሬሽኑ የሚሰጠውን የስልጠና ዝርዝር ጠይቀው ለመሰልጠን አቅጣጫ አስቀምተዋል


ይህ በእነዲ እዳለ አጠቃላይ በክፍሉ የሚከኑ የስራ መረጃዎች እንደሚከተለው ቀርቦዋል

ሰንጠረዥ 4.2.1

2.2.5.3.ለድሬደዋ አስተዳደር ዉሃ መዐድንና ኢነርጂ ቢሮ

5.1 ውሃ ኮንስትራክሽን ቢሮ

በዚህ ክፍል ካገኘናቸው የስራ ክፍል አላፊ ጋር እንደተለመደው የኮርፕሬሽኑን የስራ ራዕይና
የሚሰራቸውን ስራ ካስረዳን በዋላ የነሱ የኮንስትራክሽን ግብዓት ችግር ጂይ ፓይፕ መሆኑን
ገልፀውልናል፡፡

5.2 መዐድን ኢነርጂ ቢሮ

መዐድንን በተመለከተ ሰፊ የመዐድን ሀብት መኖሩን ገልፀው ኮርፕሬሽኑ በተለይም በሲሚንቶ


ምርት ላይ ቢሰማራ አካባቢውንና ራሱን ብሎም ለአገርም ትልቅ አስተዋፆ ማበርከት እንደሚቻል
ገልፀው፡፡በተጨማሪም በከተማዋ በመዐድን ስር የሚገኙ የከተማ የኮንስትራክሽን ግብዓቶች
ላይምስቶን፣ሲልካ ሳንድ፣ሳንድስቶን እና የመሳሰሉት የሚገኙ ሲሆን፡፡ በተጨማሪም 2016 እቅድ
አለመፅደቁን እና መስጠት እንዳልቻሉ ገልፀውልናል

2.2.5.4.ለድሬደዋ አስተዳደር ከተማ መንገዶች ባለስልጣን ቢሮ

ከከተማዋ መንገድ አስተዳደር ጋር ሰፋ ያለ መረጃ ከተለዋወጥን በዋላ ኮርፕሬሽናችን ያለበትን


የስራ እድገት በመረዳት ከተማ አስተዳደሩ በ 2016 ዓ.ም አዲስ የመንገድ ስራ እቅድ አለመኖሩንና
ያሉትን ስራዎች መጨረስ ብቻ እንደ እቅድ የተያዘ ስራ ሲሆን የግባዓት ፍላጎትን በተመለከተ
ምንንም የግብዓት አቅርቦት ፍላጎት እንደሌለና የሲሚኒቶና የብረት ፍላጎት ግን ዋንኛ ችግር
መሆኑን ተገልጧል፡

15
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን

2.3 ሐረር

2.3.1 የሀረሪ ክልላው መንግስት የፕሬዝዳትን አማካሪ ቢሮ

ከአቶ አብዱልሀኪም አብዱልመሊስ ጋር በነበረን ሰፋ ያለ ውይይት በማድረግ የመጣንበትን ጉዳይ በስፋት


ከተወያየን በዋላ በሀሳቡ በጣም የተስማና አብሮ የመስራት ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለ ገልፀውልናል፡፡የኮንስትራክሽን
ግብዓን በተመለከተ በአሁን ሰዓት የግብዓት ቸግር እንደሌለና አብዛኛው ፕሮጀክቶች በወርልድ ባንክ ድጋፍ
እንደሚሰሩና በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸውን ገልፀውልናል ሆኖም ግን በከተማዋ እና አካባቢው በጥናት የተለዩ
የኮንስትራክሽን ግብዓት እንዲሁም መዐድን መኖሩን ገልፀው እንደዲሁም በአሀሁን ሰዓት በከተማዋ ምንም አይነት
የጠጠር ማምረቻ ክሬሸር አለመኖሩንረ ጠጠር ከድሬደዋ እየተመላለሰ እንደሚሰራ ገልፀውልናል ይህንን እምቅ
ሀብት በማምረት ለተለያ የኮንስትራክሽን ፕሮጅክቶች ማቅረብ እንድንችል አሰስፈላጊውነ ሁሉ ድጋፍ

በቢሮዋቸውና ከሚመለከታቸው ክፍሎች ጋር በመነጋገር አብረው ለመስራት ፍላጎት መኖራቸውን ገልፀዋል፡፡

2.4 ጅግጅጋ

ፕሮፋይል
የሱማሌ ክልል መንግስት
2.4.1 የሱማሌ ክልል መንግስት የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ቢሮ

በዚህ ክፍል ካሉ የቢሮ አላፊ ከ አቶ ጠይብ መሀመድ ጋር በነመበረን ቆይታ ስለ ኮርፕሬሽናችን አሁናዊ አቋምና ወደ
ክሉሉ የመጣንበትን ጉዳይ በሰፊው በማስረዳት ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጎዋል፡፡በምላሹም በጅግጅጋ ከከተማ
ለምንክፍተው ቢሮ ማንኛውንም ትብብር በማድረግና አብረውን ለመስራት ከፍተኛ ጉጉት እንዳሳደረባቸው
ግልፀውልናል፡፡በዚሁ መሰረት በክልሉ እየተካሄዱ ላሉ የኮንስትራክሽን ስራዎች ግብዓትን በተመለከተ ከፍተኛ
ፍላጎት መኖሩንና አስፈላጊውን ለማድረግ ፍቃደኛ መሆናቸውን ግልፀዋል ለምሳሌ የጠጠር ፍላጎትን በሰፊው
ለማግኘት የኳሪ ሳይቶችን እንደሚያመቻቹ እንዲሁም በክልሉ የሚገኙትን የማዕድን ምርቶች በማውጣት ጥቅም
ላይ ሊውሉ እንዲችሉ እንደሚፈልጉና በውይይታችን ላይ የሲሚንቶ ፋብሪካ የመክፈት እቅድ መኖሩን በመደገፍ

16
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን

አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደርጉ እንደዚሁም የፊኒሺንግ ማቴሪያል ጥሬ ዕቃዎች በክልሉ በስፋት ስለሚገኙ ወደ
ምርት እንድንገባ አስፈላጊውን እገዛ እንደሚያደረርጉ ገልፀዋል፡፡

ጊዜያዊ ቢሮ ለማመቻቸትና ለዘለኬታው ግን ቦታ ወስደን የራሳችንን ቢሮ እንድንሰራ ከሚመለከታቸው የስራ


ክፍሎች ጋር በመነጋገር እንደሚሰጡን ግልጸውልናል፡፡

ሰንጠረዝ

የክልልሉ የ 2016 እቅድ ሰንጠረዝ

2.4.2 የጅግጅጋ ከተማ አስተዳደር

2.4.2.3 የጅግጅጋ ከተማ አስተዳደር አግልግሎት መስጫ ቢሮ

በዚህ ከክፍል ያሉ የቢሮ አላፊ ኢ/ር አህመድ ሁመር ጋር በነበረን ቆይታ ሰፋ ያለ ውይይት የነበረን ሲሆን ስለ
ኮርፕሬሽናችን ገለፃ ካደረግን በኋላ የመጣብትን አላማ ሲጠብቁት የነበረና በአለው ነገር ደስተኛ መሆናቸውን
ግልፀው እስከዛር ድረስ በከተማዋ እንደዚ አይነት የኮንስትራክሽን አጋር አለመኖሩ ከተማዋን እንዳታድግ እንቅፋት
እስደነበር ገልፀዋል፡፡በተጨማሪም ስለ ኮርፕሬሽናችን በቂ መረጃ እንዳላቸውና ለወደፊቱም አብሮ ለመስራት
ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው በመግለፅ በተለይ በአሁኑ ሰዓት በከተማዋ የስቶርም ዋትር ድሬኔጅ እና የጎርፍ
መከላከያ ሪቴንግ ወል ስራ ለማሰራት በቀጥታ ለማሳተፍ(ዳይሬክት ኦፈር) ለመስጠት ዝግጁ መሆናቸውንና
በደብዳቤም ለመጠየቅ አስፈላጊውን እንደሚያደርጉ ገልፀዋል እንደዚሁም የኮንስትራክሽን ግብዓት ማቅረብን
በተመለከተ ከፍተኛ ፍላጎት መኖሩንና ለዚህም የሚያስፈልጉ በጥናት የተለዩ ኳሪ ሳይቶችን ከሚመለከታቸው
ክፍሎች ጋር በመነጋገር ለመስጠት አስፈላጊውን ሁሉ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል፡፡የኮንስትራክሽን ጥገና እና
ስፔፓርት አቅርቦትን በተመለከተ ከፍተኛ ክፍተት መኖሩን በመግለዕ አብሮ ለመስራት ፍቃደኝነታቸውን
አሳይተዋል በከተማ ውስጥ የሚገኙ የኮንስትራክሽን ሮጅክቶችን በተመለከተ ከጅግጅጋ ከተማ አስተዳደር
ዩአይይዲፒ ኮርዲኔተር አላፊ ኢ/ር መሀመድ አህመድ ሙሴ ጋር ሰፋ ያለ ውይይት አድርገን ከዚህ በፊት
ለኮርፕሬሽናችን በቀጥታ ስረ ለመስጠት(ዳይሬክተ ኦፍር) 4 ጂፕላስ እንፃዎችን መግባባት ላይ ከተደረሰ በዋላ
በበጀት እጥረት ሳይሳካ መቅረቱንና ስለ ኮርፕሬሽኑ በቂ መረጃ እነዳላቸው ገልፀውልናል፡፡በተቸማሪም ለወደፊት

17
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን

ሰፋ ስራዎችን አብሮ ለመስራት ከፍተኛ ፍላጎት መኞሩን ተናግረው ቢሮ ለማመቻቸት ቃል ግብተዋል፡፡ በሌላ
መልኩ የአቅም ግንባታ ስልጠናን በተመለከተ በስራቸው ሚገኙ መአንዲሶች ከፍተኛ ክፍተት መኖሩን በመግለፅ
ፍላጎት መኖሩንና በቅርብ ጊዜ መሀንዲሶችን በመመልመል ለስልጠና ዝግጁ ለማድረግ እንደሚችሉና ሆኖም ግን
ልልነሰጣቸው የምንችላቸውን የስልጠና ስም ዝርዝር ከኮርፕሬሽናችን እንደሚፈልጉ ገልፀዋል፡፡ኮንስትረካሽን
ግብዓትን በተመለከተ ከፍተኛ እጥረት መኖሩን እና ለግብዓት የሚሆን ሰፊ እና በቂ ጥሬ እቃ መኖሩን ገልፀዋል፡፡
በእንዲ እንዳለ እምቅ የማእድን ሀብት ስነዳለ እና ከሚመለከታቸው የስራ ክፍለች ጋር አስፈላውን ለማድረግ
ፍቃደኝነታቸውን ገልቷል የተወሰኑ የኳሪ ቦታዎችን አብረን ጎብኝተናል፡፡ በቀ የጠገኘው መረጃ እነደሚከተልው
ቅርቦዋል፡፡ ፕሮጀክቶችን በተመለከተ በወርልድ ባንክ ፈንድ የሚሰሩና በአብዛኛው መጠናቀቃቸውን ገልጸውልናል
የ 2016 እቅድ አለመኖሩን ገልጸቊልናል፡፡

ክፍል 3

18
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን

3.1 ከመስክ ጥናት የተገኙ ግኝቶች

3.1.1 ጅማ

ግብዓት

የግብዓት ውጤቶችን በተመለከተ ማምረት እንደሚቻልና በጅማ ከተማም ሆነ በዞኑ ለሚገኙ


ፕሮጀክቶች እንዲሁም አዲስ ለሚሰሩ ፐፕሮጀክቶች በቂ የሆነ የኳሪ ሳይት መኖሩንና
አስፈላጊውን የመንግስት መመሪያ በመከተል በተጠኑ ሳይቶች ላይ የማምረቻ ፕላንቶችን
በአስቸኳይ ተክለን ገበያውን እንድንቀላቀል ከፍተኛ ፍላጎት መኖሩን ተረድተናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ
የሲሚንቶ፣ ብረት፣ ቢትሚነስና የፈንጅ አቅርቦት እጥረት በመኖሩ ኮርፖሬሽኑ ጊዜ ሳይወስድ
ቢያቀርብልን ትልቁን የፕሮጀክት ማነቆ መቅረፍ እንደሚቻል ተገልጧል

የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች ጥገናና መለዋወጫ

የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች ጥገናና መለዋወጫ በተመለከተ በሄድንባቸው ቢሮዎች ሁሉ ከፍተኛ


ፍላጎት መኖሩን ተረድተናል

ኢንቨስስመንት

ኢንቨስትመንትን በተመለከተ በዞኑም ሆነ በከተማው እምቅ የመዐድን ሀብት መኖሩንና በተለይም


ለሲሚንቶ ፋብሪካ ግብዓት የሚኑ ማዕድናት በመኖራቸው አቅሙ ካለ ፋብሪካውን ብንተክል
አስፈላጊው ሁሉ ትብብር እንደሚደረግ ተልጧል፤ ከዚህ በተጨማሪም ለአግሮ ፐሮሰሲንግ
የሚሆኑ የግብርና ምርቶች በአካባቢው ስለሚገኙ ፋብሪካዎች ቦከፈቱ ፍላጎት እንዳለ ተገልጧል
ለምሳሌ፡- የሳሙና፣ ቸኮሌት፣ ዱቄትና ብስኩት ከብዙዎቹ ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

የአቅም ግንባታና ስልጠና ፍላጎት

19
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን

የአቅም ግንባታና ስልጠና ፍላጎት በሄድንባቸው ሁሉም ቢሮዎች በተለይም ምህንድስናን


በተመለከተ ከፍተኛ ከረፈተት መኖሩን ጠቅሰው መሀንዲሶቻቸውን መልምለው ለመላክ
የምንሰጣቸውን የስልጠና ዓይነቶች ዝርዝር እንድናሳውቃቸው ጠየቀውናል፡፡

የቢሮና የቦታ በተመለከተ

በዞኑም ሆነ በከተማ አስተዳደሩ የቢሮ እጥረት ስላለባቸው ማግኘት እንደማይይል ገልፀው


ለወደፊቱ የቦታም ሆነ የቢሮ ችግርን ለመፍታት አብረው እንደሚሰሩ ቃል ገብተውልናል፤ ሆኖም
ግን ኮሚቴው ባደረገው ጥናት ተከራይቶ ለመስራ እንደሚቻልና ቤቶቹንም በአካል በመገኘት
ከባለቤቶቹ ጋር በመነጋገር በአሁኑ ሰዓት በካሬ ብር እንደ ሆነ ተገንዝብናል፡፡(ፎቶ)

3.2.2 ድሬደዋ

1.ግብዓት

የግብዓት ውጤቶችን በተመለከተ ማምረት እንደሚቻልና በድሬደዋ ከተማ ለሚገኙ ፕሮጀክቶች


እንዲሁም አዲስ ለሚሰሩ ፕሮጀክቶች በቂ የሆነ የኳሪ ሳይት መኖሩንና አስፈላጊውን የመንግስት
መመሪያ በመከተል በተጠኑ ሳይቶች ላይ የማምረቻ ፕላንቶችን በአስቸኳይ ተክለን ገበያውን
እንድንቀላቀል ከፍተኛ ፍላጎት መኖሩን ተረድተናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የሲሚንቶ፣ ብረት፣
አቅርቦት እጥረት በመኖሩ እንዲሁም የፊኒሺንግ ማቴሪያል ኮርፖሬሽኑ ጊዜ ሳይወስድ
ቢያቀርብልን ትልቁን የፕሮጀክት ማነቆ መቅረፍ እንደሚቻል ተገልጧል

የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች ጥገናና መለዋወጫ

የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች ጥገናና መለዋወጫ በተመለከተ በሄድንባቸው ቢሮዎች ሁሉ ከፍተኛ


ፍላጎት መኖሩን ተረድተናል

ኢንቨስስመንት

20
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን

ኢንቨስትመንትን በተመለከተ በከተማው እምቅ የመዐድን ሀብት መኖሩንና በተለይም ለሲሚንቶ


ፋብሪካ ግብዓት የሚኑ ማዕድናት በመኖራቸው አቅሙ ካለ ፋብሪካውን ብንተክል አስፈላጊው ሁሉ
ትብብር እንደሚደረግ ተልጧል፤

የአቅም ግንባታና ስልጠና ፍላጎት

በሄድንባቸው ሁሉም ቢሮዎች በተለይም ምህንድስናን በተመለከተ ከፍተኛ ከረፈተት መኖሩን


ጠቅሰው መሀንዲሶቻቸውን መልምለው ለመላክ የምንሰጣቸውን የስልጠና ዓይነቶች ዝርዝር
እንድናሳውቃቸው ጠየቀውናል፡፡

የቢሮና የቦታ በተመለከተ

ለወደብ ካለው ቀረቤታ ብሎም አካባቢው ካለው በርካታ የኮንስትራክሽን ፕሮጀክቶች እንዲሁም
ነፃ ንግድ ቀጠነና አንፃር የምንክፍተው ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ከጅግጅጋ ይልቅ ድሬደዋ ላይ ብንከፍት
አዋጭ ይሆናል የሚል ሀሳብ እንዳላቸው ገልፀውልናል፡፡ቦታን በሚመለከት ወደፊት ከከተማ
አስተዳደሩና ከሚመለከታቸው ክፍሎች ጋር በመነጋገር እንደሚያመቻቹ ገልፀዋል፡፡ኮሚቴው
ባደረገው የከተማ ደሰሳ ለቢሮ ኪራይ ሚሆኑ በተቶችን ላመየት ተሞክሮዋል በአሁኑ ሰዓት በካሬ
ብር እንደ ሆነ ተገንዝብናል፡፡(ፎቶ)

3.1.3 ሐረር

ግብዓት

የግብዓት ውጤቶችን በተመለከተ ማምረት እንደሚቻልና ሀረር ከተማ ሆነ በዙሪያው ለሚገኙ


ፕሮጀክቶች እንዲሁም አዲስ ለሚሰሩ ፕሮጀክቶች በቂ የሆነ የኳሪ ሳይት መኖሩንና አስፈላጊውን
የመንግስት መመሪያ በመከተል በተጠኑ ሳይቶች ላይ የማምረቻ ፕላንቶችን በአስቸኳይ ተክለን
ገበያውን እንድንቀላቀል ከፍተኛ ፍላጎት መኖሩን ተረድተናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የሲሚንቶ፣
ብረት፣ አቅርቦት እጥረት በመኖሩ ኮርፖሬሽኑ ጊዜ ሳይወስድ ቢያቀርብልን ትልቁን የፕሮጀክት
ማነቆ መቅረፍ እንደሚቻል ተገልጧል

21
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን

የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች ጥገናና መለዋወጫ

የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች ጥገናና መለዋወጫ በተመለከተ በሄድንባቸው ቢሮዎች ሁሉ ከፍተኛ


ፍላጎት መኖሩን ተረድተናል

ኢንቨስስመንት

ኢንቨስትመንትን በተመለከተ በከተማው እምቅ የመዐድን ሀብት መኖሩንና በተለይም ለሲሚንቶ


ፋብሪካ ግብዓት የሚኑ ማዕድናት በመኖራቸው አቅሙ ካለ ፋብሪካውን ብንተክል አስፈላጊው ሁሉ
ትብብር እንደሚደረግ ተልጧል፤ የአቅም ግንባታና ስልጠና ፍላጎት

የአቅም ግንባታና ስልጠና ፍላጎት በሄድንባቸው ሁሉም ቢሮዎች በተለይም ምህንድስናን


በተመለከተ ከፍተኛ ከረፈተት መኖሩን ጠቅሰው መሀንዲሶቻቸውን መልምለው ለመላክ
የምንሰጣቸውን የስልጠና ዓይነቶች ዝርዝር እንድናሳውቃቸው ጠየቀውናል፡፡

የቢሮና የቦታ በተመለከተ

ቢሮን በተመለከተ ጅግጅጋ ከመክፈት ሐረር ከተማ ለድሬደዋ እና ለጅግጅጋ አዋሳኝ ስለሆነች
ፎካል ፐርስ ብታስቀምጡ የሚል ሀሳብ

3.2.4 ጅግጅጋ

ግብዓት

የግብዓት ውጤቶችን በተመለከተ ማምረት እንደሚቻልና በጅግጅጋ ከተማ ለሚገኙ ፕሮጀክቶች


እንዲሁም አዲስ ለሚሰሩ ፕሮጀክቶች በቂ የሆነ የኳሪ ሳይት መኖሩንና አስፈላጊውን የመንግስት
መመሪያ በመከተል በተጠኑ ሳይቶች ላይ የማምረቻ ፕላንቶችን በአስቸኳይ ተክለን ገበያውን
እንድንቀላቀል ከፍተኛ ፍላጎት መኖሩን ተረድተናል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የሲሚንቶ፣ ብረት፣
አቅርቦት እጥረት በመኖሩ እንዲሁም የፊኒሺንግ ማቴሪያል ኮርፖሬሽኑ ጊዜ ሳይወስድ
ቢያቀርብልን ትልቁን የፕሮጀክት ማነቆ መቅረፍ እንደሚቻል ተገልፃል፡፡ይህ በእንዲ እንዳለ

22
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን

የጠጠር ምርትን በተመለከተ በሚፈለገው ጥራትና ግሬድ ማግኘት ስለማይቻል ከድሬደዋ አካባቢ
እየተመላለሰ እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡ለወደፊቱ በአሁኑ ሰዓት የቻይና ኮንትራክተሮች የተያዙትን
የኳሪ ሳይቶች የኮንትራት ጊዜ ገደባቸው ሲጠናቀቅ በቀጥታ ወደኛ እንደሚያዞሩና እንዲሁም
አዳዲስ የተጠኑ የኳሪ ሳይቶችን ለማመቻቸትና ወደማምረት ስራ እንድንገባ አስፈላጊውን
እንደሚያደርጉ ቃል ተገብቶዋል፡፡

የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች ጥገናና መለዋወጫ

የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች ጥገናና መለዋወጫ በተመለከተ በሄድንባቸው ቢሮዎች ሁሉ ከፍተኛ


ፍላጎት መኖሩን ተረድተናል

ኢንቨስስመንት

ኢንቨስትመንትን በተመለከተ በከተማው እምቅ የመዐድን ሀብት መኖሩንና በተለይም ለሲሚንቶ


ፋብሪካ ግብዓት የሚኑ ማዕድናት በመኖራቸው አቅሙ ካለ ፋብሪካውን ብንተክል አስፈላጊው ሁሉ
ትብብር እንደሚደረግ ተልጧል፤

የአቅም ግንባታና ስልጠና ፍላጎት

በሄድንባቸው ሁሉም ቢሮዎች በተለይም ምህንድስናን በተመለከተ ከፍተኛ ክፍተት መኖሩን


ጠቅሰው መሀንዲሶቻቸውን መልምለው ለመላክ የምንሰጣቸውን የስልጠና ዓይነቶች ዝርዝር
እንድናሳውቃቸው ጠየቀውናል፡፡

የቢሮና የቦታ በተመለከተ

ቢሮን በተመለከተ በጊዜአዊነት ከተማ አስተዳደ ከሚመለከታቸው ክፍሎች ጋር ተወያተው ቢሮ


እንደሚሰጡን በተጨማሪም በቀጣይ ቦታ ሰተውን የራሳችንን ቢሮ ገንብተን ለከተማ ውበት
አስተዋፆ እንድናበረክት ነግረውናል፡፡

3.2 ምክረ ሀሳብ

23

You might also like