Professional Documents
Culture Documents
4 Zone
4 Zone
ማውጫ
ገጽ
መግቢያ……………………………………………………………………………………….. 1
1. መግቢያ
ሀገራችንን ካለችበት ድህነት በማላቀቅ በ 2015 መካከለኛ ገቢ ካላቸዉ ሀገሮች ተርታ ለማሰለፍ ዘርፈ ብዙ የልማት
እንቅስቃሴዎች በመደረግ ላይ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በተለይ ሀገራችንን የኢኮኖሚ ዕድገት እና ልማት ለማፋጠን ከግብርናዉ
ዘርፍ ቀጥሎ የኢንዱስትሪዉን ዘርፍ ማስፋፋት ትልቅ ትኩረት የተሰጠዉ ጉዳይ ነዉ፡፡ ለኢንዱስትሪዉ ዘርፍ ዉጤታማነት
ደግሞ የተደራጀ እና ዘመናዊ የኢንዱስትሪ ቀጣና መስፋፋት የማይተካ ሚና ይኖረዋል፡፡ በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር 2004 ዓ.ም
በተዘጋጀዉ የኢንዱስትሪ ቀጣና ልማት ስትራቴጂ ጥናት ሰነድ ላይ እንደተመለከተዉ የኢንዱስትሪ ቀጣና ማለት
የኢንዱስትሪ ስብስብ (cluster of business) እና የተለያዩ ኢንዱስትሪዎች የሚቋቋሙበት እና ልማቱን ለማፋጠን ልዩ ልዩ
ማበረታቻዎች በሕግ አግባብ የሚሰጡበት የተከለለ አካባቢ ወይም ቦታ ሲሆን ይህ ቦታ ሁሉን አቀፍ የሆነ መሠረተ ልማት
አካቶ የተመሰረተ ነዉ፡፡ የኢንዱስትሪ ቀጣና የመንገድ፣ የውኃ፣ የኤሌክትሪክ ኃይል፣ የቴሌኮሙኒኬሽንና ሌሎች መሠረተ
ልማቶች የተገነቡበት ሆኖ የጋራ መገልገያዎች (common facilities)፣ መጋዘን (warehouse)፣ የብክለት ማጣሪያና
ማስወገጃ (effluent treatment) የያዘ ፣ የጥናትና ምርምር ማዕከል፣ የጋዝ ማደያ፣ ወዘተ እንዲሁም የተለያዩ ማኅበራዊ
አገልግሎቶች (መኖሪያ ቤቶች፣ የቢሮ ህንፃዎች፣ የሕክምና ማዕከል፣ ት/ቤት፣ መዋዕለ ህፃናት) ያሉበት የተረጋጋና
የተመቻቸ የሥራ አካባቢ በመፍጠር ሠራተኛው ምርታማ የሚሆንበት፣ ኢንዱስትሪዎቹም የእርስ በርስ ቁርኝት ያላቸውና
እርስ በርስ የሚመጋገቡ እንዲሆኑ ሁኔታዎች የተመቻቹበት ነው፡፡ ከዚህ አንጻር በክልሎች እና በከተሞች በኢንዱስትሪ
ቀጣናነት ተከልለዉ ወደተግባር የገቡትን ስንመለከት ተገቢዉን አገልግሎት መስጠት የማይችሉ እና የኢንዱስትሪ ቀጠና
ማሟላት የሚገባቸዉን መሰረታዊ አቅርቦቶች ሳይቀር የተጓደሉበት ሆኖ እናገኛለን፡፡ በመሆኑም ቀጣናዎቹ የታሰበዉን
ዉጤት ከማምጣት ይልቅ የልማት ሂደቱን በአግባቡ ለማፋጠን የሚያስችሉ አለመሆናቸዉን ለመገንዘብ ይቻላል፡፡ ለዚህ
እንደችግር የሚቀርበዉ የከተሞች የፋይናንስ አቅም ችግር እንደተጠበቀ ሆኖ ዘመናዊ ኢንዱስትሪ ቀጠና ማሟላት
በሚገባቸዉ ጉዳዮች እና በአሰራሩ ላይ ሰፊ የግንዛቤ ክፍተት እንዳለም ለመረዳት ተችሏል፡፡ በእድገት እና ትራንስፎርሜሽን
ዕቅዳችን ላይ በየከተሞች መልማት ያለባቸዉ ወደ 72 የሚጠጉ የኢንዱስትሪ ቀጣናዎች እንዳሉ ተመልክቷል፡፡
ከዚህ አንጻር ከተሞች በኢንዱስትሪ ቀጠና ልማት ረገድ ያለባቸዉን ችግር እንዴት መቅረፍ እንዳለባቸዉ እና ዝርዝር
አሰራሩን ለማስጨበጥ የሚያስችል ይህ የኦፕሬሽናል ማኑዋል ተዘጋጅቷል፡፡
ክፍል አንድ፡- የኢንዱስትሪ ቀጠና ልማት ቅንጅት እና ክትትል አካል ስለማቋቋም
ከተሞች ለኢንዱስትሪ ቀጠና የሚዉል ቦታን ለመከለል ተገቢዉን ጥናት እና ጥንቃቄ ማድረግ የሚኖርባቸዉ
ይሆናል፡፡ ለኢንዱስትሪ ቀጠና ዝግጅት የሚዉለዉን መሬት ለመከለል መዋቅራዊ ፕላኑ ያስቀመጣቸዉ
ታሳቢዎች እንደተጠበቁ ሆኖ የሚከተሉት ዋና ዋና ጉዳዮች መሰረታዊ ናቸዉ፡፡
በመሆኑም ለኢንዱስትሪ ቀጠና የሚዉሉ ቦታዎችን በመከለል ረገድ ለነዚህ አዉታሮች በቀላሉ ተደራሽ
የሆነ ቦታ መምረጥ ተገቢ ይሆናል፡፡ የኢንዱስትሪ ቀጠና በምርት ሂደት እና በአጠቃላይ እንቅስቃሴዉ
ግብአት እና ጠቀሜታ የሚዉል ከፍተኛ የዉሃ ፍጆታን የሚጠይቅ በመሆኑ እና ይህም ፍጆታ በአማካይ
በቀን ለአንድ መለስተኛ ከተማ ከሚቀርበዉ ጋር ተመጣጣኝ በመሆኑ በጥልቅ ጉድጓድ ቁፋሮ የታገዘ
የዉሃ አቅርቦት ሊኖር የሚገባ ይሆናል፡፡ በመሆኑም ለኢንዱስትሪ ቀጠና የሚዉለዉ መሬት ክለላ
በአካባቢዉ ይህንን አቅርቦት ለማግኘት በሚያስችል መልኩ ጥናት በማከናወን መረጋገጥ የሚኖርበት
ይሆናል፡፡
ክፍል ሶስት፡- የኢንዱስትሪ ቀጠና ዝርዝር የአካባቢ ልማት ፕላን እና ዲዛይን ስለማዘጋጀት
1. ዝርዝር የመሬት አጠቃቀም ፕላን ማዘጋጀት
የኢንዱስትሪ ቀጠና ዝርዝር የልማት ፕላን ዝግጅት ትልቅ አቅምን እና ብቃትን የሚጠይቅ በመሆኑ በክልል
ከተሞች ይህንን ለማዘጋጀት የሚችል አቅም በሂደት እስከሚገነባ ድረስ በክልል የፕላን ተቋማት ወይም ብቁ
በሆኑ የግል አማካሪዎች ወይም ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አማካይነት ፕላኑን ማስጠናት እንደአማራጭ
ሊታሰብ የሚገባዉ ይሆናል፡፡ የኢንዱስትሪ ቀጠና የፕላን ዝግጅት ታሳቢዎች በቀጠናዉ በመሰረታዊነት
እንዲመረት ከተፈለገዉ ምርት እና የኢንዱስትሪ ትስስር አግባብ የሚነሳ ይሆናል፡፡ በዚህ ረገድ ቀጠናዉ
ለጨርቃ ጨርቅ ወይም ለብረታ ብረት ወይም ለሌሎች ምርቶች በስፔሽያላይዜሽን ወይም በቅይጥ
የሚመረትበት መሆኑ የሚወሰን ይሆናል፡፡ የኢንዱስትሪ ቀጠናዉ ከማምረቻ ኢንዱስትሪዎች በተጨማሪ
የተለያዩ አገልግሎቶችን ማለትም የንግድ ሥራና የሙያ አገልግሎቶች በማካተት ምርቱን ከግብይቱ፣
ኢንዱስትሪውን ከአገልግሎቱ ሰጪው ዘርፍ በማቆራኘት ሁለንተናዊ ልማትን በሚያስገኝ መልኩ የሚዘጋጅ
በመሆኑ የኢንዱስትሪ ቀጠናዎች የገበያ ማዕከሎችን፣ መኖሪያ ቤቶችን፣ መዝናኛ ሥፍራዎችን፣
ሆስፒታሎችንና ትምህርት ቤቶችን የጉምሩክ አገልግሎቶችን፤ የነዳጅ ማደያዎችን፤ የኃይል አቅርቦት ሰብ
ስቴሽኖችን፤ የዉሃ አቅርቦት ማሰራጫ እና ማጠራቀሚያ ስትራክቸሮችን፤ ልዩ ልዩ የአገልግሎት መስጫ
ተቋማትን፤ ከፍተኛ የማከማቻ መጋዘኖችን እና ጋራዦችን ወዘተ ታሳቢ ሊያደርግ ይገባል፡፡ ቀጠናዉ በርካታ
እና ትላልቅ ተሸከርካሪዎች የሚመላለሱበት በመሆኑ ደረጃዉን እና ስፋቱን የጠበቀ የዉስጥ ለዉስጥ መንገድ
እና በቂ መቆሚያ ቦታ እንዲኖረዉ ይጠበቃል፡፡ ቀጠናዉ ተገቢዉ የአካባቢ ደህንነት መጠበቂያ አረንጓዴ
ቦታዎችን፤ የፍሳሽ እና ቆሻሻ፤ የብክለት ማከሚያ እና ማስወገጃ ስትራክቸሮችን ታሳቢ የሚያደርግ ይሆናል፡፡
የኢንዱስትሪ ቀጠና ዝርዝር ፕላን የሽንሻኖ ፕላንን ያካተተ ሆኖ የሽንሻኖዉ ታሳቢዎች በቦታዉ ላይ
ሊተገበር በታቀደዉ የኢንዱስትሪ ዓይነት እና የአገልግሎት ደረጃ እና ይዘት የሚወሰን ይሆናል፡፡
በአጠቃላይ የኢንዱስትሪ ቀጠናዉ ዝርዝር የልማት ፕላን ከላይ የተመለከቱትን ታሳቢዎች መሰረት በማድረግ
የሚዘጋጅ እና ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ቀርቦ መዳበር የሚገባዉ ይሆናል፡፡
2. የኢንዱስትሪ ቀጠና ዝርዝር የአካባቢ ልማት ፕላን ስለማጽደቅ
የኢንዱስትሪ ቀጠና ዝርዝር የልማት ፕላን ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ቀርቦ እና ታይቶ
በክልል ወይም በከተማዉ ካቢኔ በኩል የሚጸድቅ ይሆናል፡፡ ፕላኑ አግባብ ላለዉ አካል ቀርቦ ከጸደቀ
በኋላ ህጋዊነቱ የተረጋገጠ ሲሆን ከፕላኑ ጋር የሚጣረስ ተግባር መፈጸም ወይም በፕላኑ መሰረት
አለመፈጸም በህግ አግባብ የሚያስጠይቅ ይሆናል፡፡
የኢንዱስትሪ ቀጠና ልማት ዲዛይን ዝግጅት ዝርዝር የአካባቢ ልማት ፕላኑን ተከትሎ የሚዘጋጅ ይሆናል፡፡
የኢንዱስትሪ ቀጠና ዲዛይን በአማካሪ ተቋም ወይም በራስ ሃይል ወይም በመሰረተ ልማት ዘርጊ ተቋሙ
ወይም በግንባታ ፈጻሚዉ አካል የሚከናወን ሆኖ ዲዛይኑ የሚከተሉትን በዋነኛነት የሚይዝ ይሆናል፡፡
2. የሽንሻኖ እና ቅየሳ ስራ
የሽንሻኖ ፕላኑን መሰረት በማድረግ የኢንዱስትሪ ቀጠናዉ በሚገባ ተቀይሶ በስታንዳርዱ መሰረት የሚሸነሸን
ይሆናል፡፡ ስታንዳርድ የኢንዱስትሪ ቀጠና ሽንሻኖ በእዝል 3 ተመልክቷል፡፡ በፕላኑ መሰረት ልኬት ተከናዉኖ
በተሸነሸነዉ ቦታ ላይ የወሰን ድንጋይ መትከል ተገቢ ይሆናል፡፡ ለዚህ ስራ ደግሞ አንዱ ግብዓት የወሰን
ድንጋይ ወይም ችካል ሲሆን ይህም የቅየሳ ስራ ከመከናወኑ በፊት አስቀድሞ መዘጋጀት ይኖርበታል፡፡
የሚተከለውም የወሰን ድንጋይ አራት ማእዘን ያለው ሆኖ የተለየና ጎላ ብሎ የሚታይ አተካከሉ በቀላሉ ሊነቀል
በማይችል መልኩ እንደ አፈሩ ፀባይ በጥልቀት መተከል የሚገባው ሲሆን በተጨማሪም ፕሎቶቹን በቀላሉ
ለመለየት እንዲቻል የወሰን ድንጋዩ ኮድ እና ኮኦርድኔት ቁጥር ሊሰጠው ይገባል፡፡ በሽን ሸናው መሰረት የወሰን
ድንጋይ ከተተከለ በኋላ ቦታው በአግባቡ ስለመሸንሸኑ የሚያስረዳ የመስክ ሪፖርትና የርክክብ ፎርማት
ተዘጋጅቶና ተፈርሞ ለሚመለከተው አካል መቅረብ አለበት፡፡
በቦታው ላይ በዝርዝር የሽንሻኖ ፕላኑ መሰረት የወሰን ድንጋይ ከተተከለ በኋላ ዝርዝር የሽንሻኖ ፕላኑ ላይ
ለእያንዳንዱ ፓርሴል መለያ ቁጥር በመስጠት በመሬት ባንክ እንዲመዘገብ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ እያንዳንዱ
ፓርሴል የሚሰጠው መለያ ቁጥር ከሌላው የተለየ እና የራሱ ብቻ የሆነ (Unique) መሆን አለበት፡፡ ይህ ቁጥር
በተለይ በቀጣይ በየከተሞቹ ለሚዘረጋው የመሬት እና መሬት ነክ ቋሚ ንብረት ምዝገባ የሚያገለግል ስለሚሆን
ተገቢውን የኮድ አሰጣጥ ፎርማት ተከትሎና አንዱን ፓርሴል ከሌላው ፓርሴል/ፕሎት ለመለየት በሚያስችል
መልኩ መከናወን አለበት፡፡
የመለያ ቁጥር አሰጣጡ ወጥነት እንዲኖረው ለማድረግ ከተሞች እስካሁን እየሰሩበት የነበረውን የኮድ አሰጣጥ
መፈተሽና ከላይ ለተገለጸው የቋሚ ንብረት ምዝገባ አገልግሎት ጭምር የሚጠቅም የፓርሴል መለያ ቁጥር
አሰጣጥ ስርዓት የሚዘረጋበትን መንገድ መቀየስ አለባቸው፡፡
ክፍል ስድስት፡- ግንባታን ማከናወን እና ማከራየት፤ መሬትን በሊዝ አግባብ ማስተላለፍ
በኢንዱስትሪ ቀጠናዉ ዉስጥ በአልሚዉ በኩል ከሚገነቡ ተቋማት እና ህንጻዎች በስተቀር በክልሉ ወይም
በከተማዉ አስተዳደር ለአገልግሎት መስጫነት ወይም በኪራይ አግባብ አገልግሎት የሚሰጡ ግንባታዎች
በዲዛይኑ መሰረት መዘጋጀት እና መጠናቀቅ የሚኖርባቸዉ ይሆናል፡፡ በተለይ በኢንዱስትሪ ቀጠናዉ መሰረታዊ
አገልግሎት የሚሰጡ እንደመኖሪያ ቤት፤ ት/ቤት፤ የጤና ተቋማት፤ መዝናኛ ማዕከላት፤ የነዳጅ ማደያ
የመሳሰሉት አቅርቦቶችን በግል አልሚ በኩል የሚቀርብበትን አግባብ ማመቻቸትም እንደአማራጭ የሚታይ
ይሆናል፡፡ ለማምረቻ ማዕከላት የሚሆኑ ሼዶችን እና መጋዘኖችን እና ጋራዦችንም እንደተጨባጭ ሁኔታዉ
በግል አልሚ አማካይነት እንዲለማ እና ለቀጠናዉ አገልግሎት እንዲሰጥ ማድረግ ተመራጭ ሊሆን ይችላል፡፡
ግንባታዉ በክልሉ ወይም በከተማዉ የሚከናወን ሲሆን የኪራይ ዋጋዉን በመወሰን አልሚዉ እንዲገለገልበት
ማድረግ ተገቢ ይሆናል፡፡
ከግንባታ ዉጪ የሆኑ የተሸነሸኑት የኢንዱስትሪ ቀጠና ቦታዎች በሊዝ አዋጁ አግባብ የሚተላለፉ ይሆናል፡፡
የይዞታ አስተዳደሩም ይህንኑ ህግ መሰረት ያደረገ ይሆናል፡፡ ዝርዝር አሰራሩ በሊዝ ኦፕሬሽናል ማንዋል ላይ
ተመልክቷል፡
አባሪዎች
ቀን፡ --------------------
በ……….……… ከተማ ማዘጋጃ ቤት (ከዚህ በኋላ ውል ሰጪ) እና በሊዝ ባለይዞታነት መብት ባለቤት
አቶ/ወ/ሮ/ድርጅት ……………………………. (ከዚህ በኋላ ውል ተቀባይ) መካከል የጋራ መግባባትና ጥቅምን
መሠረት ያደረገ የውል ስምምነት ተፈጽሟል፡፡
ውል ሰጪ፡
ውል ተቀባይ፡
አንቀጽ 2 ውል ስለማቋቋም
ይህ ውል በውል ሰጪና በውል ተቀባይ ነፃ ፍላጐት፤ ውል ሰጪ በዚህ ውል የተጠቀሰውን የከተማ ቦታ ለኢንዱስትሪ
አገልግሎት ይዞታ በውሉ ለተወሰነው ጊዜ ለውል ተቀባይ በሊዝ ባለይዞታነት
ሊያስተላልፍና ውል ተቀባይም ከውል ሰጪ የተረከበውን ቦታ ይዞታ በዚሁ ውል በተመለከተው የጊዜ ገደብ ውስጥ
ለተፈቀደው አገልግሎት ዓይነት ብቻ በዚህ ውል የተጠቀሰውን ዋጋ ከፍሎ በመውሰድ ሊገለገሉበት ፈቅደውና ወደው
ያቋቋሙት ውል ነው፡፡
3.4 በሊዝ የሚያዘው ቦታ በ ……………………… ቁጥር የተመዘገበ ለኢንዱስትሪ አገልግሎት የሚዉል ቦታ ነው፡፡
3.9 በሊዝ የሚያዘው ቦታ …………………የቦታ ደረጃና ……….. ንዑስ የቦታ ደረጃ ያለው ነው፡፡
4.2 ውል ተቀባይ እንዲከፍሉ የተስማሙበት የቅድሚያ ክፍያ በካርኒ ቁጥር ………………………… . በተመዘገበ
ሰነድ በብር ………………/በፊደል፡ …………………………………..……./ብር ተከፍሏል፡፡
4.3 ውል ተቀባይ የቦታውን ጠቅላላ የሊዝ ዋጋ ክፍያ ሊከፍሉ በተስማሙበት የክፍያ ዘመን ውስጥ ለማጠናቀቅ
ግዴታ ገብተዋል፡፡
4.4 በዚህ ሰነድ አንቀጽ 7.5 የተጠቀሰው እንደተጠበቀ ሆኖ ውል የተገባበት የአንድ ሜትር ካሬ የሊዝ ዋጋ በብር
………. / በፊደል ………………………………….. ብር/ ለውል ዘመኑ ሁሉ የፀና ይሆናል፡፡
አንቀጽ 5 የችሮታ ጊዜ
5.1 ውል ተቀባይ በሊዝ አዋጅ 721/2004 አንቀጽ 15 እና በክልሉ/ከተማ አስተዳደሩ ደንብ ቁጥር….. አንቀጽ………
መሠረት ለ…… ዓመት የሚቆይ የክፍያ/የግንባታ/ ሌላ የችሮታ ጊዜ ተፈቅዶላቸዋል፡፡
አንቀጽ 6 የውል ዘመን
6.1 ውል ተቀባይ የተስማማበት ወይም በሊዝ አዋጁ አንቀጽ 18 ንኡስ አንቀጽ 1 (ለ/2) እና (ሐ/2) በአዲስ አበባ
ከተማ 70 ዓመት እና በሌሎች ከተሞች 80. ዓመት የውል ዘመኑ ጣሪያ ይሆናል፡፡
6.1 በዚህ ውል መሠረት የሊዝ ዘመኑ የሚጀምረው ከ…….ቀን ……..ዓ.ም. ጀምሮ እስከ …….ቀን ……….ዓ.ም.
ድረስ ይሆናል፡፡
6.1 በአዋጁ አንቀጽ 19 ንኡስ አንቀጽ 2 መሠረት የሊዝ ውል ዘመኑ ከማብቃቱ ከ 10 እስከ 2 ዓመታት ውስጥ ውል
ተቀባዩ የውል ዘመኑ እንዲታደስለት ማመልከት ይችላል፡፡
7.1 በሊዝ የያዘውን ቦታ በሊዝ ዘመኑ ውስጥ ያለገደብ ለማስተላለፍ፣ በዋስትና ለማስያዝ ወይም የከፈለውን የሊዝ
ዋጋ በካፒታል አስተዋጽኦ መልክ የመጠቀም መብቶች ይኖሩታል፡፡
7.2 በሊዝ አዋጁ አንቀጽ 25 ንኡስ አንቀጽ 1(ለ) መሠረት ውሉ ሲቋረጥ በዚሁ አዋጅ አንቀጽ 25 ንኡስ አንቀጽ 4
መሠረት ተገቢውን ካሣ ያገኛል፡፡
8.2 ይህ ውል እንደተፈረመ ውል ሰጪ ለውል ተቀባይ የሊዝ ይዞታ የምስክር ወረቀት ወዲያውኑ የመስጠት ግዴታ
አለበት፡፡
8.4 ውል ሰጪ ውል ተቀባይ በውሉ መሠረት እየሠራ መሆኑን መከታተልና ከውል ውጭ የሆነ ጉዳይ ሲያጋጥም
በወቅቱ እንዲታረም የማድረግ ግዴታ አለበት፡፡ በውል ሰጪ የክትትል ማነስ ውል ተቀባይ ከውል ውጭ ሠርቶ
ከተገኘ ወይም ይህ ጉዳይ ውል መቋረጥ ካስከተለ ውል ሰጪ በኃላፊነት ይጠየቃል፡፡
9.1 በሊዝ አዋጁ አንቀጽ 21(1) መሠረት ውል ተቀባይ ቦታውን ለተፈቀደለት አገልግሎት ብቻ የማዋል ግዴታ
አለበት፡፡
9.2 በሊዝ ደንቡ አንቀጽ ……… መሠረት ውል ተቀባይ በ……… ወራት የጊዜ ገደብ ውስጥ ግንባታ የመጀመር
ግዴታ አለበት፡፡
9.3 በሊዝ አዋጁ አንቀጽ 21(2) መሠረት የከተማ አስተዳደሩ በጽሑፍ ካልፈቀደ በስተቀር ውል ተቀባይ የቦታውን
አጠቃቀም/አገልግሎት መቀየር አይችልም፡፡
9.4 ውል ተቀባይ የተፈቀደለትን ኘላን መቀየር ቢፈልግ የተቀየረውን ኘላን አቅርቦ ማፀደቅና የበፊቱን መመለስ
ይኖርበታል፡፡
9.5 የከተማ ቦታ አጠቃቀም ሲቀየር የሊዝ ዘመኑ እንደ አገልግሎት ዓይነቱ የሚቀየር ሲሆን ዋጋው ከፍ ያለ ከሆነ ውል
ተቀባዩ ልዩነቱን የመክፈል ግዴታ አለበት፡፡
10.2 የውል ተቀባይ የልማት እንቅስቃሴና የመሬት አጠቃቀሙ ሥራ ላይ ባለው ሕግና ተመሳሳይ የመሬት
አጠቃቀምን በሚመለከቱ መመሪያዎች ይገዛል፡፡
10.3 ውል ተቀባይ ባቀረበውና በጸደቀለት የሕንጻ ፕላን መሠረት ግንባታ መጀመር ይኖርበታል፡፡
10.4 የመሬት ውስጥ ሃብት፣ የተቀበሩ የመሠረተ ልማትና የአገልግሎት አውታሮች የመሬት የመጠቀም መብት ጋር
አይገናኙም፡፡
10.6 በይዞታው ውስጥ አካባቢን ሊበክል የሚችል መርዛማ ነገሮችን ማከማቸት አይችልም፡፡
10.7 ግንባታዎች በተፈቀደላቸው የጊዜ ገደብ ውስጥ መጀመራቸውን ውል ሰጪው በመቆጣጠር ውሉ እንዲቀጥል
ወይም በሊዝ አዋጁ አንቀጽ 25 (1/ሀ እና ሐ) መሠረት እንዲቋረጥ ያደርጋል፡፡
10.8 ማንኛውም ግንባታ በተፈቀደለት አገልግሎት መሠረት ግልጋሎት መስጠቱን ውል ሰጪው ይቆጣጠራል፣
የኢንዱስትሪ ቀጠና (Zone) ልማት ኦፕሬሽናል ማንዋል
14
12.1 ውል የተቋረጠው በዚህ ውል አንቀጽ 11/11.3 እና በሊዝ አዋጁ አንቀጽ 21/1 ሀ እና ሐ መሠረት የሆነ እንደሆነ
ውል ተቀባዩ ያሰፈረውን ንብረት በ 6 ወር ጊዜ ውስጥ በማንሳት ቦታውን ለውል ሰጪ የማስረከብ ግዴታ አለበት፡፡
12.2 ውል የተቋረጠው በሊዝ ደንቡ አንቀጽ……/……. መሠረት ከሆነ በአዋጁ አንቀጽ 21/3 መሠረት ውል ተቀባዩ
ተገቢውን የካሳ ክፍያ ያገኛል፡፡
12.3 ውሉ የተቋረጠው በሊዝ ደንቡ አንቀጽ …./…….. ከሆነ በደንቡ አንቀጽ …./…... መሠረት ተገቢው ወጪና
መቀጫ ተቀንሶ የሊዝ ክፍያው ለውል ተቀባይ ተመላሽ ይሆናል፡፡
12.4 ውሉ የተቋረጠው በሊዝ ደንቡ አንቀጽ …./…. የሆነ እንደሆነና ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት መቋረጡ
ከተረጋገጠ ውል ተቀባዩ መቀጫ አይኖርበትም፡፡
ሰ ሚዛን ……………
……………..
[የካርታ ቦታ]
መፍቻ
C1፡ ለኤግዚብሽን አዳራሽ
C2 ፡ ለሙዚየም
D1፡ ለትላልቅ ኢንዱስትሪ
D2፡ ለመካከለኛ ኢንዱስትሪ
D3፡ ለትናንሽ ኢንዱስትሪ
D4 ፡ በግንባታ ግዜ ለሚሠሩ ጊዜያዊ መጋዘኖች
ማብራሪያ፡ ሠንጠረዡ እንደሚያሳየው በ G+0 ሌቭል ለኢንዱስትሪና ወርክሾፕ የሚውል ቦታ እስከ ደረጃ
አራት እንደማይዘጋጅና በ G+1 ሌቭልም ቢሆን በደረጃ አንድ እንደማይዘጋጅ ያሳያል፡፡
G1,B1, 300
6 G+2 120-125 150-162 200 250 325
B2,B3,, 100
G1,B1, 10 ዐዐ
7 G+4 250 325 325 500 500
B2,B3,, 2 ዐዐ
G1,B1, 21 ዐዐ
8 G+6 375 500 600 750 1000
B2,B3,, 3 ዐዐ
G1,B1, 36 ዐዐ
9 G+8 500 651 800 1000 1325
B2,B3,, 4 ዐዐ
G1,B1,
1ዐ 55 ዐዐ G+10 625 625 1000 1250 1250
B2,B3,,
መፍቻ
G1፡ ለቢሮዎች
B1፡ ለትንንሽ ንግድ ማዕከላት
B2፡ ለመካከለኛ ንግድ ማዕከላት
B3፡ ለትልልቅ ንግድ ማዕከላት
ማብራሪያ፡ ሠንጠረዡ እንደሚያሳየው በ G+0 ሌቭል ለኢንዱስትሪና ወርክሾፕ የሚውል ቦታ እስከ ደረጃ ሦስት
እንደማይዘጋጅ ያሳያል፡፡
3. ለመጋዘኖችና ለጋራዥ አገልግሎት
ጠ/የወለል ስፋት
የሚያስፈልገው የቦታ ስፋት (ሜ/ካሬ)
የህንፃው ህንፃው የህንፃው
ተ.ቁ.
አገልግሎት የሚያርፍበት ከፍታ ደረጃ
ደረጃ 1 ደረጃ 2 ደረጃ 3 ደረጃ 5
የወለል ስፋት 4
1 J1, J2, J3, J4, 1 ዐዐ G+0 _ _ _ 100-250 330
1 ዐዐ
2 J1, J2, J3, J4, 200 G+0 _ _ _ 200-500 651
2 ዐዐ
3 J1, J2, J3, J4, 500 G+0 _ _ _ 500- 1650
5 ዐዐ 1250
4 J1, J2, J3, J4, 700 G+0 _ _ _ 700- 2320
700 1750
5 J1, J2, J3, J4, 1000 G+0 _ _ _ 1000- 3320
1000 2500
6 J1, J2, J3, J4, 300 G+2 _ 100-162 150-200 250 325
300
7 J1, J2, J3, J4, 100 G+4 250-285 285 400 500 651
2 ዐዐ
8 J1, J2, J3, J4, 35 ዐዐ G+6 700 700 1000 1250 1250
5 ዐዐ
9 J1, J2, J3, J4, 63 ዐዐ G+8 1000 1150 1150 1750 2280
7 ዐዐ
1ዐ J1, J2, J3, J4, 11000 G+10 1425 1425 2000 2500 2500
1000
መፍቻ
J1, J2, J3፡ ለመጋዘኖች
J4፡ ለጋራዥ አገልግሎት
ማብራሪያ፡ ሠንጠረዡ እንደሚያሳየው በ G+0 ሌቭል ለመጋዘኖችና ጋራዥ አገልግሎት የሚውል ቦታ እስከ ደረጃ
ሦስት እንደማይዘጋጅ ያሳያል፡፡
መፍቻ
F1፡ ለትልልቅ ሱቆች
F2፡ ለትንንሽ ሱቆች
F3 ፡ ለሸቀጣ ሸቀጥ መጋዘን
ማብራሪያ፡ ሠንጠረዡ እንደሚያሳየው ከ G+2 በታች ለሆኑ ትናንሽ ሱቆች ግንባታ የሚውል ቦታ በደረጃ አንድና ሁለት
እንደማይዘጋጅ ያሳያል፡፡ በተመሳሳይም በ G+0 ሌቭል ለትናንሽ ሱቆች መስሪያ ተብሎ እስከ ቦታ ደረጃ
አራት አይዘጋጅም፣
የኢንዱስትሪ ቀጠና (Zone) ልማት ኦፕሬሽናል ማንዋል
24