Professional Documents
Culture Documents
ህዳር/2016
ደብረ ማርቆስ
ማውጫ
1
መግቢያ..........................................................................................................................................................5
2. የፕሮጀክቱ ገለፃ.....................................................................................................................................10
2.2. ግብዓቶች......................................................................................................................................10
3. የአማራጮች ትንተና..............................................................................................................................13
2
5.1. በፕሮጀክቱ ትግበራ ወቅት የሚጠበቁ አሉታዊና አዋንታዊ ተጽኖዎች.........................................................18
5.2. አሉታዊተፅዕኖዎች..........................................................................................................................19
6. የህብረተሰብ ተሳትፎ..................................................................................................................................21
8.2. መግቢያ.............................................................................................................................................23
8.15. ዋቢ ማጣቃሻዎች.............................................................................................................................27
8.16. እዝሎች...........................................................................................................................................27
3
10. የአካባቢና ማህበራዊ ተጽእኖ ግምገማ ጥናት የሚካሄድበት የጊዜ ሰሌዳ.....................................................28
ሰንጠረዦችና ስዕሎች
4
መግቢያ
ቢቤት ትሬዲንግ የእምነ በረድና ግራናይት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በአማራ ክልል በደብረ ማርቆስ ከተማ እየተገነቡ
ካሉ ፋብሪካዎች መካከል አንዱ ነዉ፡፡ ቢቤት ትሬዲንግ የእምነ በረድና ግራናይት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማህበር በአማራ
ክልል በደብረ ማርቆስ ከተማ በመንቆረር ክፍለ ከተማ ቀበሌ 11 በ 25,283,726.93 ብር ከፒታል በመመደብ በእምነ
በረድና ግራናይት ፋብሪካ ለመሰማራት 2 ሄክታር ቦታ ጠይቆ ከተማ አስተዳደሩ ይሁንታ ሰጥቶታል፡፡ ፕሮጀክቱ በግንባታ
ወቅትና ስራ በሚጀምርበት ወቅት ከ 143 በላይ ስራ ፈላጊዎችን በጊዜያዊና በቋሚነት የሥራ እድል ተጠቃሚ ያደርጋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም የእምነ በረድና ግራናይት ፋብሪካ በተለያየ መጠን ጥራቱን የጠበቀ ምርት ለአገር ዉስጥ እና 60%
ለዉጭ ገበያ በማቅረብ በግንባታዉ ዘርፍ ለተሰማሩ የማህበረሰብ ክፍሎች በግብአትነት በማቅረብ የበኩሉን ድርሻ
በመሆኑም የዚህ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ቢኒያም አእምሮ ይህንን የአቅርቦትንና የፍላጎትን ክፍተት
ለመሙላት ካለው ጥልቅ ራዕይ የተነሳ ይህንን የእምነ በረድና ግራናይት ፋብሪካን አቋቁመዉ ለመስራት በዝግጅት ላይ
ይገኛሉ፡፡ ፕሮጀክቱን ከማቋቋም ጎን ለጎን ከፕሮጀክቱ ጋር ተያይዞ የሚመጡ ጉልህ የአከባቢ ተፅዕኖዎችን ለይቶ እነዚህ
ተፅዕኖዎች በፕሮጀክቱ አከባቢ በስነምህዳር፣ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ከመፍጠራቸው በፊት ተፅእኖዎችን
ለመከላከል የተፅዕኖዎችን የማቅለያ እቅድ እና የአፈፃፀም ስልት በባለሙያ አስጠንተው እና በሚመለከተው የአከባቢ
ባለሃብቶቹ በኘሮጀክቱ ግብዓት፣ተግባራትና ውጤት የተነሳ የሚከሰቱ ተጽዕኖዎችን ለመከላከልና ለመቀነስ የሚከናወኑ
ተግባራት በመፈጸም ተፅዕኖውን መቀነስ ካልቻሉ ለተጽዕኖው የካሳ ክፍያ እንዲፈፅሙ በአዋጅ ቁጥር 181/2 ዐዐ 3
ያስገድዳል፡፡ የአካባቢ አያያዝ እቅድ ተግባራትን/ግዴታዎችን በተቀመጠላቸው መጠን፣ የአፈጻጸም ጥራትና የጊዜ መርሃ
ግብር በማከናወን በየስድስት ወሩ የአፈጻጸም ሪፖርት ለሚመለከተው የአካባቢ መስሪያ ቤት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን ግዴታዎች አለመወጣቱ በአካባቢ ምርመራ፣ ክትትልና ቁጥጥር ከተረጋገጠ በአዋጅ ቁጥር
181/2 ዐዐ 3 አንቀጽ 25/4 መሰረት ብር 2 ዐ,ዐዐዐ /ሃያ ሺ ብር/ ቅጣት ያስቀጣል፡፡ ስለሆነም እነዚህን ስራዎች ለመስራት
እንዲመች ይህ የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ሰነድ አማካሪ ድርጅት በሆነው ኢትዮ ግሪን የአከባቢ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ
ሪፓርቱ የተዘጋጀው በአማራ ክልል የአካባቢ ተፅዕኖ ግምገማ መመሪያ ቁጥር 01/2010 አንቀጽ 11፣ ንኡስ አንቀጽ 11.1
እና 11.2 መሰረት ነው፡፡ ጥናቱ ከመጀመሩ በፊት ከፕሮጀክቱ ባለቤት ጋር ስምምነትና የስራ ውል ተወስዷል፡፡ ይህ ሪፓርት
5
ከመዘጋጀቱ በፊት አማካሪ ድርጅቱ የጥናት ቡድን በማቋቋም ስለፕሮጀክቱ የሚገልጹ መረጃዎችን ከባለቤቱ በመጠየቅና
ከኢንተርኔት በማፈላለግ፣ እንዲሁም ፕሮጀክቱ የሚካሄድበትን ቦታ በማየት አስፈላጊ የመስክ መረጃዎች ተሰባስበዋል፡፡
የአካባቢያዊና ማህበራዊ ነባራዊ ሁኔታዎች፣ የጥናት ስልትና የአካባቢውን ነዋሪዎች ተሳትፎን ያካተቱ መረጃዎችን
ይዟል፡፡ ለሪፓርቱ አጋዥና ተጨማሪ መረጃዎች በእዝል የተያያዙ ሲሆን ሪፓርቱ ሲዘጋጅ ጥቅም ላይ የዋሉ
ማጣቀሻዎችንም ይዟል፡፡ ሪፖርቱ በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ አረንጓዴ ልማት ጽዳትና ዉበት
የፕሮጀክቱ ጥቅል አላማ በከተማዉ እና በአካባቢዉ የሚስተዋለውን የግራናይት እና እምነ በረድ ፍላጎትና አቅርቦት
ክፍተት በመሙላት ለፕሮጀክቱ ባለቤት ገቢንና ለአካባቢው ማህበረሰብ የስራ እድልን መፍጠር ሲሆን ዝርዝር አላማው፣
1. ገቢን እና የስራ እድልን በመፍጠር ለአከባቢው ማህበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ለውጥ አስተዋፅኦ ማበርከት
2. ጥራት ያለው የእምነ በረድና የግራናይት ምርት በማምረት በግንባታዉ ዘርፍ መሻሻል አስተዋፅኦ ማበርከት
የተለዩ የአካባቢ ተጽእኖዎችን በአግባቡ ለመያዝ የሚያስችል የማቅለያ መሳሪያ /እርምጃዎችን/ ለማቅረብ፣
የፕሮጀክቱ ቦታ ሰሜን ኤርምያስ ንጉሴ ደቡብ ኤልሳቤት አለማየሁና ሶሎሞን አዲስ ምስራቅ መንገድ፣ ምዕራብ ክፍት
ቦታ ያዋስኑታል፡፡
6
ተ.ቁ ሰሜን ኬክሮስ ምስራቅ ኬንትሮስ
1 359831.59 1137707.047
2 359871.242 1137615.245
3 360052.587 1137700.116
4 360012.815 1137791.86
በመሙላት ለፕሮጀክቱ ባለቤት ገቢንና ለአካባቢው ማህበረሰብ የስራ እድልን በመፍጠር የፕሮጀክት ባለቤቱን
7
1.4.1. የፕሮጀክቱ ዝርዝር አላማዎች፡-
ለአወንታዊ ተጽእኖወች የማጎልበቻ እርምጃ እንዲሁም ለአሉታዊ ተጽእኖወች የማቅለያ እርምጃወች በመዉሰድ
ፕሮጀክቱን ገለልተኛ በሆነ አካል ከአካባቢና ከማህበራዊ እይታ አኳያ በመዳሰስ ሊከሰቱ የሚችሉ ተፅዕኖዎችን
የተለዩ የአካባቢ ተጽእኖዎችን በአግባቡ ለመያዝ የሚያስችል የማቅለያ መሳሪያ /እርምጃዎችን/ ለማቅረብ፣
ተያይዘው ሊመጡ የሚችሉ ጉልህ አውንታዊና አሉታዊ የአካባቢ ተፅዕኖዎችን ለመተንተን፣ የትንተና ዘዴዎችን፣ የተለዩ
አማራጮችን፣ የተፅዕኖ ማቅለያ እቅዶችንና የክትትልና ግምገማ እቅዶችን ለማመላከት ነው፡፡ ይህ የወሰን ልየታ ሪፖርቱ
በደብረ ማርቆስ ከተማ አካባቢ ጥበቃ አረንጓዴ ልማት ጽዳትና ዉበት ተጠሪ ጽ/ቤት ቀርቦ ከፀደቀ በኋላ ሙሉ የአከባቢ
ተፅዕኖ ግምገማ ጥናት ሰነድ የሚዘጋጅለት ይሆናል ፡፡ የአከባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ሪፖርቱም ጉልህ የአከባቢ ተፅእኖ
ሊያመጡ የሚችሉ ነገሮችን ለመለየት፣ የማቅለያ ዘዴዎችን ለመጠቆምና የአከባቢ ተፅዕኖ እቅድን፣ የክትትልና ግምገማ
8
1.7. የጥናቱ ስልት (ዘዴ)
1.7.1. ጥናቱ በሚካሄድበት ጊዜ ጥቅም ላይ የዋሉት ስልቶች ወይም ዘዴዎች፡-
ሪፓርቶችና ጽሁፎችን ማንበብ፡- በፕሮጀክት ባለቤቱ የቀረቡ ስለፕሮጅቱ የተዘጋጀ ጽሁፎችን፣ በአገሪቱ በክልሉ የወጡ
የፓሊሲ፣ የህግና አስተዳደራዊ ማዕቀፎችን በሚመለከት የወጡ ሰነዶችና ከድረ-ገጾች የሚገኙ መረጃዎችን በማሰባሰብ
ለዚህ ሪፓርት ዝግጅት ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡ ይህ ዘዴ በዋናነት ስለፕሮጅቱ ምንነትና ምንግብአት ተጠቅሞ ምን ምርት
ህይወታዊ፣ቁሳዊና ማህበራዊ ሀብቶች ሁኔታ በሚመለከት መረጃ ተሰብስቧል፡፡ በዚህም የመስክ እይታ ወቅት
ፎግራፎችን በማንሳት ለሪፓርት ዝግጅት ጥቅም ላይ ውለዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የፕሮጅቱን መሬት መገኛ ኮርዲኔቶች
በጅ.ፒ.ኤስ. ለክቶ ከሳይት ፕላኑ ጋር በማረጋገጥ የኬንትሮስና ኬክሮስ መስመሮችን እንዲሁም ከባህር ጠለል ያለውን
የሳተላይት ምስሎችን መጠቀም፡- ከጎግል መሬት (Google Earth) ያለን የፕሮጀክቱን ቦታና አካባበውን የሚያሳይ ምስል
በመጠቀም የአካባቢው ሁኔታ፣ያላቸውን ርቀት፣ እንዲሁም የውሃ መውረጃዎችና ተዳፋታማነት ወዘተ. ለማወቅ ጥቅም
በአካባቢው የሚገኙ ሰዎችን ማናገር (መደበኛ ያልሆነ ቃለ መጠይቅ በማካሄድ) መረጃ ማሰባሰብ፡ በመስክ ጉብኝት ወቅት
የተገኙ ሰዎችን በተለይም ከፕሮጀክቱ አቅራቢያ የሚገኙ ነዋሪዎችን በመስክ ጉብኝት ወቅት ያገኘናቸውን ኗሪዎች
የተለያዩ የማወዳደሪያ መስፈርቶችን መጠቀም፡- ከፕሮጀክቱ አማራጮች ውስጥ የተሻለውን ለመምረጥ የሚያግዙ
መስፈርቶች የተዘጋጁ ሲሆን የአጥኝ ቡደኑ አባላት ለእያንዳንዱ አማራጭ ነጥብ እንዲሰጡ በማድረግ የተሻለው
እንዲመረጥ ተደርጓል፡፡ በተመሳሳይ ከተዘረዘሩ ተፅዕኖዎች መካከል ትኩረት የሚያስፈልጋቸውን ለመለየት መስፈርቶችን
ጥቅም ላይ እንዲውሉ ተደርጓል፡፡ የተባበሩት መንግስታት የአካባቢፕሮግራም (UNEP) ባዘጋጀው የስልጠና ማንዋል እና
የአማራ ክልል በቅርቡ ያወጣውን የአካባቢተፅዕኖ ግምገማ መመሪያ ቁጥር 001/2010 በተሰጠው አቅጣጫ መሰረት
መሆኑን ለመለየት ተችሏል፡፡ ምንም እንኳን መስፈርቶቹ የተፅዕኖ ግምገማውን ይዘት እንዳይለቅ ቢያደርጉትም
9
1.5. በጥናቱ የሚሳተፉ ባለሙያዎች ስብጥር
በጥናቱ በተለያዩ የሙያ ዘርፎች የተመረቁ እና በቂ ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች የሚመደቡ ሲሆን
2. የፕሮጀክቱ ገለፃ
የዚህ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ የሆኑት ቢኒያም አእምሮ በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ደብረ ማርቆስ ከተማ
መንቆረር ክፍለ ከተማ ቀበሌ 11 በ 2 ሄክታር ቦታ ላይ የእምነ በረድና ግራናይት ፋብሪካ ፕሮጀክት በማቋቋም እየተገበሩ
ያሉ ሲሆን ፕሮጀክቱ በሙሉ አቅሙ ሲሰራ በአመት 20,500 ሜትር ስኩየር የሚሆን እምነ በረድ ማምረት አቅም ያለዉ
ፋብሪካ ለመገንባት መሰረት አድርጎ የሚቋቋም ፕሮጀክት ነዉ፡፡ የፕሮጀክቱ የኢንቨስትመንት ወጪ ብር 126,062,551
ለ 143 ዜጎች ቋሚእና ጊዚያዊ የስራ እድልን ይፈጥራል፡፡ ለዚህ ጥናት የመስክ መረጃ በተሰባሰበበት ወቅት ፕሮጀክቱ
ቀደም ባሉት አመታት ጀምሮ ከ 3 ኛ ወገን ጸድቶ የቆየ ሲሆን ባለሃብቱ ባቀረቡት የኢንቨስትመንት ጥያቄ መሰረት
የከተማ አስተዳደሩ የፕሮጀክቱን አስፈላጊነት ከግምት ዉስጥ በማስገባት ይሄንኑ ፕሮጀክት ሊፈቅድላቸዉ ችሏል፡፡
2.2. ግብዓቶች
ቢቤት ትሬዲንግ የእምነ በረድና ግራናይት ማምረቻ ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የሚጠቀማቸዉ ዋና ዋና ግብአቶች
ከሃገር ዉስጥ የሚገኙ እምነ በረድና ግራናይት ማዕድን እነዚህ ግብአቶች በፕሮጀክት ባለቤቱ ከህጋዊ ማዕድን አዉጭዎች
እንደሚከተለው ይቀርባል፡፡
ፕሮጀክቱ የሚከተሉትን ማሺኖች በመግዛት ምርት ለማምረት ያቀደ ሲሆን የማሺኖቹ ጠቅላላ ዋጋ ብር
10
ተ. ዝርዝር HLQ_1600 HLQY-2300/2500
1. Max blade diameter mm 1600 230/250
2 Cross bram length mm 6000 7600/7800
3 Cutting length mm 3500 3500
4 Cutting width mm 2000 2000
5 Lifting strock mm 800 1350
5 Power of main monitor Kw 55(4p) 55(4p)
7 Power of pump motor Kw 4 4
8 Power of strock motor Kw 2.2 2.2
9 Power of vertical motor Kw 1.1 1.1
10 Gross power Kw 62.3 62.3
11 Gross weight Kg 10000 13000/14000
12 Diamenssion mm 65000*5000*4000 7800*5000*4500
ምንጭ፡- ከቢቤት ትሬዲንግ የእምነ በረድ እና ግራናይት ፋብሪካ የአዋጭነት ጥናት 2022 የተወሰደ
2.4. የግንባታ ወጪ
ክፍል፤ የቢሮ አገልግሎት የሚዉል ክፍል፣ የምርት ማከማቻ መጋዘን፣ መጸዳጃ ቤት እና የሰራተኞች የልብስ
መቀየሪያ ክፍሎችአሉት፡፡ ፕሮጀክቱ ለ 50 ቋሚእና ለ 25 ጊዚያዊ የሰው ኃይል የስራ እድል የሚፈጥር ሲሆን ብር
673,200 ብር አመታዊ ደመወዝ የሰው ኃይል ወጪ ተይዟል፡፡ ለፕሮጀክቱ የሚሰው ኃይል ብዛት እንደሚከተለው
ይቀርባል፡፡
ሠንጠረዥ 4 ፡ የሰው ኃይል
11
16 ጥበቃ ሰራተኛ 16 1026 196992
ልዩ ክፍያ 20 % 479640.20
ጠቅላላ ድምር 143 2877841.20
የግንባታ ዲዛይንና ሌሎች አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታዎችን አጠናቅቆ ከመጋቢት 2016 ዓ.ም ጀምሮ የግንባታ ስራዉን
የሚጀምር ሲሆን ከሚያዚያ 2018 ጀምሮ የምርት ማምረት ስራዉን ጀምራል፡፡ የፕሮጀክቱ የትግበራ ምዕራፎች
በጥቅሉ ቀጥሎ ባለው ሰንጠረዥ የተመለከተ ሲሆን በእያንዳንዱ ምዕራፍ ስር ያሉ ዝርዝር ተግባራት ደግሞ ከሰንጠረዡ
ቀጥሎ ተዘርዝረዋል፡፡
ሠንጠረዥ 5፡ የፕሮጀክት ትግበራ እና የሚካሄድበት ጊዜ ሰሌዳ
ተ.ቁ የሚከናወንበት ጊዜ
የፕሮጀክት ምዕራፍ
ከ እስከ
1 የግንባታ ስራ ማካሄድ ከየካቲት 2016 ሚያዚያ /2018 ዓ.ም
በሙሉ አቅሙ ምርት ማምረት ከሚዚያ/ 2018 ዓ.ም የካቲት/2095.ም
2 የመዝጊያ ምእራፍ ከየካቲት/ 2095 ዓ.ም ሰኔ 2095 ዓ.ም
12
የፋብሪካው ግብአቶችን መግዛትና ወደ ፋብሪካው ማስገባት
የጥራት ምርመራ ማካሄድ
የማስታወቂያ ስራ መሰራት
ፍሳሽና ደረቅ ቆሻሻዎችን ማስተዳደር
ለመንግስት አስፈላጊውን ግብርና ሌሎች የአገልገሎት ክፍያዎችን መፈጸም
የተቀጠሩ የፕሮጀክቱ ሰራተኞች በሌላ ተመሳሳይ ወይም አማራጭ ስራ እንዲቀጠሩ ማድረግ ወይም
በውሉ መሰረት ካሳ በመክፈል ማሰናበት፣
ፕሮጀክት የመዝጊያ እቅድ ማዘጋጀት ወይም/እና የአካባቢ አያያዝ እቅዱን መከለስ
ማሽኖችና ሌሎች መስሪያ መሳሪያዎችን ለዳግም ኡደት ወይም ለሌላ ተመሳሳይ ስራ የሚፈልጋቸው
ካለ ማስታወቂያ በመንገር ከተገኘ ውል መያዝ፣
ግንባታዎችና ማሽኖች ማፈራረስ አስፈላጊ ከሆነ (አስፈላጊ ፈቃድ/ዶች ያለውን የግንባታ አፍራሽ
መቅጠር) ፣
ግንባታው ሲፈርስ ጉዳት ሊደርስባቸው የሚችሉ ንብረቶች ካሉ ቦታ መቀየር፣ በአጎራባች ለሚገኙ
ፕሮጀክቶችም ማስጠንቀቂያ መስጠት (በወቅቱ በሚኖረው ህግ መሰረት) ፣
በግንባታዎች ላይ የተገጠሙና እንደገና ጥቅም የሚሰጡ ቁሳቁሶችን በጥቃቄ በማንሳት መሸጥ፣
የማምረቻ፣ አስተዳደርና ሌሎችንም ግንባታዎችን ማፈራረስ፣
የተተከሉ ማሽኖችንና ሌሎች መሳሪያዎችን መንቀል፣
የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን ማፈራረስ
በግቢ ውስጥ የተፈጠሩ ጉድጓዶች በመድፈን ቦታውን በፊት እንደነበረው ማስተካከል፣
ቦታውን ለማስተካከል ጥቅም ላይ ያልዋለውን ቆሻሻ የከተማ አስተዳደሩ በፈቀደው ቦታ ላይና ሁኔታ
መድፋት፣
የፕሮጀክቱን ቦታ በማስተካከል ማስረከብ ወይም በሚመለከተው አካል ሲፈቀድ ለሌላ ፕሮጀክት
መጠቀም
ስለ ፕሮጅቱ መዘጋትና የተወሰዱ ጥንቃቄዎች ወዘተ የሚገልጽ ሪፓርት ለተቆጣጣሪው መስሪያ ቤት
ማቅረብ
3. የአማራጮች ትንተና
ይህንን ፕሮጀክት ተግባራዊ ለማድረግ ከአካባቢ ተፅዕኖ መቀነስ አንጻር የሚከተሉት አማራጮች ተለይተዋል፡፡
የሚኖሩ አሉታዊ ተጽዕኖዎች አይከሰቱም፡፡ ነገር ግን ተግባራዊ ካልተደረገ አውንታዊ ተጽዕኖዎች ማለትም
የፕሮጀክቱ ባለቤት የሚያገኘውና ለመንግስት የሚኖረው የግብር ገቢ ሊኖር አይችልም፡፡ ከዚህም በተጨማሪ
13
ፕሮጀክቱ ስራ ሲጀምር የሚኖረው የስራ እድል፣ ለአካባቢው የምጣኔ ሀብት እድገትና መሬቱን ለበለጠ
አማራጭ 2፡ ፕሮጀክቱ ተግባራዊ ቢደረግ፤ ፕሮጀክቱ ተግባራዊ ሲደረግ በዚህ ሪፓርት ውስጥ የተዘረዘሩት
አሉታዊ ተፅዕኖዎች የሚኖሩ ቢሆንም የፐሮጀክቱ ባለቤት ትርፍ ይጨምራል፣ መሬቱ የተሻለ አጠቃቀም
ይኖረዋል፣ የስራ እድል ይኖራል እንዲሁም የአካባቢውና የኢንዱስትሪ ክፍለ ኢኮኖሚ እድገት ላይ አወንታዊ
እንዲቀርቡ ያስችላል፡፡
ለፕሮጀክቱ የሚሆነው ዋናው ጥሬ እቃ የእምነ በረድ ማዕድን ሲሆን ይህ ማዕድን ከምዕራብ ጎጃም ዞን ከሚገኙ
ወረዳዎች፣ከአዊ ዞን ከሚገኙ ወረዳዎችና ከቤኒሻንጉል ክልል አሶሳ በመግዛትና በማስመጣት ለማምረት የታሰበ መሆኑን
አማራጭ 1፤ የእምነበረድ እና ግራናይት ፋብሪካ ግብዓት የመግዛት አማራጭ፡- ይህ አማራጭ ግብዓቱ በአማራ ክልል
ከሚገኙ የማዕድን አዉጭዎች ጥሬ ማዕድኑን ስለሚገዛና በተለይ በምዕራብ ጎጃምና በአዊ ዞን ፍቃድ ያላቸዉ ጥራቱን
የጠበቀ እመነ በረድና ግራናይት ማዕድን አዉጭዎች ስለሚገዛ ጥራቱን ለማረጋገጥ የሚባክነውን ጊዜ እና ወደ ቆሻሻነት
አማራጭ 1፡ ከአገሪቱ የኤሌክትሪክ ሀይል መረብ (ግሪድ) ሀይል ማግኘት፤ ፕሮጅከቱ የኤሌክትሪክ ሀይል በመጠቀም
ምርቱን ለማምረት አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ሲሆን ይህ የሀይል ምንጭ አቅርቦት የሚመቻቸው የደብረ ማርቆስ ከተማ
ለኢንዱስትሪ መንደሩ ከሚዘረጋው መስመር ሲሆን የሃይል ምንጩ ካለው አካባቢያዊ ተዛማጅነት አኳያ ተመራጭ ስለሆነ
ይህም ለፕሮጀክቱ ባለቤትም ሆነ ለአካባቢው ስነ ምህዳር ደህንነት ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል፡፡ ነገርግን የፕሮጀክቱ ባለቤት
ካላቸው ተነሳሽነት እና ፍላጎት አኳያ የኤሌክትሪክ ማከፋፋያ መስመሩ ፈጥኖ ካልተዘረጋ ፕሮጀክቱ ግንባታውን ጨርሶና
ለመተካትና የከተማ አስተዳደሩ የሚያቀርበውን የኤሌክትሪክ ሀይል አቅርቦት ከመጠበቅ በነዳጅ የሚሰራ “ጀኔሬተር”
መጠቀም ጥሩ አማራጭ ነው፡፡ ይሁን እንጅ በነዳጅ የሚሰራ ጀኔሬተር የድምጽ ሁከት ከማስከተሉ በተጨማሪ
የሚያወጣው ጭስ አየር ይበክላል፤ እንዲሁም የነዳጅ ዋጋ ከኤሌክትሪክ ዋጋ በበለጠ ወጭ ያስወጣል፡፡ ከአካባቢ ብክለት
14
አይን ሲታይ ነዳጅ አካባቢን ሚበክልና የአለምን ሙቀት የሚጨምር ሲሆን በኢትዮጵያ የሚመረተውና የሚከፋፈለው
የኤሌክትሪክ ሀይል ግን ከውሃ የሚፈጠር ስለሆነ ታዳሽ በመሆኑ በአካባቢ ላይ የሚያሳድረው ብክለት አነስተኛ ነው፡፡
ከላይ በዝርዝር ከተመለከቱት አማራጮች መካከል ለታቀደው ፕሮጀክት የተሻለ የሆነውን ለመወሰን የጥናት ቡድኑ
አባላት ቀጥሎ በተቀመጠው የማወዳደሪያ መስፈርትና ሰንጠረዥ ተጠቅመው የተሻለውን መርጠዋል፡፡ የማወዳደሪያ
መስፈርቶች ምጣኔ ሀብታዊ ጠቀሜታ (የመነሻ እና ስራውን ለማስኬድ የሚያስፈልገው መዋእለ ንዋይ አነስተኛነት)፣
ለአካባቢ እንክብካቤ ያለው ጠቀሜት፣ እና ስራ ላይ ለማዋል ያለው ምቹነት ናቸው፡፡ በነዚህ የማወዳደሪያ መስፈርቶች
ስር ለእያንዳንዱ አማራጭ ከ 1 እስከ 10 ነጥብ እንዲሰጡ ከተደረገ በኋላ (10 ለጥሩ 1 ለመጥፎው አማራጭ) የአማካዩ
ማሳሰቢያ፡- ለእያንዳንዱ ማወዳደሪያ መስፈርት ከ 1 እስከ 10 ነጥብ እንዲይዝ የተደረገ ሲሆን፣ 10 የሚሰጠው በጣም
ጠቃሚ ለሆነው ሲሆን 1 ደግሞ ለማይጠቅመው (ጉዳትላለው) ነው፡፡ በእያንዳንዱ ጉዳይ ስር ከተቀመጡት አማራጮች
ውስጥ አጠቃላይ ውጤቱ ከፍተኛ የሆነው ለፕሮጀክቱ በአጥኝ ቡድኑ የተመረጠው አማራጭ ሆኗል፡፡
እንደ ደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት መምሪ የደብረ ማርቆስ ከተማ ከባህር ወለለል በላይ
ከ 2350 እስከ 2500 ሜትር ከፍታ ላይ የምትገኝና 18 ዱግሪ ሴንቲግሬድ አማካይ የሙቀት መጠን ያላት ናት፡፡ ከዚህ
15
በተጨማሪ በከተማ አስተዳደሩ ግብርና ጽ/ቤት መረጃ መሰረት ከተማዋና አካባቢው ከ 1300 እስከ 1380 ሚሊ ሜትር
የደብረ ማርቆስ ከተማ በምስራቅ ጎጃም ዞን ካሉት 5 የከተማ አስተዳደሮች አንዷ ስትሆን ስትራቴጅክ መገኛ ያላትና
ከአዲስ አበባ በሰሜን ምእራብ አቅጣጫ በ 300 ኪሎ ሜትር ፣ ከክልሉ ዋና ከተማ ከባህር ዳር ደግሞ በ 265 ኪ.ሜ ርቀት
ሊይ የምትገኝና የዞኑ ርእሰ ከተማ ሆና በማገልገል ላይ ትገኛለች፡፡ ከከተማዋ ከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ የተገኘዉ
መረጃ እንደሚያሳየው ከተማዋ በከተማ አስተዳደር ደረጃ በ 4 ክፍለ ከተሞችና በ 20 የቀበሌ አስተዳደሮች የተከፈለች
ከተማ ናት፡፡ አንፃራዊ መገኛዋን በተመለከተም መረጃው እንደሚያሳየው በሰሜን ጎዛምን ወረዳ፣ በደቡብ ጎዛምን ወረዳ
፣ በምስራቅ አነደድ ወረዳ ፣ በምዕራብ ጎዛምን ወረዳ ያዋስኗታል፡፡ ጂኦግራፉያዊ መገኛዋም 100 170 እስከ 100 21'30'
ሰሜን ኬክሮስ እና 37 042'00'' እስከ 37 045'30'' ምስራቅ ኬንትሮስ ላይ ነው፡፡ የከተማዋ አጠቃላይ ስፊት 17000 ሄ /ር
ያህል ሲሆን ከከተማ አስተዳደ ግብርና ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ እንደሚያሳየው ከተማዋ ከባህር ወለል በላይ በ 2388
ሜትርና በ 2500 ሜትር ከፍታ ልዩነት መካከል ትገኛለች ፡፡ የከተማዋ የሙቀት መጠን ከፍተኛው 24 ዲግሪ ሴንቲግሬድ
ዝቅተኛው 18 ዲግሪ ሴንቲግሬድ እና አማካይ አመታዊ የሙቀት መጠን ደግሞ 21 ዱግሪ ሴንቲግሬድ መሆኑን የጽ/ቤቱ
መረጃ ያሳያል፡፡ ይህን መነሻ በማድረግ ወይና ደጋ አካባቢ ላይ የተከተመች ከተማ ናት፡፡ የከተማዋን የመሬት አቀማመጥ
ስናይ ሜዳማ ፣ተራራማና ተዳፊታማ ገጽታዎችን የተላበሰችና በውስጧ ጨሞጋ ፣ውትረን፣ውሰታ፣ የግምጅ፣አባሂም
እና ሌሎች ወቅታዊና አመታዊ የሚፈሱ ወንዞችን የያዘች ከተማ ስትሆን እንዲሁም የወንቃ እና ፣የራባ ጥብቅ ደን
ያለባት ከመሆኑም በላይ የጮቄ የውሀ ማማም በከተማዋ በቅርብ ርቀት የሚገኝባት ከተማ ናት
16
እየሰጡ ይገኛሉ፡፡ የሚያመነጩትን የምርት መጠንም ቁጥር ስድስት፣ቁጥር 10 እና ቁጥር 11 እንደቅደም ተከተላቸው
30፣9፣እና 28 ሊትር/ሴኮንድ ነው፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ሶስቱ ምንጮች ደግሞ በ 2007 እና በ 2008 ዓ.ም ተቆፍረው አገልግሎት መስጠት የጀመሩ ሲሆን ሙሉ
በሙሉ ሳይሆን በከፊል አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ መረጃው ያሳያል፡፡ በመረጃው መሰረት የውሀውን ጥራት
ለመጠበቅም በሳምንት ሶስት ጊዜ እንደሚመረመር እና ክሎሪን እንደሚጨመር ይደረጋል፡፡ የንፁህ መጠጥ ውሀ ሽፋኑ
67% ላይ እንደሚገኝም መረጃው ያሳያል፡፡ ክልሉ ያለበትን የንጹህ መጠጥ ውሀ ሽፋን ስናይ ደግሞ በገጠር 90.9%
በከተማ 75.05% መሆኑን ከፕላን ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡ በመሆኑም የከተማዋ የንጹህ መጠጥ ውሀ ሽፋን
ክልሉ በ 2011 ዓ/ም በከተማ ከደረሰበት 75.05% የውሀ ሽፋን ጋር ሲነጻጸር ዝቅተኛ ከመሆኑም በላይ 33 % ህዝብ
የንጹህ መጠጥ ውሀ ተጠቃሚ እንዳልሆነ ያሳያል፡፡ በአቅርቦት ዙሪያ ያሉትን ችግሮችን በተመለከተ የመብራት
መቆራረጥ በመኖሩ ምክንያት በተፈለገው መጠን ማምረት አለመቻሉን መረጃው ያሳያል፡፡
17
4.3.3. የህዝብ አሰፋፈር፣ሃይማኖት፤ቋንቋናባህል
ከተሞች የተለያዩ ማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋማትእና መሰረተ ልማት አውታሮች ፣በርካታ የሰው ሀይል የሚጠይቁ
ኢንዱስትሪዎችና የመንግስት ተቋማት ፣የተሻለ የንግድ እንቅስቃሴና የስራእድል ያላቸው በመሆኑ ፈጣን የህዝብ እድገት
ይስተዋልባቸዋል፡፡ የደብረማርቆስ ከተማ ስነ-ህዝብ ሁኔታም ከላይ በተገለጹት ምቹ ሁኔታዎች እንዲሁም ባላት ምቹ
የአየር ንብረት ምክንያት ከገጠር ወደ ከተማ ከፍተኛ ፍልሰት በመኖሩ እና በከተማዋ ባለው ውልደት ምክንያት ፈጣን
የህዝብ እድገት ይስተዋልባታል፡፡ በመሆኑም በ 1999 ዓ.ም የተካሄደው ህዝብና ቤቶች ቆጠራ መረጃ የከተማዋን ህዝብ
ሊገልጽ ስለማይችል የከተማዋ አስተዳደር ከንቲቫ ጽ/ቤት የከተማዋ ህዝብ በ 2012 ዓ.ም ወንድ 102,933 ሴት 112,067
በድምሩ 215,000 ህዝብ እንደሚገኝ የተገኘዉ መረጃ ያረጋግጣል ፡፡
በፕሮጀክቱ ውስጥም ሆነ በቅርብ እርቀት ምንም አይነት የምርምር፣ አርኪኦሎጂና ሃይማኖታዊ ተቋማት የሉም፡፡
ስለሆነም ፕሮጀክቱ ተግባሩን በማካሄዱ ቀጥተኛ በሆነ መንገድ የሚፈጠር ተጽዕኖ አይኖርም፡፡
በቀጥታና በተዘዋዋሪ የስራ እድል መፈጠር ይህ የሚስማር ፋብሪካ ፕሮጀክት በስራ ላይ ሲውል ለ 143 ቋሚና
ጊዜያዊ ሰዎች የስራ እድል የሚፈጠርላቸው ሲሆን የስራ እድል ፈጣራው ቅድሚያ ለአከባቢው ነዋሪዎች
ለአካባቢው ኗሪዎች የሚሰጥ እድል ይሆናል፡፡ፕሮጀክቱ ከሚሰጠው ቀጥተኛ የስራ እድል በተጨማሪ
የፕሮጀክቶችን ምርቶች በማከፋፈል በሚሳተፉ አገልግሎት ሰጭዎች አማካይነት በተዘዋዋሪ የስራ እድል
ይፈጥራል፡፡
ፋብሪካዉ ደረጃቸዉን የጠበቀ የእምነ በረድና ግራናይት ምርቶችን በማምረት በተለይም ለደብረ ማርቆስ
በማቅረብ ተጠቃሚ የሚያደርግ ሲሆን 60% የሚሆነዉን ምረቱን ደግሞ ወደ ዉጭ በመላክ የዉጭ
ምንዛሬ ያስገኛል፡፡
ድርጅቱ የገቢ ግብርና የትርፍ ግብር ለመንግስት ስለሚያስገባ የመንግስት ገቢ እንዲጨምር ያደርጋል፡፡
18
5.1.4. ለባለሀብቱ ትርፍ ማስገኘት
ፋብሪካዉ ከመጀመሪያ አመት ጀምሮ ትርፋማ ስለሆነ ባለሃብቱ የሚያገኙትን ትርፍ በሌሎች ተመሳሳይ
5.2. አሉታዊተፅዕኖዎች
5.2.1 በግንባታ ጊዜ የሚከሰቱ
የደረቅ ቆሻሻ መፈጠር፡- ፕሮጀክቱ በግንባታ ወቅት የላይኛው የአፈር ክፍል ለግንባታ ስለማይፈለግ ተቆፍሮ
በሚወጣበት ጊዜ ቆሻሻ ይፈጠራል፡፡ ይህ ቆሻሻ በአቅራቢያው በሚገኙ መንገዶች ወይም ወንዝ ወይም የጎርፍ
መፋሰሻዎች ላይ ከተደፋ የትራፊክ እንቅስቃሴን ያውካል ፣መንገዶችን ያቆሽሻል እንዲሁም በክረምት ወቅት
የጎርፍ መፋሰሻዎችን በመዝጋት መጥለቅለቅን ያስከትላል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የተከመረ አፈር የአካባቢው
መልካም እይታ ያበላሻል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ይህ አፈር የሚደፋበት ቦታ በውሃ አካላት ውስጥ ወይም አጠገብ
ወይም በእርሻ ወይም ለሌላ አገልግሎት በተዘጋጁ ቦታዎች ላይ ከተደፋ የአፈር ብክለትን ይፈጥራል፣ የወንዝ
ደለልን ይጨምራል፣ ወንዞች ወይም ወራጅ ውሃዎች የሚፈሱበትን መስመር ሊያስቀይር ይችላል፡፡
በግንባታ ጊዜ ከሚፈጠሩ የደረቅ ቆሻሻዎች ውስጥ እንደ ሲሚንቶ፣ ቀለም ፣ጅፕሰም ፣ ሚስማር፣ወዘተ
መያዣዎች ጥቅም ከሰጡ በኋላ በመጠራቀም የአካባቢውን መልካም ገጽታ ከማበላሸታቸው በተጨማሪ
በቀላሉ በነፋስ የሚወሰዱት ቆሻሻዎች የጎርፍ መፋሰሻዎችን በመዝጋት የጎርፍ መጥለቅለቅን ሊያስከትሉ
ይችላሉ፡፡ በተለይ የፕላስቲክነትና ብረታ ብረት ባህሪ ያላቸው ቆሻሻዎች በቀላሉ ስለማይቀልዙ የተክሎች ስር
ከመጸዳጃ ቤት ውጭ በመጸዳዳት አካካቢን ማቆሸሽ፡- በግንባታ ምዕራፍ በግምት እስከ 143 የሚደርሱ
ሰራተኞች በአንድ ጊዜ ሊሰማሩ ይችላሉ፣ እነዚህ ሰዎች በስራ ሰዓት የሚጸዳዱበት ሽንት ቤት ከሌለ በየክፍት
በግንባታ ሰራተኞች ላይ አደጋ ወይም የጤና ችግር መከሰት፡- ፕሮጀክቱ በሚገነባበት ጊዜ በጉድጓድ ውስጥ
በመሸከም አደጋ ሊደርስባቸው ይችላል፡፡ በተመሳሳይ ለግንባታ ጥቅም ላይ ያልዋለ ቆርቆሮ ወይም ሚስማር
19
5.2.2. በአገልግሎት ምዕራፍ የሚከሰቱ ተፅዕኖዎች
የደረቅ ቆሻሻ መፈጠር፡- ጥቅም በማይሰጡ የምርት መጠቅለያዎች፣ጥቅም ላይ የዋሉ የውሃ መያዣ
ፕላስቲኮች፣ ከአስተዳደር ክፍል የሚፈጠሩ ወረቀትና የመሳሰሉ የጽህፈት መሳሪያዎች፣ ወዘተ የቆሻሻ
ምንጮች ናቸው፡፡በገቁፋሮ ወቅት የሚወጣ አፈር ወደወንዝ በመግባት ብክለትን ሊያስከትል ይችላል፡፡
የደረቅቆሻሻ አያያዝ ደካማ ከሆነ በየቦታው በመበታተን የአካባቢውን ውበት ከመቀነሱ በተጨማሪ እንደ አይጥና
ሌሎች ጉዳት የሚያስከትሉ እንስሳትና ተባይ መደበቂያና መራቢያ በመሆን በሰውን ንብረትና ጤና ላይ ጉዳት
ያስከትላል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በነፋስና በዝናብ ውሃ በመጓዝ የውሃ መፋሰሻዎችን በመዝጋት በክረምት የውሃ
ጥለቅለቅ ከማስከተሉም በላይ የውሃ አካላትን በመበከል ለሰው ልጅ ጤና ተስማሚ እንዳይሆን ያደርጋል፡፡
የፍሳሽ ቆሻሻ መፈጠር፡ ከፋብሪካዉ የሚወጣ አገልግሎት የሰጠ የዉሃ ፍሳሽ፣ ከመጠዳጃ ቤቶች ፤
መታጠቢያ ክፍሎች የሚፈሰው ፍሳሽ ቆሻሻ፣ በአግባቡ ካልተወገደ አፈርን፣ የከርሰምድርንና የገፀ
ቆሻሻ በመሬት ላይ ከፈሰሰ አካባቢን በመበከል ለሰው እና ለእንስሳት ጤና ጠንቅ ከመሆኑ በተጨማሪ
የድምጽ ሁከት፡- ከፕሮጀክቱ ማሽኖች የሚወጣ ድምጽ በድርጅቱ ሰራተኞች ላይ ወቅታዊ የመረበሽ
የብዝሀ ህይወት መመናመን፡- ፍሳሽና ደረቅ ቆሻሻ በአግባቡ ቁጥጥር ካልተደረገባቸው በአካባቢዉ ስነ
በፕሮጀክቱ ሰራተኞች ላይ የሚደርስ የጤና ተፅዕኖ፡- የፕሮጀክቱ ሰራተኞች በስራ ደህንነት ማነስ
ምክንያት የጤና ጉዳት ሊደርስባቸው ይችላል፡፡ በዚህ ምዕራፍ ከላይ በተገለጹት በድምጽ ሁከት፣
በመጥፎ ሽታ፣ በእሳት ቃጠሎና በሌሎች አደጋዎች ምክንያት የጤና ችግር የሚገጥማቸው ሲሆን
20
የኤሌክትሪክ ንዝረትና በእሳት መቃጠል፡-የኤሌክትሪክ መስመሮች ያልተሸፈኑ ከሆነና ሰራተኞች
ሊደርሱባቸው የሚችሉ ከሆነ በኤሌክትሪክ በመያዝ ጉዳት ሊደርስባቸው ይችላል፡፡ በተጨማሪም የክር
ማምረቻ ፋብሪካው ጥብቅ ቁጥጥር ካልተደረገለት የእሳት አዳጋ ሊፈጠር ስለሚችል የድርጅቱ
ሰራተኞች እና በአካባቢዉ የሚገኙ ሌሎች ፋብሪካወች የእሳት አዳጋ ተጋላጭ ሊሆኑ ያችላሉ፡፡
በተላላፊ በሽታዎች መያዝ ፡- በፕሮጀክቱ ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች ከተለያዩ ቦታዎች ከሚገኙ
ደንበኞች ጋር ስለሚገናኙ ለተላላፊ በሽታዎች እንደ ኤች አይቪ፣ ኮሌራ፣ የአባለዘር በሽታች፣ ኮረና
ቫይረስና ለሌሎች ተላላፊ በሽታዎች ሊያዙ ይችላሉ፡፡ ስለሆነም ተላላፊ በሽታዎች እንዳይተላለፉ
በፕሮጀክቱ በኩል የመከላከልና የመቆጣጠር እርምጃ ላልተወሰደ አጠቃላይ የጤና ተዕዕኖ ስለሆነ ከፍተኛ
በፕሮጀክት መዝጊያ ምዕራፍ የሚከሰቱ ተፅዕኖዎች በሁለት መልኩ ማየት ይቻላል፡፡እነሱም አንዱ የፕሮጀክት
ባለቤቱ ግንባታዎች ናማሽኖች ወዘተ እንዳሉ ትቶ ሲሄድ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የፕሮጅት ባለቤቱ
ግንባታዎችን አፈራርሶ መሬቱን ወደነበረበት በመመለስ ሲያስረክብ ነው፡፡የዚህ ጥናት ቡድን ሁለተኛውን
ቢሆንስ ማለትም የፕሮጅቱ ባለቤት ፕሮጅቱን አፈራርሶ መሬቱን እንደነበረበ ማስተካከል ይመለሳል የሚለውን
ቋሚና ጊዜያዊ ሰራተኞች ከስራ እንዲለቁ መደረግ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ሌላ ገቢ የሌላቸው ወይም ሌላ
የደረቅ ቆሻሻ መፈጠር፡ ማሽኖች ሲነቀሉ፣ ህንጻዎች ወይም ቤቶች ሲፈርሱ፣ በሲሚንቶ የተደለደሉ
መንገዶችና ሌሎች ግንባታዎች በሚፈርሱበት ጊዜ የተለያየ ባህሪ ያለው ቆሻሻ ይፈጠራል፡፡ ከነዚህም
ቆሻሻዎች ውስጥ የብረትነት ባህሪ ያላቸው (ማሽኖች፣ ቆርቆሮዎች፣ የአርማታ ብረቶች፣ በርና መስኮቶች፣
ወዘተ)፣ የድንጋይና አፈርነት ባህሪ ያላቸው፣ የፕላስቲክ፣ እንጨትናመስታውትነት ባህሪ ያላቸው ቆሻሻዎች
ይፈጠራሉ፡፡
21
በአቅራቢያ ያለንብረት ላይ ጉዳት ማድረስ፡- አንዳንድ ቁመታቸው ከፍተኛ የሆኑ ግንባታዎች በሚፈርሱበት
6. የህብረተሰብ ተሳትፎ
የቢቤት ትሬዲን የእምነ በረድና ግራናይት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ፋብሪካ ፕሮጀክት አካባቢ ቦታ የወሰን ልየታ
ቪጋርና የአካባቢ ተፅዕኖ ሰነድ ለማዘጋጀት በቀን 27/02/2016 ዓ.ም ከቦታው በመሄድ ቅኝት በማካሄድ የታየ
ሲሆን ቦታው በኢንዱስትሪ መንደር የሚገነባ በመሆኑ ከመኖሪና ከድርጅት አካባቢ ብዙም ቅርበት የሌለዉ
በመሆኑ በመኖሪያ አካባቢ ይደርሳል ተብሎ የሚያሰጋ አሉታዊ ተፅዕኖ የለም፡፡ የእምነ በረድና ግራናይት ፋብሪካዉ
ግንባታ የሚካሄድበት መሬት ካሳ ተከፍሎበት በኢንደስትሪ መንደር የተከለለና ከማንኛዉም የግልም ሆነ
የመንግሰት ይዞታ ነፃ የሆነ በመሆኑ በግለሰብ ደረጃ የሚፈናቀልም ሆነ ንብረት የሚያጣና ቀጥተኛ አሉታዊ
ተፅዕኖ የሚደርስበት የማህበረሰብ አካልም ሆነ ድርጀት ባለመኖሩ የማህበረሰብ ዉይይት ማድረግ አላስፈለገም ፡፡
ፕሮጀክቱ በአከባቢው በሚኖሩ ውሃማ አካላት እና በውሃ ውስጥ በሚኖሩ እንስሳት እና እፅዋት ላይ
ኢትዮ ግሪን የአከባቢ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች አማካሪ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር
የፕሮጀክቱን ዝርዝር የአከባቢ ተፅዕኖ ግምገማ ለማካሄድ በሚከተሉት ነጥቦች ላይ ትኩረት ለማድረግ
22
8.1. አጠቃላይ መግለጫ
የፕሮጀክት ስምና አድራሻ፣ የፕሮጀክት ባለቤትስም፣ ጥናቱን ያጠናው የአማካሪ ድርጅት ስም፣የፕሮጀክቱ
ምንነት አጭርና ግልፅ ማብራሪያ፣ የፕሮጀክቱ ቦታ አጭርና ግልፅ መረጃ፣ የፕሮጀክቱ አማራጮች፣ በፕሮጀክቱ
ምክንያት ይከሰታሉ ተብሎ የሚገመቱ ዋና ዋና የአከባቢ ተፅዕኖዎች፣ የተለዩ የተፅዕኖ ማቅለያ ዘዴዎችና፣
8.2. መግቢያ
ጥቅል አላማ
ዝርዝር አላማ
23
ያጋጠሙ እጥረቶችንና ውስንነቶችን ለማስወገድ የተወሰዱ የመፍትሄ እርምጃዎችን መግለፅ
የአከባቢ የመሬት ስሪት ወይም የይዞታ ሁኔታ፣በዙሪያው የሚገኝ የመሬት ሁኔታ፣ በአከባቢው ያሉ ግልፅ የሚታዩ
ተግዳሮቶች፣በፕሮጅቱ አካባቢ ያለው የመሰረተ ልማት የአገልግሎት ሁኔታ
አሀዛዊና አሃዛዊ ያልሆኑ ፊዚካላዊና ስነህይወታዊ መረጃዎች ለምሳሌ የአየር ንብረት፣ አፈር፣ የውሃ
ሀብት፣የስርዓተ ምህዳር፣የመሬት አቀማመት፣የእፅዋትና እንስሳት አይነት ስርችትና ብዛት
የምጣኔ ሀብታዊ መረጃዎች ለምሳሌየህዝብ ቁጥርና ስርጭት፣የእድሜ ስብጥር፣ የኢኮኖሚያዊ እድገት
ሁኔታ፣የውልደት ሁኔታ፣ የቤተሰብ የገቢ ሁኔታ መረጃ፣የኑሮ ሁኔታ፣የመሰረተ ልማት አገልግሎት፣የቤቶች
ሁኔታ፣የሀይል ፍጆታ፣ የውሃ አቅርቦት
ባህላዊና ታሪካዊ ቦታዎች ለምሳሌ ፓርከች፣ የዱር እንስሳት መጠለያ ቦታዎች፣ መህስብ ቦታዎችና ሀውልቶች፣
ትኩረት የሚሰጣቸው የሀይማኖት ቦታዎች
ተፅዕኖ የሚደርስበትን ቦታ የሚያመላክቱ ኮርዲኔቶች፣ ከለርድ ፎቶ ግራፎች፣ ሰንጠረዦችና ሌሎች ገላጭ
መረጃዎች
የፕሮጀክት ትግበራ ቦታን የሚያሳይ ካርታና የፕሮጀክት ሳይት ፕላን
ፕሮጀክቱ ድንበር ተሸጋሪ ተፅዕኖ የሚያደርስ ከሆነ ተፅዕኖ የሚደርስበትን አካባቢ የፊዚካላዊና ስነህይወታዊ
እንዲሁም ማህበራዊና ምጣኔ ሀብታዊ መረጃዎች
24
8.11. የተፅዕኖ ማቅለያ እርምጃዎች
የተፅዕኖዎች ዝርዝር
በእያንዳንዱ ተፅዕኖ የታቀዱ የተፅዕኖ ማቅለያ ዝርዝር ተግባራት የተመደበ የገንዘብ መጠን
በእያንዳንዱ ተፅዕኖ የታቀዱ የተፅዕኖ ማቅለያ ዝርዝር ተግባራትን የሚተገበሩበት የጊዜ ሰሌዳ
በእያንዳንዱ ተፅዕኖ የታቀዱ የተፅዕኖ ማቅለያ ዝርዝር ተግባራትን የሚፈፅሙት አካላት ዝርዝር
25
ዕዝል 2 በአካባቢና ማህበራዊ ተጽዕኖዎችን ለመለየት የሚያገለግል ቸክሊስት
ሊከሰቱ የሚችሉ ተፅዕኖዎች አሉታዊ ተፅዕኖ አዎንታዊ
ተፅዕኖዎች የለውም ተፅዕኖዎች
በቁስአካላዊ አካባቢ ላይ የሚፈጠር ተፅዕኖ
1.1 ገፀ-ምድር
የአፈር ክለት X
የመሬት አጠቃቀም ለውጥ X
የመሬት ገደላማነትና ተዳፋትነት መፈጠር X
1.2 አየር
በብናኝ ምክንያት የአየር መበከል X
የመጥፎ ሽታ መፈጠር X
የአደገኛ አየር በካይና ኦዞንን የሚጎዱ ጋዞች ልቀት/CFC ጋዞች/ X
በዐየር ነፃ\ዝውውርና ሙቀት ላይ የሚፈጠር ተፅዕኖ X
1.3 የውሃ ሃብት
በተበከለ የውሃ ልቀት ምክንያት በውሃ ሃብቶችና ስርዓት ላይ የሚደርስ ብክለት X
በውሃ ስርገት፣ፍሰት ስርዓትና የጎርፍ መጠን ላይ የሚፈጠር ለውጥ X
በከርሰ ምድር ውሃ ጥራት ላይ የሚከሰት ለውጥ X
በገፀ-ምድር ውሃ ላይ የመልክ የሙቀትና መሰል የበሃሪ ለውጦች መከሰት X
በሰው ወይም በንብረት ላይ በጎርፍና መሰል ችግሮች የሚከሰት ችግር X
በውሃ አዘል መሬቶች ላይ በሚኖር ግንባታ የሚፈጠር ተፅዕኖ X
1.4 ቆሻሻ
ጉልህ የሆነ የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ መፈጠር X
1.5 የድምፅ ብክለት X
በስነህይወታዊ አካባቢ ላይ የሚኖር ተፅዕኖ
2.1 ዕፅዋት
የዕፅዋት ዝርያ ብዝሃነትና ምርታማነት ላይ የሚፈጠር ተፅዕኖ X
በመናመን ላ እነደሆኑ በተለዩ የእፅዋት ዝርያዎችና መኖሪያቸው ላይ የሚደርስ X
ተፅዕኖ
መጤ የእፅዋት ዝርያዎችን የማስገባትና ነባሮችን የመገደብ ተፅዕኖ X
o . የእንስሳት ህይወት
በመናመን ላ እነደሆኑ በተለዩ የእንስሳት ዝርያዎችና መኖሪያቸው ላይ የሚደርስ X
ተፅዕኖ
በዱር እንስሳት መኖሪያና እንቅስቃሴ አኗኗር መረበሽ X
የዱር እንስሳትን መኖሪና አኗኗር ማናጋት
3. ማህበራዊና ምጣኔሃብታዊ አካባቢ X
26
ሊከሰቱ የሚችሉ ተፅዕኖዎች አሉታዊ ተፅዕኖ አዎንታዊ
ተፅዕኖዎች የለውም ተፅዕኖዎች
3.1 የተፈጥሮ ሃብቶች
የተፈጥሮ ሃበቶችን ለልማት የመጠቀም ሁኔታ መጨመር X
ታዳሽ ያልሆኑ ሃብቶች የመመናመን/የማለቅ X
ጥብቅ ቦታዎች ፓርኮች ወንዞች ፣ ሃይቆች ላይ የሚኖር ተፅዕኖ X
3.2 ሃይል
በካይ የሃይል ምንጮችን መጠቀም/ነዳጅ X
ባለው የሃይል ምንጭ ፍላጎት ላይ ጭማሪ ማሳየት X
3.3 የትራፊክ ፍሰትና ተሸከርካሪ ዝውውር
ባለው የትራፊክ ፍስት ላይ ተጨማሪ ጫና መፈጠር X
በወቅታዊ የሰዎችና ቁሳቁስ እንቅስቃሴ ላይ ለውጥ መፈጠር X
የትራፊክ አደጋ ክስተት በእግረኛና በተሽከርካሪ ላይ መጨመር X
የአዲስ መንገድ መከፈት/ መገንባት X
o የህዝብ ቁጥር
የህዝብ ቁጥር እና ስርጭት በአካባቢው መቀየር X
3.5 የድንገተኛ አደጋ ክስተት
ፍንዳታ፣እሳት ቃጠሎ፣ የኬሚካልና አሌክቲሪክ አደጋ፣ ህንፃ መደርመስ ክስተቶች X
3.6 የሰው ጤና
በስራ ላይ በሚከሰት አደጋ የሚፈጠሩ የጤና እክሎች X
በአባላዘርና ተዛማጅ በሽታዎች ሚከሰት የጤና ተፅኖዎች X
3.7 ምጣኔሃብት
በአካባቢውም ሆነ በክልላዊ ምጣኔ ሃብት ላይ የሚኖር አወንታዊ ተፅዕኖዎች/ ገቢ X
ማደግ፣ መሬት ዋጋ ማደግ ወዘተ.
ለአካባቢው ማህበረሰብ የስራ እድል መፈጠር X
3.8 የማህበረሰብ ምላሽ
ከአካባቢው እሴት ባህልና ወግ ጋር የሚፃረሩ ሁነቶች መከሰት X
4.ውበትና ዕይታ
በአካባቢውና ዙሪያው ውበትና እይታ ላይ የሚኖር አሉታዊ ለውጥ X
5. ታሪካዊ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ቅርሶች
በቅርስነት በሚታወቁ ታሪካዊ ሃይማኖታዊ ባላዊና ተፈተሮአዊ ሃበቶች ላይ X
የሚደርስ ተፅዕኖ
8.15. ዋቢ ማጣቃሻዎች
8.16. እዝሎች
የቦታው ካርታ
የጥናት ቡድኑን የግል ሁኔታዎችን የሚገልፅ መረጃ
የአማካሪ የሙያና የንግድ ፍቃዶች
የፕሮጀክቱ ባለቤት ስለጥናቱ የሰጠው ትክክለኛ ማረጋገጫ
በቀረበው የመጀመሪያ የተፅዕኖ ዘገባ ላይ ገምጋሚ ባለሙያዎች የሰጡት አስተያት
27
አጠቃላይ መግለጫ
መግቢያ
የአካባቢ ተፅዕኖ ጥናቱ አላማ
የጥነት ወሰን
የጥናቱ ስልት ወይም ዘዴ
በጥናቱ ወቅት የተወሰዱ ታሳቢዎችና የነበሩ የእዉቀት ክፍተቶች
የፖሊሲ፣ የህግና የአስተዳደር ማዕቀፎች
የፕሮጀክቱ ገለጻ
የባዮፊዚካልና ሶሾኢኮኖሚ መሰረታዊ መረጃዎች ትንተና
የአካባቢ ተፅዕኖ ትንተና
የተፅዕኖ ማቅለያ እርምጃዎች
የአካባቢ አያያዝ እቅድ
የአካባቢ ክትትል እቅድ
በፕሮጀክቱ ትግበራ ተፅዕኖ የሚደርስባቸዉና የሚመለከታቸዉ አካላት ምክክር
ማጠቃላያ ምክረሃሳብ
ዋቢ መጽሀፍት ወይም ማጣቀሻዎች
በኢትዮጲያ እንዲሁም በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በወጡ የአካባቢና ማህበራዊ ተጽእኖ ግምገማ
ጋይድላይን፣ አዋጆችና መመሪያዎች መሰረት ማንኛዉም ፕሮጀክት ወደትግበራ ከመግባቱ በፊት በአካባቢ
ተጽእኖ ግምገማ ሂደት ዉስጥ ማለፍ እንዳለበት ይደነግጋሉ፡፡ በዚህም መሰረት በደብረ ማርቆስ ከተማ
መንቆረር ክፍለ ከተማ ቀበሌ 11 ኢንዱስትሪ መንደር ዉስጥ ሊቋቋም ለታቀደው ፕሮጀክት የአካባቢ ተጽእኖ
ግምገማ ጥናት ለማካሄድ ይህ የጊዜ ሰሌዳ /ቢጋር/ተዘጋጅቷል፡፡ ይህ ቢጋር በፕሮጀክት ባለቤቱ በቢቤት
ትሬዲንግ እምነ በረድና ግራናይት ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማህበር እና በአማካሪ ድርጅቱ ኢትዮ ግሪን የአካባቢ
ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች አማካሪ ኃ/የተ/የግ/ማ/ እንዲሁም ሰነዱን ገምግሞ በፕሮጀክቱ ላይ ዉሳኔ
የሚፈጽምአካል
1 የፕሮጀክቱን ቦታ በማየት መረጃዎችን ማሰባሰብ ዉይይት 27/02/2016 ዓ.ም በአጥኚ ቡድን
2 የአካባቢ ወሰን ልየታ ሪፖርት አዘጋጅቶ ማቅረብ 29/02/2016 ዓ.ም በአጥኚ ቡድን
ማካሄድ
28
3 የፕሮጀክት ባለቤቱ የአካባቢ ወሰን ልየታ ሪፖርቱን በደብዳቤ 02/03/2016 ዓ.ም በፐሮጀክቱ ባለቤት
ለደብረ ማርቆስ ከተማ አካባቢ ጥበቃ አረንጓዴ ልማት ጽዳትና
5 ዉበት ተጠሪ ጽ/ቤት ማቅረብ
የቀረበዉን የወሰን ልየታ ሪፖርት በመገምገም ግብረ መልስ 07/03/2016 ዓ.ም ገምጋሚ ቡድን
6 መስጠት
የአካባቢ ወሰን ልየታ ሪፖርት እንዲስተካከል ገምጋሚ ቡድኑ 03/03/2016 ዓ.ም በአጥኚ ቡድን
7 ግብረመልስ ከሰጠ አስተካክሎ በድጋሜ ለገምጋሚ ቡድኑ
የመጀመሪያዉን የአካባቢ ተጽእኖ ግምገማ ዘገባ ረቂቅ 11/03/2016 ዓ.ም በአጥኚ ቡድን
8 በማዘጋጀት ለፕሮጀክት ባለቤቱ ማቅረብ
በረቂቅ የአካባቢ ተጽእኖ ግምገማ ዘገባ ላይ ከፕሮጀክት ባለቤቱ 13/03/2016 ዓ.ም የፐሮጀክቱ ባለቤቱ
9 ግብረ-መልስ ካለ እንዲስተካከል ለአማከሪዉ መስጠት
የመጀመሪያዉን የአካባቢ ተጽእኖ ግምገማ ዘገባ ረቂቅ 16/03/2016 ዓ.ም የፐሮጀክቱ ባለቤቱ
10 ለገምጋሚ ቡድኑ ማቅረብ
የቀረበዉ የአካባቢ ተጽእኖ ግምገማ ዘገባ ገምጋሚ ቡድኑ 18/02/2016 ዓ.ም በአጥኚ ቡድን
የማስተ ካከያ አስተያየት ካለ ሰነዱን አስተካክሎ ማቅረብ
11 ተስተካክሎ የቀረበዉን ዘገባ መስተካከሉን መገምገም 20/03/2016 ዓ.ም ገምጋሚ ቡድን
12 በደ/ማ/ከ/አካ/ጥ/አረ/ል/ጽ/ዉ/ተ/ጽ/ቤት ፕሮጀክቱ ተግባራዊ 24/03/2016 ዓ.ም ገምጋሚ ቡድን
እንዲሆን ከተስማማ የይሁንታ ሰርቲፍኬት ለፕሮጀክት ባለቤቱ
ይሰጣል
11. የአማካሪ ድርጅቱ የንግድ ፈቃድ
29
30
31
32
33
በዚህ ጥናት የተሳተፍ ባለሙያዎች ሲቪ (CV)
CURRICULUM VITAE
Name: Tiruneh Engida Worku
Nationality: Ethiopian
Religion: Orthodox
Education Qualification
Amharic
English
Skill:
34
Basic Computer Skill
Basic SPSS soft wear Application skill
Basic Auto Cad and GIS Soft wear Application Skill
Hobby:
Reading Books
Following and attending spiritual events and spiritual songs
Watching T.V
Reference:
35
CURRICULUM VITAE
PERSONAL DETAILS
OBJECTIVE OR PROFILE
My qualification coupled with my career has led me to specialize in planning Monitoring and evaluation
of Hygiene and environmental health, global health and pollution, MBS, EIA, WASH HIV /ADIS IDSR,
ICCM, IMNCI, EPI, malaria, nutrition, hygiene and sanitation, TB, leprosy, supportive supervision,
communication skill, IEC/BCC vector biology, disease surveillance, reporting and response, project
management, Health service extension programs. And this opportunity helped me to take part in the
control of major communicable disease in our country in line with MDGs. My supervision experience has
left me skilled in with the function of Ethiopian health system reforms, organization structures, program,
and to preparing environmental impact assessment (EIA) and to suggested mitigation masseur for each
problem of the project.
EDUCATIONAL BACKGROUND
Debre Markos University:- Masters Degree in General Masters of Public Health on June 27/2015 G.C.
TOT ;- WASH on PHCU management and District Transformation and performance management
by FMOH 2018
EIA;- and Inter personal communication skill and building the skill of health professional to
work with community and to protected environment, population (April 2009)
Courses , Training and certification
TOT on TB and HIV integrated refresher training module for health extension professional
(October 2012)
36
TOT on EIA , CLTSH and on inter personal communication skill And IEC/BCC (April 2009)
TOT on accelerated implementation of health service extension program on EPI,RH, IMNCI, ENA
Malaria, Hygiene and environmental health, HIV/AIDS ,IEC ,Monitoring & Evaluation (July –
August 2006)
TOT on maternal, neonatal, child and Adolescent health ,Malaria, hygiene &
sanitation ,Nutrition and communication for health extension professional (NOV 2011)
TOT on ICCM and IMNCI ( Integrated Community Child Illness Management) September 2012
NGOs and Specia experience
Health service extensions program coordinator and Hygiene and environmental health officer
Gozamen district Health office November 2010 – to Present
Develop detail M&E monthly, quarterly and yearly action plan for programs
Monitor and evaluate these program based on the stretched objective
Follow up & evaluate the performance of health professional
Provide technical support & capacity building for health professional
Collect analyze and interpret the daily use of data
Conduct facilitative supervision and provide feed back
Recognize encourage and motivate health professional so as to maintain & improve
performance
Facilitate experience sharing meetings in collaboration with district health office and
Disseminate lessons learnt
Work in coordination with stake holders, NGOs supporting the health service delivery
system
Inspect both Urban and Rural water and sanitation projects
Take water sample and sent it for further lab analysis
Take part in water, sanitation &Hygiene projects site selection
Organize support and supervise school water sanitation and hygiene program
Prepare a summary of the activity report
37
Amahra Region Drought prevention and Food security program coordination Biro Relief
Regional coordinator under WFO (October 2009 – October 2010)
Prepare detail M&E annually, quarterly & yearly action plan and identify risk and drought
areas
Conduct supervision at zonal and district level stakeholder using designed checklist
Give in service training for health and agriculture professional
Regularly observe model households for graduation approval in collaboration with district
and health center staffs
Strengthen the referral linkage & health extension programs to HC ,
Prepare a detail monitoring and Evaluation of monthly, quarterly and yearly action plan
Give new license for nongovernmental for profit health facilities those which meet
minimum requirements
Project planning, monitoring and evaluation officer, Enarji Enawga district health office
Prepare detail M&E monthly quarterly & yearly action plan of a program
Take part in malaria epidemic forecasting, preparedness and control
Highly participate in indoor residual chemical spray for the control of malaria vector
Provide technical support and capacity building for health professionals
Conduct facilitative supervision & provide feed back
Train health staffs on HIV/AIDS and malaria prevention and control
Collect analyze and interpret the daily use of data and Produce and submit detail report
Other skills:- Computer literate, MS-Office Packages , XL
REFERENCES
38
1. Ato Ayalew Shiferaw Ayalaw Senior Program Officer at The Carter Center-Ethiopia (TCC),
ayalewsisu2003@gmail.com Tel. 09-13-49-13-65
2. Ato Wodosen Sige Amahra Region WASH Capacity building Advisor e-mail wendetsige@gmail.com Tel.
09-13-03-92-87
39
Curriculum vitae (CV)
I. Personal information
Name: Balager Anteneh Date of birth: May 16,1975 E.C
Junior: Shellel Junior secondary school (From Grade 7-8) From 1986-87 E.C.
High school: Dembecha senior secondary school (From Grade 9-12) From1988-92 E.C.
III. Qualification
B.Ed in Geography Minor Economics
IV. Experience
From 1998-2001 Teaching Geography in Amanuel senior secondary and higher education
Preparatory school
From 2002-2007 Teaching Civics in Deber markos technical and vocational institute
From 2008- till now land use expert in East Gojam Zone.
v. Language
40
English Excellent Excellent Excellent Excellent
VI. Skill
VI. Hobby
VII. Reference
41
Curriculum vitae (CV)
42
43
12. በዚህ ጥናት የተሳተፍ ባለሙያዎች የሙያ ፈቃድ
44
45
46
47