You are on page 1of 87

ማውጫ

ምህጻረ-ቃላት (Acronyms and Abbreviations) ................................................................................ I


የፍኖተ ካርታው ይዘት.................................................................................................................. II
1 መግቢያ ................................................................................................................................ 1
መቅድም ............................................................................................................. 1
የፍኖተ ካርታው አላማዎች /Rail Sector’s Roadmap objectives/ ....................... 2
የፍኖተ ካርታው አዘገጃጀት ................................................................................... 3
2 የባቡር ዘርፍ አመጣጥ ፣ የዘርፉ ተዋናዮችና አስተዳደራዊ የለውጥ ሂደት .................................. 4
የባቡር ዘርፍ አመጣጥ /ታሪካዊ እድገት ................................................................. 4
2.1.1 የአለም አቀፍ የባቡር ዘርፍ እድገት ............................................................... 4
2.1.2 የባቡር ዘርፍ በአውሮፓ አሜሪካና በኢሲያ ...................................................... 4
2.1.3 የባቡር ዘርፍ በአፍሪካ ................................................................................... 6
2.1.4 የባቡር ዘርፍ በኢትዮጵያ ............................................................................... 7
የባቡር ትራንስፖርት ዘርፍ አስፈላጊነትና ከመንገድ ትራንስፖርት ጋር ያለው ንጽጽር 9
የባቡር ዘርፍ ተዋናዮችና አገነባብ ........................................................................ 11
2.3.1 የባቡር ዘርፍ ባለቤቶች /key owners /አገነባብ ............................................. 11
2.3.2 የባቡር ዘርፍ ተዋናዮች /key Players)........................................................ 13
የባቡር ዘርፍ አስተዳደራዊ የለውጥ (Sectoral Reform) ሂደትና ወቅታዊ ሁኔታ ... 14
2.4.1 የዘርፉ አስተዳደራዊ ጽንሰ ሃሳቦች /መሠረታዊ ጽንሰ ሃሳቦች/......................... 14
2.4.2 የዘርፉ አስተዳደራዊ ሂደት እድገት ውጤቶች................................................ 18
2.4.3 የባቡር ዘርፍ ወቅታዊ ሁኔታ ...................................................................... 19
3 የኢትዮጵያ ባቡር ዘርፍ ስትራቴጂያዊ ትንተና........................................................................ 21
አካባቢያዊ ትንተና (SWOT) ............................................................................... 22
አስቻይ ሁኔታዎች (ጥንካሬ + መልካም አጋጣሚዎች) ......................................... 28
ፈተናዎች (ድክመት + ስጋቶች) .......................................................................... 31
የተለዩ ስትራቲጂክ የትኩረት መስኮች .................................................................. 34
4 የአሠራርና የፋይናንስ ሁኔታ (Business & Finance Model) ............................................... 36
የአሠራር ሁኔታ (Business Model) .................................................................. 36
4.1.1 የዓለም አቀፍ ባቡር ዘርፍ ተሞክሮ .............................................................. 36
4.1.2 ለኢትዮጵያ የባቡር ዘርፍ የሚመከረው የቢዝነስ ሞዴል ................................. 40
የፋይናንስ ሞዴል (Financial Model) .............................................................. 43
4.2.1 የካፒታል ኢንቨስትመንትን በተመለከተ ......................................................... 43
4.2.2 የኦፕሬሽን ወጪን ገቢ ወጪ ሚዛንን በተመለከተ ......................................... 48
5 ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች............................................................................................... 50
ቁልፍ ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች ............................................................................... 51
5.1.1 ዘላቂ የፋይናንስ አቅም መፍጠር .................................................................. 51
5.1.2 የዘርፉን ገቨርናንስ ሥርዓት ማጠናከር ......................................................... 55
መሠረታዊ ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች ........................................................................ 57
5.2.1 ጠንካራ የሃገራዊ ባቡር ዘርፍ አቅም፣ .......................................................... 57

የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)


5.2.2 አስተማማኝ የባቡር ደኅንነትና ጸጥታ፣ ......................................................... 64
አበይት ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች ............................................................................. 68
5.3.1 ዘላቂ የመሠረተልማት ሃብት፣..................................................................... 68
5.3.2 ውጤታማ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት፣ .............................................. 76
6 ማጠቃለያ ........................................................................................................................... 80
7 ዋቢ ምንጮች ...................................................................................................................... 81

የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)


ምህጻረ-ቃላት (ACRONYMS AND ABBREVIATIONS)

AALRT Addis Ababa Light Rail Transit


CB Capacity Building
C.D.E. “Compagnie de Chemin de Fer Djibouto-Ethiopien”/The Djibouti-
Ethiopian Railway/
EDR Ethio-Djibouti Railway
ERC Ethiopian Railways Corporation
FDRE Federal Democratic Republic of Ethiopia
IM Infrastructure Manager
JV Joint Venture
LRT Light Rail Transit
MoTL Ministry of Transport and logistic
OP Operator
OTBU Other Business Units
PEHAA Public Enterprise Holding and Administration Agency
PPP Public Private Partnership
SDGs Sustainable Development Goals
SPV Special Purpose Vehicle
SWOT Strength, weakness, opportunity and treat
PESTEL Political, Economical, Social, Technological, Environmental and
Legal
TBL Transboundary Lines
TOD Transit Oriented Development
UIC “Union Internationale Des Chemins De Fer” /The International Union
of Railways/

I
የፍኖተ ካርታው ይዘት

ይህ ፍኖተ ካርታ በተወሰነ የጊዜ ወሰን አንድ ራዕይን ለማሳካት በሚል የተቀረጸ ስትራቴጂክ ዕቅድ
ሳይሆን፤ የባቡር ሴክተሩን ተልዕኮ በትክክል ለማስቀመጥ፣ በተቀመጠው ተልዕኮ የሚኖር የሴክተር
አደረጃጀትን ለመወሰን፣ ሴክተሩ ለውጤታማነት ሊያከናውን የሚገባውን ለውጥ አምጪ ስትራቴጂዎች
ለመለየት፣ እንዲሁም የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን ሚና በአግባቡ ለማመላከት በሚል የተዘጋጀ ፍኖተ
ካርታ ነው።

ፍኖተ ካርታው በስድስት ምዕራፎች የተከፈለ ነው። የመጀመሪያው ምዕራፍ መቅድምና የፍኖተ ካርታው
አላማ ያካተተ ነው። ሁለተኛው ምዕራፍ የዓለም አቀፍ ባቡር ዘርፍን ታሪካዊ አመጣጥ ከለውጥ ሂደቱና
ውጤቶቹ ጋር ያስቃኛል። የኢትዮጵያ ባቡር ዘርፍ ነባራዊ ሁኔታ በዝርዝር ተተንትኖ ለፍኖተ ካርታው
መነሻ የሆኑ አስቻይና ፈታኝ ሁኔታዎች ተለይተው የትኩረት አቅጣጫዎች በሦስተኛው ምዕራፍ
ተመለክተዋል። የትኩረት አቅጣጫዎቹን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችል የቢዝነስና የፋይናንስ ሞዴል
በአራተኛው ምዕራፍ ቀርቧል። በምዕራፍ አምስት ደግሞ በየትኩረት መስኮች ሴክተሩ ሊከተላቸው የሚገቡ
ስትራቴጂያዊ አቅጣጫዎች ቀርበዋል። የመጨረሻው ምዕራፍ ደግሞ የማጠቃለያ ሃሳብ የያዘ ነው።

II
1 መግቢያ

መቅድም

ሃገራችን ከ2ኛው ሚሊኒየም መባቻ ጀምሮ በተከታታይ የኢኮኖሚ ዕድገት እያስመዘገበች የመጣች ሲሆን
ይህን ዕድገት በዘላቂነት ለማስቀጠል እና የተነቃቃውን የጭነትና መንገደኛ ትራንስፖት ፍላጎት
ለማስተናገድ የሚያስችል በቂ የመንገድ መሠረተ-ልማት አልነበራትም። ይህን በመገንዘብ መንግስት የየብስ
ትራንስፖርት ዘርፉን ኢኮኖሚውን የሚደግፍ እንዲሁም የሚያነቃቃ ማድረግ የሚቻልበትን አቅጣጫ
ለመወሰን እንዲያስችለው የቴክኒካል አማካሪ ቡድን አቋቁሞ ጥናት አስጠንቷል። ይህ ቡድን በወቅቱ
የትራንስፖርትና መገናኛ ሚኒስቴር በኩል ከተሰጠው ኃላፊነት በመነሳት የተለያዩ የመረጃ ምንጮችን
በመፈተሽ እንዲሁም የሌሎች አገራትን ተሞክሮ በመዳሰስ ሪፖርቱን አቅርቧል።

ሪፖርቱ በቀጣይ መንግስት ትኩረት እንዲያደርግባቸው ከጠቆማቸው ሃሳቦች መካከል የሃገሪቱን የመንገድ
መሠረተ-ልማት አውታር ማስፋፋት ወሳኝ ሲሆን፤ ሃገሪቱ ያላትን የትራንስፖርት ፍላጎት የሚያስተናግድ
የመንገድ ኔትወርክ ደረጃ ላይ ለመድረስ ሰፊ ኢንቨስትመንት ወጪ እና ረጅም ጊዜ የሚጠይቅ እንደሆነ
አመላክቷል። ይህን ችግር ለመወጣት ባቡር አዋጭ በሆነባቸው የርቀት መጠኖች እና በተመረጡ የልማት
ኮሪደሮች ላይ የዘመናዊ የባቡር ኔትወርክ መዘርጋት ጊዜ የማይሰጠው አማራጭ መሆኑን አስረግጧል።
በዚህም ሳይወሰን የባቡር ኔትወርክ ሊዘረጋባቸው የሚገቡ ኮሪደሮችን ከማህበረ-ኢኮኖሚያዊ መስፈርት
አንጻር በመለየት አስቀምጧል። በማጠቃለያውም ይህን የባቡር መሠረተ-ልማት የሚገነባ፣ የሚጠግን፣
የሚያስተዳድር እና አገልግሎት የሚሰጥ ተቋም እንዲኖርም ምክር ለግሷል።

ከላይ በተጠቀሰው ሪፖርት መሠረት የተቋቋመው ተቋም የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን በመንግስት
የጸደቀውን የ5006 ኪሜ ማስተር ፕላን መሠረት አድርጎ በመጀመሪያው እና በሁለተኛው የዕድገትና
ትራንስፎርሜሽን ዕቅዶች መጠነ ሰፊ የባቡር መሠረተልማት ግንባታ ፕሮጀክቶችን (2470 ኪ.ሜ. =
በ1ኛው ዕትዕ፣ 2801 ኪ.ሜ. = በ2ኛው ዕትዕ) ለማከናወን አቅዶ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል። እስከ አሁን ድረስ
656 ኪ.ሜ. ተገንብቶ የተጠናቀቀ እና ወደ አገልግሎት የገባ፣ 610 ኪ.ሜ. በግንባታ ላይ የሚገኝ የሃገር
አቀፍ የባቡር መስመር ተግባራዊ ያደረገ ሲሆን፤ 34 ኪ.ሜ. የከተማ ቀላል የመንገደኞች ባቡር መስመርም
ገንብቶ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።

ኮርፖሬሽኑ ከላይ የተጠቀሰውን ዕቅድ ለማሳካት ባደረገው ጥረት በዕቅድ ወቅት ያልታሰቡ ከፍተኛ
ፈተናዎች መካከል ዝቅተኛ ብድር የመመለስ አቅም ፣ ቀጣይነት ያለው ፋይናንስ ምንጭ እጦት፣ ሃገራዊ
የሰው ኃይልና የቴክኖሎጂ አቅም ደካማነትና በውጭ ሃገር አቅም ጥገኛ መሆን በዋነኝነት ይጠቀሳሉ።
እነርሱንም ለማለፍ የተለያዩ ስትራቴጂያዊ አማራጮችን በመጠቀም ሃገራዊ የባቡር ሴክተሩ አሁን
የሚገኝበት ደረጃ ላይ ደርሷል።

1
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
የፕሮጀክት ትግበራ ስራ ከተገባ ጀምሮ ሁለት ጊዜ ስትራጂክ ዕቅድ የተዘጋጀ ሲሆን ሆኖም በሀገሪቱ
ባጋጠሙ የጦርነትና ኢኮኖሚያዊ ተግዳሮቶች የተነሳ በአሁኑ ወቅት ወደስራ ይገባል ተብሎ ይጠበቅ
የነበረው የአዋሽ ወልድያ ሀራገበያ የባቡር መስመር ሳይጠናቀቅና ክዚህ በፊት ወደ ስራ የገቡት የአዲስ
ጅቡቲ የባቡር መሰመርና የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር መስመሮች ቀጣይነት ያለው የትራንስፖርት ስራ
መስራት እንዲችሉ የስትራቴጂ ለውጥ አስፍላጊ ሆኖ ተገኝቷል።

ኮርፖሬሽኑ ሃገራዊውን የባቡር ማስተር ፕላን እየገነባ የሚቀጥልበትን ዕድል እያጠበበ የመጣ እና
በቀጣይም ያለበትን የፋይናንስ ጫና የመቋቋም አቅሙን እየተፈታተነ የመጣ በመሆኑ ቀደም ብሎ
ስትራቴጂያዊ አካሄዱን መከለስ፣ በዚህም የተገነባውን የባቡር መሠረተ-ልማት በአግባቡ በመጠቀም
ውጤታማ ማድረግ፣ ዘርፉን ለኢኮኖሚው ወሳኝ ሚና የሚጫወትበትን አካሄድ መቀየስ እንዲሁም የዘርፉን
የገቢ አቅም ማሳደግ በሚችሉ ተጓዳኝ የስራ ዘርፎችን ማጤን አስፈልጓል።

በመሆኑም ይህ ሰነድ በሴክተሩ ላይ የተጋረጡ ችግሮችን ለመፍታት ሊያዙ የሚገባቸውን ስትራቴጂያዊ


አጀንዳዎች ከነባራዊ ሁኔታዎች እና ከሌሎች የዓለም ሃገራት ተሞክሮ አንፃር በመቀመር ያቀረበ ሲሆን
መንግስት በሴክተሩ ላይ ለሚይዘው አቅጣጫ ጥናታዊ መነሻ ሆኖ ለውሳኔ ቀርቧል።

የፍኖተ ካርታው አላማዎች /RAIL SECTOR’S ROADMAP OBJECTIVES/

ተዘጋጅቶ የቀረበው የባቡር ዘርፍ ፍኖተ ካርታ ኢትዮጵያ አገር በቀልና አለም አቀፍ የልማት ግቦችን
በማስተሳሰር ከባቡር ኢንዱስትሪው የአገርን እና የህዝብን የላቀ ኢኮኖሚያዊ፣አከባቢያዊ፣ማህበራዊ እና
ፖለቲካዊ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ ነው። በዚሁ መሰረት የባቡር ዘርፍ ፍኖተ ካርታ የሚከተሉትን ወሳኝ
አለማዎች ለማሳካት ተዘጋጅቶ ቀርቧል።

• የባቡር ዘርፍ ለኢትዮጵያ የሚያበረክተውን ኢኮኖሚያዊ የአብዥነት ሚና በማሳደግና በማጠናከር


ኢትዮጵያ ወደ መካከለኛ ገቢ ለመሸጋገር ያስቀመጠችውን ግብ ለማሳካት፤
• በባቡር ዘርፍ አገራችን አስተማማኝ፣ተወዳዳሪና ዘላቂ የባቡር ትራንስፖርት ሽፋን እና አገልግሎት
ባለቤትና ተጠቃሚ እንድትሆን ለማስቻል፤
• የባቡር ዘርፍ ተዋናዮችን በዘርፉ ቁልፍ፣መሰረታዊና አበይት ስትራቴጂክ ጉዳዮች ላይ በቀጥታ
እንዲሳተፉ በማድረግ የዘርፉን የፋይናንስ፣ የአቅም፣ የቴክኖሎጂና የአሰራር እጥረቶችን
ለመሙላት፤
• በራስ ኃይል የባቡር ዘርፉን ገቢ በሚያሳድጉ ተጓዳኝ የገቢ ማመንጫ ስራዎች ላይ በመሰማራት
በዘርፉ ላይ የሚስተዋለውን የብድርና የድጎማ ጫና ለመቀነስ እና ወደ ትርፋማነት ለመሸጋገር፤
• የባቡር ኢንዱስትሪን አጠቃላይ አገራዊ ፋይዳ ለመንግስት ውሳኔ ሰጭ አካላት የተሻለ ግልጽነትና
የጋራ መግባባትን በመፍጠር ፍኖተ ካርታውን አጸድቆ በየደረጃው ወደ ትግበራ ለመግባት፤

2
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
የፍኖተ ካርታው አዘገጃጀት

ኮርፖሬሽኑ ይህን የባቡር ዘርፍ ፍኖተ ካርታ ለማዘጋጀት የሚከተሉትን ዘዴዎች ተጠቅሟል ፦

• በቅድሚያ ከኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን የተለያዩ የስራ ክፍሎች የተውጣጡና የተለያዩ
የሙያ መስክ ያላቸው የስራ መሪዎችን ያቀፈ የፍኖተ ካርታ አዘጋጅ ኮሚቴ በተቋም ደረጃ ተዋቅሮ
ወደ ስራ እንዲገባ ተደርጓል፡፡
• በባቡር ዘርፍ ዋና ዋና ተዋናዮች በኮርፖሬሽኑና አጋር ድርጅቶች በዘርፉ ፍኖተ ካርታ ዙሪያ
አስቀድሞ የተዘጋጁ ሰነዶችን፣ በአማካሪ ድርጅቶች የተጠኑ የባቡር ዘርፍ ሪፎርም ጥናቶች፣
በሬጉላቶሪ ተቋማት ስለባቡር ዘርፍ የተቀመጡ ጥናቶችና ግዴታዎች እና የባቡር ዘርፍ አሁን
ያለበትን ማነቆዎችና ችግሮች የመለየት፣የማጥናት፣የመገምገምና የመከለስ ስራ በስፋት
ተከናውኗል፡፡
• የባቡር ዘርፍን አለማቀፋዊና አህጉራዊ ታሪካዊ አመጣጥ፣ ስለ ኢንዱስትሪው እድገትና በዚያ
ውስጥም የተከተላቸው የአደረጃጀትና የአሰራር ጽንሰ ሃሳቦች ዙሪያ ያሉ ልምዶችን፣ተሞክሮዎችንና
ጥናቶች የመለየትና የመተንተን ስራ ተከናውኗል፡፡
• የባቡር ዘርፍ ልማት/ማስፋፋት/ ከአለም አቀፍ የዘላቂ ልማት ግቦች /SDGs/፣ ከአፍሪካ ህብረት
ቪዥን 2063 እና ከኢትዮጵያ ብሄራዊ የልማት እቅድ፣ ከአገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ፖሊሲ፣
ከትራንስፖርት ሴክተር ማስተር ፕላን፣ በዘርፉ ያሉ ሬጉላቶሪ ግዴታዎች፣ስለዘርፉ የገቢ
ምንጭነትና ፋይዳ ብሎም ከሉሌች የሴክተሩ ፍላጎቶች ጋር ያለው ትስስርና ቁርኝትን በጥልቀት
የመፈተሸና የማጥናት ስራ ተከናውኗል፡፡
• የኢትዮጵያ ባቡር ዘርፍ ነባራዊ ሁኔታ በዝርዝር ተተንትኖ ለፍኖተ ካርታው መነሻ የሆኑ አስቻይና
ፈታኝ ሁኔታዎች በአግባቡ በመለየት ተገቢውን የትኩረት አቅጣጫዎችን በፍኖተ ካርታው
የማካተትና ለውሳኔ ሰጭ አካል በግልጽ የማመላከት ስራ ተከናውኗል።
• የአለም አቀፍ ምርጥ ተሞክሮን በመውሰድ የትኩረት አቅጣጫዎቹን በኢትዮጵያ ተግባራዊ
ለማድረግ የሚያስችል የተጣጣመ የቢዝነስና የፋይናንስ ሞዴል በመቅረጽ የፍኖተ ካርታው አካል
እንዲሆኑ ተደርጓል፡፡ በየትኩረት መስኮች ሴክተሩ ሊከተላቸው የሚገቡ ስትራቴጂያዊ አቅጣጫዎች
ተለይተው በዚህ ፍኖተ ካርታ እንዲካተቱም ተደርጓል፡፡

በአጠቃላይ በጥናት፣በግምገማና በክለሳ የተለዩ በርካታ የባቡር ኢንዱስትሪ መረጃዎችና ማስረጃዎች ብሎም
ተሞክሮዎች የስታንዳደር የፍኖታ ካርታ አዘገጃጀት ይዘትን ተከትለው፣ተደራጅተውና ተጠናቅረው
በቀረበው መልኩ ሰነዱ ተዘጋጅቷል፡፡

3
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
2 የባቡር ዘርፍ አመጣጥ ፣ የዘርፉ ተዋናዮችና አስተዳደራዊ የለውጥ ሂደት

የባቡር ዘርፍ አመጣጥ /ታሪካዊ እድገት

2.1.1 የአለም አቀፍ የባቡር ዘርፍ እድገት

የምድር ባቡር (railway) ማለት በላዩ ላይ የሚንቀሳቀሱትን ተሸከርካሪዎች የሚጓዙበትን መስመር


እንዳይለቁ እንዲመራ የተዘጋጀ መስመር ወይም “‘railway is a prepared track which so guides
the wheels of the vehicles running on it that they cannot leave the track” ነው በማለት
ቀደምት የባቡር ምሁር የሆኑት ዶ/ር ማይክል ማቲው ሌዊስ ብያኔ እንደሰጡት ማስረጃዎች ያሳያሉ
(Lewis፣ 1974)። ይህ ገለጻ የራሱ የሆነ ቴክኒካዊ ቅለት ቢኖረውም በውስጡ የምድር ባቡር ተብሎ
በተለምዶ ከሚታወቀው ሰፋ አድርጎ ማንኛውም በተከለለ መስመር /ሃዲድ/ ላይ የሚደረግ እንቅስቃሴን
በሙሉ ያቀፈ ወሰን አለው። በገለጻው “prepared track” የሚለው ሃረግ ሃዲዶች ለአንድ ለተለየ ዓላማ
ተብለው የሚገነቡ አካላትን ለማመለካት ሲሆን የመተግበሪያ ሥርዓታቸው እንደዓላማው የተለያየ ቢሆንም
የአሠራር መርሆቻቸው ግን ተመሳሳይ ናቸው። በዚህም የምድር ባቡር ቀጥተኛ የመጓጓዣ ዓይነት (linear
transport feature) ነው የሚለውን ጽንሰ ሃሳብ ያሳያል።

በዶ/ር ሊዊስ ሰፊ የምድር ባቡር ትርጓሜ መሠረት የምድር ባቡር (railway) ከክርስቶስ ልደት በፊት
ከ6ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ እስከ 9ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ በጥንታዊ ግሪክ ከድንጋይ የተሠራ 6ኪ.ሜ.
የሚረዝም ሃዲድ የነበረውና በደቡባዊ ግሪክ ፖሎፖኔዝ ሰርጥ መርከቦችን የሚያጓጉዙበት ዳዮሎኮስ
(Diolokos) የተባለው ጥንታዊ የባቡር መስመር ቀደምት መሆኑን እንረዳለን። ከዚህ በመቀጠል እስከ
15ኛው ክፍለ ዘመን አካባቢ ድረስ ለብዙ ክፍለ ዘመናት ያገለገሉ ከዕንጨት የተሰሩ ሀዲዶችንና በእነርሱም
ላይ የሚንቀሳቀሱ ተሸከርካሪዎችን ጥቅም ላይ ይውሉ እንደነበረ በጥንታዊ የታሪክ መፃፍት/Agricola’s
De Re Metallica) መረጃው ይገኛል።

18ኛው ክፍለ ዘመን ከእንጨት የተሰሩ የባቡር ሀዲዶች ለከፍተኛ ጭነቶች እና ለተለያየ ዓላማዎች መዋል
ጀመሩ። ሀዲዶች በሰዎች ከሚገፉ የድንጋይ ከስል፤ ድንጋይ እና ማዕድናትን ከሚያጓጉዙ ባለ 4 እግር
የጭነት ጋሪ አስተናጋጅ አጫጭር መስመሮች በፈረስ እስከ ሚጎተቱ ትላልቅ የጭነት ጋሪ አመላላሽ
ረጃጅም መስመሮች ድረስ እያደጉና እየተስፋፉ መጥተዋል። በዚያው ክፍለ ዘመን ማጠናቀቂያ አካባቢ
የእንጨት ሀዲዶችና ተሸከርካሪዎች በብረት ወደ ተሰሩ መቀየር ጀምረዋል።

2.1.2 የባቡር ዘርፍ በአውሮፓ አሜሪካና በኢሲያ

የመጀመሪያዎቹ በሞተር ሀይል የሚንቀሳቀሱ ባቡሮችን የሚያስተናግዱ መስመሮች በ19ኛው ክፍለ ዘመን
መጀመሪያ በእንግሊዝና ዌልስ በጥቂት የማዕድንና አነስተኛ ኢንደስትሪዎች አላማ ተገንብተው ጥቅም ላይ

4
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
ውለዋል። በ1830 በሊቨርፑልና በማንችስተር ከተሞች መካከል የተዘረጋው መስመር የ “ዘመናዊ የባቡር
መስመር” መከሰት መነሻ መሆኑን አብዛኞቹ የዘርፉ ታሪክ ምሁራን ይስማማሉ ። ለዚህም መነሻው
ሰዎችንና ጭነትን በጋራ የሚያንቀሳቅስ፣ ለማንኛውም የትራንስፖርቱ ተጠቃሚ ክፍት የሆነ፣ በሞተር
የሚንቀሳቀስ እና መንግስታዊ የቁጥጥር ስርዓት የተተገበረበት የመጀመሪያው መስመር መሆኑ ነው።
(Robbins 1998).

በ1850 አብዛኞቹን የህዝብና የኢንዱስትሪ ማዕከላት የሚያገናኝ ብሄራዊ የባቡር መረብ በመገንባቷ
ብሪታንያ ከፍተኛ ጥቅም አግኝታለች። በሌሎች የአውሮፓ ሃገራትም የብሪታንያ መሃንዲሶች በመዘዋወር
ለአህጉሪቱ ከፍተኛ ጥቅም የሰጡ መስመሮችነ በመገንባት በ1907 አውሮፓ የባቡር መስመር ሽፋን እስከ
320000 ኪሜ እንዲደርስ አስተዋጽዖ አድርገዋል (Gourvish 1996; Channon 1996; Ambler 1999;
Robbins 1998) ። በተመሳሳይ ወቅት በአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች ባለሃብቶች ወደቦችን ከንግድ ማዕከላት
ጋር ለማያያዝ ውድድራዊ በሚመስል መልኩ የባቡር መስመሮችን መገንባት የጀመሩ ሲሆን በ1907
የአሜሪካ የባቡር መስመር ሽፋን 379000 ኪሜ ሊደርስ ችሏል (Robbins 1998) ። የምጣኔ ሃብት ታሪክ
አጥኚዎች የምድር ባቡር ለኢኮኖሚ ዕድገትና ኢንዱስትሪ መስፋፋት ያበረከተው ግልጽ አስተዋጽዖ መጠን
ላይ ወጥ ስምምነት ባይኖራቸውም የ19ኛው ክፍለ ዘመን ኢንዱስትሪ መስፋፋት በዋነኝነት በእንፋሎት
ሞተሮች በሚሠሩ ባቡሮች ተጽዕኖ የመጣ መሆኑን ሁሉም ይቀበሉታል። በተለይ በአሜሪካ የፖለቲካ፣
የፋይናንስ፣ የንግድና አስተዳደር መዋቅሮችን በኋላም ለግዙፍ የኮርፖሬት ቢዝነሶች መፈጠር ምክንያት
የባቡር ሚና አቻ የለሽ ነበር (Dobbin 1994; Chandler 1990) ።

እ.ኤ.አ. በ1850 ዎቹ የምድር ባቡር ተጽዕኖ ቀድመው ኢንዱስትሪ ካስፋፉት ከአውሮፓና አሜሪካ አልፎ
በሌሎች የኣለም ሃገራትም ግንባታዎች የተጀመሩ ሲሆን በተለይም የአውሮፓ ቅኝ ግዛቶች፣ ደቡብ
አሜሪካ፣ አውስትራሊያ፣ እስያና ካናዳ በተከታታይ ከ1852 እስከ 1864 ባሉት ጊዜያት ወደ ባቡር
መሠረተልማት ግንበታ ተቀላቅለዋል። በ19ኛው ክፍለ ዘመን ሩስያም ለኢኮኖሚያዊ ትስስርና ፖለቲካዊ
ሃያልነትን ለማረጋገጥ ወደ ባቡር መስመር ልማት ገብታለች። በዚህም በ 1907 እ.ኤ.አ. ከአውሮፓና
አሜሪካ ውጭ ባሉ የዓለም ሃገራት 268,800 ኪሜ (በወቅቱ ገንዘብ 1.5 ቢሊየን ፓውንድ የፈጀ) የባቡር
መሠረተ-ልማት እንደተገነባ ታሪክ ይናገራል (Robbins 1998) ።

ከላይ የተጠቀሱት የባቡር መሠረተ-ልማት ዝርጋታዎች የሰፊውና ውስብስቡ አብዛኛውን የዓለም ክፍል
ያዳረሰ የአውሮፖውያን ኢምፔሪሊዝም መስፋፋት አንዱ አካል ነበር። አውሮፓውያኑ የባቡር መሠረተ-
ልማትን በተለያዩ የዓለም ክፍሎች በመዘርጋታ ከእነርሱ ቀጥተኛ አገዛዝ ያመለጡትን እንደ ቱርክ፣ ቻይና፣
ጃፓን ደቡብ አሜሪካና ታይላንድ ያሉትን በተዘዋዋሪ በፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ተጽዕኖአቸው ስር ማድረግ
ችለው ነበር።

የየብስ ትራንስፖርትን በሞኖፖሊ በመቆጣጠር ደረጃ ለምድር ባቡር ታላቅ ወይንም “ወርቃማ” የሚባለው
ጊዜ በ1ኛው የአለም ጦርነት ወቅት በአብዛኛው የአለም ሀገራት ጥቅም ላይ የዋለበት ጊዜ ሲሆን በ20ኛው
5
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
ክፍለ ዘመን አጋማሽ የዘመናችን አብዛኛው የአለም የባቡር መስመሮች ተገንበተው ስራ ላይ እንደነበሩ
መረዳት እንችላለን። ከዚህ ጊዜ በኋላ አብዛኛው የአለማችን የባቡር መስመሮች ታሪክ በዝግታ የመቀነስ
አዝማሚያ አሳይቷል እስከ 1964 እ.ኤ.አ ድረስ በአብዛኛው የነበሩትን መስመሮች አቅም በመጠኑ ከማሳደግ
ውጪ ጥቂት መስመሮች ብቻ የተገነቡበት ሲሆን በ1964 እ.ኤ.አ ጃፓን የመጀመሪያውን ለሰው ማጓጓዣ
የሚውል “ቶካይዶ“ የተባለውን ፈጣን የባቡር መስመር ወደስራ አስገብታለች። የጃፓንን ፈለግ በመከተል
የመንገደኞች ኤክስፕረስ መስመሮችን ፈረንሳይና ሌሎች ሀገሮችም የገነቡ ሲሆን ይህ አካሄድም
የአለማችንን የመንገደኞች ብዝሀ ትራንስፖርት አገልግሎት (Passenger Mass Transit Service)
አሰጣጥን እስከ ወዲያኛው የቀየረ ነበር ።

ከዚህ በተለየ የተለመዱትን የጭነትና መንገደኞች ባቡሮችን በጋራ የሚያስተናግዱ መስመሮች


(Conventional Railways) ግንባታ የቀጠለችው ቻይና ስትሆን ምንም እንኳን ከጀማሪዎቹ አውሮፓውያን
የባቡር መሠረተ-ልማት ገንቢዎች የአሰራር ስልት የግብዓት ፤ የሀይል አጠቃቀምና የአስተዳደር ስርዓት
ልዩነት ቢኖርም የተለመዱትን የጭነትና መንገደኞች ባቡሮችን በጋራ የሚያስተናግዱ መስመሮች
(Conventional Railways) ግንባታዎች መቀጠል ኢኮኖሚያዊና ማኀበራዊ አስተዋፅኦው ላቅ ያለ መሆኑን
በቻይና ኢኮኖሚ ላይ ያመጣውን መልካም ተፅዕኖ በማየት መረዳት ይቻላል ።

በአጠቃላይ ባቡር ለሃገራት ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ዕድገትና ትስስር የሚያበረክተው


አስተዋጽዖ ከፍተኛ የሆነ አይነተኛ የየብስ ትራንስፖርት ዘርፍ በመሆኑ ቴክኖሎጂው በየጊዜው እየተሻሻለ
አሁን ላለንበት ዘመናዊ የባቡር ዘርፍ መፈጠር ምክንያት ሆኗል።

2.1.3 የባቡር ዘርፍ በአፍሪካ

እንደ አህጉር በአፍሪካ የባቡር ትራንስፖርት ታሪካዊ አመጣጥ የሚጀመረው የኢንግሊዝ ኢምፓየር
የመጀመሪያውን የባቡር መስመር እኤአ በ1856 በግብጽ የገነባው ሲሆን መስመሩም አሌክሳንደሪያን ከካይሮ
በባቡር የሚያገኛኝ ነበር። ይህም የሆነው እኤአ ከ1800 ጥቂት አስርተ አመታት ቀደም ብሎ በአውሮፓ
ማለትም በቅደም ተከተል በታላቋ ብሪታንያና በፈረንሳይ የመጀመሪያው ሎኮሞቲቭ መሰራትን ተከትሎ
ነው። በውሃ ተከባ በምትገኘው አፍሪካ አብዛኛው የባህር በሮች የተገነቡት ለባሪያ ንግድ መሆናቸው
በአብዛኛው የአውሮፖ ባህረተኞች የሚታወቁ ነበር። ባቡር ከባህር ዳርቻ ወደ ውስጥ ለቀኝ ገዢዎች
የመጀመሪያ የቅኝ ግዛት ማስፈጸሚያ ስትራቴጂ ስልት ሆኖም አገልግሏል።

የባህር ተጓዥ የሆነው Stanley (1841-1904), የቤልጀም ንጉስ የሆነውን ሊዮፖልድ ሁለተኛን /Leopold
II/ እንዳስገነዘበው ኮንጎን በቀኝ ግዛት ለማቆየትና ለማስተዳደር በቅድሚያ የባቡር መስመር መገንባት
አስፈላጊ መሆኑ ታምኖቦት በኮንጎ የካታንጋ ምድር ባቡር እኤአ በ1902 ተገነባ። በተለያዩ በቅኝ ግዛት
በተያዙ የአፍሪካ አገራት የባቡር መንገድ ንብረታቸውን አንድ ቦታ ለማቆየት፣አስተዳደራቸውን
ለማቀላጥፍ፣ ወታደራቸውን በፍጥነት ወደ ጦርነት ቦታ ለመጓጓዝና ለመዋጋት፣ቦታ ይዘው ንግድን
6
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
ለማሳደግ ጥቅም ላይ እንደዋለ ታሪክ ያስረዳል። በተለያዩ ግዛቶች የቀኝ ገዢዎች ቁልፉ የባቡር
ትራንስፖርት ፍላጎት የነበረው ጥሬ እቃ ከአፍሪካ ለማጓጓዝ ሲሆን ከነዚህ ውስጥም ወርቅ፣ አልማዝ፣
ኮባልት፣ ማንጋኔዝ፣ ጥጥ፣ ጣውላ ወዘተ. ይገኙበታል። መነሻውም ከትላልቅ የማዕድን ማዕክል ተነስቶ
በአቅራቢያ ወደ ሚገኝ ወደብ ሲሆን ህጉም ለቀኝ ገዢዎች ያደላ ነበር።

በአፍሪካ ከታሪክ ማስረጃዎች መረዳት እንደሚቻለው በቀኝ ገዢዎች የተስፋፋው የባቡር መሠረተ-ልማትና
የትራንስፖርት አገልግሎት የቀኝ ገዢዎችን ፍላጎት ለማርካት እንጂ የአፍሪካ አገራትንና ቀጠናዎችን ዘላቂ
የኢኮኖሚ እድገትና የሎጀስቲክ ትስስርን ለማረጋገጥ አልነበረም። በአፍሪካ የነበረው የባቡር መሰረተ ልማት
ትኩረት አካባቢያዊ እንጂ ቀጠናዊ አልነበረም።

በአፍሪካ ሃገራት በባቡር ሀገራዊና አህጉራዊ ትስስርን የሚፈጥሩት የቴክኒካል ስታንዳርድስ /Technical
standardization/፣ መጣጣም /harmonization/ እና ድንበር ተሻጋሪነት /effective border-crossings/
መስፈርቶች አልነበራቸው ። በመሆኑም የንግድ ልውውጥ እና ሰፊ የድንበር ገበያ ሽፋን ዝቅተኛነት ጋር
ተዳምሮ የአፍሪካ አገራትን ከማቀራረብ ይልቅ የሚያራርቅ ነበር። ለዚህም የባቡር መስመሮቹ የተለያየ
ጌጅ /gauge/ ነበራቸው። በአጠቃላይ የባቡር ዘርፍ ለአፍሪካ አገራት ቀጠናዊ ትስስርና ልማት
የሚጠበቅበትን አገልግሎት አላበረከተም።

2.1.4 የባቡር ዘርፍ በኢትዮጵያ

ኢትዮጵያ በባቡር ትራንስፖርት ዘርፍ ከመቶ ዓመት በላይ ታሪክ ያላት አገር ናት። በኢትዮጵያ የባቡሩ
አገልግሎት ከመጀመሩ በፊት በ18ኛው ክፍለ ዘመን በጅቡቲ ወደብ በኩል ለውጭ ገበያ በየዓመቱ 12 ሺህ
ቶን የሚሆን ሸቀጥ ታቀርብ እንደነበርና ሸቀጡን ወደ ወደብ ለማድረስም 50 ሺህ ግመሎችን ትጠቀም
እንደነበርና ጉዞውም ከሰባት ወራት በላይ ይፈጅ እንደነበር መዛግብት ያሳያሉ። ይህ ከመቶ ዓመት በላይ
የቆየ ታሪካዊ ባቡር በአሁኑ ወቅት በአዲስ ቴክኖሎጂ ቢተካም ነባሩ በቱሪስት መስሕብነት ከፍተኛ
ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ይኖራል።

ኢትዮጵያ እስከ 19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ማብቂያ ድረስ የባህር እና የየብሱን ትራንስፖርት የሚሳልጥ
ምቹ አማራጭ ያልነበራት በመሆኑ ከሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ጋር የመገናኘት እንዲሁም ለሀገሪቱ ዕድገት
እንቅፋት መሆኑን የተረዱት ንጉሰ ነገስት ዳግማዊ ምኒልክ ከሲውዘርላንድ መሀንዲስ ጋር የባቡር መስመር
በሶስት ሴክሽን ከጅቡቲ ወደ ሐረር፣ ከሐረር ወደ እንጦጦ እንዲሁም ከእንጦጦ በከፋ በኩል ወደ ነጭ
አባይ ድረስ ለማስገንባት የካቲት 11 ቀን 1893 ውል አሰሩ።

በ1893 በተገባው ውል መሰረት የባቡር መስመር ለማስገንባት የተለያዩ አስቸጋሪ ሁኔታዎች


በመፈጠራቸውና የባቡር መስመር ዝርጋታውን እውን ለማድረግ ባለመቻላቸው እ.ኤ.አ በጃንዋሪ 30 ቀን

7
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
1908 ከአዲስ አበባ - ጅቡቲ የባቡር መስመር በመገንባት አገልግሎት ለመስጠት የፍራንኮ - ኢትዮጵያ
የባቡር ኩባንያ በሚል አዲስ ኩባንያ ተቋቋመ።

እ.ኤ.አ በ1909 አዲሱ ኩባንያ የባቡር ግንባታውን በይፋ የጀመረ ሲሆን ከሰባት ዓመት ከስድስት ወር
የግንባታ ምዕራፍ በኋላ አዲስ አበባ እ.ኤ.አ በጃንዋሪ 17 ቀን 1917 ደርሷል በዚህም በተጠናቀቀው 784
ኪ.ሜ የባቡር መስመር ላይ የአገልግሎት ስራውን መስጠት ችሏል።

በ1936 እ.ኤ.አ ጣሊያኖች ኢትዮጵያን በድጋሚ በወረሩበት ወቅት 1000 ኪሜ የሚሸፍን አዲስ አበባን
ከምፅዋ እና ከሞቋዲሾ የሚያገናኝ አዲስ የባቡር መስመር ፕሮጀክቶች አቅዶ የነበረ ቢሆንም ግንባታውን
ማከናወን ሳይችል ቀርቷል ።

ፍራንኮ ኢትዮጵያን የባቡር ኩባንያ ፈረንሳይና ኢትዮጵያ በኖቬምበር 12 ቀን 1959 እ.ኤ.አ በገቡት ውል
መሰረት ኢትዮጵያ የጅቡቲን የባህር በር የሁሉንም በባቡር የሚጓጓዙ ነገሮች እስከ ዲሴምበር 31 ቀን
2016 እ.ኤ.አ ድረስ እንድታጓጉዝ እና ወደቡን እንድትጠቀም የኮንትራት ውል የተዋዋሉ ቢሆንም በጁን
19 ቀን 1977 እ.ኤ.አ የፈረንሳይ ቅኝ ግዛት የነበሩት አፋር እና ኢሳን ነፃ በማውጣት የራሳቸው ሪፐብሊክ
ኦፍ ጅቡቲ በማለት አገር መሰረቱ (Crozet, n.d.) ። ከዚህ በኋላ በድርጅቱ የጋራ ባለቤትነት የነበራት
ፈረንሳይ በጅቡቲ በመተካቷ በኢትዮጵያና ጅቡቲ መካከል ዳግመኛ በየካቲት 12/1978 ዓ.ም ለ50 ዓመታት
እንዲቆይ በተፈረመ ስምምነት (Treaty) የሚተዳደርና ከሁለቱ መንግሥታት በተውጣጣ የጋራ አስተዳደር
ምክር ቤት (Board) የሚመራ የባቡር ድርጅት መሰረቱ። ይህ ድርጅትና የሚያስተዳድረው መስመር
በወቅቱ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታን የሚሰጥ የገቢና ወጪ ጭነት እንዲሁም የመንገደኛ ትራንስፖርት
ዋነኛ አማራጭ የነበረ እና ለአዳዲስ የምስራቅ ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማዕከላት እና ከተሞች መፈጠር
ምክንያት ነበር።

ሆኖም ግን በቴክኖሎጂ ማርጀት እንዲሁም በተለያዩ ውስጣዊና ውጫዊ ችግሮች ምክንያት ሴክተሩን
በዘላቂነት ለማስቀጠል የነበረውን ዕድል ሳይጠቀምበት ቀርቶ በጅቡቲ በኩል ያለው አገልግሎት ሙሉ
በሙሉ የተቋረጠ ሲሆን በኢትዮጵያ በኩልም አለ የማይባልበት ደረጃ ላይ ይገኛል። በዘርፉ የነበረውን
ከፍተኛ የባቡር ኦፕሬሽንና ጥገና እውቀት ወደ አዲሱ የባቡር ኮርፖሬሽን ለማስተላለፍ አለመቻል ሀገሪቱ
ለማኔጅመንትና ኦፕሬተሮች ከፍተኛ ክፍያ እንድትከፍል ያስገደደና ከዚህ በፊት በኢትዮጵያ ምንም አይነት
የባቡር ቴክኖሎጂ ያልነበረ ያህል በውጭ ሀገር ሰራተኞች ላይ ጥገኛ አድርጎት ቆይቷል።

ከላይ የታየው የቀደመውን የባቡር ዘርፍ እውቀትና ልምድ ወደ አዲሱ የባቡር ኮርፖሬሽን የማስተላለፍ
ችግርና አያይዞ ማሻገር አለመቻል በዋነኝነት የተፈጠረው የኢትዮ ጅቡቲ የምድር ባቡር ኩባንያ
አስተዳዳሪነት በረጅም ጊዜ ውል መስመሩን ሲያስተዳድር ለቆየው የጋራ ኩባንያ በመሰጠቱና ይህም ድርጅት
በኢትዮጵያ መንግስት ቀጥተኛ የተጠሪነት አደረጃጅት ውስጥ ያልነበረ በመሆኑ ከፍተኛ ማነቆ ሆኖ
ቆይቷል።

8
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን በ 2000 ዓ/ም ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ በተለያዩ አጋጣሚዎች
ከቀድሞው የኢትዮ ጅቡቲ የምድር ባቡር ኩባንያ ጋር አብሮ መስራትና ከቀድሞው ድርጅት ዘርፈ ብዙ
ልምዶች መቅሰም የሚችልብት እድሎችን ሳይጠቀምበት አልፈዋል። ሌላው ዋነኛ በአሁን ሰዓት ያለው
የባቡር ዘርፍ ሊማርበት የሚችለው መስክ የዘርፉን አደረጃጀት በረጅም ጊዜ አስተሳሰብ በአሁን ሰዓት
እየሰሩ ያሉትንም ሆነ ለወደፊቱ ሊመጡ የሚችሉ የሴክተሩ ተዋናዮች ምቹ መደላድል የሚፈጥር አድርጎ
መቅረጽ ነው። ምንም እንኳ ከመቶ ዓመታት በላይ ዕድሜ ያስቆጠረ የባቡር ታሪክ ቢኖረንም ዘመናዊው
የባቡር ዘርፍ ከ2000 ዓ.ም ጀምሮ ከምድር ባቡር ኮርፖሬሽን መመስረት ጋር አብሮ እንደ አዲስ ለሃገሪቱ
ተዋውቋል።

በአሁኑ ወቅት 656 ኪሜ የአዲስ አበባ - ጅቡቲ የባቡር መስመር (በጅቢቲ ያለውን መጠን ሳይጨምር)
እንዲሁም 34 ኪሜ የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር አገልግሎት በመስጠት ላይ ሲሆኑ፤ በግንባታ ላይ ያሉ
የ390 ኪሜ የአዋሽ - ሃራ ገበያ እና የ220 ኪሜ የመቀሌ - ሃራ ገበያ መስመሮችም ከተጠናቀቁ የሃገር
አቀፍ ኔትወርኩ መጠን 1266 ኪሜ የሚደርስ ይሆናል።

የባቡር ትራንስፖርት ዘርፍ አስፈላጊነትና ከመንገድ ትራንስፖርት ጋር ያለው


ንጽጽር

የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ የ 10 ዓመታት ዕቅድ (2020/21 _ 2029/30) ለማዘጋጀት በተሰራው
የመነሻ ጥናት ላይ እንደተገለጸው ሀገራችን ኢትዮጵያ ካሳየችው የ10 ዓመት ፈጣንና ከፍተኛ ዕድገት ጋር
ተያያዥ የሆኑና የእድገቱን ቀጣይነትና አካታችነት የሚፈታተኑ ከፍተኛ ተግዳሮቶችም ተስተውለዋል፡፡
ለተስተዋሉት መልከ ብዙ ችግሮች የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያው 3 ዋና ዋና መንገዶችን ለይቷል ፡

1. የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ፣

2. የሴክተር ማሻሻያ እና

3. የአደረጃጀት ማሻሻያዎች

በአደረጃጃት ማሻሻያው ሂደት ውስጥ የተቀናጀ የትራንስፖርትና የሎጂስቲክስ አገልግሎት በመስጠት


የትራንዚት ጊዜና የክፍያ ወጪን በመቀነስ የግብርብናና የአምራች ኢንደስትሪዎች ምርቶችን ተወዳዳሪነት
ማሳደግ ላይ ያተኮረ እንዲሆን ማድረግን ዋነኛ የትኩረት መስክ አድርጎ አስቀምጧል፡፡ በዚህም ሀገራችን
በአሁን ሰዓት ካለችበት በአለም 126ኛ የሎጂስቲክስ ውጤታማነት ኢንዴክስ (LPI) ወደ 40ኛ ደረጃ
ለማድረስ የባቡር መሰረተ ልማት ሽፋንን ወደ 4199 ኪሜ ለማሳደግ ታቅዷል፡፡

ሀገራችን ከግብርና ወደአምራች ኢንዱስትሪ ለምታደርገው ኢኮኖሚያዊ ሽግግር የሎጂስቲክስ ዘርፉ አብሮ
ማደግ ጊዜ የማይሰጠው ስትራቴጂያዊ ጉዳይ ሆኖ የተለየ በመሆኑም የገፍ ጭነትን በዝቅተኛ ዋጋ ፣

9
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
በአነስተኛ ከባቢያዊ ተጽዕኖ ፣ በፍጥነት እና እሴትን በሚጨምር መልኩ የሚያጓጉዝ የትራንስፖርት
አማራጭ የሆነው የባቡር ዘርፍ ዋነኛ የሎጂስቲክስ ዘርፉ ተዋናይ ሆኖ ተለይቷል፡፡

በአለማችን በከፍተኛ የእድገት ደረጃ የሚገኙትም ሆነ እያደጉ የሚገኙ ሀገራት ወደአምራችነት ሲሸጋገሩ
በከፍተኛ ደረጃ ጥቅም ላይ የዋለና ውጤታማ የሆነ የጭነት ትራንስፖርት ዘርፋቸው ባቡር እንደነበረ
ከተለያዩ መዛግብት መረዳት እንችላለን፡፡ በተለይም እንደ ሀገራችን ኢትዮጵያ የባህር በር የሌላቸውና
ከ90% በላይ ገቢና ውጪ ምርት እንቅስቃሴ በአንድ አቅጣጫ ብቻ (በአዲስ_ጅቡቲ) ኮሪደር በሆነበት ሀገር
የባቡርን ያህል ተመራጭ የጭነት ትራንስፖርት ዘርፍ ሊኖር አይችልም፡፡

የመንገድ ዘርፍ ለአጫጭር ርቀቶች እና ዝቅተኛና መካከለኛ የጭነት መጠኖችን ለማጓጓዝ ተመራጭ ዘርፍ
ቢሆንም የኢንዱስትሪ ፣ ትላልቅ የእርሻና የማዕድን ዘርፍ ስራዎችን መስፋፋት ለመደገፍ የባቡር ዘርፉ
አይነተኛ ተመራጭ ሆኖ ይቀርባል ምክንያቱም ባቡር በአንድ ጊዜ ከፍተኛ መጠን ያለው ጭነትን በአንድ
ጊዜ በዝቅተኛ ዋጋ በረጅም ርቀት ውስጥ ከማጓጓዙ ባሻገር የኢንደስትሪ ዞኖችና ደረቅ ወድቦችን
የሎጂስቲክስ ስራዎች አውቶሜት ለማደረግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የማድረግ አቅም ያለው በመሆኑ ነው፡፡

የባቡርና የመንገድ ትራንስፖርት ንዑስ ዘርፎች ተመጋጋቢ ተፈጥሮ ያላቸው የትራንስፖርት ንዑስ ዘርፎች
ናቸው፡፡ አንዱ ንዑስ ዘርፍ የሌላኛውን ደካማ ጎን የመሸፈንና አጠቃላይ ሀገራዊ የሎጂስቲክስ አቅምን
የማሳለጥ ባህሪ ያላቸው የትራንስፖርት አማራጮች ናቸው፡፡ ለምሳሌ፡ በባቡር ከወደብ ላይ የተነሳ ገፍ
ጭነት ወደ አማካይ የጭነት ማራገፍያ መናኽሪያ ከደረሰ በኋላ በከባድ ጭነት መኪኖች ደግሞ በተለያዩ
አቅጣጫዎች ወደሚገኙ ማከፋፈያ መጋዘኖች የሚደርሱ ይሆናል በመጨረሻም በቀላል የጭነት ማጓጓዣ
ተሽከርካሪዎች በመጠቀም ለተጠቃሚዎቹ

ከዚህ በታች በቀረበው ሰንጠረዥ በባቡር ዘርፍና በመንገድ ዘርፍ መካከል ያሉ ልዩነቶች በንጽጽር ቀርበዋል

10
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
ሁለቱ ዋና ዋና የየብስ ማጓጓዣ አማራጮች ንጽጽር
መለኪያ የባቡር ትራንስፖርት የመንገድ ትራንስፖርት

የገፍ ጭነት የማጓጓዝ አቀም (የባቡር የጭነት ማጓጓዝ አቅም በ 1


ነጠላ የባቡር መስመርና በባለ 4 መስመር መደበኛ ሀይዊይ መካከል
በተደረገ የጭነት ማጓጓዝ ውጤታማነት ጥናት ባቡር 335,000 ቶን
በኪሜ/በሜ2/በቀን የሚያጓጉዝ ሲሆን መንገድ ደግሞ
150,000ቶን በኪሜ/በሜ2/በቀን የማጓጓዝ አቅም አለው በዚህም ዝቅተኛ የመሰረተ ልማት ግንባታ ወጪ
ባቡር ከእጥፍ በላይ የማጓጓዝ አቅም እንዳለው ያሳያል) እንደ
ኢትዮጵያ ላሉ ወደብ የሌላቸው ሀገሮች በጣም ተመራጭ የየብስ
ትራንስፖርት አማራጭ መሆኑ (በአንድ ጉዞ ከፍተኛ የጭነት መጠን
በማንቀሳቀስ የእቃዎችን የወደብ ላይ ቆይታ በማሳጠር ከተጨማሪ
የዲመሬጅና ሌሎች ክፍያዎች የሚታደግ አማራጭ በመሆኑ)
ጠንካራ
ዝቅተኛ የካርበን ልቀት /በታዳሽ ኃይል የሚንቀሳቀስ መሆኑ
ጎኖች
(ለምሳሌ ፡ በተመሳሳይ ርቀት ውስጥ እና ተመሳሳይ ጭነት ምጣኔ
በጀርመን የመንገድ የጭነት ማጓጓዣ ስርዓት የካርበን ልቀት 5 ያልተገደበ እንቅስቃሴ
እጥፍ ከ ባቡር ሴክተሩ ብልጫ ያሳያል)
ዝቅተኛና ርካሽ የሃይል ፍላጎት ለአጭር ርቀት የጭነት ትራንስፖርት ርካሽ አማራጭ መሆኑ
ዝቅተኛ የትራፊክ ተጽዕኖ
ለረጅም ርቀት ርካሽ የትራንስፖርት አማራጭ
ዝቅተኛ የሰው ሰራሽና ተፈጥሮአዊ አደጋ ተጋላጭነት
ከመርከቦች የዕቃ ማንቀሳቀሻ ክሬን ስር በቀጥታ በመግባት ጭነትን
የሚወስድ በመሆኑ የተጨማሪ (Double Handling) ክፍያዎችን
የማስቀረት አቅም ያለው መሆኑ
ከፍተኛ የመሰረተ ልማት ካፒታል ወጪ ከፍተኛ የካርበን ልቀት

ደካማ የተገደበ የእንቅስቃሴ ወሰን


ለረጅም ርቀት የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት ከባቡር አንጻር ውድ
ጎኖች መሆኑ
ለአጭር ርቀት የጭነት አገልግሎት ተመራጭ የትራንስፖርት
ዝቅተኛ የገፍ ጭነት የማጓጓዝ አቅም
አማራጭ አለመሆን
ከፍተኛ የአደጋ ተጋላጭነት መጠን

የባቡር ዘርፍ ተዋናዮችና አገነባብ

2.3.1 የባቡር ዘርፍ ባለቤቶች /key owners /አገነባብ

ከላይ እንዳየነው የምድር ባቡር አጀማመር እና የዕድገት ሂደት በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች የተለያየ
ምስል ያለው ሲሆን፤ እንደየታሪካዊ ዳራቸው በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሴክተሩ አካላት ሚና እና
ባለቤትነት ሁኔታ የተለያየ ቅርጽ ይዞ መጥቷል።

በአውሮፓና በእስያ በጥቅሉ የምድር ባቡር መሠረተ-ልማትም ሆነ አገልግሎት በመንግስት ባለቤትነት ስር


ያለ ነው። በተቃራኒው በአሜሪካ የባቡር መሠረተልማቶች በአብዛኛው በግል ባለሃብት ባለቤትነት የተያዙ

11
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
ናቸው። በአውሮፓም ቢሆን በ 19ኛው እና በ 20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ የባቡር መሠረተ-ልማት
ግንባታ በአብላጫ በግሉ ዘርፍ ሲካሄድ ቆይቷል። በኋላም መንግስት በባቡር ዘርፉ ላይ የሚያደርገውን
ቁጥጥር እያጠናከረ መጥቷል።

የመንገድ መሠረተ ልማታቸውን እስካአሁን እምብዛም ያላሳደጉ ሃገራት ጭምር ለምጣኔ ሃብታቸው
ዕድገት የባቡር መሠረተ-ልማት ወሳኝ ጠቀሜታ እንዳለው መገንዘብ ችለዋል። የባቡር መሠረተልማት
በአብዛኛው በግል ባለሃብቶች የተገነባና አገልግሎትም ይሰጥ የነበረ በመሆኑ በሂደት መንግስታት የህዝብን
ፍላጎት የሚያስጠብቅ እና በአግባቡ አገልግሎት የሚሰጥ የባቡር መሠረተ-ልማትን መገንባትና ለአገልግሎት
ዝግጁ ማድረግ መንግስታዊ ግዴታቸው አድርገው መውሰድ ጀምረዋል። በዚህም መነሻ የአውሮፓ ሃገራት
በዘርፉ ላይ ለትርፍ የሚደረግ እንቅስቃሴንና የንግድ ውድድርን መገደብ ጀመሩ። ይህም የባቡር ሴክተሩ
የሚያስተናግደው የተጓዥ እና የጭነት መጠን እንዲቀንስ እና የፋይናንስ አቋሙም በጎላ መልኩ
እንዲፍረከረክ አድርጎታል። በውጤቱም የምድር ባቡር ላይ የተሠማሩ የግል ባለሃብቶች በባቡር መሠረተ-
ልማትና በባቡር ተሸከርካሪዎች ላይ መዋዕለ ንዋያቸውን የማውጣት ፍላጎታቸው ቀነሰ። በዚህም የተነሳ
እ.ኤ.አ በ1950ዎቹ በአውሮፓ የሚገኙ ሁሉም የባቡር መሰረተ ልማቶች ወደ መንግስት ባለቤትነት
የተቀየሩ ሲሆን በአሁን ሰዓትም አብዛኛዎቹ የባቡር መሰረተ ልማቶች በመንግስት ባለቤትነት ስር ይገኛሉ።

ከዚህ ጋር በተያያዘ በአሜሪካ ያለው እውነታ የተለየ ነው። እ.ኤ.አ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያዎቹ
ላይ የአሜሪካን ባቡር ኩባንያዎች በነበረው የስቶክ ገበያ ውስጥ ጭምር ተጠቃሽ ነበሩ።እ.ኤ.አ በ1970
ከተሞችን የሚያገናኙ የባቡር አገልግሎቶች (የመንገደኛም የጭነትም አገልግሎት) በሙሉ በግሉ ባለቤትነት
የተያዙ ሲሆን የቁጥጥር ስራውን መንግስት ያከናውን ነበር። ሆኖም የባቡር መንገደኞች ቁጥር እየቀነሰ
ከመምጣቱ የተነሳ ገቢው የባቡር መሠረተ-ልማቱን ለመጠገን የሚያስፈልገውን ኢንቨስትመንት እንኳ
የማይሸፍንበት ደረጃ ላይ ሊደርስ ችሏል። ይህም የአሜሪካው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የባቡር
ኩባንያዎች ሃብታቸውን ከማስተዳደር አንጻርና ለሚሰጧቸው አገልግሎቶች ታሪፍ ከማውጣት አንፃር
የተሻለና የተመጣጠነ ነፃነት የሚሰጣቸውን የቁጥጥር ስርዓት እንዲያጸድቅ አድርጎታል። በስተመጨረሻም
ምንም ትርፍ የሌለው መንገደኞችን የማጓጓዝ ስራው ጭነትን ከማጓጓዝ ስራው ተለይቶ በመንግስት
ባለቤትነት ለተቋቋመው አም-ትራክ (Amtrack) በኩል እንዲከናወን ተደርጓል።

የታላቋ ሶቭየት ህብረት፣ የዩጎስላቪያ እና የቼኮስሎቫኪያ መበታተን ከሃያ ለበለጡ አዳዲስ ብሄራዊ የባቡር
ኩባንያዎች መመስረት ምክንያት ሆኗል። ከነዚህም መካከል ብሔራዊው የሩስያ ፌደሬሽን፣ የካዛኪስታን
እና የዩክሬይን የባቡር ኩባንያዎች በአለም ላይ ግዙፍ ከሆኑት ተርታ የሚመደቡ ናቸው።

12
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
2.3.2 የባቡር ዘርፍ ተዋናዮች /key Players)

የዓለማችን የባቡር ሴክተር ታሪክ እንደሚያሳየው የምድር ባቡር ዘርፍ ባለቤትነት እና ሚና በተለያዩ
ወቅቶች እየተለዋወጠ የመጣ ቢሆንም፤ በየትኛውም የዓለም ክፍል የሚገኝ የባቡር ሴክተር ውስጥ የሚገኙ
አበይት አካላት ሚና በሂደት እየነጠረ ወጥቶ በተለያዩ የሴክተሩ ተዋናዮች የሚተገበር ሆኗል።

የባቡር ሴክተር ተዋናዮች አሰላለፍ በሁለት ክንፎች የተለየ ሲሆን ይህም የሴክተሩ የቁጥጥር ክንፍ እና
የሴክተሩ ፈጻሚ (ቢዝነስ) ክንፍ ናቸው። የሴክተሩ የቁጥጥር ክንፍ የተለያየ ሚና የሚወስዱ አንድ ወይም
ከዚያ በላይ ተቆጣጣሪ አካላትን የሚያቅፍ ሲሆን፤ ገለልተኛ አካል ሆኖ ፖሊሲ እና ደረጃዎች በማውጣትና
በማስፈጸም፣ ቁጥጥር በማድረግ እና ፈቃድ በመስጠት የባቡር ሴክተሩን ደኅንነት መጠበቅ እና በዘርፉ
የሕዝብና የመንግስት ጥቅም መከበሩን ያረጋግጣል።

የሴክተሩ ፈጻሚ (ቢዝነስ) ክንፍ ደግሞ በዋናው የባቡር ሴክተር ሥራ በመሳተፍ ሴክተሩ በገበያ ተወዳድሮ
በዘላቂነት እንዲቀጥል በማድረግ ለሃገራዊ ኢኮኖሚ ዕድገት አስተዋጽዖ የሚያበረክት ክንፍ ነው። ይህ
ክንፍ ሦስት አበይት ተዋናዮችን ያሳትፋል። እነዚህም የባቡር መሠረተ-ልማት አስተዳዳሪ (Infrastructure
Manager) ፣ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ (Railway Undertaking/Operator) እና ሌሎች

ተዋናዮች (ኮንትራክተር፣ ኮንሰልታንት፣ አምራች፣ እና አቅም ገንቢ) ናቸው።

• የመሠረተ-ልማት አስተዳዳሪ (Infrastructure Manager) ፡- የባቡር መሠረተ ልማቱን የሚገነባ፣


የሚጠግንና የሚያስተዳድር አካል ሲሆን የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች መሠረተ ልማቱን
እንዲጠቀሙ ድርሻ የሚሰጥና በዚህም ገቢ የሚያመነጭ ነው፤
• የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ (Railway Undertaking/Operator) ፡- በተገነባው
መሠረተ-ልማት ላይ ባቡሮችን በማንቀሳቀስ የጭነት እና/ወይም የመንገደኛ ባቡር ትራንስፖርት

13
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
አገልግሎት የሚሰጥ አካል ሲሆን ከአገልግሎቱም ገቢ የሚሰበሰብ እና ለሚጠቀምባቸው ባቡሮች
ጥገናም ኃላፊነት ያለበት አካል ነው።
• ሌሎች አበይት ተዋናዮች፡- እነዚህም

- ተቋራጭ፡ የባቡር መስመር ጣቢያና ሌሎች ግንባታዎችን የሚያከናውኑ፣


- አማካሪ፡ የማኔጅመንትና የምህንድስና ምክር አገልግሎት እና የግንባታ ቁጥጥር የሚተገብሩ፣
- አምራች፡ ለዘርፉ ባቡሮችን፣ መሣሪያዎችንና የግንባታ ማቴሪያሎችን የሚያቀርቡ፣ እና
- አቅም ገንቢ፡ የሴክተሩን የሰው ኃይል እና የቴክኖሎጂ አቅም በትምህርትና ስልጠና እንዲሁም
በምርምርና ስርጸት የሚወጡ አካላት ሲሆኑ ለባቡር ሴክተሩ ምሉዕ ዕድገት ከፍተኛ ድርሻ
የሚወጡ አካላት በመሆናቸው ከአበይት ተዋናዮች የሚመደቡ ናቸው።

የባቡር ዘርፍ አስተዳደራዊ የለውጥ (SECTORAL REFORM) ሂደትና ወቅታዊ ሁኔታ

2.4.1 የዘርፉ አስተዳደራዊ ጽንሰ ሃሳቦች /መሠረታዊ ጽንሰ ሃሳቦች/

ከታሪኩ አንጻር የባቡር ሴክተር ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማሕበራዊ ፋይዳ ያለው በመሆኑ በመንግስት
የሚሰጠውን ኃላፊነት የሚያከናውን እና ወጪውም በመንግስት በጀት የሚደገፍ ነበር። ሆኖም ዓለማችን
ካሳለፈቻቸው የፖለቲካል ኢኮኖሚ ለውጦች እና በሃገራት ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የተነሳ፣ በተለይ ከነፃ-ገበያ
ኢኮኖሚ መስፋፋት ጋር ተያይዞ የባቡር ዘርፉ ከሌሎች የትራንስፖርት አማራጮች (Transport Modes)
ጋር ተወዳድሮ ቀጣይነቱን በራሱ የማረጋገጥ ኃላፊነትን እንዲሸከም ሆኗል።

ዓለም ዓቀፍ የባቡር ዘርፍ ልምድ እንደሚያሳየው በሃገራት እና በአህጉራት ደረጃ የባቡር ዘርፉን አፈፃፀም
ለማሻሻል፣ ተወዳዳሪነትን እና ትርፋማነት ለማረጋገጥ በሴክተሩ ስትራቴጂያዊ ለውጦች ሲከናወኑ
ቆይተዋል።

በዚህም መሠረት በብዙ የዓለማችን ሃገራት በባቡር ዘርፉ የንግድ-ተቋም ባህርይ መላበስን (Business
Organization Concept) ፣ በገበያ ተወዳዳሪ መሆንን (Market Competition Concept) እና በዋና
ተግባራቱ አንጻር ኢ-ማዕከላዊ በሆነ መንገድ መደራጀትን (Separability Concept) መሠረት ያደረጉ
የለውጥ እንቅስቃሴዎች ተከናውነዋል። እነዚህ ለውጦችም የየሃገራቱን የባቡር ዘርፍ ደንበኛ-ተኮር እና
አትራፊ እንዲሆን የሚያደርጉ መሆናቸው በተግባር ተረጋግጧል። በአብዛኛው ለውጦቹ የተመሠረቱት
በሦስት መሠረታዊ ጽንሰ-ሃሳቦች መስተጋብር ላይ ነው።

14
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
ምስል 2 ፡ የዓለም አቀፍ ባቡር ዘርፉ መዋቅራዊ ለውጥ
መሠረታውያን
ከላይ የተጠቀሱት ጽንሰ-ሃሳቦች ለባቡር ዘርፉ መዋቅራዊ ለውጥ ወሳኝ የመሠረት ድንጋዮች (Main-
building blocks) መሆናቸውን ዓለም-አቀፋዊ ልምድ የሚያሳየን ሲሆን፤ በእነዚህ ሦስት የባቡር ዘርፍ
ለውጥ ወሳኝ የመሠረት ድንጋዮች (Main-building blocks) መሠረት የተለያዩ የመዋቅራዊ ለውጥ
የፖሊሲ አማራጮች በትግበራ ጥቅም ላይ ሲውሉ ይስተዋላል።

ሀ. የንግድ ተቋም ጽንሰሃሳብ (Business Organization Concept)

ይህ ጽንሰ ሃሳብ የባቡር ዘርፉ አበይት ተግባራት (መሠረተ-ልማት ማስተዳደርና አገልግሎት መስጠት)

በንግድ ማዕቀፍ የሚደራጁበትን የፖሊሲ አማራጮች ያካተተ የለውጥ ጎዳና ሲሆን፤ በዋነኝነት ሁለት
አማራጮችን ይዟል። እነዚህም፡-

• መንግስታዊ የልማት ድርጅት ፡- ነባራዊውን መንግስታዊ የባቡር ዘርፍ መዋቅር (departmental


structure) በንግድ ሕግ የሚተዳደር የመንግስት ልማት ድርጅት አድርጎ ማደራጀት የመጀመሪያው
የፖሊሲ አማራጭ ነው። ይህም ከአደረጃጀት ለውጥ በዘለለ በመንግስታዊ ሲቪል ሰርቪስ መዋቅር
ይመራ የነበረውን ተቋም በገለልተኛ እና በባለሙያዎች በተዋቀረ የዳይሬክተሮች ቦርድ እንዲመራ
ማድረግን፣ በሙያዊ ውድድር በተመሠረተ (Merit-based) ምርጫ በቦርዱ የተሰየሙ አባላትን የያዘ
ማኔጅመንት ማዋቀር፣ በረጅም እና በአጭር ጊዜ የንግድ ዕቅድ ዒላማዎች አፈጻጸም ላይ የተመሠረተ
የማኔጅመነት ተጠያቂነት ስርዓት ማስፈን፣ በገበያው ፍላጎትና በአበይት ተግባራት ላይ ያተኮረ
የአስተዳደር መዋቅር መዘርጋት፣ ከፍተኛ የዋጋ ትመና ነጻነት መስጠት፣ ዓለም አቀፋዊ ስታንዳርድ
15
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
የተከተለ የንግድ ሂሳብ መዝገብ አያያዝና የፋይናንስ ቁጥጥር ስርዓት መጠቀም፣ በመንግስት ለሚጠየቁ
ሕዝባዊ የባቡር አገልግሎቶች ግዴታዎች (Public Service Obligations) ግልጽ የሆነ የኮንትራት
ውል በመንግስትና በልማት ድርጅቱ መካከል እንዲኖር ማድረግ…እና የመሳሳሉት ማሻሻያዎችን
ያካትታል።

• የግል ድርጅት ፡- ይህ ደግሞ ፍጹማዊ የንግድ ባህርይን የተላበሰ የባቡር ዘርፍን መፍጠርን ያለመና
የባቡር ዘርፉ አበይት ተግባራት ሙሉ በሙሉ በግል ባለሃብቶች አንዲከናወን የሚያደርግ የፖሊሲ
አማራጭ ነው።

በዓለም ደረጃ በባቡር ከሚጓጓዘው 63 በመቶው ጭነት እና 90 በመቶው መንገደኛ የሚንቀሳቀሰው


በመንግስታዊ የልማት ድርጅቶች ነው። ከዚህ ውስጥ የዓለማችንን ከፍተኛ የባቡር መስመር ድርሻን
የያዙት የቻይና፣ ሕንድና ሩስያ መንግስታዊ የልማት ተቋማት ይገኙበታል። በሌላ መልኩ በዓለም ላይ
ከ500 በላይ የግል የባቡር ጭነት ትራንስፖርት ሰጪ ተቋማት የሚገኙ ሲሆን አብዛኞቹ በሰሜን አሜሪካ፣
ደቡበ አሜሪካ፣ ከሰሃራ-በታች የአፍሪካ ክፍል፣ አውስትራሊያ እና በአውሮፓም አገልግሎት በመስጠት
የሚገኙ ናቸወ።

በጃፓን እና በብሪታንያ የግል ሃገር አቀፍ የመንገደኞች ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች
በብዛት ያሉ ሲሆን በአውሮፓ በተለይ ጀርመን፣ ስዊድንና ብሪታንያ የከተማ-አቀፍ መንገደኛ ባቡር
ትራንስፖርትን በረጅም ጊዜ ውል (Concesssion) ተረክበው አገልግሎት የሚሰጡ ኩባንያዎች የተለመዱ
ናቸው። በላቲን አሜሪካ እና በሰሃራ-በታች አፍሪካ ሃገራት በረጅም ጊዜ ውል (Concesssion) የጭነት
አገልግሎት የሚሰጡ አንዳንድ ኩባንያዎች የመንገደኛ ትንስፖርት አገልግሎትንም በተመሳሳይ ስምምነት
ዓይነት ያከናውናሉ።

ለ. የተወዳዳሪነት ጽንሰሃሳብ (Market Competetion Concept)

ነባሩን/ጥንታዊውን የባቡር ሴክተር ደንበኛ-ተኮር እና በተወዳዳሪነት ላይ የተመሠረተ የንግድ አገልግሎት


የሚሰጥ ዘመናዊ የባቡር ሴክተር አድርጎ ማዋቀርን ዓላማ ያደረገ የለውጥ ጽንሰ ሃሳብ ነው። ይህም ሁለት
የፖሊሲ አማራጮች አሉት፡

• ለሴክተሩ የገበያ ድርሻ የሚደረግ ተወዳዳሪነት (Competetion for the Market) ፡- በዓለም ዙሪያ
ነባሩ የባቡር ሴክተር መዋቅር መንግስታዊው የባቡር አካል ከመንግስት በሚመደብለት በጀት እና
የገበያ ድርሻ የተመሠረተ በመሆኑ አትራፊነት ዋነኛ አጀንዳው ሳይሆን ቆይቷል። ከገበያ መር ኢኮኖሚ
መስፋፋት ጋር ተያይዞ ባለንበት ዘመን የባቡር ሴክተሩ ከሌሎች የትራንስፖርት ዘዴዎች የበለጠ
ተመራጭ የሚያደርገው አገልግሎት በማቅረብ የገበያ ድርሻውን በውድድር ማግኘት ይጠበቅበታል።

16
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
የባቡር ትራንስፖርት ዘዴ ከሌሎች ዘዴዎች በተሻለ መልኩ ገፍ ጭነትንና ብዙ መንገደኞችን በአንድ
ጊዜ፣ ያለትራፊክ መጨናነቅና ደኅንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ የማጓጓዝ ልዩ ባህርይ ያለው ሲሆን ይህንም
ለማድረግ የሚጠቀመው ኃይል አነስተኛ ነው። በመሆኑም የባቡር ሴክተሩ ይህን ልዩ ባህርይውን
እንደመወዳደሪያ ነጥብ በመያዝ በጥሩ ይዞታ የተጠበቀ መሠረተ-ልማት እና የባቡር አካላት እንዲኖረው
ማድረግ፣ ደንበኞችንና የገበያ ድርሻ ለማግኘት ተደራሽ/ተመጣጣኝ ዋጋ የሚጠይቅ አድርጎ ማዋቀር
የለውጡ ትኩረት ነው።

• በሴክተሩ ገበያ ድርሻ ውስጥ የሚደረግ የእርስበርስ ተወዳዳሪነት (Competetion in the Market) ፡-
የባቡር ሴክተሩ በቴክኖሎጂ አንዲያድግ እና የሰውን ልጅ ኑሮ የበለጠ እንዲቀልለት የሚያደርግ
አገልግሎት በአነስተኛ ዋጋ የሚሰጥ ለማድረግ በሴክተሩ ውስጥም ተወዳዳሪነት መፍጠር ያስፈልጋል።

ይህ የፖሊሲ አማራጭ በባቡር ዘርፉ ውስጥ የጭነትም ሆነ የመንገደኛ ትንስፖርት አገልግሎትን


የሚሰጡ ተቋማት በቁጥር እንዲበዙ ማድረግና የባቡር ሴክተሩ ያለውን የገበያ ድርሻ ተወዳድረው
በማግኘት ጥራት ያለው አገልግሎት አንዲሰጡ ማድረግ አንዲሁም እርስ-በርስ በሚያደርጉት ወድድር
የተነሳ ለፈጠራ እንዲነሳሱና የዘርፉን ቴክሎጂ በማሳደግ ከሌሎች የትራንሰፖርት ሴክተሮችም ደንበኛን
አንዲስቡ፣ እንዲሁም አገልግሎቱ በዝቅተኛ ዋጋ ተደራሽ አንዲሆን ማድረግ ላይ ያተኩራል። አብዛኞቹ
የዓለም ሃገራትም ይህን አማራጭ በተለያየ አግባብ በመተግበር ከፍተኛ የባቡር ዘርፍ የቴክሎጂ እና
የገበያ ዕድገት ማረጋገጥ ችለዋል።

ሐ. የኢ-ማዕካላዊነት ጽንሰሃሳብ (Separability Concept)

ይህ ጽንሰ ሃሳብ ደግሞ ከባቡር ሴክተሩ የእሴት ሰንሰለት ውስብስብነት አንጻር የእሴት ሰንሰለቱን ሙሉ
ድርሻ በአንድ መንግስታዊ ተቋም ብቻ መያዝ በገበያ መር ኢኮኖሚ ውስጥ ውጤታማ ለመሆን የማያስችል
በመሆኑ የተነሳ የተፈጠረ የለውጥ አቅጣጫ ነው። በዚህ ጽንሰ-ሃሳብ መሠረት በውስን የእሴት ሰንሰለቱ
ክፍሎች ትኩረት ሰጥተው የሚሰሩ እና በገበያ ተወዳዳሪ የመሆን አቅም ያላቸውና ራሳቸውን የቻሉ
አካላትን በማዋቀር የባቡር ዘርፉን ለማደራጀት ሁለት ዋና ዋና የፖሊሲ አማራጮች ይጠቀማል።

• ጎንዮሻዊ ንጥጥሎሽ (Horizontal Separability) ፡-ይህ አማራጭ ሁለት አይነት መልክ ሊይዝ የሚችል
ሲሆን አንደኛው የባቡር ዘርፉ አገልግሎቶች በአንድ መንግስታዊ የልማት ተቋም እንዲሰጡ ማድረጉን
ሳይለቅ ነገር ግን አበይት ሥራዎቹ በተቋሙ ባለቤትነት በሚቋቋሙ የተለያዩ ስትራቴጂክ የቢዝነስ
አኃዶች (Strategic Business Units) በተከፋፈለ አደረጃጀት እንዲሰጡ የሚያደርግ አማራጭ ነው።
ይህ ፖሊሲ የውሳኔ አሰጣጥ ኢማዕከላዊነትን (decentralized decision making) ፣ ትኩረት የሰጠ
የአመራር (focused management) ባህርይን የተላበሱ ገበያ ተኮር አካላትን በመንግስታዊው የንግድ
ተቋም ውስጥ በመፍጠር ለውጥን የሚያመጣ ነው። ሁለተኛው ደግሞ በዘርፉ ውስጥ በተዋረዳዊ

17
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
መሰናሰል የተደራጁ የመንግስትና የግሉ ዘርፍ ተዋናዮች በጎንዮሻዊ ንጥጥሎሽ በሴክተሩ ውስጥ
እንደሚሳተፉ የሚያሳይ ሲሆን የመንግስቱም ሆነ የግሉ ዘርፍ ተዋናዮች የአሰራር ፍትኃዊነትን
በሚያሰፍን የሴክተሩ ተቆጣጣሪ አካል ክትትል ይደረግባቸዋል።
• ተዋረዳዊ ንጥጥሎሽ (Vertical Separability) ፡- ይህ አማራጭ ደግሞ አንድ ወጥ የነበረውንና የእሴት
ሰንሰለቱን በሙሉ ይሸፍን የነበረውን ተቋም በእሴት ሰንሰለቱ ትኩረት መስኮች መሠረት በመነጣጠል
የባቡር ዘርፍ የተለያዩ ተግባራት በተለያዩ ተቋማት እንዲከናወኑ አድርጎ ማዋቀር ነው።

ምስል 3፡ የዓለም አቀፍ ባቡር ዘርፉ የለውጥ ሂደት ውጤቶች

2.4.2 የዘርፉ አስተዳደራዊ ሂደት እድገት ውጤቶች

ከላይ በተብራራው የባቡር ዘርፍ ለውጥ ሂደት ምክንያት አሁን ባለንበት ዘመን በተለያዩ ሃገራት የባቡር
ዘርፍ የመሠረተ-ልማት አስተዳዳሪው አካል (Infrastructure Manager) እና የአገልግሎት ሰጪው አካል
(Railway Undertaking/Operator) እንደየሃገሪቱ ሁኔታ የተለያየ አደረጃጀት፣ ባለቤትነት እና የኃላፊነት
ወሰን ያላቸው ናቸው።

አብዛኞቹን ባቡር ያላቸውን ሃገራት የሚያመሳስላቸው ደግሞ ከዋነኞቹ የባቡር ዘርፍ ተዋናዮች ውስጥ
የተቆጣጣሪው አካል (Regulatory Body) ድርሻ የመንግስት መሆኑ እና ከላይ ከተጠቀሱት ተቋማት
በአደረጃጀት ተነጥሎ ዘርፉን የሚያስተዳድር ባለስልጣን መሆኑ ነው።

የሚቀጥለው ሰንጠረዥ 1 ባለንበት ዘመን ያለውን ዋና ዋና የዓለም የባቡር ዘርፍ አደረጃጀት ባህሪያት
ከምሳሌዎች ጋር ያሳያል

18
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
ወሰን
አደረጃጀት ባለቤትነት መሠረተ ልማት አገልግሎት ተወዳዳሪነት ምሳሌዎች
ማስተዳደር መስጠት
ከሌሎች የትራንስፖርት
ቻይና፣ ህንድ፣
አኃዳዊ አይነቶች (modes) ጋር
መንግስት መንግስታዊ ድርጅት ደቡብ አሜሪካ
(Monolith) (Intermodal
(ኮንሴሽኖች)
Competetition)
መንግስታዊ
መንግስታዊ ድርጅቱ እና ከሌሎች የትራንስፖርት ሩስያ፣ አውስትራሊያ
ጎንዮሻዊ ንጥጥሎሽ ድርጅት ሌሎች የግል አይነቶች (modes) ጋር
(Horizontal መንግስት እና የግል ድርጅቶች እና እርስ በእርስ
Separation) ባለሃብት የመንግስራዊ የግል ድርጅቱ፣ (Intermodal &
ድርጅት የግል ሌሎች የግል Intramodal አሜሪካ፣ ካናዳ፣
ድርጅት ድርጅቶችና Competetition) ጃፖን
መንግስት
ከሌሎች የትራንስፖርት
አይነቶች (modes) ጋር
ተዋረዳዊ ንጥጥሎሽ መንግስታዊ ሌሎች የግል በአውሮፖ ህብረት
መንግስትና የግል እና እርስ በእርስ
(Vertical ድርጅት የግል ድርጅቶችና (EU) ውስጥ ባሉ
ባለሃብት (Intermodal &
Separation) ድርጅት መንግስት ብዙ ሃገሮች
Intramodal
Competetition)

ሰንጠረዥ 1፡ የዓለም አቀፍ ባቡር ዘርፍ ወቅታዊ የአደረጃጀት ቅርጾች

2.4.3 የባቡር ዘርፍ ወቅታዊ ሁኔታ

በዓለም አቀፉ የባቡር ሕብረት ስታቲስቲካዊ መረጃ መሠረት የዓለም ሃገራት የባቡር ዘርፍ በደረሰበት
የኔትወርክ ስፋት መጠን ሲነጻጸሩ አሜሪካ በ257 ሺህ ኪሜ የቀዳሚነቱን ስፍራ ስትይዝ ቻይና እና ሩስያ
በ127 ሺህ እና በ85 ሺህ ኪሜ ይከተላሉ። በዓለም የባቡር ኔትወርክ የመጀመሪዎቹ አስር ሃገራት ደረጃ
ከዚህ በታች ባለው ሰንጠረዥ 2 ቀርቧል።

ጠቅላላ የባቡር መሠረተ-ልማት


ተ/ቁ ሃገር
መጠን (ኪ.ሜ.)
1 አሜሪካ 257,560
2 ቻይና 150,000
3 ሩስያ 85,600
4 ሕንድ 70,225
5 ካናዳ 49,422
6 ጀርመን 40,682
7 አርጀንቲና 36,966
8 አውስትራሊያ 33,270
9 ብራዚል 30,122
10 ፈረንሳይ 29,273

ሰንጠረዥ 2፡ የዓለም ሃገራት ደረጃ በባቡር መሠረተልማት አውታር መጠን

19
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
ከዓለም አንጻር የአፍሪካ ሃገራትን የባቡር መሠረተ-ልማት ሽፋን ስንመረምር እጅግ አነስተኛ እና ከቆዳ
ስፋታቸውም ሆነ ከሕዝብ ብዛታቸው አንጻር ገና በእንጭጭ ያለ መሆኑን ከሚከተለው ሰንጠረዥ 3
መረዳት እንችላለን።

የሃገራዊ ምርት
የቆዳ ስፋት
ጠቅላላ የባቡር የህዝብ ብዛት / መጠን በሰው
(ሜ.ካሬ) / ባቡር
ተ/ቁ ሃገር መሠረተ-ልማት ባቡር መስመር (Nominal GDP
መስመር
መጠን (ኪ.ሜ.) (ኪ.ሜ.) per Capita-USD
(ኪ.ሜ.)
GDP-2016)
1 ግብጽ 9570 104.7 11,210 3698.83
2 ሱዳን 5898 319.78 7,741.6 751.82
3 ታንዛንያ 3676 257.09 17,298.7 1099.29
4 ናይጄሪያ 3505 263.56 60,884.45 2065.75
5 ኬንያ 2046 284.77 25,909.1 2081.8
6 ኡጋንዳ 990 243.47 46,313.13 883.89
7 ኢትዮጵያ 659 1,675.72 182,549.32 925.08

ሰንጠረዥ 3፡ የአፍሪካ ሃገራት ደረጃ በባቡር መሠረተልማት አውታር መጠን

20
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
3 የኢትዮጵያ ባቡር ዘርፍ ስትራቴጂያዊ ትንተና

በኢትዮጵያ የዘመናዊ ባቡር መሠረተ-ልማት እንዲገነባ እና የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲስፋፋ


ሲታቀድ ከላይ የተጠቀሱትን የዘርፉን አበይት ተዋናዮች ሚና በሙሉ በብቸኝነት እንዲወጣ የተቋቋመው
የኢትዮጵያ የምድር ባቡር ኮርፖሬሽን (ኢምባኮ) ነው።

በመሆኑም ኢምባኮ ሃገራዊ የባቡር መሠረት ልማት አውታርን ከመዘርጋትና አገልግሎቱን ከመስጠት
በተጨማሪ የዘርፉን አቅም የመገንባትና በሃገሪቱ ጠንካራ የምድር ባቡር ዘርፍ የመመስረት ኃላፊነትም
ወስዶ እስከ አሁን ሲንቀሳቀስ ቆይቷል። ዘርፉን የማደራጀት ጫና በአንድ ወገን፣ በተልዕኮ የተሰጡትን
አበይት ሚናዎች ማስፈጸም በሌላ ወገን በመያዝ ኢምባኮ በተለያዩ ወቅቶች አደረጃጀቱን ለዚህ እንዲመች
እያደረገ የተጣሉበትን ኃላፊነቶች ለመወጣት ሲጥር ቆይቷል።

ለአብነት በመጀመሪያዎቹ ዓመታት የሃገሪቱን የባቡር አውታር መሪ ዕቅድ ማዘጋጀት፣ በተዘጋጀው መሪ


ዕቅድ የተያዙትን ኘሮጀክቶች በአፈፃፀም (ትግበራ) ቅደም ተከተል (በፌዝ) ከፋፍሎ ዕቅድ ማዘጋጀት፣
በመጀመሪያው ዙር ሊተገበሩ ለታሰቡት መስመሮች የአዋጭነት ጥናት ማዘጋጀትና የቅድመ ቴክኒካል
ጥናቶችና የጽንሰ-ሃሣብ ዲዛይኖችን የማዘጋጀት ሥራዎችን አከናውኗል። በመቀጠል ወደ ትግበራ ሲገባም
ከኘሮጀክት ፋይናንስ ማፈላለግ እስከ ግንባታ፣ ከግንባታ እስከ ኦኘሬሽን ቅድመ ዝግጅት የሚደርሱ
ሥራዎችን ከማከናወን ጎን ለጎን የዘርፉን የሰው ኃይል፣ የቴክኖሎጂና የተቋም አቅም ግንባታ ተግባራትን
ሠርቷል።

አሁን ባለንበት ወቅትም የገነባቸውን ኘሮጀክቶች ወደ አገልግሎት የማስገባት፣ የተጀመሩትን ኘሮጀክቶች


የማጠናቀቅና አዳዲስ ኘሮጀክቶችን የማስጀመር እንዲሁም የዘርፍ አቅም ግንባታ ሥራውን በተደራጀ
መልኩ የማስቀጠል ስትራቴጂክ ዕቅድ ነድፎ በመተግበር ላይ ይገኛል። ለባቡር አውታር ዝርጋታው
የሚያስፈልገውን ፋይናንስ ከብድር በተጓዳኝ በሌሎችም አማራጮች ለመሸፈን ፋይናንስ ከማፈላለግ
በተጨማሪ፤ ተጓዳኝ ገቢ የሚያስገኙ ሥራዎችን ለማከናወን፣ እንዲሁም የሰው ኃይሉን በሃገር ውስጥ
አቅም የኮርፖሬሽኑን ዓላማ የሚያሳካ እንዲሆን ለማድረግ ያላሰለሰ ጥረት በማድረግ ላይ ነው።

ከዚህ በታች የተቀመጠው ትንተና የኢትዮጵያ ባቡር ሴክተር ያለበትን ነባራዊ ሁኔታ በአካባቢያዊ ሁኔታ
የሚዳስስ ሲሆን፣ በመቀጠል አስቻይ ሁኔታዎችና ፈተናዎች ከተዘረዘሩ በኋላ፤ የስትራቴጂያዊ ትኩረት
አቅጣጫዎች ተለይተው ለእያንዳንዱ የትኩረት አቅጣጫ ሊተገበሩ የሚገባቸው ነጥቦች በመጨረሻ
ተቀምጠዋል።

21
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
አካባቢያዊ ትንተና (SWOT)

ሀ. ጥንካሬና ድክመቶች

ጥንካሬ ድክመት
• በአ.አ. ቀላል ባቡር እና በአዲስ ጅቡቲ ኦፕሬሽን ኮንትራት ፈጣን
• ቁልፍ በሆኑ የባቡር ቴክኖሎጂ ዘርፎች አሁንም በውጭ ሃገር እውቀትና
የእውቀት ሽግግር መደረጉ
ቴክኖሎጂ ላይ ጥገኝነት መኖሩ

• የሰው ሃብት ስምሪት እና አጠቃቀም ላይ ውስንነት መኖሩ


• ወጣትና በዘርፉ የተማረ የሰለጠነና ልምድ ያለው የሰው ሀይል
o በከፍተኛ ደረጃ የሰለጠነው የሰው ሀይልን የሚያቅፍ ሥራ በሴክተሩ
መኖሩ
በሰዉ ሃብት፣ ባለመፈጠሩ ከስራ ጋር ያልተገናኘ የሰለጠነ የሰው ሃይል ቁጥር መብዛቱ እና
o መነሻው የተለጠጠው የመሠረተልማት ግንባታ ዕቅዱ
የሰራተኛ የስራ ተነሳሽነት መቀነስ
(ambitious plan) ቢሆንም በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ
• የከፍተኛ ባለሙያ መብዛትና በተጻራሪው ለኦፕሬሽን የሚያስፈልገው መካከለኛ
ሃገር የሰለጠነ የዘርፉ ከፍተኛ ባለሙያ በብዛት እንዲፈራ
ባለሙያ እጥረት መኖሩ
መደረጉ
• በዘርፉ የሰለጠኑ የሴክተሩ ሰራተኞች በሴክተሩ በቂ ስራ ባለማግኘታቸው ወደሌላ
የስራ ዘርፍ መሰማራት
• ሴክተሩን ውጤታማ የሚያደርግ ተቋማዊ አደረጃጀት አለመፈጠሩ
o ወቅታዊና ነባራዊ ሁኔታን ያገናዘበ የመዋቅር ለውጥ አለመኖር
o በሴክተሩ ውስጥ ያሉና ወደፊት የሚቀላቀሉ ዋና ዋና ተዋናዮች መዋቅራዊ
• በአለም አቀፋዊ የባቡር ዘርፍ አማካሪ ድርጅት የተዘጋጀ ግንኙነት አለመኖሩ
የኮርፖሬት አደረጃጀት መዋቅር መኖሩ o ERC, EDR, AALRT, CDE, FUTURE RAILWAY LINES,
o ቢዝነሶችን ለመፍጠርና የጥናትና ምርምር ስራዎችን RELATED BUSINESSES እና REGULATORY BODY
ለመስራት የሚያስችል አደረጃጀት o በአማካሪ ድርጅቱ ተዘጋጅቶ የቀረበው አደረጃጀት በአግባቡ አለመተግበሩ
በአደረጃጀት፣
• የሴክተሩ አደረጃጀት ሴክተሩ የሚሰማራባቸውን የቢዝነስ o ከተለጠጠው ዕቅድ (ambitious plan) ጋር አብሮ የሚሄድ የሰው ሃይልን
አማራጮች ያማካለ ሆኖ እንዲደራጅ ስራዎች እየተሰሩ በአግባቡ ለመጠቀምና ለማስተዳደር የሚያስችል አደረጃጀት አለመተግበሩ
መሆናቸው o ከቀደመው የባቡር ዘርፍ ጠንካራና ደካማ ጎኖች ለመማር የሚቻልበት
አደረጃጀት አለመፈጠሩ
o የባቡር ዘርፉ ከተለያዩ አምራች፣ ገንቢ፣ አቅራቢና አገልግሎት ሰጪ ዘርፎች
ጋር በተሳሰረ መልኩ አለመደራጀት

22
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
ጥንካሬ ድክመት

• የሴክተሩን ዓለም አቀፍ ዕድገት የሚመጥን ዘመናዊና የዳበረ የአሠራር ሥርዓት


አለመኖሩ
o የተደራጁ ተቋማዊ ኦፕሬሽናል ማኑዋሎች ተዘጋጅተው አለመተግበራቸው
o በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሰራር በስፋት አለመዘርጋትና አለመተግበር
• አበይት ተልዕኮዎችን ለመፈጸም ጅምር አዲስ የአሰራር ስርዓት
o የሴክተሩ አፈጻጸም ውጤታማ (effective) እና ቀልጣፋ (effecient)
መኖሩ
በአሰራር አለመሆኑ
• በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሠራር ለመዘርጋት እንቅስቃሴ መኖሩ
ስርአት፣ o በዚህም የደንበኞች እርካታ ዝቅተኛ መሆኑ
• የ (IFRS) ትግበራ
• የዘርፉን አለማቀፋዊ ደረጃ የጠበቀ የአሰራር ስርዓት በስፋት አለመጠቀም
• ዘመናዊ የሀብት አመዘጋገብና አስተዳደር ስርዓት አለመኖር
• ሴክተሩ በውስጡ ያሉትን ባለሙያዎች በትክክል መጠቀም የማያስችል የአሰራር
ስርዓት
o ብዙ ስራዎችን ለውጭ ተቋራጮች ማስተላለፍ
• እጅግ ደካማ የፋይናንስ አቅምና የሚያሰጋ የፋይናንስ አቋም
o የባቡር መሠረተልማት ግንባታ የሚጠይቀውን ፋይናንስ የመሸፈን አቅም
• ያለውን ውስን የፋይናንስ ሀብት በተገቢው መንገድ ለመጠቀም
አለመኖሩ
የተደረገ ጅምር ጥረት
o የብድር ክፍያን ለመሸፈን የሚያስችል የፋይናንስ ጥንካሬ አለመኖር (ዝቅተኛ
• የባቡር ሴክተሩ ከዚህ በፊት ካደረጋቸው ኢንቨስትመንቶች
ገቢ የማመንጨት አቅም)
በፋይናንስና የተገኙ በከፍተኛ ደረጃ መልማት የሚችሉ ሀብቶች
o ያለውን የፋይናንስ ክፍተት ለመሙላት ለከፍተኛ የውጭ እና የሃገር ውስጥ
ቁሳዊ ኃብት፣ o ቢዝነስ ዩኒቶችና ትራንዚት ተኮር ልማቶች
ብድር ክምችት መዳረጉ (በዚህም የዕዳ፡ ሃብት ምጣኔ አስጊ ደረጃ ላይ
o ያሉትን ሀብቶች በመጠቀም ከግሉ ዘርፍ ጋር የጋራ
መድረሱ)
ኢንቨስትመንት ለማካሄድ እንቀስቃሴ መኖሩ
• የቁስ ሀብቶችን አቅም ወደ ፋይናንስ ለመለወጥ ሙሉ አቅምን አሟጦ የመጠቀም
ውስንነት

• የዘርፉ አመራር በፍጥነት መለዋወጥ ዘላቂ የሆነ ተቋማዊ ስትራቴጂያዊ ጉዳዮችን


• በአመራሩ ዘንድ የሴክተሩን ነባራዊ ችግሮቹን ተረድቶ
በአመራር ለማስፈጸም ተግዳሮት መፍጠሩ
ስትራቴጂያዊ በሆነ መንገድ ለመምራት ተነሳሽነት መኖር
• የዘርፉን ራዕይ በግልጽ ለሁሉም ሠራተኛ እና ባለድርሻ አካላት ማስረጽ አለመቻል

23
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
ጥንካሬ ድክመት
• ሴክተሩን በዘመናዊ መንገድ ለመምራት እና ለማሻገር የሚያስችል በየደረጃው ያለ
የአመራር አቅም ውስንነት መኖር
• ወቅታዊና ፈጣን የውሳኔ ሰጪነት ችግር
• ተተኪ አመራርን የማብቃት ስርዓት አለመኖር
• በአ. አ - ጅቡቲ እና በአ.አ. ቀላል ባቡር ደንበኞች የአገልግሎት ፍላጎት እና
• ለሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊና ማሃበራዊ እድገት የባቡር ዘርፉን
አቅርቦት አለመጣጣም በተፈጠረ የእርካታ ማነስ የተነሳ በማህበረሰቡ ዘንድ
አስፈላጊነት ግንዛቤ ማደግ
የተቋም/ ለሴክተሩ የተዛባ አሉታዊ ግንዛቤ መፈጠሩ
• ሜጋ ፕሮጀክትን የመፈጸም አቅም ማሳያ መሆን መቻሉ
የሴክተር ገጽታ • የሴክተሩን አካባቢያዊና ማሃበራዊ ፋይዳ በአግባቡ ባለመስረጹ በማሃበረሰቡ የተነሱ
• በታዳሽ ሀይል የሚንቀሳቀስ የባቡር ዘርፍ መሆኑ
ቅሬታዎች
• ዝቅተኛ የደህንነት እና የአደጋ ስጋት መከላከል ሪከርድ

ሰንጠረዥ 4፡ የአካባቢያዊ ሁኔታ ዳሰሳ (ጥንካሬዎችና ድክመቶች)

24
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
ለ. መልካም አጋጣሚዎችና ስጋቶች

መልካም አጋጣሚዎች ስጋቶች


• በሀገሪቱ በአሁን ሰዓት የተጀመረው የለውጥ
እንቅስቃሴ አለም አቀፋዊ ተቀባይነት ማግኘቱና
• በሃገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች የሚነሱ ግጭቶች በተረጋጋ ሁኔታ ግንባታውንና
በመጭው ጊዜያት ኢንቨስተሮችን ለመሳብ
አገልግሎቱን ለማከናወን፤ እንዲሁም የኢንቨስተሮችን መተማመን ለማግኘት አዳጋች
አበረታች ሁኔታዎች መፈጠሩ
ሁኔታ መፍጠራቸው
• በሀገሪቱ የተፈጠረው አንጻራዊ ሰላምና
መረጋጋት መኖሩ
ፖለቲካዊ • ኢትዮጵያ በአህጉር አቀፍ ደረጃ (በተለይ
(P) በምስራቅ አፍሪካ) በዘመናዊ የባቡር መሠረተ-
ልማት ዝርጋታ እና ትራንስፖርት አገልግሎት
የተሻለ አቋምና ተቀባይነት ያላት መሆኑ • የባቡር ሴክተር ለደኅንነት አደጋ ስጋት ተጋላጭ መሆኑና ከተከሰተም ጉዳቱ ከፍተኛ
• የባቡር መሰረተ-ልማት ከዋና ዋና የመንግስት መሆኑ
የልማት አጀንዳዎች መካከል መሆኑና
በመንግስት ዘንድ ይህን ለማስፈጸም ቁርጠኝነት
መኖሩ
• ዘርፉ የሚፈልገው ከፍተኛ የግንባታና የኦፕሬሽን ወጪ በሃገር ውስጥ አቅም ብቻ
• ዘርፉ ከዘላቂ የልማት ግቦች ጋር የተያያዘ
የሚሸፈን አለመሆኑ እና የውጭ ፋይናንስም ለማግኘት አዳጋች መሆኑ
መሆኑ (SDG እ.ኤ.አ 2015 -2030)
• የሴክተሩ የፋይናስ መዋቅር (Financial Structure) የሴክተሩን ፈጻሚ ተቋማት ለከፍተኛ
• የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠና መመስረትና ወደ
የዕዳ ጫና በሚዳርግ መልኩ መሆኑ
ተግባራዊ እንቅስቃሴ መገባቱ
• የባቡር ሴክተር በአጭር ጊዜ ትርፋማ አለመሆን የተነሳ በተለይ የመንገደኞች
• የባቡር ዘርፉ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም
ትራንስፖርት አገልግሎት ድጎማ በመፈለጉ ምክንያት ለመሠረተ-ልማትና ለኦፕሬሽን
አካል መደረጉ እና ይህን ለመፈጸም በራስ ሀይል
ኢንቨስትመንት የባለሃብቶች ፍላጎት ዝቅተኛ መሆኑ
ኢኮኖሚያዊ ስራዎችን ለማከናወን መነሻ መሆኑ ( ብሄራዊ
• ከሃገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት ጋር ተመጣጣኝ የሆነ የኃይል አቅርቦት ባለመኖሩ የባቡር
(E) የትራንስፖርት ፖሊሲ ፣ 2012)
ሴክተሩን የኃይል ፍላጎት በአስተማማኝ ሁኔታ አለማርካቱ
• በሃገሪቱ ከፍተኛ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴና በፈጣን
• ባለው የአለም የአኮኖሚ አለመረጋጋትና የፖለቲካ ሁኔታ በአነስትኛ ወለድ በረጅም ጊዜ
የሕዝብ ዕድገት ምክንያት ከፍተኛ የሆነ
የሚመለስ (Concessional Loan) አለመገኘት
የጭነትና የሕዝብ ትራንስፖርት ፍላጎት መኖሩ
• ከጊዜ ወደ ጊዜ በውጭ ምንዛሬ ስጋት (Foreign Exchange risk) የብር የመግዛት አቅም
• የመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት አገልግሎት
መቀነስን ተከትሎ የብድርና ወለድ መናር
ለሌሎች ስራ አከናዋኞች ክፍት መሆኑ (ብሄራዊ
• በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆኑ ጠንካራ የፋይናንስ ተቋማትና የፋይናንስ ስርዓት
የሎጂስቲክስ ዘርፍ ፖሊሲ 2012)
በሀገራችን አለመኖሩ

25
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
መልካም አጋጣሚዎች ስጋቶች
• ተለዋጭ አለማቀፋዊ የ Climate Financing
የማግኘት ዕድል መኖሩ
• በፕሮጀክቶች አላግባብ የካሣ ክፍያ ጥያቄዎች የተነሳ ማህበረሰቡ ሴክተሩን ለናረ የካሣ ክፍያ
ወጪ መዳረጉ እንዲሁም የፕሮጀክቶች አፈጻጸም ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ማሳደሩ
• በየአካባቢው የሚገኙ የመንግስት ሀላፊዎች ለባቡር መሠረተ-ልማት ግንባታ
• በአብዛኞቹ የአፍሪካ ሃገራት በባቡር መሠረተ- የሚያስፈልገውን መሬት ለመስጠት ተባባሪ አለመሆንና ካሳ የተከፈለባቸውን የሴክተሩን
ልማት ለመተሳሰር ፍላጎት መኖር (በአፍሪካ መሬቶች ከግንዛቤ እጠረት የተነሳ መንጠቅና ለሶስተኛ ወገን ማስተላለፍ መኖራቸው (ለባቡር
ማሕበራዊ
ህብረት አጀንዳ 2063 መሠረት) መሠረተ-ልማት ፕሮጀክቶች ክልሎችና የአካባቢ አስተዳደሮች ተገቢውን ድጋፍና እገዛ
(S)
• የሰዎች ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ የመስራት ባህል አለማድረግ)
ማደግ • ዝቅተኛ የባቡር መሰራተ ልማትና አገልግሎት ፋይዳ ግንዛቤ መኖር በዚህም ምክንያት
የመሠረተ-ልማት ዝርፊያና ውድመት በየአካባቢው መታየት
• የመልካም አስተዳደርና ብልሹ አሰራር ችግር

• በአፍሪካና በዓለም ዙሪያ ያለው ወቅታዊ የባቡር • በሃገሪቱ የባቡር ቴክኖሎጂ ሽግግርና የመጠቀም እንዲሁም በዘርፉ የምርምርና ስርፀት
ቴክኖሎጂ መነቃቃት መኖር ልምድና ባህል የዳበረ አለመሆን
• ከኮርፖሬሽኑ ጋር በጋራ ከሚሠሩና ለመስራት • በሴክተሩ የሃገር በቀል ተዋናዮች (ኮንትራክተር፣ ኮንሰልታንት፣ አምራች…) ተሳትፎ
ፍላጎት ካላቸው የውጭ ሃገር ግንባር ቀደም እጅግ ዝቅተኛ መሆኑ
የዘርፉ ኩባያዎች (ኮንትራክተሮች፣ • የባቡር መስመር ዲዛይን በባህሪው ከመንገድ መስመር ዲዛይን አንጻር በቀላሉ ማሻሻልን
ቴክኖሎጂያዊ
ኮንሰልታንቶችና የኦፕሬሽን ኩባንያዎች) የሚገድብ ባህሪ ስላለው ነባር ይዞታዎችን (existing land use) በመንካት ማለፍን
(T)
የዕውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ለማድረግ ዕድል በማስገደዱ ለከፍተኛ የካሣ ክፍያ ወጪ የሚዳርግ መሆኑ
መኖሩ • በሴክተሩ የሰለጠኑ ባለሙያዎች በባቡር መሰረተ-ልማት ዲዛይን፣ ግንባታና፣ ቁጥጥር ስራ
• በአለም አቀፍ ደረጃ እያደገ ያለውን በባቡር ዘርፍ ላይ እየተሳተፉ ልምድ እንዲያዳብሩ የሚደረግ እንቅስቃሴ ደካማ መሆን
መተግበር የሚችል የአርቴፊሻል ኢንቴሊጀንስ • በኦፕሬሽንም ሆነ በግንባታ ዘርፍ ለቴክኖሎጂ ሽግግር ወደሀገር ውስጥ የሚገቡ ተቋማት
እድገት ቴክኖሎጃቸውን ለሀገር በቀል ባለሙያወች ለማስተላለፍ ያላቸው ፍላጎት ዝቅተኛ መሆን
• የተመረጠው የባቡር ቴክኖሎጂ በሚጠቀመው
ታዳሽ የሃይል ምንጭ ምክንያት ከአካባቢ ጋር
• የሃገሪቱ ለባቡር መሠረተ - ልማት የማያመች ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ ከፍተኛ የግንባታ
ተስማሚ ልማት ስለሆነ ዓለም አቀፍ
ከባቢያዊ (E) ሥራዎች (ረጃጅም ድልድዮችና ዋሻዎች) እና ከፍተኛ ወጪ መጠየቁ
ተቀባይነትና ድጋፍ የማግኘት ዕድል መኖሩ
• ዘርፉ ለአየር ንብረት ለውጥና ለአደጋ ስጋት ተጋላጭ መሆን
• አለማቀፋዊ የታዳሽ ሀይል የሚጠቀሙ
ቴክኖሎጂዎች እድገት

26
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
መልካም አጋጣሚዎች ስጋቶች

• በሃገር አቀፍ ደረጃ በተያዘው የግል ባለሃብትን


በፕሮጀክት ፋይናንሲንግ እና በሴክተሮች
ማሳተፍ (PPP) አቅጣጫ የመጠቀም ዕድል
መኖሩ፤ ይህም በሕግ የተደገፈ መሆኑ
የመንግስትና ግል አጋርነት (PPP) (አዋጅ ቁ
1076/2010)
• የካፒታል ገበያ መቋቋሙና በዚህም የባቡር ዘርፉ
ካፒታል ማፍራት የሚችልባቸው እድሎች • የባቡር መሠረተ-ልማት ግንባታ ከሌሎች መሠረተ-ልማቶች ጋርና ከክልል መንግስታትና
ሕጋዊ (L) መኖራቸው (አዋጅ ቁ 1248/2013) ከየአካባቢው መንግስታት ጋር በቅንጅት የሚሠራ በመሆኑ በቅንጅት ሊያሰራ የሚችል
• የመንግስት የልማት ድርጅቶች ማቋቋሚያ አዋጅ አስገዳጅ የሕግ ማዕቀፍ አለመኖር
25/84 ማነቆዎችን ለመፍታት ማሻሻያ የማድረግ
ሂደት ላይ መሆኑ
• የባቡር ኮርፖሬሽን የማቋቋሚያ ደንብ 141/2000
• የባቡር ትራንስፖርት አስተዳደር አዋጅ
1048/2009
• የባቡር ኮርፖሬሽን የማቋቋሚያ ደንብ የካፒታል
ማሻሻያ መደረጉ

ሰንጠረዥ 5፡ የአካባቢያዊ ሁኔታ ዳሰሳ (መልካም አጋጣሚዎችና ስጋቶች)

27
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
አስቻይ ሁኔታዎች (ጥንካሬ + መልካም አጋጣሚዎች)

ከባቡር ሴክተሩ ነባራዊ ሁኔታ ትንተና በመነሳት የሴክተሩ አስቻይ ሁኔታዎች የተለዩ ሲሆኑ እነዚህም
ለሴክተሩ ማደግ እና መስፋፋት እንዲሁም የተሻለ አፈጻጸም ምቹ ሁኔታዎችን የሚፈጥሩ ናቸው።

አህጉራዊ የሴክተሩ መነቃቃት ፡- የአፍሪካ ሃገራት በባቡር መሠረተ-ልማት ለመተሳሰር ከፍተኛ ፍላጎት
አሳይተዋል። ተግባራዊነቱንም እውን ለማድረግ አህጉራዊ የሴክተሩ
መነቃቃት
በአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 ውስጥ ባቡር ዋንኛ ከባቢያዊሜታ
ጠቀሜታ
የልማት አጀንዳ ሆኖ ተካትቷል። በተለይም በምስራቅ በራስ አቅም ገቢ
ማመንጨት
አፍሪካ ዘመናዊ የባቡር መሠረተ-ልማት ዝርጋታ እና የሴክተር
አደረጃጀት
ትራንስፖርት አገልግሎት የተሻለ አቋምና ተቀባይነትን
የተሻለ የአፈጻጸም
አግኝቷል። የአፍሪካ ነጻ የንግድ ቀጠናም ተመስርቶ አቅም መኖር
ፖለቲካዊ ምቹ
ወደ ተግባራዊ እንቅስቃሴ መገባትና ወቅታዊ የባቡር ሁኔታ
የላቀ የደንበኞች
ቴክኖሎጂ እድገት በአፍሪካና በዓለም ዙሪያ ካሳየው ፍልላጎት
ምቹ የኢንቨአትመንት
መነቃቃት ጋር ተዳምሮ ኢትዮጵያ በሰላሳ አመቱ ሁኔታዎች መፈጠር

የትራንስፖርት ማስተር ፕላን /እ.ኤ.አ. ከ2022-2052/


ምስል 4፡ የባቡር ዘርፉ አስቻይ ሁኔታዎች
ላይ የባቡር መሰረት ልማት ሽፋንን ለማሳደግ
ያስቀመጠችሁን የልማት እቅድ ለማሳካት ትልቅ አቅም ይፈጥራል።

ከባቢያዊ ጠቀሜታ (Environmental Friendliness)፡- በሃገሪቱ ተግባራዊ እየሆነ ያለውና ለማስፋፋት


የተመረጠው የባቡር ቴክኖሎጂ ከታዳሽ ኃይል የሚገኝን የኤሌክትሪክ ሃይል የሚጠቀም ነው። ይህም
ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚን /Build climate resilient
green economy) ለመገንባት ካስቀመጠችው የአረንጓዴ የልማት አቅድ ጋር የተሳሰረ ነው። የታዳሽ
ሃይልን የሚጠቀም የባቡር ትራንስፖርት የበካይ ጋዝ ልቀትን በመቀነስ የሚያበረክተው አውንታዊ
አስተዋጽዎ ከፍተኛ ነው። ይህም ከአለም ዘላቂ የልማት ግቦች /SDG13: Climate Action- Prioritized
climate smart technologies, 2015 – 2030/ ጋር የተጣጣመ በመሆኑ የሴክተሩን ፋይዳ ለማሳደግ
የሚደረግን አለም አቀፍ የፋይናንስ ድጋፍ /Climate finance/ የሚያስገኝ እና ጉልህ ተቀባይነት ያለው
ነው። በአለም አቀፍ ደረጃ የታዳሽ ኃይል የሚጠቀሙ የዘርፉ ቴክኖሎጂዎች እድገትንም ያጎለብታል።

የሴክተር አደረጃጀት፡- የባቡር ዘርፉ የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም አካል መደረጉ እና ይህን ለመፈጸም
በራስ ሀይል ስራዎችን ለማከናወን መነሻ መሆኑ ( ብሄራዊ የትራንስፖርት ፖሊሲ ፣ 2012) ፤ የመንግስት
የልማት ድርጅቶች ማቋቋሚያ አዋጅ 25/84 ማነቆዎችን ለመፍታት ማሻሻያ የማድረግ ሂደት ላይ መሆኑ፤
የመልቲ ሞዳል ትራንስፖርት አገልግሎት ለሌሎች ስራ አከናዋኞች ክፍት መሆኑ ፤(ብሄራዊ የሎጂስቲክስ

28
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
ዘርፍ ፖሊሲ 2012)፤ የባቡር ኮርፖሬሽን የማቋቋሚያ ደንብ 141/2000፤የባቡር ትራንስፖርት አስተዳደር
አዋጅ 1048/2009 ፤ የአለም አቀፍ የፋይናንስ ሪፖርት ሰታንዳርድ (IFRS) ትግበራ፤ በአሁን ሰዓት ዘርፉ
ሊሰማራባቸው የሚችልባቸውን የተልያዩ የቢዝነስና የገቢ አመንጪ አደረጃጀቶች ለማስተናገድ የሚችል
መዋቅር በመሰራት ላይ መሆኑ፤ በዚህም ቢዝነሶችን የመፍጠር የጥናትና ምርምር ስራዎችን ለመስራት
የሚያስችል አደረጃጀት በመኖሩና የሴክተሩ አደረጃጀት ሴክተሩ የሚሰማራባቸውን የቢዝነስ አማራጮች
ያማካለ ሆኖ እንዲደራጅ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸው ሴክተሩን ዉጤታማ ለማድረግ ያስችላል።

ፖለቲካዊ ምቹ ሁኔታ፡- መንግስት የሃገሪቱን ክፍሎች በተለያዩ የትራንስፖርት አውታሮች ለማገናኘት


እቅድ ይዞ እየተንቀሳቀሰ በመሆኑና ይህንን ከግብ ለማድረስ ይህን ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ የሚፈልግ
ሴክተር ለመደገፍ እና ለመተግበር ያለው ቁርጠኝነት ከፍተኛ መሆኑ ለሴክተሩ ቀጣይነት እና እድገት
ጉልህ አስተዋጽኦ ይኖረዋል። በተጨማሪም በሀገሪቱ የተጀመረው የለውጥ እንቅስቃሴ የውጪ
ኢንቨስተሮችን የሚስብ በመሆኑና በሀገሪቱ የተፈጠረው አንጻራዊ ሰላምና መረጋጋት መኖሩ በሴክተሩ
ሊሳተፉና ስትራቴጂያዊ አጋር ሊሆኑ የሚችሉ የውጪ ኢንቨስተሮችን የመሳብ እድሉ ከፍተኛ ነው።

ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታዎች መፈጠራቸው፡- በሀገሪቱ የተጀመረው የለውጥ እንቅስቃሴ የሃገሪቱን


አለም አቀፍ ተቀባይነት የሚጨምር እና የውጪ ሃገራት ኢንቨስተሮችን በሀገር ውስጥ ኢንቨስት
እንዲያደርጉ የሚያበረታታ እንዲሁም ከኮርፖሬሽኑ ጋር በጋራ ከሚሠሩና ለመስራት ፍላጎት ካላቸው
የውጭ ሃገር ግንባር ቀደም የዘርፉ ተዋናዮች (ኮንትራክተሮች፣ ኮንሰልታንቶችና የኦፕሬሽን ኩባንያዎች)
እና ከግሉ ዘርፍ ጋር የሽርክና እና የጥምረት አሰራሮች መፈጠር ያስችላል። ከዚህ በተጨማሪ ከኩባንያዎች
የዕውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ለማድረግ ዕድል መኖሩ፤ በሃገር አቀፍ ደረጃ በተያዘው የግል ባለሃብትን
በፕሮጀክት ፋይናንሲንግ እና በሴክተሮች ማሳተፍ (PPP) አቅጣጫ የመጠቀም ዕድል መኖሩና ይህም
በሕግ የተደገፈ መሆኑ የመንግስትና ግል አጋርነት (PPP) (አዋጅ ቁ 1076/2010) ከዚህ በፊት በባቡር
ሴክተሩ ሲሳተፉ የነበሩትን እንዲሁም በቀጣይ በሴክተሩ መሳተፍ የሚፈልጉትን የውጭ ሃገራት ግንባር
ቀደም የዘርፉ ኩባንያዎች ወደ ሃገር ውስጥ ለመሳብ እና በሴክተሩ የሚደረገውን የእውቀትና ቴክኖሎጂ
ሽግግር ለማሳደግ የሚረዳ ነው።

የላቀ የደንበኛ ፍላጎት፡- የሀገራችን ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ማደግና ፈጣን የህዝብ ቁጥር እድገት ከፍተኛ
የሆነ የጭነት እና የህዝብ ትራንሰፖርት እንዲሁም ባጠቃላይ የሎጂስቲክስ አቅርቦት ፍላጎት እንዲኖር
አድርጓል። በሌላ በኩል በርካታ የአፍሪካ በተለይም የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በመንገድና በባቡር
ትራንስፖርት ለመተሳሰር የላቀ ፍላጎት ማሳየት በአንድ ግዜ በርካታ ጭነቶችን በገፍና በፍጥነት
ለሚያጓጉዘው የባቡር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ዘርፍ ማደግ እጅግ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል።
በተጨማሪም የሰዎች ከቦታ ቦታ ተዘዋውሮ የመስራት ባህል ማደግ ለሴክተሩ የደንበኛ ፍላጎት መጨመር
ትልቅ አስተዋጽኦ ያደርጋል።

29
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
የተሻለ የመፈጸም አቅም መኖሩ፡- በአመራሩ ዘንድ የሴክተሩን ነባራዊ ችግሮቹን ተረድቶ ስትራቴጅያዊ
በሆነ መልኩ ለመምራት ተነሳሽነት አለ። ለዚህም ማሳያ በሀገር ውስጥ በዘርፉ በከፍተኛ ደረጃ የሰለጠነ
ወጣት የሰው ሃብት ማፍራት ተችሏል እንዲሁም በባቡር ኦፕሬሽን ልምድ ያለው የሰው ሀይል ተፈጥሯል
ይህም ከአቅም ግንባታ ሂደት አንጻር የእውቀት ሽግግር በማምጣት በራስ አቅም የግንባታና የኦፕሬሽን
ስራ ለማከናወን የታየው የተሻለ ልምድ በቀጣይ የሴክተሩን አፈጻጸም የሚደግፍ ነው። የሜጋ ፕሮጀክቶችን
የመፈጸም የተሻለ አቅም ተፈጥሯል። ለምሳሌ የአዲስ አበባ ጅቡቲና የአዲስ አበባ ቀላል ባቡርን የግንባታ
ስራ በማጠናቀቅ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጡ ተደርጓል። በሌላ በኩል አለም አቀፍ ተቀባይነት
ያለው የፋይናንስ ሪፖርት አቀራረብ ስርአት የሆነውን (IFRS) ተግባራዊ እንዲሆን ተደርጓል።

የዘርፉን ዘለቄታዊ ህልውና ለማስጠበቅ በራስ ሃይል የገቢ ማመንጨት ስራዎችን የመስራት ዕድል መኖሩ
(በራስ ሀይል ገቢ ማመንጨት የሚያስችሉ ሁኔታዎች (Own-Force Business Activities))፦ በዘርፉ
በአሁን ሰዓት እየተከናወኑ ያሉ የባቡር ሴክተሩ ከዚህ በፊት ካደረጋቸው ኢንቨስትመንቶች የተገኙ
በከፍተኛ ደረጃ መልማት የሚችሉ ሀብቶችን የማልማት እንቅስቃሴዎች ተስፋ ሰጪ ጅምሮች ሆነው
ይታያሉ። በተለይም ከባቡር ዘርፍ ተጓዳኝና ትራንዚት ተኮር ልማቶች ጋር በተያያዘ በራስ ሃይልና ከግሉ
ዘርፍ ጋር በሚደረጉ የሽርክናና የመንግስት ግል ዘርፍ አጋርነት (PPP) እንቀስቃሴዎች ዋና ዋና ማሳያዎች
ናቸው ።

የባቡር ዘርፉ ለሀገሪቱ ኢኮኖሚያዊና ማሃበራዊ እድገት ያለው ከፍተኛ ጠቀሜታ በመንግስት አመራር
አካላት በመታመኑ በቅርቡ የባቡር ኮርፖሬሽን የማቋቋሚያ ደንብ የካፒታል ማሻሻያ መደረጉ (221 ቢሊየን
ብር የተፈቀደ ፤ 120 ቢሊየን ብር የተከፈለ) ፣ በትራንስፖርት ዘርፍ የ 30 ዓመታት (እኤአ 2022-
2052) መሪ ዕቅድ ውስጥ ለባቡር ዘርፉ ከፍተኛ አትኩሮት መሰጠቱ በዚህም የሀገራችን የባቡር መሰረት
ልማት ሽፋንን 7360 ኪሜ ለማድረስ መታቀዱ ፤ ዘርፉ ስቶክና ቦንድ ለገበያ በማቅረብ በራሱ ካፒታል
ማፍራት የሚችልባቸውን ዕድል የሚፈጥረው የካፒታል ገበያ መቋቋሙና ሌሎች አስቻይ ሁኔታዎች
የዘርፉን ቀጣይነት ለማረጋገጥ ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ።

30
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
ፈተናዎች (ድክመት + ስጋቶች)

ከባቡር ሴክተሩ ነባራዊ ሁኔታ ትንተና በመነሳት የቴክኖሎጂ ጥገኝነት


የሴክተሩ ፈተናዎች የተለዩ ሲሆኑ እነዚህም የፋይናንስና የሀብ
የጸጥታና የሴክተሩ አጠቃቀም ተግዳሮት
በሴክተሩ ማደግ እና መስፋፋት ሂደት ውስጥ ስጋት ደህንነት ችግር
የሚሆኑ ናቸው። እነዚህን ስጋቶች ለማስወገድ እና የደንበኞች እርካታ
ማነስ
የሴክተሩን አፈጻጸም ለማሻሻል ለተለዩት የአቅም ግንባታ
ውሱንነት
ፈተናዎች/ስጋቶች ስትራቴጂያዊ መፍትሄዎች ሴክተር ዘለል
የመልካም አስተዳደር መሰናክሎች
ሊቀረጹላቸው የሚገባቸው ናቸው። ችግር

የቴክኖሎጂ ጥገኝነት፦ በባቡር ሴክተሩ የዳበረ የሴክተር ገቨርናንስ


ተግዳሮት
የእውቀትና ልምድ ክምችት ያልነበረ በመሆኑ
እንዲሁም በሴክተሩ የሀገር በቀል ተዋናዮች ምስል 5፡ የባቡር ዘርፉ ፈተናዎች
(ኮንትራክተር፣ ኮንሰልታንት፣ኦፐሬተር፣ አምራች
ወዘተ) ያላቸው ተሳትፎ እጅግ ዝቅተኛ በመሆኑ ሴክተሩ በውጭ ሀገር እውቀትና ተክኖሎጂ ላይ ጥገኛ
ሆኗል። ከዚህ በተጨማሪ የሀገሪቱን ቀደምት የባቡር ቴክኖሎጂን የማቆየትና የመጠቀም፤ በዘርፉ
የምርምርና ስርጸት ልምድና ባህል የዳበረ ባለመሆኑ ሴክተሩ በውጭ ሀገራት ላይ ያለውን የቴክኖሎጂ
ጥገኝነት መቅረፍ አልቻለም።

የፋይናንስና የሀብት አጠቃቀም ተግዳሮቶች፡-በዘርፉ ከፍተኛ የፋይናንስና የሃብት አጠቃቀም ተግዳሮቶች


ይገኛሉ፡፡

o የፋይናንስ ተግዳሮቶች፡ የባቡር ሴክተር ከፍተኛ የግንባታና የኦፕሬሽን ወጪ የሚፈልግ ከመሆኑም


በላይ በአገር ውስጥ አቅም ብቻ መሸፈን የማይችል መሆኑ ይታወቃል፡፡ በተለይም የአገሪቱ መልክዓ
ምድራዊ አቀማመጥ ለባቡር መሠረተ ልማት ዝርጋታ የማይመች በመሆኑ ከፍተኛ የግንባታ
ሥራዎችን ማለትም ረጃጅም ድልድዮችና ዋሻዎች ግንባታን ተከትሎ ከፍተኛ የግንባታ ወጪን
የሚጠይቅ ነው፡፡ ግንባታው በሚጠይቀው ከፍተኛ ወጪና የባቡር ሴክተር በአጭር ጊዜ ትርፋማ
ካለመሆን የተነሳ የባለሃብቶች በዘርፉ ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎት በጣም ዝቅተኛ ነው፡፡ ይህን ተከትሎ
በሴክተሩ የሚገኙት መሠረተ ልማቶች የተገነቡት በነበረው የሴክተሩ የፋይናንስ መዋቅር ማለትም
የአገር ውስጥና የውጭ አገር ብድርን በተቋም ደረጃ በመበደር ሲሆን ይህም ከነበረው ዝቅተኛ ገቢን
የማመንጨት አቅም ጋር ተዳምሮ ከፍተኛ የዕዳ ጫናን ፈጥሯል፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ከውጭ አገር
ብድሮች ጋር ተያይዞ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ስጋት (Foreign Exchange Risk) ያለ ሲሆን ለአንድ
ዶላር የሚወሰነው የብር ምንዛሬ በጨመረ ቁጥር የሴክተሩ ፈጻሚ አካላት ዕዳቸው በከፍተኛ ደረጃ

31
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
ይጨምራል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞም ለዚሁ የውጭ አገር ብድርና ወለድ ክፍያ ከአገር ውስጥ
የሚወሰደው የብድር መጠን ይጨምራል፡፡ ይህ ከፍተኛ የሆነ የአገር ውስጥና የውጭ አገር የተመላሽ
ብድርና የወለድ ክፍያ ከፍተኛ መጠን ካለው የመሠረተ ልማትና የሎኮሞቲቭ የእርጅና ተቀናሽ
(Depreciation) ጋር ተዳምሮ የሴክተሩን ፈጻሚ አካላት ዕዳ - ካፒታል (D/E Ratio) ምጣኔ በከፍተኛ
ደረጃ ጎድቶታል፡፡ በአጠቃላይም በእነዚህ የብድር፣ የወለድና የእርጅና ተቀናሽ (Depreciation)
ወጪዎች ምክንያት የሚፈጠሩት የተበላሹ የሴክተሩ ፈጻሚ አካላት የፋይናንስ መግለጫዎች
(Financial Statements) የባቡር ሴክተሩ ከተለያዩ ፋይናንሰሮች፤ አልሚዎችና ሌሎች ባለድርሻ
አካላት ጋር የሚኖረውን የሥራ ግንኙነት የሚያበላሹ ናቸው። የኢፌዲሪ መንግስት እነዚህን በከፍተኛ
ዕዳ የተዘፈቁ የሴክተሩ ፈጻሚ አካላትና ሌሎች የመንግስት ተቋማትን ለመታደግ የዕዳና የሃብት
አስተዳደር ኮርፖሬሽንን በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 483/2013 ያቋቋመ ሲሆን ይህን
ተከትሎ የሴክተሩ የአገር ውስጥ ዕዳም ወደዚህ ወደ ተቋቋመው ኮርፖሬሽን በመዘዋወር ላይ ይገኛል፡
፡ ይሁን እንጂ የውጭ አገር ዕዳው ባለመዘዋወሩና የሴክተሩን ፈጻሚ አካላት የፋይናንስ ሁኔታ
በከፍተኛ ደረጃ ያጎበጠው የውጭ አገር ብድር በመሆኑ መንግስት ይህንን የውጭ አገር ብድር ወደ
ተቋቋመው ኮርፖሬሽን እንዲዘዋወር በማድረግ የሴክተሩን የዕዳ ሸክም ሊያቀለው ይገባል።
o የሃብት አጠቃቀም ተግዳሮቶች፡ በሴክተሩ የተለያዩ በርካታ ሃብቶች የሚገኙ ሲሆን የገቢ አመንጪነት
አስተሳሰብ አለመስረጽ፤ ተገቢ ትኩረት አለመስጠትና ዘመናዊ የሃብት አመዘጋገብ አጠቃቀምና
አስተዳደር ስርዓት ባለመኖሩ ምክንያት ሃብቶቹ ተጨማሪ ገቢ ለማመንጨት መዋል ሳይችሉ
ቀርተዋል፡፡ ሃብቶቹ በከፍተኛ ደረጃ የሠለጠነ የሰው ሃይል፤ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ያላቸው
መሬቶች፤ የተለያዩ የኮንስትራከሽን ማሽነሪዎች፤ የተለያዩ ተሸከርካሪዎች፤ የተለያዩ ዓይነት
ግንባታዎች እና ሌሎችም ሲሆኑ በአሁኑ ወቅት እነዚህን የሴክተሩ ሃብቶች እና ይዞታዎች በመጠቀም
ተጨማሪ ገቢ ለማመንጨት እየተሠራ ቢሆንም ከግሉ ዘርፍ አልሚዎች ጋር በመንግስትና ግል
አጋርነት (PPP) እና ሌሎች የፋይናንሲንግ መንገዶች ለማልማት የሚደረገው ጥረት ላይ እንደ አገር
የአሠራሮቹ አዲስነትና በዘርፉም ልምድ አለመኖር፤ ጠንካራና አስተማማኝ አልሚዎችን ማግኘት
ፈተና መሆን፤ እንዲሁም በአገሪቱ ጠንካራ የፋይናንስ ተቋማትና ጠንካራ የፋይናንስ ስርዓት አለመኖሩ
ተግዳሮት ሆነዋል።

የደንበኞች እርካታ ማነስ ፡- የሴክተሩ ዓለም አቀፋዊ ተሞክሮ የሚያሳየው በባቡር ትራንስፖርት
ተጠቃሚዎች ከፍተኛ ተቀባይነት ያለው ቢሆንም በሃገራችን ግን የኦፕሬሽን ስራ አዲስ በመሆኑ፣አቅርቦቱ
ባለመመጣጠኑ፣አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት ባለመኖሩ እንዲሁም በሚገባ ባለመደራጀቱ በባቡር
ትራንስፖርት ተጠቃሚዎች ዘንድ የእርካታ ማነስ ችግር ይታያል። የሴክተሩ አካባቢያዊ እና ማሕበራዊ
ፋይዳ ከፍተኛ እንደሆነ ቢታመንበትም ወደ ማሕበረሰቡ በአግባቡ ባለመስረጹ ምክንያት በማሕበረሰቡ
የሚነሱ አንዳንድ ቅሬታዎች በመኖራቸው ለደንበኞች እርካታ ማነስ ምክንያት ሆኗል።

32
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
ሴክተር ዘለል መሰናክሎች፡- የባቡር መሠረተ-ልማት ግንባታ ከሌሎች መሠረተ-ልማቶች ጋር በቅንጅት
በመስራት ሊያስገኘው የሚችለው ጠቀሜታ ከፍተኛ በመሆኑ ይህንን ዕውን ለማድረግ በቅንጅት ሊያሰራ
የሚችል የሕግ ማዕቀፍ (የፌደራል የተቀናጀ መሰረተ ልማቶች ማስተባበሪያ ኢጀንሲ 2006) ቢኖርም
አተገባበር ላይ ግን ችግር ይታይበታል። ከሃገሪቱ የኢኮኖሚ ዕድገት ጋር ተመጣጣኝ የሆነ የኃይል
አቅርቦት ባለመኖሩ የባቡር ሴክተሩን የኃይል ፍላጎት በአስተማማኝ ሁኔታ ማርካት አልተቻለም።
እንዲሁም የፕሮጀክቶች ካሳ ክፍያ የሚፈጸምበት ደንብ እና አዋጅ ቢኖርም ስራውን ለማከናወን ሃላፊነት
የተሰጣቸው አካላት (ከተማ እና ወረዳ መስተዳድሮች) የመልካም አስተዳደር ችግር የተነሳ አላግባብ የካሣ
ክፍያ ጥያቄዎች የተነሳ ሴክተሩን ለናረ የካሣ ክፍያ ወጪ የዳረገ ሲሆን በዚህ ምክንያትም በፕሮጀክቶች
አፈጻጸም ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ አሳድሯል።

የሴክተር አደረጃጀትና አሰራር ስርዓት ተግዳሮት፡- የሴክተሩን ዓለም አቀፍ እድገት የሚመጥን ዘመናዊና
ደረጃውን የጠበቀ አሰራር ስርዐት በስፋት አለመተግበሩ ሴክተሩ በቴክኖሎጂ የተደገፈና አፈጻጸሙ
ውጤታማ (effective) እና ቀልጣፋ (efficient) እንዳይሆን አድርጎታል። ወቅታዊ ሁኔታን ያገናዘበ
የመዋቅር ለውጥ አለመደረግና በሴክተሩ ውስጥ ያሉትንና ወደፊት የሚቀላቀሉ ተዋናዮችን (ለምሳሌ ERC,
EDR, AALRT, CDE, FUTURE RAILWAY LINES, RELATED BUSINESSES እና
REGULATORY BODY) ለማስተናገድ የሚያስችልና ከቀደመው የባቡር ዘርፍ ጠንካራና ደካማ ጎኖች
ለመማር የሚቻልበት አደረጃጅት አለመኖር በሴክተሩ ውጤተማነት ተጽእኖ ይኖረዋል። ከዚህ በተጨማሪ
ሴክተሩ በውስጡ ያሉትን ባለሙያዎች በትክክል መጠቀም የሚያስችል የአሰራር ስርዓት ባለመኖሩ ብዙ
ስራዎችን ለውጭ ተቋራጮች ለማስተላለፍ አስገድዷል።

የሴክተር ገቨርናንስ ተግዳሮት፦ ሴክተሩን በዘመናዊ መንገድ ለመምራትና ለማሻገር የሚያስችል በየደረጃው
ያለ የአመራር አቅም ውሱን መሆን ፤ ተተኪ አመራርን የማብቃት ስርዐት አለመኖር፣ የዘርፉን ራዕይ
በግልጽ ለሁሉም ሠራተኛ እና ባለድርሻ አካላት ማስረጽ አለመቻልና ፤ ወቅታዊና ፈጣን የውሳኔ ሰጭነት
ችግር ለሴክተሩ እድገት ፈተና ሆኗል። የባቡር ኔትዎርክ ማስተር ፕላንን በአጭር ጊዜ ለመገንባት ታሳቢ
በማድረግ በከፍተኛ ደረጃ የሰለጠነው የሰው ሀይልን የሚያቅፍ ስራ በሴክተሩ ባለመፈጠሩ ከፍተኛ ቁጥር
ያለው የሰለጠነ የሰው ሃይል ከስራ ጋር ማገናኘት አልተቻለም፤ በዚህም ምክንያት የሰራተኞች የስራ
ተነሳሽነት መቀነስና ወደሌላ የስራ ዘርፍ መሰማራት የሴክተሩን የተማረ የሰው ሀይል ብክነትን አስከትሏል።

የጸጥታና የሴክተሩ ደህንነት ችግር፦ የባቡር ዘርፍን ደህንነትና ፀጥታ ማረጋገጥ ለዘርፉ እድገት ቁልፍ
መለኪያ ነው። ይሁን እንጂ ዘርፉ በውጫዊና በውሳጣዊ ምክንያቶች የደህንነት እና የአደጋ ስጋት
የመከላከል ሪከርዱ ዝቅተኛ ነው። በሃገሪቱ በተለያዩ አካባቢዎች የሚነሱ ግጭቶች በተረጋጋ ሁኔታ የባቡር
መሠረተ-ልማት የግንባታ ስራዎችን ለማከናወንና ተገቢውን የትራንስፖርት አገልግሎት በአስተማማኝ
ሁኔታ ለመስጠጥ አዳጋች አድርጎታል። ይህም አልሚዎችን በመሳብና የነሱን መተማመኛ አግኝቶ የዘርፉ

33
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
ቁልፍ አጋር እንዲሆኑ ለማድረግ ፈታኝ ሁኔታን ይፈጥራል። የባቡር ዘርፍ ለደህንነት አደጋ ስጋት
ተጋላጭ ነው። አደጋ ከተከሰተም የሚያስከትለው አካባቢያዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጉዳትም ከፍተኛ
ነው። በተለይ የዘርፉ ባለቤትና ተጠቃሚዎች ዘርፉ የሚሰጠውን ፋይዳ ባለመገንዘብ ባቡሩ በሚያልፈባቸው
አካባቢዎች ያለውን የባቡር መሠረተ-ልማት ሃብት መዝረፍና ማውደም የዘርፉን የፀጥታና ደህንነት ችግር
የበለጠ አባብሶታል።

የመልካም አስተዳደር ችግር፦ በየአካባቢው የሚገኙ የመንግስት ሀላፊዎች የዘርፉን ባህሪና ጠቀሜታ
በአግባቡ ካለመረዳት የተነሳ ለባቡር መሠረተ-ልማት ግንባታ የሚያስፈልገውን መሬት ለመስጠት ተባባሪ
አለመሆንና ካሳ የተከፈለባቸውን የሴክተሩን መሬቶች በመንጠቅ ለሌሎች አልሚዎች ማስተላለፍ (ለባቡር
መሠረተ-ልማት ፕሮጀክቶች ክልሎችና የአካባቢ አስተዳደሮች ተገቢውን ድጋፍና እገዛ አለማድረግ)

የአቅም ግንባታ ውስንነት፦ በሴክተሩ የሰለጠኑ ባለሙያዎች በባቡር መሠረተ-ልማት ዲዛይን፣ ግንባታ፤
ኦፕሬሽንና ቁጥጥር ስራ ላይ እየተሳተፉ ልምድ እንዲያዳብሩ የሚያደርግ እንቅስቃሴ ደካማ መሆን
እንዲሁም በኦፕሬሽንም ሆነ በግንባታ ዘርፍ ወደሀገር ውስጥ የሚገቡ ተቋማት ቴክኖሎጂያቸውን ለሀገር
ውስጥ ባለሙያዎች ለማስተላለፍ ያላቸው ፍላጎት ዝቅተኛ መሆንና የሰራተኛውም ልምድ ለመውሰድ
ተነሳሽነት ማነስ የሴክተሩን የአቅም ግንባታ ውሱንነት አስከትሏል።

የተለዩ ስትራቲጂክ የትኩረት መስኮች

የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ከላይ እንደተጠቀሰው በሦስት አበይት የዕድገት ምዕራፎች አልፎ ላለንበት
ደረጃ የበቃ ሲሆን ወቅታዊ የሴክተሩን ዋነኛ ተግዳሮቶች የለየ፣ የዓለም አቀፍ ባቡር ሴክተሩን ልምድ
የቀመረ እና የወደፊት አድማሱን ያገናዘበ ስትራቴጂያዊ አቅጣጫ መከተል ይኖርበታል። ይህንንም
ስትራቴጂያዊ አቅጣጫ በወሳኝ የትኩረት መስኮች ላይ የሚተገበሩ መነሾዎች (Initiatives) በመለየት
ሴክተሩን ውጤታማ ማድረግ ያስፈልጋል። ከላይ በተተነተነው አካባቢያዊ ዳሰሳ መሠረት የተለዩ እና
ስትራቴጂ ተቀርጾላቸው ውጤታማነት የሚያመጣ ለውጥ የሚስፈልጋቸው የትኩረት መስኮች ከዚህ
የሚከተሉት ናቸው፡-

1. ዘላቂ የፋይናንስ አቅም መፍጠር፣

2. የዘርፉን ገቨርናንስ ሥርዓት ማጠናከር፣

3. ጠንካራ የሃገራዊ ባቡር ዘርፍ አቅም፣

4. አስተማማኝ የባቡር ደኅንነትና ጸጥታ፣

5. ዘላቂ የመሠረተልማት ሃብት፣

34
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
6. ውጤታማ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ናቸው።

ከላይ በተጠቀሱት ትኩረት መስኮች ውስጥ የተለዩ መነሾዎች (Initiatives) በምዕራፍ አምስት በዝርዝር
ተብራርተዋል። በተለዩት የትኩረት መስኮች ስትራቴጂያዊ አቅጣጫውን ለማስፈጸም እንዲረዳ ግን
በቅድሚያ ሴክተሩ በወሳኝ ምዕራፍ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ቀጣይ አሰላለፉ ላይ ውሳኔ ተሰጥቶበት መቀጠል
የሚያስፈልግ ከመሆኑ አንጻር ውይይት እንዲደረግበትና ውሳኔ እንዲሰጥበት የቀረበው አዋጭ የሴክተሩ
የአሠራርና የፋይናንስ ሁኔታ (Business & Finance Model) በምዕራፍ አራት ተገልጧል።

35
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
4 የአሠራርና የፋይናንስ ሁኔታ (Business & Finance Model)

የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር በቀጣይ ሊይዘው ስለሚገባው የሚገባው የአሠራር እና የፋይናንስ አካሄድ
(Business & Finance Model) የተለያዩ አማራጮችን በመዳሰስና አዋጭ የሆነውን በመጠቆም ከዚህ
በታች የቀረበ ሲሆን ስትራጂያዊ የትኩረት አቅጣጫዎቹን ለመተግበር ወሳኝ በመሆኑ ትኩረት ተሰጥቶት
ሊወሰን ይገባል።

የአሠራር ሁኔታ (Business Model)

4.1.1 የዓለም አቀፍ ባቡር ዘርፍ ተሞክሮ

ከዓለም አቀፋዊ የባቡር ሴክተሩ ተሞክሮ መረዳት እንደሚቻለው የሴክተሩ ዋን ዋና የንግድ ሚናዎች
/Business Functions/ የመሠረተ-ልማት መገንባትና ማስተዳደር እና የትራንስፖርት አገልግሎት
ሥራዎችን መስጠት ቢሆንም የባቡር ሴክተሩን የገቢ ምንጭ ለማጠናከርና ህልውናውን ለማስጠበቅ በብዙ
ሀገራት የባቡር ሴክተሩ ተጓዳኝ በሆኑ በሌሎች ዘርፎች ለምሳሌ በኮንስትራክሽን፣ በሎጅስቲክ፣ በ Transit
Oriented Development (TOD)፣ በ Real estate ና በመሳሰሉት ዘርፎች ተሰማርቶ ይገኛል። ነገር
ግን የብዙ ሀገራት ተሞክሮ እንደሚያሳየው የሴክተሩ አደረጃጀት በዋናንት የሚቃኘው ሴክተሩ በዋናነት
ከተቋቋመለት አላማ አንጻር ነው። እንደየሀገራቱ ነባራዊ ሁኔታ የሴክተሩ ባለቤትና ዋና ዋና ተግባራት
ፈጻሚ አካላት የተለያዩ ናቸው። በተወሰኑ ሀገራት ለምሳሌ አሜሪካና ጃፓን አብዛኞቹ የባቡር መሰረተ
ልማቶች በግል የተያዙ ሲሆን አብዛኞቹ የትራንስፖርት አገልግሎቱም እንዲሁ በግል ድርጅት የሚሰጥ
ነው። በሌሎች ሀገሮች ለምሳሌ ቻይና፣ ደቡብ ኮሪያ፣ ጣሊያንና በመሳሰሉት ሀገራት ደግም መንግስት
በራሱ አቅም ወይም በሌሎች በተለያዩ የቢዝነስ አደረጃጀቶች መሰረተ ልማቱን ገንብቶ አገልግሎት
የሚሰጥበትና ለግሉ ዘርፍ ለአገልግሎት የሚያከራይበት አሰራር ይገኛል።

የሴክተሩን ዋና ዋና ሚናዎች ማለትም መሠረተ-ልማት ማስተዳደርንና የትራንስፖርት አገልግሉት


የሚሰጥበት አደረጃጀት የብዙ ሀገራት ልምድ ከታች በምስል 6 እንደተገለጸው በሶስት የቢዝነስ ሞዴል
አይነቶች ማየት ይቻላል፡፡ እነዚህም፡-

ሀ. በተዋረድ የተሰናሰለ ቢዝነስ ሞዴል (Vertically Integrated Business Model) ፣

ለ. ጎንዮሻዊ ንጥጥል ውድድራዊ የመስመር ተጠቃሚነት ቢዝነስ ሞዴል (Horizontally


Separated Competitive Access Business Model)

36
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
ሐ. በተዋረድ የተነጣጠለ ቢዝነስ ሞዴል (Vertically Separated Business Model) ፣

ለ. ጎንዮሻዊ ንጥጥል ውድድራዊ


የመስመር ተጠቃሚነት
(Horizontally Separated ሐ. በተዋረድ
ሀ. በተዋረድ የተሰናሰለ የተነጣጠለመ
Vertically Integrated Competitive Access ) Vertically Separated

የባቡር ኦፐሬሽንና
ጥገና

የባቡር
ኢንቨስትመንት

የመሰረተ-ልማት
ኦፐሬሽንና ጥገና

የመሰረተ-ልማት
ኢንቨስትመንት

የመሰረተ-ልማት
ባለቤትነት

የመንግስታዊ የግል / የሁለት መንግስታት የጋራ ንብረት የግል ሴክተር (አክሲዮን/ሽርክና/የግል)


ሴክተር

ምስል 6፡ የባቡር ዘርፍ የቢዝነስ ሞዴል አማራጮች

ሀ. በተዋረድ የተሰናሰለ የባቡር ዘርፍ ቢዝነስ ሞዴል (Vertically Integrated Business Model)

ይህ የቢዝነስ ሞዴል በባቡር ኢንዲስትሪው የተለመደ ሲሆን የባቡር ዘርፍ እሴት ሰንሰለት ሥራዎች፤
በተለይም የመሠረተ-ልማት ግንባታ ኦፕሬሽንና ጥገና እንዲሁም የባቡር ትራንስፖርት ኦፕሬሽንና
የባቡሮች ጥገና በአንድ መንግሥታዊ የልማት ድርጅት ኃላፊነት ሥር የሚከናወኑበት ነው።

ቀደም ሲል በቀረበው ታሪካዊ ዳሰሳ እንደተገለፀው፣ የባቡር ዘርፉ ሥራዎች በአንድ መንገሥታዊ ድርጅት
ሲተገበሩ የመጡ መሆኑን ለዚህ ሞዴል መስፋፋት ተፅዕኖ አሳድሯል። በተጨማሪም የባቡር መሠረተ-
ልማት ግንባታ ኢንቨስትመንት ወጪ ከፍተኛ መሆን፣ እንዲሁም የኦፕሬሽን ወጪዎች ከፍተኛ መሆንና
የገቢው አናሳነት፤ በዘርፉ ለመሠማራት ከፍተኛ የፋይናንስ አቅም የሚጠይቅ እንዲሆን በማድረጋቸው
የዘርፉ ሥራዎች በሙሉ በመንግሥታዊ ተቋም እንዲተገበሩ የማድረግ ዝንባሌ ፈጥሮ ቆይቷል።
በመሆኑም በመንግሥታዊ ልማት ድርጅቶች የሚመሩ የባቡር ዘርፍ ባላቸው ሀገራት በአብዛኛው በተዋረድ
የተሠናሠለ የቢዝነስ ሞዴል ተግባራዊ ይደረጋል።

37
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
በተለይ ባቡር ከፍተኛ ማሕበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ሚና በሚያበረክትበት መካከለኛ ገቢ ላላቸው ሃገራት
ተመራጭ ሞዴል ሲሆን ስኬታማ ለማድረግ ጠንካራ የመንግስት በጀት ድጋፍ እና ቁርጠኝነት ይፈልጋል።

ይህ አሠራር የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት እና የመሠረተልማት አስተዳደር ሥራዎች በቅንጅት


የሚሠሩበትን ጠቀሜታ የሚያስገኝ ሲሆን በአንድ ተቋም ስር ሲሆን ለቅንጅት የሚያስፈልገውን ጉልበት
ጊዜና ገንዘብ ይቆጥባል። በተጨማሪም ከመሠረተ ለማት ግንባታው ጀምሮ እስከ ባቡር ትራንስፖርት
አገልግሎትና ጥገና በባቡር ዘርፉ ወጥ በሆነ ስታንዳርድ ጠንካራና አስተማማኝ የባቡር ደህንነትን
ለማረጋገጥ ምቹ ነው።

የዚህ ሞዴል ዋነኛ ድክመት የሴክተሩ ሥራዎች በሙሉ በአንድ ተቋም ብቻ በሞኖፖሊ እንዲያዙ በማድረግ
በተለይ ሌሎች የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች እንዳይሳተፉ ማገዱ እና በሥራ ላይ ያለው
አገልግሎት ሰጪ ደካማ ቢሆንም እንኳ ሌላ አማራጭ አለመኖሩ ነው። ይህ አሠራር በዓለም ውስጥ
የተለመደ ሲሆን ከእስያ በሕንድ (በአብዛኛው)፣ ከነጻ ገበያ በፊት በአውሮፓ የነበረ እና አሁንም በሩስያ
ያለ፣ ከሰሜን አፍሪካ ደግሞ በሞሮኮ እና በቦትስዋና ተግባራዊ የተደረገ ነው።

ለ. ጎንዮሻዊ ንጥጥል ውድድራዊ የመስመር ተጠቃሚነት ቢዝነስ ሞዴል (Horizontally Separated


Competitive Access Business Model)

ይህ ሞዴል በሁለት ዋና ዋና ባለቤቶች የሚተዳደሩ የባቡር መሰረተ ልማቶችን የያዘ ሲሆን አንድ የባቡር
ትራንስፖርት ኦፕሬሽንና የመሠረተ-ልማት አስተዳዳሪነትን የሚያከናውን የመንግሥት ልማት ድርጅትና
አንድ ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ የግል ዘርፎችን በመሠረተ-ልማት አስተዳዳሪነትና የባቡር ትራንስፖርት
አከናዋኝነት የያዘ ሲሆን የመሠረተ-ልማት አስተዳዳሪዎቹ የመስመር መጠቀም መብትን (Access Right)
ለሌሎች የባቡር ትራንስፖርት አገልገሎት ሰጪ ኩባንያዎች በፍትሐዊና በውድድር መርህ የሚሰጥበት
ሞዴል ነው።

በዚህ ቢዝነስ ሞዴል ውስጥ የሚሳተፈው መንግሥታዊ የልማት ድርጅት ሙሉ በሙሉ በቢዝነስ መርህ
የሚተዳደር ራሱን የቻለ የባቡር መሰረተ-ልማት አስተዳዳሪና የባቡር ትራንስፖርት አገልገሎት ሰጪ
ቢዝነስ ዩኒት የሚኖረው ሲሆን፤ በሚያስተዳድረው የመሰረ-ተልማት የመስመር መጠቀም መብትን
ከሌሎች አገልግሎት ሰጪ ኩባንያዎች ጋር በገበያ ውድድር መርህ ተወዳድሮ ይሆናል። በሌላ በኩል
የግሉ ዘርፍ የመሠረተ-ልማት አስተዳዳሪና የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ክንፍ አደረጃጀት
በአሜሪካ ለረጅም ጊዜ ተግባራዊ ተደርጎ የቆየ ሲሆን በዚህ አደረጃጀት ውስጥ የግሉ ዘርፍ በተዋረዳዊ
የተሰናሰለ ስርዓት የባቡር አገልግሎቱንና የመሠረተ-ልማት አስተዳዳሪነቱን ተቆጣጥሮ የሚሰራ ሲሆን
በተጨማሪም ለመንግስታዊና ለሌሎች የግል የጭነትና የመንገደኛ የባቡር ትራንስፖርት ኦፐሬትሮች
መስመሩን እንዲጠቀሙ (Access Right) ክፍት ያደርጋል።

38
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
ይህ ሞዴል በተለያዩ ሀገራት የሚተገበሩ ሞዴሎች ጥምር ሲሆን በመንግስት የተዋረዳዊ መሰናሰልና
ውድድራዊ አገልግሎት አሰጣጥ የተሰራው የግራ ክንፍ በአሁን ሰዓት በእንግሊዝና ሌሎች የምዕራብ
አውሮፓ ሀገራት እየተተገበረ የሚገኝ ሲሆን በግሉ ዘርፍ በተዋረዳዊ መሰናሰል ተደራጅቶ በውድድራዊ
መንገድ የባቡር አገልግሎትን ለሚሰጡ ሌሎች የዘርፉ ተዋናዮች እድል የሚሰጠው የቀኝ ክንፍ ደግሞ
በአሜሪካና ኒውዚላንድ እየተሰራበት የሚገኝ ነው ።

በመንግስት ዘርፍ ብቻ በተዋረድ የተሰናሰለ የቢዝነስ ሞዴል የግሉ ዘርፍ በመሠረተ-ልማት ባለቤትነትና
ማስተዳደር ተወዳዳሪነትን የሚገድብና የዘርፉን ምርታማነት የሚቀንስም ሲሆን በሌላ በኩል በግሉ ዘርፍ
ብቻ የተያዘ በተዋረድ የተሰናሰለ የቢዝነስ ሞዴል የግሉ ዘርፍ አትራፊ ናቸው ብሎ የሚያምንባቸውን
መስመሮች ብቻ እየለየ የማሳደግና የመጠገን ስራዎችን እንዲሰራና ሌሎች ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ
ጠቀሜታ ኖሯቸው ነገር ግን አትራፊ ያልሆኑ መስመሮችን ግን እንዲዘነጋቸውና ሀገራትን ከፍተኛ
ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ችግር ውስጥ እንዲገቡ ያደርጋል ። ለምሳሌ በደቡብ አሜሪካ ከፍተኛ የባቡር
መሠረተ-ልማት ካላቸውና እስካሁንም ድረስ በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ የባቡር መሠረተ-ልማት ያላት
አርጀንቲና እኤአ በ1990 መጀመሪያ አብዛኛውን የመሠረተ-ልማት በኮንሴሽን ወደ ግሉ ዘርፍ ቢተላለፍም
በወቅቱ አርጀንቲና ከነበራት 47,000 ኪሜ የባቡር መሠረተ-ልማት እኤአ በ2015 ወደመንግስት ዳግመኛ
ሲመለሱ 36,966 ኪሜ ደርሷል። ይህም ወደ ግሉ ዘርፍ ከተላለፉት የባቡር መስመሮች ውስጥ ወደ
10,000 ኪሜ ያህሉ ከጥቅም ውጪ መሆናቸውን ያሳያል። ስልሆነም በአሁን ሰዓት አርጀንቲና አብዛኛውን
የሀገሪቱን የባቡር መሠረተ-ልማት በመንግስታዊ የልማት ድርጅት በኩል እያስተዳደረችው ስትገኝ የግሉ
ዘርፍ ውጤታማ ስራ ይሰራል ተብሎ በታመነባቸው መስመሮች እንዲቀጥል አድርጋለች።

በአጠቃላይ ይህ ሞዴል መንግስት ኢኮኖሚያዊና ማሃበራዊ ጠቀሜታ እንዳላቸው የሚያምንባቸውን


መስመሮች መገንባትና አገልግሎት እንዲሰጡ እድል የሚሰጥ ሲሆን የግሉ ዘርፍ አዋጭ እንደሆኑ
ባመነባቸው የባቡር መስመሮች ላይ የመሠረተ-ልማት አስተዳዳሪነትና የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት
ሰጪነት መስመሮች ላይ ደግሞ በውድድር እንዲሳተፉ የሚጋብዝ ነው።

ሐ. በተዋረድ የተነጣጠለ ቢዝነስ ሞዴል (Vertically Segregated Business Model)

በዚህ አማራጭ የሴክተሩ የባቡር መሠረተልማት አስተዳደር እና የትራንስፖርት አገልግሎት ሚናዎች


የራሳቸው አደረጃጀት ያላቸው የተለያዩ ተቋማት እንዲተገብሩት ተደርጎ ይደራጃሉ።

የባቡር መስመሮችን የመገንባት፣ የማስተዳደር ማለትም የትራፊክ ኦፕሬሽን መምራት፣ መስመርን


ለትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪው በማስጠቀም ገቢ መሰብሰብ እና በሰበሰው ገቢ የመስመር ጥገና
ማከናወን በአንድ የመንግስት የልማት ድርጅት የሚተገበር ይሆናል።

39
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎቱን በተመለከተ ኃላፊነት የሚሰጠው ሌላ የመንግስት የልማት ድርጅት
ደግሞ ከመሠረተ-ልማት አስተዳዳሪው በሚሰጠው የኦፕሬሽን ፕላን (Slot) መሠረት በመስመሮቹ ላይ
ባቡሮችን በማንቀሳቀስ የመንገደኛና የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ገቢ መሰብሰብ፣
እንዲሁም የተንቀሳቃሽ ሃብት (ባቡሮች)ን ጥገና የማከናወን ኃላፊነት ይኖረዋል።

በባቡር ትራንስፖርት ኦፕሬሽን ላይ ፍላጎት ያለው እና የተቆጣጣሪ አካልን መስፈርት የሚያሟላ የግል
የባቡር ትራንስፖርት ሰጪ አካልም በባቡር ኦፕሬሽንና ጥገና ገብቶ ለመወዳደር ይችላል። ይህ ሞዴል
በአብዛኛው የአውሮፓ ሃገራት ከነጻ ገበያ መርህ በኋላ የተተገበረው የተዋረዳዊ ንጥጥሎሽ (Vertical
Separation) ሞዴል ነው። የዚህ አማራጭ ጠቀሜታ ከመነሻው ዐበይት የሴክተሩ ሚናዎች ላይ ግልጽ
የሆነ የኃላፊነት ክፍፍል ስለሚኖር ለግልጽነትና ተጠያቂነት አመቺ ነው። በተጨማሪም እያንዳንዱ ተቋም
በሚሰጠው የኃላፊነት ሚና ውጤታማ እና አትራፊ መሆን ስለሚጠበቅበት ለሴክተሩ ማደግ አበረታች
ምክንያት ይፈጥራል።

ሆኖም ይህ ሞዴል በመሠረተ-ልማት አስተዳዳሪውና በትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪው መካከል ለሚኖር


የፋይናንስ ዝውውር ወጪና በውስን መስመር ላይ ለሚደረግ የስራ ቅልጥፍና እንቅፋት የመሆን አደጋ
አለው።

4.1.2 ለኢትዮጵያ የባቡር ዘርፍ የሚመከረው የቢዝነስ ሞዴል

የሌሎችን ሀገራት ተሞክሮ እንደግብዐት በመጠቀም ኢትዮጵያ ውስጥ የተገነቡትንና ወደፊት የሚገነቡትን
የባቡር መሰረተ-ልማቶችና የኦፕሬሽን ስራ በሶስት ተከፍለው ከዚህ እንደሚከተለው ቀርቧል

➢ የከተማ ውስጥ የባቡር አገልግሎት (Tram/LRT/Metro/Subway): አገልግሎታቸው ለከተማ ውስጥ


ብቻ የሆኑ የ Tram፣ LRT፣ Metro ና subway የባቡር መሰረተ-ልማቶች የመሰረተ ልማቱ
ባለቤት መሰረተልማቱ የሚገኝበት የከተማው መስተዳድሩ ሲሆን የመሰረተ-ልማት ቁጥጥርና
(Infrastructure Management) የኦፐሬሽኑን ስራም የሚሰራው ከተማ መስተዳድሩ በሚያቋቁመው
ድርጅት ይሆናል። የኢትዮ ሬይልዌይ ግሩፕ የከተማ አስተዳደሩን ጥያቄና በጀት መነሻ በማድረግ
የመሰረተ-ልማት ይገነባል፣ የተለያይዩ ሙያዊ ድጋፎችን ያደርጋል።
➢ ሀገር አቋራጭ የባቡር አገልግሎት ( Railway lines crossing regional states)፡ ይህ የባቡር
መሠረተ-ልማት ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ከተሞችን ወይም አካባቢዎችን የሚያገናኝና እስከ
ኢትዮጵያ ድንበር ሊዘረጋ የሚችል ይሆናል። የመሰረተ ልማቱ ባለቤት በዋናነት መንግስት ሲሆን
የግሉ ዘርፍም የመስመሩን አዋጭነት እየገመገመ መሰረተ ልማቱን ገንብቶ ወይም ተከራይቶ

40
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
የሚያስተዳድርበት አሰራር ይኖራል። በዚህ መሠረተ-ልማት አገልግሎት የሚሰጡ ኦፐሬተሮች
የመንግስት ተቋም፣ የአክሲዮን ወይም የሽርክና ድርጅቶች ወይም የግል ድርጅቶች ሊሆኑ ይችላሉ።
➢ ወሰን ተሻጋሪ የባቡር አገልግሎት (Trans-boundary Railway Line)፡ ይህ መሠረተ-ልማት
ኢትዮጵያን ከጎረቤት ሀገሮች ጋር የሚያገናኝ የባቡር መስመር ሲሆን ባለቤቶቹም እንደአስፈላጊነቱ
የኢትዮጵያ መንግስት፣ የኢትዮጵያ መንግስትና በመሰረተ ልማቱ የተገናኘው የጎረቤት ሀገር
መንግስት ወይም የግል ባለሀብቶች ሊሆን ይችላል። የዚህ መሠረተ-ልማት ተቆጣጣሪ
(Infrastructure Manager) ሁለቱ ሀገሮች በስምምነት የሚያቋቁሙት ካምፓኒ ወይም የኢትዮጵያ
መንግስት የሚያቋቁመው ድርጅት ወይም የመሰረተ ልማቱ ባለቤት የሚያቋቁመው ድርጅት ሊሆን
ይችላል። በዚህ መሠረተ-ልማት አገልግሎት የሚሰጡ ኦፐሬተሮች የመንግስት ተቋም፣ የአክሲዮን
ወይም የሽርክና ድርጅቶች ወይም የግል ድርጅቶች ሊሆኑ ይችላሉ።

ኢትዮጵያ ልትከተለው የሚገባው የሀገር ውስጥና የድንበር ተሻጋሪ የባቡር መሠረተ-ልማት ቁጥጥር
(Infrastructure Management) ና የኦፕሬሽን ቢዝነስ ሞዴል ከዚህ በታች ለማብራራት ተሞክሯል።
አሁን ባለው ተጨባጭ ሁኔታ የዘመናዊ ባቡር ዘርፍ ሃገራዊ አቅም ግንባታው በጥንስስ ላይ ያለ በመሆኑ
በአነስተኛ ደረጃም ቢሆን የተከማቸው የሴክተሩ ዕውቀትና ልምድ ሳይበታተን ሴክተሩን የሚያሳድግበት
እና በቅንጅት ውጤታማ የሚሆንበትን ቅርጽ መያዝ ይገባዋል። ይህን መነሻ ከያዝን በክፍል “ሀ” የቀረበው
በተዋረድ የተሰናሰለ ሞዴል በአሁን ሰዓት በመንግስት በተገነቡና በመገንባት ላይ ያሉ የባቡር መሰረተ
ልማቶችን የማስተዳደርና የጭነትና የመንገደኛ አገልግሎት የመስጠት ስራዎችን በአንድ የመንግስት ልማት
ድርጅት በኩል እንዲሰሩ በማድረግ ውጤታማነትን ለማምጣት የምንከተለው ሞዴል ሊሆን ቢችልም
የግሉን ዘርፍ በአገልግሎት ሰጪነትም ይሁን በመሠረተ-ልማት ገንቢነትና አስተዳዳሪነት ከማስተናገድ
አንጻር ቦታ የሌለው በመሆኑ በክፍል ‘‘ለ’’ የቀረበውን ሞዴል ከዘርፉ የአጭር ፣ የመካከለኛና ረጅም ጊዜ
እቅዶች አንጻር ማለትም (ከ 2016 እስከ 2030 ዓ.ም) ልንጠቀመው የሚገባ ሞዴል ነው።

ምንም እንኳ ስራ ላይ እንዲውል የተመረጠው ሞዴል ‘ለ’ በአሁን ሰዓት በስራ ላይ የሚገኘውና
በኢትዮጵያና ጅቡቲ መካከል በተፈረመው የሁለትዮሽ ስምምነት መሰረት የሚተዳደረውን የኢትዮ ጅቡቲ
የባቡር አክሲዮን ማህበር (EDR)ን ከአዲስ አበባ ጅቡቲ በተዘረጋው የባቡር መስመር ላይ የባቡር ኦፕሬተር
ሆኖ እንዲቀጥል የሚያስችለው ቢሆንም የዚህን ማኅበር አደረጃጀት በድጋሜ ማጤንና ማስተካከል ተገቢ
ነው። በግንባታ ላይ ያሉና ወደፊት የሚገነቡ ከሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች ወደጅቡቲ የሚዘረጉ የባቡር
መስመሮች የአዲስ አበባ-ጅቡቲ መሠረተ-ልማትን በከፊል የሚጠቀሙ ስለሆነና ከነዚህ አካባቢዎች
የሚደረግ የባቡር ኦፕሬሽን የኢትዮ-ጂቡቲን የባቡር መሠረተ-ልማት በከፊል ስለሚጠቀም ከነዚህ ኮሪደሮች
የሚደረግ የባቡር ትራንስፖርቶችን የመስመር ተጠቃሚነት ክፍያ (Access fee) እንዳያስከፍል ወይም
በተወዳዳሪነታቸው ላይ ተጽዕኖ እንዳይፈጥርና መስመሩንም በአግባቡና በጊዜው እየጠገኑ የአገልጎት
ዘመኑን ላማራዘም ያመች ዘንድ የኢትዮ ጅቡቲ የባቡር አክሲዮን ማህበር በባቡር ትራንስፖርት

41
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
አገልግሎት ሰጪነት ብቻ እንዲቀጥል ማድረጉ ኢትዮጵያን ተጠቃሚ የሚያደርግ ይሆናል ። በሌላ በኩል
በጅቡቲ ግዛት ውስጥ የሚገኘውን የባቡር መሰረት ልማት በኢትዮጵያ የባቡር ዘርፍ ስር ለማስተዳደር
ይቻል ዘንድ አስፈላጊ የሆነ ንግግርና ድርድር በሁለቱ መንግስታት መካከል እንዲደረግ ይመከራል።

በመሆኑም የሀገሪቱ የባቡር ዘርፍ ለመንግስትም ሆነ ለግሉ ዘርፍ ክፍት በሆነ ውድድራዊ አደረጃጀት
የተዋቀረና ወደፊት የሚመጡ የግሉ ዘርፍ የባቡር መሠረተ-ልማት ገንቢዎች ፣ አስተዳዳሪዎች ወይም
የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎች በተሳካ ሁኔታ እንዲሳተፉ የሚረዳ ይሆን ዘንድ ከዚህ በታች
በተቀመጠው የተመረጠው የቢዝነስ ሞዴል (ምስል 7) ና እሱን ተከትሎ በሚኖረው ዝርዝር የዘርፉ
አደረጃጀት (ምስል 8) ተመላክቷል።

ጎንዮሻዊ ንጥጥል ውድድራዊ የመስመር


ተጠቃሚነት (Horizontally Separated
Competitive Access

የባቡር ኦፐሬሽንና
ጥገና
የባቡር
ኢንቨስትመንት

የመሰረተ-ልማት
ኦፐሬሽንና ጥገና
የመንግስታዊ ሴክተር
የመሰረተ-ልማት
ኢንቨስትመንት የግል / የሁለት መንግስታት የጋራ ንብረት
የመሰረተ-ልማት የግል ሴክተር (አክሲዮን/ሽርክና/የግል)
ባለቤትነት

ምስል 7፡ ለኢትዮጵያ የሚመከረው የባቡር ዘርፍ ቢዝነስ ሞዴል

አሁን ካለው የዘርፉ እድገት አንጻር የባቡር ዘርፉ ዋና ተወካይ የሆነው የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን
በአዋጅ በተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት መሰረት በመሠረተ-ልማት አስተዳዳሪነትና የባቡር ትራንስፖርት
አገልግሎት ሰጪነት እንዲሁም የዘርፉን ቀጣይነት በሚያረጋግጡ የዘርፉ ተዛማጅ ስራዎች (በሎጂስቲክስ
፣ በ TOD ፣ በባቡር መለዋወጫ ማምረት ፣ በግንባታ ፣ በዲዛይንና ቁጥጥር እንዲሁም ሌሎች ስራዎች)
እንዲቀጥል ለማድረግ የሚያስችልና በማንኛውም ጊዜ የግሉ ዘርፍ ለመሰማራት የሚችልበትን መደላድል
የሚፈጥር አደረጃጀት ከላይ ከተቀመጠው የዘርፉ ቢዝነስ ሞዴል ጋር በተጣጣመ መልኩ በሚከተለው
ሴክተራዊ ዝርዝር አደረጃጀት መታየት ይችላል ፦

42
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
MoTL PEHAA

Board

Railway
ER _ Tram/LRT/Metro/Subway
Regulatory
Group
Body

Joint
Ownership
Private IM
IM OP OT BU CB Logistic
BU BU
Private Parts Manuf.
Operator
TOD
Core Function Other
Private Business Units TBL
Companies

ምስል 8 ፡ ለኢትዮጵያ የሚመከረው የባቡር ዘርፍ አደረጃጀት

የፋይናንስ ሞዴል (Financial Model)

የባቡር ሴክተር ቢዝነስ ሞዴል የእሴት ሰንሰለቱ ሥራዎች በምን መልኩ በተደራጀ እና በማን ባለቤትነት
ስር በሆነ ተቋም ይከናወናል የሚለውን የሚመልስ ሲሆን፤ የፋይናንስ ሞዴሉ ደግሞ እያንዳንዱን የእሴት
ሰንሰለት ተግባራትን ለማከናወን የሚያስፈልገውን የካፒታል እና የኦፕሬሽናል ፋይናንስ ወጪ ምንጭ እና
የገቢ ሁኔታን በተመለከተ ምን መምሰል እንዳለበት ይጠቁማል፡፡

በዚህም መሠረት ለኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር የተመረጠውን የቢዝነስ ሞዴል ውጤታማ ለማድረግ
የፋይናንስ ሁኔታው የሚይዘውን ቅርጽ (Financial Model) ከዚህ በታች ቀርቧል፡፡

4.2.1 የካፒታል ኢንቨስትመንትን በተመለከተ

ሀ. በዓለም የሚተገበሩ የባቡር መሠረተ-ልማት ፋይናንሲንግ ሞዴሎች

43
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
በዓለም አቀፍ ደረጃ ካለው ልምድ አንጻር የባቡር መሠረተ-ልማትን ለመዘርጋትና የባቡር ግዥዎችን
ለመፈጸም የሚያስፈልገው ወጪ በተለያዩ መንገዶች የሚሸፈን ሲሆን ይህም በሚከተለው ስዕላዊ መግለጫ
(ምስል 9) ቀርቧል፡፡

Sovereign
Financing

Railway Corporate
Financing Financing On Balance
Sheet

Project
Off Balance
Financing
Sheet

ምስል 9፡ የባቡር ዘርፍ የመሠረተ-ልማተ ፋይናንሲንግ ሞዴል


አማራጮች
ከላይ በተቀመጠው ስዕላዊ መግለጫ መሠረት የባቡር መሠረተ-ልማት ግንባታና የባቡር ግዥ ፋይናንስ
በዋነኝነት በሦስት መንገዶች ይሸፈናል። የመጀመሪያው በመንግስት የሚሸፈንበት መንገድ (Sovereign
Financing) ነው፡፡ ሁለተኛውና ሦስተኛው ደግሞ ተቋማቱ በራሳቸውና ከግል ባለሃብት ጋር በጋራ
የመሠረተ-ልማትና የባቡር ግዥ ወጪን የሚሸፍኑባቸው መንገዶች ሲሆኑ ሶስትቱ መንገዶች የየራሳቸው
ባህሪ አላቸው፡፡

1. Sovereign Financing፦ ይህ የፋይናንሲንግ መንገድ ለባቡር መሰረ ልማት ግንባታና ለባቡሮች


ግዥ የሚያስፈልጉ ወጭዎች በሙሉ በመንግስት የሚሸፈንበት መንገድ ሲሆን፤ የባቡር ዘርፍ
ልማት ከፍተኛ ወጪን የሚጠይቅና የአጭር ጊዜ አትራፊነቱም ዝቅተኛ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ
በአለም ደረጃ በብዙ ሀገሮች በስፋት ተቀባይነት ያለውና እየተተገበረ ያለ መንገድ ነው፡፡ በዚህ ዘዴ
መንግስታዊ ባለቤት (በብዛት የፋይናንስ ወይም የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር)
ለፕሮጀክቱ የሚያስፈልገውን ገንዘብ ይበደራል፡፡ የፕሮጀክቱ አስፈጻሚ መንግስታዊ አካል በመሆኑ
የፕሮጀክቱ ስኬት (ወይም የኢንቨስትመንቱ ምላሽ - Return on Investment) የሚለካው
ፕሮጀክቱ በሚያመጣው የገንዘብ ምላሽ (Financial internal rate of return) ሳይሆን ለሃገሪቱ
በሚመነጨው ኢኮኖሚያዊ እና ማሕበራዊ ሃብት (Economic IRR & social welfare) አንጻር
ነው፡፡ ይህ መንገድ በአፍሪካም የተለመደ የፋይናንሲንግ አካሄድ ነው፡፡

44
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
2. Corporate Financing፦ በዚህኛው የፋናንሲንግ መንገድ ተቋማቱ በራሳቸው የተለያየ መንገድን
ተጠቅመው ፕሮጀክቶቻቸውን ፋይናንስ የሚያደርጉበት መንገድ ነው፡፡ ከእነዚህ የተለያዩ
የፋይናንሲንግ መንገዶች መካከል በራሳቸው ብድር መውሰድ፤ ኮርፖሬት ቦንድ ማቅረብ (መሸጥ)፤
የአክሲዮን ድርሻ (Equity) መሸጥ: ከተለያዩ ቢዝነሶቻቸው የሚያገኙትን ትርፍ መጠቀም እና
ሌሎችም ይገኛሉ፡፡ በኮርፖሬት ፋይናንሲንግ መንገድ ተቋማት ብድር የሚወስዱት ለአበዳሪዎች
ሙሉ ዋስትና በማቅረብ (ፕሮጀክቱ ብድሩን ባይከፍል ተቋሙ ዕዳውን የሚከፍልበት) ሲሆን ይህ
መንገድ አዋጭ የሚሆነው አትራፊነታቸው ከፍተኛ ለሆኑ ፕሮጀክቶች ብቻ ነው፡፡ ይህ ካልሆነ
ተቋማቱን ዕዳ ውስጥ የሚዘፍቅ ሲሆን በሌላ መንገድም ዕዳው በተቋሙ የፋይናንስ መዝገብ ላይ
የሚታይ (On Balace Sheet) በመሆኑ የተቋሙ የፋይናንስ አቋም ላይ ጫና ያሳድራል፡፡

ኮርፖሬት ቦንድ ለሽያጭ ማቅረብን በተመለከተ አትራፊ ፕሮጀክቶችን ለመተግበር አንዱ አማራጭ
ሲሆን ቦንድ ገዢ ማግኘት ከአጠቃላይ የተቋሙ የፋይናንስ ጥንካሬ ጋር የተገናኘ ነው፡፡ ይህን
የፋይናንሲንግ መንገድ ዕዳቸውን በአግባቡ ሊከፍሉ በማይችሉ ፕሮጀክቶች ላይ ከተተገበረ ከላይ
የተጠቀሱት የብድር ጫናዎችንም ይፈጥራል፡፡ የአክስዮን ሽያጭ በአክስዮን መልክ የተደራጁ
ተቋማት የአክስዮን ድርሻን (ሼር) በመሸጥ ፋይናንስ የሚያመነጩበት አካሄድ ሲሆን ይህን
ለማድረግ ተቋሙ አክስዮን ገዢዎችን መሳብ በሚያስችል የፋይናንስና የማናጅመንት ቁመና ላይ
መገኘት ይኖርበታል፡፡ ሌላው አካሄድ ደግሞ ተቋማቱ ከተለያዩ ቢዝነሶቻቸው የሚሰበስቡትን ትርፍ
ሌሎች ፕሮጀክቶችን ለማቋቋም ወይም ለመደገፍ የሚጠቀሙበት አካሄድ ነው፡፡ ከላይ
እንደተጠቀሰው የኮርፖሬት ፋይናንሲንግ አካሄድ አዋጭ የሚሆነው በከፍተኛ ደረጃ አዋጭ
ለሚሆኑ ፕሮጀክቶች (አንዳንድ ቢዝነስ ዩኒቶችና ትራንዚት ኦሬንትድ ልማቶች) እንጂ ለባቡር
መሠረተ-ልማት ግንባታ የሚመከር አይደለም፡፡

በሌላ በኩል የኢንዱስትሪ ተቋማት (በብዛት የማዕድን አውጪ ኩባንያዎች ወይም ፋብሪካዎች)
ከዋና መስመር ጋር ኢንዱስትሪያቸውን ለማገናኘት የሚያገለግሉ የራሳቸውን የተለዩ መስመሮች
(dedicated lines) ለመገንባት ይህንን አማራጭ ሊከተሉ ይችላሉ፡፡ የነዚህ መስመሮች
አስገንቢዎች የግል ኩባንያዎቹ በመሆናቸው የፕሮጀክቱ ስኬት በሚያመጣው የገንዘብ ምላሽ
(Financial internal rate of return) ላይ የተመሠረተ ነው፡፡

3. Project Financing፦ ይህ የፋይናንሲንግ መንገድ ደግሞ ተቋማት የፕሮጀክቱን የፋይናንስ ስጋት


በኩባንያቸው ውስጥ ላለመሸከም ከሕግም ሆነ ከፋይናንስ አንጻር ራሱን የቻለ የፕሮጀክት ኩባንያ
(Project Company) ወይም የልዩ ዓላማ መሣሪያ (Special Purpose Vehicle-SPV)
አቋቁመው ለአበዳሪዎች ፕሮጀክቱን ራሱን የቻለ ተበዳሪ ተቋም በማድረግ የሚያቀርቡበት መንገድ
ነው፡፡ ይህ የልዩ ዓላማ መሣሪያ (SPV) ተቋማት ከብድር አለመክፈል ጋር በተያያዘ ሊኖርባቸው

45
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
የሚችለውን የፋይናንስ ስጋት እንዲሁም በሂሳብ መዝገባቸው የማይመዘገብ (Off Balance
Sheet) በመሆኑ በፋይናንስ ሁኔታቸው ላይ የሚያደርሰውን ጫና ከሂሳብ መዝገባቸው ላይ
የሚያርቁበት መንገድ ነው፡፡

ይህ የፋይናንሲንግ አካሄድ ተቋማት ከግሉ ዘርፍ ባለሃብት አልሚዎች ጋር በተለያዩ የልማት


ጥምረት መንገዶች ማለትም መንግስት-ግል-አጋርነት (PPP)፤ ጆይንት ቬንቸር (JV); አክስዮን
ማህበርና ሌሎችንም በመጠቀም በጋራ ለማልማት ዕድል የሚሰጥ ነው፡፡ እንደማንኛውም ኩባንያ
የዚህ SPV እሴት ከካፒታል እና ከዕዳ የሚገነባ ሲሆን በአብዛኛው 80/20 ወይም 70/30 በሆነ
የዕዳ፡ካፒታል ምጣኔ የሚዋቀር ነው፡፡ ይህ የፋይናንሲንግ መንገድ ከፍተኛ የካፒታል ወጪ
በቅድሚያ ለሚጠይቅ እና የገቢ ፍሰታቸው በረጅም ጊዜ ለሚመነጭ የመሠረተ-ልማት
ኢንቨስትመንቶች በግል ባለሃብቶችም ሆነ በመንግስታት የተለመደ፤ በተለይም በመንግስተና-ግል-
አጋርነት (PPP) ኢንቨስትመንቶች ላይ የሚተገበር ነው፡፡ በባቡር መሠረተ-ልማት ፋይናንሲንግ
በአብዛኛው የኮንሴሽን ውሎች (ከሰሃራ በታች ባሉ አፍሪካ ሃገራት ጨምሮ) የሚተገበር
የፋይናሲንግ ዘዴ ነው፡፡

ለ. ለኢትዮጵያ የሚመከረው የባቡር መሠረተ-ልማት ኢንቨስትመንት ፋይናንሲንግ ሞዴል

የባቡር መሠረተ-ልማት ለሃገራዊ ዕድገት የሚያበረክተው ኢኮኖሚያዊ አስተዋጽዖ ለግንባታና ለባቡር ግዥ


ከሚወጣበት ወጪ ጋር ሲነፃጸር ኢኮኖሚያዊ አትራፊነቱ የሚያመዝን በመሆኑ የባቡር ኢንቨስትመንትን
በማክሮ ኢኮኖሚ ደረጃ ማየቱ ተገቢ ያደርገዋል፡፡ በመሆኑም የባቡር ሴክተሩ ለሃገራዊ ኢኮኖሚ ዕድገት
የሚያበረክተውን ከፍተኛ ሚና ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ እንዲሁም ከሌሎች የትራንስፖርት ሞዶች
(በተለይ መንገድ) እና ከሌሎች ሃገራት ልምድ በመቀመር የባቡር መሠረተ-ልማት ሃገራዊ የኢኮኖሚ
እሴት (Public Good) መሆኑ ላይ ሊታመንበት ይገባል፡፡

እንደ ከዚህ ቀደሙ ይህን ሃገራዊ መሠረተ-ልማት ለመዘርጋት የሚያስፈልገው ከፍተኛ የኢንቨስትመንት
ወጪ አንድ መንግስታዊ ተቋም በራሱ እንዲበደርና በአንድ መንግስታዊ የልማት ተቋም የሂሳብ መዝገብ
እንዲስተናገድ ማድረግ ተቋሙን በተከታታይነት በአሉታዊ የሂሳብ መዝገብ (Negative Balance Sheet)
እንዲሰጥም እና እንደ መንግስታዊ የልማት ድርጅት ዘላቂነት (Sustainability) እንዳይኖረው ያደርገዋል።
የዚህ ችግር ዋነኛ ምክንያትና ውጤት ደግሞ ከዚህ የሚከተለው ነው፡፡-

1ኛ. የመሠረተ-ልማቱ የእርጅና ተቀናሽ (depreciation) እና የወለድ ወጪ (interest expense)


በተከታታይ እየተሠላ ከገቢው ላይ የሚቀነስ በመሆኑ ተቋሙን አክሳሪ የሚያደርገው መሆኑ፣

46
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
2ኛ. ይህ ደግሞ ካፒታሉን በፍጥነትና በተከታታይ እየቀነሰው ስለሚሄድ በተከታታይ የካፒታል
ማሳደግ ሥራ መንግስትን የሚጠይቅ መሆኑ፣

3ኛ. የተቋሙ የሂሳብ መዝገብ (Income Statement and Balance Sheet) በከፍኛ ደረጃ በዕዳ
የተዘፈቀ ስለሚሆን በአበዳሪዎች ዘንድ ተዓማኒነት (credit worthiness) እንዳይኖረው
ያደርጋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ ሁሉንም የፋይናንስ ጫና መንግስት ላይ መጣሉ ተገቢ አለመሆን እንዲሁም መንግስት
በመንግሥት ባለቤትነት የተያዙ ድርጅቶች ከግል ድርጅቶች ጋር በግልጽ ውድድር መሥራት የሚችሉበትን
አቅም ለማጠናከርና ምርታማነታቸውንና ትርፋማነታቸውን ለመጨመር በተጨማሪም ለንግድ ያላቸውን
አመለካከት የሚቀይር አመቺ አሠራርን እየቀረጸ ከመሆኑ አንጻር የባቡር ዘርፉ በአንድ የፋይናንሲንግ
አካሄድ ላይ ብቻ ተወስኖ መንቀሳቀስ አይኖርበትም፡፡ ይልቁንም በውድድሩ ሜዳ አሸናፊ አድርጎ ሊያወጣው
የሚችለውን የፋይናንሲንግ መንገዶች ስብጥር መጠቀሙ የሚመረጥ ይሆናል፡፡ በመንግስት በኩል ግን
ከዚህ ቀደም ለተገነቡትና በግንባታ ላይ ላሉት መስመሮች ዝርጋታ የወጣውን የብድር ወጪ ከባቡር
ሴክተሩ ጫንቃ ላይ ለማንሳትና የኢምባኮን የሂሳብ መዝገብ ጤናማ ለማድረግ የጀመረውን ሥራ በመቀጠል
የውጭ አገር ብድሩን በማንሳት ተወዳዳሪ የልማት ተቋም የሚሆንበት የፋይናንስ አቋም እንዲይዝ ማድረግ
ይኖርበታል፡፡

ሰንጠረዥ 6፡ ፋይናንሲግ ሞዴል ስብጥር

ከላይ የተመለከተውን (ሰንጠረዥ 6) የፋይናንሲንግ ስብጥር አካሄድ በመከተል፡

የባቡር መሠረተ-ልማት ዝርጋታና ኦፕሬሽንን በተመለከተ

47
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
1. በዋናነት በመንግስት ላይ ያለውን የበጀት እጥረት ጫና መቀነስ እንዲያስችል የባቡር መሠረተ-
ልማት ዝርጋታና ኦፕሬሽንን ሥራ ዘርፉን ለግል ባለሃብቱ ኢንቨስትመንት ምቹ ባማድረግ
በመንግስት-ግል-አጋርነት (PPP) በመጠቀም በፕሮጀክት ፋይናንሲን መንገድ የሚለማ ይሆናል፡፡

2. ዘርፉ በአሠራርና በአቅም ጎልብቶ የግሉን ባለሃብት ዘርፍ በሚፈለገው ደረጃ መሳብ እስከሚችል
ድረስ መንግስት እንዲገነቡለት የሚፈልጋቸው የባቡር መሠረተ ልማቶች ሲኖሩና ለዚህም
አስፈላጊውን በጀት ካቀረበ በሶቨሪን ፋይናንሲንግ አካሄድ የሚለማ ይሆናል፡፡ እንዲሁም አሁን
በመገንባት ላይ ያሉና ወደ ኦፕሬሽን ያልገቡ እንዲሁም ወደፊት በሚገነቡት የባቡር መሠረት
ልማቶች ላይ ኢምባኮየኦፕሬሽን ሥራዎችን በብቸኝነት እንዲያከናውን ከተፈለገ ይህም የሶቨሪን
ፋይናንሲንግ አካሄድን የሚከተል ይሆናል፡፡

በራስ ሃይል የሚሠሩ ቢዝነሶችን በተመለከተ፡ እነዚህ ሥራዎች ዘርፉ ለዓመታት ይዟቸው ነገርግን
ሳይጠቀምባቸው የቆዩትን የተለያዩ በርካታ ሃብቶችን በመጠቀም በራስ ሃይል ገቢ ለማመንጨት ቀርፆ
እየተንቀሳቀሰ የሚገኝባቸው የቢዝነስ ሥራዎች ናቸው፡፡ እንደተገለፀው እነዚህ የቢዝነስ ሥራዎች በዘርፉ
ያለ ሃብትን በዋናነት የሚጠቀሙና ተጨማሪ ከፍተኛ ኢንቨስትመንት የማይጠይቁ በመሆናቸው ሥራዎቹ
የሚጠይቁትን መጠነኛ ኢንቨስትመንት በኮርፖሬት ፋይናንሲንግ አካሄድ በመጠቀም የሚሠሩ ይሆናሉ፡፡

ቲኦዲና ሌሎች ቢዝነሶችን በተመለከተ፡ እነዚህ ቢዝነሶች በዋናነት ታሳቢ የሚያደርጉት በዘርፉ የሚገኙ
የተለያዩ ሃብቶችና ዕድሎችን የግሉን ዘርፍ ባለሃብት አልሚዎችን በመጋበዝ የሚለሙ ትላልቅ ቢዝነሶችን
ነው፡፡ በእነዚህ ቢዝነሶች የግሉ ባለሃበት ዘርፍ ፋይናንስ፤ ልምድና ተሞክሮ፤ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን
በከፍተኛ ደረጃ የሚፈለግባቸው እንደ እንዶዴ ሎጅስቲክ ፖርት ያሉት ቢዝነሶች ናቸው፡፡ እነዚህን የቢዝነስ
ሥራዎች እንደ ተጨባጭ ሥራው ባህሪ በሚደረግ የአዋጭነት ጥናት መሠረት በኮርፖሬት ፋይናንሲንግና
በፕሮጀክት ፋይናንሲንግ አካሄዶች የሚለሙ ይሆናሉ፡፡

4.2.2 የኦፕሬሽን ወጪን ገቢ ወጪ ሚዛንን በተመለከተ

የባቡር ሴክተር የፋይናንስ አቋም በዘላቂነት የተስተካከለ እንዲሆን ለማድረግ በኦፕሬሽን ወጪና ገቢ
ሚዛን ላይ ትኩረት ሰጥቶ መሥራት ያስፈልጋል፡፡ ሃገራችን ዘመናዊ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት
እየተለማመደች ያለችበት ወቅት ከመሆኑ አንጻር በአዲስ አበባ ቀላል ባቡርም ሆነ በአዲስ አበባ - ሚኤሶ
- ደወንሌ የባቡር መስመሮች የኦፕሬሽን ማኔጅመንት ኮንትራክተር በመቅጠር የእውቀት ሽግግር ላይ
ያለንበት ወቅት ከመሆኑ አንጻር ከፍተኛ ወጪ ለማኔጅመንት ኮንትራክተር ይከፈላል፡፡ በተጨማሪም
የመደበኛ፣ ድንገተኛ እና አጠቃላይ ጥገና እንዲሁም የመለዋወጫ ግዢ ወጪዎች ከፍተኛ ናቸው፡፡

48
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
የኃይል ግብዓት እና የሰው ኃይል ክፍያም ከአገልግሎት ወጪ ይካተታሉ። አነዚህና ሌሎችም ያልተጠቀሱ
ዝርዝር የኦፕሬሽን ወጪዎች ከትኬት በሚገኘው ገቢ ብቻ ሊሸፈኑ አይችሉም፡፡

በሌላ በኩል የባቡር ትራንስፖርት ታሪፍ ላይ ለማህበራዊ ጥቅም ሲባል በመንግስት የትኬት ቁጥጥር
የሚደረግ በመሆኑ ዘርፉ አዋጭ የሚያደርገውን ታሪፍ የሚያወጣበት የንግድ ነጻነት የለውም፡፡ ወጪውን
የሚሸፍንለትን ታሪፍ ያውጣ ቢባልም እንኳ ከወጭው አንጻር እጅግ ከፍተኛ ስለሚሆን ሴክተሩን ከገበያ
ውድድር ያገልለዋል፡፡ በመሆኑም የባቡር ትራንስፖርት የኦፕሬሽን ወጪውን አንዲሸፍን፤ በሂደት ደግሞ
ገቢውን ከወጪው የተሻለ በማድረግ ትርፋማ እንዲሆን ለማስቻል ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ማከናወን
ይጠቅማል፡፡

ሀ. የባቡር መንገደኛ ትራንስፖርትን በተመለከተ

የባቡር ትራንስፖርት ለማህበረሰቡ የሚሰጠውን ጥቅም ከግምት ውስጥ በማስገባት በገቢውና በኦፕሬሽናል
ወጪው መካከል ያለውን ጉድለት በድጎማ መልክ እንዲሞላ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ይህ ሲሆን ግን
አገልግሎቱን በውጤታማነት ለመስጠት የሚያስፈልገውን ወጪ ከሴክተሩ ጋር በጥልቀት አጥንቶ
በመተማመን መለየት የአሠራር ክፍተት (inefficiency) በድጎማ ውስጥ እንዳይካተት ለማድረግ ይረዳል።
የባቡር መንገደኞች ድጎማ በሶስት መንገዶች ሊከናወን ይችላል፡፡ ይኸውም፡

• በትራንዚት ኦሬንትድ ልማትና ሌሎች ቢዝነሶች ከሚገኝ ገቢ


• የባቡር ጭነት ትራንስፖርትን ትርፋማ በማድረግ ከሚገኝ ገቢ
• ከከተማ አስተዳደሮች (ለከተማ ውስጥ ባቡር) እና ከፌደራል መንግስቱ (ለአገረ አቀፍ ባቡር)
ከሚገኝ ድጎማ

ለ. የባቡር ጭነት ትራንስፖርትን በተመለከተ

የባቡር የጭነት ትራንስፖርት ከባህርይው አንጻር ለረጅም ርቀት የጭነት ትራንስፖርት አዋጭ በመሆኑ
በሃገሪቱ የጭነት ትራንስፖርት ገበያ አስፈላጊውን ምቹ የመወዳደሪያ አካባቢ በመፍጠር በራሱ ተወዳድሮ
አትራፊ መሆን የሚችልበት ደረጃ ላይ እንዲደርስ ስትራቴጂ በመቅረፅ መሥራት ይገባል፡፡

49
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
5 ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች

የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ከላይ እንደተጠቀሰው በሦስት አበይት የዕድገት ምዕራፎች አልፎ ላለንበት
ደረጃ የበቃ ሲሆን ወቅታዊ የሴክተሩን ዋነኛ ተግዳሮቶች የለየ፣ የዓለም አቀፍ ባቡር ሴክተሩን ልምድ
የቀመረ እና የወደፊት አድማሱን ያገናዘበ ስትራቴጂያዊ አቅጣጫ መከተል ይኖርበታል።

ከዓለም አቀፍ የባቡር ዘርፍ ታሪካዊ ሂደት እና ምርጥ ተሞክሮ እንዲሁም ከኢትዮጵያ የባቡር ዘርፍ
የእስካሁን ጉዞ እና ከአካባቢያዊ ትንተና በመነሳት በመጪዎቹ ጊዜያት የባቡር ዘርፉ አተኩሮ ሊሠራባቸው
የሚገቡ ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች ተለይተዋል።

በዚህም መሠረት ስትራቴጂያዊ ፍኖተ ካርታው እርስ በርስ በመደጋገፍ የባቡር ዘርፉን ውጤታማ
በማድረግ ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ለማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ የተቀናጀ 2*2*2 ስትራቴጂ ሆኖ
ተቀርጿል። ይህም ሁለት ቁልፍ (ፈጣን ምላሽ የሚሹ) ፣ ሁለት መሠረታዊ፣ እንዲሁም ሁለት አበይት
ስትራቴጂያዊ የትኩረት አቅጣጫዎችን፤ በአጠቃላይ ስድስት ስትራራጂያዊ ጉዳዮችን የያዘ ነው።

እነዚህም፡-

 ቁልፍ ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች፡-

• ዘላቂ የፋይናንስ አቅም መፍጠር፣

• የዘርፉን ገቨርናንስ ሥርዓት ማጠናከር፣

 መሠረታዊ ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች፡-

• ጠንካራ የሃገራዊ ባቡር ዘርፍ አቅም፣

• አስተማማኝ የባቡር ደኅንነትና ጸጥታ፣

 አበይት ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች፡-

• ዘላቂ የመሠረተልማት ሃብት፣

• ውጤታማ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ናቸው።

ምስል 10፡. የባቡር ዘርፉ ፎኖተ-ካርታ


ስትራቴጂዎች

50
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
ቁልፍ ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች

ቁልፍ ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች የተባሉት የባቡር ዘርፉ ያሉበትን እጅግ ፈታኝ ሁኔታዎች ለመፍታት በሚል
የተለዩ እና ስትራቴጂያዊ ምላሽ ከተሰጠባቸው ዘርፉን በዘላቂነት በስኬት ለማስቀጠል መሠረት የሚጥሉ
በመሆናቸው ነው። በተጨማሪም ስትራቴጂያዊ ጉዳዮቹ ፈጣን ምላሽ የሚሹ ሲሆኑ፤ በትግበራም ደረጃ
እነዚህ ጉዳዮች በቅድሚያ ካልተከናወኑ የዘርፉ ፈተናዎች ባሉበት የሚቀጥሉበት ዕድል ከፍተኛ በመሆኑ
ለዘርፉ ውጤታማነት ቁልፍ ሚና አላቸው።

5.1.1 ዘላቂ የፋይናንስ አቅም መፍጠር

የባቡር መሠረተ-ልማትም ሆነ ተንቀሳቃሽ ሀብት ከፍተኛ የካፒታል አቅም የሚጠይቁ መሆናቸው፤


በተጨማሪም በትራንስፖርት አገልግሎት በሚገኘው ገቢ የካፒታል ኢንቨስትመንቱን መሸፈን አዳጋች
በመሆኑ፤ ማንኛውም መንግሥት በባቡር ዘርፍ የፋይናንስ ጉዳይ ላይ የተለየ ትኩረት እንዲያደርግ
የሚያደርጉ የባቡር ዘርፍ ዋነኛ ባህርያት ናቸው።

በተለይም የባቡር ትራንስፖርት መኖር ለሀገር አጠቃላይ የኢኮኖሚ ዕድገት፣ ለማኅበራዊ አገልግሎቶች
መስፋፋትና ለኢንዲስትሪዎች መጠናከር፣ ከጎረቤት ሀገራት ጋር የሚኖርን የንግድ ልውውጥ ለማሳለጥ፣
በተጨማሪም ለተፈጥሯዊ አካባቢ መጠበቅ (ዘመናዊው የባቡር ቴክኖሎጂ) ያለው ከፍተኛ ፋይዳ የባቡር
ዘርፍን ከፋይናንስ ውጤታማነቱ ይልቅ ከኢኮኖሚ ጠቀሜታው አንፃር መታየት እንዳለበት ዓለም አቀፋዊው
ተሞክሮው ይጠቁማል። በመሆኑም የመሠረተ-ልማት ግንባታና ተያያዥ ወጪዎች የሚገመገሙት
ከሚያስገኙት የኢንቨስትመንት የፋይናንስ ምላሽ (Financial Return On Investment) ሳይሆን አጠቃላይ
አገራዊ የሆነ የኢኮኖሚያዊ ምላሽን (Economic Return On Investment) በመመልከት ነው።

በኢትዮጵያ የባቡር ዘርፍ ላይ የተከተልነው የፋይናንሲንግ ሞዴል በዓለም አቀፍ ካለው ምርጥ ተሞክሮ
ጋር የማይገናኝ በመሆኑ ማሻሻያ ሊደረግበት እንደሚገባ እንዲሁም ከዚህ ጋር ተያይዞ በዘርፉ ባህርይ
ምክንያት የመጡ የፋይናንስ ጫናዎችም ላይ ስትራቴጂያዊ መፍትሔ መሰጠት እንደሚገባው መረዳት
ይቻላል። በዚህም መሠረት የዘርፉን የፋይናንስ አቅም ጠንካራና ዘላቂ ለማድረግ ከዚህ በታች የተገለፁት
ስትራቴጂያዊ አቅጣጫዎች ተለይተዋል።

1ኛ. በዘርፉ የፋይናንስ መዋቅር ላይ ማስተካከያ ማድረግ፡ በዚህ ስትራቴጂያዊ አቅጣጫ ሥር ከዚህ
በፊት የተከተልነውን የፋይናንሲንግ አካሄድ ማለትም የባቡር መሠረተ-ልማትን ለመገንባት ዘርፉ በራሱ
የአገር ውስጥና የውጭ አገር ብድርን በመውሰድ ለከፋ የፋይናንስ ቀውስ መዳረጉ ይታወቃል።
በመሆኑም ይህንን የፋይናንሲንግ አሠራር በመቀየር ዘርፉ ከግሉ ዘርፍ አልሚዎች ጋር በመተባበር
በፕሮጀክት ፋይናንሲንግ አማራጭ የመሠረተ-ልማት ግንባታን ለማከናወን የሚሰራ ሲሆን ፤

51
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
ከመንግስት የመሠረተ-ልማት ግንባታ ጥያቄ የሚቀርብ ከሆን ግን ሶቨሪን ፋይናንሲንግን (Soveriegn
financing) በመጠቀም የሚገነባ ይሆናል።

በተጨማሪም እስካሁን ለመሠረተ-ልማት ግንባታ ፋይናንሲንግ የተወሰደውን የአገር ውስጥና የውጭ አገር
የብድር ጫና ከዘርፉ የሂሳብ መዝገብ ለማንሳት የተጀመረው እንቅስቃሴ ተጠናሮ መቀጠል ይኖርበታል።
ይኸውም ተመሳሳይ ከፍተኛ የብድር ጫና ያለባቸውን የመንግስት የልማት ተቋማት ከዕዳ ነጻ ለማድረግ
የተቋቋመ የዕዳና ሃብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን መኖሩ ሲሆን የባቡር ዘርፉ የአገር ውስጥ ዕዳ ወደ
ተቋቋመው ኮርፖሬሽን ተዘዋውሯል ነገር ግን በዋነኛነት የዘርፉ ፋይናንስ ጫና የሆነው የውጭ አገር ዕዳ
እስካሁን ባለመዘዋወሩ አስቸኳይ ውሳኔ ተሰጥቶበት እንዲዘዋወር መደረግ ይኖርበታል።

2ኛ. የዘርፉን እምቅ ሃብት በመጠቀም ገቢ ማመንጨት፡ በባቡር ዘርፉ ለረጅም ጊዜ በስራ ላይ ያልዋለ
በጣም በርካታ የሰውና ቁሳዊ ሃብት ይገኛል። ይህንን ሃብት ወደ ሥራ አስገብቶ ገቢ ለማመንጨት
የሚያስችል የገቢ አመንጪነት አስተሳሰብ (Business mindset) ያለመኖርና በቂ ትኩረት ያለመስጠት
የነበረ ሲሆን አሁን ላይ ሊያድግና ሊሰፋ የሚገባው የዘርፉን ሃብት ተጠቅሞ ገቢ የማመንጨት እንቅስቃሴ
ጅምር አለ። በቀጣይ ይህንን ጅምር በማሳደግ ዘርፉ ማግኘት የሚገባውን ገቢ ማመንጨት ይችል ዘንድ
በዘርፉ ከመንግስት ፋይናንስ ጥገኝነት ተላቆ በራስ ሃይል ገቢ የማመንጨትን አስተሳሰብ ማስረጽ፤ለሥራው
ከፍተኛ ትኩረት መስጠትና ዕንቅፋቶችን በማስወገድ ምቹ መደላድል መፍጠር ግድ ይላል። በተጨማሪም
እንደ Transit Oriented Development (TOD) እና ሌሎች የገቢ ማመንጫ ሥራዎች (Buisiness
Units) ላይ የግሉን ዘርፍ አልሚዎች በመጋበዝ በተሻለ አፈጻጸም የተሻለ ገቢ ለማመንጨት በትጋት
መሠራት ይኖርበታል።

በዘርፉ በዋናነት በኮንስትራክሽን፤ በዲዛይንና ማማከር፤ የመሠረተ-ልማትና የባቡሮችን መለዋወጫ እቃ


ግብዓት ማምረት ፣ በሎጂስቲክስ ፖርት፤ በፋሲሊቲ ኪራይ አገልግሎት፤ እና በመልቲ ሞዳል
ትራንስፖርት በቢዝነስ ዩኒት መልክ ተደራጅተው እንቅስቃሴ የጀመሩ ሲሆን በተጨማሪም በተለያየ መልኩ
በትራንዚት ኦሬንትድ ልማት ሊለሙ የሚችሉ በርካታ የዘርፉ የሆኑ በባቡር መሰረት ልማቱ አቅራቢያ
የሚገኙ መሬቶች፤ ስቴሽኖች፤ እና ካምፖች አሉ። ከላይ እንደተገለጸው እነዚህን ሃብቶች በራስ ሃይልና
ከተለያዩ አልሚዎች ጋር በመቀናጀት በማልማት የዘርፉን አቅም ለማሳደግ አስፈላጊውን ቅድመ ሁኔታ
ሁሉ በማሟላት በስፋት ወደ ሥራ መግባት ተጀምሯል።

3ኛ. የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ ማሳደግ፡ ለግሉ ዘርፍ አልሚዎች የኢትዮጵያ መንግሥት እየተከተለ ካለው
ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ጋር በተጣጣመ መልኩ ለኢንቨስትመንት ምቹ የሆነ ከባቢን በመፍጠር
በባቡር መሠረተ-ልማት ግንባታና አስተዳደር፤ በባቡር ተንቀሳቃሽ ሀብት (Rolling Stock) ግዢና ኦፕሬሽን
ሥራ ላይ እንዲሁም በሌሎች የዘርፉ ገቢ አመንጪ ሥራዎች ኢንቨስትመንት ላይ የግል ባለሀብቱን
ተሳትፎ እንዲኖር በማድረግ በሂደት ከ Sovereign Financing መውጣት ይገባል። ለዚህም የመንግሥትና

52
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
የግል አጋርነት (PPP) ላይ የተመረኮዘ የProject Financing /Off-balance sheet Financing/ ጨምሮ
ሌሎች ተስማሚ የፋይናንሲንግና የቢዝነስ ሞዴሎችን በመተግበር የዘርፉን የፋይናንስ አቋም ዘላቂና
ጠንካራ ማድረግ ያስፈልጋል። በተጨማሪም ከግሉ ዘርፍ በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን፤ በተቀናጀ ስጋት
አስተዳደር፤ በወጪ ቅነሳ፤ በደንበኞች አገልግሎትና ሌሎችም የሚገኘው ልምድና ተሞክሮ ዘርፉ
ለሚያደርገው ዘላቂ ልማትና የፋይናንስ አቅም መጎልበት ጥረት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።

4ኛ. የኦፕሬሽን ፋይናንስ ተግዳሮቶችን መፍታት፡ በመንገደኛ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚገኘው ገቢ


እምበዛም ከመሆኑም በላይ የታሪፍ ቁጥጥር ስለሚደረግበት አገልግሎቱን ለመስጠት የሚወጣውን ወጪ
(Operational Expense) እንኳን ለመሸፈን የማይቻል መሆኑ ሌላው የባቡር ዘርፍ ባህሪይ ነው።

በዚህም የተነሳ የዓለም ሀገራት የመንገደኛ ባቡር ትራንስፖርት አገልግሎትን በሶስት መንገድ ይደጉማሉ
የመጀመሪያው ለከተማ ውስጥ የባቡር አገልግሎት ከተማውን የሚያስተዳድረው ግዛት የሚደጉምበት፣
ሁለተኛው በባቡር ጭነት ትራንስፖርት ከሚገኘው ትርፍ የመንገደኛ ትራንስፖርት አገልግሎት ወጪ
እንዲደጎም የሚደረግበት ዘዴ ሲሆን ሶስተኛው አማራጭ ደግሞ የባቡር መስመሩን ተከትሎ በሚለሙ
ትራንዚት ኦሪየንትድ ልማቶች (TOD) በሚገኝ ገቢ የመንገደኛ ትራንስፖርት አገልግሎትን ይደጎማል።

በሀገራችንም የመንገደኛ ባቡር ትራንስፖርትን በተመለከተ ተመሳሳይ ሁኔታ ያለ ቢሆንም በትኬት ገቢውና
በወጪው መካከል ያለውን ክፍተት በመንግሥት ብቻ እንዲደጎም ማድረጉ በአሁን ሰዓት በመንግስት ላይ
ያለውን ጫና እንደሚያባብስ ከግምት በማስገባት ድጎማው በዋናነት ከጭነት ትራንስፖርት ፤ትራንዚት
ኦሪየንትድ ልማቶች (TOD) ወይም ሌሎች ተዛማጅ የቢዝነስ ስራዎች ከሚገኙ ገቢዎች መደጎም
ይኖርበታል። የባቡር ሎጅስቲክስና ጭነት ትራንስፖርትን በተመለከተ ግን ምቹ የመወዳደሪያ መድረክ
ስለተፈጠረ ከሌሎች የትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አከናዋኞች ጋር ተወዳድሮ ገበያ በማግኘት በኦፕሬሽን
ረገድ ትርፋማ (Operationally Profitable) የሚሆንበት ዕድል ሰፊ ነው።

ከዚህ ጋር በተያያዘ የሎጂስቲክስና የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት በፍትሃዊ ውድድር ለማካሄድ


እንዲቻል በ ኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን መመሪያ ቁ 802/2013 መሰረት በመልቲ-ሞዳል
ትራንስፖርት ላይ የባቡር ዘርፉ ከጭነት ምንጭ እስከ መድረሻው የጭነት ትራንስፖርት አገልግሎትን
ከሎጂስቲክስ ጋር አቀናጅቶ እንዲያቀርብ የፖሊሲ ማሻሻያ መደረጉ ይታወቃል። ይህን ተከትሎ የብቃት
ማረጋገጫ ከማሪታይም ባለስልጣን በማውጣት በዘርፉ ላይ ለመሰማራት የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት
ስራ ተጠናቋል። በመሆኑም የብቃት ማረጋገጫ ፍቃዱ እንደተገኘ ወደ ስራ በመግባት የሴክተሩን የፋይናንስ
አቋም መደገፍ የሚቻልበት እድል ይሰፋል። በተጨማሪም በዘርፉ የፕሮጀክት ፋይናንሲንግ ሞዴልን
በመጠቀም የእንዶዴ ሎጅስቲክስ ፖርትን ለማልማት ሥራ የተጀመረ ሲሆን ይህን ፕሮጀክት በማጠናቀቅ
እንዲሁም ሌሎች የትራንዚት ኦሬንትድ ልማቶችን በመስመሩ በማከናወን የመስመሩን ኦፕሬሽን ስራ
ውጤታማነት በማጎልበት በተጓዳኝ ፋይናንሱን ለማሻሻል ከፍተኛ ዕድል ይፈጥራል።

53
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
5ኛ/ ከዘርፉ የ Climate Finance ገቢ ማመንጨት ፡ በኢትዮጵያ ተግበራዊ እየሆነ ያለው የባቡር
ቴክኖሎጂ /Mitigation Project/ ከታዳሽ ኃይል የሚገኝን የኤሌክትሪክ ሃይል በስፋት የሚጠቀም ነው፡፡
የታዳሽ ሃይልን የሚጠቀም የባቡር ትራንስፖርት የበካይ ጋዝ ልቀትን በመቀነስ የሚያበረክተው አውንታዊ
አስተዋጽዎ ከፍተኛ ነው። የዘርፉ የበካይ ጋዝ ልቀት የመቀነስ አቅምን /Emission Reduction
Potentials/ በተጨባጭ የሚያረጋግጡ /MRV/ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ፣ በመተግበር እና በአለም አቀፍ
የካርበን ክሬዲት ገበያ ወይም Climate Finace በመሸጥ ከዘርፉ ተጨማሪ ገቢ ማመንጨትና የፋይናንስ
አቅሙን ማሳደግ ይቻላል፡፡

ተ.ቁ ዋና ዋና ሊከናወኑ የሚከናወኑበት አተገባበር ፈጻሚ


የሚገባ ተግባራት ጊዜ
እስከመቼ?
1 በዘርፉ የፋይናንስ 2016 2016 የዘርፉ የፕሮጀክት ፋይናንሲንግ መዋቅርን ወደ ኢምባኮ ፤
መዋቅር ላይ ፕሮጀክት ፋይናንሲንግ (Project Financing) እና ገንዘብ ሚኒስቴር
ማስተካከያ ማድረግ ሶቨሪን ፋይናንሲንግ (Sovereign Financing) መቀየር

2016 2017 ከዚህ ቀደም ለግንባታ የወጣውን የውጭ ሀገር ብድር ገንዘብ ሚኒስቴር
ወደ እዳና ሀብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን በማዘዋወር
የዘርፉን የሂሳብ መዝገብ ጤናማ ማድረግ

2 የዘርፉን እምቅ ሃብት 2016 2030 የገቢ አመንጪነት አስተሳሰብ በዘርፉ ማስረጽ ኢምባኮ
በመጠቀም ገቢ የገቢ ማመንጨት ስራ ላይ ያሉ እንቅፋቶችን
ማመንጨት ማስወገድ
በገቢ አመንጪንት ስራ ላይ በስፋት መግባት
3 የግሉን ዘርፍ ተሳትፎ 2016 2030 በቀጣይ ለሚገነቡ ፕሮጀክቶችና የቢዝነስ ስራዎች ትራንስፖርትና
ማሳደግ የመንግስትና የግል አጋርነት (PPP) እና ሌሎች ሎጂስቲክስ
ፋይናንሲንግ መንገዶችን በመጠቀም የጎለበተ የባቡር ሚኒስቴር፣ ገንዘብ
ዘርፍን መፍጠር ሚኒስቴር፣ የባቡር
ዘርፍ

4 የኦፕሬሽን ፋይናንስ 2016 2022 የመንገደኛ ትራንስፖርት አገልግሎትን በትራንዚት ገንዘብ ሚኒስቴር፣
ተግዳሮቶችን ኦሪየንትድ ልማት ፣ በጭነት ትራንስፖርት የከተማ
መፍታት አገልግሎት እንዲሁም መንግስት መደጎም አስተዳደሮች ፤
የባቡር ዘርፍ
2016 2022 የመልቲሞዳል ጭነት ትራንስፖርትን ለባቡር ዘርፍ ትራንስፖርትና
ክፍት የሚያደርግ የፖሊሲ ማሻሻያ በመደርጉ ሎጂስቲክስ
አስፈላጊውን ፎርማሊቲ በመጠቀም ወደስራ መግባት ሚኒስቴር፣ ገንዘብ
ሚኒስቴር፣ የባቡር
ዘርፍ
5 ከዘርፉ የClimate 2016 2030 የዘርፉ የበካይ ጋዝ ልቀት የመቀነስ አቅምን ኢምባኮ
Finance ገቢ /Emission Reduction Potentials/ በተጨባጭ የኢትዮጵያ የአካባቢ
ማመንጨት የሚያራግጡ /MRV/ ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ፣ ጥበቃ ባለስልጣን
በመተግበር እና በአለም አቀፍ የካርበን ክሬዲት ገበያ ገንዘብ ሚኒስቴር፣
ወይም Climate Finance በመሸጥ
ሰንጠረዥ 6፡ የዘላቂ የፋይናንስ አቅም መፍጠር ስትራቴጂያዊ አቅጣጫ የጊዜ ሰሌዳ

54
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
5.1.2 የዘርፉን ገቨርናንስ ሥርዓት ማጠናከር

ከዓለም ዓቀፍ ተሞክሮ እንደምንረዳው የየትኛውም ውጤታማ የባቡር ዘርፍ የያዘ ሀገር ስኬት መነሻዎች
አንዱ የዘርፉን የእሴት ሠንሠለት ሥራዎች ውጤታማ በሆነ መንገድ አደራጅቶ በጥበብ የተመራበት
መንገድ ነው። የዓለም ዓቀፍ የባቡር ዘርፉ የለውጥ ሂደት ትንተና (ምዕራፍ ሁለት) ላይ የተገለፀው የዘርፉ
ታሪክም የሚያስረዳው ይሄንኑ ነው።

በሀገራችንም ለባቡር ዘርፉ አዲስ ባንሆንም ውጤታማ የሰው ኃይል፣ ቁሳዊና የፋይናንስ ሀብት አጠቃቀም
ላይ ድክመት የነበረ በመሆኑ የስታንዳርድ ጌጅ የኤሌክትሪክ ባቡር ዝርጋታ እንደ አዲስ ለመጀመር
ተገደናል። ይህ በቀጣይም የሚደገም ታሪካዊ ክስረት እንዳይሆን የዘርፉ ቢዝነስ ሞዴል ላይ ዘርፉን
በውጤታማነት የሚያስቀጥለውን በመምረጥ ካሁኑ ቅርፅ ማስያዝ ያስፈልጋል።

ለዚህም በተመረጠው የባቡር ዘርፍ ሞዴል መሰረት ስራዎችን ከ 2016 ዓም ጀምሮ ወደመሬት ማውረድ
ይቻል ዘንድ ይህም የዘርፉን የመንግስት ክንፍ ወደፊት ከሚመጡ የግል ዘርፍ የባቡር ሴክተር ተዋናዮች
ጋር ተወዳዳሪ የሚያደርጉ የዘርፉን የፋይናንስ ጫና ከዘርፉ ላይ በማንሳት ፣ የሴክተሩ ዋና ዋና አካልትን
አደረጃጀት በመወሰን፣ ጠንካራ የባቡር ዘርፍ ተቆጣጣሪ አካልን በማቋቋም ዘርፉን ለውጤታማነት
በሚያመቻች መሠረት ላይ ማስቀመጥ የሚሉ ስትራቴጂያዊ አቅጣጫዎች ተለይተዋል።

እነዚህ ስትራቴጂያዊ አቅጣጫዎችን ለመተግበር በየጊዜ ምዕራፉ የሚከናወኑ ዝርዝር ጉዳዮች ከዚህ በታች
በተቀመጠው ሰንጠረዥ ውስጥ ተብራርተው ተቀምጠዋል።

55
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
ተ ቁ አደረጃጀቱ ውስጥ የሚኖሩ ዋና ዋና የ ጊዜ ገደብ የሚጠበቁ ዋና ዋና ስራዎች ፈጻሚ
ተዋናዮች
1 • ኢምባኮ 2016_ • አዲሱን የሴክተር አደረጃጀት ማጽደቅ ትራንስፖርትና
(Vertically Integrated) 2017 • የዘርፉን ተቆጣጣሪ አካል ማቋቋም ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር
• የኢምባኮ ና የኢዲአር ግንኙነት በተመለከት በአፈጽጸም ላይ የታዩ ፤ ኢምባኮ
ክፍተቶችን በማረም ግልጽ የሆነ የአክሲዮን ድርጅት ገቨርናንስ
እንዲከተል ማስቻል
• በከተሞች የሚኖሩ የቀላል ባቡርና የሜትሮ አገልግሎቶች ግንባታና
ኦፕሬሽን ከኢምባኮ ጋር የሚኖር ግንኙነት የሚወስን የህግ ማዕቀፍ
ማዘጋጀት
• የተለያዩ በመንግስትና በግሉ ዘርፍ 2016_ • በኢምባኮ ስር የሚገኙትን የቢዝነስ ዩኒቶች በራስ ሃይልና ኢምባኮ
የሚለሙ ባቡር ነክ ቢዝነሶች 2030 በመንግስት ግል አጋርነት የማልማት ስራዎችን ማስቀጠል

2 • ኢምባኮ 2016_ • በመንግስት የኢኮኖሚ አቅጣጫ መሰረት ወደ ግሉ ዘርፍ ትራንስፖርትና


(Competitive Access Model) 2025 ለመተላለፍ ዝግጁ የሆኑ የሴክተሩ ተዋናዮችን ማብቃት ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር
• የተለያዩ በመንግስትና በግሉ ዘርፍ • የግሉ ዘርፍ የሚገባባቸውን የሴክተሩ ክንፎች ተወዳዳሪነት ፤ ኢምባኮ
የሚለሙ ባቡር ነክ ቢዝነሶች መጨመር
• የግሉ ዘርፍ ኦፕሬተሮች • በግሉና በመንግስት ዘርፎች መካከል ፍትሃዊ አሰራርን የሚያሰፍን
ጠንካራና የተደራጀ የባቡር ተቆጣጣሪ አካልን መፍጠር
• በራስ ሃይል የተጀመሩ ስራዎችን በማጠናከር
3 • ኢምባኮ (Competitive Access 2026 _ • የመሠረተ-ልማት አስተዳደር እና የኦፕሬሽን ቢዝነስ ዩኒቶቹን ትራንስፖርትና
Model) 2030 በማጠናከር ወደጠንካራ ንዑሳን በማሳደግ (ማለትም ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር
• የተለያዩ በመንግስትና በግሉ ዘርፍ የመሠረተልማት አስተዳዳሪ ንዑስ ኩባንያ፣ የባቡር ትራንስፖርት ፤ ኢምባኮ
የሚለሙ ባቡር ነክ ቢዝነሶች ኦፕሬሽን ንዑስ ኩባንያ)
• የግሉ ዘርፍ ኦፕሬተሮች • በባቡር ትራንስፖርት ኦፕሬሽን የግል ባለሃብቶችን ተሳትፎ
• የግሉ ዘርፍ መሰረት ልማት በማረጋገጥ
አስተዳዳሪ

ሰንጠረዥ 7፡ የዘርፉን ገቨርናንስ አደረጃጀት ማስተካከያ ስትራቴጂያዊ አቅጣጫ የጊዜ ሰሌዳ

56
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
መሠረታዊ ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች

መሠረታዊ ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች የተባሉት የባቡር ዘርፉን ዘላቂነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ እና አበይት
ተልዕኮዎቹን ለማከናወን የሚያስችል መሠረታዊ አቅም የሚፈጥሩ፤ እንደ ዘርፍ በስኬታማነት ለመራመድ
የህልውና መሠረት በመሆናቸው ነው።

5.2.1 ጠንካራ የሃገራዊ ባቡር ዘርፍ አቅም፣

የሃገሪቱ የባቡር ዘርፍ ካሉበት ወሳኝ ፈተናዎች መካከል የሰው ሃይል እና የቴክኖሎጂው አቅም
አለመዳበር፤ በዚህም የተነሳ የዘርፉን አበይት ሥራዎች ለማከናወን በውጭ አቅራቢዎች (ተቋራጭ፣
አማካሪ፣ የትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ…) ጥገኛ መሆን ዋነኞቹ ናቸው።

ይህንን ፈተና በዘላቂነት ለመፍታት ሃገራዊ የባቡር ሴክተሩን አቅም በሰው ሃይልም ሆነ በቴክኖሎጂ
መገንባት፤ እንዲሁም በሴክተሩ እሴት ሰንሰለት ላይ የሚሳተፉ ሃገር በቀል ተዋናዮችን አቅም በተደራጀ
እና ስትራቴጂክ በሆነ መንገድ መገንባትም በፍኖተ ካርታው የጠንካራ ሃገራዊ ባቡር ዘርፍ አቅም ግንባታ
ስትራቴጂያዊ የትኩረት አቅጣጫ ሆነው ተቀርጸዋል።

ሀ. የሰው ሀብትና የቴክኖሎጂ አቅም ግንባታ

1ኛ. በተቋማዊ ስልት የሰው ኃይል አቅም መገንባት፤

• የባቡር ልህቀት ማዕከል ግንባታን ተግባራዊ ማድረግ

የዘመናዊ ባቡር ዘርፉ የሰው ኃይል አቅም ከእጥረት ተነስቶ አሁን ካለበት በመሠረታዊ ደረጃ የሰለጠነ
ከፍተኛ ባለሙያዎች በተለይ በባቡር ምሕንድስና በብዛት የያዘበት ደረጃ ላይ ደርሷል። ይህም የሃገራዊ
ባቡር ዘርፉን አበይት ሥራዎች በራስ ኃይል መስራት አንደምንችል ድፍረት ያገኘንበት ደረጃ ላይ የደረሰ
ቢሆንም፤ አሁንም ተግባራዊ ልምድ ላይ ክፍተት ይታያል። በተጨማሪም የባቡር ዘርፉ በወሳኝ ሙያዎች
በብዛት የሚጠቀመው የመካከለኛ ባለሙያ ክፍተት አለበት። ከሃገሪቱም አልፎ አፍሪካ በቀጣይ ወደ አንድ
የኢኮኖሚ ቀጠና ለመሸጋገር የምታደርገውን ጉዞ ዕውን ለሚያደርገው አህጉራዊ የባቡር ትራንስፖርት
ዘርፍ የሚያስፈልገው የሰው ኃይል ቁጥር እጅግ በጣም ከፍተኛ ነው።

በመሆኑም ሃገራዊውም ሆነ አህጉራዊው የባቡር ዘርፉ ለሚያስፈልገው የሰው ኃይል ፍላጎት በበቂ ሁኔታ
እንኳ ባይሆን በመጠኑ ምላሽ ለመስጠት ተቋማዊ በሆነ መልኩ የሰው ኃይል አቅም ግንባታ ላይ መስራት
ያስፈልጋል። ለዚህም ከዘርፉ ቴክኒካዊ ይዘት አንጻር በዘርፉ የሚገነባ እና በተግባር በተፈተኑ የዘርፉ
ባለሙያዎች የሰው ኃይል ስልጠና የሚሰጥበት እና የቴክኖሎጂ ልማት የሚተገበርበት አህጉር አቀፍ

57
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
የባቡር ልህቀት ማዕከል (አካዳሚ) መገንባት እና በሰው ኃይል፣ በሲስተምና በማቴሪያል ማጠናከር አቅም
የሚገነባበትን መሠረት መጣል እና የሰው ኃይል ልማቱን ዘላቂነት ማረጋገጥ ያስፈልጋል።

• በተገነባው የልህቀት ማዕከል በየፈርጁ የሰው ኃይልን ማልማት

የተገነባውን የባቡር ልህቀት ማዕከል (አካዳሚ) እሴት በመጠቀም ከሦስት እይታዎች አንጻር የዘርፉን
የሰው ኃይል ልማት ማከናወን በቀጣይ የሚጠበቅ ወሳኝ ስትራቴጂያዊ አቅጣጫ ነው። እነዚህም፡-

o በሴክተሩ ያለውን የሠው ኃይል ከማብቃት አንጻር፣


o ለሴክተሩ የሚያስፈልገውን አዳዲስ የሰው ኃይል ከማፍራት አንጻር፣ እና
o ለአህጉሪቱ የሚፈለገውን የሰው ኃይል ከማዘጋጀት አንጻር ናቸው።

በሴክተሩ ያለውን የሰው ኃይል ማብቃት፡- ዘመናዊ የባቡር ሴክተር ለሃገሪቱ አዲስ ከመሆኑ አንጻር
በሴክተሩ ላይ የተሠማራው በየደረጃው ያለው የሰው ኃይል በልምድ፣ በመፈጸምና በማስፈጸም አቅም
ውጤታማ ደረጃ ላይ አልደረሰም። በመሆኑም ሴክተሩን በተደራጀ መልኩ ለማነቃቃት የተሠማራው ፈጻሚ
እና አመራርን ማጠናከር የግድ ይላል። በመሆኑም በየደረጃው ያለውን የሰው ኃይል አቅም ክፍተት
በመለየት አስፈላጊውን የአቅም ግንባታ ሥራን የሙያ ዕድገት መሰላልን የተከተሉ ተከታታይ የሙያ
ማበልጸጊያ ስልጠናዎች (Continuous Professional Development (CPD)) እና የተለያዩ የማነቃቂያ
መካከለኛ ስልጠናዎችን (Refreshing Short Courses) በመስጠት መተግበር ያስፈልጋል፣

ለሴክተሩ የሚያስፈልገውን አዲስ የሰው ኃይል ማፍራት፡- የሴክተሩን የሰው ኃይል ፍላጎት ከትኩረት
አቅጣጫዎች አንጻር በማጥናት በከፍተኛ ባለሙያ እና በመካከለኛ ባለሙያ ደረጃ የሚያስፈልገውን የሰው
ኃይል ማዘጋጀት ያስፈልጋል (formal Technical and Skill Training – TVET Programmes) ፣

የሰው ኃይል ልማቱን በምስራቅ አፍሪካ ደረጃ ተደራሽ ማድረግ፡- ከሃገራዊ የሰው ኃይል ልማቱ በተጨማሪ
በአህጉሪቱ ደረጃ ከተፈጠረው የመሠረተ-ልማት እና የትራንስፖርት ዘርፍ መነቃቃት አንጻር የሰው ኃይል
ስልጠና ለአፍሪካ ሃገራትም በመስጠት የዕውቀት ሽግግር ማድረግ እና የሰለጠነ የሰው ኃይል ወደ ውጭ
መላክ (Knowledge & Skills Exporting) ፣ በቀጣይ በትኩረት ሊተገበሩ የሚገባቸው ናቸው።

2ኛ. በምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር የቴክኖሎጂ አቅም መገንባት

ሃገራዊ ባቡር በሴክተሩ ያለንበት የቴክኖሎጂ ደረጃ ዝቅተኛ በመሆኑ አብዛኞቹን ግብዓቶች ከውጭ
በማስገባት የምንተገብር መሆኑ ይታወቃል። በመሆኑም የሃገሪቱን የባቡር ሴክተር በዓለም አቀፍ ደረጃ
ተወዳዳሪ ለማድረግ ከመሠረታዊ ዕውቀት ወደ ጥልቅ፣ ቴክኖሎጂን ከመጠቀም ወደ መቅዳት፣ ማላመድና

58
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
መፍጠር ማሳደግ ያስፈልጋል። ለዚህም በምርምር የታገዘ የቴክሎጂ ሽግግር፣ እንዲሁም የሃገር በቀል
ኢንዱስትሪዎችን ማስፋፋት ወሳኝ ስትራቴጂያዊ አቅጣጫ ነው።

• የዘርፉን ችግሮች የሚፈቱ ተግባራዊ ምርምሮችን ማከናወን

የባቡር ዘርፉ ካለበት ከፍተኛ የውጭ ሃገር የቴክኖሎጂ ጥገኝነት ተጽዕኖ ለማላቀቅ ልዩ ትኩረት በመስጠት
ዘርፉን በሃገራዊ አቅም ሊያንጹ የሚችሉ የምርምርና የስርፀት እንዲሁም የቴክኖሎጂ ሽግግር ሥራዎች
ማከናወን ወሳኝ ነው።

ለዚህም፡-

o የባቡር ዘርፉን መሠረታዊ ቴክኒካል ችግሮች ሳይንሳዊ በሆነ ዘዴ በመለየትና ቅደም ተከተል
በማስያዝ በአንገብጋቢዎቹ ችግሮች ላይ ዘርፉ ያለውን የሠው ኃይል በመጠቀም ለችግሮቹ
ሃገራዊ መፍትሄ መፈለግ፣
o ለየሃገር ውስጥ የፈጠራና ምርምር ሥራዎች በቂ ትኩረት ሰጥቶ በፋይናንስ እና በአሠራር
ሥርዓት በመደገፍ የዘርፉን የሃገር ውስጥ ምርምርና ስርጸት አቅምን ማሳደግ ያስፈልጋል።
• የቴክኖሎጂ ሽግግር ሥራዎችን ማከናወን

የባቡር ዘርፉ የተገነባው ከተለያዩ ሙያዎች ጥምረት (Integration of Disciplines) ከመሆኑ አንጻር
እንዲሁም ከተጀመረበት የእድሜ ርዝማኔ አንጻር የተለያዩ የቴክኖሎጂ ማሻሻያዎች እየተደረጉለት አሁን
ለደረሰበት ውስብስብ የቴክኖሎጂ ደረጃ ላይ ደርሷል።

ሀገራዊው የባቡር ዘርፍ ወደ ዘመናዊው የባቡር ቴክኖሎጂ በቅርብ ዓመታት የተቀላቀለ ከመሆኑ አንጻር
የኋላ-መጪ ጥቅም (late-comer advantage) በከፍተኛ መጠን በመጠቀም ከውጭ ሃገር የቴክኖሎጂ
ጥገኝነት ተጽዕኖ ለማላቀቅ በትኩረት መሠራት ይኖርበታል። ለዚህም ዘርፉን በሃገራዊ የቴክኖሎጂ አቅም
ሊያንጹ የሚችሉ ፡-

o መደበኛ የቴክኖሎጂ ሽግግር ሥራዎች፣ እንዲሁም


o የምልሰት ምህንድስና (reverse-engineering) ሥራዎች ማከናወን ወሳኝ ነው።

መደበኛ የቴክኖሎጂ ሽግግር ሥራዎች፡-

ይህ በተለምዷዊ መንገድ የቴክኖሎጂ ሽግግርን ለማሳካት የሚጣርበት ስትራቴጂያዊ አቅጣጫ ሲሆን፤


ዓላማውን ለማሳካት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን ማከናወን ይጠይቃል።

59
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
• የዘርፉን ሃገራዊ የቴክኖሎጂ አቅም ለመገንባት ግልጽ የሆነ የቴክኖሎጂ ፍኖተ ካርታ
በማዘጋጀት በቀጣይ ትኩረት የሚሰጥባቸውን ቴክኖሎጂዎች መለየት፣
• በፍኖተ ካርታው በተመረጡ የቴክኖሎጂ የትኩረት መስኮች ላይ የምርምርና ስርጸት እና
የቴክኖሎጂ ሽግግር ሥራዎችን መተግበር፤
• በሃገር አቀፍ ደረጃ የዘርፉ ቴክኖሎጂ እንዲዳብር በማኛውም ዓለም አቀፍ ግዢዎች የሃገር-
ውስጥ ይዘት (local-content) መጠንን፣ አንዲሁም የቴክኖሎጂ ማላመጃ ወይም ማሸጋገሪያ
localization/transfer of technology) መጠንን በመወሰን በሕግ ማዕቀፍና በአሠራር ስርዓት
መደገፍ፣
• በሃገር ደረጃ ከተለያዩ የዘርፉ መሪ ሃገራት ጋር የሁለትዮሽ ስምምነት በማድረግ የቴክኖሎጂ
ሽግግር ትብብር እንዲያደርጉ እና በፋይናንስም አንዲደግፉ ማድረግ፣
• የዘርፉን የቴክኖሎጂ አቅም ግንባታ ጉዳይ እንደ ሃገራዊ ወሳኝ የትኩረት አቅጣጫ በማየት
የሚያስፈልገውን በቂ ፋይናንስ መመደብ

የምልሰት ምህንድስና (reverse-engineering) ሥራዎች

የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎትን ለመስጠት በመሠረተ-ልማቱ እና በባቡሮቹ ላይ ያሉ የተለያዩ ውስብስብ


ሥርዓቶች ቅንጅት (Integration of Systems) በሥራ ላይ የሚውል ሲሆን እያንዳንዱ ሥርዓት ደግሞ
በውስጡ የተለያዩ ንዑስ ሥርዓቶችን የያዘ ነው።

መንገደኛን እና ጭነትን ለማጓጓዝ በሚደረገው ምልልስ ሂደት ቶሎ ቶሎ የሚያልቁ የባቡር


መለዋወጫዎችን በፍጥነት መተካት እና ለጠቅላላ ሥርዓቱ ጤናማ እንቅስቃሴ ወሳኝ የሆኑ ግብዓቶች
በበቂ መጠን ተመርተው በገበያ ላይ ሊገኙ እና ለሴክተሩ ተደራሽ መሆን ይገባቸዋል።

እነዚህ ግብዓቶች በመሠረተ ልማቱም (መስመሩ) ሆነ በተንቀሳቃሽ ሃብቱ (ባቡሮች) ውስጥ የተካተቱ
ሲሆኑ የባቡር አላቂ መለዋወጫዎች፣ የኃይል አስተላላፊ መስመር ኬብሎች፣ የሀዲድ ፓዶች፣ ክሊፖች፣
እና ሌሎች ግብዓቶች ከብዙ ጥቂቶቹ ናቸው።

በሃገሪቱ የባቡር ዘርፍ የመሠረተ ልማቱም ሆነ የባቡሮቹ ምንጭ ሌሎች ሃገራት በመሆናቸው እና
ግብዓቶቹን የማምረት ልምድ በሃገር ውስጥ ያልዳበረ ከመሆኑ አንጻር በከፍተኛ ደረጃ በውጭ ሀገራት
ተጽዕኖ ስር እንዲወድቅና ግብዓቶቹን ለማግኘትም ለከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ እንዲዳረግ ሆኗል። ከሃገሪቱ
የውጭ ምንዛሮ የማመንጨት አቅም ማነስ አንጻር ደግሞ በበቂ መጠን እና ፍጥነት የውጭ ምንዛሬ
ተገኝቶ ግብዓቶቹን ማቅረብ ፈታኝ ስለሚያደርገው፣ እንዲሁም የውጭ ምንዛሬ ቢገኝም እንኳ ምርቶቹ
ታዘው ተመርተውና ተጓጉዘው በስራ ላይ እስኪውሉ ረጅም ጊዜ የሚወስድ በመሆኑ አላስፈላጊ
የአገልግሎት መጓደልን እየፈጠረ ይገኛል። ይህን ችግር ለመፍታት አምራች ንዑስ ሴክተሩን በአቅም

60
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
በማጠናከር እና የተለያዩ ግብዓቶችን በሃገር ውስጥ የማምረት (Local Inputs Manufacturing) ስልትን
በመከተል ሃገርን ከከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ ወጪ መታደግና በአህጉራዊ ገበያም በመግባት ተወዳዳሪ
መሆን ይቻላል። በዋነኝነትም የሴክተሩን የግብዓት አቅርቦት ችግር በዘላቂነት መፍታት ይቻላል። ይህ
ስልት በአጭርና በረጅም ጊዜ ተከፍሎ ከቀላል ወደ ውስብስብ የአሰራር ስርዓት አንዲያድግ ማድረግ
ያስፈልጋል።

የሴክተሩን ግብዓቶች በሀገር ውስጥ ለማምረት የሴክተሩ ዋነኛ ተዋናይ ኢምባኮ ቀዳሚ ሚናውን በመያዝ
የዘርፉን የማምረት ስራዎች ማስተባበር፣ ከፍተኛ ወጪና አቅም የሚሹትን ስራዎች ከውጭ ባለሀብቶች
ጋር በጋራ በመሆን በራሱ አቅም ሊያከናውነው ይችላል።

ከሃገር በቀል አምራች ኢንዱስትሪዎች ጋር በጋራ የመስራት ዕድልም ያለ ሲሆን ያሉትን ሀገራዊ አቅሞች
በትክከለኛው ስትራቴጂ ማስተሳሰር ከተቻለ ከአጠቃላይ የእሴት ሰንሰለቱ አብዛኛውን ስራ በሀገር ውስጥ
ምርቶች መተካት የሚቻልበት ጊዜን ማሳጠር ይቻላል።

ዋና ዋና ሊተገበሩ የሚከናዎንበት ጊዜ ተግባራት ፈጻሚ አካል

ተ.ቁ. የሚገባቸው ከመቼ? እስከመቼ?


ስራውዎች
1 የሰው ኃይልና ቴክኖሎጂ አቅም መገንባት
1.1 ተቋማዊ የሰው 2016 2020 የባቡር ልህቀት ማዕከል (አካዳሚ) በመገንባትና ኢምባኮ
ኃይል ልማት በማጠናከር
ማከናወን 2016 2026 የዘርፉን የሰው ኃይል በሙያ ዕድገት መሰላል መሠረት ኢምባኮ
በተግባራዊ ክህሎት በማብቃት (CPD & Refreshing
Courses)
2016 2026 በመካለኛ ባለሙያ ደረጃ ወደ ዘርፉ የሚቀላቀለውን ኢምባኮ
አዲስ የሰው ኃይል በማብቃት (TVET Training
Programs)
2017 2022 የሰው ኃይል ልማቱን በምስራቅ አፍሪካ ደረጃ ተደራሽ ኢምባኮ
በማድረግ (Knowledge & Skills Exporting)

1.2 የቴክኖሎጂ 2016 2030 የዘርፉን ችግሮች የሚፈቱ ተግባራዊ ምርምሮችን ኢምባኮ
አቅምን በማከናወን ትራንስፖርት
በምርምርና ና ሎጂስቲክ
ቴክኖሎጂ ሽግግር ሚኒስቴር፣
ማሳደግ 2016 2030 የዘርፉን ግብዓቶች በሃገር ውስጥ በማምረት (ቴክኖሎጂ ኢምባኮ
በማላመድ)

ሰንጠረዥ 8፡ የጠንካራ የሃገራዊ ባቡር ዘርፍ አቅም ግንባታ ስትራቴጂያዊ አቅጣጫ የጊዜ ሰሌዳ (የሰው
ኃይልና ቴክኖሎጂን በተመለከተ)

61
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
ለ. በባቡር ዘርፍ የሃገር ውስጥ ተዋናዮችን አቅም መገንባት፤

የባቡር ሴክተሩን አቅም በተቋም፣ በሰው ኃይልና በምርት በማሳደግ በሁሉም የሴክተሩ ንዑስ ሥራዎች
ላይ የሃገር ውስጥ ድርሻን መጨመር ያስፈልጋል። ለዚህም የመጀመሪያው እርምጃ ለባቡር መሠረተ-
ልማት ግንባታና ኦፕሬሽን የሃገር ውስጥ ባለሙያዎች፣ ኩባንያዎችና ግብዓቶች ተሳትፎን ከፍ በማድረግ
የሴክተሩን የሃገር ውስጥ ድርሻ (Local Content) ማሳደግ ነው።

1ኛ. የሃገር በቀል የግንባታና የማማከር ተቋማትን አቅም መገንባት፤

በዲዛይንና ሱፐርቪዥን እና በባቡር መሠረተ-ልማት ግንባታ በሃገር ውስጥ ያለውን አቅም በተለያዩ
የአቅም ግንባታ ዘዴዎች በማጠናከር ለሴክተሩ አስተዋጽዖ እንዲያደርግ ድጋፍ ማድረግ፤ በቀጣይ
የሚገነቡ የባቡር መስመሮች በሃገር ውስጥ አቅም እንዲገነቡ ለማድረግ ያስችላል።

ይህም በዋነኝነት በሃገር ውስጥ የባቡር ዲዛይንና ግንባታ የእውቀትና ልምድ ሃብት ክምችት እንዲኖር
ከማድረጉም በላይ፤ ለውጭ ኩባንያዎች ይወጣ የነበረውን የውጭ ምንዛሬ ለመቀነስ እንዲሁም ለሃገር
ውስጥ ዜጎች ተጨማሪ የሥራ ዕድል ለመፍጠር ያስችላል።

ይህንንም ከዚህ በሚከተሉት መልኩ በሂደት ማሳካት ያስፈልጋል፡-

• በማንኛውም ግንባታ ውስጥ በራስ አቅም ወይም በሃገር ውስጥ መከናወን የሚችሉትን ሥራዎች
ለይቶ ለኢምባኮ ቢዝነስ ዩኒት ወይም ለሃገር ውስጥ ገንቢዎችና አማካሪዎች በሰብኮንትራት (sub-
contract) መንገድ እንዲሳተፉ የውጭ አቅራቢዎችን ማስገደድ የሚያችል አሰራር መዘርጋትና
ተግባራዊነቱም በቅርበት መከታተል፣
• የኢምባኮ ኮንስርታርሽን፣ ዲዛይንና ቀጥጥር ቢዝነስ ዩኒቶችና የሀገር ውስጥ የስራ ተቋራጮች
እንዲሁም አማካሪዎች ከውጭ ገንቢዎቸና አማካሪዎች ጋር በቅንጅት (JV) እንዲያከናውኑ
በመደገፍ፣
• በሂደትም አብዛኛውን ሥራ ለዘርፉ ባለቤት ለሚሆነው ኢምባኮ ወይም ለሃገር ውስጥ ገንቢዎችና
አማካሪዎች በመስጠት ሙሉ በሙሉ ቴክኖሎጂውን እና ዕውቀቱን አሸጋግረው በሃገር ውስጥ
አቅም የሚሠሩበትን መንገድ በመጥረግ (local-content dominated contracting = 55%)

ሆኖም አሁን ባለንበት ሁኔታ በባቡር ዘርፍ የተሠማሩ አማካሪዎችና ተቋራጮችን በበቂ ሁኔታ ማግኘት
ስለማይቻል ይህ ዕውን እስከሚሆን ድረስ እነዚህን ንዑስ ዘርፎች የማጠናከር ኃላፊነት የሴክተሩ ዋና
ተዋናይ ኢምባኮ በባለቤትነት የሚያከናውነው ይሆናል።

62
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
በመሠረተ-ልማት ዲዛይንና ቁጥጥር በኩል ከቅድመ-አዋጭነት ጥናት እስከ ቅድመ ዲዛይን በሂደትም
እያደገ እስከ ዲዛይን፤ በግንባታውም በኩል ከዕለታዊ የመስመር ጥገና እስከ የሙከራ መስመር ግንባታ
(test Km) ፣ በሂደት እያደገ ለጣቢያዎች የሚያስፈልጉ ተጨማሪ ትራኮችን (side-tracks) ወደ መገንባት፣
ከዚያም አገናኝ መንገዶች (link roads) ና አገናኝ ሃዲዶችን (link rails) እስከመገንባት ድረስ በኢምባኮ
ሥር በቢዝነስ ዩኒት መልኩ ተጠንስሰው የሚያድጉ ኢኒሼቲቮችን መተግበር ያስፈልጋል።

እነዚህ ኢኒሼቲቮች ሲያድጉ የሴክተሩን የዲዛይንና ቁጥጥር አንዲሁም የግንባታ አቅም መሠረት የሚጥሉ
ተቋማትን ለመፍጠር የሚስችሉ ናቸው።

2ኛ. የባቡር አገልግሎት ሰጪዎችን አቅም መገንባት፤

ከባቡር መሠረተልማት ዲዛይንና እና ግንባታ በተጨማሪ በተገነባው የባቡር መስመር ላይ አገልግሎትና


ጥገና ማከናወን ላይ ሙሉ አምነት መጣል የሚያስችል የተከማቸ የሃገር ውስጥ አቅም ካለመኖሩ የተነሳ
ከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የጠየቁ የማኔጅመንት ኮንትራት ውስጥ ለመግባት አስገዳጅ ሆኖ ቆይቷል። የዚህ
የውጭ ዕውቀት ጥገኝነት አካሄድ ካልተቀየረ ዘርፉ በከፍተኛ የፋይናንስም ሆነ የሰው ኃይል ኪሣራ ውስጥ
ሲዳክር እንደሚኖር መገመት አያዳግትም።

በመሆኑም ከላይ ለግንባታው እና ለዲዛይን በተቀረጸው ስትራቴጂያዊ አቅጣጫ አንጻር በአንድ ወገን የራስ
ኃይል ኦፕሬሽን ቢዝነስ ዩኒት በማደራጀት ባለው አቅም እየተጠቀሙና ለሚጎድለው የውጭ ባለሙያ
በተለያዩ አማራጮች ቀጥሮ በማሟላት የዘርፉን የኦፕሬሽንና ጥገና ተቋማዊ አቅም መገንባት አንዱ
አቅጣጫ ነው። ይህም የባቡር ዘርፉ የተሰጠውን ተልዕኮ፤ በተለይም የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት
መስጠትን በራስ ኃይል በማከናወን የውጪ ሃገር ባለሙያ ድርሻን መቀነስ በዚህም የውጪ ምንዛሬ
ኢንቨስትመንት ፍላጎትን መቀነስ ያስችላል። በሌላ በኩል ደግሞ ሃገር በቀል የግል ባለሃብቶችን
በማበረታታት በባቡር ዘርፉ የኦፕሬሽንና ጥገና አገልግሎት ላይ አንዲሳተፉ በማድረግ ሃገራዊ የባቡር
ትራንስፖርት አቅም መፍጠር እና የአገልግሎት ሰጪ ንኡስ ሴክተሩን ማጠናከር ነው። ይህ ደግሞ
በትራንስፖርት አገልግሎቱ ላይ ውድድር በመፍጠር ለተጠቃሚዎች የአገልግሎት ጥራትና የዋጋ
ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ያስችላል።

63
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
ዋና ዋና ሊተገበሩ የሚከናዎንበት ጊዜ ተግባራት ፈጻሚ አካል

ተ.ቁ. የሚገባቸው ስራውዎች ከመቼ እስከመቼ

የዘርፉን ተዋናዮች አቅም መገንባት


1 የመሠረተ-ልማት 2016 2022 በአ.አ. - ጅቡቲ እና በአዋሽ - መቀሌ መስመሮች ኢምባኮ
ተቋራጮችን አቅም የመሠረተ-ልማት ጥገና እና የአገናኝ ሃዲዶች
መገንባት ግንባታ ሥራዎችን በራስ ኃይል ማከናወን

2016 2030 በ 2030 በባቡር የመሠረተ-ልማት ግንባታ የሃገር ኢምባኮ


ውስጥ ተቋራጮች ተሳትፎ 55% እንዲደርስ
ማድረግ
2 የመሠረተ-ልማ 2016 2030 የቅድመ-አዋጭነት፣ የአዋጭነት፣ የኮንሴፕት ኢምባኮ
ዲዛይንና ቁጥጥር ዲዛይን፣ እንዲሁም መጠነኛ የቁጥጥር
አማካሪዎችን አቅም ሥራዎችን በራስ ኃይል ማከናወን
መገንባት 2016 2030 በ2030 በባቡር የመሠረተ-ልማት ዲዛይንና ኢምባኮ
ቁጥጥር የሃገር ውስጥ አማካሪዎች ተሳትፎ
55% እንዲደርስ በማድረግ
3 የባቡር ትራንስፖርት 2019 2025 የአዋሽ - መቀሌ መሰመርን ኦፕሬሽን በራስ ኢምባኮ
አገልግሎት ሰጪዎችን ኃይል በማከናወን - ክፍተት ያለባቸውን
አቅም መገንባት የዕውቀት መስኮች የሚሟሉበትን የተለያዩ
አማራጮች በመከተል (Shadow Operator,
Expat. & After Sales)
2016 2030 በ 2030 በባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት የግል ኢምባኮ
ባለሃብቶችን ተሳትፎ 55% እንዲደርስ በማድረግ ትራንስፖርት ና
ሎጂስቲክ
ሚኒስቴር፣
የገንዘብ ሚኒስቴር
MoF

ሰንጠረዥ 9፡ የጠንካራ የሃገራዊ ባቡር ዘርፍ አቅም ግንባታ ስትራቴጂያዊ አቅጣጫ የጊዜ ሰሌዳ (የዘርፉ ተዋናዮችን
በተመለከተ)

5.2.2 አስተማማኝ የባቡር ደኅንነትና ጸጥታ፣

የባቡር ዘርፉ ደኅንነትና ጸጥታ መረጋገጥ ደንበኞች በዘርፉ ላይ ያላቸውን አመኔታ እና ዋስትና
ከማረጋገጡም በላይ፤ ዘርፉ በዘላቂነት በስኬት የሚዘልቅበትን መሠረት የሚጥል ነው። የዘርፉ ደኅንነት
አለመጠበቅ ደግሞ ከሌሎች ዘርፎች በተለየ ከፍተኛ ሰብዓዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ አካባቢያዊ፣ ማኅበራዊ እና
ፖለቲካዊ ጉዳት የሚያስከትል ነው። በመሆኑም የዘርፉን ደኅንነትና ጸጥታ አስተማማኝ ለማድረግ
በአደረጃጀት፣ በአሠራር ሥርዓትና በባለድርሻ አካላት ቅንጅት ላይ ትኩረት ተሰጥቶባቸው የሚከናወኑ
ስትራቴጂያዊ አቅጣጫዎች ተለይተዋል።

ሀ. የባቡር ደኅንነትን የሚያረጋግጥ አደረጃጀት መዘርጋት

64
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
የደህንነት ጉዳይ በሴክተሩ ዋነኛና ከፍተኛ ትኩረት የሚሻ ጉዳይ እንደመሆኑ የዘርፉ አደረጃጀትም
የደህንነት ስጋቶችን ከመነሻው ሊያከስም በሚያስችል /Preventive System/ እና ከተከሰቱም የአደጋ
መከላከል ስራዎችን ቀልጣፋና በዝቅተኛ የአደጋ ውጤቶች /Faster & Lowered casualities/ መመከት
የሚያስችል ሊሆን ይገባል።

1ኛ. ተቆጣጣሪ አካል ማደራጀት፤

ከሌሎች በሴክተሩ በቂ ልምድ ካላቸው ሀገራት ተሞክሮ ማየት እንደሚቻለው የባቡር ዘርፍ የደህንነትና
የሌሎች የከፍተኛ ስጋት ምንጭ ሊሆኑ የሚችሉ ተያያዥ ጉዳዮችን፤ የደህንነት መመሪያዎችና ደረጃዎችን
(Railway Safety Regulations & Standards/ በማውጣት፣ አተገባበራቸውን በመከታተል የሚያስፈፅም
የዘርፉ ተቆጣጣሪና ፖሊሲ አውጪ አካል ይኖራል። ይህ አካል ሌሎች የባቡር ሴክተሩን ስራዎችም ደረጃ
የመስጠት፣ የስራ ጥራትና አፈፃፀምን የመመዘንና የዘርፉን ተዋናዮች መስተጋብር የመወሰን ስልጣን
ያለው ነው። በተጨማሪም ፈጻሚው የደኅንነትን ጉዳይ የሚያረጋግጥበት አደረጃጀት እንዲኖረው ድጋፍና
ክትትል ያደርጋል። በመሆኑም የሃገራችን ባቡር ሴክተርን ደኅንነት ለማረጋገጥ ራሱን የቻለ የሴክተሩ
ተቆጣጣሪ አካል በሂደት ማደራጀት ያስፈልጋል።

2ኛ. የደህንነትና ፀጥታ መዋቅር ማደራጀት፤

ከሌሎች ሃገራት ልምድ መረዳት እንደሚቻለው የባቡር መሠረተልማት እና አገልግሎት የራሱ የሆነ
የደኅንነትና የጸጥታ አደረጃጀት ሊኖረው ይገባል። በሃገራችንም ሴክተሩ በሌሎች ባለድርሻ አካላት ድጋፍ
ላይ ተንጠልጥሎ የሚገኝ በመሆኑ በአስተማማኝነት የሴክተሩን ደኅንነት ለማረጋገጥ የራሱ የሆነ የጸጥታ
መዋቅር ማደራጀት ያስፈልጋል።

ለ. የደኅንነትና የስጋት አሠራር ስርዓቶችን መዘርጋት

1ኛ. የባቡር ትራንስፖርት የሕግ ማዕቀፍ ማጠናከርና መተግበር

የባቡር ትራንስፖርት የራሱ የሆነ መስመርን ተከትሎ በከፍተኛ ፍጥነት የሚጓዝ፣ በአስተማማኝ የትራፊክ
ስርዓት የሚመራ፣ እንዲሁም የሚከሰተው አደጋ ከሚኖረው ከፍተኛ ተጽዕኖ አንጻር በወሰኑ ውስጥ
ለሚከሰት አደጋ የሚያስጠነቅቁ የመንገድ ምልክቶች ያሉት እና የአደጋ ክስተት ተጠያቂነቱን መስመሩን
አቋርጦ አደጋ ለሚደርስበት አካል የሚሰጥ መሆኑን ዓለም አቀፋዊ ልምዱ ያሳያል። በመሆኑም በሃገራችን
የባቡር ትራንስፖርትን ሕግ በማጠናከር ተግባራዊ ማድረግ በተደጋጋሚ በመከሰት ለሴክተሩ ፈተና
የሆኑትን አደጋዎች ጉዳት ለማስቀረት ይጠቅማል።

2ኛ. የባቡር ዘርፉ በዓለም አቀፍ ስታንዳርዶች መሠረት እንዲመራ ማድረግ

65
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
በአለም አቀፍ ደረጃ በሀገራት መካከል ስምምነት የተደረሰባቸው የስራ ላይ ጤናና ደህንነት ደረጃዎች
እስካሁን በሀገራችን በሌሎች የትራንስፖርት ዘርፎች ላይ እየተተገበሩ የሚገኙ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን፤
የባቡር ሴክተር ለሀገራችን አዲስ እንደመሆኑ በአለም አቀፍ ደረጃ ያለውን የትግበራ ልምድ በመቅሰም
በሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ መሠረት መቅረጽና መተግበር ያስፈልጋል።

ከዚህ ጋር በተያያዘ ከዓለም አቀፍ ልምድ በመቀመር የሴክተሩ ስትራቴጂክ ዕቅዶች ለደኅንነት ቅድሚያ
የሰጡ እና በስጋት አስተዳደር መርህ የተቀረጹ ማድረግ፣ በእያንዳንዱ ንዑስ ዘርፍ ውስጥ የሚታቀዱ
ዓመታዊ ዕቅዶችም ሆኑ የረጅም ጊዜ ስትራቴጂያዊ ዕቅዶች በውስጣቸው የስጋት አስተዳደርን ያማከሉና
የተለያዩ የመፍትሄ አቅጣጫዎችን የሚያስቀምጡ ሆነው ሊሰናዱ እና ሊተገበሩ ይገባል። ይህንንም
ከፕሮጀክት ዲዛይን ጀምሮ በግንባታ እና በትራንስፖርት አገልግሎት ወቅት የደኅንነት ሥራዎችን
ማስተግበር የሚያስችል አሠራርን በመዘርጋት ዕውን ማድረግ ይቻላል።

ሐ. ለባቡር ዘርፉ ደኅንነት ባለድርሻ አካላትን በባለቤትነት ማሰማራት

የዘርፉን ደኅንነት ዘለቄታ ያለውና አስተማማኝ ለማድረግ የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ተሳትፎና የባለቤትነት
ስሜት ማስረፅ ይጠይቃል። ይህንንም ተግባራዊ ለማድረግ በተለያዩ ተከታታይ የግንዛቤ ማስጨበጫ
ስልጠናዎችና ውይይቶች መግባባትን መፍጠርና በሁሉም ባለድርሻ አካላት ተሳትፎ በሚረቀቅ የድርጊት
መርሃ-ግብር በጋራ ማሠማራት ይጠይቃል። በተጨማሪም ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቅንጅት ለባቡር
ደኅንነት እንዲሠሩ በበላይ የመንግስት አካል ቁጥጥር እየተደረገበት የሚያስተባብር ታስክ ፎርስ ማቋቋም
ይመከራል። ይህም ታስክ ፎርስ የቅድመ አደጋ ሥራዎችን ከማከናወን በተጨማሪ የአደጋ ጊዜ ፈጣን
ምላሾችን የሚተገብር ማድረግ ያስፈልጋል።

ከባለድርሻ አካላት በተጨማሪ ማኅበረሰቡም የባቡር መስመርና ተንቀሳቃሽ ሃብቱን በእኔነት ስሜት
እንዲጠብቀው እና እንዲንከባከበው አስፈላጊውን የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች መስራት፣ በየደረጃው
የተለያዩ የማኅበረሰብ አደረጃጀቶችን በመጠቀም (ጎጥ፣ ቀበሌ፣ ወረዳ፣…) የባቡር ማኅበረሰብ አደረጃጀት
በመፍጠር ለመስመሩና ለተንቀሳቃሽ ሃብቱ ጥበቃ ማሠማራት ሊተገበሩ የሚገባቸው ስትራጂያዊ
አቅጣጫዎች ናቸው።

መ. የተቀናጀ የባቡር ዘርፍ ስጋት አስተዳደርን በየደረጃው መተግበር

የባቡር ዘርፍ ለኢትዮጵያ የሚያበረክተውን ዘላቂ ኢኮኖሚያዊ፣አካባቢያዊና ማህበራዊ ጥቅምን


እንዲያረጋግጥ የዘርፉን የተሳሰሩ የኢንደስትሪ ምዕራፎች /Planning and design, construction,
operation and maintenance/፣ የስራ እንቅስቃሴዎች /Business Activities/ እና የመሰረተ ልማት
ሃብቶች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ከሚያስከተሉ ውስጣዊና ውጫዊ የዘርፉ ስጋቶች /Internal and external
risks/ በአግባቡ መከላከልና መጠበቅ ያስፈልጋል፡፡ ለዚህም የተቀናጀ የስጋት አስተዳደር ስርዓትን በባቡር

66
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
ዘርፍ በየደረጃው በመዘርጋትና በመተግበር ለተለዩ የዘርፉ ስጋቶች /Identified rail sector risks/ ተገቢና
ወቅታዊ የማስተካከያ እርምጃ /Mitigation Measures/ መውሰድ ለዘርፉ ቀጣይነት ቁልፍ ጉዳይ በመሆኑ
ተግበራዊ ማድረግ ይገባል፡፡ የዘርፉን እድገት ተከትሎ ያለውን አለም አቀፍ ምርጥ ተሞክሮ፣ ልምድና
የቴክኖሎጂ አማራጮችን በመጠቀም የባቡር ኢንዱስተሪውን ለአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭ እንዳይሆን
ማድረግም /Climate resilient rail sector development/ ይገባል፡፡

ዋና ዋና ሊተገበሩ የሚከናዎንበት ጊዜ ተግባራት ፈጻሚ አካል

ተ.ቁ. የሚገባቸው ስራውዎች


ከመቼ? እስከመቼ?

1 ለባቡር ደኅንነት አደረጃጀት 2016 2018 የዘርፉን የደኅንነት ጉዳዮች ተቆጣጣሪ አካል ትራንስፖርት ና
መዘርጋት (Regulatory Authority) በማደራጀት ሎጂስቲክ ሚኒስቴር
2016 2022 የባቡር ዘርፍ ጸጥታን የሚያስከብር መዋቅር ኢምባኮ፣
(Railway Police) በማደራጀት ትራንስፖርት ና
ሎጂስቲክ ሚኒስቴር

2 የክልልና የፌዴራል የጸጥታ 2016 2017 የባቡር ዘርፉ በተዘረጋባቸው ክሉሎች የባቡር የክክል መንግስታትና
አካላት የባቡር ጸጥታውንና ደህንነቱን ያሚያስጠብቁ የክልልና የፌደራል የጸጥታ የፌደራል መንግስት
ደህንነቱን እንዲጠብቁ ሀይሎች እንዲደራጁ ማድረግ
የአሰራር ስርዐት መዘርጋት

3 የደኅንነት አሠራር 2016 2022 የባቡር ትራንስፖርት የሕግ ማዕቀፍን በማጠናከርና ኢምባኮ፣
ስርዓቶችን መዘርጋት ተግባራዊ በማድረግ ትራንስፖርት ና
ሎጂስቲክ ሚኒስቴር

2016 2030 ዘርፉ በዓለም አቀፋዊ የደኅንነት ስታንዳርዶች ኢምባኮ፣


እንዲመራ በማድረግ (የዓለም አቀፍ የባቡር ትራንስፖርት ና
ማኅበራትን UIC, IRSC, … በመቀላቀል እና ሎጂስቲክ ሚኒስቴር
ለኢትዮጵያ የሚሆኑ ስታንዳርዶችን ቀምሮ
በመውሰድ)
4 አሳታፊ የባቡር ደኅንነት 2016 2020 ባለድርሻ አካላትን የሚያሳትፍ ቅንጅታዊ የደኅንነትና ኢምባኮ፣
ትግበራ ማከናወን የአደጋ ጊዜ ምላሽ ሰጪ (Emergency Handling) ትራንስፖርት ና
አሠራር መዘርጋት ሎጂስቲክ ሚኒስቴር

2016 2030 ኅብረተሰቡን አቀፍ የደኅንነት ሥራዎች (Community ኢምባኮ፣


based safety management) ማከናወን ትራንስፖርት ና
ሎጂስቲክ ሚኒስቴር

ኢምባኮ
የባቡር ዘርፍ የተቀናጀ ስጋት የተቀናጀ የስጋት አስተዳደር ስርዓትን በባቡር ዘርፍ
የባቡር ዘርፍ
5 አስተዳደር 2016 2030 በየደረጃው በመዘርጋትና በመተግበር
ትራንስፖረትና
ሎጀስቲክ ሚኒስተር

ሰንጠረዥ 10፡ የአስተማማኝ የባቡር ደኅንነትና ጸጥታ ስትራቴጂያዊ አቅጣጫ የጊዜ ሰሌዳ

67
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
አበይት ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች

አበይት ስትራቴጂያዊ ጉዳዮች የተባሉት የባቡር ዘርፉ ዋነኛ ምርትና አገልግሎቶችን ለተጠቃሚዎች
በውጤታማነት ለማቅረብ እና ዘርፉን ተወዳዳሪ ለማድረግ የሚያስፈልጉ ሲሆኑ፤ የዘርፉ ዋና ተልዕኮ
አተገባበር ላይ ስርነቀል ለውጥ በማምጣት ዘርፉን ወደ ስኬት ጎዳና ያሻግራሉ በሚል የተለዩ ናቸው።

5.3.1 ዘላቂ የመሠረተልማት ሃብት፣

የባቡር ሴክተሩ የሚጠበቅበትን ምርት (የመንገደኛና የጭነት ትራንስፖርት) እንዲያበረክት በዋነኝነት እንደ
እሴት የሚጠቀመው በመሠረተ-ልማት ሃብቱ መሆኑ ይታወቃል። ይህንን የመሠረተ-ልማት ሃብት
በውጤታማነት ለተፈለገው ዓላማ በዘላቂነት በማዋል ምርታማነትን ለማሳደግ ዘመናዊ የመሠረተ-ልማት
አስተዳደር ስርዓት መዘርጋት እና የመሠረተ-ልማቱን አጠቃቀም ማሻሻል ያስፈልጋል። በተጨማሪም
የዘርፉን ተወዳዳሪነት ለማረጋገጥ የመሠረተልማት ሽፋኑን ማሳደግና የአገልግሎት ተደራሽነትን መጨመር
የግድ ይላል።

ሀ. የመሠረተ-ልማት ሃብት አስተዳደርን ማሳለጥ

1ኛ. ዘመናዊ የመሠረተ-ልማት ሃብት አስተዳደር ስርዓት መዘርጋት

የመሠረተ-ልማት አስተዳዳሪው አካል ተልዕኮ የተገነባውን የባቡር መስመር እና ተያያዥ ሃብቶችን በአግባቡ
በመያዝ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት በሚችሉበት አቋም ላይ መሆናቸውን ማረጋገጥ፣ ከዚያም
ለትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪው በክፍያ በማቅረብ ገቢ እንዲያመነጩ ማድረግ እና በሚያመነጩት
ገቢ በዘላቂነት ለመቀጠል የሚያስችላቸውን የመሠረተ-ልማት ጥገና ማከናወን ነው።

በሃገራችን የባቡር ሴክተር በዚህ የእሴት ሰንሰለቱ አካል ዋነኛ ሚናዎች ላይ አስፈላጊው ልምድ ገና በበቂ
ሁኔታ ያልዳበረ ከመሆኑ አንጻር ለመሠረተ-ልማት አስተዳደር ውጤታማነት ከዚህ የሚከተሉት
መሠረታዊ የአሠራር ስርዓት ዝርጋታ ተግባራት መከናወን ይኖርባቸዋል።

➢ ውጤታማ የሆነ የመሠረተ-ልማት አመዘጋገብና አያያዝ ስርዓት መቅረጽና መተግበር


በሃገሪቱ ተገንብተው ወደ አገልግሎት የገቡትን እንዲሁም ግንባታቸው በቅርቡ ተጠናቆ አገልግሎት
የሚጀምሩትን ከባቡር መስመሮች ጋር ተያይዘው የሚገኙ የመሠረተ-ልማት ሃብቶች፣የመሬት ይዞታ እና
ተጓዳኝ ሃብቶች በአግባቡ በልዩነት በሚታወቁበት (uniqly identifiable) መንገድ የሚመዘገቡበት እና
በመረጃ ቋት የሚያዙበትን፣ ዋጋቸውም በአግባቡ ተሰልቶ የእሴት መጠናቸው የሚታወቅበትን (Asset
Valuation) ፣ የእሴት እንክብካቤ/ጥገና/ ታሪካቸው በአግባቡ የሚሰነድበትን ዘመናዊ የአሠራር ሥርዓት
ከዓለም አቀፍ የኢንዱስትሪው ልምድ በመቀመር መቅረጽ እና በሥራ ላይ ማዋል ያስፈልጋል።

68
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
➢ የመሠረተ-ልማት ደህንነት መጠበቅ
ደህንነቱ የጠበቀ የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት አጠቃላይ መሠረተ-ልማት ሀብቱ እና የደህንነት
የመገናኛ መሳሪያዎች ደህንነታቸው የተጠበቀ መሆኑን ማረጋገጥ ያስፈልጋል። መሰረተ ልማቱ
የሚጠቀሙ አካላት አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ዝግጅት እና አቅም ያላቸው እንዲሁም
የሚያከናውኗቸው ተግባራት ደህንነቱ የጠበቀ ስለመሆኑ ቀድሞ መረጋገጥ ይኖርበታል። ይህንን
ለመቆጣጠር የመሠረተ-ልማት ደህንነት አስተዳደር ስርዓት ተቀርጾ ተግባራዊ ማድረግ።
➢ የመጠቀሚያ ክፍያን (acess-fee) በመተመን የመጠቀሚያሥርዓት መዘርጋት
የመሠረተ-ልማት አስተዳዳሪው ለሚሰጠው የባቡር መሠረተ-ልማት የመጠቀም አገልግሎት የሚያስከፍለው
የመጠቀሚያ ክፍያን (acess-fee) መጠን እና አገልግሎቱ የሚሰጥባቸው ሁኔታዎች የሚወሰነው
በቁጥጥር ክንፉ ሲሆን ይህም ከመሠረተ-ልማቱ ጥገና እና የሠራተኛ ወጪ አንጻር አዋጭ በሆነ እና
ለገበያ ተደራሽ በሆነ ሚዛናዊ መርህ ማውጣት እና ግልጽ ማድረግ የሚያስፈልግ ሲሆንለዚህም የአጠቃቀም
እና የክፍያ አሰራር ሥርዓት የሚዘረጋ ይገባል። ከዚህ በተጨማሪ በመስመሩ የሚሰማሩ አገልግሎት
ሰጪዎች በፍትሃዊነት መስመሩን የሚጠቀሙበት ተገቢ የሕግ ማዕቀፎችን በማዘጋጀት ተግባራዊ
የሚያደርግ ይሆናል።
የመሠረተ-ልማት አስተዳዳሪው ለሚሰጠው የትራንስፖርት አገልግሎት የመጠቀሚያ ክፍያ የሚወሰነው
በቁጥጥር ክንፉ ቢሆንም አስተዳዳሪው ሊያስከፍል የሚፈልገውን የታሪፍ መጠን በማጥናት ማቅረብ
የሚችል ሲሆን የታሪፍ መጠኑ ለመወሰን የተጠቀመባቸውን ዝርዝር መረጃዎች አያይዞ በማቅረብ ታሪፉን
በማጸደቅ ጥቅም ላይ የሚያስውል ይሆናል።
➢ በመስመሩ የሚሠማሩ አገልግሎት ሰጪዎችን በፍትሃዊነት የሚጠቀሙበትን ሥርዓት መዘርጋት
የመሠረተ-ልማት አጠቃቀም ተመን ከተዘጋጀ በኋላ በመስመሮች ላይ የጭነትና መንገደኛ ትራንስፖርት
አገልግሎት ለመስጠት የተደራጁ ተቋማትን በፍትሃዊነት መስመሩን የሚጠቀሙበትን ተገቢ የሕግ
ማዕቀፎችን በማዘጋጀት የክፍያ አሠራር ስርዓትን ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል። ይህም በአውሮፓ
ሃገራት ከተተገበረው የክፍት ተደራሽነት (open-access) የለውጥ መንገድ ጋር ተመሳሳይነት ያለው
ነው።

2ኛ. የመሠረተ-ልማት ሃብትን አጠቃቀም ውጤታማ ማድረግ

ጠንካራ የመሠረተ-ልማት አስተዳደር የአሰራር ስርዓት ቢዘረጋም የመሠረተ-ልማት ሃብቱን ውጤታማ


በሆነ መንገድ ጥቅም ላይ እንዲውል ካልተደረገ የባቡር ሴክተሩ ስኬት አያገኝም። በመሆኑም የመሠረተ-
ልማት ሃብቱን አጠቃቀም ለማሳደግ ከዚህ የሚከተሉት ሊተገበሩ ይገባል።

➢ የመሠረተ-ልማት ሃብቶችን አጠቃቀም በተመለከተ የሕግ ማዕቀፍ ማዘጋጀት

69
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
የመሠረተ-ልማት አስተዳደርን ለመተግበር የሚያስፈልጉ የአሠራር ስርዓቶች በሴክተሩ ፈጻሚ ተቋም
መተግበር የሚችሉ ሲሆን የአሠራር ስርዓቱን ተግባራዊ ለማድረግም ሆነ ሌሎች ባለድርሻ አካላትን በግልጽ
ተልዕኮ ለማንቀሳቀስ እንዲቻል በሃገራዊ ደረጃ የሕግ ማዕቀፍ ማዘጋጀትና ወደ ትግበራ መግባት
ያስፈልጋል። ይህም፡-
• ለባቡር ዘርፉ የመሠረተ-ልማት ሀብት አያያዝና አጠቃቀም የፖሊሲና የስትራቴጂ አቅጣጫ፤
እንዲሁም በዘርፉ ይዞታ ስር ላሉ ሃብቶች አስፈላጊውን ከለላ የሚሰጥ መመሪያ/አዋጅ
ማውጣት፣
• የባቡር ሴክተር ቋሚም ሆነ ተንቀሳቃሽ ንብረቶች ደህንነት የሚያረጋግጥ የህግ ማዕቀፍ
ማዘጋጀትና መተግበር፣
• የባቡር ሴክተሩ ውስን ሃብቶችን ዘለቄታዊነትና ምርታማነትን ለማረጋገጥ ይህን ሃብት የዘርፉ
ዋና ዋና ተዋናዮች እንዴት እንደሚያስተዳድሩትና ስራ ላይ እንደሚያውሉት እንዲሁም
የአጠቃቀምና የባለቤትነት ወሰናቸው እስከምን ድረስ እንደሆነ የሚወስን ፖሊሲ ማውጣት እና
ሥራ ላይ ማዋልን ያካትታል።
➢ የመሠረተ-ልማት ሃብቶችን እሴት መጠበቅ

የመሠረተ-ልማቱን አጠቃቀም የማሳደግ ዋነኛው ዓላማ መስመሮቹ በኦፕሬሽን አቅማቸው መጠን ሙሉ


በሙሉ አገልግሎት እንዲሰጡ በማድረግ በአጠቃቀም ጉድለት ምክንያት ከመስመሮቹ ሊገኝ የሚችል
ጥቅም እንዳይባክን ለማድረግ ነው። ለዚህም መስመሮቹ በዘላቂነት ለረጅም ዘመን የሚያገለግሉበትን ሁኔታ
ማምጣት የሚያስችሉ ከዚህ በታች የተጠቀሱ ጉዳዮችን ተግባራዊ ማድረግ ያስፈልጋል።

• ወቅቱን የጠበቀ ጥገናና እድሳት በማድረግበመሠረተ-ልማቱ ላይ የሚገኙ እንከኖችን በየጊዜው


መፍታት፣
• የመሠረተ-ልማቶቹን ተፈጥሮአዊ አካባቢ በመጠበቅ ዘላቂነታቸውን ማረጋገጥ (የአፈር መሸርሸርና
የመሬት መናድን ለመከላከል በአረንጓዴ ሽፋን የተዳፋት ጥበቃ /Slope protection/ ሥራ መተግበር፣
የተፋሰሶችን /drainage/ ችግር በመፍታት የጎርፍ አደጋን አስቀድሞ መከላከል) ፣
• መሠረተ-ልማት ሃብቱ ከጸጥታ ችግር ለመከላከል ከፌደራል ፖሊስ፣ ከክልል ጸጥታ ሃይሎች
ጋር እንዲሁም ከማሕበረሰብ አቀፍ የጸጥታ አካላት ጋር የተጠናከረ ጥበቃ ማድረግ ።
• በአጠቃላይ የባቡር መሠረተ-ልማት ሀብት ጥበቃ (Rail infrastructure protection plan) ቀርጾ
ተግባራዊ ማድረግ

3ኛ. የመሠረተ-ልማትና ተያያዥ ሃብቶችን ምርታማነት ማሳደግ

በመሠረተ-ልማት አስተዳደር ላይ ከላይ የተጠቀሱት ስትራቴጂያዊ አቅጣጫዎች ያለ ተጨማሪ


ኢንቨስትመንት ያሉት የመሠረተ-ልማት ሃብቶች ውጤታማ አገልግሎት መስጠት የሚችሉበትን መንገዶች

70
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
የሚያሳዩ ናቸው። ሆኖም በተገነቡት መስመሮች ላይ እሴት በመጨመር እና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታቸውን
በማሳደግ የሃብቶቹን ምርታማነት መጨመር የሚስችሉ አቅጣጫዎች ካልታሰቡ ከመሠረተ-ልማቱ ሊገኝ
የሚችለውን ሰፊ ውጤት በተሟላ መልኩ ለማግኘት ይገድባል። በመሆኑም ከዚህ በታች የተቀመጡት
አቅጣጫዎች ተለይተዋል።

➢ በመሠረተ-ልማት ሃብቶቹ ላይ እሴት መጨመር፡-

የመሠረተ-ልማት ሃብቶቹ (በዋነኝነት የባቡር መስመሮቹ) የተገነቡበትን ዓላማ በስኬት በማከናወን


ከመስመሩ የሚጠበቀውን ምርታማነት ለማግኘት በራሱ በመስመሩ ላይ ተጨማሪ ኢንቨስትመንት
በማድረግ የአገልግሎት አቅሙን ማሻሻል ያስፈልጋል። በመሆኑም፡-
• የየባቡሮችን ምልልስ ቁጥርና ፍጥነት ከፍ ለማድረግ እንዲቻል፡-
✓ በአነስተኛ ወጪ በመስመሮች ላይ የተወሰነ የግንኙነት ቴክኖሎጂ ማስተካከያ ማድረግ፣
✓ የእግረኛና ተሸከርካሪ የምድር ማቋረጫዎችን (level crossing) ብዛት በመቀነስ የድልድይ
ማቋረጫዎችን (un-level crossing) ማቅረብ፣
• የሚሰጠውን አገልግሎት መጠን ለመጨመር እና የአገልግሎቱን ተደራሽነት ለማሳደግ ደግሞ፡-
✓ መስመሮቹን ከኢንዱስትሪ እና ከከተሞች ጋር የሚያገናኙ አገናኝ ሃዲዶችና መንገዶችን
መገንባት፣
✓ ተጨማሪ መተላለፊያ ሃዲዶችን በመገንባት የመስመሮችን ባቡር የማስተናገድ አቅም ማሳደግ
ያስፈልጋል።
➢ የመሠረተ-ልማት ሃብቶቹን ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ማሳደግ፡-

በመሠረተ_ልማቱ ላይ አስፈላጊው የአያያዝና የማሻሻያ ሥራዎች ቢሠሩም ስትራቴጂያዊ በሆነ መንገድ


መሠረተ-ልማቱ ሊያመነጭ የሚችለውን ገቢ እንዲያመነጭ ለማድረግ በቢዝነስ መርህ በመቃኘት መሠረተ-
ልማቱ አቅሙን አሟጦ አገልግሎት እንዲሰጥ መደረግ ይኖርበታል። ለዚህም፡-
• ሁሉንም የባቡር ጣቢያዎች ወደ አገልግሎት በማስገባት የአገልግሎቱን ተደራሽነት መጨመርና
ገቢን ማሳደግ፣
• የባቡር መስመር ተከትለው በተገነቡት የባቡር ጣብያዎችና ለቀጣይ ማስፋፊያ ስራ ታሳቢ ተደርገው
ተገቢውን የካሳ ክፍያ ተከፍሎባቸው የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ባላቸው ይዞታዎች ላይ ተጨማሪ
ገቢ ሊያስገኙ የሚችሉ ስራዎች በማከናወን የሴክተሩን ተቋማዊ ሕልውና ለማስቀጠል የሚያግዝ
ገቢማመንጨት ይቻላል።

ለ. የመሠረተ-ልማት ሽፋንን ማሳደግ

የባቡር ሴክተርን ውጤታማነት ለማረጋገጥ የተገነቡ የባቡር መስመሮችን ከማጠናከር ጎን ለጎን የተጀመሩ
እና በግንባታ ላይ ያሉ ፕሮጀክቶችን ትኩረት ሰጥቶ በማጠናቀቅ ወደ አገልግሎት ማስገባት በቀጣይ

71
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ስትራቴጂያዊ ጉዳይ ነው። ለዚህም የፕሮጀከቶቹን የፋይናንስ ጉዳይ መፍታት፣
ለመስመሮቹ አስፈላጊ አጋዥ መሠረተ ልማቶችን ማሟላትና የባለድርሻ አካላትን በቅንጅት ማሠማራት
ያስፈልጋል። በተጨማሪም የባቡር መሰረተ ልማቱን ከወደቦች ፣ ከኢንዱስትሪ ፓርኮችና ሰፋፊ ኮሜርሻል
እርሻዎችና ሌሎች የትራንስፖርት መሰረተ ልማቶች ጋር የማቀናጀት ስራ መስራት ወሳኝ ጉዳይ መሆነ
ታምኖበታል፡፡

1ኛ. በ2014 በጸደቀው የትራንስፖርት ማስተር ፕላን መሰረት አዳዲስ መስመሮች በመገንባት ሽፋኑን
ማሳደግ

ሃገራዊ የባቡር ሴክተሩ አሁን ባለው የኔትወርክ መጠን በቂ እና ተደራሽ የሆነ አገልግሎት ለመስጠት
የሚያዳግተው በመሆኑ የመስመሮቹን መጠን በመጨመር የአገልግሎቱን ተደራሽነት ለአገልግሎት
በሚያወጣው ዋጋ አነስተኛነትም ሆነ በደንበኛ ቁጥር ለማሻሻል ያስችለዋል። ሆኖም የባቡር መሠረተልማት
ለመገንባት የሚያስፈልገው የካፒታል ወጪ እጅግ ከፍተኛ ከመሆኑ አንጻር በቀጣይ የሚገነባቸው የባቡር
መሰመሮች ከመንግስት የሚሰጥ አቅጣጫ መነሻነትኢኮኖሚያዊ አዋጭነታቸው መሰረት በማድረግ ቅደም
ተከተል ወጥቶላቸው መገንባት ያስፈልጋል።

• የሚገነቡ አዳዲስ መስመሮች የሴክተሩን ውጤታማነት በሚያረጋግጥ መልኩ መምረጥ፤ ማለትም


የተገነቡ መስመሮችን ውጤታማ በሚያደርግ መልኩ፣ እንዲሁም የምርትና የኢንዱስትሪ
ማዕከላትን ከገበያ ጋር ማስተሳሰርን መሠረት ባደረገ መልኩ መምረጥ እና በሃገር አቀፍ ደረጃ
መግባባት መፍጠር፣
• ከጂቡቲ ወደብ በተጨማሪ ከሌሎች ጎረቤት ሀገራት ወደቦችና ከደረቅ ወደብ እንዲሁም ከኤርፖርት
ጋር የሚያገናኝ ተጨማሪ የባቡር መስመር በመገንባት ለሀገሪቱን የወጭና ገቢ ንግድ እምርታ
ድጋፍ ማድረግ ያስፈልጋል።
• የዘርፉ ውጤታማነትን ከሚወስኑ ጉዳዮች አንዱ ከሌሎች የትራንስፖርት አማራጮች ጋር
ተወዳድሮ የሚያገኘው የገበያ ድርሻ ከፍ ማለት ሲሆን፤ ይህም የአገልግሎቱ የተጠቃሚ ቁጥር
ሲጨምር ነው። ከዚህ አንጻር ተጠቃሚው ድረስ የሚደርስ የትራንስፖርት መሠረተ-ልማት
አውታር መዘርጋትን የሚጠይቅ ቢሆንም የባቡር ትራንስፖርት እንደመንገድ መሠረተልማት
ከደንበኛው በር ድረስ የሚዘረጋ መሠረተልማት ለመገንባት ባህሪው ስለማይፈቅድ በተቻለ መጠን
አካባቢያዊ ተደራሽነትን በሚያረጋግጥ መልኩና ከሌሎች የትራንስፖርት አማራጮች ማለትም
ከመንገድ፣ ከአየርና ከባህር ትራንስፖርት ጋር ተቀናጅቶ የሚሰራበትን መንገድ ማመቻቸት
ያስፈልጋል፣

72
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
• የተለያዩ የብድር ጫና በማያመጡ የፋይናንስ አማራጮች ቅደም ተከተልን እና ኢኮኖሚያዊ
አዋጭነትን ባማከለ መልኩ የገበያ ፍላጎቱን እስኪሸፈን ድረስ አዳዲስ መስመሮችን መገንባት
ያስፈልጋል።
• የዘርፉን የኢኮኖሚ ስኬል በመጨመር ተደራሽ የትራንስፖርት ዋጋ እንዲያቀርብ በማድረግ
ተወዳዳሪ የሚያደርገው ሲሆን፤ የሃገርን ኢኮኖሚ ዕድገት በማሳለጥ የሚያበረክተው አስተዋጽዖ
ደግሞ እጅግ የጎላ ነው።
በመሆኑም በሃገሪቱ ከተያዘው ሀገር በቀል (Home grown) የኢኮኖሚክ ሪፎርም አንጻር የባቡር
ትራንስፖርት ዘርፍ ለሀገሪቱ የሎጂስቲክስ አይነትኛ መፍትሄነቱ ታምኖበት ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ
ተቀሜታቸው ላቅ ያለ መሆኑ በጥናት የተደረሰባቸው የባቡር መሰረተ ልማት ፕሮጀክቶችን ለይቶ
ወደግንባታ በማስገባት በቀጣይ የዘርፉን ውጤታማነት በሚያጠናክር መልኩ መከናወን ይኖርበታል።

73
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
ተ.ቁ. ዋና ዋና ተግባራት የሚከናወንበት አተገባበር ፈጻሚ
ጊዜ

1 የመሠረተ-ልማት ሀብት አስተዳደርን እና ደህንነት ማሳለጥ

1.1 የመሠረተልማት ሀብት 2016 2017 የመሠረተልማት ሃብት አመዘጋገብና አስተዳደር የአሠራር ሥርዓት በመቅረጽ ትራንስፖርትና
አስተዳደር አሠራር ወደ ትግበራ መግባት ሎጂስቲክሰ
ስርዓቶችን መዘርጋት ሚኒስቴር ፣
ኢምባኮ
1.2 የመሠረተ ልምት ሀብት 2016 2017 የመሠረተ-ልማት ደህንነት አስተዳደር ስርዓት በመቅረፅ ወደ ትግበራ መግባት ትራንስፖርትና
ደህንነት መጠበቅ ሎጂስቲክሰ
ሚኒስቴር ፣
ኢምባኮ
2 የመሠረተ-ልማት ሃብት 2016 2017 የመጠቀሚያ ክፍያን (acess-fee) በመተመን የመጠቀሚያ ሥርዓት ኢምባኮ
አጠቃቀም ውጤታማነት መዘርጋት ወደ ትግበራ መግባት
ማሳደግ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪዎችን የሚስተናግድ የሕግ ማዕቀፍ፣ ኢምባኮ
ፍትሃዊ የመሠረተ-ልማት መጠቀሚያ (Fair Access) የአሠራር ስርዓት
መዘርጋት
የመሠረተ-ልማት ሃብቶችን አጠቃቀም የሕግ ማዕቀፍ ማዘጋጀት የትራንስፖርት እና
ሎጂስቲክ
ሚኒስቴር፣
ኢምባኮ
3 የመሠረተልማት ሃብቶችን 2016 2026 የመሠረተልማት ሃብቶቹን ደህንነቱ በመጠበቅ፣ እሴት መጨመር ማለትም ኢምባኮ
ምርታማነት ማሳደግ ወቅቱን በጠበቀ የመሠረተልማት ጥገናና እድሳት፣ በተፈጥሮአዊ አካባቢ
እንክብካቤ፣ የግንኙነት ቴክኖሎጂዎችን በማሻሻል፣ አገናኝ ሃዲዶችንና

74
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
መተላለፊያ ሃዲዶችን በመገንባት፣ የሰው የእንስሳትና የተሸሸርካሪ
ማቋረጫዎችን በማሻሻል…)

2016 2026 ከመሠረተ-ልማት ሃብቱ ጋር የተያያዙ እሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ኢምባኮ


በማሳደግ (በባቡር ጣቢያዎችና መስመር ዙሪያ ያሉ ይዞታዎችን በማልማት -
Transit Oriented Development)
4 የመሠረተ-ልማት ሽፋንን ማሳደግ

4.1 በ2014 በጸደቀው 2016 2030 የሚገነቡ አዳዲስ መስመሮች የሴክተሩን ውጤታማነት በሚያረጋግጥ እና ኢምባኮ
የትራንስፖርት ማስተር የሃገር ውስጥ ድርሻ በሚያሳድግ መልኩ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው የባቡር
ፕላን መሰረት የመሠረተ- መስመሮች መምረጥ እና መገንባት እንዲሁም በሃገር አቀፍ ደረጃ መግባባት
ልማት ሽፋን ማሳደግ መፍጠር፣

ሰንጠረዥ 11: ዘላቂ የመሠረተልማት ሃብት ስትራቴጂያዊ አቅጣጫ የጊዜ ሰሌዳ

75
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
5.3.2 ውጤታማ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት፣

የባቡር ሴክተርን ውጤታማ ለማድረግ ድንበር ዘለል የባቡር የጭነትና የመንገደኛ ትራንስፖርት
አገልግሎት (TBL) ሀገር አቀፍ (Regional railway) እንዲሁም የከተማ ውስጥ የባቡር መስመር
(Tram/LRT/Metro/Subway) ትራንስፖርት ለመስጠት የተገነቡትን እና ወደ አገልግሎት የገቡትን የባቡር
መስመሮች ውጤታማ ማድረግ ወሳኝ ነው። ለዚህም ሃብትን በውጤታማነት መጠቀም፣ የአገልግሎት
ተደራሽነትን ማሳደግ፣ እንዲሁም ለሴክተሩ አስፈላጊ ድጋፎችን ማድረግ ያስፈልጋል።

ሀ. የተንቀሳቃሽ ሃብት (Rolling Stock) ምርታማነትን ማሳደግ

የባቡር ዘርፉ ባለው መሠረተ-ልማት እና ዘመናዊ ባቡሮች ከፍተኛ አገልግሎት የመስጠት አቅም ያለው
ሲሆን፤ ያለውን የመሠረተ-ልማት እና የተንቀሳቃሽ ሃብቶቹን አገልግሎት አቅም በሙሉ አሟጦ መጠቀም
ውጤታማቱን ያሳድገዋል። ተንቀሳቃሽ (ባቡሮች) ሃብቶችን በውጤታማት ለመጠቀም፡-

• በቂና ዘላቂ የመለዋወጫ ግብዓት ማቅረብ፣ እንዲሁም


• የጥገና ማዕከል አቅርቦት እና አስተማማኝ የጥገና ስርዓት እንዲኖር ማድረግ ያስፈልጋል።

ለ. የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎትን ለተጠቃሚዎች ተደራሽ ማድረግ

የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት በሃዲድ ላይ የተገደበ የየየብስ ትራንስፖርት ዓይነት (guided rail
transport) በመሆኑ ተደራሽነቱን ለማሳደግ የሚስችሉ ሥራዎች ያስፈልጉታል።

የትራንስፖርት አገልግሎት ተደራሽ የሚሆነው መንገደኛ ከመነሻው እስከ መጨረሻ መድረሻው፤


የሚጓጓዘውም ጭነት ከምንጩ እስከ ተጠቃሚው መድረሱ እና የእንቅስቃሴው ዓላማ ሙሉ በሙሉ ሲሳካ
ነው። በመሆኑም የእሴት ሰንሰለቱ ሁሉም ንዑስ ክፍሎች ሙሉ በሙሉ በተመጣጣኝ አቅም ቀልጣፋና
ውጤታማ አገልግሎት ሊሰጡ ይገባል።

በሃገራችንም በዋነኝነት ከሃገር ወደ ውጭ ገበያ የሚቀርበው ምርትም ሆነ ለተጠቃሚዎች ከውጭ


የሚገባው አቅርቦት ከምንጩ እስከ ተጠቃሚው የሚያደርስ የተቀናጀ የትራንስፖርት ሥርዓት
እስካልተተገበረ ድረስ የሃገርን የዕድገት ፍጥነት መግታቱ አይቀርም።

በመሆኑም በመርከብ ተጓጉዞ የሚገባውን ጭነት ባቡር ከወደብ ተረክቦ እስከ ተጠቃሚው መድረሱን
ለማረጋገጥ በሃገር ውስጥ ያለውን ደካማ የሎጂስቲክስ ሥርዓት መደገፍ የሚስችል የባቡር ሎጂስቲክስ
አገልግሎት (Railway Logistics Service) በሴክተሩ ተግባራዊ መደረግ ይኖርበታል።

ይህም በገፍ የመጣውን ጭነት አራግፎ (Freight Handling) እና አከማችቶ (Warehousing) በዋና ዋና
ማዕከላት ለሚያዳርሱ አሠራጮች ምቹ ማድረግን (Dry Port Service including customs clearance)

76
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
፤ እንዲሁም ከወጪ ጭነት በኩል ደግሞ ዋና ዋና ኢንዱስትሪዎች የሚያመርቱትን የኤክስፖርት ምርት
የወጪ ንግድ ሂደቶቹን የሚፈቱ የጭነት ማስተላለፍ (Freight Forwarding) ፣ ከየምንጩ የመሰብሰብ
(Trucking) አገልግሎቶችን መስጠትን ሊያካትት ይችላል።

ሐ. የአገልግሎት ውጤታማትን የሚያመጡ ድጋፎችን ማድረግ

የባቡር ትራንስፖርትን ውጤታማ ለማድረግ በሴክተሩ ከሚከናወኑ ተግባራት በተጨማሪ በመንግስት ደረጃ
በሴክተሩ ላይ ሊፈጸሙ የሚገባቸው ወሳኝ የፖሊሲ እና የስትራቴጂ ለውጥ እርምጃዎች ከዚህ በታች
ተጠቅሰዋል።

1ኛ. የባቡር ዘርፍ የፖሊሲ ማዕቀፍ ማዘጋጀት

የባቡር ሴክተር ካደገባቸው ሃገራት ተሞክሮ እንደምናየው ዘርፉ በሙሉ አቅም ወጪውን ሸፍኖ አገልግሎት
መስጠት እንዲችል ለማድረግ በከፍተኛ ደረጃ በመንግስት የፖሊሲ ድጋፍ ይደረግለታል። በኢትዮጵያ
በተለይ በጭነት ትራንስፖርት ገበያ እንደ አዲስ አገልግሎት ሰጪ ለመቀላቀል ከፍተኛ እንቅፋቶች
(Barriers of Entry) ያሉ ሲሆን ከእነዚህም መካከል የካፒታል አቅም፣ ለሴክተሩ ገበያ በመፍጠር አቅም
የነባር አገልግሎት ሰጪዎች ተጽዕኖ እና የመሳሰሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው።

ዘመናዊ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት በሃገራችን ገና በጅምር ላይ ያለ ከመሆኑ አንጻር፤ እንዲሁም


ከሚፈልገው ከፍተኛ የካፒታል አቅም አንጻር የየብስ ትራንስፖርት የሚፈልገውን የመሠረተልማት አቅም
ገንብቶ እና የነባር አገልግሎት ሰጪዎችን ተጽዕኖ ተቋቁሞ ደንበኞችን በፍላጎት ባቡርን መርጠው ጭነት
እንዲያጓጉዙ ማድረግ በጣም ፈታኝ ያደርገዋል።

ማንኛውም የትራንስፖርት ዘርፍ አይነት የራሱ ጠንካራ የተወዳዳሪነት አቅምና ደካማ ጎኖች ሊኖሩት
እንደሚችሉ ይታወቃል፤ የባቡር ትራንስፖርት ሴክተርም የራሱ ጠንካራና ደካማ ጎኖች ያሉት ሲሆን
ከሌሎች የትራንስፖርት አይነቶች (Transport Modalities) አንፃር ሲወዳደር የሚከተሉት ባህሪያቶቹ
ከፍተኛ ተመራጭነት እንዲኖረው የሚያስችሉ ናቸው ፡-

1. ገፍ ጭነት በአጭር ጊዜ የማጓጓዝ አቅም


2. ረጅም ርቀት የሚጓጓዙ ጭነቶችን በዝቅተኛ ዋጋ የማጓጓዝ ጥቅም
3. የባቡር መስመሩ እስከ ወደብ ጫፍ ከተዘረጋ በቀጥታ ከመርከብ ወደ ባቡር ጭነት ማራገፍ
መቻሉ ሀገሪቱን ከተጨማሪ የዲመሬጅና የወደብ ተያያዥ ክፍያዎች የሚያድን መሆኑ

ከላይ የተጠቀሱትን የባቡር ከሌሎች ዘርፎች መወዳደሪያና የተለዩ ጥቅሞች ታሳቢ በማድረግ ጭነትን
ከወደብ የማውጣትና በረጅም ርቀት ውስጥ ወደሚገኙ ደረቅ ወደቦች የማጓጓዝ ስራ ለባቡር አገልግሎት
ተስማሚና በዘርፉ በዝቅተኛ ዋጋ መሰራት የሚችሉ በመሆናቸው ጭነትን በባቡር ከባህር ወደቦች ወደ

77
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
ደረቅ ወደቦች የማጓጓዝ ስራ በገበያ ተወዳዳሪነት ላይ ብቻ ባተኮረ መልኩ ለባቡር ትራንስፖርት ሴክተሩ
ክፍት እንዲሆን ማስቻል የመንግስት የፖሊሲ ድጋፍን ይጠይቃል።

2ኛ. የባቡር መሠረተ ልማቱን ለግል ኦፕሬተሮች ክፍት ማድረግ፤

የዘርፉን ውጤታማነት ሊያመጣ የሚችል ሌላውና ዋነኛው ስትራቴጂያዊ ምላሽ ደግሞ የንግድ
ተፎካካሪነትን በዘርፉ ውስጥ መፍጠር ነው። ሃገራችን ዕድሜ ጠገብ ነባር የባቡር መስመር ከጅቡቲ ጋር
የነበራት ቢሆንም የንግድ ተፎካካሪነትን በሚያሳድግ መልኩ ሌሎች ተዋናዮችን (በተለይ የትራንስፖርት
አገልግሎት ሰጪዎችን) ባለማሳተፉ የመሠረተ-ልማትም ሆነ ተንቀሳቃሽ ሃብቱ ምርታማ ካለመሆን
በተጨማሪ እያረጀና እየተበላሸ፣ የሰው ሃብቱም ተነሳሽነቱ አሽቆልቁሎ በቴክኖሎጂም ከዓለም ጋር
መራመድ ሳይችል ቀርቶ የመፍረሻ ዕድሜውን በመጠበቅ ላይ እንደሚገኝ ይታወቃል። ካለፈው ታሪካችን
በመማር፣ ከሌሎች ሃገራት እና ከዓለም አቀፍ የኢንዱስትሪውም ሂደት (trend) ተሞክሮ በመቅሰም
ዘመናዊው የሃገራችን የባቡር ሴክተር ውጤታማ እንዲሆን የገበያ ተወዳዳሪነትን ጽንሰ ሃሳብ ማስረጽ
የግድ ይላል።

ለዚህም ምንም እንኳ አሁን ያለው አጠቃላይ የባቡር መስመር ዝርጋታ አነስተኛ ቢሆንም በባቡር መንገደኛ
እና ጭነት ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ከአንድ በላይ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን በማሠማራት
ለደንበኛው የሚሰጠው አገልግሎት የተሻለ እንዲሆን ማድረግ እንዲሁም የዘርፉም የቴክኖሎጂ ደረጃ
በማሻሻል የገበያ ድርሻውን ማሳደግ ያስፈልጋል። በዚህ ሂደት ከመንግስት በተጨማሪ የግል ባለሃብትንም
በሴክተሩ ማሳተፍ ምሉዕ የገበያ ውድድር ማዳበር እና የዘርፉ ውጤታማነት ያረጋግጣል።

78
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
ዋና ዋና የሚከናወንበት አተገባበር ፈጻሚ
ተ.ቁ. ተግባራት ጊዜ
የተንቀሳቃሽ ሃብት 2016 2030 አስተማማኝና ዘላቂ የመሠረታዊ መለዋወጫ አቅርርትን ኢምባኮ

1 (Rolling Stock) በማረጋገጥ (ከአቅራቢዎች ጋር አስተማማኝ ግንኙነት


ምርታማነትን በመመስረት)
ማሳደግ
2016 2030 በፍጥነት የሚያልቁ የባቡርና የመሠረተ-ልማት አካላትን ኢምባኮ
በሃገር ውስጥ በማምረት (የራስ ኃይል የባቡር ግብዓቶች
ማምረቻ ቢዝነስ ዩኒት በማደራጀትና ከዓለም አቀፍ
አጋሮች ጋር በቅንጅት በመስራት)
2021 2026 በ 2030 ከባቡርና ሃዲድ አካላት 30% በሃገር ውስጥ ኢምባኮ
በማምረት (የአምራች ንዑስ ዘርፉን በግል ባለሃብት
ተሳትፎ በማጠናከር)
2016 2030 ለሃገር አቀፍ የባቡር መስመር እና ለከተማ ባቡር ኢምባኮ/ ከተማ
እንደአስፈላጊነቱ አስተማማኝ የጥገና ማዕከላት መገንባት አስተዳደር

የባቡር 2016 2016 የባቡር ሎጂስቲክስ አገልግሎትን በዘርፉ በራስ ኃይል ኢምባኮ

2 ትራንስፖርት መጀመር
አገልግሎትን
ለተጠቃሚዎች
ተደራሽ ማድረግ
2016 2030 የባቡር ሎጂስቲክስ አገልግሎትን የግል ባለሃብቶችን ኢምባኮ
ተሳትፎ በማረጋገጥ (በመንግስትና የግል ባለሃብት
ሽርክና - PPP)
2016 2030 የግል ኦፕሬተሮች ሊያሳትፍ የሚችል የባቡር ኢምባኮ
ትራንስፖርት ፖሊሲ መቅረፅ
የአገልግሎት 2016 2030 የባቡር ዘርፍ የፖሊሲ ማዕቀፍ መቅረፅ እና ተግባራዊ ኢምባኮ፤

3 ውጤታማትን ማድረግ ትራንስፖርትና


የሚያመጡ ሎጀስቲክ
ድጋፎችን ማድረግ ሚኒስተር
2016 2030 ኢምባኮ ፤

መሠረተ ልማቱን ለግል ኦፕሬተሮች ክፍት በማድረግ ትራንስፖርትና

የባቡር ሴክተር ውጤታማ የሚደርግ የገበያ ተወዳዳሪነትን ሎጀስቲክ

ጽንሰ ሃሳብ መቅረጽ እና ተግባራዊ ማድረግ። ሚኒስተር

ሰንጠረዥ 12፡ የውጤታማ የባቡር ትራንስፖርት አገልግሎት ስትራቴጂያዊ አቅጣጫ የጊዜ ሰሌዳ

79
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
6 ማጠቃለያ

የኢትዮጵያ የባቡር ትራንስፖርት ዘርፍ ልክ እንደ ሌሎች የአፍሪካ አገራት ሁሉ እድሜን ያስቆጠረ
ቢሆንም በተለያየ ወቅት በሚከሰቱ ችግሮችና ከቀደመው የባቡር ዘርፍ ትምህርት መውሰድ ሳይቻል
ቀርቷል ፡፡ የኢትዮጵያ ዘመናዊ የባቡር ሴክተር ከተደራጀ ከአስር ዓመት የሚበልጠው ቢሆንም በተለያዩ
የዕድገት ምዕራፎች በማለፍ እና ጥቂት የማይባሉ ስኬቶችን በማስመዝገብ አሁን ላለበት ደረጃ ደርሷል።
እስካሁን ባለው እድገት ሂደት መንግስት ለዘርፉ ያለው ትኩረት እና የገንዘብ ድጋፍ ከፍተኛ ሚና አላቸው፡
፡ ሆኖም ይህ የመንግስት የገንዘብ ድጋፍ አሁን ባለው ሁኔታ መቀጠል ስለማይችል የባቡር ዘርፉ እራሱን
ችሎ መቆም የሚችል፣ በአገር ውስጥ ባለሙያና ቴክኖሎጂ የሚደገፍ፣ ተወዳዳሪነትን መርህ ያደረገ
ስትራቴጂያዊ አቅጣጫን መዘርጋት ስላስፈለገ ይህ ፍኖተ-ካርታ ተዘጋጅቷል፡፡

ይህን ፍኖተ-ካርታ ለማዘጋጀት በሀገሪቱ እስካሁን የነበረውን የባቡር ትራንስፖርት ዘርፍ እድገት፣ በጊዜ
ሂደት የተገኙ ጠንካራ ጎኖች፣ ደካማ ጎኖችና፣ የተለያዩ አለማቀፋዊ ምርጥ የዘርፉ ተሞክሮዎች ፤
ለወደፊት አስቻይ ምቹ ሁኔታዎችን እና ሊያጋጥሙ የሚችሉ ተግዳሮቶችን በጥልቀት በመዳሰስ ለዘርፉ
የወደፊት እድገት ይጠቅማል የተባለውን የቢዝነስና የፋይናንስ ሞዴል ለትግበራ ቀርቧል፡፡

በአጠቃላይ ከወቅታዊ ተግዳሮቶች እና ከዓለም አቀፋዊ ተሞክሮዎች እንዲሁም ከዘርፉ የላቀ ሀገራዊ
ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ፋይዳ አንጻር ለሃገሪቱ የሚበጀውን የባቡር ሴክተር ስትራቴጂያዊ አቅጣጫ
በጥልቀት በመመርመር መንግስት ስትራቴጂያዊ ውሳኔ ሊያሳልፍ ይገባል።

80
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
7 ዋቢ ምንጮች

1. የመንግስትና ግል አጋርነት (PPP) (አዋጅ ቁ 1076/2010)


2. የካፒታል ገበያ ማቋቋሚያ (አዋጅ ቁ 1248/2013)
3. የመንግስት የልማት ድርጅቶች ማቋቋሚያ አዋጅ 25/84
4. የባቡር ኮርፖሬሽን የማቋቋሚያ ደንብ 141/2000
5. የባቡር ትራንስፖርት አስተዳደር አዋጅ 1048/2009
6. የባቡር ኮርፖሬሽን የማቋቋሚያ ደንብ የካፒታል ማሻሻያ
7. የኢትዮጵያ ማሪታይም ባለስልጣን መመሪያ ቁ 802/2013
8. African Development Bank Group, 2015: Rail Infrastructure in Africa, Financing Policy
Options, Transport, Urban Development & ICT Department, AFRICAN DEVELOPMENT
BANK.
9. Coulls, A. (2011, November 14). Railways as World Heritage Sites - International
Council on Monuments and Sites. ICOMOS. https://www.icomos.org/en/116-english-
categories/resources/publications/230-railways-as-world-heritage-sites
10. Cui, S., Pittman, R., & Zhao, J. (2021). Restructuring the Chinese freight railway: Two
scenarios. Asia and the Global Economy, 1(1), 100002.
https://doi.org/10.1016/j.aglobe.2021.100002
11. Dobbin, F. (1994). Cultural Models of Organization: the social construction of rational
organizing principles. https://ssrn.com/abstract=2417452
12. EFCCC, 2020: Ethiopia’s Climate Resilient Green Economy (CRGE) Strategy (2011-2019)
– Implementation Progress Assessment Report, Addis Ababa, Ethiopia
13. Federal Democratic Republic of Ethiopia, 2011: Climate Resilient Green Economy
(CRGE) Strategy. Addis Ababa, Ethiopia.
14. Federal Democratic Republic of Ethiopia Ministry of Transport and Logistic,2022:
ETHIOPIAN TRANSPORT MASTER PLAN POLICY AND STRATEGY 2022-2052,
Summary Report, Addis Ababa, Ethiopia.
15. Federal Democratic Republic of Ethiopia, Planning and Development Commission, 2021:
TEN YEARS DEVELOPMENT PLAN, A PATHWAY TO PROSPERITY 2021-2030,
Infrastructure Development Plan, PP. 48-53, Addis Ababa, Ethiopia.
16. Gourvish, T. (2006). THE OFFICIAL HISTORY OF BRITAIN AND THE CHANNEL
TUNNEL. Routledge. http://ndl.ethernet.edu.et/bitstream/123456789/76066/1/103.pdf

81
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)
17. IISD, 2016: THE SUSTAINABLE DEVELOPMENT GOALS (SDGs)/2015-2030/, IISD
Perspectives on the 2030 Agenda for Sustainable Development, the International Institute
for Sustainable Development, Geneva, Switzerland.
18. International Union of Railways /UIC/, 2007: THE RAILWAYS OF AFRICA “VISIONS
2025” Background paper, UIC strategy, 2007.
19. Kostas Tzanakakis, 2019: The Regulation of the Railway Sector Targeting an Optimal
Level of Service Quality and Efficiency, February 2019.
20. Organisation for Economic Co-operation and Development [OECD]. (1997). Railways:
Structure, Regulation and Competition Policy. https://www.oecd.org.
https://www.oecd.org/daf/competition/1920239.pdf
21. Stacey, J. (2018). A brief history of the railways. Rail Discoveries. Retrieved July 11,
2023, from https://www.raildiscoveries.com/the-discovery-blog/2018/september/a-brief-
history-of-the-railways/
22. The African Union Commission, 2015: AGENDA 2063, THE AFRICA WE WANT, “A
Shared Strategic Framework for Inclusive Growth and Sustainable Development & A
Global Strategy to Optimize the Use of Africa’s Resources for the Benefit of All
Africans”, September 2015.

82
የኢትዮጵያ የባቡር ሴክተር ፍኖተ-ካርታ (2016 - 2030)

You might also like